text stringlengths 4 267 |
|---|
የሚቃጠሉ መባዎችህን፣ ሥጋውንና ደሙን በአምላክህ በይሖዋ መሠዊያ ላይ ታቀርባለህ፤ የመሥዋዕቶችህም ደም በአምላክህ በይሖዋ መሠዊያ ላይ መፍሰስ ይኖርበታል፤ ሥጋውን ግን መብላት ትችላለህ። |
“እኔ የማዝህን እነዚህን ቃላት በሙሉ በጥንቃቄ ፈጽም፤ ምክንያቱም እንዲህ ስታደርግ በአምላክህ በይሖዋ ፊት መልካምና ትክክል የሆነውን ትፈጽማለህ፤ ይህን የምታደርገው ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ ምንጊዜም መልካም እንዲሆንላችሁ ነው። |
“ከምድራቸው የምታስለቅቃቸውን ብሔራት አምላክህ ይሖዋ ሲያጠፋቸውና በምድራቸው ላይ ስትኖር |
እነሱ ከጠፉ በኋላ በእነሱ እንዳትጠመድ ተጠንቀቅ። ‘እነዚህ ብሔራት አማልክታቸውን ያመልኩ የነበረው እንዴት ነው? ቆይ እኔም እንደ እነሱ አደርጋለሁ’ ብለህ ስለ አማልክታቸው አትጠይቅ። |
አንተ በአምላክህ በይሖዋ ላይ ይህን ማድረግ የለብህም፤ ምክንያቱም እነሱ ይሖዋ የሚጠላውን አስጸያፊ ነገር ሁሉ ለአማልክታቸው ያደርጋሉ፤ ሌላው ቀርቶ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአማልክታቸው በእሳት ያቃጥላሉ። |
እናንተ እኔ የማዛችሁን እያንዳንዱን ነገር በጥንቃቄ ፈጽሙ። በእሱ ላይ ምንም አትጨምሩ፤ ከእሱም ላይ ምንም አትቀንሱ። |
“ሌዋውያኑ ካህናት አልፎ ተርፎም መላው የሌዊ ነገድ ከእስራኤል ጋር ድርሻም ሆነ ውርሻ አይኖራቸውም። የእሱ ድርሻ የሆኑትን ለይሖዋ በእሳት የሚቀርቡትን መባዎች ይበላሉ። |
በመሆኑም በወንድሞቻቸው መካከል ውርሻ ሊኖራቸው አይገባም። አስቀድሞ በነገራቸው መሠረት ውርሻቸው ይሖዋ ነው። |
“ካህናት ከሕዝቡ ሊያገኙ የሚገባቸው ድርሻ የሚከተለው ይሆናል፦ በሬም ሆነ በግ መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው የእንስሳውን ወርች፣ መንገጭላውንና ሆድ ዕቃውን ለካህኑ ይስጥ። |
የእህልህን በኩር፣ አዲስ የወይን ጠጅህንና ዘይትህን እንዲሁም ከመንጋህ በመጀመሪያ የተሸለተውን ፀጉር ስጠው። |
አምላክህ ይሖዋ ከነገዶችህ ሁሉ መካከል በይሖዋ ስም ሁልጊዜ እንዲያገለግል የመረጠው እሱንና ወንዶች ልጆቹን ነው። |
“ሆኖም አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት በእስራኤል ከሚገኙ ከተሞችህ ከአንዱ ወጥቶ ይሖዋ ወደሚመርጠው ስፍራ መሄድ ቢፈልግ |
በይሖዋ ፊት ቆመው እንደሚያገለግሉት ሌዋውያን ወንድሞቹ ሁሉ እሱም በዚያ በአምላኩ በይሖዋ ስም ሊያገለግል ይችላል። |
የአባቶቹን ርስት በመሸጥ ከሚያገኘው ገንዘብ በተጨማሪ ከእነሱ እኩል ምግብ ይሰጠዋል። |
“አምላክህ ይሖዋ ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ በዚያ የሚገኙ ብሔራት የሚፈጽሟቸውን አስጸያፊ ነገሮች አታድርግ። |
ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፣ ሟርተኛ፣ አስማተኛ፣ ሞራ ገላጭ፣ ምትሃተኛ፣ |
ድግምተኛ፣ መናፍስት ጠሪ፣ ጠንቋይ ወይም ሙታን አነጋጋሪ በመካከልህ አይገኝ። |
ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ሁሉ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው፤ አምላክህ ይሖዋም እነሱን ከፊትህ የሚያባርራቸው በእነዚህ አስጸያፊ ነገሮች የተነሳ ነው። |
በአምላክህ በይሖዋ ፊት እንከን የለሽ ሆነህ መገኘት አለብህ። |
