text
stringlengths
707
989
### Text: አሳ ዛኝ ዜና️በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ጃማ ወረዳ በጫነው አሸዋ ላይ 31 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የሰዎች ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ።የጃማ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የትራፊክ አደጋ መርማሪ እንደገለጹት ሲኖትራክ ተሽከርካሪው በቶ ከተባለ ስፍራ በጫነው አሽዋ ላይ 31 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ደጎሎ ከተማ በመጓዝ ላይ እያለ ነበር አደጋው ያጋጠመው።ተሽከርካሪው በዛሬው እለት ከጠዋቱ 12 ሰዓት ገደማ 14 ቀበሌ ልዩ ቦታው ዝግባ ከሚባል...
### Text: ዩኒቨርሲቲዎች የፌዴራል ተቋምነታቸው ሊረጋገጥ የአካዳሚክ ነጻነታቸውም ሊከበር ይገባል አሁን ባለው ሁኔታ ዩኒቨርሲቲዎች የሚስተዋለው እንደ ፌዴራል ሳይሆን እንደ አንድ አከባቢ ተቋም የመንቀሳቀስ አዝማሚያ ፈር ሊበጅለትና የፌዴራል ተቋምነታቸው ሊረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ የአካዳሚክ ነጻነታቸው ተከብሮ እንዲሰሩ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ተጠቁሟል፡፡የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋምም ምልከታው ተገቢና ሊታረም እንደሚገባው በመጠቆም ዩኒቨርሲቲዎች የፌዴራል ተቋም ሆነው እንዲሰሩ እንደሚደ...
### Text: የአትክልትና ፍራፍሬ ዋጋ በጥቅምት መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል የጥቅምት ወር የአትክልትና ፍራፍሬ ዋጋ መጠነኛ ቅናሽ ማሳየቱን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ገለፀ። የጥቅም ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 18 ነጥብ 6 በመቶ ሆኖ መመዝገቡንም አስታውቋል። ኤጀንሲው ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የዚህ ወር የአትክልትና ፍራፍሬ ዋጋ ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር በዜሮ ነጥብ ሁለት ከመቶ ቅናሽ ታይቷል።በወሩ ቲማቲም፣ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ድንች፣ ጎመን፣ ካሮት፣ ምስር፣ ቅቤ፣ የምግብ ዘ...
### Text: የሞት ፍርድ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት እና የሳውዲው ልዑል በሌሉበት የሞት ፍርድ ተፈረደባቸው።በየመን የሑቲ ታጣቂዎች ፍርድ ቤት የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕንና የሳኡዲውን ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማንን በሌሉበት ሞት ፈረደውባቸዋል።ፍርድ ቤቱ በነዶናልድ ትራምፕ መዝገብ ተከሰው የነበሩ ዘጠኝ ሰዎች ከትናንት በስቲያ በአደባባይ በሞት ቀጥቷቸዋል፡፡በሞት ከተቀጡት ዘጠኝ ሰዎች መሀል በሚያዝበት ወቅት አዳጊ የነበረ አንድ ልጅ ይገኝበታል፡፡በሰንዓ አደባባይ ላይ በመቺ ኃይል...
### Text: የፌዴራል ፖሊስ ለልጆቻችሁ ሙሉኃላፊነት ይወስዳል አስተማማኝ ጥበቃም ያደርግላቸዋል የጋምቤላ ትምህርት ቢሮከሰሞኑን በጋምቤላ ክልል የፀጥታ ችግር መከሰቱና የሰዎች ህይወት ማለፉ ፣ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል።ይህን ተከትሎም በክልሉ የሰዓት እላፊ ገደብ ታውጆ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እንዴት ሊሆን ነው የሚለው የብዙሃን ጥያቄ ነው።የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሰሞነኛው የክልሉ ...
### Text: የሲዳማ እና ወላይታ እርቀ ሰላም️የሲዳማና ወላይታ የሀገር ሽማግሌዎች የእርቀ ሠላም ውይይት እያካሄዱ ነው።በሀዋሣና ሌሎችም አንዳንድ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን ግጭት በመፍታት በሲዳማና ወላይታ ሕዝቦች መካከል ዘላቂ እርቀ ሠላም ለማውረድና የሀገር ሽማግሌዎች እየተወያዩ ነው።የሁለቱን ህዝቦች የቆየ ታሪካዊና ሁለንተናዊ ትስስር እንዲሁም መልካም ጉርብትና ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።የሀገር ሽማግሌዎቹ በዚህ ዓመት ከታየው ጊዜያዊ ግጭት ይልቅ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ለረጅም ዘመናት ጸንቶ...
### Text: ተስፋ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከምንም በላይ ለበርካታ ወራት የእናት አባቶቻቸውን የእህት ወንድሞቻቸውን ፣ የወዳጆቻቸውን ድምፅ ያልሰሙ እጅግ በርካቶች ስምምነቱ በፍጥነት ወደተግባር ገብቶ ያናፈቋቸውን ሁሉ ድምፃቸውን ሊሰሙ ጓግተዋል።ከዚህ ቀደም የባንክ አገልግሎት በመኖሩ እያገዟቸው የነበሩ መላ ቤተሰቦቻቸውን ዳግም አግኝተዋቸው የየትኛውም የእርዳታ ድርጅት እና ተቋም አካል ደጅ እንዳይጠኑ ለማድረግና ያለባቸውን ችግር ለመቅረፍ እየተጠባበቁ ነው።ቤተሰቦቻቸው በህይወት ይ...
### Text: በአሜሪካ የሚደርስበትን ዘር ጥቃት በመሸሽ ኑሮውን አፍሪካ ያደረገው ግለሰብ በአሜሪካ የሚደርስበትን የዘር ጥቃት በመሸሽ ኑሮውን በአገረ ጋና መስርቶ እየኖረ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡ ኦባዴል ካምቦን የተባለው ትውልደ አሜሪካዊው አሜሪካ እያለ መልኩ ጥቁር በመሆኑ በፖሊሶች ዘር ተኮር ጥቃት ሲደርስበት እንደቆየ ይናገራል፡፡በተለይ በአሜሪካ ቆይታው የህይወቱን ወሳኝ ምዕራፍ የቀየረው በአውሮፓዊያኑ 2007 ተገቢ ያልሆነ ክስ ተመስርቶበት ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ መሆኑን ኦባዴል ካምቦን ...
### Text: የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን የተመለከተ ውይይት በባህርዳር ተካሄደ።የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በክልል ደረጃ ፈተናውን ውጤታማ ለማድረግ ከዞንና ወረዳ የፈተና ክፍል ሰራተኞች ጋር በባህር ዳር ከተማ ፈተናውን አስመልክቶ ውይይት አድርጓል፡፡የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምኃላፊ አቶ ሙላው አበበ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ባለው አጭር ጊዜ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራ በመስራት በክልሉ ያለመንም ችግር በውጤታማነት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።የፈተና ጊዜው...
### Text: በሚዛን አማን 1 ኪሎ ስጋ ከ360 ብር በላይ መሸጥ ተከለከለ።የቤንች ሸኮ ዞን ንግድ እና ገበያ ልማት በልኳንዳ ቤቶች የስጋ መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ አድርጓል።በስጋ ዋጋ ላይ እየታየ ያለዉ የዋጋ ጭማሪ የህብረተሰቡን የመግዛት አቅም የሚፈታተን እና ወጥነት የሌለዉ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ችግሩን ለመፍታት የቤንች ሸኮ ዞን ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ በዞኑ ከሚገኙ የልኳንዳ ቤት ባለቤቶች ጋር ዉይይት አካሂዷል።ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በተደረገዉ ዉይይት የስጋ ዋጋ ወጥነት እንዲኖረው መግባባ...
### Text: ዛሬ በመቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው ተጋጩ። ፓሊስም ወደግቢው በመግባት አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም ሁኔታውን ለማረጋጋት ችሏል።የግጭቱ ምክንያት ዛሬ በግቢው በተደረገ ስብሰባ ላይ ተማሪዎች የሰነዘሩት ቃል አለመግባባትን እና ቁጣን በመፍጠሩ ነው። ስብሰባው በግቢው እየተስተጓጎለ የሚገኘውን የትምህርት ስርዓትን በሚመለከት ከተማሪዎች ጋር ወይይት ለማድረግ የታቀደ ነበር። በተፈጠረው ግጭት የተጎዱ ተማሪዎች እንዳሉ እና ብሄርን መሰረት ተደርጎም አንዳንድ ግለሰቦች በሰዎች ላይ ድብደባ መ...
### Text: በባቲ ከተማ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በመስጠት የተጠረጠረ ግለሰብ ተያዘ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ባቲ ከተማ ሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በመስጠት የተጠረጠረ ግለሰብን እጅ ከፍንጅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ። የከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መሃመድ አሊ እንደገለጹት ሀሰተኛ ማስረጃ በመስራት በህገ ወጥ መንገድ የመጠቀም 0ተግባር እየተስፋፋ መጥቷል። ሰሞኑን ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት ፖሊስ ባካሄደው ፍተሻ ከ170 በላይ የሀሰተኛ የትምህርት ማ...
