text
stringlengths
707
989
### Text: 1 2019 31 2019 ነገር ሲደጋገም ይሰለቻል ግን እውነታው ይሄ ነው በተመላላሽ ህክምና ክፍል የጡት ካንሰር እንዳለባቸው የሚነገራቸው ሴቶች ቁጥር ቀላል አይደለምአይነተኛ የጡት ካንሰር ምልክቶችን የማያውቁ ነገሩ ከረፈደ በኋላ ወደጤና ተቋማት የሚመጡ ሴቶች ቁጥር ቀላል አይደለምየጡት ካንሰር0የሞት ፍርድ እንደሆነ የሚያስቡ ሴቶች ቁጥር ቀላል አይደለምነገር ሲደጋገም ይሰለቻልግን ማህበራዊ ገጾችን ትምህርት ልንሰጣጥባቸው እንችላለንነገር ሲደጋገም ይሰለቻልግን ...
### Text: አጫጭር መረጃዎች ቻይና ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 22 አዲስ ኬዞችን ሪፖርት አድርጋለች። ሀያ አንዱ 21 ከውጭ የገቡ ናቸው። በኳታር ተጨማሪ 643 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 12564 ደርሷል። በኢራን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 93657 ደርሷል ባለፉት 24 ሰዓት 1073 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል በተጨማሪ 80 ሰዎች ሞተዋል። በስፔን የሟቾች ቁጥር ከትላንት ጨምሯል ባለፉት 24 ሰዓት 325 ሰዎች መሞታቸው ሪ...
### Text: በትላንትናው ዕለት ከጋምቤላ ከተማ 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከቀኑ 11 ሰዓት ከ30 አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቁ 5 ግለሰቦች በከፈቱት ተኩስ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰው ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የጋምቤላ ክልል የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶማስ ቱት አስታወቁ።ጉዳቱን ተከትሎ በከተማው በተከሰተው ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉንና ሶስት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።በግጭቱ ባጠቃላይ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አምስት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ...
### Text: የተሰረዘው የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ነገ ይወጣል።በቅርቡ በተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ምክንያት ተሰርዞ የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ በነገው ዕለት እንደሚወጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።በጉዳዩ ላይ በምከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ ያስሚን ወሀቢረቢ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሽመልስ ታምራት ዛሬ በሰጡት መግለጫ የተናገሩት ነገ 25 ሺህ 791 የ4060 እና 2080 ቤቶች ዕጣ ይወጣባ...
### Text: አይካ አዲስ ስራ አቆመ️በቱርካውያን ባለሃብቶች በሠበታ ከተማ የተቋቋመው አይካ አዲስ የጨርታ ጨርቅ ፋብሪካ ከትናንት ጀምሮ ሥራ ማቆሙን ለሠራተኞቹ አስታወቀ፡፡4000 አራት ሺ የሚሆኑ የፋብሪካው ሠራተኞች ከረብዕ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ ላይ የሠነበቱ ሲሆን አርብ ጠዋት ወደ ፋብሪካው ሲመለሱ በማስታወቂያ ቦርድ ላይ ሳይሰራ የሚከፈል ደሞዝ ስለሌለ፣ ፋብሪካው ለጊዜው ስራ አቁሟል የሚል ማስታወቂያ ተለጥፎ፣ ሠራተኛው እንዲመለስ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡የፋብሪካው ባለቤት ቱሪካዊው ...
### Text: የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የምትገነባው ሙሌት አካሂዳ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ነው ፕር ያዕቆብ አርሳኖበአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር እና የዓባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ኢትዮጵያ ታላቁን የህዳሴ ግድብ የምትገነባው ሙሌት አካሂዳ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት በመሆኑ የሙሌት ጉዳይ ብዙ የሚያነጋግር እንዳልሆነ ገለፁ።ፕሮፌሰር ያዕቆብ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት ቃል ሁለተኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ...
### Text: ፑራቶስ የኢትዮጵያን ገበያ ተቀላቀለ።ፑራቶስ ኢትዮጵያ ዛሬ በአዲስ አበባ የገነባውን ልዩ የፈጠራ ማዕክል ማስመሩቁን ለቲክቫህ በላከው መልዕክት አሳውቋል።ፑራቶስ ኢትዮጵያ ዛሬ ያስመረቀው ወሎ ሰፈር አካባቢ ያስገነባውን የዳቦ፣ ኬክና ሸኮሌት ግብዓት ማምረቻ ፋብሪካ እና ልዩ የምግብ ፈጠራ ማዕከል ነው።የኩባንያው ዋና ስራ አፈፃሚ ዶሚኒክ ኤድዋርዶ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ባሰሙት ንግግር በዓለም ላይ የታወቀው ፑራቶስ የንግድ ስያሜ የኢትዮጵያን ገበያ በመቀላቀሉ ደስታ እና ኩራት እን...
### Text: ብሄራዊ ቤተ መንግስት️የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመና የቀድሞው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዳኜ መላኩ አሸኛኘት ተደረገላቸው፡፡በዝግጅቱ ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበው፣ እርሳቸውም የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድም ዶክተር ሙላቱ ላበረከቱት ያልተቆጠበ የዲፕሎማሲና የመሪነት ሚ...
### Text: በአንደኛው ሟች ኪስ ውስጥ ተጨማሪ ያልፈነዳ ቦንብ ተገኝቷል ፖሊስአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንበልደታ ክከተማ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ የቦንብ ፍንዳታ የሁለት ግለሰቦች ህይወት ማለፉን የአዲስ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ ነው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ከሚትሮሎጂ ፊት ለፊትለልማት በተዘጋጀ ቦታ ላይ በተከሰተ የቦንብ ፍንዳታ የሁለት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ያለፈው።በፍንዳታው አንድ ግለሰብ በፅኑ ተጎድቶ ወደ ሆስፒታል መሄዱን ፖሊስ አሳውቋል።በልደታ ክ...
### Text: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም እና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የበላይ ጠባቂ ሊቀጳጳስ ዕረፍትን በማስመልከት አባታዊ የሐዘን መልዕክት አስተላለፉ።ቅዱስነታቸው የትህትና፣ የጸሎት ሕይወት እና የመልካምነት ምሳሌ የነበሩት ብፁዕ አባ ሰላማ ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የሰማነው በታላቅ ሐዘን ነው። ብለዋል...
### Text: የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል️በአርባምንጭ ከተማ ዛሬ ጠዋት ላይ በደረሰ የመኪናአደጋ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ምኢንስፔክተር አባሃጅጉጆ እንደገለጹት የካቲት 192011 ዓም ጠዋት 2 ሰዓት ላይ በአርባምንጭ ከተማ ወዜ ቀበሌ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3 53362 ኢት የሆነ ሲኖ ትራክ መኪና እና ኮድ 415376 ኢት የሆነ ፒካፕ መኪና ከፍጥነት ወሰን በላይ ሲያሽከረክሩ በተፈጠረ አደጋ እስከ አሁን የ5 ሠዎች ሕይወት አልፏል፡፡በቦታው ከነበሩ አይን እ...
### Text: በሕገ ወጥ መንገድ በቡድን ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኮሚሽኑ ገለፀ፡፡ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን በቡድን በሕገ ወጥ መንገድ የነበሩ ተጠርጣሪዎች፣ መሳሪያና ገንዘብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።በዞኑ ጎዛምን ወረዳ ጭምት በተባለ ቀበሌ ሐምሌ 262011ዓም ነው በሕገ ወጥ መንገድ በቡድን መሳሪያ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 14 ሰዎችን እና ለጊዜው መጠኑ በግልፅ ያልታወቀ ከፍተኛ ገንዘብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን በአ...
### Text: የቴፒ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ዓመታት በፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ሀዘኑን ገልፆ ለደረሰው ጉዳትና እና ህዝብ ላይ ለደረሰው በደል ይቅርታ ጠይቋል።የቴፒ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ገላቲያስ ሻሜ ዛሬ በከተማው በነበረ የሰላም ኮንፈረንስ መድረክ ላይ ንግግር አድርገዋል።ከንቲባ አቶ ገላቲያስ ሻሜ ባሰሙት ንግግር ባለፉት ዓመታት በተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸው ለደረሰው ጉዳናት፣ የህዝብ በደል ይቅ...
### Text: የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ፣ ከየካቲት 4 ቀን 2015 ዓም ምሽት ጀምሮ በተለያዩ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የተፈጸሙ እስሮችን በተመለከተ የአዲስ አበባን፣ የፌዴራል እና የኦሮሚያ ክልል ፖሊስና የጸጥታ አካላት፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤትን፣ ምስክሮችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በማነጋገር እንዲሁም በአዲስ አበባ የተለያዩ ማቆያ ቦታዎችን በመጎብኘት ክትትል በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።የተወሰኑ በቁጥጥር ስር የዋሉ...
