text
stringlengths
707
989
### Text: የሲዳማ ብሔር ህዝብ ውሳኔ ውጤት አስመልክቶ ከወላይታ ዞን አስተዳደር የተላለፈ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ወላይታ ሶዶ ህዳር 132012 ዓምየሲዳማ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ ሆኖ የቆየው ራሱን በራስ የማስተዳደር በክልል የመደራጀት ህገመንግስታዊ ጥያቄ ከረጅም ጊዜ ትግልና መስዋትነት በኋላ የተገኘ በመሆኑ የወላይታ ዞን አስተዳደር የተሰማውን ታላቅ ደስታ በዞኑ መንግስትና ህዝብ ስም ይገልጻል፡፡የወላይታና የሲዳማ ወንድም ህዝቦች ለዘመናት አብሮ የኖሩ፣ አንድ ትውልድ በሌላው ትውልድ ስተ...
### Text: በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የኢትዮጵያ መንግስትን ወልክለው ፊርማቸውን ያኖሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከዛሬው የናይሮቢው ስምምነት በኃላ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።አምባሳደር ሬድዋን ከዛሬው የቀጠለ ውይይት በወታደራዊ ኃላፊዎች መካከል የዛሬ ወር ገደማ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ ላይ ሊደረግ እንደሚችል ጠቁመዋል።ዋናውና የውይይቶቹ ፍፃሜ ደግሞ በፈረንጆቹ አዲስ አመት አዲስአበባ ላይ ሊደረግ እንደሚችል ገልፀዋል።የናይሮቢው ውይይት በተጀመረበት ዕለት...
### Text: የአቅም ማሻሻያ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና0 ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ ጊዜ ብቻ0 የሚያገለግል የአቅም ማሻሻያ እንዲተገበር መወሰኑ ይታወቃል። በዚሁ መሰረት በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍ...
### Text: ነገ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባ አዲስ አፈ ጉባኤ እንደሚመርጥ ይጠበቃል፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሚያቀርቧቸውን እጩ የካቢኒ አባላቶች ሹመት ምክር ቤቱ በነገው እለት እንደሚያጸድቅም ፋና ብሮድካስተንግ ኮርፖሬት ዘግቧል፡፡የምክር ቤቱን መዶሻ ከክቡር አባዱላ ገመዳ እጅ ተረክበው አዲሱ አፈ ጉባኤ በመሆን የሚሰየሙት ወሮ መፍሪሂት ከሚል ስለመሆናቸው ምንጮች ለድሬቲዩብ ገልጸዋል፡፡ በአዲሱ የጠቅላይ ሚንስትሩ ካቢኒ ውስጥ የፌድራል ም...
### Text: ሰበር ዜና የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የዶክተር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ የ62 ተከሳሾችን የክስ ሂደት ማንሳቱን አስታወቀ።ተከሳሾቹ የወንጀለኛ መቅጫ ህግን አንቀጽ 464 እና 494 በመተላለፍ ጉዳያቸው በፍርድ ሂደት ላይ ያለና እንዲከላከሉ ብይን የተሰጠባቸው ናቸው።ኢዜአ ከፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ባገኘው መረጃ መሰረት በእነ አበበ የኋላ የክስ መዝገብ የተጠቀሰውን አንቀጽ በመተላለፍ ጉዳያቸው በፍርድ ሂደት ላይ ያሉ 18 ተከሳሾች ክስ እንዲነሳም ተወስኗል።በእነ ማስረሻ ሰጠኝ መዝገብ በፌዴራል...
### Text: ጊፋታ2012 የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ግፋታ በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ቅድመዝግጅት መጠናቀቁን የወላይታ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ፡፡ በበዓሉ አከባበር የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡የወላይታ ህዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር የነበረውን አንድነት በይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል በዞኑ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ የጉዞ ግፋታ ልዑካን ቡድን ወደተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች መጓዛቸውን ተነግ...
### Text: የትንሳኤ ሎተሪ ወጣትንሳኤ ሎተሪ ቅዳሜ ሚያዝያ 23 2013 ዓም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል 1ኛ 5000000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 01488062ኛ 2500000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 04188753ኛ 1250000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 07795944ኛ 600000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 1653940 5ኛ 3000...
### Text: ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ️የቀድሞዋ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ አመራር የነበሩት ወት ብርቱካንሚዴቅሳ ቅንጅት የፈረሰበትን ትክክለኛ ምክንያት ለማናገር አልፈልግም አሉ። ወደ አገር ቤት ከተመለሱ በሁዋላ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ሰፋ ያለ ቃለ መጠይቅ ያደረጉት ወት ብርቱካን ቅንጅት የፈረሰበት ትክክለኛ ምክንያት ምንድን ነበር ተብለው ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ እውነት ለመናገር አሁን ይሄንን ጥያቄ ልመልስ አልፈልግም፡፡ ልመልስ የማልፈልገው መልስ ስለሌለኝ ወይም ደግሞ ምክንያቱን ...
### Text: 1859 ተማሪዎችን አስመረቀ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 353 ሴት ተማሪዎችን ጨምሮ 1859 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡በመልዕክታቸውም በዩኒቨርስቲ የሚታዩ በዘርኝነት የሚከሰቱ መጠፋፋቶች ኋላ ቀር አስተሳሰብ በመሆናቸው ይህ ትውልድ መፍቀድ የለበትም ብለዋል፡፡ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒ...
### Text: ዶክተር ቴድሮስ ከዢ ጂንፒንግ ጋር መክረዋልየዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ወደ ቻይና አቅንተው ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በሚደረጉ ጥረቶች ላይ በዛሬው ዕለት መክረዋል።ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ቻይና ሙሉ አቅም እና በራስ መተማመን እንዳላት ለዶር ቴድሮስ አድኃኖም ገልጸውላቸዋል።ዢ ጂንፒንግ እንደተናገሩት ቻይና በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱን ለመከላከል ከምንም ነገር በፊት ቅድ...
### Text: ዛሬ ይፋ በተደረገው የተማሪዎች ምደባ ላይ ቅሬታ አለን ያሉ ወላጆች እና ተማሪዎች መልዕክታቸውን እያደረሱ ይገኛሉ ዛሬ የአዲስ ተማሪዎችን ምደባ ይፋ ያደረገ ሲሆን ምደባቸውን የተመለከቱ አንዳንድ ተማሪዎች እና የተማሪዎቹ ወላጆች ቅሬታ እንዳለባቸው ገልፀዋል። ባስቀመጠው የቅሬታ መቀበያ አድራሻ ድህረገፅ ቅሬታቸውን እንደሚያሳውቁ ገልፀው ተገቢው ምላሻ እንዲሰጣቸውም አሳስበዋል።ከውጤታ ጋር የፈለጉት ምርጫ አልተሰጠኝም ያለ አንድ የቲክቫህ አባል በሀገር አቀፉ ፈተና ከ630 በላይ ቢያመጣም...
### Text: የፌዴራል መንግስት የሰብአዊ ዕርዳታ እንዲርደስ ለማስቻል አልሜ ያደረኩት የተናጠል የተኩስ አቁም በሕወሃት ትንኮሳ መደናቀፉን ቀጥሏል ብሏል።በትግራይ ክልል በሚገኙ መጋዘኖች ውስጥ ከ400000 ኩንታል የሚበልጥ ስንዴ እና ከ25 ሚሊዮን ሊትር የሚበልጥ የምግብ ዘይት መቀመጡን ገልጿል።የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል ያሉት ዜጎቻችን ደህንነት ያሳስበኛል ያለ ሲሆን ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ በተለይም ደግሞ በትግራይ ድጋፍ በመስጠት ላይ የሚገኙት፣ ህወሓት የአፋርን ክልል መተናኮሱን አ...
### Text: በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ተከሄደው ጦርነት መቋጫ የሆነው አልጀርስ ስምምነት እንዲፈረም ሚና የነበራቸው የቀድሞ የአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብደላዚዝ ቡተፍሊካ በ84 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።በፈረንጆቹ 1999 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ቦተፍሊካ እጅግ ከባድ የሚባለውን የኢትዮኤርትራ ግጭት አንዲፈቱ ሃላፊነት ተጥሎባቸው ነበር፡፡በሁለቱ ሀገራት መካከልም ስምምነት እንዲፈረም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።ቦተፍሊካ በፈረንጆቹ ሚያዚያ 2019 ...
