text
stringlengths
707
989
### Text: የጥቆማ መስጫ ስልክ መስመሮችየአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽቤት በከተማው የሚታዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታዎች፣ በህገወጥ መንገድ ታጥሮ የተቀመጡ መሬቶች ፣ ህገወጥ የቀበሌ ቤቶች እና የኮንደሚኒየሞች እንዲሁም በአገልግሎት መስጫ ተቋማት እና የመንግስት መስሪያ ቤት ኃላፊዎች ወይም ሰራተኞች በአጠቃላይ በከተማው ውስጥ የሚከናወኑ ማንኛውንም ህግን ያልተከተሉ ሥራዎች ላይ ህብረተሰቡ ተሳትፎ እንዲያደርግ ይፈልጋል፡፡ ወሪት ፌቨን ተሾመየከንቲባ ፅቤት የፕሬስ ሴክሬታሪ በዚህ ሳምንት ...
### Text: ወሎ ዩኒቨርሲቲደሴ ካምፓስ የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠል ዛሬ ከተማሪ ተወካዮች ጋር ውይይት እንደሚደረግ ተነግሮናል። አብዛኛው ተማሪ ትምህርት ፈላጊ ነው ዛሬ ውይይት ከተደረገ በኃላ ነገ ትምህርት ይጀምራል የሚል ተስፋ አድሮብናል ብሎናል አንድ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ተወካይ። በሌላ በኩል አሁንም ስጋታቸው ሙሉ በሙሉ እንዳተቀረፈ ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ እንደሚፈልጉ መልዕክቶቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ ተማሪዎች ገልፀዋል።በተመሳሳይ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒስቨርሲቲ ዛሬ...
### Text: በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈበትግራይ ደቡባዊ ዞን ራያ አዘቦ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ አራት ሰዎች ወድያውኑ ሲሞቱ በስድስት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።በመምሪያው የትራፊክ አደጋ ደህንነትና አጣሪ ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር አብርሃ ወረደ እንደተናገሩት አደጋው የደረሰው ዛሬ ከንጋቱ 11ሰዓት ከ30 ደቂቃ ላይ በወረዳው ኮርማ በሚባል አከባቢ ነው።የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 ትግ 08801 የሆነ የደረቅ ጭነት አይሱዝ ተሽ...
### Text: አሜሪካ የ2025 አመልካቾችን መቀበል ጀመረች።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመታዊውን የዲይቨርሲቲ ቪዛ ዲቪ ፕሮግራም ግሪን ካርድ ሎተሪ በመባል የሚታወቀውን በአሜሪካ ለመኖር እና ለመስራት ለሚፈልጉ አመልካቾች ዛሬ ክፍት አድርጓል።እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ መርሃ ግብሩ ዛሬ ሩቡዕ ጥቅምት 4 ተጀምሮ ማክሰኞ ህዳር 7 ቀን 2023 ይጠናቀቃል።አሜሪካ አሁን ባለው ፕሮግራም 55000 ለሚደርሱ የውጭ ዜጎች የግሪን ካርድ እድል ትሰጣለች።የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዲቪ...
### Text: የኢትዮጵያ መንግስት ህዝቡን ይቅርታ ጠየቅማምሻውን ለሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ጠሚር ሀይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ በተከሰተው የስኳር እጥረት ምክንያት ለተፈጠረው መጉላላት መንግስት ህዝብን ይቅርታ ይጠይቃል አሉ። እጥረቱ ስኳር በሚመረትባቸው አካባቢዎች ያልተጠበቀ ዝናብ በመጣሉ፣ ወደ ስራ ይግባሉ ተብለው የተጠበቁት አዲስ የስኳር ፋብሪካዎች ወደ ስራ ባለመግባታቸው እና ነባሮቹም በሚፈለገው ደረጃ ባለማምረታቸው የመጣ ነው ብለዋል። አሁን ላይ ስኳር ከውጭ በግዢ የገባ በመሆኑ የተፈ...
### Text: ስምምነት ሊፈራረሙ ነውየአማራና ትግራይ ክልሎች ርዕሳ መስተዳድሮች ስምምነት ሊፈራረሙ ነው፡፡ የአማራና ትግራይ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች በሁለቱ ክልሎች መካከል እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ስምምነት ዛሬ በሂልተን ሆቴል ከደቂቃዎች በኋላ ይፈራማሉ ፡፡ሕዝቡ ችግሩ የአማራና ትግራይ ክልሎች መንግሥታት ነው ማለቱንና በሁለቱ ክልል ሕዝቦች መካከል ችግሮች አለመኖራቸውን የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተናግረዋል፡፡የሁለቱን ክልል መንግሥታት መሪዎች ችግሮች መፍትሔ...
### Text: ክብ ውስተ ደመናበደሴ እና በአንዳንድ የወሎ አካባቢዎች በፀሐይ አካባቢ የታየው ክስተት ግርዶሽ አይደለም ተብሏል፡፡ ክስተቱ የፀሐይ ግርዶሽ ሳይሆን የክብ ቀስተ ደመና መፈጠር ነው ተብሏል፡፡በወሎ ዩኒቨርስቲ የፊዚክስ መምህርና በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የህዋ ሳይንስ የዶክትሬት ተማሪ መምህር ሰይዴ መብሬ ስለክስተቱ ማብራሪያ ሰጥተውበታል፡፡ እንደ መምህሩ ገለጻ ዛሬ ግንቦት 292011 ዓም በደሴና በአንዳንድ የወሎ አካባቢዎች የተፈጠረው ትዕይንት የፀሐይ ግርዶሽ ሳይሆን ክብ ቀስተ ደመና ነው፡፡...
### Text: አዲስአበባ በአዲስ አበባ የነበረው የኢሬቻ በአል አከባበር ባማረ መልኩና በሰላም ተጠናቋል። ይህን አስመልክቶም የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለከተማዋ ነዋሪዎችና ለበአሉ አከባበር አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ የምስጋና መልእክት አስተላልፈዋል።ኢንጂነር ታከለ በሁሉም የከተማዋ ጫፎች የሚገኙ የከተማዋ ነዋሪዎች ያሳዩት ትብብር የሚደነቅና የሚከበር ነው ብለዋል። በአሉን ለማክበር ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡትን በልዩ ፍቅርና ያላቸውን በማቅረብም ጭምር አክብሮታቸውን ስላሳዩም ለከ...
### Text: በኮቪድ19 የተያዙ ሰዎች ከ5000 አለፉባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 4034 የላብራቶሪ ምርመራ 186 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5034 ደርሷል።ቫይረሱ የተገኘባቸው 73 ወንድ እና 113 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ6 ወር 75 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 181 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 5 የውጭ ዜጋ ናቸው።147 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 16 ሰዎች ከሱማሌ ክልል ፣ 10 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 8 ሰዎች ከድሬዳ...
### Text: በ13 ከተሞች አዲስ የወባ በሽታ ተህዋስ አስተላላፊ ትንኝ መሰራጨቱ ተገለፀ በኢትዮጵያ 13 ከተሞች አዲስ የወባ በሽታ ተህዋስ አስተላላፊ ትንኝ መሠራጨቱን አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ትንኞች የሚለየው ለመራባት የሚመርጠው አካባቢ ከተሞችን መሰረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡ኢንስትትዩቱ ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት መሰረት አዲስ የወባ በሽታ ተህዋስ አስተላላፊ ትንኝ በሶማሌ፣ አፋር፣ አማራና ምሥራቅ ኦሮሚያ ክልሎች መስፋፋቱን አመላክቷል፡፡አዲስ የወባ...
### Text: ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛልትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማድረግና ኮሮናን በመከላከል ትምህርት መጀመር የሚቻልባቸውን ሁኔታዎች እያጠና ይገኛል።በተደረጉ የዳሰሳ ጥናቶች ተማሪዎች የትምህርት መጀመርን በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን ለመረዳት እንደተቻለ ሚኒስቴሩ ገልጿል። በሌላ በኩል ወላጆች የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት ልጆቻቸው ትምህርት ቤት ሲሄዱ ለኮሮና ቫይረስ ሊጋለጡ ይችላሉ የሚለው...
### Text: ወላጆች ልጆቻችሁን ጠብቁ ትላንት በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ዋና እንዋኛለን ብለው ወንዝ ውስጥ ከገቡ 2 ልጆች የአንዱ ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ገልጿል።ህይወቱ ያለፈው የ12 ዓመት ታዳጊ መሆኑ ተነግሯል።የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ ወረዳ አንድ ለቡ አርሴማ አካባቢ ነው በአንድ ወንዝ ውስጥ እድሜያቸው የ8 እና የ12 ዓመት ታዳጊዎች ዋና ለመዋኘት በሚል ነው ወንዝ ውስጥ ገብተው ዋና ሲዋኙ የ12 ዓመት ታዳጊ...
### Text: ለግል መገልገያ ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ሆነው የሚገቡ ዕቃዎች የትኞቹ ናቸው ሲጋራ መለኪያ ግራም 0 የሚፈቀደው መጠን 200 ሲጋር መለኪያ በቁጥር 0 የሚፈቀደው መጠን 20 ብትን ትንባሆ መለኪያ በቁጥር የሚፈቀደው መጠን 250 የአልኮል መጠጥ መለኪያ ሊትር የሚፈቀደው መጠን 2 ለስላሳ ሽቶ መለኪያ ሚሊ ሊትር የሚፈቀደው መጠን 500 ሽቶ መለኪያ ሚሊ ሊትር የሚፈቀደው መጠን 500 ሞባይል መለኪያ በቁጥር የሚፈቀደው መጠን 2 ሁለት ...