### Text: በትግራይ ሰሜን ምእራብ ዞን ታሕታይ ቆራሮና ዛና ወረዳዎች ከባድ ነጎድጓድና ዝናብ ተከትሎ የወደቀ መብረቅ አራት ሰዎችና ሰባት የቤት እንስሳት መግደሉ ተገልፀ። አደጋው የደረሰው በታሕታይ ቆራሮ ወረዳ ቀላቕልና በዛና ወረዳ ዋልካ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው። በወረዳው ቀላቕል በተባለ ቀበሌ ገበሬ ማህበር የወደቀው መብረቅ የ18 የ23 የ47 እድሜ ያላቸው ሶስት ሰዎችና ሰባት የቤት እንስሳት ፣ በዛና ወረዳ ዛና ዋልካ ቀበሌ የ15 ዕድሜ እንስት መግደሉ የቀበሌው አስተዳዳሪ አቶ ብርሃነ ገመድህን...
### Text: ጄፍሪ ፌልትማን ኢትዮጵያ ይገኛሉ።የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ዳግም ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ከዚህ ቀደም ተገልጾ ነበር።ፌልትማን በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ የሚገኙ ሢሆን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ውይይት አድርገዋል።አቶ ደመቀ መኮንን ህወሃት በሰሜን ዕዝ ላይ ስላደረሰው ጥቃት እንዲሁም ቡድኑ እየፈጸማቸው ያለው አስከፊ ድርጊቶች አሁን ለተፈጠረው ችግር መዳረጉን ገልጸዋል።ህወሓት በአሁኑ ወቅት በአፋርና በአማራ ክልሎች ግ...
### Text: ከአርባ ምንጭ️ጤና ይስጥልኝ ፀግሽ ነኝ ከአርባ ምንጭ አስካሁን የክረምት በጎ ፍቃድ አልጀመርንም ለምን እንዳልተጀመረ ለመጠየቅ ከተማ አስተዳደር ብንሄድም ከከተማዋ ከንቲባ በተላለፈ ትዛዝ የቁም ከመባሉ በስተቀር ምናቀው ምንም ነገር የለም ነው ሚሉን የከተማውን ከንቲባን ለማናገር በተደጋጋሚ ወደ ከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ብንሄድም በስብሰባ ላይ ናቸዉ እያሉ ለሁለት ሳምንት ከማመላለስ በስተቀር ትክክለኛ ምላሽ ሚሰጠን አካል አላገኘንም ከተማዋ በምትገኝበት ጋሞ ጎፋ ዛን የሚገኙ ወረዳዎች ስ...
### Text: አብንየአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን በቅርቡ በሚካሄደው የህዝብና የቤት ቆጠራ ላይ ስጋት እንዳለው ገለጸ። የፊታችን መጋቢት በሚካሄደው አገር አቀፍ የህዝብና ቤት ቆጠራ ላይ ከፖለቲካዊ ተጽዕኖ ነጻ መሆን መቻል አለበት ሲል አብን የገለጸው መጪውን የህዝብና ቤት ቆጠራ አስመልክቶ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ነው።የፓርቲው ሊቀመንበር ዶር ደሳለኝ እንዳሉት በመጪው መጋቢት 292011 የሚካሄደው 4ኛው ዙር አገር አቀፍ የህዝብና የቤት ቆጠራ በትክክል እንዲካሄድ...
### Text: በራይድ እና ዛይ ራይድ መካከል ውዝግብ ተነስቷል በራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት እና ዛይ ራይድ ሜትር ታክሲ መካከል ከንግድ ስም ባለቤትነት እና ከፈጠራ ባለቤትነት መብቶች ጋር በተያያዘ በተነሳው ውዝግብ ራይድ ባቀረበው አቤቱታ መሰረት በንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ምርመራ ተጀመረ።ከአራት ወራት በፊት ራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት የስያሜው የባለቤትነት መብት ይገባኛል በሚል ለኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት እና ለንግድ ውድድር እና ሸማቾች መብት ጥበቃ ባለሥል...
### Text: በኢትዮጵያ ተጨማሪ 129 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧልባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5274 የላብራቶሪ ምርመራ 129 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3759 ደርሷል።ቫይረሱ የተገኘባቸው 79 ወንድ እና 50 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 70 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።ቫይረሱ የተገኘባቸው 85 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 11 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 10 ሰዎች ...
### Text: አጫጭር መረጃዎች በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 75 ሰዎች በኮቪድ19 ተይዘዋል ከነዚህ ውስጥ 16 ከለገጣፎ፣ 15 ከቢሾፍቱ፣ 11 ከአዳማና 11 ከምስራቅ ሸዋ ይገኙበታል። በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 19 ሰዎች በኮቪድ19 ተይዘዋል13 ሰዎች ንክኪ ያላቸው፣6 ሰዎች የጉዞ ታሪክ ያላቸውና 3 ሰዎች የጉዞ ታሪክና ንክኪ የሌላቸው ናቸው። በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 19 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 181 ደርሰዋል። በቤኒሻንጉል ጉ...
### Text: የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በጀት️የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2011 በጀት ዓመት ከፌደራል መንግስት የተመደበ በጀት1 መደበኛ በጀትተቁ የበጀት ኮድ የተመደበለት የሥራ ክፍል የተመደበ በጀት መጠን ምርመራ1 3820101 የበላይ አመራር1074953002 3820201 ለመማር ማስተማር2229163003 3820202 ለተማሪ አገልግሎት798598004 3820302 ለምርምር ህትመት126644005 3820301 ለጥናትና ምርምር 15195006 3820401 ለማህበረሰብ አገለግሎት 988679007 3820402...
### Text: 4 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመገንባት የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ ነው አራት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመገንባት የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ገለጸ። ኮርፖሬሽኑ በፓርኮች ግንባታና ምርት ዙሪያ ከምሁራን፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የሙያ ማህበራት ጋር ተወያይቷል። ውይይቱ በኢትዮጵያ በመስኩ እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ፣ እየተገኙ ያሉ ውጤቶችና ችግሮች ላይ ያተኮረ ነው።የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ሺፈራው ሰለሞን እንደተናገሩት ...
### Text: ነሃሴ 92012 ዓምየኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች 1 በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 3448 የላብራቶሪ ምርምራ ተደርጎ 202 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 32 አአ ከተደረገ ምርመራ 22 ቡራዩ 18 ጉጂ ዞን 18 ገላን 17 ምዕራብ ሸዋ 14 ሞጆ 14 ቢሾፍቱ 12 ሰበታ ይገኙበታል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 645 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። 1 ከአሶሳ ዞ...
### Text: ለጅቡቲ ጉምሩክ ደብዳቤ ፅፈናል የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽንበጅቡቲ ጉምሩክ የወደብ ጭነት መዘግየት ችግር የተፈጠረ ሲሆን ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አሳውቋል።የጂቡቲ ጉምሩክ ከ20 ሺህ ዶላር በታች የክፍያ ደረሰኝ የያዙ ጭነቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዳያልፉ በሚል መመሪያ እቃዎች እንዳይንቀሳቀሱ እንዳገደ ተነግሯል።የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ዘርይሁን አሰፋ በሰጡት ቃል በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረ...
### Text: ጠቅላይ ሚንስትሩ ትላንት በፓርቲዎች ቃልኪዳን ሰነድ ፊርማ ስነስርዓት ላይ ካስተላለፉት መልዕክት1 ህገ መንግስት የሚሻሻለው በስምምነት ብቻ እንደሆነ ያ ካልተቻለ እያንዳንዱ ዜጋ ድምፅ ሰጠተውበት አብላጭ ድምፅ ያገኘው ሃሳብ ገዥ እንደሚሆን አስምረው ተናግረዋል።የአንድ ሀገር ህገ መንግስት የመላው ሀገሪቷ እንጂ የአንድ አከባቢ ፍላጎት ብቻ እንደማይሆን እና የትም ሀገር ሁሉም ዜጋ በሁሉም ነገር ላይ ተመሳሳይ አቋም ሊኖረው እንደማይችል አከለው ገልፀዋል።2 አብዛኛዎቹ ዋናዋና ፓርቲዎች በቀጥታ...
### Text: ከዚህ በኃላ ውሳኔ፣ ማዕቀብ፣ ተፅእኖ የሚባለው ባዶ መዝሙር ነው አምባሳደር ዲና ሙፍቲበአውሮፓ ህብረት እንዲሁም በአሜሪካ ይቀርቡ የነበሩት ቅሬታዎች መፍታት እንደተቻለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባዳደር ዲና ሙፍቲ በትላንት መግለጫቸው ተናግረዋል።እንደ አምባሳደር ዲና ገለፃ ይቀርቡ ከነበሩ ቅሬታዎች መካከል የመጀመሪያው ወደትግራይ እንዳንገባ በሩን ዘግታችሁብናልአልተፈቀደልንም፣ ህዝቡ ተቸግሯል ፣ ተፈናቅሏል ፣ ተርቧል ፣ ሱዳን የገባ አለ ገብተን እንዳንረዳ ተደርገናል ሲሉ ነ...