### Text: ቃላት እንደሚያድኑት እንደሚያፅናኑት ሁሉ ቃላት ለማጥፋትም ስሜትን መቀስቀስ ይችላሉ ዶክተር ፀደይ ወንድሙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በ2011 ዓም ላይ እጅግ እየተባባሰ የመጣው የ ጥላቻ ንግግር በሀገሪቱ ላይ ስለሚያመጣው የከፋውድመት በመረዳት በኦሮሚያ ፣ በአማራ ፣ በትግራይ ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ክልሎች በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከጥላቻ ንግግሮች እንቆጠብ 0 በሚል ዘመቻ አካሂዶ ነበር።በወቅቱ ወደ ትግራይ ፣ መቐለ ...
### Text: ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገሪቱ ያሉ ችግሮች በውይይት እና በስምምነት እንዲፈቱ በድጋሚ ጥሪ አቀረበች።ይህ ጥሪ የቀረበው ቅዱስ ሲኖዶስ የጥቅምት 2016 ዓም ጉባኤውን ካጠናቀቀ በኃላ ባወጣው መግለጫ ነው።ቅዱስ ሲኖዶስ ትላንት በሰሜኑ ኢትዮጵያ የሀገራችን ክፍል በተካሄደው ጦርነት በጠፋው የሰው ሕይወትና በወደመው ንብረት ከደረሰብን ሐዘን እኛ ኢትዮጵያውያን ገና ሳንጽናና ዛሬም በሀገራችን ኢትዮጵያ በበርካታ አካባቢዎች የተከሰቱት ጦርነቶች፣ ግጭቶችና ...
### Text: በትናንትናው ዕለት በተባበሩት መንግስታት በአቢዬ ጊዜያዊ የደኅንነት ሀይል ግቢ ውስጥ በሂሊኮፍተር አደጋ ህይወታቸው ያለፈው ኢትዮጵያውያን የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሰራዊት አስክሬን ዛሬ ጠዋት ወደ አዲስ አበባ መሸኘቱ ተገለጸ፡፡ የሱዳንና በደቡብ ሱዳን ተወካዮች ለተጎጂ ቤተሰቦች የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡ ሂሊኮፍተሯ ትናንት የተከሰከሰችው 23 የሠላም አስከባሪ አባላትን አሳፍራ በአካባቢው ቅኝት እያደረገች ሳለ መሆኑና ምክንያቱ እስካሁን አለመታወቁን ሲጂቲኤን ዘግ...
### Text: ከንፈር በመምጠጥ ለውጥ አይመጣም አቶ እንድግዳ ማንደፍሮ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እጅግ በርካታ ሰዎች እገዛ ያስፈልጋቸዋል።በትግራይ ክልል ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ፣ በደቡብ ክልል በኮንሶ፣ አሌና ደራሼ አሁንም ከፍተኛ እርዳት የሚፈልግ ሰው ቁጥር አለ።እየተደረገ ያለው ድጋፍ ከእርዳታ ፈላጊው ቁጥር ጋር ሲነፃፀር ገና የሚቀረው በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ እየቀረበ ይገኛል።ማህበረሰቡ የቻለውን ያህል ድጋፍ ማድረግ አለበት።ምግብ ፣ ለህፃናት የአልሚ ...
### Text: ከመርሳ፣ ከወልዲያ እና ከውርጌሳ አካባቢ በርካታ ሰው በስፋት እየመጣ ነው እሱን እየለየን ወደ ማረፊያ ቦታ እየገቡ ነው አቶ አበበ ገመስቀል የደሴ ከንቲባእየተካሄደ የሚገኘውን ጦርነት በመሸሽ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከሰሜን ወሎ ወደ ደሴ ከተማ መግባታቸውን የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገመስቀል ተናገሩ።አቶ አበበ ይህንን ያሳወቁት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ነው።ቀደም ብሎ ከ4 አስከ 5 ሺ የሚሆኑ ሰዎች ከሰሜን ወሎ የተለያዩ አካባቢዎች ወደ ደሴ ከተማ ገብተው ነበር ...
### Text: ወንጀል ነክ መረጃ️ከባድ የውንብድና ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ። ተከሳሽ እስጢፋኖስመለሰ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 010203 ክልል ልዩ ቦታው መርካቶ ለይላ ህንፃ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ግንቦት 21 ቀን 2008 ዓም ከቀኑ 6፡30 ሲሆን በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 6711ለ ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ተከሳሽ የማይገባውን ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ ካልተያዘው ግብራበሩ ጋር በመሆን የግል ተበዳይፋሲል ማሞ የተባለ...
### Text: አንጋፋው የኢትዮጵያ አርቲስት ክቡር ዶር አሊ ቢራ በህይወት አለ።በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አንጋፋው የሀገራችን አርቲስት ክቡር ዶክተር አሊ ቢራ አረፈ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።ክቡር ዶር አርቲስት አሊ ቢራ ባጋጠመው የጤና እክል የተነሳ በአዳማ ጄነራል ሆስፒታል ለላፉት ቀናት የሕክምናክትትል እየተደረገለት ይገኛል።የ75 ዓመቱ አርቲስት አሊ ቢራ ከዚህ ቀደምም የጤና እክል አጋጥሞት በአዲስ አበባ እና አዳማ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታ...
### Text: በትናንትናው ዕለት በአዲስአበባ ዙሪያ በቡራዩ፣ አሸዋ ሜዳ፣ ከታ እና ፊሊ ዶሮ አካባቢ በንፁሀን ዜጎች ላይ በተፈጸመውን ግድያ ብዙ ወገኖቻችን ተፈናቅለው በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ። ፊሊጶስ ሚኪሊላንድ ቃሌ ብስራት ጉለሌ ፋና አወሊያ ፊትአውራሪ መድሀኒያለም ትቤትእንዲሁም ሌሎችበነዚህ ትምህርት ቤቶች የተጠለሉ በብዙሺህ የሚጠጉ ዜጎቻችን አስቸኳይ የምግብ የህጻናት ምግቦች እና ዳይፐር እና የአልባሳት እርዳታ ያስፈልጋቸዋል በተጨማሪም...
### Text: አሳዛኝ ዜና️በጅማ ከተማ በተከሰተ የአፈር መንሸራተት የ3 ሰዎችን ህይወት መለፉን ፖሊስ አስታወቀ።የጅማ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የኮሙዩኒኬሽን ዲቪዚዮን ኃላፊ ኢንስፔክተር ገዛኸኝ አውግቻው እንደገለጹት አደጋው የደረሰው አንድ ሲኖትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ትናንት ቀን አስር ሰዓት አካባቢ በቦቼ ቦሬ ቀበሌ ቺሻየር በተባለው ሰፈር የደፋው አፈር መኖሪያ ቤት ላይ በመደርመሱ ነው፡፡አፈር ተደርምሶ የመኖሪያ ቤት በመጫን ባስከተለው አደጋ የ3 ሰዎችን ህይወት መጥፋቱ የተገለጸ ሲሆን ከሟቾቹ መካከ...
### Text: በኢትዮጵያ የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ 3 መተግበሪያዎች በዚህ ሳምንት ይፋ ሆነዋል።መተግበሪያዎቹ ይፋ የሆኑት በ ዚ ትራክ የትራንስፖርት አገልግሎት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር ነው።ዚ ትራክ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት በሞባይል ስልክና በኮምፒውተር ላይ ተጭነው የሚሰሩ ሶስት መተግበሪያዎችን ሰርቶ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።መተግበሪያው በሀገራችን ውስጥ ያለውን የሎጀስቲክ አሰራር የሚያሻሽሉና የሚያቀሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጅን በመጠቀም...
### Text: የመንግስት ኮሚኒኬሽን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ዛሬ 74 ዕርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በአባአላ መንገድ በኩል ወደ ትግራይ ክልል መላካቸውን አስታውቋል።በ3ኛ ዙር ወደ ትግራይ ክልል ከተላኩት ተሽከርካሪዎች ውስጥ 6ቱ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ናቸው ብሏል።የኢትዮጵያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ በትግራይ ክልል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደርሳቸው ለማድረግ የገባውን ቃል በማክበር ምቹ የሰብአዊ ዕርዳታ ማጓጓዣ ሁኔታን ለመፍጠር እ...