### Text: በአስቸኳይ መስጂዶችን ማፍረስ አቁሙ የፈረሱትንም በፍጥነት መልሳችሁ አሰሩ ህዝበ ሙስሊሙንም በይፋ ይቅርታ ጠይቁ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትየኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአዲሱ በሸገር ከተማ መስጂዶች እየፈረሱ መሆኑን በመግለፅ ይህ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም አሳሰበ።ምክር ቤቱ ለኦሮምያው ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በፃፈው ደብዳቤ ነው ይህንን ማሳሰቢያ ያስተላለፈው።ጠቅላይ ምክር ቤቱ በደብዳቤው የኦሮሚያ...
### Text: የኦነግ መግለጫበኢትዮጵያ መንግስት እየተፈጸመ ያለዉ የሰብዓዊ መብት ረገጣ በነፃ እና ገለልተኛ አካል ምርመራ ልደረግበት ይገባል ከምዕራብ ኦሮሚያ የወለጋ ዞኖች ቴሌፎንና ኢንተርኔትን የመሳሰሉት የመገናኛ አገልግሎቶች በመንግስት ከተቋረጡ 1 ወር ኣለፈ። ከዚህም የተነሳ የዕለት ተዕለት ክስተቶችን በጊዜዉ ከነበቂ መረጃ ጋር ማግኘት አዳጋች ብሆንም እንኳ የመንግስት ወታደሮችና ታጣቂዎች በሰላማዊ ትጥቅኣልባ ዜጎች ላይ እያካሄዱ ባሉት ግድያ የሰዎች ህይወት እንደቅጠል እየረገፈ መሆኑ መተለያየ መ...
### Text: አጫጭር መረጃዎች በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት 123 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል ከመጋቢት 10 በኃላ የተመዘገበ ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው። በዩናይትድ ኪንግደም ከመጋቢት 17 በኃላ ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ተመዝግቧል ባለፉት 24 ሰዓት 210 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 32000 ደርሷል። ኮቪድ19 በቻይና ዳግም እንዳያገረሽ ተፈርቷል ባለፉት 24 ሰዓት 17 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል አምስቱ 5 ከውሃን ከተማ ናቸው። በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር 80807 ...
### Text: ከሰኔ 302011ዓም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ እንዳይደረግ ተከለከለ፡፡ኢር ታከለ ኡማ በከተማዋ አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታ እና የክረምት የበጎ ፈቃድ ስራ ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡የአለምአቀፍ ተቋማት መቀመጫ፣ የአገራችን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ማዕከል በሆነችው አዲስ አበበ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደራጀ መልኩ በሞተር ሳይክል በመታገዝ የቅሚያ እና የዝርፊያ ድርጊቶች ተበራክተዋል፡፡የከተማዋን ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ ፣...
### Text: ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 10 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታውቋል። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ የመስሪያ ቤቱን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ስራ አፈፃጸም በተመለከተ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።ወይዘሪት ፍሬ ህይወት በመግለጫቸው ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው በጀት ዓመት መጀመሪያ ሩብ ዓመት ላይ የተለያዩ የአሰራር ማሻሻያዎች ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህ መሰረትም ተቋሙ በተያዘው በጀት ዓመት መጀመሪያው...
### Text: ኢትዮጵያ ወንበሩን ባዶ በማድረግ ስብሰባውን ማለፏ በበሳል ዲፕሎማሲ የተደረገ ውሳኔ ነው አምባሳደር ዲና ሙፍቲየኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሩሲያ ዩክሬን ቀውስ ላይ በመከረው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ወንበሯን ባዶ በማድረግ ስብሰባውን ማለፏ በበሳል የዲፕሎማሲ ውሳኔ የተደረገ ነው አለ።ኢትዮጵያ በዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት ዙሪያ በተመድ ጠቅላላይ ጉባኤ ላይ ሩስያን በማውገዝ ወታደሮቿንም እንድታስወጣ በሚል በቀረበው የውሣኔ ሃሳብ ላይ ሙሉ በሙሉ ድምፅ ሳትሰጥ መውጣቷ...
### Text: በአውሮፓ የሙቀት መጠን በድጋሜ ከፍተኛ ሪከርድ ሊያስመዘገብ እንደሚችል ተጠቆመ። በአብዛኛው የምዕራብ አውሮፓ ሃገራት በአንድ ወር ውስጥ ክብረ ወሰን ይሰብራል በተባለለት የሙቀት ወጀብ እንደሚመቱ ቢቢሲ ዘገቧል፡፡ፖሪስ ውስጥ ያለው የትንበያ ተቋም በሰሜናዊ ፈረንሳይ 41 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሚለካ ሙቀት ሊኖር እንደሚችል መተንበዩን ዘገባው አመልክቷል፡፡እንግሊዝ ደግሞ 39 ዲግሪ ሴንቲ ግሬት የሚለካ ሙቀትን የምታስተናግድ ሲሆን የባቡር እንቅስቃሴዎችም ሙቀቱን ለመቋቋም በሚያስችል ፍጥ...
### Text: ትራምፕ ጀግና ለተባለው 0ውሻ ሜዳሊያ እንደሰጡ የሚያሳይ ሀሰተኛ ፎቶ መልቀቃቸው እያነጋገረ ነው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አል ባግዳዲን ለመግደል በተካሄደው ዘመቻ ተሳትፎ ለነበረው ውሻ ሜዳሊያ ሲሰጡ የሚሳይ የተቀነባረ ፎቶ በመልቀቃቸው ተቃውሞ እየቀረበባቸው ነው።ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ የለቀቁት ፎቶ በአይ ኤስ መሪ አል ባግዳዲ ግድያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለነበረው ጀግና ውሻ0 በአንገቱ ላይ ሜዳሊያ ሲያጠልቁለት ያሳያል፡፡ ነገር ግን ይህ ፎቶ በተግባ...
### Text: ኤርትራዊው ሙዚቀኛ በአዲስ አበባ ጥቃት ደረሰበትወዲ ማማ በሚል የቅጽል ስም የሚታወቀው ኤርትራዊ ሙዚቀኛ፣ ተክለ ነጋሲ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በማይታወቁ ሰዎች ጥቃት እንደተፈጸመበት ተነገረ።ድምጻዊው ባለፈው እሁድ ከሰዓት በኋላ ገርጂ በሚገኘው አንበሳ ጋራዥ አካባቢ በእግሩ በሚጓዝበት ወቅት ማንነታቸውን በማያውቃቸው አምስት ሰዎች ጥቃቱ እንደተፈጸመበት ተክለ ለቢቢሲ ተናግሯል። ጨምሮም ጥቃቱን ከፈጸሙበት ሰዎች ጋር ምንም አይነት ንግግር እንዳልነበረና አላማቸው ጉዳት ማድረስ እንደነበረ ገ...
### Text: የጤና ሙያ ብቃት ምዘና ለወሰዱ ከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ማሳሰቢያ አሰራጭቷል።ከሰሞኑን ከጤና ጥበቃ ወደ ኤጀንሲው ዝርዝራቸው የተላከላቸው የሙያ ብቃት ምዘና የተፈተኑ የጤና ሳይንስ ተመራቂዎች የትምህርት ማስረጃ የማረጋገጥ አገልግሎት እየተሰጣቸው ነው።ነገር ግን የተገልግላዮች ቁጥር እየተበራከተ በመምጣቱ በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ማሻሻይ የሚያደርግ መሆኑን ኤጀንሲው አሳውቋል።በዚህ መሰረት ከግንቦት 23 ከጥዋት 230 ሰዓት ጀምሮ በስልክ ቁጥር 01112...
### Text: የብሄራዊ ኩላሊት ንቅለ ተከላ ማዕከል በዚህ አመት ለ50 ህሙማን የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማከናወን ማቀዱን አስታወቀ። ይህ የተገለፀው ማዕከሉ የኩላሊት እጥበት ህክምና መስጫ መከፈቱንና የኩላሊት ንቅለ ተከላ የተጀመረበት ሁለተኛ ዓመትንአስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።የማዕከሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ሞሚና መሃመድ ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ከሰሐራ በታች ካሉ ሀገራት ውጤታማ የሆነ የኩላሊት ንቅለ ተከላበማካሄድ ከቀዳሚዎች ተርታ መሰለፏን ተናግረዋል።ባለፉት ሁለት ዓመታት ...
### Text: ስፖርት የ2018ቱ የሩሲያ ዓለም ዋንጫ ምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል። ሩሲያ በምታዘጋጀው የ2018ቱ የዓለም ዋንጫ ምድብ ድልድል በሩሲያ ሞስኮ ከተማ ይፋ ተደርጓል፡፡በዚሁ መሰረት፡ምድብ 1፡ ሩሲያ ሳኡዲ አራቢያ ግብጽ ኡራጋይምድብ 2፡ ፖቹጋል እስፔን ሞሮኮ ኢራንበምድብ 3፡ ፈረንሳይ አውስትራሊያ ፔሩ ዴንማርክበምድብ 4፡ አርጄንቲናአይስላንድ ክሮሺያ ናይጄሪያምድብ 5፡ ብራዚል ስዊዘርላንድ ኮስታሪካ ሰርቢያምድብ 6፡ ጀርመን ሜክሲኮ ስዊድን ደቡብ ኮሪያምድብ 7፡ ቤልጂየም ፓናማ ቱኒዚያ እንግሊ...