### Text: በትግራይ ክልል ጦርነት ሲቀሰቀስ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ሱዳን መግባታቸው ይታወሳል።እነዚህ ኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች በነበሩባቸው የሱዳን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የግዳጅ የውትድርና ምልመላ ይካሄድ እንደነበረ መረጃ እንዳለው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ለቢቢሲ በሰጠው ቃል አሳውቋል።ተቋሙ ከወራት በፊት ከስደተኞቹ መካከል አንዳንድ ጊዜ በኃይል ጭምር ተዋጊዎችን ለመመልመል የሚደረጉ ጥረቶች እንደነበሩ ተአማኒ ሪፖርቶች 0 ደርሶኛል ብሏል ...
### Text: የሰኔ 16ቱ ጥቃት️የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንደኛ የወንጀል ችሎት የሰኔ 16ቱን የቦምብ ጥቃት አስተባብረዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩት የብሄራዊ የመረጃና ደህንነት ባልደረባ የነበሩት አቶ ተስፋዬኡርጌ ላይ ፖሊስ የሚያደርገውን ምርመራ እንዲያጠናቅቅ የመጨረሻ ቀጠሮ ሰጠ፡፡ፖሊስ ችሎቱ በፈቀደለት 10 ቀናት የሰው ምስክር መቀበሉን ብሎም ከመስሪያ ቤታቸው የተገኘው ቦምብ ለምርመራ መወሰዱንና ሌሎች ተግባራትን ማከናወኑን ጠቅሷል፡፡ ለተጨማሪ የምርመራ ስራ 10 ቀና...
### Text: የውድድር ማስታወቂያ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአይቢኤ ኢትዮጲያና ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ አህጉራዊ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ንቅናቄ አፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት በሚል ርዕስ ከጥቅምት 17 እስከ ጥቅምት 222012 ድረስ በአዲስ አበባ ያካሂዳል፡፡ስለሆነም ችግር ፈቺ ሀብት ፈጣሪና ወደ ምርትና አገልግሎት ሊቀየር የሚችል የፈጠራ ስራ ያላችሁ በዚህ አህጉራዊ መድረክ ላይ ሀገራችሁን ወክላችሁ እንድትወዳደሩና የፈጠራ ውጤቶቻችሁን ለውጭና ለሀገር ውስጥ ...
### Text: በሀገር አቀፍ ደረጃ ላለፉት አራት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ተጠናቋል፡፡ የፈተናው መጠናቀቅን ተከትሎ ተፈታኝ ተማሪዎች ወደየመጡበት መመለስ ጀምረዋል። በሌላ በኩል ትላንት ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ቀኑን ሙሉ በከባድ ተኩስ ስትናጥ እንደዋለች አንድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህር ገልፀውልናል።ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ የነበረው በከተማ አቅራቢያ ላይ እንደነበር ጠቁመዋል።እሳቸው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሚገኝ የመምህራን መኖርያ ወ...
### Text: ጉባኤው ተጠናቋል 8ኛው የኦህዴድ መደበኛ ጉባኤ ባለ11 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ።ጉባኤው በኦሮሚያ ክልል በሰላም በልማት እና በማህበራዊ ዘርፎች ያለውን ለውጥ የበለጠ በማጠናከር በቁርጠኝነት መስራትበሚቻልበት መንገድ ተወያይቷል።ጉባኤው መጠናቀቁን ተከትሎ ጋዜጣው መግለጫ የሰጡት የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሜቴ ጽቤት ኃላፊ ወይዘሮ አዳነች ሃቤቤ የኦሮሞ ህዝብ ሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ መሰረት ነው ብለዋል።የጽቤት ሃላፊዋ አያይዘውም ክልሉ ያለውን ራዕይ ሃገራዊ በማድረግ በአንድ መ...
### Text: አዲስ አበባ ዛሬ️1ዛሬም በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ስንደቅአላማ በመስቀልና የከተማዋን ጎዳናዎች በማቅለም ዙሪያ አለመግባባቶች ታይተዋል። አዲሱገበያ አካባቢ የኦነግን አርማ ይሰቀልይቀባ በሚሉና ቀድሞ የተሰቀለው አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ስንደቅ አናስነካም ባሉ ወጣቶች መካከል ግብ ግብ ተነስቶ ፖሊስ ጣልቃ ገብቷል። በአስለቃሽ ጭስ ወጣቶቹን መበተን ያቃተው ፖሊስ ጥይት ወደ ስማይ ተኩሷል ። ኋላም በዶፍ ዝናብ ምክንያት ወጣቶቹ ተበትነዋል ።2የ...
### Text: ኒፕሲ ሐስል ተገደለ️ትውልደ ኤርትራዊው የሎስ አንጀለሱ ታዋቂ ራፐር፣ ኤርምያስአስገዶም ኒፕሲ ሐስል በተከፈተበት ተኩስ ሎስ አንደለስ ውስጥ መገደሉን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።የ33 ዓመቱ ራፐር በርካታ ቦታዎች ላይ በጥይት መመታቱን እና ሆስፒታል እንደደረሰ ሕይወቱ ማለፉን ሎስ አንጀለስ ታይምስ ዘግቧል። ሌሎች ሁለት ሰዎችም በተተኮሰባቸው ጥይት ቆስለዋል ።ከኤርትራዊ አባት እና ጥቁር አሜሪካዊ እናት የተወለደው ኤርሚያስ አስገዶም በዚህ ዓመት ለሽያጭ ያበቃው አልበሙ ...
### Text: መስጂድ አሰሪው አባ እና የክርስቲያኖች ተንከባካቢው ሼህ ወዳጅነት በጋዜጠኛ ወንድሙ ሃይሉ ሸገር ኤፍ ኤምአባ ቅዱስ ቁርዓንን ጠንቅቀው ያውቃሉ፣ ሼሁም መፅሐፍ ቅዱስን ያነባሉ አሉ፡፡ አባ አክሊለ ማርያም በአዲስ አበባ መስጂዶች እየተዘዋወሩ ለምስራቅ ሐረርጌው የላንጌ ቢላል መስጂድ መስሪያ 300 000 ብር አሰባስበዋል፡፡ ወዳጃቸው ሼህ አህመድ ነጃሺ ኡስማንም እንደ መስጂዱ ሁሉ የቤተ ክርስቲያን እና የክርስቲያኖች ነገር አይሆንላቸውም፣ ለክርስቲያኖች አባታዊ ምክር የሚለግሱ ናቸው።መልዐ...
### Text: ኤጀንሲው የሰነድ ማረጋገጫ ማህተም አሰራርን ቀየረ።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ እየተበራከተ የመጣውን ሰነድ አስመስሎ የመስራት ወንጀል ለመቀነስ ኤጀንሲው በሚሰጣቸው የልደት፣ የጋብቻ ፣ የፍቺ ፣ የያላገባ እንዲሁም ሌሎች ማስረጃዎች አገልግሎት ሲሰጥበት የነበረውን የማረጋገጫ አሰራር በዘመናዊ አሰራር በመተካት ፎርጀሪ እያደረሰ ያለውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳት ለመቀነስ የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቋል።ተቋሙ በዋና መስሪያ ቤት ...
### Text: በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሊቀመንበር ሮበርት ሜንዴዝ የቀረበው 3199 ረቂቅ ህግ ዛሬ ማለፉ ተሰምቷል።ኮሚቴው በኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲ ለማበረታታ በሚል ርዕስ የቀረበው 3199 ላይ ተወያይቶ ማማሻያ ካደረገ በኃላ ነው ማሳለፉ የታወቀው።የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ኮሚቴ ተመልክቶ ያሳለፈው 3199 ረቂቅ ህግ በጠቅላላ የምክር ቤቱ አባላት እንዲፀድቅ የሚመራ ሲሆን ህግ ሆኖ ለመውጣት የህግ አውጪው ምክር ቤት ድምፅ እና ...
### Text: ከአርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ ባባ ስርዓተ ቀብር ጋር በተያያዘ ካሜራ ይዘው ቪድዮ ለመቅረፅ እና በየማህበራዊ ሚዲያው ለማስራጨት የሚሞክሩ ከድርጊታቸውን እንዲታቀቡ ስርዓተ ቀብሩን ለማስፈፀም የተቋቋመው ኮሚቴ አሳስቧል።ከኮሚቴው አባላት አንዱና የአርቲስቱ የቅርብ ወዳጅ ዲጄ ቢቢ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ሬድዮ በሰጠው ቃል ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር በተለይም ፌክ ኒውስ፣ የተለያዩ ቪድዮ እየቀረፁ ፣ ፎቶዎችን እያነሱ ርዕስ እየሰጡ የሚለጥፉ አሉ ወጣቶቻችን ታናናሾቻችን በዚህ ላይ ጥንቃቄ ያ...