### Text: ለሁሉም አዲስ ወደ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የመጀመርያ ዓመት ተማሪዎች ከሁሉም በማስቀደም ወደ ዩኒቨርሲቲያችን ስለተመደባችሁ እንኳን ደስያላችሁ። ዓዲግራት ውብና ተወዳጅ ከተማ ስትሆን ከኣዲስ ኣበባ በስተሰሜን በኩል ወደ 900ኪሜ ያህል ርቃ የምትገኝ ናት። ከመቐለ 120ኪሜ በስተሰሜን በኩል ተግኛለች።በኣውሮፕላን እስከ መቐለ ለምትምጡ እስከ መነሃርያ ብላችሁ ታክሲ በመያዝ ከመነሃርያ ወደ ዓዲግራት በህዝብ ማመላለሻ በ4050 ብር ኣከባቢ ወደ ዓዲግራት መነሃረያ ወይም ወደ ...
### Text: ሮሜሎ ሉካኩ ከትላንት ምሽት የዘረኝነት ጥቃት በኋላ ያስተላለፈው መልዕክት ባሳለፍነው ወር በርካታ ተጫዋቾች የዘረኝነት ጥቃት ደርሶባቸዋል። እኔም በትላንትናው ዕለት የጥቃቱ ገፈጥ ቀማሽ ሆኛለው። እግር ኳስ ሁሉም የሰው ዘር በእኩል የሚዝናናበት ጨዋታ ነው አንዱን ከሌላው ማግለል የምንወደውን ጨዋታ ዝቅ ያደርገዋል። በሁሉም ሀገራት የሚገኙ የእግርኳስ ፌዴሬሽኖች ለእንደዚህ አይነት ማግለል ጠንከር ያለ እርምጃ ይወስዳሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለው። የማህበራዊ ትስስር አውታሮች ኢንስታ...
### Text: ሲአይኤ መፈንቅለ መንግሥት አሲሮብኝ ነበር የኤርትራ መንግስትየኤርትራ መንግሥት ትላንት አርብ ባወጣው ያልተለመደ መግለጫ ሲአይኤን በመፈንቅለ መንግሥት ሽረባ ይከሳል። የእስራኤል የስለለ መረብ ሞሳድንም ስም በማጥፋት ተባብሯል ይላል።የኤርትራ መንግሥት ይህን ስኢረ መንግሥት ተሸርቦብኝ ነበር የሚለው በፈረንጆች 2011 ላይ ነው። ይህንኑ የተመለከተ ሁነኛ ምሥጢራዊ መረጃ እጄ ገብቷል ብሏል።ምስጢራዊው የመፈንቅለ መንግሥት ሴራው በኤርትራ ውስጥ ልክ እንደ አረቡ ጸደይ ዓይነት ሕዝባዊ ተቃውሞና ...
### Text: ኢራን የአውሮፕላን አደጋውን በቪድዮ የቀረፀውን ሰው በቁጥጥር አውላለችኢራን የአውሮፕላን አደጋውን በምስል የቀረጸውን ሰው በቁጥጥር ስር አውላለች፡፡ አውሮፕላኑ በሚሳኤል ተመቶ ሲወድቅ በምስል ያስቀረውን ሰው በቁጥጥር ስር ማዋሏን ነው ኢራን ያስታወቀችው፡፡ ግለሰቡ ከብሄራዊ ደህንነት ጋር በተያያዘ ክስ ይመሰረትበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የበረራ ቁጥሩ 752 የሆነው ይህ አውሮፕላን ባለፈው ሳምንት ረቡእ እለት ነበር ከቴህራን ከተነሳ በኋላ በሚሳኤል ተመቶ የተከሰከሰው፡፡ ኢራን ድርጊቱ በስህተት...
### Text: በትግራይ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች 28 ሚሊዮን ማስክ ይከፋፈላል ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያየትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ስርጭትን በተመለከተ ክልሎች ለተማሪዎቻቸው ተረክበው እንዲያሰራጩ የሚገልጽ እና ድልድሉንም አስመልክቶ የጊዜ እና የመጠን ዝርዝር ያለው ደብዳቤ ለክልል ትምህርት ቢሮዎች ጽፏል፡፡ በዚህ ደብዳቤ ውስጥ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ አልተካተተም፡፡ ይህም በበርካቶች ዘንድ ጥያቄ ፈጥሯል፡፡ጉዳዩን በተመለከተ ሚኒስቴር መስሪያ ቤ...
### Text: ትምህርት ቤቶች ዳግም ሊዘጉ የሚችሉበት እድል አለ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮበትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶች በአግባቡ ተግባራዊ ባለመደረጋቸው ትምህርት ቤቶች ዳግም ሊዘጉ የሚችሉበት እድል መኖሩን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።ትምህርት ቢሮው ይህን ያሳወቀው በባህር ዳር ከተማ እንድናገለግሎ ማስክዎን ያድርጉ የሚል ንቅናቄ በተጀመረበት ወቅት ነው።በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶች ተገቢው ጥንቃቄ እየተደረገ ትምህርት እንዲቀጠሎ...
### Text: ከኢትዮጵያ ያመለጠው ኤርትራዊ ሰው አዘዋዋሪ ኪዳኔ ዘካሪያስ ሀብተማርያም በኔዘርላንድስ በጥብቅ ከሚፈለጉ ዝርዝር ውስጥ ተካተተ።የኔዘርላንድስ ዐቃቤ ሕግ ኤርትራዊውን በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪነት የሚፈለገውን ኪዳኔ ዘካርያስ ሀብተማርያምን በሕግ በጥብቅ ከሚፈለጉ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ አካቶታል።ኪዳኔ ዘካርያስ ሀብተማርያም ከሚቀርቡበት በርካታ ክሶች መካከል ግድያ፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ መጠቀም የሚሉት ይገኙበታል።የኔዘ...
### Text: ወላጆች ልጆቻቸው እንዲመለሱ ጠይቀዋልልጆቻቸውን ለትምህርት ወደቻይና የላኩ ወላጆች መንግስት ወደ አገራቸው እንዲመልሳቸው ጠይቀዋል። በቻይና በተለይም በዉሃን ግዛት ከ300 በላይ ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች የሚገኙ ሲሆን መንግስት እነዚህን ተማሪዎቸ ወደ አገር ያስመልስልን ሲሉ ወላጆቻቸዉ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡የተማሪ ወላጆችበጭንቀት ዉስጥ ነን መንግስት ልጆቻችንን ይመልስልን በሰው አገር በረሃብ እና በበሽታ ሊያልቁብን ነው ሲሉ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝተው በአካል ጠ...
### Text: ነሃሴ 182012 ዓም የኢትዮጵያ የኮቪድ19 መረጃዎች 2 ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 601 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 78 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰድ ህይወት አልፏል።በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 22 ከሀዋሳ ከተማ 16 ከወንዶ ገነት ወረዳ 8 ከይርጋለም ከተማ 6 ከአለታ ጩኮ ከተማ ይገኙበታል።አጠቃላይ በሲዳማ 1206 በቫይረሱ የተያዙ 14 ሞት 328 ያገገሙ በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 849 የላብራቶሪ ምርመራ...
### Text: ዙምባዌ️በዚምባቡዌ የተቀሰቀሰውን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር የተሰማሩ የጸጥታ ኃይሎች ቤት ለቤት በሚያደርጉት አሰሳ ሴቶችን አስገድደይደፍራሉ ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ወነጀሉ። መንግስት እየወሰደ ያለው ኃይል የተቀላቀለበት እርምጃ መቀጠሉ ተነግሯል።ቁጥራቸው በርከት ያሉ ሴቶች በጸጥታ ኃይሎች አባላት እንደሚደፈሩ የሚያመለክቱ የሚረብሹ መረጃዎችን ተቀብለናል ሲሉ የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ሂዩማን ራይትስ ዎች የደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ዴዋ ማሂንጋ ለአሶሴትድ ፕሬ...
### Text: ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስረኞች አመለጡ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዞን አንድ በነፍስ ግድያ ጥፈተኛ ተብለው በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የነበሩት 2 ታራሚዎች አሸናፊ መለሰ ሳሙኤል መካ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ ም ከረፋዱ 3 እስከ 4 ባለው ሰአት ውስጥ ከማረሚያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ያመለጡ ሲሆን ኤፍሬም ገ ጊዩርጊስ የተባለ ሌላ እስረኛ ደግሞ ለህክምና ወደ ሆስፒታል ሲወሰድ ከመኪና ላይ ዘሎ ማምለጡን ተሰማ፡፡ ማረሚያ ቤቱ የሁለቱ የታራሚዎቹን ማምለጥ ማታ በቆጠራ ሰአት እንዳወቀ ዋ...