“አንተ ከምድራቸው የምታስለቅቃቸው እነዚህ ብሔራት አስማተኞችንና ሟርተኞችን ይሰማሉ፤ አንተ ግን እንዲህ እንድታደርግ አምላክህ ይሖዋ አልፈቀደልህም። |
አምላክህ ይሖዋ ከወንድሞችህ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳልሃል። እናንተም እሱን ማዳመጥ ይኖርባችኋል። |
ይህም የሚሆነው በኮሬብ ተሰብስባችሁ በነበረበት ዕለት ‘እንዳልሞት የአምላኬን የይሖዋን ድምፅ ከእንግዲህ አልስማ ወይም ይህን ታላቅ እሳት ከእንግዲህ አልይ’ በማለት አምላካችሁን ይሖዋን በጠየቃችሁት መሠረት ነው። |
ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘የተናገሩት ነገር መልካም ነው። |
ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሳላቸዋለሁ፤ ቃሌንም በአፉ ላይ አደርጋለሁ፤ እሱም እኔ የማዘውን ሁሉ ይነግራቸዋል። |
በእኔ ስም የሚናገረውን ቃሌን የማይሰማውን ሰው በእርግጥ ተጠያቂ አደርገዋለሁ። |
“‘እኔ እንዲናገር ያላዘዝኩትን ቃል በእብሪት ተነሳስቶ በስሜ የሚናገር ወይም በሌሎች አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ ካለ ያ ነቢይ ይገደል። |
ሆኖም አንተ በልብህ “ታዲያ ቃሉን ይሖዋ እንዳልተናገረው እንዴት እናውቃለን?” ብለህ ታስብ ይሆናል። |
ነቢዩ በይሖዋ ስም ቢናገርና የተናገረው ቃል ባይፈጸም ወይም እውነት ሆኖ ባይገኝ ይህን ቃል የተናገረው ይሖዋ አይደለም። ይህ ቃል ነቢዩ በእብሪት ተነሳስቶ የተናገረው ነው። እሱን ልትፈራው አይገባም።’ |
“የዘር ፍሬው ተቀጥቅጦ የተኮላሸ ወይም ብልቱ የተቆረጠ ማንኛውም ሰው ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግባ። |
“ዲቃላ ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግባ። ሌላው ቀርቶ እስከ አሥረኛ ትውልድ ድረስ ዘሮቹ ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግቡ። |
“አሞናውያንም ሆኑ ሞዓባውያን ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግቡ። ሌላው ቀርቶ እስከ አሥረኛ ትውልድ ድረስ ዘሮቻቸው ፈጽሞ ወደ ይሖዋ ጉባኤ አይግቡ፤ |
ምክንያቱም እነሱ ከግብፅ ወጥታችሁ እየተጓዛችሁ በነበረበት ጊዜ ምግብና ውኃ በመስጠት አልረዷችሁም፤ ደግሞም በሜሶጶጣሚያ በምትገኘው በጰቶር የሚኖረው የቢዖር ልጅ በለዓም አንተን እንዲረግም በገንዘብ ቀጥረውት ነበር። |
አምላክህ ይሖዋ ግን በለዓምን ለመስማት ፈቃደኛ አልሆነም። ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ ለአንተ ሲል እርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው፤ ይህን ያደረገው አምላክህ ይሖዋ ስለወደደህ ነው። |
በዘመንህ ሁሉ መቼም ቢሆን ለእነሱ ሰላምን ወይም ብልጽግናን አትመኝ። |
“ወንድምህ ስለሆነ ኤዶማዊውን አትጥላው። “የባዕድ አገር ሰው ሆነህ በአገሩ ትኖር ስለነበር ግብፃዊውን አትጥላው። |
ለእነሱ የሚወለዱላቸው የሦስተኛው ትውልድ ልጆች ወደ ይሖዋ ጉባኤ መግባት ይችላሉ። |
“ጠላትህን ለመውጋት ወጥተህ በምትሰፍርበት ጊዜ ከማንኛውም መጥፎ ነገር መራቅ ይኖርብሃል። |
አንድ ሰው ዘሩ በመፍሰሱ ምክንያት ቢረክስ ከሰፈሩ ውጭ ይውጣ፤ ወደ ሰፈሩም ተመልሶ አይግባ። |
አመሻሹ ላይ በውኃ ይታጠብ፤ ከዚያም ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ወደ ሰፈሩ ተመልሶ መግባት ይችላል። |