### Text: በሀዋሳ እና በወላይታ ሶዶ ከተማ ያለምንም ጥፋታቸው ያለምንም በደላቸው ህይወታቸውን ባጡት ወንድም እና እህቶቼ የተሰማኝን መሪር ሀዘን ለመግለፅ እወዳለሁ። የሞቱት ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ብሄራቸው ምንም ሊሆን ይችላል የሞቱት ወንድሞቻችን እህቶቻችን ናቸው። ማንም ብሄሩን መርጦ አልተወለድም ባነሰ አስተሳሰባቸው የሰው ህይወት እንዲጠፋ ላደረጉት ፈጣሪ የእጃቸውን ይሰጣቸዋል። ሜዳ ላይ የፈሰሰው ምንም በደል የሌለበት ምንም ወንጀል ያልሰራ ንፁህ የለፍቶ አደር ኢትዮጵያዊ ደም ነው። ሀዘኑ የወላይ...
### Text: 9167 የአጭር የስልክ መስመር 0115527110 የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ስልክ ቁጥር የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እስካሁ ከ300 ያላነሱ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር መረጃ እንዲለዋወጡ መደረጉን አስታውቋል።የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ዶክተር ሰለሞን አሊ በክልሉ ከሚገኙ አለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል የሚገኙ ተማሪዎችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።እ...
### Text: ከ5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስገልገዋል የአማራ ክልል መንግስትየአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስታና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን በክልሉ ህወሓት ወረራ በፈፀመባቸው ዞኖች ማለትም ሰሜን ወሎ ደቡብ ወሎ ከፊል ደቡብ ጎንደር ዋግኽምራ ውስጥ የሚኖሩ እና ተፈናቅለው ያሉትን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል አሳውቋል።ህወሓት በከፈተው ጦርነት ከ991 ሺ በላይ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን በወረራ በተያዙ አካባቢዎ...
### Text: በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚለውን አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ እንቅስቃሴን በዛሬው እለት ተቀላቅለዋል የዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እያደረገች ያለውን ጫና ለመቃወም እንደሆነ የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ገልፀዋል የዛሬው ሰልፍ የተጠራው በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሲሆን የሰልፉ አላማም በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደ...
### Text: ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ️ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በያዝነው የትምህርት ዘመን ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚመጡ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፊታችን ጥቅምት 10 እስከ 12 ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚገቡ ተማሪዎችን ይቀበላል፡፡ ለዚህም ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አረጋግጧል፡፡የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶር ፍሬውተገኘ እንደተናገሩት ተማሪዎችን ለመቀበል ሙሉ ዝግጅት ተደርጓል፡፡ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ልክ እንደ ወላጆቻቸ...
### Text: ህወሓት️የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ ህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ የድርጅቱን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥር ከ11 ወደ ዘጠኝ ዝቅ አደረገ።ማዕከላዊ ኮሚቴው ትናንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ነው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥሩን ቀደም ሲል ወደነበረበት የቀነሰው።በድርጅቱ ህገደንብ መሰረት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥርን የመጨመርም ሆነ የመቀነስ የድርጅታዊ ጉባኤ ስልጣን ነው።ቀደም ሲል ማዕከላዊ ኮሚቴው ከዘጠኝ ወደ 11 ቁጥሩን ከፍ ሲያደርግ በድርጅታዊ ጉባኤ ...
### Text: አማሮ ወረዳ️በአማሮ ወረዳ ታጣቂዎች በድጋሚ ጥቃት አደረሱ። በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 4 ሰዎችን ገድለው 1 ማቁሰላቸውን የወረዳው መስተዳድር ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽሕፈት ቤቱ ዋና አዛዥ ኢንስፔክተር ሲዳሞ ማዳሞ ለ እንደገለጹት ጥቃቱ የተፈጸመው በወረዳው የኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞንን በምትዋሰነውና ካርማ ጅላ በተባለች አነስተኛ መንደር ውስጥ ነው፡፡በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አራት ...
### Text: ጄኔራል ስብሃት ኤፍሬም አገግመው ወደ ቤታቸው ተመለሱ ተባለ በአስመራ በተደረገባቸው የግድያ ሙከራ ቆስለዋል ተብለው የነበሩት የኤርትራ የማዕድን ምኒስትር ጄኔራል ስብሃት ኤፍሬም አገግመው ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን በጃፓን የኤርራ አምባሳደር እስጢፋኖስአፈወርቂ አስታወቁ። ጄኔራል ስብሃት በአስመራ ከተማ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸዋል የተባለው ባለፈው ታኅሳስ 2011 ዓም ነበር። በኤርትራ ላይ የሚያተኩሩ እና በተቃዋሚዎች የሚተዳደሩ ማኅበራዊ ድረገፆች ጄኔራሉ በሽጉጥ ጭንቅላ...
### Text: በጦርነት የደቀቀችውን ከተማ ያበረታቱ የሰሜን ወሎዋ ወልድያ ከተማ በኢንቨስትመንቱ ዘርፉ በሯን ክፍት ማድረጓን አሳውቃል። ከተማዋ ጥር 6 ቀን 2015 ዓም0 የኢንቨስትመንት ፎረም ያዘጋጀች ሲሆን ቢዝነስ ብሔር አልባ መሆኑን የተረዱ እና እራሳቸውን ብቻ ሳይሆን ሕዝብን ለመጥቅም ሁለተናዊ አቅሙና ክህሎቱ ያላቸውን ትክክለኛ0 ባለሀብቶች ጋብዛለች ሲል የከተማው አስተዳደር ገልጿል። የከተማው አስተዳደር ወልድያ በ5 አገር አቋራጭ መንገዶች የምትማከል ዲዛይኑ በተሻሻለው ከጅቡቲ ወደብ አዲስ ...
### Text: በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 800 ማክስ አውሮፕላን ላይ በደረሰው አደጋ ላይ የተሰጠ መግለጫየኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737800 ማክስ የበረራ ቁጥር 302 አውሮፕላን የገጠመውን አደጋ ተከትሎ የሟቾችን አስክሬን ለመለየት ይቻል ዘንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የፎረንሲክ ምርመራ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡በዚህም መሰረት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንና ከኢትዮጵያ ትራንስፖርት ሚንስቴር ...
### Text: ነሃሴ 142012 ዓምየኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 768 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። 2 ከማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ 1 ከአሶሳ ወረዳ ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 390 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 5 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተረጋግጧል የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።አጠቃላይ በድሬዳዋ 742 በቫይረሱ የተያዘ 20 ሞት 606 ያገገሙ በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስ...
### Text: አሳዛኝ ዜና ዜና እረፍት ይፈታል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የፖለቲካ እስረኛ በእስር ቤት ህይወቱ አለፈ በእነ እስከዳር ይርጋ ክስ መዝገብ በበሽብር ክስ አራት አመት ተፈርዶበት ይፈታል ተብሎ እየተጠበቀ የነበረው 2ኛ ተከሳሽ ገበየሁ ፈንታሁን በእስር ቤት ባጋጠመው የጤና እክል ህይወቱ አልፏል። ተከሳሹ በቂ ሕክምና ባለማግኘቱ ከደከመ በኋላ ወደ ፖሊስ ሆስፒታል ተወስዶ የካቲት 182010 በፖሊስ ሆስፒታል ህይወቱ አልፏል። ገበየሁ ፈንታሁን ማዕከላዊ 8 ቁጥር በሚባል ጨለማ ቤት ታስሮ እንደነበ...
### Text: ሰበር ዜና በቅርቡ ከእስር የተፈቱት እስክንድር ነጋ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ አንዱአለም አራጌ፣ በፍቃዱ በሀይሉን ጨምሮ ሌሎች 12 ግለሰቦች ዛሬ ምሽት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል። ዛሬ በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት ቤት ጀሞ ወጣቶች ከእስር ለተፈቱ ሰዎች የምስጋና እና የስጦታ ፕሮግራም አዘጋጅተው ነበር። ፕሮግራሙ ላይም ተመስገን ደሳለኝ፣ አንዲለም አራጌ፣ እስክንድር ነጋ፣ ኦልባና ሌሊሳ፣ ናትናኤል መኮንን፣ እማዋይሽ ዘውዱ እና አበበ ቀስቶ ተካፋይ ነበሩ።ወደ ፕሮግራሙ ማለቂያ ...
### Text: አካላዊ ጉዳት አልደረሰብኝም አረጋዊ በርሄ ዶርበጄነራል ሰዓረ መኮንን እና ሜጀር ጄነራል ገዛኢ አበራ የቀብር ስነስርዓት ላይ ለመካፈል ወደ መቀሌ ያቀኑት የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ትዴት መሪ አረጋዊ በርሀ ዶር የወጣቶች መንጋ ባሏቸው ሰዎች ጥቃት እንደተሞከረባቸው ተናግረዋል፡፡ ቢሆንም ግን አካላዊ ጉዳት አልደረሰብኝም ብለዋል።የቀብር ስነስርዓቱ ላይ ለመገኘት የሰማእታት ሃውልት ደጃፍ ላይ ሲደርሱ ከውስጥና ከውጭ የነበሩት ወጣቶች መግባት የለበትም ብለው በመቃወማቸውና ጥቃት ለማድረስ በ...