### Text: አጫጭር መረጃዎች በፈረንሳይ የሟቾች ቁጥር መቀነስ አሳይቷል። ባለፉት 24 ሰዓት 389 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 22245 ደርሷል። በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ51000 በልጧል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ905000 በልጧል። የዓለማችን ግዙፍ ጸረተህዋሲያን የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች አቅራቢው ምርቶቼ ለመድሃኒትነት አይውሉም ሲል አስጠንቅቋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ከኮቪድ19 ለመዳን ሰዎች ለምን ጸረተህዋሲያን አይወጉም ሲሉ አስተያየት ...
### Text: በኢትዮጵያ አሁን ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት የአኗኗር ሁኔታችንን እንድንቀይር ያስገዳል ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል። ዶር ሊያ ዛሬ በሱጡት መግለጫ እንዳሉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው በርካታ ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ እየተገኘባቸው ነው። ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ሳይኖራቸው ቫይረሱ የሚገኝባቸውም ሰዎች ቁጥር ጨምሯል ሲሉ ተናግረዋል።የኮቪድ19 ስርጭት ጎረቤት አገራት ጋር በማይዋሰኑ አካባቢዎችም ጭምር እየሰፋ መጥቷል ያሉት ዶክ...
### Text: አሳዛኝ የትራፊክ አደጋ️ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንጎላላ እና ጣራ ወረዳ ዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ 15 ሰዎች ህይወት አለፈ።አደጋው የደረሰው ከቀኑ 6 ሰአት ከ30 ሲሆን ከደብረ ብርሀን የሚመጣ ሲኖትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሀን ሲጓዝ ከነበረ ኮድ የህዝብ ማመለሻ አይሱዙ ቅጥቅጥ ጋር በመጋጨታቸው መሆኑን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ምክትል ኮማንደር ወርቅአገኘሁ ሸዋ ለ ተናግረዋል።የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን የተናገሩ...
### Text: መግለፂ ሓዘን ብሄራዊ ክልላዊ መንግስቲ ትግራይሎሚ ዕለት 18082011 ዓም አባላት ጋንታ ዋልታ ፖሊስ ትግራይ ኣብ ማእኸል ሃገር ዝነበሮም ፀወታ ዛዚሞም ናብ ትግራይ እናተመለሱ ኣብ ዝነበረሉ እዋን ኣብ ዓፋር ክልል ፍሉይ ቦታ ጉዋኔ ዝተብሃለ ከባቢ ዛጊድ መንነቶም ብዘይተፈለጡ ዑጡቓት ብዝተፈነወ መጥቃዕቲ ንሕልፈተ ህይወት ሓደ ሰብን ኣብ ልዕሊ ካልኦት ሓሙሽተ ኣባላት እታ ጋንታ ድማ ናይ ኣካል ጉድኣት ከም ዝበፀሐ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስቲ ትግራይ ኣረጋጊፁ እዩ፡፡ብሄራዊ ክልላዊ መንግስቲ ...
### Text: በተሽከርካሪ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውር የተያዘው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ ተከሳሽ አብዱራህማን ዩኑስ ከሚመከለተው የመንግስት ፈቃድ ውጪ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ገደብ የተደረገባቸው የጦር መሳሪያዎችን በተሸከርካሪ ደብቆ ወደ ሀገር ሊያስገባ ሲል ተይዞ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በእስራት ተቀጥቷል፡፡ተከሳሽ 53 ቱርክ ስሪት ሽጉጦችንና 35 ሺህ 766 ጥይቶችን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 350931 አአ በሆነ ላንድክሩዘር መኪና ደብቆ ወደ ሀገር ሊያስገባ ሲሞከር በተደረገው ክትትል በአዲስ አበባ የካ...
### Text: ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5414 የላብራቶሪ ምርመራ 250 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5425 ደርሷል። ቫይረሱ የተገኘባቸው 158 ወንድ እና 92 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ3 ወር 90 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 240 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 10 የውጭ ዜጋ ናቸው።177 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 21 ሰዎች ከትግራይ ክልል ፣ 20 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 18 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል፣ 8 ሰዎች...
### Text: ፍርድ ቤት የአሥራት ጋዜጠኞች ላይ የተከፈተው መዝገብ ላይ ለመበየን ቀጠሮ ሰጠበዋስትና እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው በኋላ ሲቪል በለበሱ ግለሰቦች በድጋሜ ታስረው ከሀጫሉ ግድያ በኋላ አመፅ አስነስተዋል በሚል ሌላ የምርመራ መዝገብ የተከፈተባቸው በላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብርና ምስጋናው ከፈለኝ ለመስከረም 72013 ዓም ለብይን ተቀጠሩ።የአሥራት ጋዜጠኞች በድጋሜ የተከፈተባቸውን መዝገብ ከቀደመው ጉዳይ የተለየ አይደለም ብለው በመከራከራቸው ፍርድ ቤቱ የፖሊስና የፍርድ ቤቱን መዝገብ መርምሮ በ...
### Text: በአአ ከተማ የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪ ተደረገ።በአአ አስተዳደር የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ መደረጉ በዛሬው ዕለት መደረጉ ታውቋል።ለታሪፍ ማሻሻያው እንደምክንያትነት የተቀመጠውም ወቅታዊው የነዳጅ ጭማሪ መሆኑ ተገልጿል።ቢሮው ባለፉት 2 ወራት በነዳጅ ላይ የ5 ነጥብ 90 ብር ጭማሪ መኖሩን ከግምት በማስገባት የነዋሪውን የኑሮ ሁኔታ ከግምት በማስገባት በሚኒ ባስ፣ ሃይገርና መካከለኛ አውቶብሶች ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል።በሚድ ባስ ወይም የሃይገር እና መካከለኛ አውቶብሶች...
### Text: ፋይዘር የመጀመሪያውን በታብሌት መልክ የሚወሰድ የኮቪድ 19 መድሃኒት እየሞከረ ነው ፋይዘር የመድሃኒት አምራች ተቋም በታብሌት መልክ የሚወሰድ የኮቪድ 19 መድሃኒት ለመስራት ሙከራዎችን እያደረገ እንደሆነ ተነግሯል።አሁን ላይ ባለው ህክምና በጽኑ ህሙምነት ላሉ ሰዎች የሚደረገው የህክምና እርዳታ ኦክስጅን እንዲያገኙ በማድረግ ሰውነታቸው በራሱ የበሽታ መከላከል ብቃቱን በማሳደግ እስኪያገግሙ መጠበቅ ነው፡፡ ይህ ግን ሁል ጊዜ አዋጭ አይሆንም ለዚህም ነው ብዙዎች ኦክስጅን እንኳን እያገኙ እን...
### Text: የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ ጉዳዮች ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ ትግራይ ክልል ውስጥ የኤርትራ ኃይሎች የትግራይ ህዝብ ለረሃብ እንዲጋለጥ እያደረጉ ነው ሲሉ ከሰዋል።ሎውኮክ ይህን ያሉት ከሮይተርስ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ወቅት ነው።ኃላፊው የኤርትራ ወታደሮች እና የአከባቢው ተዋጊዎች ሆን ብለው ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ ባሉ አካባቢዎች ለሚገኙ ከ 1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሰብዓዊ አቅርቦት እንዳይደርስ እያገዱ ነው ብለዋል።በእርግጠኝነት ምግብ እንደ ጦር መሳሪያነት ...
### Text: ላሊበላ የገባው የህወሓት ሽብር ቡድን አሁን ላይ በመከላከያ ሰራዊት እና በክልሉ ልዩ ሃይል እየተመከተ ነው አቶ ግዛቸው ሙሉነህበትላትናው ዕለት የህወሓት ታጣቂዎች አማራ ክልል ወደምትገኘው ላሊበላ ከተማ መግባታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም የከተማይቱ ምክትል ከንቲባ አቶ ማንደፍሮ ታደሰ ማረጋገጣቸው ይታወቃል።የቡድኑ ታጣቂዎች በሶስት ትምህርት ቤቶች ውስጥም ካንፕ ሰርተው መቀመጣቸውን ነዋሪዎች እንደገለፁ አይዘነጋም።ላሊበላ ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ በዛሬው ዕለት የአ...
### Text: ደንበኞች በሚበዙበት አካባቢ የፖስ ማሽን የሙከራ አገልግሎት እየተሰጠ ነው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች በሚበዛባቸው አካባቢዎች የሚስተዋለውን መጨናነቅ ለመቀነስ የሚያስችል የፖስ ማሽን የሙከራ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አሳውቋል።የፖስ ማሽን የሙከራ አገልግሎቱ በስራ ላይ የዋለው በአዲስ አባባ በአራቱም ዲስትሪክቶች በሚገኙና ደንበኛ በሚበዛባቸው የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ነው፡፡በሙከራ ደረጃ አገልግሎት መስጠት ...
### Text: 4 ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ በንብረት ግምጃ ቤት ውስጥ የተቀመጡ ከ 1 ሺህ 800 በላይ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ህዳር 8 ቀን 2014 ዓም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 በሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ብርበራ ከ1 ሺህ 800 በላይ ጥይቶች በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።በቤተ ክህነቱ ግቢ በሚገኝ የንብረት ግምጃ ቤት በሚገኝ የፅህፈት እና የፅዳት እቃዎች ማስቀመጫ ውስጥ በተደረገው ብርበራ የተገኙት...