### Text: ቱርክ በየትኛዉም ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጎን ትቆማለች አምባሳደር ያፕራክ አልፕበኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ የህዳሴዉ ግድብ ሶስትዮሽ ድርድር እና የኢትዮ ሱዳን የድንበር ዉዝግብ በሠላማዊ መንገድ ሊፈታ ይገባል አሉ።አምባሳደሩ ይህን ያሉት ለኢትዮ ኤፍ ኤም 1078 በሰጡት ቃለምልልስ ነው።ቱርክ ከሱዳን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ግንኙነት ያላት አገር መሆኗን የገለፁት አምባሳደሩ ጦርነት ለሁለቱም አገራት ስለማይበጅ ልዩነታቸዉን በዉይይት እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡አምባሳደር ...
### Text: የታላቁ ህዳሴ ግድብ 3ኛውን የውሃ ሙሌት ለማከናወን በ21 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የምንጣሮ ስራ እየተከናወነ ነው ሰራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ በትኩረት እየተሰራ ነው ሌጀኔራል ደስታ አብቼየመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ሌጀኔራል ደስታ አብቼ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው የምትገኘው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲከናወን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።ሌጀኔራል ደስታ ሠራዊቱ የተሠጠውን ተልኮ ...
### Text: በአሁኑ ሰዓት የወልድያ ከተማ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ከተማሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ተሳታፊና ተባባሪዎች ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 13 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ወልዲያ ዩኒቨርሲቲየዩኒቨርሲቲያችንን ወቅታዊ መረጃ በተመለከተበቅድሚያ ከትናንት ወዲያ ጥቅምት 292012 ዓም ምሽት 500 ስዓት ላይ በወልድያ ዪኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ ግጭቱ የሁለት ተማሪዎ...
### Text: ደብረብርሃን ድጋፍ ይዘው መምጣት የሚፈልጉ ክልከላው አይመለከታቸውም ይህንን አውቀው ወደ ከተማው መምጣት ይችላሉ አቶ ደስታ አንዳርጌ በደብረ ብርሃን ከተማ የቀን እንቅስቃሴ ገደብ አስመልክቶ ተጨማሪ መልዕክት ከከተማው ከንቲባ ተላልፋል።የደብረ ብርሃን ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ የአሸባሪው ቡድን አባላት ከተፈናቃዮች ጋር ተመሳስለው ወደ ከተማው በመግባት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛትም ሆነ በሌሎች መንገዶች የከተማውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዳያውኩ እንዲሁም ለተፈና...
### Text: ሰሞኑን በሲዳማ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች እና ከተሞች በተከሰተው ግጭት ሀኪም ቤት ሳይደርሱ በየአካባቢው የተቀበሩትን ሳይጨምር 53 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 54 ሰዎች ደግሞ መጎዳታቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አረጋገጠ። በወቅቱ ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘም እስካሁን 935 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥራ ማዋሉን የሲዳማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።የመምሪያው ዋና አዛዥ ምክትል ኮማንደር ዳኛው ደምሴ ዛሬ በተለይ ለጀርመን ራድዮ እንደገለፁት የግጭቱ መነሻ ሐምሌ 11 ቀን 2011ዓም በሐዋሳ ከተማ...
### Text: በባሌ ሮቤ የሰላም ኮንፍረንስ በመካሄድ ላይ ነው በባሌ ሮቤ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች፣ የሃይማኖት አባቶች የሮቤ ነዋሪዎች ከፌዴራልና ከክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ጋር የሰላም ኮንፍረንስ በማካሄድ ላይ ናቸው፡፡የገቢዎች ሚኒስቴር ወሮ አዳነች ሀቤቤ እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምርዕሰ መስተዳዳር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ ዶር ግርማ አመንቴ መድረኩን የእየመሩ ነው፡፡ባሌ የምትታወቀው በሃይማኖትና በብሄር መቻቻል መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሯ ባሳለፍ...
### Text: የሾፌሮችን እንቅስቃሴ ከስጋት ነጻ ለመድረግ ከኦሮሚያ ክልል ሃላፊዎች ጋር እየተነጋገርን ነው ኮማንደር ቢምረው አሰፋበአሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰውን ግድያ እና የንብረት ዘረፋ መንግስት ባለማስቆሙ ለስራቸው አስቸጋሪ እንደሆነባቸው በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ከተማ የሚገኙ እና ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ አሽከርካሪዎች ለወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ተናግረዋል።በኦሮሚያ ክልል በተለይ ደግሞ አሊ ዶሮ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተደጋጋሚ በታጠቁ ሀይሎች በሾፌሮች ላይ ግድያና የንብረት ዘረፋ እየተ...
### Text: አሐዱ ባንክ ሐምሌ 9 ቀን 2014 ዓም ሥራውን በይፋ ይጀምራል።ይህ አስመልክቶ ባንኩ ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አንተነህ ሰብስቤ 10 ሺህ በሚደርሱ ባለአክሲዮኖችንና በ564 ሚሊዮን የተከፈለ ካፒታል እና በ702 ሚሊዮን በተፈረመ ካፒታል ተዋቅሯል ብለዋል።ሀላፊው እስከ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓም የቅርንጫፎቹን ብዛት 50 እደሚያደርስም ተናግረዋል።ባንኩ ️ ከሚያቀርበው ብድር እስከ 15 በመቶ የሚሆውን ለስራ ፈጣሪዎች እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ማቅ...
### Text: ምስራቅ ሀረርጌ️በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ቆላማ ወረዳዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮች የተገዙት 318 የውሃ መሳቢያ ጀኔሬተር ፓምፖችን በመመዝበር ለግል ጥቅሙ ያዋለው ግለሰብ በ11 ዓመት ጽኑ እስራትና በ15 ሺህ ብር ተቀጣ ።የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የመንግሥት ኮሙኬሽን ጉዳዮች ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ስዩም ደገፋ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ግርማደረሰ ፍላቴ የተባለው ወንጀለኛ0 ቅጣቱ የተጣለው በድርቅ የተጎዱ አርሶ አደሮችን ለመታደግ0 በ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የተገዙትን ፓ...
### Text: የፍርድ ቤት ውሳኔ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶጃዋር የክስ መዝገብ የተከሰሱ ሰዎች የሕክምና ጉዳይን በማስመልከት ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ በማድረግ ተከሳሾች በግል ሐኪም እንዲታከሙ ፈቀደ።ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት እነ አቶ ጃዋር መሐመድ በመረጡት የግል ሃኪም እና የግል ሕክምና ጣቢያ እንዲታከሙ መፍቀዱን በመቃወም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብሎ ነበር።ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቤቱታን ውድቅ ...
### Text: ከሰሞኑን የተለያዩ የውጭ ሀገራት ሚዲያዎች ተናበው ሚሰሩ በሚመስል መልኩ ኢትዮጵያን የተመለከተ በርካታ ዘገባዎችን አውጥተዋል።የሚዲያ ተቋማቱ ድርጊት ኢትዮጵያውያንን ክፉኛ አስቆጥቷል።ለአብነት በአራት ቀናት ብቻ ፣ ፣ አልጀዚራ ፣ ፍራንስ 24 ፣ አሶሼትድ ፕሬስ በድምሩ 72 ዜናዎችን በኢትዮጵያ ጉዳይ አውጥተዋል ይህን ቁጥራዊ መረጃ ያጋራው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ የሚሰራው ጋዜጠኛ ሰለሞን ካሳ ነውከ72ቱ ዜናዎች 21ዱን ፣ 13ቱን ፣ 11ዱን አልጀዚራ ፣ 19ኙን ፍራንስ 24 እና...
### Text: አቶ ጌታቸው ከሀገር ወጡ️ይህ የአንጋፋው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ዘገባ ነውሰበር ዜናከአዲስ አበባ ለአዋዜ የደረሰው ትኩስ ዜና። የቀድሞው ተፈሪ የብሄራዊ ስለላና ደህንነት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ ከኢትዮጵያ ጠፍተው ሱዳን መግባታቸው በይፋ ተረጋገጠ ። አንድ ከፍተኛ ውስጥ አዋቂ ምንጭ ምሽቱን ለአዋዜ እንደተናገሩት ከሆነ ፌደራል መንግስቱ በህግ ይፈልጋቸው የነበሩ ባለስልጣን ናቸው ጌታቸው አሰፋ።ማዕከላዊ መንግስቱ በይፋ በህግ ሊጠይቃቸው እና ሊፋረዳቸ...
### Text: ማሳሰቢያውድ የአጠቃላይ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት የ10ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች ከግንቦት22242010 ዓም የኢትዮጵያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት የ10ኛ ክፍል ፈተና ለ1200676 ተማሪዎች እንዲሁም ከግንቦት 27302010 ዓም የኢትዮጵያ ዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና የ12 ክፍል ፈተና 284312 ተማሪዎች መሰጠቱ ይታወሳል፡፡የፈተናውን መሰጠት ተከትሎም ወደ እርማት ስራው በመግባት ከምንጊዜውም በፈጠነ መልኩ የ12ኛ ክፍል ውጤት በ...
### Text: ጎረቤታችን ሶማሊያ ነገ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች።ይህን ተከትሎ የሶማሊያ ፖሊስ ምርጫ እስኪጠናቀቅ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ በጸጥታ ሥጋት ሳቢያ ከአስቸኳይ አገልግሎቶች ውጪ ሁሉንም ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች የሚያግድ የሰዓት ዕላፊ ተግባራዊ አድርጓል።የታወጀው ሰዓት እላፊ ከዛሬ ምሽት 3 ሰዓት እስከ ሰኞ ጧት ድረስ የሚቆይ ነው ተብሏል።ነገ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የሚመርጠው የታችኛው እና የላይኛው ምክር ቤቶች በጋራ በሚሰጡት ድምጽ ነው። ጎሳን መሰረት ባደረገው በዚህ ለ6ኛ ጊዜ በሚካሄድ...