### Text: የኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ምላሽበጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረትየሙዚቃ መሳርያ ያለበት የዩኒቨርሲቲ ምርቃት ፕሮግራም እንዲሁም የእነ እስክንድር ፕሮግራም አጠገብ ለአጠገብ ባሉ የአዳራሽ ክፍሎች ተገጣጥሞብን ነበር። የዩኒቨርሲቲው ፕሮግራም ቀደም ብሎ የተያዘ የነበረ ሲሆን ይሄኛው ግን በሁዋላ ላይ የተያዘ ነበር ፣ እርግጥ ሁለቱንም አንድ ላይ መቀበል አልነበረብንም። ትናንት ማታ ደውለን ሌላ ቀን በፈለጋችሁበት ቀን አድርጉት፣ አለበለዛ የሙዚቃ መሳርያ ያለበት ፕሮግራም አጠገባችሁ ያለ አዳራ...
### Text: ማስረጃ ካገኘን ነገ ጥዋት እናነሳለን ዶር ዐቢይ አህመድጠቅላይ ሚኒስትር ዶር ዐቢይ አህመድ ካቢኔያቸውን ለምክር ቤቱ አቅርበው አፀድቀዋል።እጩዎች ሹመታቸው ከመፅደቁ በፊት በምክር ቤቱ አባላት አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ቀርበው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።አንድ አስተያየት የሰጡ የምክር ቤት አባል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት እጩዎች 95 በመቶ አስደሳች መሆኑን ገልፀው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚኒስትሮቹን ሲመርጡ ካነሷቸው ነጥቦች ሌብነትን የማስቀረት ጉዳይ አንዱ መሆኑ...
### Text: እኛ ለጎንደር ከተማ እና ለህዝቡ ክብር አለን 0 አቶ ኢሳያስ ጅራየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዛሬው ዕለት የምርጫ የጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስብሰባ አዳራሽ በማካሄድ ላይ ይገኛል ።ምርጫው ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ለምን ተቀየረ ይሄ አስተዳደራዊ ጉዳይ ነው ያሉት የወቅቱ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ጣልቃ ገብነቶች እና ሂደቶችን ስላየን ቦታውን ቀይረናል ፣ ውሳኔውን አስተላልፈን ለስራ አስፈፃሚ አቀረብን ሂደቱን ጠብቀን ነው ...
### Text: በሀገራችን የስኳር እጥረት እንዳለ የሚታወቅ ነው። ኢቢሲ ዛሬ ስኳር ማብዛት ለካንሰር ያጋልጣል ብሎ በፌስቡክ በለጠፈው የጥናት ውጤት ኢትዮጵያዊያን አዝናኝ አስተያየቶችን ሲሰጡ ውለዋል እኔም ለእናተ ጥቂቱን መረጥኩላችሁ ኧረ በቃ ይቅርብና ውጪ ይሸጥና አለምን በካንሰር ጨርሱት እኛ ጤና እንሁን።እንኳን ጠፋ ስኳር የታባቱ ድሮም ያለምክንያት አልጣፈጠም። ወዴት ወዴት ነው ነገሩ ምነው የመብራቱን ጥናት ረሳችሁትሳ መብራት አዘውትሮ ማብራት ለትራኮማ ያጋልጣል ይላሉ አንዳንድ ጥናቶች ሃሃሃሃ ድ...
### Text: ተመራቂ ተማሪዎች ለሀገር በመስራት ብድሯን መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 9 ሺህ 637 ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ንግግር አድርገዋል፡፡በንግግራቸውም ወላጆች ማየት የሚፈልጉት የተመራቂ ተማሪዎችን ስኬት ነው ያሉ ሲሆን ተመራቂ ተማሪዎችም ወላጆቸውን ማስታወስ ይገባቸዋል ብለዋል።እንዲሁም ከታችኛው የትምህርት ደረጃ ጀምሮ ያሉ መምህራኖቻቸውን ሊያስታውሱ እንደሚገባ እና እነሱን ሊያስደስቱ የሚችሉ ተግባራትን...
### Text: ዶር አብይ ግብፅን አስጠንቅቀዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ባሰሙት ንግግር የ«ታላቁ ህዳሴ ግድብ»ን በተመለከተ ግብጽን አስጠነቀቁ። ግድቡ የማንንም ጥቅም ለመንካት ሳይኾን ኢትዮጵያ የሚገባትን ጥቅም ለማግኘት የሚከወን መኾኑን አስገንዝበዋል። በግብጽ በኩል ግድቡን በተመለከተ ቀደም ሲል ስለተሰጠው ማስጠንቀቂያ ሲናገሩም አስፈላጊ ከኾነ ኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶቿን ለጦርነት ማሰለፍ እንደምትችል አሳስበዋል።«አንድ አራተኛው የኢትዮጵያ ሕ...
### Text: ችሎት ብርጋዴርጄነረልተፈራማሞ የአብክመ ጠቅላይ ፍቤት ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ተመልክቷል።በዚህም የጊዜ ቀጠሮውን ጉዳይ መርማሪ ፖሊስ ምርመራየን ጨርሸ የምርመራ መዝገቡን ለዐቃቢ ህግ ለመላክ በዝግጅት ላይ ነኝ ያለ ሲሆን የክልል ዐቃቤ ህግ በችሎት ቀርቦ አዎ ምርመራው አልቋል የክስ መመስረቻ ጊዜ 15 ቀናት ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል።የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው ምርመራ ካለቀ ደንበኛችን የተከሰሱበት ጉዳይ ዋስትና የ...
### Text: የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠሚ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በጣና ፎረም የተናገሩት ያለፈው ታሪካችን ሊያስተምረን ይገባል ስለችግሮቻችን ማንንም አንወቅስም መውቀስ ካለብን ራሳችንን ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ በአክሱም ዘመን የነበረንን ስልጣኔ ተመልከቱ በግብጽ የነበረንን የቀደመ ስልጣኔ አስቡ ችግራችን የነበረንን ጥንታዊ ስልጣኔ እና ታሪክ በተገቢው መንገድ ለልጆቻችን አለማስተማራችን ነበር። አሁን ግን ለልጆቻችን ከማስተማራችን በፊት ስለራሳችን የተሳሳተውን እይታችን ማረም ይገባናል።አዎ ላለ...
### Text: መምህራኑ ወደ ተቋማቸው እንዲመለሱ ጥሪ ተደረገ።በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ተመድበው የነበሩ የኣክሱም እንዲሁም የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መምህራን ወደ ተቋማቸው እንዲመለሱ ጥሪ ተደርጓል።አክሱም ዩኒቨርሲቲ ተቋርጦ የቆየውን ትምህርት ለመጀመር የሚያስችለውን የቅድመ ዝግጅት ሥራ ማጠናቀቁን ሐምሌ 202015 ዓም ለትምህርት ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ አሳውቋል።በመሆኑም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ተመድበው የነበሩ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ መምህራን የአገልግሎት ጊዜና የተከፈላቸውን ደመ...
### Text: ከአዲስ ቸኮል️አሁን መረጋጋት ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡ ቁጣን የሚቀሰቅሱና ወደጎዳና መውጣትን የሚያበረታቱ ፅሑፎች ጉዳት እንጂ ጠቀሜታ የላቸውም፡፡ በተፈፀመው ግድያ ዙሪያ የየራሳችን ትንታኔዎች ይኖሩናል፡ የምዝበራ ሚስጥር እንዳያወጣ ነው የጠሚ አብይ ጉዞን ለማደብዘዝ ነው በኢንጂንሩ ቦታ ሌላ ሰው ለማስቀመጥ ተፈልጎ ነው እርስ በርስ በጥርጣሬ እንድንተያይና ወደግጭት እንድንገባ ነው ኦሮማራን ለማፍረስ ነው የግብፅ ሴራ ነው፣ ብዙ መላምቶች አሉ፡፡ አንድና ከዚያ በላይ ለልባችን የቀረ...