ለመጸዳጃ የሚሆን ቦታ ከሰፈሩ ውጭ አዘጋጅ፤ አንተም መሄድ ያለብህ ወደዚያ ነው። |
ከመሣሪያዎችህም ጋር መቆፈሪያ ያዝ። ውጭ በምትጸዳዳበትም ጊዜ በመቆፈሪያው ጉድጓድ ቆፍር፤ ከዚያም በዓይነ ምድርህ ላይ አፈሩን መልስበት። |
ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ ሊታደግህና ጠላቶችህን በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥህ በሰፈሩ ውስጥ ይዘዋወራል፤ በመሆኑም ነውር የሆነ ምንም ነገር እንዳያይብህና ከአንተ ጋር መሄዱን እንዳይተው ሰፈርህ ቅዱስ መሆን አለበት። |
“አንድ ባሪያ ከጌታው አምልጦ ወደ አንተ ቢመጣ መልሰህ ለጌታው አትስጠው። |
ከከተሞችህ መካከል በመረጠውና ደስ ባለው ቦታ አብሮህ ሊኖር ይችላል። በደል አትፈጽምበት። |
“ከእስራኤል ሴቶች ልጆች መካከል የትኛዋም የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ አትሁን፤ ከእስራኤል ወንዶች ልጆችም መካከል የትኛውም የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ አይሁን። |
ለሴት ዝሙት አዳሪ የተከፈለን ዋጋም ሆነ ለወንድ ዝሙት አዳሪ የተከፈለን ዋጋ አንድን ስእለት ለመፈጸም ስትል ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ቤት አታምጣ፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ ሁለቱንም ይጸየፋቸዋል። |
“ወንድምህን ወለድ አታስከፍለው፤ ከገንዘብም ሆነ ከእህል ወይም ወለድ ሊያስከፍል ከሚችል ከማንኛውም ነገር ወለድ አታስከፍለው። |
ከባዕድ አገር ሰው ወለድ መጠየቅ ትችላለህ፤ ሆኖም አምላክህ ይሖዋ ገብተህ በምትወርሳት ምድር በሥራህ ሁሉ እንዲባርክህ ወንድምህን ወለድ አታስከፍለው። |
“ለአምላክህ ለይሖዋ ስእለት ከተሳልክ ለመፈጸም አትዘግይ። ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ በእርግጥ ከአንተ ይፈልገዋል፤ አለዚያ ኃጢአት ይሆንብሃል። |
ሳትሳል ከቀረህ ግን ኃጢአት አይሆንብህም። |
ከአፍህ የወጣውን ቃል ጠብቅ፤ ለአምላክህ ለይሖዋ የፈቃደኝነት መባ አድርገህ ለማቅረብ በገዛ አንደበትህ የተሳልከውን ፈጽም። |
“ወደ ባልንጀራህ የወይን እርሻ ከገባህ እስክትጠግብ ድረስ ወይን መብላት ትችላለህ፤ በዕቃህ ግን ምንም ይዘህ አትሂድ። |
“ወደ ባልንጀራህ የእህል ማሳ ከገባህ እሸት ቀጥፈህ መብላት ትችላለህ፤ ሆኖም የባልንጀራህን እህል በማጭድ ማጨድ የለብህም። |
ከዚያም ሙሴ ከሞዓብ በረሃማ ሜዳ ተነስቶ ወደ ነቦ ተራራ ይኸውም በኢያሪኮ ትይዩ ወደሚገኘው ወደ ጲስጋ አናት ወጣ። ይሖዋም ምድሪቱን በሙሉ አሳየው፤ ይኸውም ከጊልያድ እስከ ዳን፣ |
ንፍታሌምን በሙሉ፣ የኤፍሬምንና የምናሴን ምድር፣ በስተ ምዕራብ በኩል እስካለው ባሕር ድረስ ያለውን የይሁዳን ምድር በሙሉ፣ |
ኔጌብን፣ የዮርዳኖስን አውራጃ እንዲሁም የዘንባባ ዛፍ ከተማ በሆነችው በኢያሪኮ ካለው ሸለቋማ ሜዳ አንስቶ እስከ ዞአር ድረስ አሳየው። |
ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ‘ለዘርህ እሰጣታለሁ’ በማለት የማልኩላቸው ምድር ይህች ናት። በዓይንህ እንድታያት አድርጌሃለሁ፤ ነገር ግን ወደዚያ አትሻገርም።” |
የይሖዋ አገልጋይ ሙሴም ልክ ይሖዋ እንደተናገረው በዚያው በሞዓብ ምድር ሞተ። |