### Text: አንድነት ፓርክ በየሳምንቱ ሰኞ ለጎብኝዎች ዝግ እንደሚሆን ተገለፀ በአንድነት ፓርክ ያሉ ቅርሶችንና፣ ንብረቶችን በተገቢው ሁኔታ ለመጠበቅ ሲባል ፓርኩ በሳምንት አንድ ቀን ሰኞ ለጎብኚዎች ዝግ እንደሚሆን ተገለፀ። በቤተ መንግስት ቅጥር ግቢ ውስጥ የተሰራውን የአንድነትፓርክ ከመስከረም 2012 ዓም ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት መሆኑ ይታወሳል።ለአገልግሎት ክፍት ከሆነበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ከ20 እስከ 25 ሺህ የሚደርሱ ጎብኚዎች ፓርኩን መጎብኘታቸውን ከአንድነት ፓርክ የተገኘው መረጃ ያ...
### Text: የታገቱት ተማሪዎች እስካሁን ድምጻቸው አልተሰማም ህዳር 2021 የታገቱበት ቀን። ህዳር 24 አምልጣ የወጣችው ተማሪ መታገታቸውን የተናገረችበት። ታህሳስ 27 የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በጋዜጣዊ መግለጫቸው የታገቱ ተማሪዎች እንዳሉ ቁጥራቸውም እስከ 4 እንደሚደርስ የገለፁበት ቀን። ጥር 2 የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬተርያት ኃላፊ ክቡር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ስለታገቱት ተማሪዎች በሰጡት መግለጫ 21 ተማሪዎች መለቀቃቸውንና 6 ተማሪዎች ታግተው...
### Text: ነሃሴ 242012 ዓምየኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች 1 በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 783 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 53 ሰዎች በኮቪድ19 መያቸው ተረጋግጧል በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 4067 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 119 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 21 ከምዕራብ አርሲ 10 ከአሰላ ከተማ 10 ከቢሾፍቱ ከተማ 9 ከምዕራብ ሸዋ 8 ከጅማ ዞን 8 ከነቀምቴ ከተማ ይገኙበታል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል...
### Text: የቀጠለየቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት 1 ትምህርት ቤት2 የህፃናት ማቆያ3 ክሊኒክ4 መኖሪያ ህንፃ ፓርኩ የሚያካትታቸው የኢንዱስትሪ ዓይነቶች ፓርኩ በዋናነት የሚያካትታቸው ኢንዱስትሪ አይነቶች የግብርና ምርትን በግብዓትነት የሚጠቀሙና የሚያቀነባብሩ፣ ምርታቸውን በጋራ ወይም በተናጠል ወደ ውጭ የሚልኩ፣ ለግብርናው ምርት መዘመን መሰረት የሚሆኑ፣ የተሻሻለ ቴክኖሎጅ የሚያስተዋውቁ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ አስተዋጽኦ ያላቸውና ሌሎችም ይገኙበታል። በፓርኩ እ...
### Text: ባቲ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በባቲ፣ ከሚሴና ሮቢት ከተሞች ብሔርን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው የትግራይ ተወላጆች ለቢቢሲ ተናግረዋል።ነዋሪዎች ብሄርን መሰረት ያደረገ ነው ባሉት ጥቃት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን አስታውቀዋል።ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ድጋፍ ሰልፍ ጋር ተያይዞ በደረሰው በዚህ ጥቃት ቤቶች መቃጠላቸውንንና ዝርፊያ መፈፀሙንም ጨምረው ገልፀዋል።ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች በደሴና በመቀሌ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደ...
### Text: የህዳሴው ግድብ️በኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የተለዩ ክፍተቶችን በማስተካከልበፈረንጆቹ 2022 እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ።በዛሬው ዕለት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ ውይይት እየተካሄደ ነው።ጥልቅ ጥናትና ምርምር ስራ ሳይከናወንለት ግንባታው በመጀመሩ ምክንያት ግንባታ ጊዜው ሊጓተት እንደቻለ የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።ታላቁ የኢትዮዽያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ያስከተለው ጉዳት ሀገሪቷ በየዓመቱ 800 ሚሊየን ዶላር እንድታጣ አድ...
### Text: በአዲሱ የትምህርት ሥርዓት የሚሰጡ ኮርሶች ተለዩ በአዲሱ ትምህርት ሥርዓት ይቀራልበአዲሱ የትምህርት ሥርዓት ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመሪያ ዓመት የሚሰጡ 18 የትምህርት ዓይነቶች ኮርሶች ተለዩ፡፡ በአዲሱ ትምህር ስርዓት ወይንም ኤፍ የሚባል ውጤት መፋቅ ይቀራል ተብሏል፡፡የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ኤባ ሚጀና የሥርዓተ ትምህርት ማዕቀፍ፣ ኮርስ ካታሎግ፣ የምዘና ሥርዓትና የሙያ መስክ ፕሮግራም ድልደላ አስመልክቶ እስካሁን ያለውን ተሞክሮ እና ቀጣይ ...
### Text: በአፋር ክልል ፣ አብአላ ከተማ በሚሰነዘር የከባድ መሳሪያ ድብደባ የከተማው ነዋሪ ከቄዬው እየተሰደደ መሆኑን የከተማው ከንቲባ ተናገሩ።ከንቲባው ይህን የተገሩት ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ነው።ከመቐለ ከተማ 40 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኘው የአፋር የንግድ ከተማ አብአላ ከንቲባ አቶ ጣሂር ሀሰን ህወሓት ተቆጣጥሯቸው ከነበሩት የአፋር እና አማራ ክልሎች እንዲወጣ ከተደረገ በኃላ አብአላ ላይ ተደጋጋሚ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።የከተማው ከንቲባ አሁንም ድረስ አላቋረጠም ንፁሃን መደብደብ በከባድ...
### Text: የ12ኛ ክፍል ፈተና ወረቀት እስከ አርብ ድረስ ተጓጉዞ ይጠናቀቃል።የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከየካቲት 29 ቀን 2013 ጀምሮ የሚሰጠዉ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወረቀት በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እስከ መጪዉ አርብ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓም ድረስ ተጓጉዞ እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ።የፈተናዎች ኤጀንሲ ከኢትዮጲያ አየር መንገድ ጋር ባደረገዉ ስምምነት መሰረት ፈተናዎቹ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እየተጓጓዙ መሆናቸዉን የኤጀንሲዉ ዋና ዳይሬክተር ዶር ዲላ...
### Text: ልዩ ሎተሪ ወጣበጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የልዩ ሎተሪ ህዳር 282011 ዓም በብሔራዊ ሎተሪ ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል።1ኛ 7000000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 12993262ኛ 3000000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር13866793ኛ 2000000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 05554544ኛ 1000000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 0691566...
### Text: ዘጠኝ አመታትን ያስቆጠረው ካለፉት አመታት በተጠናከርረ ሁኔታ እንደገና ተመልሷል በትልልቅ የኢትዮጲያን በአል ላይ በአዲስ አመት፣በገና እና ፋሲካ የሚደረገው ወጣት በጎ ፍቃደኞችን በማስተባበር ከ 1000 በላይ ለሆኑ ጎዳና ተዳዳሪ ልጆች ፣ ወጣቶች እና አዛውንቶችን ተደራሽ ያደረገ ነውይሄ መልካም ተግባር በዋናነት የበአሉ እለት የምሳ ፕሮግራም በማድረግ በበአሉ ቀን ምንም ሳይሰማቸው ደስተኛ ሆነው እንደማንኛውም የኢትዮጲያ ህብረተሰብ በአሉን እያከበርን እንድንውል እና ከዛም...
### Text: የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርሜሽን ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዘውዱ እምሩ የተናገሩትሙሉ በሙሉ የታገዱት አራት ተማሪዎችን ጨምሮ ትምህርት እንዲስተጓጎል ያደረጉ 21 ተማሪዎች ከአንድ ዓመት እገዳ ጀምሮ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።ሌሎች ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸውን አካላትም በመለየትና በማጣራት በቀጣይ ተመሳሳይ እርምጃ ይወሰዳል።የዩኒቨርስቲ ምሁራን ከመማር ማስተማር ስራው ጎን ለጎን ተማሪዎችን በስነ ምግባር በማነጽ ችግር ፈቺ ሆነው እንዲወጡ ማድረግ ይገባቸዋል።ባለፉት...
### Text: ችሎት እነ አቶ ስብሃት ነጋ ጉዳያችን በትግራይ ክልል ፍርድ ቤት ይታይልን ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ፡፡ይህን አቤቱታ ያቀረቡት ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው።የጠቅላይ አቃቤ ህግ ቡድን በበኩላቸው የፌዴራል መንግስትን ስልጣን ለመጣል በሚል የሽብር አዋጁን በመተላለፍ በመላው ሀገሪቱ የተፈጸመ ወንጀል መሆኑን በመጥቀስ ተጠርጣሪዎቹ መቀሌ ሆነው በሰጡት ትዕዛዝ ባህርዳር እና ጎንደርን በሮኬት ማስደብደባቸው አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።በተጨማሪም ተከሳሾቹ ስልጣን ተከፋፍ...