### Text: በጄዳ የሹሜሲ ዲፖርቴሽን ማዕከል ከገቡ በኃላ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በተለያዩ ሆስፒታሎች ውስጥ ህይወታቸው ያለፈ የኢትዮጵያ ዜጎችን የሚያውቃቸው ቤተሰብ ፣ ዘመድ እና ጎደኞች ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠየቀ።ከዚህ በታች የሟቾች ስም አስክሬናቸው የሚገኝበት ሆስፒታል የተገለፀ ሲሆን የምታውቋቸው ሰዎች በቢሮ ቁጥር 13 ቀርባችሁ ሪፖርት እንዲያደርጉ በጄዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅቤት አሳውቋል። ሂክመት መሀመድ የአስክሬን መገኛ ሸርቅ ጂዳ ሆስፒታል ከዲጃ ማህመድ የአስክሬን መገኛ...
### Text: የአፍሪካ ህብረት የጸጥታው ምክር ቤት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በህብረቱ ልዩ መልዕክተኛ ኦባሳንጆ ገለጻ እንደተደረገለት አል ዐይን በድረገፁ አስነብቧል።ህብረቱ ዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓም አስቸኳይ ዝግ ስብሰባ አካሂዷል፡፡ ስብሰባው በበይነ መረብ የተካሄደ እንደነበር ተገልጿል።በስብሰባው ላይ የህብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዲዎዬ፣ የህብረቱ የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት0ኦሊሴገን ኦባ...
### Text: የ2014 ዓም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።ለዚህም ተማሪዎች እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል።የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ ለኦቢኤን በሰጡት ቃል በአጠቃላይ በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።ፈተናውን ከሚወስዱት ውስጥ የማህበራዊ ሳይ...
### Text: መከላከያሰራዊት የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጽንፈኛ ሀይሎችንና ህገወጦችን በመታገል የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት እንደሚያረጋግጥ አስታወቀ፡፡ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታና በሰራዊቱ ውስጣዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄደዋል፡፡ በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮችና በሰራዊቱ ውስጣዊ ሁኔታ ላይ አተኩሮ የተካሄደውን ውይይት ያስጀመሩት የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አደም መሀመድ ናቸው፡፡ ከፍተኛ አመራሮቹ በቅርቡ በተቋሙና በአማራ ክልል አመራሮች ላይ ...
### Text: 0 በትግራይ የሰብዓዊ ረድዔት ሠራተኞች ችግር ላይ ያሉ ማህበረሰቦችን ለመድረስ በሚያደርጉት እንቅስቃሴዎች ላይ የሚገጥማቸው መሰናክል ተባብሷል ሲል የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ አሳስቧል።አጣዳፊ የምግብ እርዳታ ከሚያስፈልገው 52 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ከመጋቢት ወር መጨረሻ ወዲህ ለመድረስ የተቻለው 18 ሚሊዮኑን ብቻ ነው ብሏል።በክልሉ አሁን ካለው የከፋ የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት እንዳይከሰት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ያስታወቀው ኦቻ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ...
### Text: በናይጄሪያ አንድ የ40 ዓመት ጎልማሳ በዝንጀሮ ፈንጣጣ መሞቱን የሀገሪቱ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ትላንት ምሽት አስታውቋል።ይህ ሞት በዚህ ዓመት በሀገሪቱ ከተመዘገበው አጠቃላይ 21 ኬዝ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 21 ሰዎች መካከል ነው። በናይጄሪያ ከሚገኙት 36 ግዛቶች ዘጠኙ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ተመዝግቦባቸዋል።በሌላ በኩል በኮንጎ በ2022 9 ሰዎች በበሽታው መሞታቸው ሪፖርት መደረጉን ዋሽንግተን ፖስት አስነብቧል።ከግንቦት መጀመሪያ ጀምሮ ከ200 በላይ የተጠረጠሩ ኬዞች እና በቫ...
### Text: የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሰራተኛ ማህበር አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄዱን ገለፀ።ጉባኤው ትናንትና እና ዛሬ ነው የተካሄደው።ትላንህ ጉባኤው በማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኪያ ለማ፣ በአየርመንገዱ የሰዉ ሀብት ም ፕሬዚዳንት ወሮ ዘነበወርቅ ገጻድቅ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን የማህበሩ የስራና የኦዲት ሪፓርቶች፣ የማህበሩ የ20222023 በጀትና እቅድ ውይይትና ማጽደቅ እንደተደረገባቸው ተገልጿል።የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በዛሬው ውሎ ከድርጅቱ ዋና ስራ...
### Text: የሁሉንም የክልል ልዩ ኃይሎችን እንደገና የማደራጀው ለዘላቂ የሀገር ጥቅም እና ድህንነት ነው ፌዴራል መንግሥትየፌዴራሉ መንግሥት በሁሉም ክልል ያለውን የልዩ ኃይል አደረጃጀት እንደገና የማደራጀቱ ስራ0 ለዘላቂ የሀገር ጥቅም እና ድህንነት ሲባል የሚደረግ ነው ብሏል።መንግሥት የዚህ ተግባር ዓላማ ትጥቅ ማስፈታት አይደለም ያለ ሲሆን ስራውን ከሁሉም የክልል መዋቅር ጋር በመወያየት እና በመግባባት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።ለዘላቂ የሀገር ጥቅም እና ድህንነት ሲባል የሚሰራው ስራ...
### Text: ዛሬም ድረስ አሸናፊም ሆነ ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ ያልተገኘለት የጎረቤት ሀገር ሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት አራት ወራት ሊያስቆጥር ተቃርቧል። በዚህ ጦርነት ምክንያት ከ24 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይህ ማለት ከሀገሪቱ አጠቃላይ ዜጎች ውስጥ ግማሹ ያህሉ የምግብ እና ሌሎች ዕርዳታ እንዲፈልጉ አድርጓቸዋል።ነገር ግን በአሰቃቂው ጦርነት እና የገንዘብ ድጋፍ እጦት ምክንያት 25 ሚሊዮን ዜጎች ብቻ ናቸው ድጋፍ ያገኙት ተብሏል።እንደ ተመድ መረጃ ድጋፍ ከሚፈልጉ ዜጎች 14 ሚሊዮኑ ህፃናት ናቸው...
### Text: ሰበር ዜና️ዓለማቀፉ ጣናን መልሶ ማቋቋም ማህበር ሲያካሂድ የነበረውን ጥናት በማጠናቀቅ ሁለት ከፍተኛ አረም ማጨድ የሚያስችሉ ማሽኖች ከነሙሉ መለዋወጫቸው ግዥ ፈጽሟል።359 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም 10 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው እነዚህ ሁለት 9 905 የተባሉ ከፍተኛ የአረም ማጨጃ ማሽኖች እያንዳንዳቸው 75 የፈረስ ጉልበት አላቸው፡፡በአንዴ 262 ሜትሪክ ኪዩብ አረም ማጨድ የሚያስችሉ ናቸው። ይህም ከዚህ በፊት ከተገዛው ማሽን ጋር ሲነጻጸር በአምስት እጥፍ አረም የመሸከም...
### Text: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ብሔራ ቡድን ከፊታችን ላለበት የ 2021 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ የምድቡ ሁለት ከባድ ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ ልምምዳቸውን በመቀሌ የሚያካሂዱ ይሆናል ፡፡ በዚህም መሰረት በኢንስትራከተር አብርሀም መብርሀቱ የሚሰለጥኑት ዋልያዎቹ ፕሮግራማቸው የሚከተለውን ይመስላል ፡፡ጥቅምት 24 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ መቀሌ በማቅናት በዚሁ ዕለት ልምምዳቸውን ማምሻውን የሚያደርጉ ይሆናል ፡፡ህዳር 1 ልምምዳቸው...
### Text: ችሎት የዙና ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ጌታሰው በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ300 ሺህ ብር ተቀጡ። የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት በዛሬው ዕለት የዙና ትሬዲንግ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ዘሪሁን ጌታሰውን ጉዳይ ተመልክቷል። አቶ ዘሪሁን ከ109 ግለሰቦች ሲኖትራክ ተሽከርካሪ አስመጣለሁ በማለት በአጠቃላይ ከ73 ሚሊየን ብር በላይ በማጭበርበር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህ...