### Text: ጥቆማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ የሥራ መደቦች ሰልጣኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ሰልጣኝ አብራሪፓይለት ሰልጣኝ የአውሮፕላን ቴክኒሽያን ሰልጣኝ የአውሮፕላን ሜካኒክ ሰልጣኝ የበረራ አስተናጋጅ ሰልጣኝ የመንገደኛ አገልግሎት ኢጀንት አመልካቾች ለምዝገባ ሊያሟሉ የሚገባቸው የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውንና ኮፒው፣ የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ካርድ፣ የልደት ካርድ፣ የታደሰ የቀበሌ የነዋሪነት ማረጋገጫ ካርድ እና አንድ ጉርድ ፎቶግራፍአመልካቾች ከተዘረዘሩት...
### Text: ጋምቢያ ፕሬዚዳንት አዳም ባሮ ላይ በ2017 ከተቃጣ የመፈንቅለ መንግስት ሴራ የተጠረጠሩ በርካታ የቀድሞ ወታደሮችን በቁጥጥር ስር አውላለች፡፡የሀገሪቱ ወታደራዊ ፍርድ ቤት በመፈንቅለ መንግስት ተሳትፈዋል ተብለው ከቀረቡለት ውስጥ በሰባቱ ላይ 9 አመት እስራት ሲወስን በቀሪዎቹ ላይ 3 አመት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡የምእራብ አፍሪካዊቷን ሀገር ለ22 አመታት መርተው እአአ 2016 በተደረገ ምርጫ ተሸንፈው ከሀላፊነት አለቅም ቢሉም በግፊት ከወረዱት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ያህያ ጃሜህ ለመፈንቅለ ...
### Text: የቲክቫህ አባላት ከ1 ሚሊዮን አልፈዋልበኢትዮጵያ እና በውጭ የሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከ1000000 አልፈዋል። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላቶች እድገት ላደረጋችሁር ትልቅ ስራ ምስጋና ይገባችኃል እንኳን ደስ አለን ሁላችንም እንኳን ደስ አላችሁ እያላችሁን ያላችሁ አባላት መልዕክታችሁ እንኳን ደስ አለን በሚል ይቀየርልን እኛ ምን አቅም አለን 1 ሚሊዮን ሰው በአንድ ቦታ የማሰባሰብ ይህ ሁሉ የናተው ተግባር ነውዛሬ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ዙሪያ ጥያቄ መጠየቅ ትችላላችሁ የምንችለውን ምላሽ ለ...
### Text: ከኃላፊነታቸው ተነሱ በምስራቅ ወለጋ ዞን መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በየደረጃው በተካሄደው የጥልቅ ተሃድሶ ግምገማ 195 አመራሮች ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን የዞኑ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ኦህዴድ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡በዞኑ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ በሪሶ ተመስገን እንደገለጹት መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ከዞን ጀምሮ በተዋረድ በየደረጃው ባሉ የስልጣን እርከኖች የተነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በተካሄደው ጥልቅ የተሃድሶ ግምገማ 195 ነባር አመራሮች ከኃላ...
### Text: ከኢህአዴግህወሓት ቁጥጥር ኮሚሽን አባላት የተሰጠ መግለጫከተቋማዊና ሕጋዊ አሰራር እንዲሁም ከመርህ ውጭ የሚገነባ ድርጅት እና ሀገር የለምከኢኮኖሚ ኮንትሮባንድ ይልቅ የፖለቲካ ኮንትሮባንድ ሀገርን በባሰ ሁኔታ ይንዳልህዳር 152012 ዓምየኢህአዴግ ምክር ቤት ፅሕፈት ቤት ሰሞኑን ባካሄዳባቸው ተከታታይ መድረኮች ግንባሩ ወደ አንድ ወጥ ፓርቲያደረገውን የውህደት ውሳኔ አስመልክቶ የተሰጠው መግለጫ በመገናኛ ብዙኃን ተከታትለናል፡፡ በመግለጫው የኢህአዴግ ቁጥጥር ኮሚሽን ድጋፉን ሰጥተዋል የሚልምሰም...
### Text: 2012 የምርጫው የጊዜ ሰሌዳ በቅርቡ ይፋ ይደረጋልወሪት ሶሊያና ሽመልስየምርጫው የጊዜ ሰሌዳ እስካሁን ድረስ ይፋ ያልሆነው ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስፈልጉ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ በመሆናቸው ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከመንግስት ለምርጫው ማስፈጸሚያ ከጠየቀው አራት ቢሊዮን ብር ገደማ በጀት ውስጥ እስካሁን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈቀደው 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም 40 ሚሊዮን ዶላር ከልማት አጋሮች እያሳ...
### Text: የአገር ነፃነት በገንዘብ አይለወጥም አምባሳደር ዲና ሙፍቲየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው አሜሪካ ስላሳለፈችው እገዳ አንስተዋል።የአሜሪካ እገዳ የ2ቱን አገራት ግንኙነት ቢጎዳም ቀዩ መስመር ግን የኢትዮጵያ ነፃነት በገንዘብ ሊቀየር የሚችል አለመሆኑ ነው ሲሉ ተናግረዋል።አክለውም የአገር ነፃነት በገንዘብ አይለወጥም ብለዋል። አምባሳደር ዲና ወቅታዊዉ የአሜሪካ ው...
### Text: የጠሚ ጽቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ምን አሉ መንግስት የሰሜኑ ጦርነት በሰላም ለመቋጨት በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር ለሚደረገው ሂደት ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል። የሰላም ሂደቱ ውስብስብ እና ረጅም መሆኑን ገልፀዋል። የትኛውም የሰላም ሂደት ረጅም ነው። ቀላል አይደለም። ውስብስብና የተደራረቡ ሁነቶችን የያዘ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪ ለሆኑት ኦባሳንጆ ትልቅ ቦታ እንዳላት ተናግረዋል። ከባለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ 2 ነጥብ 1 ቢሊየን ጥሬ ብር፣ 87 ሺ ሜትሪክ...
### Text: ዶክተር ነገሪ ስለ ደምቢ ዶሎ️በኦሮሚያ ክልል ደምቢ ዶሎ ከተማ በአንድ ነፍሰጡር እና በሌሎች አራት ሰዎች ላይ ጥቃት የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩንኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ አስታወቁ።ትናንት ማምሻውን ደምቢዶሎ ከተማ በአንድ በለሶስት እግር ተሽከርካሪ አንድ ነፍሰጡር እናት ይዞ ወደ ሆስፒታል በመጓዝ ላይ ያለ ቤተሰብ ላይ ጥቃት ደርሶ ነበር።በጥቃቱም ነፍሰጡሯ እናት ህይወቷ ሲያልፍ በቀሪዎቹ አራት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለ...
### Text: ያለ አግባብ ዲግሪያችንን ተከልክለናል የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችትምህርቱን ቢያጠናቅቁም የመግቢያ መስፈርቱን ላላሟሉ ዲግሪ አንሰጥም ዩኒቨርሲቲውበኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በቡራዩ ቅርንጫፍ ለአራት ዓመታት ስማር ቆይቻለሁ። የተማርኩት ለማወቅ ብቻ ሳይሆን ዲግሪ አግኝቼ በሥራዬ ዕድገት ለማግኘትና ለመሻሻል ነበር የሚሉት አቶ ገመቹ ዳባ ትምህርቱን ሲያጠናቅቁ ያልገመቱትን ዲግሪ አይሰጥህም የሚል ምላሽ ማግኘታቸውን ይናገራሉ።እንደ አቶ ገመቹ ገለፃ ትምህርቱን ለአራት ዓመታት ሲከታተሉ ዲ...
### Text: መፍትሄ ባልተበጀለት ግጭት እየተበጠበጠች ያለችዉ ድሬደዋ ከተማገንደ ገራዳ በተባለው የከተማይቱ አካባቢ ትናንት የተቀሰቀሰ ግጭት ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ አንድ የህክምና ባለሞያ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ እንደገለፁት ትናንት እና ዛሬ ብቻ በከተማው አካባቢዎች እየተፈጠረ ካለው ግጭት ጋር በተያያዘ ወደ ድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ከመጡ ተጎጂዎች የሁለቱ ሕይወት አልፏል። ከዚህም ሌላ የህክምና ባለሞያው «በዛሬው ዕለት ተጎድተው የመጡ ሰዎች ቢኖሩም እንኳን ወደ ሆስፒታሉ...
### Text: የአቶ እስክንድር ነጋ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ የወንጀል ችሎት አቶ እስክንድር ነጋን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።መርማሪ ፖሊስ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ያገኘውን የምርመራ ሥራ ለፍርድ ቤቱ አብራርቶ ለቀሪ የምርመራ ሥራዎችም የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።ጠበቆችም አቶ እስክድር ነጋ የዋስትና መብቱ እንዲጠበቅ የጠየቁ ሲሆን ፣ ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል።ምክን...
### Text: በአፋርና ኢሳ ጎሳ መካከል ተከስቶ የነበረውን ግጭት ለመፍታት የሚያስችል የሰላም ኮንፈረንስ ተካሄደ በአፋርና ኢሳ ጎሳ መካከል ተከስቶ በነበረው ለመፍታት የሁለቱ ጎሳ አባላት እና የአካባቢው ነዋሪዎች የተሳተፉበት የሰላም ኮንፈረንስ በሚሌ ወረዳ አዳይቱ ቀበሌ ተካሂዷል፡፡በኮንፈረንሱ ላይ የተሳተፉ የሁለቱ ጎሳ አባላት በአፋር እና በኢሳ መካከል ችግር እንደሌለ ገልፀው በአካባቢው ባለፉት 11 ወራት የተከሰተው ግጭት ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ወጣቶች ወዳልተገባ ግጭት እንዲገቡ በመደረጉ ...