### Text: የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስርቆት በአፋር ክልል ውስጥ እየተስፋፋ የመጣውን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስርቆት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በጋራ እንዲከላከል ጥሪ ቀረበ።የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በክልሉ እያደገ የመጣውን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ለማሟላት በከፍተኛ የውጭ ማንዛሬ በማስገባት የማስፋፊያ የመልሶ ግንባታ እና አዳዲስ ከተሞች ላይ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ በማከናወን የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን በማስፋት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።ነገር ግን በአንዳድ የክልሉ ከተሞች በተ...
### Text: ወለጋ ዩኒቨርሲቲ️የወለጋ ዩኒቨርሲቲ በፀጥታ ችግር የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ የእረፍት ቀናት ጨምሮ እየሰራ መሆኑን ገለጸ፡፡በጸጥታ ችግር ምክንያት የባከነ የትምህርት ጊዜን በማካካስ የመጀመሪያውን መንፈቅ ዓመት በስኬት ለማጠናቀቅ የበኩላቸውን እየተወጡ መሆናቸውን የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና መምህራን ለኢዜአ ገልጸዋል።አሁን አንጻራዊ ሰላም በመስፈኑ ተቋሙ ያመቻቸላቸውን የትምህርት ማራዘሚያ ጊዜ በመጠቀም የባከነውን ጊዜ ለማካካስ ከመምህራን ጋር እየሰሩ እ...
### Text: የጥላቻንግግር የጀርመን ባለስልጣናት የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ የሆነው ፌስቡክ የሀገሪቱን የጥላቻ ንግግር ህግ በመጣሱ በ2 ነጥብ 3 ሚሊየን የአሜሪካ እንዲቀጣ ውሳኔ ማሳለፋቸውን አስታውቀዋል።ባለስልጣናቱ በፌስቡክ ላይ ቅጣቱን በትናንትናው እለት ያሳለፉ ሲሆን ቅጣቱ የተላለፈውም ህጉን የጣሱ ይዘቶችን በፌስቡክ ገፅ ላይ ሲሰራጩ ምንም አይነት የማስተካከያ እርምጃ ባለመውሰዱ ነው ተብሏል። የጀርመን የፌደራል ፍትህ ቢሮ ባወጣው መግለጫ ፌስቡክ የጥላቻ ንግግር ህግ የጣሱ ይዘቶ...
### Text: ነገ በኢትዮጵያአዲስ አበባ ምን አለ በነገው ዕለት ብሔራዊ ክብር በሕብር በሚል የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም በያሉበት ሆነው ጽምጻቸውን የሚያሰሙበት መርሃግብር ይካሄዳል ተብሏል።ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሃገራትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ በሚል መሪ ሐሳብ በያሉበት ሆነው ለአንድ ሰዓት መልዕክታቸውን የሚያስተላልፉበት መርሃግብር ነው።ማነው ያዘገጀው መርሃግብሩ ያዘጋጁት ከማህበረሰብ አንቂዎች፣ አርቲስቶች፣ ሲቪክ ማህበራትና ታዋቂ ግለሰቦች...
### Text: የዋጋ ንረቱ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ የኑሮ ውድነቱ ከፍ እያለ የሰዎችን ኑሮ በእጅግ እየተፈታተነው ነው።በተለይ ዝቅተኛ ደሞዝ የሚያገኘ ሰራተኞች ኑሮ ለመግፋት ፈተና እየሆነባቸው ነው በየዕለቱ ሚጨምረው የዋጋ ንረት የኑሮውን ጫና መቋቋም ከማይቻልበት ደረጃ እየደረሰ ነው።ቤት ኪራይ፣ ምግብ የልጆች ትቤት ክፍያ፣ የቀን ወጪ ሌሎችም ወጪዎች ሲጨምሩ እንጂ ሲቀንሱ አይታይም የሚገኘው ደሞዝ እዛው ነው።ከቅርብ ጊዜ በኃላ ደግሞ በኢትዮጵያ ሰሜናዊው ክፍል የተፈጠረውን ጦርነት እንደመልካ...
### Text: ሀዋሳ ከተማ️ሀዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት ባለፉት 2 ወራት የተገነቡ ህገ ወጥ ቤቶች ላይ መንግስት እርምጃ ወስዷል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ህዝቡን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ለመውሰድ አንዳንድ አካላት በማህበራዊ ሚዲያዎች በመጠቀም ትክክል ያልሆነ መረጃ እያሰራጩ እንደሚገኝ ተደርሶበታል። ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ቤቶች ፈርሰዋል ወደ ተባለበት ቦታ ደውዬ ከአካባቢውን ነዋሪ ጋር ቆይታ አድርጌ ነበር ነዋሪው በሰጠኝ መረጃ ዛሬ የተወሰደው እርምጃ ምንም አይነት ብሄርን መሰረት ያደረገ እንዳ...
### Text: በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ፍሬህይወት ቁጥር አንድ ትምህርት ቤት ዛሬ ኅዳር 172012 ጠዋት ላይ 25 ተማሪዎች እና 5 አስተማሪዎች ላይ በተፈጠረው የጤና ዕክል ምክንያት ወደ ጥቁር አንበሳ እና ዘውዲቱ ሆስፒታሎች የተወሰዱ ተማሪዎች ከሁለት ተማሪዎች በስተቀር ቀሪዎቹ ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሳቸውን የትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር ፍርህይወት አዳል ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስታውቀዋል። የ5እና የ7ኛ ክፍል የሚማሩ በተማሪዎቹ እና በአስተማሪዎቹ ላይ የማሳል፣ ማስመለስ፣ ብርድብ...
### Text: ዶር ደብረፅዮን ገሚካኤልለሀገራችን እና ለራሳችን ስለማይጠቅመን ብዙ ተሸክመን ነው ያለነው። ነገሮቹ ይቀየሩና ይስተካከላሉ ይሆናል በሚል። እኛ በክልላችን ብቻ አይደለም ሃላፊነት ወስደን እየሰራን ያለነው በሀገር ደረጃ ጉዳት እንዳይደርስ በሚል ተጠንቅቀን እየሰራን ነው የምንገኘው።እንደ ትግራይ የታገልነው ለእኩልነት ነው እንጂ በሀገር ላይ የበላይነት ለማግኘት አይደለም ወደዛም አልሄድንም። አሁን ላይ ግን በእኩልነት ላይ የተመሰረተው አንድነት የሚያፈርስ እና ህብረ ብሄራዊ የፌደራሊዝም ስርዓ...
### Text: የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደራጅ ኮሚቴ ከአካባቢው ተወላጅ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሀዋሳ ውይይት እያካሄደ ነውበመድረኩ የክልሉን የምስረታ አፈጻጸም አስመልክቶ የተከናወኑ ተግባራትን ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ምክክር እየተደረገ ይገኛልአዲሱን ክልል በታለመለት ጊዜ አደራጅቶ ወደ ስራ ለማስገባት ልዩ ልዩ ግብረ ሀይል መቋቋሙ በመድረኩ ተገልጿልአዲስ የሚመሰረተው ክልል ከነባሩ ክልል ያለውን ሀብት አስመልክቶ የሀብት ክፍፍል ግብረ ሀይል መቋቋሙ ይፋ ሆኗልየህገ መ...
### Text: አምነስቲኢንተርናሽናል የፕሪቶሪያ የ ሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ የ ኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ወሲባዊ ባርነት ፣ ግድያዎችን እና ሌሎች ከባድ ጥሰቶች መፈጸማቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አዲስ ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርጓል።ሪፖርቱ ምን ይላል ከሰላም ስምምነቱ በኃላ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ምድር ወሲባዊ ባርነት፣ ግድያ፣ ከባድ ጥሰቶችን ፈፅመዋል። የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት መድፈር፣ ሴቶችን ለወራት ለወሲባዊ ባርነት መዳረግ፣ የዘፈቀደ ግድያ፣ ዘረፋዎችን እየፈጸሙም እን...
### Text: በጋምቤላ ክልል 52 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች እና 10 ኪሎ ግራም ሐሺሽ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በተጨማሪም ከአንድ ሺህ በላይ የብሬን መትረየስና ክላሽንኮቭ ጥይቶች ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር ተይዘዋል። የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ቱት ኮር እንደገለጹት የጦር መሳሪያዎቹና ሐሺሹ በቁጥጥር ሥር የዋለው ከሕዝብ በደረሰ ጥቆማና በኬላዎች በተደረገ ፍተሻ ነው። የጦር መሣሪዎቹና ሐሺሹን ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከሚያዚያ 6 እስከ 9፣ 201...
### Text: የአፋር ክልል ተፈናቃዮች ከ250 ሺህ በልጠዋል።የአፋር ክልል ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አህመድ ካሎይታ ህወሓት በሁለት ዙር ባካሄደው ወረራ የኢትዮጵያ የወጪ እና ገቢ ንግድ የሚሳለጥበትን ሚሌን ለመያዛ እና ለመዝጋት አስቦ ነበር ያ ግን ሳይሳካ ቀርቷል አሁን ደግሞ በሶስተኛ ዙር ወራር በሰርዶ በኩል ያሰበውን ለማሳካት ተነስቷል ብለዋል።አቶ አህመድ ክልሉ ከዚህ ቀደም ቡድኑ ባካሄደው ወረራ የተፈናቀለውን ህዝብ ለማቋቋም እየተሰራ ባለበት ሁኔታ ዳግም ለሶስተኛ ዙር ወረራ ተፈፅሞብናል...