### Text: እስከ ሀምሌ 2013 ዓም ከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ መረጃ መሰረት ካሉት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ዩኒቨርሲቲ፣ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፣ ኮሌጅ እና ኢንስቲትዩት የሚል የደረጃ ስያሜ ያላቸው የሚከተሉት ናቸው።ዩኒቨርሲቲ የሚል የደረጃ ስያሜ ያላቸው እስካሁን 5 ሲሆኑ እነርሱም፡1 ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ2 ቅድስተማርያም ዩኒቨርሲቲ3 ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ4 ሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ እና5 አድማስ ዩኒቨርሲቲ ናቸው፡፡ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ስያሜ ያላቸው የግል ተቋማት እስካሁን 5 ሲሆ...
### Text: የኢትዮጵያ መንግስትና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስምምነት የጋራ መግለጫ️በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ዶር ለማ መገርሳ የሚመራውና የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ወርቅነህ ገበየሁ የሚገኙበት የልዑካን ቡድን፣ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር ኣቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራውና ኣቶ ኢብሳ ነገዎ፣ ኣቶ ኣቶምሳ ኩምሳ፣ ኣቶ ቶሌራ ኣደባና ኣቶ ገመቹ ኣያና የሚገኙበት የልዑካን ቡድን ነሃሴ 7 ቀን 2018 በኣስመራ ኤርትራ በመገናኘት ወንድማዊ መንፈስ በተንጸባረቀበትና በሙሉ መተማመን በተ...
### Text: የኤሌክትሪክ ኃይል በፈረቃ መከፋፈሉ ከዛሬ ጀምሮ መቆሙ ተገለጸ። የኃይል ማመንጫ ግድቦች በቂ ውኃ ባለመያዛቸው ምክንያት የኤሌክትሪክ ኃይል በፈረቃ ማከፋፈል የተጀመረው ባለፈው ግንቦት 9 ቀን 2011 ዓም ነበር። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ «ምንም እንኳን ሁሉም ግድቦች የሚጠበቀውን ያህል ውኃ የያዙ ባይሆንም በክረምቱ እንደሚሞሉ ታሳቢ በማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ፈረቃው እንዲቀር ተደርጓል» ብሏል። የፈረቃ አቅርቦቱ መቆሙን የገለጸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ...
### Text: ላልይበላ ባሳለፍነው በጀት ዓመት ከ45 ሽህ በላይ የውጭ ሃገር ዜጎች ላልይበላን መጎብኘታቸውን የላልይበላ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽቤት አስታወቀ፡፡ የቅዱስ ላልይበላንና በዙሪው ያሉ ድንቅ ቅርሶችን 45144 ጎብኝዎች መጎብኘታቸውን ከጽፈት ቤቱ የተገኘው መረጋጃ ያመለክታል፡፡ ጽቤቱ እንዳመለከተው በየዓመቱ የጎብኝዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ያስታወቀ ሲሆን የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜም ለማራዘም እየተሰራ መሆኑን አመልክቷል፡፡ ለዚህም ደግሞ የሆቴሎችን አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ...
### Text: የሱዳንን አብዮት የመሩት ሴቶች ናቸው የአፍሪካ ህብረት ልዑክየሱዳን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ የመረጧቸውን የካቢኔ አባላት በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡እጩዎቹን ለማጥናት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጨማሪ ጊዜ መስጠት በማስፈለጉ እነርሱን ይፋ የማድረጊያው ጊዜ ዘግይቷል ነው የተባለው፡፡ በሱዳን ወታደራዊ እና ተቃዋሚ ቡድኖች በተፈረመው የአገሪቱ ህገመንግስት ማሻሻያ አዋጅ መሠረት 40 ከመቶ የሚሆነው የሚኒስትሮች እና የመንግስት የስራ ቦታዎች በሴቶች አንደሚያዙ ነው የተገለ...
### Text: የ10ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ አልተደረገም የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲም መቼ ይፋ እንደሚደረግ አላሳወቅም ። በተመሳሳይ ስለዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ የሚዋራው ሀሰት ነው። መቁረጫ ነጥብ ይፋ አልተደረገም። ውድ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች በተለያዩ ሀሰተኛ ገፆች እንዳትታለሉ ተማሪዎች እና ወላጆች አጠቃላይ ስለፈተናችሁና ውጤታችሁ ትክክለኛ መረጃን ልታገኙ የምትችሉት በዚህ መንገድ ብቻ ነው 1 ይህ ትክክለኛው የኤጀንሲው የፌ...
### Text: ሲዳማ ክልልና ደቡብ ክልል ንብረት ቆጠራሲዳማ ክልል ንብረት አለኝ የሚለውና ቆጠራ የሚደረገው በሃዋሳ ከተማ ውስጥ ያለውን በተመለከተ ነው ወይስ በሌሎች የደቡብ ክልል ስር በሚገኙ አካባቢዎችም ጭምር ያለውን ነውየአዲሱ ሲዳማ ክልል አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ፅቤት ኃላፊ አቶ ገነነ አበራ ለበገር ኤፍ ኤም የሰጡት ምላሽ56ቱም ብሄር ብሄረሰቦች አንድ ላይ በነበሩበት ጊዜ ያፈሩት ንብረት አለ። ከፌደራልም ከፌደሬሽን ምክር ቤትም በሚደጎሙ ድጎማዎች የጋራ ሃብት ናቸው ተብለው ከተቋም ጀምሮ ብዙ...
### Text: የእንግሊዙ ኩባንያ ከፊ ጎልድ በቱሉ ካፒ አካባቢ የተገኘውን የወርቅ ማዕድን ለማውጣት፣ ወደ ሙሉ የፕሮጀክት ልማት እንዲገባ የተሰጠው የጊዜ ገደብ እንዲራዘምለት ያቀረበውን ጥያቄ የማዕድን ሚኒስቴር ውድቅ ማድረጉን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።0የእንግሊዝ ኩባንያ የቱሉ ካፒ የወርቅ ማዕድን ልማትን በፀደቀው ዕቅድ መሠረት ማከናወን ባለመቻሉ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያና የጊዜ ገደቦች እየተሰጠው ለበርካታ ዓመታት የቀጠለ ሲሆን፣ በሰኔ ወር 2013 ዓም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ነበር።0ነገር ግ...
### Text: ዛሬ በኡጋንዳ በደረሱ 2 የሽብር አደጋዎች 3 ሰዎች ሲሞቱ 33 ሰዎች ቆሰሉ፡፡ካምፓላ ሁለት ቦታዎች በደረሱ የአጥፍቶ ጠፊዎች የሽብር ጥቃት ይ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሰዎች ሲሞቱ 33 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የከተማይቱ ፖሊስ አስታቋል፡፡በአደጋው ከቆሰሉት 33 ሰዎች ውስጥ አምስቱ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተገልጿል፡፡ የተጎጂዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ ይችላል፡፡በካምፓላ ሁለት የገበያ ማዕከላት ላይ ደረሰ የተባለው ይህ የዛሬ ረፋድ የሽብር ጥቃት በአገሪቱ ፓር...
### Text: የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የቀጠለ ሲሆን በግንቦት 232014 ዓም ውሎ የደቡብ ክልል ፕሬዝደንት እና ሌሎች የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች በምልዓተ ጉባኤው ተገኝተው ነበር።የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቤተክርስቲያን ላይ በየጊዜው እየደረሱ ባሉ ችግሮች ዙሪያ ውይይት ለማድረግ ነው ከደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት አቶ ርስቱ ይርዳው ከሌሎች የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደረገው።ምልዓተ ጉባኤ በሃይማኖታቸው ምክንያት ስለተገደሉ፣ ስለተቃጠ...
### Text: በዳሰነች ወረዳ የኦሞ ወንዝ በመሙላቱ ከመደበኛ ፍሰቱ ወጥቶ ሞልቶ በመፍሰሱ ዜጎቻችን እየተጎዱ ነው።እንደ ዳሰነች ወረዳ አስተዳደር መረጃ በ34 ቀበሌያትና በ7 ደሴቶች የሚኖሩ 79828 ቤተሰብ አባላት በወንዙ ሙላት የተጎዱ ተጎድተዋል። በወረዳው ካሉ 40 ቀበሌያቶች 34ቱ ቀበሌያት0 በውሃ የመዋጥና የመከበብ አደጋ ያጋጠማቸው ሲሆን ከዚህ ውስጥ 27ቱ ቀበሌያት ሙሉ በሙሉ በውሃ ሙላት ተውጠዋል 7ቱ ቀበሌያት ደግሞ በቀጣይ ስጋት ውስጥ ናቸው። በኦሞ ወንዝ ሙላት ሳቢያ 143575 ...