### Text: የሚዲያው ሚና ሃሳቦችን ለማቀራረብ እንደ ዶክተር ሙላቱ አለማየሁ ገለጻ የሚዲያው ዘርፍ በሀገራችን ከተጀመረበት 1992 እኤአ ጀምሮ ብዙ ውጣወርረዶችን ማለፉን ይጠቅሳሉ፡፡ አንድ ጊዜ የህዝብን ድምጽ ሌላ ጊዜ ደግሞ የመንግስትን ድምጽ በማሰማት አልፎ አልፎ ገለልተኛ ሆነውም ለመዘገብ ሲሞክሩ ዘመናትን አልፈዋል፡፡ መንግስትም ለዘርፉ እድገት እንዲሁም ለሞያው ክብር ማነቆ የሆኑ ህጎችን ሲቀርጽ አንዳንዴም ከዛ በተቃራኒው ህጎችን ሲያሻሽል ቆይቷል፡፡ የሚዲያዎችን ጉዳይ የመቆጣጠር ኃላ...
### Text: የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መታሰቢያ ኀውልት️ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ የተገነባው የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መታሰቢያ ኀውልት የካቲት 3 ቀን 2011 የሚመረቅ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።ለቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት መመስረት በነበራቸው ታላቅ የመሪነት ሚና የመታሰቢያ ኀውልት እንዲቆምላቸው መወሰኑ ይታወቃል።የኀውልቱ ግንባታ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ ፈለገ ሰላመ የስነ ጥበብ ባለሙያዎች መከናወኑን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር...
### Text: 2019 «አሸናፊ መሆኔ የሚገርም ነገር ነዉ። ብቻ እንደ ግለሰብ በጣም ያኮራል። ትልቁ ግን ግን ሃገርን ማስጠራት ማለት ኩራት ነዉ። ለአፍሪቃም ኩራት ነዉ። ስለዚህ ይህን ጉዳይ ጉዳያችን ብለን ለዓለም ሕዝብ ለመጀመርያ ጊዜ ለመላዉ ዓለም ያሳወቅንበት ነዉ። ጥሩ ስራ ተሰርቶአል እስካሁን ድረስ ግን ብዙ ስራ እንደሚጠብቀን ነዉ የሚያሳየን። ሆኖም ግን ብቻችንን የምንሰራዉ ስራ ስላልሆነ የዓለም ሕዝብ በሙሉ ድምፅ ሰጥቶ እዚህ ደረጃ ላይ አድርሶናል። ዘንድሮ ለዉድድር ከኔጋ የ...
### Text: የሴቶችና ህፃናት ጥቃትበኢትዮጵያ ሦስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 280 ሴቶችና ህፃናት ጥቃት እንደተፈጸመባቸው አንድ ጥናት አመለከተ።የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት መከላከልና ጥቃቱ ሲፈጸም ምን አይነት ምላሽ መስጠት ይገባል በሚሉ ጉዳዮች ላይ በሴቶች ጉዳይ ከሚሰሩ ሲቪክ ማህበራትና ፌዴሬሽኖች ጋር ዛሬ እየተወያየ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።በውይይቱ ላይ ከመጋቢት 1 ቀን 2012 እስከ ግንቦት 20 ቀን 2012 ዓም ባሉት ጊዜያት በሴቶችና ህፃናት ላይ...
### Text: ከ864 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የዋልታ የፌስቡክ ገፅ መጠለፉን ለመመልከት ተችሏል።የፌስቡክ ገፁ በክሪፕቶ ከረንሲ ጠላፊዎች እጅ እንደገባ የሚፃፉት ኮዶች እንደሚያመላክቱ የዘርፉን ባለሞያ ዋቢ አድርጎ ኢትዮጵያ ቼክ አስነብቧል።የአክስዮን እና ክሪፕቶ ከረንሲ የሚገበያይ ነጋዴ የሆነው አብነት ተፈራ እየጠየቁ ያሉት የክሪፕቶ ከረንሲ ቲተር ነው። ቴተር ማለት ወደ አሜሪካ ዶላር የሚመነዘር እና የሚተመን መጠን ያለው ሲሆን ስሌቱም 1 5000 = 5000 ነው። ብሏል።አክሎም በስተ...
### Text: ከድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ ከትላንት ህዳር 8ቀን 2011አም ከሰአት በሃላ እና ህዳር 9ቀን እረፋድ ላይ በቀበሌ 09 ፖሊስ መሬትና መጋላጨብጡ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ፖሊስ አሁን ላይ መነሻ ምክንያቱን እያጣራው ያለው ግጭትና ሁከት የተፈጠረ ሲሆን በዚህም ግጭት በህክምና ጭምር የተረጋገጠ በስለት ጉዳት ጉዳት ደርሶበት የ1ሰው ህይወት ሲያልፍ በ2 ቤቶች ላይ ቀጠሎ እንዲሁም በሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል።ፖሊስ ከፌደራል ፖሊስና ከመከላኪያ ጋር በመሆን ...
### Text: ጀዋር መሀመድ እና እክንድር ነጋ በ የአዲስ አበባ የባለቤትነት ዉዝግብ«እኛ የምንለዉ ሕጉ የሚለዉን ነዉ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሕግ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ነች ይላል። የፌደራሉ ሕገ መንግሥትም ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም እንዳለዉ ያስቀምጣል»የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅና የመብት አቀንቃኝ ጀዋርመሐመድ «የአዲስ አበባ ጉዳይ የዜግነት ጥያቄ ነዉሕገ መንግስቱ ከየት መጣ ማን አወጣዉ ምንስ አላማ ነበረዉ» ጋዜጠኛና የመብት አቀንቃኝ እስክንድርነጋ ።...
### Text: የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በትናንትናው እለት ሁለት የፖሊስ አባላቱ በቄራ ጎፋ ማዞሪያ አካባቢ የፈፀሙትን ድርጊት እያጣራ መሆኑን አስታውቋል። ኮሚሽኑ ትናንት ረፋድ ላይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ቄራ ጎፋ ማዞሪያ አካባቢ በድለላ ስራ ላይ በተሰማሩ ሁለት ቡድኖች መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር አስታውሷል።ይህን ተከትሎም የተፈጠረውን አለመግባባት ለመዳኘት ወደ ስፍራው ያቀኑ ሁለት የፖሊስ አባላት አለመግባባት የፈ...
### Text: ዛሬ ማምሻውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ለመሸፈን ጩኸቱን ቀጥሎበታል ብሏል። በአማራ ክልል እና በአፋር ክልል የተለያዩ ጥቃቶችን በመፈጸም በዜጎች ላይ ከፍተኛ አካላዊና ቁሳዊ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ገልጿል።ቡድኑ በውጫሌና ጭፍራ አካባቢዎች ላይ በፈጸመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት ከ30 በላይ ንጹሃን ዜጎች በግፍ መግደሉን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል። እያደረሰ ያለው ጭፍጨፋና ግድያ እንዳይታወቅበት ለመሸፋፈን የተለመደውን የ...
### Text: ተማሪዎቹ በድጋሚ እንዲፈተኑ ተወስኗል በኮንሶ ዞን በፀጥታ ችግር የ2013 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈትነው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በድጋሜ እንዲፈተኑ መወሰኑን የኮንሶ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታውቋል።መምሪያው ይህን ያሳወቀው የክልሉን ትምህርት ቢሮ ዋቢ በማድረግ ነው። ተማሪዎቹ ድጋሜ እንዲፈተኑ ውሳኔ የተላለፈው ለኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር በቀረበ ቅሬታ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች ከወዲሁ ለፈተናው እንዲዘጋጁ ጥሪ ቀርቧል።በኮንሶ ዞን አከባቢ ከ2011 ዓም ...
### Text: ፈተናውን 986 በመቶ ተማሪዎች አልፈዋል በትግራይ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 986 ከመቶ0ወደ ቀጣዩ ክፍል ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።ኮሮና ተከትሎ በትግራይ በተካሄደው ጦርነት ተቋርጦ የነበረው የመማርና የማስተማር ሂደት ከሚያዝያ 2015 ዓም ጀምሮ በተሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በመውሰድ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የተፈተኑ ተማሪዎች ውጤታቸዉ ይፋ ሆኗል።በትግራይ ትምህርት ቢሮ0የትምህርት ጥራትና ምዘና ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዳይሬክቶሬት አቶ ክንፈ ፍስሃ...
### Text: የገቢዎች ሚኒስቴር️ግምታዊ ዋጋቸው 1 ሚሊየን 300 ሺህ ብር በላይ የሚሆኑ የኮንትሮባንድ ዕቃች በተለያዩ የጉምሩክ የፍተሻ ጣቢያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።ባዛሬው ዕለት በተለያዩ የጉምሩክ የፍተሻ ጣቢያዎች ላይ በተደረገ ክትትል ግምታዊ ዋጋቸው 1 ሚሊየን 315 ሺህ 310 ብር የሚሆኑ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።በዚህ መሰረትም በወልዲያ የጉምሩክ ፍተሻ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ ጊዜው ያለፈበት የፋፋ ዱቄት እና ግምታዊ ዋጋቸው 385 ሺህ 50 ...