### Text: ፍትሕን በገንዘብ ያልሸጣት ምስጉን ዳኛበምእራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ነሐሴ 10 ቀን 2014 ዓም ከምሽቱ 140 ሰዓት ላይ አንዲት ህፃንን አስገድዶ በመድፈሩ ምክንያት ተከሳሽ ተይዞ ጉዳዩ በህግ ይታያል።በዚህን ጊዜ የተከሳሽ ወንድምና ጓደኛ መዝገቡን የሚያየውን ዳኛ በከተማው በሚገኝ ፅናት ሆቴል ይቀጥሩታል። ኃሳባቸውም ለዳኛው 10 ሺህ ብር ጉቦ በመስጠት ተከሳሽ ነጻ እንዲወጣ ማድረግ ነበር።ዳኛውም ቀጠሮዎን አክብሮ ከቦታው ይደርሳል የተከሳሹ ተባባሪዎችም ገንዘቡን አ...
### Text: ተጠርጣሪዎቹ በዋስ እዲወጡ ተፈቀደ️ፍርድ ቤቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በፈጸሙ ተጠርጣሪዎች ላይ በምስክርነት የቀረቡ ግለሰቦችን ፎቶ በማንሳት በማህበራዊ ድረ ገጽ ሲለጥፉ በቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች የጠየቁትን የዋስትና ጥያቄ ተቀበለ። ተጠርጣሪዎቹ ሃጎስ ግርማይ እና ተወልደ ውበት የተባሉ ግለሰቦች ሲሆኑ በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት ለሁለተኛ ጊዜ ቀርበዋል።መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በምርመራ ላ...
### Text: የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮቸ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ፡፡የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ኮሚቴ የቅዱስ ጊዮርጊስን የሜዳ ተጠቃሚነት ለማሳጣት ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ሊያደርገው የነበረን ጨዋታ በዝግ ወይም አዳማ0ተጫወቱ በማለት ሁለት ጊዜ እንዲቋረጥ አድርጎል ብሏል፡፡ይህን ጨዋታ ከዚህ በፊት የተቋረጡ የሌሎች ክለቦች...
### Text: የወንጀለኛ መቅጫ ስነስርዓት ህግ የማሻሻያ ስራ ተጠናቆ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ተመርቷል ከ50 ዓመት በላይ በስራ ላይ የቆየው የወንጀለኛ መቅጫ ስነስርዓት ህግ የማስረጃ ጉዳዮችን እንዲያካትት እና በ1996 ዓም ከወጣው የወንጀል ህግ ጋር ስያሜው እንዲጣጣም ተደርጎ ሲሻሻል የነበረው ረቂቅ ተጠናቆ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የህግ ጥናት ማርቀቅና ማስረጽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በላይሁን ይርጋ ገልፀዋል፡፡አቶ በላይሁን አያይዘውም ረቂቁ «የ...
### Text: ወፍሪ ሓርነትበመንግስት በኩል እንዲለቀቁ ከተወሰነላቸው 14 የትግራይ የፖለቲካ እስረኞች ውስጥ እስካሁን የተለቀቁት 11 ብቻ መሆናቸውን ወፍሪ ሀርነት አስታወቀ።ወፍሪ ሀርነት በፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩ የትግራይ አስረኞችን መብት ለማስከበር የተቋቋመ ኮሚቴ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ ዛሬ ረፋድ በአዲስ አበባ መግለጫ ሰጥቷል።የመግለጫው ዋና ዋና ነጥቦች መንግስት የካቲት 16 ቀን 2012 ምሽት ላይ እንዲፈቱ ውሳኔ የተላለፈላቸው 14 ሲሆኑ የተለቀቁት 11 ብቻ ናቸው። የተፈቱትም ቢሆን በተንጠ...
### Text: ችሎትበፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት እነ አቶ እስክንድር ነጋ በጠየቁት የዋስትና መብት እና የዐቃቤ ሕግ ምላሽ ላይ መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለመስከረም 12 ተለዋጭ ቀጠሮ ያዘ።አቶ እስክንድርን ጨምሮ 7 ሰዎች የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ እና በሽብር ወንጀል በዚህ ችሎት ክስ እንደተመሰረተባቸው ይታወሳል።ይህን ተከትሎም በአካል ካልተገኙት 6ኛ እና 7ኛ ተከሳሾች በስተቀር ሌሎቹ አምስቱ ተከሳሾች በአካል በችሎት ተገኝተው ክሱ ተነቦላ...
### Text: የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር ዐቢይ አህመድ ለሱዳን ጠሚ ዶር አብደላ ሃምዶክ ጥሪ ምላሽ ሰጥተዋል ጠሚ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ለሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አብደላ ሃምዶክ በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ ለጻፉት ደብዳቤ ምላሽ ሰጥተዋል።ኢትዮጵያም የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር እና ለዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ ከግድቡ ጋር በተያያዘ ባሉ መጓተቶች ላይ ስብሰባ እንዲጠራ ሃሳብ አቅርባለች፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እስካሁን በግድቡ ዙሪያ የተካሄደው ውይይት እን...
### Text: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የግንቦት 192013 ክንውን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡ ሲሆን በመግለጫቸው ተከታዮቹ ነጥቦች ተነስተዋል በትናንትናው ዕለት ውሳኔ የሰጠባቸውን 2 አጀንዳዎች ቃለ ጉባዔ ቀርቧል፡፡ በዚህም የቅዱስነታቸውን የመክፈቻ ንግግር ቅዱስ ሲኖዶስ አጽድቆታል ፡፡ ሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክቶ በሀገሪቱ በሚታዩት ወቅታዊ ችግሮች የፖለቲ...
### Text: ያለ አግባብ እንግልት እየደረሰብን ነው የትግራይ ተወላጆችበአዲስ አበባ ከተማ ጎፋ መብራት ሃይል አካባቢ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ያለ አግባብ እንግልት እየደረሰብን ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡በጎፋ መብራት ሃይል የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እንደተናገሩት በአካባቢው በሚደረጉ ፍተሻዎች በማንነታችን የትግራይ ተወላጆች በመሆናችን እየታሰርን እና ቤቶቻችን እየታሸጉ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንዳሉት ለፍተሻ የሚመጡ የፀጥታ አካላት ምንም አይነት የመፈተሸ ፍቃድ ሳይዙ በተመረ...
### Text: የነዳጅ ማዕቀብ ውጤቱ እጅግ የከፋ ይሆናል ዳፋውም ለዓለም ይተርፋል የሩስያ ምክትል ጠሚ አሌክሳንደር ኖቫክ አሜሪካ በ ሩሲያነዳጅ ላይ ማዕቀብ የመጣል ውሳኔ ካሳለፈች ሩሲያ ለአውሮጳ የምታቀብለውን የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦቷን እንደምታቋርጥ ዝታለች።የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒትር አሌክሳንደር ኖቫክ የሞስኮን ነዳጅ ማቀብ ውጤቱ እጅግ የከፋ ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ዳፋውም ለዓለም ይተርፋል ብለዋል፡፡ሚኒስትሩ በዚህ ማስጠንቀቂያቸው ሩሲያ ነዳጅ ላይ ማዕቀብ ከተጣለ ምናልባትም ...
### Text: የገቢዎች ሚኒስቴርበያዝነው ሳምንት በተለያዩ የመቆጣጠሪያ ጣቢዎች በድምሩ 4480305 ብር የሚገመት የኮንትሮባድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ቡሌሆራ የመቆጣሪያ ጣቢያ ላይ 627100 ብር የሚገመት ተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ ቻርጀሮች እና ጀነሬተሮች የሚያካትት የኮንትሮባንድ ዕቃ መጋቢት 92011 ዓም በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ የኮንትሮባንድ ዕቃው በሰሌዳ ቁጥር ኮድ394467 አአ በሆነ ተሸከርካሪ ሲጓጓዝ በኦሮሚያ ፖሊስና በጉምሩክ ሰራተኞች ትብብር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ በምስራቅሀረርጌዞ...
### Text: አፈ ጉባኤዋ ይቅርታ ጠየቁ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋናአፈጉባኤ የምክር ቤቱ አባላት ይቅርታ ያድርግልኝ ሲሉ በይፋ ጠየቁ። ዋና አፈ ጉባኤዋ ወይዘሮ ሄለን ደበበ ዛሬ ረፋድ ላይ የተጀመረውን የክልሉን አምስተኛ ዙር መደበኛ ጉባኤ በንግግር ሲከፍቱ ላለፉት አስራ አንድ ወራት የምክር ቤቱን መደበኛ ጉባኤዎች ባለመጥራቴ የተከበሩ የምክር ቤት አባላት ይቅርታ ያድርጉልኝ ሲሉ ተማፅነዋል።የህዝብ ውክልና ያለው ምክር ቤት በየጊዜው ማከናወን የነበረበትን ስብሰባ አለማድረጉ በየትኛ...
### Text: አጫጭር መረጃዎች በትግራይ ክልል 4ኛው የኮሮና ቫይረስ ሞት ተመዝግቧል ከዚህ በተጨማሪ ባለፉት 24 ሰዓት 60 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 101 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧልከነዚህ መካከል ከባሌ 18፣ ምስራቅ ሸዋ 16፣ ጅማ 6 ፣ ነቀምቴ 9 ሰዎች ይገኙበታል። በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 27 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተረጋግጧል ሁሉም የጅግጅጋ ነዋሪዎች ናቸው። በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ሁለት 2 ሰዎች በቫይረሱ መ...