### Text: ትላንት እንዲሁም ዛሬ በሀረር፣ አቦምሳና ድሬዳዋ ከተሞች ከበዓለ ጥምቀቱ ጋር ተያይዞ የተስተዋሉ አለመረጋቶችን በሚመለከት ለእናተ ለውድ ቤተሰቦቻችን መረጃዎችን ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ ለማቅረብ መረጃዎችን ስናስስ ነበር። የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ሀረርና አቦምሳ የሰጧቸውን እንዲሁም ከተለያዩ ሚዲያዎች የተገኙትን መረጃዎች በዚህ ገብታቹ ተመልከቷቸው 0120 መንግስት ግን እየታየ ያለውን አደገኛ አዝማሚያ እና ሀገር የሚያሳጣ ድርጊት ትኩረት ሰጥቶ መፍትሄ መፈልግ አለበት። ...
### Text: መንግስት ለተጎጂዎች ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል አቶ ኦርዲን በድሪ የሀረሪ ክልል ርዕሰመስተዳደርከጥምቀት በዓል አከባበር ጥር 10 እና ጥር 11 ጋር ተያይዞ በሀረር ከተማ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ለደረሰው ጉዳት መንግስት አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ የሀረሪ ክልል ርዕሰመስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ አስታወቁ።ርዕሰመስተዳድሩ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ለበዓሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አስፈላጊው ዝግጅት ቢደረግም ግጭት የመፍጠር ተልዕኮን ባነገቡ አካላት በተፈጸመ ተግባር በሰውና...
### Text: የህዳሴውን ግድብ ፕሮጀክት ለማደናቀፍ ማሰብ ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ጉዳይ እንደማይደራደሩ በቅጡ ካለመረዳት የሚመነጭ ስሕተት ነው ሌጄኔራል አስራት ዴኔሮንየኢትዮጵያ ጦር ከፍተኛ መኮንኖች ሀገራችን ኢትዮጵያ እየገነባች ያለውን ግዙፉን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ጎብኝተዋል።በግንባታው ስፍራ ተገኝተው ጉብኝት ያደረጉት የምድር ሃይል ዋና አዛዥ ሌጄኔራል አስራት ዴኔሮን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ናቸው።ከኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ አባላት በተጨማሪ የቤኒሻንጉል ...
### Text: ነዳጅ ለነዳጅ የሚደረግ ድጎማን ከሐምሌ 2014 ዓም ቀስ በቀስ ለማንሳት በዝግጅት ላይ ያለው መንግሥት፣ ከስሌቱ በታች በአነስተኛ ዋጋ ከነዳጅ እየተሰበሰበ ያለው የኤክሳይስ ታክስና የቫት ገቢ ለታለመ የነዳጅ ድጎማ ሊያውል መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።ይሁንና መንግሥት በአነስተኛ መጠን የሚሰበስበውን የኤክሳይስ ታክስና ቫት ገቢ በሕጉ መሠረት ሙሉ ለሙሉ እንዲሰበሰብ ዕቅድ አለው ተብሏል። ይህም የነዳጅን ዋጋ ይበልጥ ያንረዋል የሚል ሥጋት በመፍጠሩ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
### Text: 10 572 ሰዎች ደሴት ላይ ገና በውሃ ተከበው አልወጡም የዳሰነች ወረዳ አስተዳደርበዳሰነች ወረዳ ተከሰተ የተባለው የጎርፍ አደጋ በምን ሁኔታ እንደሚገኝ ፣ በአደጋው የሰውና የእንስሳት ሕይወት እንዳለፈና እንዳላለፈ፣ በንብረት ላይ0 ምን ያህል ውድመት እንደደረሰ0 ወረዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰጥቷል።የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ማልኮ እንደገለጹት ከሆነ፣ 10572 ሰዎች ደሴት ላይ ገና በውሃ ተከበው አልወጡም። እንዲሁም በጎርፍ አደጋው 45 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወ...
### Text: ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ፅጌ️የአማራ መስተዳድር የልዩ ጥበቃ ፖሊስ አዛዥ መኖሪያ ቤት ዉስጥ ትናንት የተያዘዉ የሽጉጥ «ክምር» በየሥፍራዉ ሊከፋፈል እና ሊሰራጭ የተቃደ እንደነበር የመስተዳድሩ የሠላም እና ደሕንነት ቢሮ አስታወቀ። ባሕርዳር በሚገኘዉ የመስተዳድሩ የልዩ ጥበቃ አዛዥ በነበሩት በኮምንደር ዉበቱ ሺፈራዉ መኖሪያ ቤት፣ በሰባት ጆንያዎች ተቋጥሮ የተገኙት ሽጉጦች ብዛት 498 ነዉ። የአማራ መስተዳድር የሠላም እና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ብርጌድየር ጄኔራል አሳም...
### Text: የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም መታሰቢያ እና ዓመታዊ ኮንፈረንስ መስከረም 22 ቀን 2015 ዓም ሊካሄድ ነው።የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ፋውንዴሽን በላከልን መልዕክት መስከረም 22 ቀን 205፣ ከ7፡30 አንስቶ ለግማሽ ቀን በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋካልቲ እሸቱ ጮሌ አዳራሽ በርካታ እንግዶች በተገኙበት ታላቅ ጉባዔ ይካሄዳል ብሏል። የተመራማሪ፣ መምህር፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ደራሲ፣ የሰላማዊ ትግል አቀንቃኝ እና የፍትሕ ተቆርቋሪ በሆኑት ፕሮፌሰ...
### Text: ላይቤሪያ️ላይቤሪያ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በነጻ እንዲማሩ ወሰነችየላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ በሀገሪቱ በየትኛውም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች ከከፍያ ነጻ ሆነው እንዲማሩ አወጁ፡፡የቀድሞው የእግር ኳስ ኮከብ እና የአሁኑ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ላይቬርያውያን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከክፍያ ነጻ ሆነው እንዲማሩ አውጇል፡፡ፕሬዝዳንት ዊሃ ይህን አዋጅ ያሳወቁት ሰሞኑን በላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ ባደረጉበት ጉብኝት ነው፡፡ ማንኛውም የሀገሪቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከዚህ ...
### Text: ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረከ29 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቀው የአዲስ አበባ የወንዞችና ወንዝ ዳርቻዎች ልማት ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት የመጀመሪያው ዙር ግንባታ ተጀመረ። የካቲት 14 ቀን 2011 ዓም በይፋ የተጀመረው የመጀመሪያው ክፍል ፕሮጀክት ከዚህ በፊት የሸራተን ማስፋፊያ በሚል የሚታወቀው ቦታ ላይ ያለው ሲሆን ዝግጅቱ ተጠናቆ ወደ ስራ መገባቱን ለማወቅ ተችሏል።ይህ በቻይናው የኮንስትራክሽን ኩባንያ አማካኝነት ስራው የተጀመረው ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት ሶስት ...
### Text: ቆይታ አቶ ሀይለ ሰመሀት መርሀ ጥበብቲኪቫህ ስፖርት ከአዲስ አበባ ከተማ የሴቶች እግር ኳስ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሀይለ ሰመሀት መርሀ ጥበብ ጋር ከደቂቃዎች በፊት በስልክ ለማውራት ችለናል።በደሞዝ ጉዳይ ለተነሱት ሀሳቦች ተጫዋቾች ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው ሲናገሩ እንደ ምክንያትነት የቀረበው ደግሞ ቡድኑ በባለፈው የውድድር አመት ከ 4 ሚልዮን ብር በላይ ያልተከፈሉ የሆቴል የትራንስፖርት መሰል ወጪዎች ስለነበሩበት እና የራሱ የሆነ የፋይናንስ ክፍል አለመኖሩ ለችግሩ መንስዔ መሆኑን ገልፀውልና...