### Text: በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫበከተማችን ሀዋሳ ከየካቲት 28 ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባኤ ውይይት እንድቋረጥ ተደርጓል።ውይይቱ የተቋረጠበት ዋናው ምክንያት ለውይይቱ በቀረበው ሰነድ ውስጥ የተካተቱ አንዳንድ ነጥቦች የሲዳማን ብሄር ህገ መንግስታዊ መብቶችን የምጻረሩ እንደሆኑ በመረዳት የብሄሩ ተወላጅ የሆኑ አመራር በሙሉ የቀረበው ሰነድ ለውይይት የማይጋብዝ እንደሆነ አቋም በመያዝ ከስብሰባው ራሳቸውን ካገለሉ በኋላ በ29062011 ዓም አጠቃላይ ክልላዊ መድረኩን ለ...
### Text: በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር 55 ሰዎች መታሰራቸውን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አስታወቀ በዛሬው የመስቀል ደመራ በአል አከባበር ላይ 55 የበዓሉ ታዳሚዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት እና ጉዳይ አስፈፃሚ መላከ ሕይወት አባ ወልደየሱስ ሰይፉ ለቢቢሲ ገለፁ። መላከ ህይወት አባ ወልደየሱስ እንደገለፁት 33ቱ ምእመናን በቁጥጥር ስር የዋሉት ቤተክርስትያኗ ላይ የሚሰነዘር ጥቃት እንዲቆም የሚያወግዝ ፅ...
### Text: በትራፊክ አደጋ የ1 ሰው ህይወት ሲያልፍ 13 ሰዎች ተጎድተዋልበወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ በተሽከርካሪ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በ13 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ፖሊስ አስታወቀ። አደጋው የደረሰው ዛሬ ረፋዱ ላይ 0በወረዳው አመያ 0በተባለው መንደር ነው።ከዳውሮ ዞን ዋና ማዕከል ተርጫ ከተማ 56 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ሀዋሳ ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 301926 ኢት የሆነ ሀገር አቋራጭ አውቶብስ በመገልበጡ አደጋው መድረሱን የወረዳው ፖ...
### Text: የፖሊስ የዘፈቀደ እስር በአስቸኳይ ሊቆም እና የታሰሩትም ሊለቀቁ ይገባልየኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንበዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ የተገኙ ሰዎች በፖሊስ እየታሰሩ ከመሆናቸው ጋር በተያያዘ በሚዲያዎች የወጡ ዘገባዎችንና ለኮሚሽኑ የቀረቡ አቤቱታዎችን ተከትሎ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ የሚከተለውን ብለዋል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመከላከል አስፈላጊ የጤና መመርያ ሲሆን ሕብረ...
### Text: የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ወደ ትግል ሜዳ ለመዝመት ተዘጋጅቻለሁ ብለዋል።ከንቲባው ዛሬ አመሻሹን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት ከእኛ ይጠበቃልና እኔም ከሌሎች ወንድሞቼ ጋር ወደ ትግሉ ሜዳ ለመዝመት ተዘጋጅቻለሁ። በግንባር ተገኝተን ያዘጋጀነውን ስንቅ እናቀብላለን ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ጀግናው ሠራዊታችንን በወኔ እናበረታታለን ብለዋል።የአስተዳደሩ የፀጥታ ኃይሎችና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ከመቼውም ጊዜ በላይ የ...
### Text: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጾመ ነነዌን በማስመልከት ያወጀው ጾምና ጸሎት ዛሬ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓም ያበቃል።ቅዱስ ሲኖዶስ ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁርልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ሲል ባስተላለፈው ጥሪ መሰረት ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት ምዕመኑን ይህንኑ ተግባራዊ ሲያደርግ ነበ...
### Text: ከሾኔ️ሀይ ፀጊሽ ነኝ ከሾኔ የሾኔ ወጣቶች በትላንትናው እለት ከቀኑ 800 ሰዓት ጀምሮ በሾኔ ሁለገብ አዳራሽ ታላቅ የሀሳብ ምልልስ በሰላማዊ መንገድ በጣም በርካታ ወጣቶች በተገኙበት ስብሰባ ተደርጓል። የስብሰባው መነሻም ሾኔ የዛሬ 107 ዓመት ነው የተቆረቆረችው ነገር ግን የዕድሜዋን ያክል ልታድግ አለመቻሏ የከተማዋ ባለስልጣናት ስልጣን ላይ ሲመጡ የራሳቸውን ጥቅም ብቻ የማስቀደም ስራ እየሰሩ ተተኪውም በእነርሱ አርአያነት እየተከተለ እንዲሄድ አድርገዋል በማለት እጅግ በጣም ኪራይ ሰብሳ...
### Text: ባህርዳር ትናንት እሁድ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ አባይ ማዶ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በአካባቢው ሚሊሻዎችና ሲፈለግ በነበረ በአንድ ግለሰብ መካከል በተደረገ የተኩስ ለውውጥ የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የባህር ዳር ፖሊስ አባል ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ተፈጸሞ ከቆየ ሌላ የግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ ሲፈለግ የቆየ ነው የተባለን ግለሰብ ሊይዙ ሲከታተሉት የነበሩ የአካባቢው ሚሊሻዎች ላይ ተኩስ በመክፈቱ ነው ጉዳት የደረሰው።ሸፍቶ...
### Text: የሶማሊያ መከላከያ ሶስት የአልሻባብ ታጣቂዎችን ገደለ። ሶስት የአልሻባብ ታጣቂዎች የተገደሉት በደቡባዊ ሶማሊያ አርብ ምሽት በተካሄደ ኦፕሬሽን ሲሆን የሶማሊያ ሃይል በአውድኒል ከተማ ባካሄደው ስምሪት ነው ተብሏል፡፡የከተማዋ አስተዳዳሪ ኢብራሂም መሃመድ ኑር ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የሶማሊያ ሃይል እርምጃውን የወሰደው የከተማዋ ነዋሪዎች ጽንፈኛው አልሻባብ አስገዳጅ ግብር እንድንከፍል አድርጎናል በሚል በሰጡት ጥቆማ ነው፡፡በተካሄደው ኦፕሬሽን ሶስት የአልሻባብ ታጣቂዎች ሲገደሉ አንዱ...
### Text: ባለፉት ሶስት ቀናት ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በቀን 28112011 በሁለት መኪና ተጭኖ ወደ ድሬዳዋ ሊገባ የነበረ ግምቱ 1785140 ብር የሚያወጣ የምግብ ዘይት ሶማሌ ክልል ሽንሌ ወረዳ በፀጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር ውሎ ድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽቤት ገቢ ተደርጓል። በተመሳሳይ ቀን ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ ይሄድ የነበረ የመንገደኞች ባቡር ሞተሩ ባለበት ክፍል ውስጥ...
### Text: ለአዲስ አበባ መምህራን ታብሌት ሊሰጥ ነው በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን የትምህርት ዝግጅትና ቁጥጥር የሚያደርጉበት እንዲሁም የትምህርት እቅድ የሚያወጡበት ታብሌት ሊሰጥ ነው። የከተማ አስተዳደሩ በአዲስ አበባ ያለውን የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ በከፍተኛ ደረጃ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል፡፡በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በከተማዋ ለሚገኙ የመንግስት ትቤት መምህራን የትምህርት ዝግጅት እና የትምህርት እቅድ የሚያወጡበት ታብሌት ለመስጠት የከተማ አስተዳደሩ ዝግጅቱን አጠናቅቋ...
### Text: 2013 በምርጫ 2013 ክልሎች የሚኖራቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፓርላማ የውክልና መቀመጫ የሲዳማ0ክልል0በሕዝብ0ተወካዮች0ምክር0ቤት0የሚኖረው0መቀመጫ0190 የደቡብ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውክልና 104 0ደቡብ ክልል ላለፉት 26 ዓመታት ገደማ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነበረው ውክልና ወይም መቀመጫ 123 ነበር ሲዳማ ከደቡብ ክልል ወጥቶ ራሱን ከቻለ በኃላ ፣ ደቡብ የሚኖረው መቀመጫ ብዛት 104 ሆኗል። ኦሮሚያ0ክልል0በነበረበት 178፣0 አማራ0ክልል0በነበረበት ...
### Text: የብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶር እና የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓም በመንበረ ጸባኦት ቅደስት ሥላሴ ካተድራል እንደሚፈጸም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶር መግለፃቸውን የኢኦተቤ ቴሌቪዥን ዘግቧል።ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶር ለረጅም ጊዜ በሀገር ውስጥ እና በውጭ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ትላንት ከዚህ ዓለም በሞተ ስጋ መለየታቸው መገለፁ ይታወቃል።ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ መጋቢት 01 ቀን 2015 ዓም...
### Text: ቆም ብለን እናስብ️ ሰውን እንደሰው የሚያከብር ማህበረሰብ ካልተፈጠረ የኢትዮጵያ ችግር መቆሚያ ያለው አይመስለኝም። ዛሬ ለምንሰማቸው አሳዛኝ ኢሰብዓዊ ድርጊቶች ብዙ የሚጠየቁ አካላት ቢኖሩም ዛሬ ያለነው በተለይም ፊደል ቆጥረናል የምንል ሰዎች ስለሰውነት ብዙ መጮኸ አለብን በምንችለው ቋንቋ ሁሉ ሰው ክቡር መሆኑን ላገኘነው ሰው ሁሉ እንናገር።የኢትዮጵያ ችግር ዴሞክራሲ እና ነፃነት ብቻ አይመስለኝም። ሌሎች መሰረታዊ ችግሮች አሉብን እውነተኛ ዴሞክራሲ እንኳን ቢመጣ እንጠቀምበት ይሆን ...