### Text: ቀጣናውን ለመረበሽ የሚያልሙ ኃይሎች በንፁህ ዜጋ ላይ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እየፈፀሙ ነው አቶ ሰለሞን አልታዬመነሻውን ደብረብርሃን መድረሻውን አጣዬ አድርጎ ሲያሽከረክር የነበረ የታርጋ ቁጥሩ 3 71650 የሆነ የሲኖ ትራክ አሽከርካሪ በጥይት መመታቱን የኤፍራታና ግድም ወረዳ ሪፖርት አደረገ።ወረዳ በአሽከርካሪውን በጥይት ተኩሰው ጉዳት ያደረሱበት ፀረ ሰላም ሃይሎች ናቸው ብሏል።አሽከርካሪው ጉዳት የደረሰበት ወደ አጣዬ በመጓዝ ላይ እያለ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ...
### Text: ትግራይ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የዛፍ አምበጣ መንጋ0የታየ ሲሆን ይኸው መንጋ በዛፍና በደረሱ እህሎች ጉዳት እያደረሰ መሆኑ የክልሉ እርሻና ገጠር ልማት ቢሮ አስታውቋል። የአምበጣ መንጋው ጉዳት ያደረሰባቸው የዞኑ ወረዳዎች ታሕታይ ኣድያቦ ፣ አስገደና ማእኸላይ ኣድያቦ የተባሉ ናቸው። የአንበጣ መንጋው ከመስከረም 22016 ዓም ጀምሮ መታየቱ የገለፀው ቢሮው በ471 ሄክታር መሬት በተካሄደው የኬሚካል መርጨት ስራ 17 በመቶ መከላከል መቻሉ በቢሮው የተባዮች መከላከል ከፍተኛ ባለሙ...
### Text: የኤምሬትስ አየር መንገድ ከጋዜጠኞች ጋር ያደረገው ቆይታ ትላንት በራዲሰን ብሉ ሆቴል የኤምሬትስ አየር መንገድ ከጋዜጠኞች ጋር ባደገው የውይይት መድረክ ላይ አየር መንገዱ በአገልግሎት ዘርፉ በሚያካትታቸውና በቅርብ አገልግሎት መስጠት በጀመረባቸው ስራዎች ላይ በአትዮጲያ የኤምሬትስ ማናጀር በሆኑት አቶ ማኖጅ ናየር በኩል ገለጻ የተሰጠበት ሲሆን ከጋዜጠኞችም ጥያቄዎች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡የኢምሬትስ አየር መንገድ በንጽጽር በአጭር ጊዜ ውስጥ አንጋፋ የሆነ አየር መንገድ ...
### Text: ይፋዊመግለጫ የአልሸባብ የሽብር ቡድን ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ ተደምስሷል የሶማሌ ክልል ፀጥታ ምቤትዛሬ ምሽት የሶማሌ ክልል ፀጥታ ምክር ቤት መግለጫ ሰጥቷል።በመግለጫው ከ4 ቀናት በፊት አቶ በሚባለው ቦታ ወደ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን አልሸባብ የሽብር ቡድን ታጣቂ መግባቱን አመልክቷል።የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ሁልሁል በሚባል ንዑስ ቀበሌ ከተከበቡ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ ተደምስሰዋል ሲል አሳውቋል።የፀጥታ ምቤቱ አልሸባብ በኤልከሬ ወረዳ አልፎ ወደ ኦሮሚያ ክልል ...
### Text: አዲስ አበባ️ከአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በመጡ ወጣቶችና ፒያሳ አካባቢ ባሉ ወጣቶች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት አካባቢው ተረብሾ ውሏል፡፡በተለያዩ አውቶብሶች ፒያሳ መሀል ላይ የተበተኑ ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ወጣቶች ገጀራና ሚስማር የተመታበት እንጨት ይዘው እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን፣ የፒያሳ አካባቢ የማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ፖሊስ ጣቢያን ለመዝረፍ እንቅስቃሴ መደረጉንና ፖሊሶችም በጥይት መበተናቸውን፣ ፖሊስ ለሪፖርተር ገልጿል፡፡የፒያሳ ማኅበ...
### Text: ህዳር 30 የሚዘጉ መንገዶች️በአዲስ አበባ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል ከትራፊክ ፍሰት ነፃ የሆነ ቀን ለማክበር ሚዘጉትመንገዶች ይፋ ሆኑ።ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ ሁለት መንገዶች የተለዩ ሲሆን አንደኛው ከጊዮርጊስ አደባባይ በቸርችል ጎዳናኢትዮ ኩባ ወዳጅነት ፓርክ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከጊዮርጊስ አደባባይበ6ኪሎበ5ኪሎ አድርጎ መድረሻውን ጊዮርጊስ አደባባይ ያደርጋል፡፡የአዲስ አበባ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከአዲስ አበባ ስፖርትና ወጣቶች ፌዴሬሽን ጋር በመሆን በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግ...
### Text: ሀላባ ከተማ ይቅርታ ጠየቀባሳለፍነው እሁድ በ6ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሀላባ ከተማ በሜዳው ኢትዮጵያ መድንን ያስተናገደበት ጨዋታ በ76ኛው ደቂቃ ላይ ከተመልካች በተወረወረ ድንጋይ የመሐል ዳኛው ኤፍሬምደበሌ ላይ ጉዳት በመድረሱ ምክንያት መቋረጡ የሚታወስ ነው። ይህንን አስመልክቶም የሀላባ ከተማ ክለብ ለፌዴሬሽኑ የይቅርታ ደብዳቤ አስገብቷል።የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ አንዋር ሲራጅ ስለ ጉዳዩ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት በተፈጠረው ስርዓት አልበኝነት በጣም እ...
### Text: የአንድ ዓመት ነጻ የኩላሊት ዕጥበት አገልግሎት የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት 20 ለሚደርሱ ህሙማን የአንድ ዓመት ነጻ ዕጥበት አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ነው ለህሙማኑ አገልገሎቱን መስጠት የጀመረው፡፡የኢትዮጵያ መድህን ድርጅትም ለህሙማኑ ለአንድ ዓመት ሙሉ የዕጥበት ክፍያ የሚውል የ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሰጥቷል፡፡ የድርጅቱ የቢዝነስ ልማትና ሪስክ ማኔጅመንት ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ መንግስቱ ...
### Text: የጅማ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ልገሳ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ኑ በጋራ የልጆቻችንን ተስፋ ብሩህ እናድርግ በሚል መሪህ ቃል ከነሃሴ 6 እስከ 102011 ዓም ባደረገዉ የልገሳ ሳምንት የተለገሰዉን የትምህርት ቁሳቁስ ለ13 ትምህርት ቤቶች በዛሬዉ እለት ጳጉሜ 12011 ዓም አስረክቧል፡፡በልገሳዉ ዝግጅት ላይ የዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች፣ አባገዳዎች፣ የከተማ አስተዳደር አካላት፣ የከተማዉ ትምህርት ቢሮ፣ የ13 ትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች፣ የወላጅ ኮሚቴ አባላት እና ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን ለ1014 ተማሪ...
### Text: የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በላከልን ባለ 7 ነጥብ የቋም መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ቆሞ ሰላማዊ ድርድር እንዲቀጥል ጠይቋል።ምክር ቤቱ በሶስተኛ ወገን አማካኝነት ግጭቱን በድርድር ለመፍታት ሲደረግ የነበረውን ቅድመ ዝግጅት በቅርበት ሲከታተል እንደነበረ የገለፀ ሲሆን የድርድር ሂደቱ ተቋርጦ ግጭት መቀስቀሱ እጅጉን እንዳሳሰበው አመልክቷል።ዳግም ግጭት እንዲቀሰቀስ ምክንያት የሆነውን ጥቃት የጀመሩት የህዉሃት ኃይሎች መሆናቸው የገለፀው ምክር...
### Text: እንኳን በጉራየሌለህን አለኝ ሳታውቅ አዋቂነኝ፣እንዳከብርህ ብቻ ውሸት አትንገረኝ።ከሌለህ ነውር አይደል ካለህ ለራስህ ነው፣እኔ የማከብርህ በሰውነትህ ነው።እንኳን በጉራ ደረት ተነፍቶ፣አልቻለውም ሰው አንገቱን ደፍቶ ።ዝቅ እያሉ ነው ተናንሶ ኑሮ፣ላካበደማ አይወን ዘንድሮ። 2ትልቅ ፈጣሪ ነው ትልቅ ለዘላለም፣የሰው ትልቅ የለምየእድሜ ሰረገላ የድሜ ሰረገላሄዶም መቶ አይሞላም 2እኔ ምን አውቃለው ካወክ አሰተምረኝ፣ ንቀቱን ተውና ይሄ ይሄ ነው በለኝ።...
### Text: ሰኔ 15 ቀን በክልልና በፌደራል ደረጃ በተፈጸመው ጥቃት ሳይደናገጡ፣ ክልላቸውንና ዞናቸውን ለማረጋጋትና ሠላም ለማስፈን በላቀ ዝግጁነት ላይ መሆናቸውን በሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ የመቅደላ ብርጌድ የልዩ ኃይል አባላት ተናገሩ።በእዙ ስር የሚገኙ ከ1 ሺ 300 በላይ ልዩ ኃይሉን የሚመሩት ከሻምበል አመራር በላይ የሆኑ መሪዎች ለሁለት ቀናት የሚቆይ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡ አባላቱ እርስ በእርሳቸው በመወያዬትና በመመካከር ችግሮችን በመፍታት በቀጣይ የአማራ ክልል ሕዝብን ካሉ...