### Text: የጅማ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት በ2011 ዓም የትምህርት ዘመን በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ስነስርዓት አካሔደ፡፡ በዚህ ስነስርዓትም ላይ አራት ነጥብ ያመጡ 53 ተማሪዎች የእውቅና ምስክር ወረቀት የተሰጣቸው ሲሆን ከነዚሁ መካከል ስምንቱ አስሩንም የትምህርት አይነት ያስመዘገቡ ናቸው፡፡ በዕውቅና ዝግጅቱ ላይ የተገኙት የጅማዩኒቨርሲቲ ፕሬዘደንት ዶር ጀማል አባፊጣ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ተማሪ...
### Text: በተፈጠረ የግለሰቦች አለመግባባት ህይወት ሊጠፋ ችሏል የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ከሰሞኑ በሀዋሳ ከተማ የግብርና ሚኒስቴር0ሜካናይዜሽን የስራ ሂደት መሪ0ስራ አስፈፃሚ አቶ በረከት ፎርሲዶ በአንድ የመዝናኛ ስፍራ በጥይት ተመተው ህይወታቸው አልፏል የሚል መረጃ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ደርሶት ተመልክቷል።ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለማጣራት ጥረት አድርጓል።በጉዳዩ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያዬታቸዉን የሰጡት የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ወንጀሉ የተፈጸመ...
### Text: ስለ ጥዋቱ የ ዘገባ ከባሌ ጎባ ነዋሪ️ሰላም ፀግሽ የሰራው ዘገባ አንብቤዋለሁ ዘገባው ሚዛናዊነትን የሳተ እንዲሁም እውነታውን ያላንፀባሩ ነው። እኛ ቀኑን ሙሉ አደባባዩ ሰፈር ነበርን። ቀብሮዋ እንድትፈረስ በደንብ ተጠንቶበት የተሰራ ስራ ነው። ለዚህም ማስረጃ አለን ከጥዋቱ 3 ሷት አካባቢ የዞኑ አስተዳደር ከገጠር የመጣውን ማህበረሰብ ሰብስቦ ስብሰባ ሲያደርግ ነበር ቀሪው ህዝብ እንዳይወጣ ደግሞ የከተማው ከፍተኛ ባለስልጣናት በዚያን ቀን ማለትም ቅዳሜ ምንም አይነት ችግር እንደማይፈጠር እ...
### Text: የኤርትራ የነጻነት ቀን አዲስ አበባ በሚገኘው የአገሪቱ ኤምባሲ ተከበረ28ኛው የኤርትራ የነጻነት ቀን አዲስ አበባ በሚገኘው አዲሱ የአገሪቱ ኤምባሲ ዛሬ ግንቦት 17 ቀን 2011 ዓም ተከብሯል።በበዓሉ የተገኙት የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እንደገለጹት በዓሉ በዚህ መልኩ መከበሩ በሁለቱ አገራት ባለፈው አንድ ዓመት ያደረጉት መቀራረብ ውጤት ነው ብለዋል።ባለፈው አንድ ዓመት በከፍተኛ ባለስልጣናት በኩል የተደረጉ የጉብኝት ልውውጦች እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙ...
### Text: በኳታር ለምትገኙ ኢትዮጵያውያንየኢትዮጵያ ኤምባሲ ዶሃየኳታር የሚኒስትሮች ምቤት የኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን ለመግታት ያስችላሉ ያላቸውን ተጨማሪ ውሳኔዎች አሳልፏል። በዚህም መሰረት ሁሉም የአገሪቱ ዜጎች እና ሁሉም ነዋሪዎች ከግንቦት 14 ቀን 2012 ዓም 22 2020 ጀምሮ ከቤታቸው ሲወጡ የቫይረስ ተጋላጭነት ደረጃን የሚያሳየውን የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ በስልኮቻቸው ማውረድ ይጠበቅባቸዋል። በግል መኪናዎች ውስጥ ከ2 ሰው በላይ ሆኖ መጓዝ አይፈቀድም። በታክሲዎች፣ በሊሞዚኖች እና በ...
### Text: ከአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ጋር ተያይዞ ሕገ ወጥ ፎርጅድ እና መታወቂያ ለማይገባው ሰው የሰጠ ከ3 እስከ 10 ዓመት እንደሚያስቀጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ በመታወቂያ አሰጣጥ ላይ ውይይት አድርጓል።በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ዶር ቀንአ ያደታ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሰረት በማድረግ የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ ...
### Text: በድጋሚ ቴሌግራም ላይ ና በሚል በአጭበርባሪዎች የተከፈቱ እንጂ ትክክልኛ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስር ያሉ አይደሉም።ገፆቹ በመቶ ሺዎች ሚቆጠሩ ሰዎች ያሉባቸው መሆኑን የተመለከትን ሲሆን ሁሉም ድርጊታቸው ከቲክቫህ ጋር የማይገናኝ እና ስራቸውም በስማችን ማጭበርበር ነው።ውድ ቤተሰቦቻችን ከመሰል አጭበርባሪዎች ራሳችሁን እንድትጠብቁ በድጋሚ አደራ እንላለን።በዚሁ አጋጣሚ በየዕለቱን የቲክቫህ አባል እየሆናችሁ ለምትገኙ በሺዎች የምትቆጠሩ ቤተሰቦቻችን በኛ ስር ያሉት ትክክለኛ ገፆች የሚከተሉት ...
### Text: ለጥያቄዎቻችሁ መልስ1የ እና 2 በተመለከተከዚህ ቀደም በባንክ እየሄደን ገንዘብ በማሰባሰብ የምንተጋገዝበትን መንገድ በሌላ በተሻለ አማራጭ ለመተካት ብዙ ሲታሰብ ነበር። ለማስጀመርም እንቅስቃሴ ተሞክሯል። ግን ያለው ሁኔታ ምቹ ባለመሆኑ ሊሳካ አልቻለም። አሁን ግን ከሜዳ ቻት ጋር በመተባበር በአሞሌ በኩል ስራዎችን ለመስራት ዝግጅታችንን ጨርሰናል። በቀጣይ እንዴት እንደሚሰራ እናሳውቃለን።2 የ የመማሪያ ቻናላችንን በተመለከተ ብዙ ለመስራት ተሞክሯል። ነገር ግን በፍቃደኝነት ላይ ...
### Text: ዳኛው በአምላክ አለቀሰከላይ ያለድ ምስል የኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማ እንባ አዘል ፎቶ ነው። ለመሆኑ በአምላክ ለምን አለቀሰሚያዚያ 52011 በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላካ ከጊኒው ሆሮያ የመልስ ጨዋታ ሊያደርጉ ሞሮኮ ላይ ተገናኝተው ነበር።ከሳምንት በፊት ሁለቱ ቡድኖች ጊኒ ላይ ያለ ጎል አቻ በመለያየታቸው የመልሱ ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል።ካፍ ደግሞ ኢትዮጵያውያኖቹን በአምላክ ተሰማን የመሀል ዳኛ ተመስገን ሳሙኤልን ...
### Text: የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ዓረፉ።ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ምሽት ላይ በተወለዱ በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።ብፁዕ አቡነ አልሳዕ በ1927 ዓም በበጌምደር አውራጃ ደራ ወረዳ አፈር ውሃ እናት የተወለዱ ሲሆን የተለያዩ ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን በመከታተል በ1971 ዓም የጵጵስና ማዕረግ ተቀብለዋል።በተሰጣቸው ሃይማኖታዊ ስልጣንና ሃላፊነት ከ40 በላይ ዓመ...
### Text: ነሃሴ 152012 ዓምየኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች 1 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 560 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 14 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። 2 ከማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ 1 ከአሶሳ ወረዳ 1 ከጉባ ወረዳ 1 ከአሶሳ ህዳሴ ኤርፖርት 3 ከአሶሳ ከተማ በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1392 ላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 273 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል የ1 ሰው ህይወት አልፏል ከአላማጣ በአስክሬን ምርመራአጠቃላይ በትግ...
### Text: የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትግራይ ክልል የመደፈር ጥቃት የተፈፀመባቸው ሴቶች እና ልጃገረዶች ቁጥር ከ1400 መብለጡን ገለፀ።በፌዴራል መንግስቱ የተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፍትህ እና የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወሮ ኢተነሽ ንጉሰ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና ተቋማት የሄዱ ሴቶች እና ልጃገረዶች ቁጥር 1408 መድረሱን ተናግረዋል።እንደትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መረጃ በመቐለ 716 ከዓዲግራት 362 ከአክሱም 85 ከሽረ 48 ከማይጨው 37 ከመሆኒ 18 የተመዘገቡ...