### Text: የኢትዮጵያ አየር መንገድ የወደብአየር የጭነት አገልግሎት ጀምሯል።የጅቡቲ ዓለም አቀፍ ነጻ የንግድ ቀጠና አካል በሆነው የጅቡቲ ወደብ የሚተላለፍና የኤሌክትሮኒክስና የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎችን የያዘው 17 ቶን የሚመዝን የመጀመሪያ የወደብአየር ጭነት አገልግሎት ጥቅምት 18 ቀን 2014 ዓም የኢትዮጵያና ጅቡቲ ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል። ጭነቱ ከሸንዘን ቻይና በመነሳት በጅቡቲ ወደብ አልፎ ሌጎስና ካኑ ይራገፋል ተብሎ ይጠበቃል።የወደብአየር የጭነት አገልግሎቱን...
### Text: ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ከሙስሊም ተማሪዎች ጋር በተያያዘ በርካታ ጉዳዮች እየተነሱ እንደሆነ ይታወቃል።የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላትም ጉዳዩ በዛው ዕለት አልያም በቀጣዩ ቀን የሚመለከታቸው አካላት በመነጋገር በፍጥነትይፈቱታል በሚል በትኩረት ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን ቀናት አልፎ አሁን ላይ ምዕመኑ ሰልፍ እስኪወጣ አስገድዶታል።ዛሬ ምዕመኑ በአንዳንድ መስጂዶች በሰልፍ ድምፁን አሰምቷል።የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሆን ተብሎ በሚመስልና በዘመቻ ...
### Text: አቃቤ ሕግ የቀድሞ የሜቴክ የስራ ሀላፊዎች በነበሩት ሻለቃ ክንደያግርማይና ሌተናል ኮሎኔል አሰፋዮሐንስ ላይ ክስ መሰረተ። በዚሁ መዝገብ ስር0 በዋና ወንጀል አድራጊነት ተጠርጥረው የተከሰሱት ብርጋዴል ጄነራል ጠና ቁርንዲ፣ሻለቃ ክንደያ ግርማይና ሌተናል ኮሎኔል አሰፋ ዮሐንስ ናቸው። በወንጀሉ ተባባሪነት ክስ የተመሰረተበት ቻይናዊ ሚስተር ዩሀን ዮን ደግሞ እስካሁን አልተያዘም። ተከሳሾቹ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘትና ለማስገኘት የኮርፖሬሽኑን የግዥ አፈፃፀ...
### Text: የ2 ወር ደሞዝ አልተከፈላቸውም የአፍሪሄልዝ ቴሌቪዥን ሰራተኞች የ2 ወር ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ተናገሩ። አፍሪሄልዝ ቴሌቪዥን ትኩረቱን በጤና ነክ ጉዳዮች ላይ በማድረግ ነበር በቅርቡ ወደ ተመልካቾች መድረስ የጀመረው።ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉት የዚህ ቴሌቪዥን ጣቢያው ሰራተኞች ለኢትዮ ኤፍ ኤም 1078 እንደተናገሩት ድርጅቱ በወቅቱ የሰሩበትን ደመወዝ እየከፈላቸው እንዳልሆነ ገልጸዋል። ሰራተኞቹ እንዳሉትም በድርጅቱ ከተቀጠሩበት ወቅት አንስቶ ደመወዛቸው በወቅቱ ተከፍሏቸው አያውቅም...
### Text: «የሽብርተኞቹን ጭንቅላት ማፍረሳችንን እንቀጥላለን» የቱርክ ፕሬዝዳንት ረቺብ ጣይብ ኤርዶኻን የኩርድ ታጣቂዎች በአሜሪካ አሸማጋይነት ተግባራዊ የሆነው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ከማብቃቱ በፊት ከሰሜን ምሥራቅ የሶርያ ክፍል ለቀው ካልወጡ «ጭንቅላታቸውን እንደሚያፈርሱ» ዛቱ። ፕሬዝዳንቱ በማዕከላዊ ቱርክ በምትገኘው የካይሴሪ ከተማ ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር ለ120 ሰዓታት የሚዘልቀው የተኩስ አቁም ስምምነት ተጨባጭ ለውጥ ካላመጣ አገራቸው የሶርያ ዘመቻዋን ትቀጥ...
### Text: የተመድ ፀጥታው ምቤት ስለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በህዳሴ ግድብ ላይ ሶስቱ አገራት ወደ ውይይት እንዲመለሱ ከማድረግ ውጪ ሌላ መፍትሔ እንደሌለ ገልጿል።በሐምሌ ወር የምክር ቤቱ ሰብሳቢ የሆኑት በተባበሩት መንግሥታት የፈረንሳይ አምባሳደር የሆኑት ኖኮላስ ደ ሪቪዬር ትላንት ለጋዜጠኞች ገለፃ አድርገዋል።በመንግስታቱ ድርጅት የፈረንሳይ አምባሳደር የሆኑት ኒኮላስ ደ ሪቬሪ በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በህዳሴ ግድቡ ላይ የገጠማቸውን አለመግባባት...
### Text: በርካቶችን ያስቆጣው ድርጊት ከትላንት ምሽት ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ አንዲት ሴት በፖሊስ ስትመታ የሚያሳይ ቪድዮ በስፋት እየተሰራጨ ነው።ድርጊቱ የተፈፀመው አዲስ አበባ ከተማ ጀሞ አካባቢ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርብ ነን ያሉ ግለሰቦች ያሳወቁ ሲሆን ድብደባው የተፈፀመው ከህፃን ልጅ ፊት ለፊት መሆኑም አስረድተዋል።የትኛውም የህግ አካል አንድ ዜጋ ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝ እንኳን በተገቢው ስነስርዓት ወደህግ ማቅረብ እንጂ ከልካይ የለኝም ብሎ በአደባባይ እንዲህ ያለውን ድርጊት ሲፈፅም መመልከት እ...
### Text: ዛሬ በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር የጣና ፎረም መካሄድ ጀምሯል።10ኛው የ ጣና ፎረም ጉባኤ በአፍሪካ የሰላም ፣ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር ሲሆን እስከ ጥምቅት 6 ቀን 2015 ዓም ድረስ ይቆያል።በባህር ዳር እየተካሄደ ባለው የጣና ፎረም ጉባኤ ላይ የኢፌዴሪ ጠሚ ዶር ዐቢይ አህመድ እና ምክትል ጠሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፣ የሶማሊያ ጠሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ ፣ የሱዳን የሉዓላዊ ምቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ...
### Text: ሻሸመኔ️በሻሸመኔ ከተማ ተፈፅሟል የተባለው ድርጊት ከወር በፊት በእርቅ የተፈታ ጉዳይ ነው፡ የከተማ አስተዳደሩበኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ የተፈፀመ ድርጊት በሚል የተለቀቀው አሰቃቂ ቪዲዮ ብዙዎችን በማህብራዊ ሚዲያ እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ሆኗል፡፡ኢቢሲ ወደ ሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ደውሎ በማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ ስለተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል ለማጣራት እንደሞከረው፣ ድርጊቱ የተፈፀመው በከተማዋ ይሁን እንጂ ከአንድ ወር ከ11 ቀን በፊት የተፈፀመ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡የ...
### Text: ታሪካዊቷ የላሊበላ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ በቁጥጥር ስር መዋሏን የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል።የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት የጋሸናን ግንባር ምሽጎችን በመሰባበር የአሸባሪውን አከርካሪ የሰበሩት የመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ልዩ ኃይል ፣ የአማራ ሚሊሻና ፋኖ ታሪካዊቷን የላስታ ላሊበላ ከተማንና የላሊበላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ተቆጣጥረዋል ብሏል።በአሁን ሰዓት የመከላከያ ሠራዊት ፣ የአማራ ክልል ልዩ ኃይ...
### Text: ከአርባ ምንጭ️ጋሞ ባይራኮጋሞይ ጊታኮዛሬ በተካሄደው የጋሞ ህዝብና የኦሮሞ ህዝብ ምክክርና ይፋ የምስጋና ፕሮግራም ላይ በርካታ የጋሞ ናቶዎችና በርካታ የኦሮሞ ቄሮዎች ተገኝተዋል።ከዛ ባሻገርም የጋሞ ወጋ አባቶች የኦሮሞ አባገዳዎች እርስ በእርስ ለእርቅ ድርድር ምቹ መንገድ ፈጥረዋል።በዛሬው ቀን ከተነሱ ሃሳቦች ውስጥ በቡራዩ በተነሳው እልቂት ቄሮ እጁ እንደሌለበት እናውቃለን ነገር ግን ቄሮ ይህንን የወንብዴ ግሩፕ ለማስቆም እንዴት ተሳነው የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል።በተጨማሪ...