### Text: 1 ሺ 442 ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በአደባባይ ይከበራልየኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ በዓልን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ አብሮነቱን እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል።1 ሺህ 442 ኛው የኢድ በዓል በአደባባይ እንደሚከበር ተገልጿል። ባለፈው ዓመት በኮቪድ19 ምክንያት የኢድ አልፈጥር በዓል በመስጊድ እንዲከበር መደረጉን አስታውሰው ዘንድሮ መንግስት እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ...
### Text: ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ሀገር መከላከያ ሰራዊት በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በመከላከያ በኩል ሌጄነራል ባጫ ደበሌ ናቸው መግለጫውን የሰጡት።ምን አሉ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከመቐለ ለቆ በመውጣቱን ገልፀዋል። እንደምንወጣ ከሳምንታት በፊት የነገርናቸው የውጭ ተቋማት ነበሩ ብለዋል። በሁሉም አቅጣጫ ማለትም በሱዳን ፣ ኤርትራ አፋር እና አማራ ወሰን ዝግ መሆኑን ገልፀዋል። የፌዴራል መንግስት ከዚህ በ...
### Text: 262 የክርስትና እምነት ተከታዮችን በመስጊድ እና በቤቱ በመደበቅ ከገዳዮች ለታደጉት ናይጀሪያዊው ኢማም አሜሪካ እውቅና ሰጥታለች፡፡ የ83 አመቱ አዛውንት ኢማም አቡበከር አብዳላሂ የአለምአቀፍ የሃይማኖቶች ነፃነት ሽልማት ያገኙ ሲሆን ከቆጵሮስ፣ሱዳን፣ብራዚልና ኢራቅ የተለያዩ ሽልማቶች አግኝተዋል፡፡ኢማም አቡበከር አብዳላሂ በማዕከላዊ ናይጄሪያ ፕላትዮ ግዛት ልዩ ስሙ ባርኪን ላዲ በተባለው አካባቢ ከገዳዮች ሲሸሹ የነበሩትን ክርስትያኖች ህይወት መታደጋቸው ነው የተገለፀው፡፡ በወቅቱ ክርስቲያ...
### Text: የእኛ ሰላምና እርቅ በየጊዜው እለት እለት ልንፈጽመው የሚገባን ተግባር መሆን አለበት 0ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በዛረው በበዓል ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዛሬው ዕለት የምናከበው በዓለ መስቀል የእግዚአብሔር ሰላምና እርቅ ፍለጋ በብርቱ የተንቀሳቀሰችው ታላቋ ክርስቲያናዊት ንግሥት ዕሌኒ የፈጸመችውን የቅድስና ተግባር እና ያስገኘቸውን ሃይማኖታዊ ስኬ...
### Text: በዛሬው ዕለት የተለያዩ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ12ኛ ጊዜ በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸው 2 ሺህ 93 ተማሪዎችን አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል ከ700 በላይ ሴቶች መሆናቸ ተገልጿል። 12 የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ4ኛ እና በ5ኛ ዙር በተለያዩ የህክምና ዘርፍ ያስተማራቸውን 127 ዶክተሮች አስመርቋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 484 የሕክምና ባለሙያዎችን አስመርቋል...
### Text: በጀርመን ኤርትራዊ ወጣት ላይ በደረሰበት ጥቃት በርካቶች አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን ገለፁ። ከቆዳው ቀለም ጋር ተያይዞ በጥይት በተመታው ኤርትራዊ ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጀርመን ዋችተርስባች ከተማ ለተቃውሞ መውጣቸው ተገለፀ፡፡የጀርመን የአገር ውስጥ ሚድያ እንደገለፀው የ26 አመቱ ኤርትራዊ ወጣት በጥቃቱ ከፍተኛ ጉዳት ቢያጋጥመውም አሁን ላይ እየተሻለው መሆኑ ተገልፅዋል፡፡የፍራንክፈርት ግዛት አቃቤ ህግ ቃል አቀባይ አሌክሳንደር ባድል እንዳሉት የሃገሪቱ ባለስልጣናት...
### Text: የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስ ጽኑ ህሙማንን መቀበል የሚያስችለውን የቅድመ ዝግጅት ስራ እያጠናቀቀ መሆኑን አስታወቀ።ሆስፒታሉ የኮሮና ቫይረስ ድንገት ወደ ሀገር ውስጥ ቢገባ በቫይረሱ የተጠቁ ጽኑ ህሙማንን ተቀብሎ እንዲያስተናግድ በጤና ሚኒስቴር መመረጡ ይታወሳል።በዚህም የተሟላ የህክምና ማሽን እና አምስት የጽኑ ህሙማን ታካሚዎችን ማስተናገድ የሚችል የጽኑ ህሙማን ማገገሚያ ማዕከል ለይቶ ማዘጋጀቱን ዋና ስራ አስፈጻሚው ዶክተር ታምሩ አሰፋ ገልፀዋል።ከዚህ ባለፈ...
### Text: የዶናልድ ትራምፕ የስንብት ንግግር ቢቢሲ የቀረበከ12 ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ተብለው የሚጠሩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው የስንብት ንግግር አድረዋል።ይህ ንግግራቸው የተሰራጨው በዩትዩብ ነው።ለማድረግ ያሰብነውን አድርገናል፣ ከዚያም በላይ ነው ያሳካነው ብለዋል ትራምፕ በንግግራቸው።ከባዱን አውደ ውጊያ ላይ ነበር የተሳተፍኩት፣ ከባድ ፍልሚያ ነው ያደረኩት ምክንያቱም የመረጣችሁኝ ያን እንዳደርግ ስለነበረ ብለዋል ትራምፕ።ትራምፕ በዚህ ንግግራቸው በጆ ባይ...
### Text: ሳይፈቱ 24 ሰአት አለፈ ተመስገን ደሳለኝ፣እስክንድር ነጋ፣አንዷለም አራጌ፣ማህሌት ፋንታሁን፣በፍቃዱ ሀይሉ፣ወይንሸት ሞላ ፣ይድነቃቸው አዲሱ፣ ተፈራ ተስፋዬ፣ አዲሱ ጌታነህ፣ ሰንታየው ቸኮል፣ ዘላለም ወርቃገኘው የራስ ዋስትና ከተሰጣቸው በኃላ ሳይፈቱ 24 ሰአት አለፈ።ሰኞ መጋቢት 242010 ዓም አመሻሹ ላይ በፖሊስ መምሪያው ሀላፊ ተጠርተው የራስ ዋስትና ከተሰጣቸው በኃላ እስካሁን አለረተፈቱም። የራስ ዋስትና ማለት በተፈለጉ ግዜ ሊቀርቡ ካልቀረቡ ግን በሌሉበት ጉዳያቸው እንደሚታይ የሚገልፅ...
### Text: ነሃሴ 222012 ዓምየኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች 1 በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 725 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 34 ሰዎች በኮቪድ19 መያቸው ተረጋግጧል።አጠቃላይ በሱማሌ 1128 በቫይረሱ የተያዙ 23 ሞት 693 ያገገሙ በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 3642 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 255 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 58 ከምዕራብ ሀረርጌ 54 ከምዕራብ አርሲ 23 ከሰሜን ሸዋ 17 ከለገጣፎ ከተማ 16 ከአዳማ...
### Text: በኦሮሚያ ሆሮ ጉድሩ ዞን 27 የጸጥታ ኃይሎች በታጣቂዎች ተገደሉ።የሆሮ ጉድሩ ዞን ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አብዮት በቀለ 27 የጸጥታ ኃይሎች ትናንት ሐሙስ በታጣቂዎች መገደላቸውን ገለፁ።አስተዳዳሪው ከተገደሉት የጸጥታ ኃይሎች በተጨማሪ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።ጸጥታ ኃይሎቹ ላይ ጥቃቱ የተነሰዘረው ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ገደማ ሲሆን ድርጊቱ የተፈጸመው በአካባቢው ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ የ ሸኔ ታጣቂዎችን በማሰስ ላይ ባሉበት ወቅት እንደነበር አቶ አብ...
### Text: እንዲህ ባማረ እና በደመቀ ሁኔታ በመቐለ ዩኒቨርስቲ ምትኩ ሀይሌ አዳራሽ ትላንት ቅዳሜ 17092011 ተመስርቷል፡፡ በቅንድል ዲጂታል መፅሔት ጠንሳሽነት ከሌሎች ተባባሪ አዘጋጆች ጋር በመሆን የተመሰረተ ነው፡፡በዚህ የምስረታ ዝግጅት ላይ ከ2300 በላይ ተማሪዎች፡ አስተማሪዎች እና የጊቢው የአስተዳደር አካላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የመቀሌ ነዋሪዎች ታድመዋል፡፡በዚህ ዝግጅት ላይ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገሂወት ለታዳሚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕ...