### Text: የተሳሳቱ መረጃዎችን በመልቀቅ ተማሪዎች የስነ ልቦና ጫና እንዲደርስባቸው የሚያደርጉ አካላትን በህግተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ ነው ዶር እሸቱ ከበደየ2014 ዓም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ስራ ሙሉ በሙሉ በመጠናቅ ላይ መሆኑን የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ ዶር ተናግረዋል፡፡የፈተና ዝግጅቱም የተማሪዎችን ልፋት ሊለካ በሚችል ከደህንነት ስጋት ነፃ እንዲሆን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑን...
### Text: ዶር ዐብይ ፕሬዚደንት ኢሣያስ አፈወርቂ አወደሱ ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማታቸውን ሲቀበሉ ባደረጉት ንግግር ፕሬዚደንት ኢሣያያስ አፈወርቂ አወደሱ። «ይኽን ሽልማት የምቀበለው በኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስም ነው። በተለይ ደግሞ ለሰላም ሲሉ ከፍተኛውን መስዋእትነት በከፈሉት ስም። በተመሳሳይ ሽልማቱን የምቀበለው በአጋሬና የሰላም ጓድ በኾኑት ፕሬዚደንት ኢሣያያስ አፈወርቂ ስም ነው» ብለዋል። ይኽ ንግግራቸውም ከታዳሚያን ሞቅ ያለጭብጨባ ታጅቧል። የፕ...
### Text: በ2013 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ለኢቲቪ ገልጸዋል። የቀጣዩ ዓመት ትምህርት ምዝገባ ከነገ ነሐሴ 20 ቀን 2012 ዓም ጀምሮ በመንግሥት እና በግል ትምህርት ቤቶች እንደሚጀመር የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን በመተግበር ምዝገባ እንዲያከናውኑ ተፈቅዷል ብለዋል። የበሽታው ሁኔታ እየተስፈፋ ቢሆንም የትምህርት ዝግጅት እና እንቅስቃሴ መጀመ...
### Text: መቀሌ ለተጨነቃችሁ ቤተሰቦች በሙሉ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሁሉም ካምፓሶች ሰላም ናቸው።ከባለፈው የወልዲያ ግጭት በኃላ አንዳንድ ስሜታዊ ወጣቶች በተለያዩ ተማሪዎች ላይ ትንኮሳ ለመፍጠር ሞክረው የነበር ቢሆንም ያን ያህል በሶሻል ሚዲያው ተጋኖ እንደተወራው አይደለም።በአሪድ ካምፖስገዳም ሰፈር ተገቢ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎች በአንዳንድ ወጣቶች እየታየ እንዳለ የገለፁት ተማሪዎች ድንጋይ የመወርወር እና ተማሪዎችን ማስፈራራት እንቅስቃሴ ነበረ። ግቢውም ጉዳዩን በማጣራት ተገቢውን ፈጣን እርምጃ እንዲወስ...
### Text: የህዳሴ ግድብ️የታላቁ ህዳሴ ግድብ የኤልክትሮ ሜካኒክ ስራዎች በዘርፉ ዓለማቀፍ እውቅና ባላቸው የውጭ ኩባንያዎች በመሰጠቱ ህዝቡ ጥራትን በተመለከተ ሥጋት እንዳይገባው ተገለጸ።ግድቡን አስመልክቶ ዛሬ በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ የተሳታፊዎቹ ዋና ጥያቄ ግድቡን እንዴት እንጨርሰዋለን እና ጥራቱስ እንዴት ይጠበቃል የሚለው ነበር።በዚህ ጉዳይ ላይ መልስ የሰጡት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ወቅት በኤሌክትሮ ሜካኒካል ...
### Text: አንዳንድ አገራት የሚያወጡትን አሃዝ የሚያምን አለ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት መግለጫ የሰጡት ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኮሮና ቫይረስ በአሜሪካ ሊያስከትለው የሚችለው ጉዳት ጣሪያን በማለፉ አንዳንድ ግዛቶች በዚህ ወር መከፈት እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።ፕሬዘዳንቱ ከአሜሪካ ግዛት አስተዳዳሪዎች ጋር ከተወያዩ በኋላ ግዛቶቹ ስለሚከፈቱበት ሁኔታ ዛሬ ምሽት መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቀዋል።አሃዞች እንደሚያሳዩት በመላው አገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው በማለት ዶናልድ ትራ...
### Text: የትግራይ አብዛኛዎቹ ከተማዎች በጨለማ ተውጠዋል።ከትላንት ሀሙስ ከሰዓት ጀምሮ በትግራይ መቐለን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል።የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በአብዛኞቹ የትግራይ ክልል ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን ገልፀው ኤሌክትሪክ የተቋረጠው ከመሆኒ 40 ኪሜ ላይ ወደ መቐለ ባለ መስመር ላይ ሊሆን እንደሚችል ነው የተቋሙ ባለሞያዎች የለዩት ብለዋል።ትክክለኛው ቦታ ባይታወቅም የባለሞያዎቹ ግምት ወደዛ መስመር ነው...
### Text: ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባለ 50 ወለል ህንጻ ሊገነባ ነው።0 ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ይታወቅበት የነበረውን ደቡብ ግሎባል ባንክ የተሰኘውን ስያሜውን እና የንግድ ምልክቱን ከቀየረ በኋላ ዋና መስሪያቤቱን በአዲስ አበባ ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ አስታውቋል።ባንኩ ለዋና መስሪያቤቱ ግንባታ ከ18 በላይ ድርጅቶችን የአርኪቴክቸራል ዲዛይን ያወዳደረ ሲሆን የባንኩን የወደፊት መስሪያ ቤት ዲዛይን ኢላፕስ ቢዝነስ ኃየተየግ ማህበር የሰራውን ዲ...
### Text: ጠሚ ዶር አብይ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል አንድ ወደፊት ስንሄድ ሁለት ወደኋላ የሚመልሱንን ሀይሎች ማስቆም እንደሚገባ ጠሚ ዶክተር አብይ አህመድ አሳሰቡ። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በመግለጫቸውም ከሰሞኑ በተከሰተው ግጭት የ86 ሰዎች ህይወት አልፏል ያሉ ሲሆን ከሟቾች መካከል 82 ወንድ፣ 4 ሴቶች መሆናቸውምን አስታውቅዋል።በብሄር ደግሞ 50 ኦሮሞ፣...
### Text: የ2014 ዓም የትምህርት ዘመን የብሄራዊ ህክምና ስፔሻሊቲ መግቢያ ፈተና ነገ ይሰጣል።ነገ ሰኞ ታህሳስ 42014 ዓም የህክምና ስፔሻሊቲ መግቢያ ፈተና የሚሰጥ ሲሆን ፈተናው በአማራ ክልልም የሚሰጥ ይሆናል።የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ለኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ፅፎ በነበረው ደብዳቤ አሸባሪው ህወሓት ወረራ በፈፀመት ወቅት በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ ፈተናውን ለመፈተን ተመዝግበው በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ጠቅላላ ሀኪሞች ላይ ጫና በመፈጠሩ መግቢያ ፈተናው ለመፈተን ስለሚቸ...
### Text: በጎንደር ከተማ ህግ ተላልፈዋል የተባሉ 53 የፀጥታ አካላት እንዲጠየቁ መደረጉን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ገለፀ።መምሪያው ይህ ያሳወቀው በመምሪያው ኃላፊ አቶ ፋሲል ሰንደቁ አማካኝነት ለከተማው ነዋሪዎች በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ የመወያያ ፅሁፍ ባቀረበበት ወቅት ነው።በከተማዋ የእገታ ወንደል ህገ ወጥ የጥይት ተኩስ ተጀራጅቶ ዘረፉ ዋና ወና የከተማዋ ወንጀሎች መሆናቸውን አቶ ፋሲል ገልፀዋል።በዚህ የእገታ ወንጀል ተሳትፈዋል የተባሉ 34...
### Text: ፕሬዝዳንት ካቦሬ በወታደሮች ታስረዋል።የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት በሀገሪቱ ወታደሮች መታሰራቸው ተነግሯል።ፕሬዝዳንት ሮች ካቦሬ የታሰሩት በአማጺ ወታደሮች ሲሆን በሀገሪቱ መዲና ኡጋዱጉ ባለ አንድ ወታደራዊ ማዘዣ ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል።የቡርኪና ፋሶ መንግስት በትናንትናው ዕለት የወታደሮቹ እንቅስቃሴ መፈንቅለ መንግስት አለመሆኑን ገልጾ ነበር።በቡርኪና ፋሶ ወታደሮች ውስጥ ጥያቄ እንዳነሱ የሚነገርላቸው አማጺ ወታደሮች አዛዦቻቸውን ጨምሮ መሪዎችን ገድለዋል።ይሄንን ተከትሎም የቡርኪና ፋሶ መ...