### Text: ትግራይ ክልል️የቱርክ ባለሀብቶች በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን አደ ጉደም ከተማ በ750 ሚሊየን ዩሮ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነቡ ነው፡፡ባለሀብቶቹ የሚገነባውን ኢንዱስትሪ ፓርክ በተመለከተ ከከተማ አስተዳደርና የህብረተሰብ0 ክፍሎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ኢንዱስትሪ ፓርኩ በ500 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ወደ ስራ ሲገባ በዓለም ተወዳዳሪና አዲስ ቴክኖሎጂ ይጠቀማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የሕንጣሎ ወጀራት ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ ከለሌ ሓጋዜ ኢንዱስትሪ ፓርኩ ተገንብቶ አገልግ...
### Text: ከደምቢዶሎ ከጠፉት 17 ተማሪዎች፡ታግተዋል ከተባሉት ውስጥ 14ቱ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መሆናቸው 2 ተማሪዎች በግቢው ውስጥ መኖራቸው 2 ተማሪዎች ጎንደር እና ጎጃም ቤተሰቦቻቸው ጋር መመለሳቸው 10 ተማሪዎች በፍለጋ ላይ መሆናቸው የተቀሩት ስማቸው እየተጠቀሱ ያሉት ተማሪዎች ግን የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች አይደሉም ተብሏል፡፡ በግቢው ዉስጥ አሉ የተባሉት ሁለት ተማሪዎች ግን መኖራቸው የተረጋገጠው የመመገቢያ ካርዳቸው ባለፉት ቀናት በጥቅም ላይ መዋሉ ታይቶ ስለሆነ ተጨባጭ መሆኑ አጠ...
### Text: የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ መቐለ ቅርንጫፍ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 47 ጤና ተቋማት 18 ሚሊየን ብር የሚያወጣ0 የመደበኛ እና የጤና ፕሮግራም መድሀኒትና00 የህክምና ግብዓቶችን በቀጥታ በማድረስ ማሰራጨቱ ገለፀ።ቅርንጫፉ ለ21 ሆስፒታሎችና 26 ጤና ጣቢያዎች በቀጥታ ያሰራጨ ሲሆን ከእነዚህም መቐለ የሚገኙ 4 ሆስፒታሎች እና ሁሉም ጤና ጣቢያዎች፣ ለውቅሮ፣ ሀውዜን፣ ዓዲግራት፣ አክሱም ቅድስተ ማርያም፣ ኮረም፣ መኾኒና ሌሎች ሆስፒታሎች ይገኙበታል ።በሌላ በኩል በሰሜን እና በ...
### Text: የይስማዕከ ባለቤት ነኝ ያለች ሴት በአዲስ አድማስ ቀርባ የተናገረችው ነገር አስደንጋጭ ሆኖብኛል።ከዳነ በኋላ አብሬው ኖሬያለሁ በደንብ ያወራል እንደሚናገር በጣም ሠላም እንደሆነ አብረውት ያሉ የእርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ነን የሚሉት ታዋቂ አርቲስቶች እና ጓደኞቹ በደንብ ያውቃሉ አካውንቱ ውስት 400 ሺ ብር መግባቱን አረጋግጫለሁ ህዝቡ እየትጨበረበረ ነው።አራት ኪሎ ባሻ ወልዴ ነበር። ከእነቤት እቃው የኔንም የልጆቼንም ልብስ፣ የልጆች መኝታና መጫወቻ ሁሉ ሳይቀር የለም። ከዚያም እኔም የምሰ...
### Text: አብዲ ኢሌ️የሶማሌ ክልል አዲሱ ፕሬዚዳንት አህመድ አብዲ መሀመድ የቀድሞው ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሀመድ ኦማር ስልጣን እንዳስረከቡና ሽግግሩም በሰላም እንደተጠናቀቀ ለቢቢሲ ሶማልኛ ተናግረዋል።የክልሉ አዲሱ ፕሬዚዳንት እንደተናገሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ስልጣን ለመልቀቅ በመጠያቃቸው የስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ ጥያቄያቸውን ተቀብሎ አዲሱን የክልሉ ፕሬዚዳንት እንደመረጠም ገልፀዋል።ሰሞኑን ለብዙ ሰዎች መሞት፣ አብያተ ክርስትያናት መቃጠልና ንብረት መውደም ጋር ተያይዞም በክልሉ የመከላከያ ሰራዊ...
### Text: ወንጀል ነክ መረጃ️ስልክ በመንጠቅ ሊያመልጥ የሞከረዉ ወንጀለኛ በእስራት ተቀጣ። ተከሳሽ ዛኪር ቢላል በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 665 1 ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፉ ስርቆት በመፈፀሙ ክስ ተመሰረቶበታል።ተከሳሹ መጋቢት 12 ቀን 2011 ዓም በግምት ከምሽቱ 12፡30 ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው 05 ቀበሌ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ የግል ንብረትነቱ የተበዳይ ባህርያ ፈይድ የሆነ የዋጋ ግምቱ 1500 የሚያወጣ ሳምሰንግ ሞባይል ከተሳፈረችብት ታክሲ...
### Text: ሞጆ ጥቅምት 172012 ዓም ዛሬ ጠዋት በሞጆ ከተማ በተከሰተ ሁከት ሁለት ሰዎች በጥይት ተመተዋል። በከተማዋ ዛሬ ጠዋት የታሰሩ ሰዎች ከእስር ይለቀቁ በማለት ሰልፍ የወጡ ሰዎች ከመንግሥት ጸጥታ አስከባሪዎች ጋር ተጋጭተው በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማው ከንቲባ ወሮ መሰረት አሰፋ ለቢቢሲ ተናግረዋል።ቅዳሜ ሌሊት ላይም በከተማዋ በምሽት ሰልፍ ተካሂዶ እንደነበር ከንቲባዋ ተናግረዋል። ቅዳሜ ሌሊት ቤተክርስቲያን ተቃጥለ የሚል ወሬ ተናፍሶ ሌሊቱን ሁከት ተፈጥሮ ነበር። በንብረት...
### Text: የቻይና ጤና ባለሙያዎች በሰሜን ምሥራቅ የአገሪቷ ክፍል የተገኘው የኮቪድ19 ታማሚ ወረርሽኙ በዉሃን ሲጀምር ከታየው በተለየ መልኩ የበሽታ ምልክትና ምልክቱ ለመታየት ረዘም ያለ ጊዜ መውሰዱን መታዘባቸውን ተናገሩ።በቻይና ብሔራዊ ጤና ኮሚሽን የህክምና ቡድን ከሚገኙ የጽኑ ህሙማን ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ዶክተር ኪው ሃይቦ ለብሔራዊው ቴሌቪዥን ቡድኑ ስለታዘበው አዲስ ነገር ተናግረዋል።ዶር ኪው ቡድናቸው በሰሜን ምሥራቅ ሄሎንግጂያንግና ጂሊን ግዛት በኮቪድ19 ታማሚዎች ...
### Text: 6 ፓርቲዎች ወደሀገር ውስጥ ገቡ️ስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ወደ ሀገር ውስጥ ገቡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር ዐቢይ አህመድ ለተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ባደረጉት በሰላማዊ መንገድ የመታገል ጥሪ መሰረት ስድስት የተፎካካሪ ፓርቲ ወደ ሃገር ውስጥ ገብተዋል፡፡ ከውጭ ሃገር ከሰሜን አሜሪካና ከእንግሊዝ ስድስት ድርጅቶች በዛሬው ዕለት ወደ ሃገር ውስጥ ተጠቃለው መግባታቸው የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ ተናግረዋል፡፡ አክለውም ከውጭ ሃገር ከሰሜን አሜ...
### Text: ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴርሪፖርተር ጋዜጣ ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በአሁኑ ወቅት ህክምና የመስጠት አቅሙ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የደረሰ በመሆኑ የቅዱስ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሪፌራል ሆስፒታል በኮሮና ቫይረስ ለተያዙ ሰዎች ብቻ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ በመወሰኑ ሆስፒታሉ ነባር ታካሚዎችን ወደ ሌሎች የህክምና ማዕከላት ለማዛዋወር ዝግጁ ሆኗል ብሎ ያወጣው ዘገባ ሀሰት ነው። በአሁኑ ሰዓት በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ለኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ተብሎ የተዘጋጀው አልጋ ጋዜጣው እንዳለው 109 ሳይሆን 600 ...
### Text: የዜጎች መረጃን የማግኘት መብት እስከምን ድረስ ነው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት ረፕሮፌሰር ዶር ሙላቱ አለማየሁ ለሀገራዊ ደኅንነት ከሚያሰጉና በልዩነት ከሚቀመጡት ውጪ ያለ ማንኛውም መረጃ የህዝብ መረጃ ነው ተብሎ ይታሰባል። ይህ ሕግ ከላይ ከተጠቀሱት ውስን ገደቦች ውጭ ማንኛውም ሰው መረጃ ጠይቆ የማግኘት መብትን ያጎናጽፋል። ለምሳሌ አንድ ግለሰብ የህተምክር ቤት የተወያዩበትን ቃለ ጉባዔ አሳዩኝ ብሎ የመጠየቅ መብት ጭምር አለው። ይህ በግለሰብ ደረጃ መተግበር የሚገባው...
### Text: የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምቤት በአሸባሪነት የሰየመውን ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ሕወሓት የሽብርተኝነት ስያሜ ይነሳ አይነሳ በሚለው ጉዳይ ላይ ዛሬ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።በምክር ቤቱ ውስጥ የብልፅና አባላት ሕወሓትን ከአሸባሪነት ለመሰረዝ ያለመ ዝግ ስብሰባ ትናንት መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓም የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔን ጨምሮ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ዶር፣ እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አም...