እሱም ከቤትጰኦር ትይዩ በሞዓብ ምድር በሚገኘው ሸለቆ ቀበረው፤ እስከ ዛሬም ድረስ መቃብሩ የት እንደሚገኝ የሚያውቅ የለም። |
ሙሴ በሞተ ጊዜ ዕድሜው 120 ዓመት ነበር። ዓይኖቹ አልፈዘዙም፤ ጉልበቱም አልደከመም ነበር። |
እስራኤላውያንም በሞዓብ በረሃማ ሜዳ ለሙሴ 30 ቀን አለቀሱለት። በመጨረሻም ለሙሴ የሚለቀስበትና የሚታዘንበት ጊዜ አበቃ። |
የነዌ ልጅ ኢያሱ ሙሴ እጁን ስለጫነበት የጥበብ መንፈስ ተሞልቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም እሱን ይሰሙት ጀመር፤ እንዲሁም ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። |
ሆኖም ይሖዋ ፊት ለፊት እንዳወቀው እንደ ሙሴ ያለ ሌላ ነቢይ እስካሁን በእስራኤል ተነስቶ አያውቅም። |
ይሖዋ በግብፅ ምድር በፈርዖን፣ በአገልጋዮቹ ሁሉና በምድሩ ሁሉ ፊት እንዲፈጽም የላከውን ምልክቶችና ተአምራት በሙሉ ፈጸመ፤ |
ከዚህም በተጨማሪ ሙሴ በእስራኤላውያን ሁሉ ፊት በኃያል ክንድ ታላቅና አስፈሪ ድርጊት ፈጸመ። |
“አምላካችሁ ይሖዋ ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ውስጥ ትጠብቋቸው ዘንድ እንዳስተምራችሁ የሰጠኝ ትእዛዛት፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፤ |
ይህም አንተ፣ ልጅህና የልጅ ልጅህ ዕድሜያችሁ ይረዝም ዘንድ በሕይወታችሁ ዘመን ሁሉ አምላካችሁን ይሖዋን እንድትፈሩ እንዲሁም እኔ የማዛችሁን የእሱን ደንቦችና ትእዛዛት ሁሉ እንድትጠብቁ ነው። |
እስራኤል ሆይ፣ ስማ፤ የአባቶችህ አምላክ ይሖዋ በገባልህ ቃል መሠረት ወተትና ማር በምታፈሰው ምድር እንድትበለጽግና እጅግ እንድትበዛ እነዚህን በጥንቃቄ ጠብቅ። |
“እስራኤል ሆይ ስማ፣ አምላካችን ይሖዋ አንድ ይሖዋ ነው። |
አንተም አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና በሙሉ ኃይልህ ውደድ። |
እኔ ዛሬ የማዝህን እነዚህን ትእዛዛት በልብህ ያዝ፤ |
በልጆችህም ውስጥ ቅረጻቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድ ላይ ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሳ ስለ እነሱ ተናገር። |
በእጅህም ላይ እንደ ማስታወሻ እሰራቸው፤ በግንባርህም ላይ እንደታሰረ ነገር ይሁኑ። |
በቤትህ መቃኖችና በግቢህ በሮች ላይ ጻፋቸው። |
“አምላክህ ይሖዋ ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማለላቸው ምድር ሲያስገባህና በዚያም አንተ ያልገነባሃቸውን ታላላቅና ያማሩ ከተሞች፣ |
አንተ ባልደከምክባቸው የተለያዩ መልካም ነገሮች የተሞሉ ቤቶችን፣ አንተ ያልቦረቦርካቸውን የውኃ ማጠራቀሚያዎች እንዲሁም አንተ ያልተከልካቸውን የወይን ተክሎችና የወይራ ዛፎች ስታገኝ፣ በልተህም ስትጠግብ |
ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን ይሖዋን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ። |
ይሖዋ አምላክህን ፍራ፤ እሱን አገልግል፤ በስሙም ማል። |
ሌሎች አማልክትን ይኸውም በዙሪያችሁ ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኳቸውን የትኞቹንም አማልክት አትከተሉ፤ |
ምክንያቱም በመካከልህ ያለው አምላክህ ይሖዋ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ አምላክ ነው። አለዚያ የአምላክህ የይሖዋ ቁጣ በላይህ ይነድዳል፤ ከምድርም ገጽ ጠራርጎ ያጠፋሃል። |