### Text: በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ተከስቶ በነበረ ግጭት መደበኛ ትምህርታቸውን መከታተል ያልቻሉ ከ7ሺህ 600 በላይ ተማሪዎች ዘንድሮ የሚሰጡትን ክልላዊና አገር አቀፍ ፈተናዎች እንደማይወስዱ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሙላው አበበ እንደገለጹት በዞኖቹ በነበረው ግጭት በ53 የአንደኛና በአምስት የሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራ ተቋርጦ ቆይቷል።በግጭቱ ተማሪዎቹን ጨምሮ የትምህርት ቤቶቹ ማኅበረሰብ አባላት በመፈናቀላ...
### Text: ምርጫ2013እናአዲስአበባ በአዲስ አበባ ድምፅ ሰጪው ረጅም ሰልፍ ነበረበት የሚልም ቅሬታ ነበር ይሄ ጉዳይ እንዴት ይታያል ወሪት ሶሊያና ምንም ጥያቄ የለውም በተወሰነ ደረጃ የድምፅ ሰጪዎች መንገላታት ቢያሳዝንም በሌላ በኩል ሲታይ ድምፅ ሰጪዎች በድምፅ መስጠት ሂደቱ ላይ ለመሳተፍ ረጅም ሰዓት ወስደው በከፍተኛ ወጥተው ድምፅ መስጠታቸው በጣም የሚያስደስት ነው ይህም በቦርዱ በጥሩ ጎኑ የታየ ነው። በአጠቃላይ በአአ የነበረው ምርጫ በወሪት ሶሊያና ሽመልስ አዲስ አበባ በጣም ጥቂት ...
### Text: ትዴት ተቃዋሚው የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ትዴት ፓርቲ ዛሬ በአዲስ አበባ ባካሄደው ውይይት ትግራይ ውስጥ አሁንም አፈና ቀጥሏል አለ። ህዝብን ከድህነት ለማላቀቅ የሚጥሩ ፓርቲዎች በነጻነት መንቀሳቀስ እንዳልቻሉም ገልጿል። የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ትዴት ትግራይ ውስጥ አሁንም አፈና መቀጠሉን እና ህዝቡን ከድህነት ለማላቀቅ የሚጥሩ ፓርቲዎች በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት ለውጥ እንዳልታየበት ገለጸ።0የትግራይ ህዝብ በጠላት ተከብበሃል እየተባለ በህወሓት ሽብር እና ፍርሃት እየተለቀ...
### Text: ነሃሴ 252012 ዓምየኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች 1 በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 599 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 22 ሰዎች በኮቪድ19 መያቸው ተረጋግጧል። በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 3343 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 127 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 28 ከአርሲ ዞን 25 ከጉጂ ዞን 14 ከቡራዩ ከተማ 13 ከቢሾፍቱ ከተማ ይገኙበታል።አጠቃላይ በኦሮሚያ 6301 በቫይረሱ የተያዙ...
### Text: ጥቅምት 12013 ዓምየኢትዮጵያ ኮቪድ19 መረጃዎች በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 142 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 7 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተረጋግጧል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 104 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 39 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1154 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 99 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከ99ኙ መካከል 64 ከምዕጎጃም ዞን ፣ 16 ከባህር ዳር ...
### Text: በትላንቱ ስብሰባ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ከኢትዮጵያ ጋር የተዋጣ ግንኙነት እንዲኖር ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን አሁንም እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።እንደውም ለኢትዮጵያ መንግስት ታደላለህ በሚል ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲወቅሱኝ ቆይተዋል ሲሉ ተናግረዋል።ለአምባሳደር ታዬ ባቀረቡት ጥያቄም በኢትዮጵያ መንግስት በኩል እስካሁን ድረስ ለተመድ የገባ ደብዳቤ የለም ከተባረሩት 7 የተመድ ሰራተኞች በአንዱም ላይ ቢሆን አንድም ደብዳቤ ካለ ያቅርቡልኝ የማውቀው ነገር የለም ስለሚባለው ክስ ብለዋል።ገተሬዝ በግ...
### Text: ዶይቼ ቨለ ከአቶ በረከት ጋር️በቅርቡ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው የታገዱት አቶ በረከት ስምዖን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከዶይቼ ቬለው ነጋሽመሐመድ ጋር ዛሬ ቃለ ምልልስ አድርገዋል። ይህ ቃለምልልስ ምሽት 1 ሰዓት በጀርመን ድምፅ ራድዮ የአማርኛ ዝግጅት ላይ የሚቀርብ ይሆናል። ዶቼ ቨለ ከቃለመጠይቁ ቀንጭቦ ለፌስቡክ ተከታዮቹ ይህን አቅርቧል️ ከማዕከላዊ ኮሚቴ ለመታገዴ የውጭ ኃይል እንዳለበት ፍንጭ አለኝ። ሃያ ሰባት ዓመት በስልጣን ስቆይ አንድም ካሬ ሜትር አልወሰ...
### Text: ካለብን ታሪካዊ እና ሞራላዊ ኃላፊነት አንጻር ናሚቢያውያን ይቅር እንዲሉን እንጠይቃለን ሄኮ ማስጀርመን ናሚቢያን ቅኝ በገዛችበት ወቅት ጅምላ ጭፍጨፋዎችን መፈጸሟን አመነች፡፡ጀርመን እአአ ከ190408 ባሉት ዓመታት በናሚቢያ ዜጎች ላይ የፈጸመችውን ግድያ በጅምላ ጭፍጨፋነት ለመቀበል ስታቅማማ ቆይታለች፡፡ነገር ግን 5 ዓመታትን በወሰደ ንግግር ጭፍጨፋውን ስለመፈጸሟ አምና ተቀብላለች።ይህን ተከትሎ በተደረሰ ስምምነት መሰረት ለተለያዩ ልማቶች የሚውል የ13 ቢሊዬን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ተስማ...
### Text: ኢትዮ ቴሌኮም የ4 አገልግሎት ተደራሽነትን እያሰፋ ይገኛል።ከዚህ ቀደም በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞች ተግባራዊ የተደረገው የ4 አገልግሎት በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ ዛሬ ተጀምሯል።ጋምቤላ ከተማ በኢትዮ ቴሌኮም የ ደቡብ ምዕራብ ምዕራብ ቀጠና የሚገኝ ሲሆን የ4 እና የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራውን ተጠናቆ ስራ ጀምሯል።በዚህ ቀጠና 28000 ደንበኞች የዳታ ተጠቃሚዎች ናቸው።በጋምቤላ ከተማ አገልግሎቱን የማስጀመሪያ ስነስርዓት የተካሄደ ሲሆን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወሪት ፍሬህይ...
### Text: ምዕራባዊ ኦሮሚያ ግጭት መታየቱ ተሰማ️በምዕራባዊ ኦሮሚያ ክልል በሚገኙት አከባቢዎች የኦሮሞ ነፃ አዉጭ ግንባር ኦነግ ስራዊት ናቸዉ በተባሉና በኢትዮጵያ መከላክያ ሰራዊት መካከል ላለፉት ቀናቶች ግጭት መታየቱን የአከባቢዉ የዓይን እማኞች ለዶይቼ ቬሌ ገልጹ። ግጭቱን ተከትሎ የክልሉ ፕሬስዳንት አቶ ለማመገርሳ በትላንትናዉ እለት እንደተናገሩት ሁኔታዉ በጣም እንዳሳዘናቸዉ ገልፀዋል። ወጣቶች መሳርያ በመታጠቅ ዘመናዊ መሳርያ ከታጠቀዉ ከመንግስት ሰራዊት ጋር ለመወጋት ወደ ጫካ መግባታቸዉ...
### Text: ሲአን ሲዳማዞን ሞረቾ ወተረሬሳ ሀገረሰላም በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን የገጠር ከተሞች በተከሰቱ ግጭቶች የሞቱት ሰዎች ቁጥር 21 መድረሱን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ አስታወቀ። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ኔሳ ዛሬ ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት በሲዳማ ዞን ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር በነበረ ግጭት 21 ሰዎች መሞታቸው ተናግረዋል። በሲዳማ ዞን ስር ባለው ወተረሬሳ 12 ሰዎች መሞታቸውን የሚናገሩት አቶ ደሳለኝ...
### Text: ብሔራዊ ባንክ ከባንክ ዉጭ ይዞ መንቀሳቀስ የሚቻለዉን የገንዘብ መጠን በድጋሜ ዝቅ ማድረጉ ተገለፀ።ባንኩ ትናንት ካቲት 29 ጀምሮ ይህንንና መሰል ጉዳዮችን የያዙ መመሪዎች ላይ ማሻሻያ አድርጓል።በማሻሻያዉ መሰረት ከባንክ ዉጭ ይዞ መንቀሳቀስ የሚቻለዉ የገንዘብ መጠን ለድርጅቶች ወደ 200000 ብር እንዲሁም ለግለሰቦች ወደ 100000 ብር ዝቅ እንዲል አድርጓል።ባንኩ ተመሳሳይ የገንዘብ መጠን ገደብ የሚጥል መመሪያ ሲያወጣ በ6 ወራት ዉስጥ ለ2ተኛ ጊዜ ሲሆን ከ6 ወራት በፊት የወጣዉና...