### Text: ከኦሮሚያ ክልል በኩል ምን ተባለ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታምሩ ባይሳ ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር 20225900 የተናግሩት አባይ ድልድይ ከመደረሱ በፊት ባለው ኮቲቻ በሚባል አካባቢ ጥቃት የተሰነዘረው ትላንት ማክሰኞ የካቲት 1 ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነው። ጥቃቱን የሰነዘሩት የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው።በጥቃቱ ኮንቲኔየር የጫነ ሎቤድ የጭነት መኪና አሽከርካሪ ተገድሏል።ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም አቅጣጫ በማሽከርከር ላይ በነበረ...
### Text: የሶማሊያው ፕሬዜዳንት በ3 ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ0 ወደ ኤርትራ አቅንተዋል።የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ለ4 ቀን የስራ ጉብኝት ዛሬ ኤርትራ፣0 አስመራ መግባታቸው ታውቋል።የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አስመራ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው የሶማሊያ አቻቸውን ተቀብለዋቸዋል።ፕሬዝዳንት ሙሀሙድ ወደ ፕሬዜዳንትነት የስልጣን መንበር ከመጡ በኃላ ወደ ኤርትራ በስራ ጉብኝት ሲያቀኑ ይህ ሁለተኛቸው ነው። ከሶስት ወር በፊት ነበር ለስራ ጉብኝት ወደ ኤርትራ ሄ...
### Text: ለሚመለከተው ሁሉ️እኛ አመልካቾች በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 03 ቀበሌ 0607 በቤት ቁጥር 737 738 739 741 ልዩ ቦታው ቤላና ፈረንሳይ መገንጠያቀድሞ 11ቀበሌ የአሁኑ የፌዴራል ካምፕ ፌት ለፊት እስከ1983 ዓም ድረስ ስንጠቀምበት የነበረውን የጋራ መጠቀሚያ ሽንት ቤት እና ማዕድ ቤት እንዲሁም መተላለፊያችንን መንገድ በማጥበብ የሬሳ ማውጫ እንኳን በማሳጣት በቦታው የቀድሞ የቤቱ ባለቤቶች በላያችን ላይ ሌላ ቤት ሰርተው እየተጠቀሙበት ይገኛል። የሚገርመው እነዚህ ቤቶች በ ላይ እን...
### Text: ፌደራል ፖሊስ️ባለፉት 6 ወራት በርካታ ሽጉጥ ክላሽ በርካታ ጥይቶችቦንብ እና የቡድን መሳሪያ መትረጊስ በአራቱም አቅጣጫዎች ማለትም በደቡብ ሞያሌ በምስራቅ ቶጎ ውጫሌ በምዕራብ ጋንቤላ ሱዳን አዋሳኝበሰሜን ከሱዳን መተማ እና በቤንሻጉል ጉምዝ አካባቢ ወደ ሃገር ውስጥ እንደሚገባና ቱርክ ሰራሽ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ ይህ ህገ ወጥ መሳሪያም በፌደራል ፖለስ ኮሚሽን የሀገር መከላከያ ሚንስቴር የቢሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት እና ከጉምሩክ ኮሚሽን እንዲሁም ከሰፊው ሰላም ወዳድ ህዝብ ጋር ...
### Text: ኢትዮጵያን ከኤርትራ የሚያገናኘው የየብስ መንገድ በአዲስ ዓመት ይመረቃል ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በየብስ የሚያገናኛትን ግዙፍ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አጠናቃ፣ በመጪው መስከረም 1 ቀን 2012 ዓም እንደምታስመርቅ ተገለጸ፡፡0ባለፈው አመት ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ የተጀመረው የ90 ኪሜትር የመንገድ ግንባታ በአሁኑ ወቅት 90 በመቶ መጠናቀቁን የዘገበው ኤርትሪያን ፕሬስ ቀሪው 10 በመቶ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት0 ውስጥ ይጠናቀቃል ብሏል፡፡0ኤርትራን ከኢትዮጵያ በየብስ እንደሚያገናኝ የተ...
### Text: ኬንያና ሶማሊያን ሲያወዛግብ በቆየው የባሕር ላይ ይዞታ ይገባኛል ጉዳይ ላይ ኔዘርላንድስ ዘ ሔግ የተሰየመው ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍቤት ብይን ሰጠ።በተፈጥሮ ሀብት የታደለ ነው የተባለውን አወዛጋቢ የውቅያኖስ ላይ ግዛትን ሁለቱ አገራት እንዲካፈሉት ጉዳዩን የተመለከቱት ፍርድ ቤት አስር ለአራት በሆነ ድምጽ ውሳኔ ሰጥቷል።የባሕር ላይ ይዞታውን በተመለከተ ኬንያ በትይዩ ያለውን ድንበር ከሶማሊያ ጋር ከስምምነት ላይ መድረሷን ያቀረበችውን መከራከሪያ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል።በ...
### Text: የዳዋ ዞን ነዋሪዎች ያሉበት ሁኔታ በሶማሊ ክልል ዳዋ ዞን የቦረና አጎራባች በተከሰተው ድርቅ የሞቱት የቁም እንስሳት 47215 መድረሳቸውን ከአንድ ሪፖርት መመልከት ችለናል። ሪፖርቱ የተዘጋጀው ከጥቅምት 25 እስከ 29 ቀን 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ በተካሄደ ዳሰሳ ሲሆን ይህም የተመራው በዳዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ፣ በዳዋ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽቤት፣ ከዞኑ የአደጋ ስጋት አስተዳደር እና የዞን መንግስት ቢሮ እና የሰብአዊ እርዳታ አጋሮች ፣ ፣ ፣ ፣ ፣ ፣ ፣ ፣ ፣ እና እን...
### Text: ሳዑዲአረቢያ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በሪያድ የቀስተደመና ቀለም ያላቸውን እቃዎች ከሱቆች እና ከመደብሮች እየሰብሰበ ይገኛል።የሳዑዲ መንግስት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ያስተዋውቃል በሚል የቀስተደመና ቀለም ያላቸውን አሸንጉሊቶች፣ ቲሸርቶች፣ የጸጉር ማስያዣዎች፣ ኮፊያ፣ እና የእርሳስ መያዣወችን ከየመደብሩ እንዲሰበሰቡ እያደረገ ነው።የሀገሪቱ መንግስት ህፃናትን ለመጠበቅ ሲል መርዛማ መልዕክት የያዙ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን የሚያስተዋውቁ ቀለም ያላቸውን እቃዎችን ከሱቅ እና ከመ...
### Text: ዛሬ ላይ ሁሉንም ነገር ማመን ነው ያቃተኝ ከትላንት በስቲያ ምሽት በአዲስ አበባ ሀዋሳ ፈጣን መንገድ ላይ መቂ አካባቢ በታጣቂዎች ተኩስ እህት እና ወንድም መገደላቸው እና ሌሎችም መቁሰላቸውን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከሻሸመኔ ማሳወቃቸው ይታወቃል።ከደቂቃዎች በፊት አንድ የቤተሰባችን አባል ሟቾች አብሮ አደጎቹ እንደሆነ ገልጿል። አብሮ አደጎቼ ናቸው ዛሬ ላይ ሁሉንም ነገር ማመን ነው ያቃተኝ ያለው ይኸው ቤተሰባችን የዚህ አይነት አስደንጋጭ ድርጊቶች ዜጎች በሰላም እና ደህንነታቸው...
### Text: አዲሱ የብር ኖት መሰራጨት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የግል ባንክ ቅርንጫፎች መሰራጨቱ ተገልጿል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት አቶ አቤ ሳኖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብሔራዊ ባንክን በመወከል አዲሱን የብር ኖት ለግል ባንኮች ጭምር በማሰራጨት ላይ ነው። አዲሱን የብር ኖት ማሰራጨት ከተጀመረ ከመስከረም 62013 ዓ ም ጀምሮ አስካሁን ባለው ጊዜ ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የግል ባንክ ቅርንጫፎች ተ...
### Text: ፍቅር እስከ መቃብር️በአምቦ ከተማ ለ70 ዓመታት በትዳር ተሳስረው የቆዩት አጋሮች በአንድ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ዐርፈዋል ፡፡የአቶ ጉርሜሣኢሬንሶና ወይዘሮ ጉዲሴቂጣታ በአምቦ ከተማ ቀበሌ 03 ነዋሪዎች ነበሩ ለሰባት አሥርታት የዘለቀው ትዳራቸው ባለፈው ዓርብ እስኪያበቃ ድረስ፡፡ በዚህ በረጅም የትዳር ቆይታቸው 18 ልጆችን አፍርተዋል በርካታ የልጅ ልጆችንም አይተዋል፡፡አቶ ጉርሜሣ ኢሬንሶ የ101 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ነበሩ። ባለቤታቸው ወይዘሮ ጉዲሴ ቂጣታ ደግሞ በ...
### Text: የሲዳማ ክልል ምስረታና የስልጣን ርክክብ ቀን የሲዳማ ክልል ምስረታ እና የስልጣን ርክክብ ቀንን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በዓሉ በታላቅ ድምቀት ከሚከበርበት ከአዲሱ ኢንተርናሽናል ስታዲየም መነሻውን ያደረገ የስታዲየሙን ዙሪያ እንዲሁም የከተማ ማፅዳት ስራ መጀመሩን አቶ ዘሪሁን ሰለሞን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ገልፀዋል፡፡ የሲዳማ ብሔር እራሱን በራሱ ለማስተዳደር ህዝበ ውሳኔ በማካሄድ በነፃ ፍቃዱ ህገመንግስታዊ መብት መጎናፀፉን ተከትሎ ...