“በማሳህ እንደተፈታተናችሁት አምላካችሁን ይሖዋን አትፈታተኑት። |
አምላካችሁ ይሖዋ እንድትጠብቋቸው ያዘዛችሁን ትእዛዛት እንዲሁም ማሳሰቢያዎቹንና ሥርዓቶቹን በጥንቃቄ ጠብቁ። |
እንድትበለጽግና ይሖዋ ለአባቶችህ የማለላቸውን መልካሚቱን ምድር ገብተህ እንድትወርስ በይሖዋ ፊት ትክክልና መልካም የሆነውን አድርግ፤ |
ይሖዋ በገባው ቃል መሠረት ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ አባረህ አስወጣ። |
“ወደፊት ልጅህ ‘አምላካችን ይሖዋ የሰጣችሁ ማሳሰቢያዎች፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ትርጉም ምንድን ነው?’ ብሎ ሲጠይቅህ |
እንዲህ ትለዋለህ፦ ‘እኛ በግብፅ የፈርዖን ባሪያዎች ሆነን ነበር፤ ይሖዋ ግን በብርቱ ክንድ ከግብፅ አወጣን። |
ይሖዋም በግብፅ፣ በፈርዖንና በቤተሰቡ ሁሉ ላይ ታላላቅና አጥፊ የሆኑ ድንቅ ምልክቶችንና ተአምራትን ዓይናችን እያየ ፈጸመ። |
እኛንም ለአባቶቻችን የማለላቸውን ምድር ሊሰጠን ከዚያ አውጥቶ ወደዚህ አመጣን። |
ከዚያም ይሖዋ ምንጊዜም መልካም ይሆንልን ዘንድ እነዚህን ሥርዓቶች ሁሉ እንድንፈጽምና አምላካችንን ይሖዋን እንድንፈራ አዘዘን፤ ይህም ዛሬ እንደሆነው ሁሉ በሕይወት እንድንኖር ነው። |
አምላካችንን ይሖዋን በመታዘዝ ልክ እሱ በሰጠን መመሪያ መሠረት እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ በጥንቃቄ ብንፈጽም ለእኛ ጽድቅ ይሆንልናል።’ |
ይሖዋ በኮሬብ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ከገባው ቃል ኪዳን በተጨማሪ ሙሴ በሞዓብ ምድር ከእነሱ ጋር እንዲገባ ያዘዘው ቃል ኪዳን ቃላት እነዚህ ናቸው። |
ከዚያም ሙሴ እስራኤላውያንን በሙሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ በግብፅ ምድር በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ እንዲሁም በመላ ምድሩ ላይ ያደረገውን ነገር ሁሉ በገዛ ዓይናችሁ ተመልክታችኋል፤ |
ደግሞም እነዚያን ታላላቅ የፍርድ እርምጃዎች፣ ድንቅ ምልክቶችና ተአምራት በዓይናችሁ አይታችኋል። |
ሆኖም ይሖዋ እስከ ዛሬ ድረስ የሚያስተውል ልብ፣ የሚያይ ዓይንና የሚሰማ ጆሮ አልሰጣችሁም። |
‘በምድረ በዳ ለ40 ዓመታት በመራኋችሁ ጊዜ ልብሳችሁ ላያችሁ ላይ አላለቀም፤ ጫማችሁም እግራችሁ ላይ አላለቀም። |
እኔ አምላካችሁ ይሖዋ መሆኔን ታውቁ ዘንድ ዳቦ አልበላችሁም፤ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣችሁም።’ |
በኋላም ወደዚህ ስፍራ መጣችሁ፤ የሃሽቦን ንጉሥ ሲሖን እና የባሳን ንጉሥ ኦግ ሊወጉን ወጡ፤ ሆኖም ድል አደረግናቸው። |
ከዚያም ምድራቸውን ወስደን ለሮቤላውያን፣ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠናቸው። |
በመሆኑም የምታደርጉት ነገር ሁሉ መልካም እንዲሆንላችሁ የዚህን ቃል ኪዳን ቃላት ጠብቁ፤ ደግሞም ታዘዙ። |
“እናንተ ሁላችሁ ይኸውም የየነገዶቻችሁ መሪዎች፣ ሽማግሌዎቻችሁ፣ አለቆቻችሁና በእስራኤል ያለ ወንድ ሁሉ በዛሬው ዕለት በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ቆማችኋል፤ |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.