### Text: ዎላይታ ታይምስ የተሰኘው ሚዲያ ከመንግስት አካል ይደርስብኛል ባለው ጫና ሥራ ማቋረጡን ገልጿል።በኢትዮጲያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በሚዲያ ሥራ ለመሰማራት ሕጋዊ ፈቃድ ወስዶ በዞናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ የነበረው ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በደረሰበት ጫና ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ሥራ ማቆሙን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላከው መረጃ ያሳያል።የሚዲያው መስራች የሆነው ጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ በሥራው በተደጋጋሚ ለእስርና ለእንግልት፣ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት መዳረጉን ጠቅሶ በቅርቡም ከቀ...
### Text: ነሃሴ 162012 ዓምየኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች 2 በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 4442 የላብራቶሪ ምርመራ 121 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 21 ከምዕጎንደር ዞን 18 ከሰወሎ ዞን 17 ከሰሸዋ ዞን 16 ከደሴ ከተማ 15 ከዋግ ብሰብ ዞን 14 ከደወሎ ዞን 8 ከባህር ዳር ከተማ ይገኙበታል።አጠቃላይ በአማራ 1772 በቫይረሱ የተያዙ 19 ሞት 668 ያገገሙ ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 307 ...
### Text: በኢትዮጵያ ውስጥ በ2021 እአአ በተለያዩ ምክንያቶች የምግብ ርዳታ የሚያስፈልገው ሕዝብ ቁጥር ከፍ ማለቱን የርሃብ ስጋት ማስጠንቀቂያ የሚያመላክተው ዓለም አቀፍ ተቋም አመለከተ። ተቋሙ ባወጣው ሪፖርት በተለይ በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ በተባባሰው የጎሳ እና የፖለቲካ ውጥረት 3 ሚሊየን ገደማ ሰዎች በሀገር ውስጥ ሳይፈናቀሉ እንዳልቀሩ አመልክቷል።ከተፈናቀሉት 3 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች አንድ ሚሊየን የሚሆኑት ትግራይ ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል።በተጨማሪ ትግራይ ክልልን ...
### Text: መግለጫ በአገሪቱ እየመጡ ያሉ ለውጦችን ለማደናቀፍ እየተሰሩ ያሉ ሴራዎችን የሚመረምሩ ኮሚቴዎች ተቋቋሙ።የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅቤት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ሰኔ16፣ 2010 በጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አብይ አህመድ መሪነት በአገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ እውቅና ለመስጠት፣አገራዊ አንድነትን ለመገንባትና የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን ለመደገፍ በወጣው ህዝብ ላይ ቦምብ ተወርውሯል፣ ሂደቱ እንዲስተጓጎልም ተደርጓል፡፡ሰላማዊ ሰልፉን ለማደናቀፍ ቦምብ ከመወርወር ጀ...
### Text: ሀዋሳ️በሐዋሳ ከተማ የድንገተኛአደጋዎችና የቀዶ ጥገና ስፔሻላይዝድ ህክምና ማዕከል ትናንት ተመረቀ።የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የክልሉ መንግሥት የኅብረተሰቡን የጤና ፍላጎት ለማሟላት ለባለሀብቶች ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።የግል ባለሀብቶች በዘርፍ ለተገኙ ውጤቶች ድርሻቸው ከፍተኛ ሲሆን÷ ወደፊትም ለዚሁ ተግባር ኢንቨስትመንት የሚውል መሬት እንደሚመቻችላቸውም ነው የተናገሩት።ባለፉት ዓመታት 4ሺህ 670 የጤና ተቋማት...
### Text: አጫጭር መረጃዎች በኢራን ባለፉት 24 ሰዓት 1481 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል 48 ሰዎች ሞተዋል። በኢራን ዛሬ መስጊዶች በጊዜያዊነት ተከፍተው ሌሎችም እንቅስቃሴ ላይ የተጣሉ ገደቦች እየተነሱ እንደሚቀጥሉ ተገልጻል በሩሲያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ በልጧል ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 10899 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 232243 ደርሰዋል። የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ኮሮና ቫ...
### Text: ለኮቪድ19 የሚሰጠው ትኩረት መቀነስ አሳሳቢ ነው በዶክተር መክብብ ካሳየዓለም ጤና ድርጅት እንደተነበየው የኮቪድ19 ወረርሽኝ ክትባት በስፋት ጥቅም ላይ እስኪውል የሁለት ሚሊየን ሰዎች ህይወት ሊያልፍ ይችላል፡፡በሀገራችን የበሽታው አሳሳቢነት ጨመረ እንጂ አልቀነሰም በየቀኑ የበርካታ ዜጎቻችንን ህይወት እየቀጠፈ ነው፡፡የዓለም ጤና ድርጅት የሚከተሉትን አራት መንገዶች ሀገራት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ይመክራል፡፡ 1 የቫይረሱን ስርጭት ሊያባብሱ የሚችሉ ኘሮግራሞችን መገደብ፡፡2 በቀላሉ ሊጎዱ ለሚ...
### Text: የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይፋ አደርገዋለሁ ያለውን አዲሱን የደንብ ልብስ እና አርማ ዛሬ በይፋ በመስቀል አደባባይ አስተዋውቋል።አዲሱ የደንብ ልብስ እና አርማ ከላይ በፎቶ ተያይዟል።አዲሱ የፖሊስ አርማ ምን አካቷል የሚሰጠው ትርጉም ምንድነው ጋሻ መከላከልን፣ ጥንካሬን፣ ድፍረትና ጀግንነትን ይወክላል ተብሏል። ቀጥ ያሉ እኩል ጨረሮች ጨረሮቹ የብሄር ብሄረሰቦችን፣ የህዝቦችን እና የሃይማኖት እኩልነትን የሚያሳዩ ናቸው። የተከበበ ክብ መስመር ጋሻነትን ለማመልከት የተቀመጠ ነው።...
### Text: ችሎት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ተከሳሾች ላይ የዐቃቤ ሕግ መስክሮችን ለመስማት የያዘው ቀጠሮ ተፈጻሚ ሳይሆን ቀርቷል።ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ሳይሰማ የቀረበው የተከሳሽ ጠበቆች ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው።ከተከሳሽ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ከድር ቡሎ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጃዋር መሐመድን ጨምሮ አራት ተከሳሾች በሌሉበት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች...
### Text: የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በዚህ ሳምንት 2 በረራዎችን ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ በማድረግ የህክምና ቁሳቁሶችን አድርሷል።ባለፈው ሳምንት በ5 በረራዎች እጅግ አስፈላጊ የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ማጓጓዙና ማከፋፈል መጀመሩን መግለፁ ይታወሳል።በዚህ ሳምንት ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር እና ከቀይ መስቀል የቀረቡ መድሃኒቶችና ሌሎች የህክምና አቅርቦቶችን በመያዝ 2 ተጨማሪ በረራዎች ወደ ትግራይ ክልል ተደርገዋል።በዚህ ሳምንት በቀሩት ቀናት እና በሚቀጥሉት...
### Text: የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻችውን አስመረቁ። ዛሬ ተማሪዎቻቸውን ካስመረቁት ዩኒቨርሲቲዎች መካከልም የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ይገኝበታል። ዩኒቨርሲው በተለያዩ መርሃ ግብር ያስተማራቸውን ከ 5 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎችን አስመርቋል። በተጨማሪም ለአርቲስት አሊ ሸቦ እና ለዶክተር አበራ ደሬሳ የክብር ዶክተሬት ሰጥቷል። በሌላ በኩልየጎንደር ዩኒቨርሲቱ በተለያዩ የትምህርት መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 8 ሺህ 365 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከልም 3 ሺህ 227 ተማሪዎች ...
### Text: ሰብሌን ያዳነችልንን ሰብልዬን እናመሠግናለን በቃሉ ወረዳ የ019 የአብቾ ቀበሌ አርሶ አደሮች የቃሉ ወረዳ የ019 የአብቾ ቀበሌ አርሶ አደሮቹ በአምበጣ መንጋው ክፋት እና በሚያደርሰው ጉዳት የተማረሩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ለ4ኛ ጊዜ በአብቾ በቀበሌ የሠፈረው የበረሀ አንበጣ መንጋ በሰብልና በእንስሳት መኖ ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ይህን መንጋ ለመከለካል የምስራቅ አፍሪካ አንበጣ መከላከል ድርጅት በተደጋጋሚ በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት ቢያከናውንም እንደዛሬው የተሳካ ርጭት አለማ...