### Text: ለ5ኛ ጊዜ የጅቡቲን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 98 የመራጮች ድምፅ በማግኘት እንዳሸነፋ የተነገረላቸው ኢስማኤል ኦመር ጌሌህ በዓለ ሲመታቸው ተከናውኗል።በበዓለ ሲመታቸው ላይ የኢትዮጵያ ጠሚ ዶር አብይ አህመድ፣ የኬንያው ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የሱማሊያ ጠሚ ሙሀመድ ሁሴን ሮቤሌን ጭምሮ ሎሎችም ተገኝነት ነበር።በሌላ መረጃ ለፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኡመር ጌሌህ በዓለ ሲመት ጅቡቲ ሄደው የነበሩት ጠሚ ዶር አብይ አህመድ ወደኢትዮጵያ ተመልሰው በአፋር ክልል የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀው ከፍተ...
### Text: ተፎካካሪ ፓርቲዎችግንቦት 2011 ዓም107 ፓርቲዎችነሀሴ 2011 ዓም137 ፖርቲዎች አቶ ኤፍሬም ማዲቦ በኢትዮጵያ ሰዎች በፓርቲ ውስጥ መደራጀትን የሚያገናኙት ከኢኮኖሚ ጥቅም መኖሩ ነው ቁጥሩን ያበዛው፣ በቅርቡ እንኳ ከምርጫ ቦርድ ጋር የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚያደርጉት ድርድር ላይ የውሎ አበል ስጡን ብለው መንግስትን የጠየቁ የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖራቸው ምን ያህል ለጥቅም የቆሙ እንደሆነ አንዱ ማሳያ ነው፣ የፖለቲካ ፓርቲ በየትኛውም አገር ውስጥ ሲመሰረት በህዝብ ድጋፍና በአባላ...
### Text: የገዋኔው ጥቃትበትግራይ ዋልታ ፖሊስ እግር ኳስ ቡድንየትግራይ ክልል ፀጥታ እና አስተዳደር ጽህፈት ቤት የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሀፍታይመለስ ጥቃቱ በዛሬው ዕለት ጠዋት 3 ሰዓት ተኩል ገደማ ላይ መፈፀሙን ተናግረዋል።በጥቃቱ ከቆሰሉ ስድስት ሰዎች መካከል የአንዱ ሕይወት ማለፉንም ተገልጿል። አቶ ሀፍታይ መለስ ስለጥቃቱ ይህ ብለዋል«የትግራይ ፖሊስ እግር ኳስ ቡድን ከጨዋታ እየተመለሰ መንገድ ላይ ማንነታቸው እስካሁን ድረስ ማንነታቸው በግልፅ ማን እንደሆኑ ያላወቅና...
### Text: የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ክሳቸው ስለተቋረጠላቸው የህወሓት አመራሮች ምን አሉ የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት የሆኑት ዶር ይልቃል ከፍያለ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር።በዚህ መግለጫ ወቅት ክሳቸው ስለተቋረጠ የህወሓት አመራሮችም አንስተው ተናግረዋል።ዶር ይልቃል አመራሮቹ የአማራን ህዝብ ጠላት አድርገው በመሳል ባለፉት በርካታ አመታት በህይወት፣ በንብረትና በስነ ልቦናው ላይ በደል እንዲደርስበት በማድረጋቸው ህዝቡ በአመራሮቹ መፈታት ላይ ቅሬታ ቢይዝ እውነት አለው ብለዋል።የአማራ...
### Text: ነጻነት ጉደታ የቫሌንሺያውን ግማሽ ማራቶን ውድድር አዲስ የዓለም ክብረወሰን በማስመዘገብ አሸነፈች ትላንት በተካሄደው የቫሌንሺያው ግማሽ ማራቶን የአለም ሻምፕዮና ውድድር ነጻነት ጉደታ የርቀቱን አዲስ ክብረ ወሰን በማስመዝገብ አሸናፊ ሆናለች፡ ከዚህ በፊት የርቀቱ ክብረወሰን ተይዞ የነበረው በኬኒያዊቷ ጀትሲሊን ጄፕኮሰጌይ የነበረ ሲሆን ነጻነት ጉዲና ይህን ድል መቀዳጀቷ ያልተጠበቀ ነው ተብሏል፡፡ ነጻነት ውድድሩን ለማጠናቀቅ 10611 ሰዓት የፈጀባት ሲሆን የርቀቱንምሰዓት በ14 ሰኮንዶች ...
### Text: አቶ ልደቱ አያሌው ፍርድ ቤት ቀረቡአቶ ልደቱ አያሌው በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር፡፡ፖሊስ በሰኔ 23 ቀን 2012 በቢሾፍቱ ከተማ ለወጣቶች ገንዘብ በመስጠት ለብጥብጥና አመፅ በማነሳሳት በሚል ወንጀል እንደጠረጠራቸው አስታውቋል።ባለፈው አርብ አራት ሰዓት ላይ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸውና በዚህም ወቅት ሁለት ሽጉጦች ማግኘቱን አስታውቋል።የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ለማቅረብም የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜንም የኦሮሚያ መርማሪ ፖሊስ ጠይቋል።አቶ ...
### Text: ባህርዳር ጎንደር ባህር ዳር ከተማ ከትላንት ለሊት ጀምሮ ዝምታ ሰፍኖባት እንደምትገኝና ዛሬ የሟቾች ስርዓተ ቀብር ሲፈፀም እንደነበር ነዋሪዎቿ ተናግሩ።ባለፉት ቀናት በከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ስትናጥ የነበረችው ባህር ዳር ከተማ ከለሊት ጀምሮ ፀጥ ብላ መዋሏን ነዋሪዎች መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።በሌላ በኩል ዛሬ በባህር ዳር በግጭቱ የሞቱ ሰዎች ስርዓተ ቀብር ሲፈፀም መዋሉን ነዋሪዎቹ አመልክተዋል።ትላንት በቀበሌ 13 ፣ 14 እና 16 በነበረ ውጊያ በርካታ ሰዎች ...
### Text: አሳዛኝ ዜና️ከሆሮ ጉዱሩ ዞን ሻምቡ ከተማ ወደ ነቀምቴ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ በሰዎች ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል።45 ሰዎች የመጫን አቅም የነበረው ህዝብ ማመላለሻ አውቶብሱ መጫን ከነረበት አቅም በላይ ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ እያለ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር አደጋው አንዳጋጠመው የሆሮ ጉዱሩ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል።የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ተፈራ እንደተናገሩት የህዝብ ማ...
### Text: በቡለን ወረዳ በተፈፀመ ጥቃት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን እንዲሁም በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የቤኒሻነጉል ጉሙዝ ክልል ቡለን ወረዳ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት አሳውቀል።የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የጤና ባለሞያዎች እንደተናገሩት በሚሰሩበት የጤና ተቋም ጉዳት ደርሶባቸው የመጡ የፀጥታ ኃይል አባላት ስምንት 8 የሚደርሱ እና በርካታ ነዋሪዎች አሉ።ከነዋሪዎች መካከል ህይወታቸው ያለፈ አጠቃላይ ቁጥራቸው እስካሁን ባይታወቅም የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን እንዳረጋገጡ ተናግረዋል እንዲሁም ...
### Text: የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት በይፋ ሲያስጀምሩ ባሰሙት ንግግር ኢትዮጵያ ማንንም የመጉዳት ፍላጎት የላትም ፍላጎቷም ኤሌክትሪክ አይተው የማያውቁ ዜጎቿን የኃይል ተጠቃሚ ማድረግ ነው ብለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአንድነታችን፣ የመነሳታችን፣ የማደጋችን እና የአይበገሬነታችን ምልክት ነው ሲሉም ተናግረዋል።ግድቡ ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ከጨለማ እና ከድህነት መው...
### Text: ብሄራዊመታወቂያ ተቋማት አገልግሎት ለመስጠት ዲጂታል መታወቂን ግዴታ ማድረግ እንደሚችሉ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል።በኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የተዘጋጀው የዲጂታል መታወቂያ ረቂቅ አዋጅ፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ደንበኞቻቸው አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡ ዲጂታል መታወቂያ መያዝን ማስገደድ እንዲችሉ ፈቀደ፡፡ረቂቅ አዋጁ በፍርድ0ቤት0ትዕዛዝ0የዲጂታል0መታወቂያ0ልዩ0ቁጥር0ሊቆለፍ0ወይም0ከሥራ0ውጪ0ሊደረግ እንደሚችል የሚደነግግ ሲሆን፣ ይህም አገልግሎት ለማግኘት ዲጂታል መታወ...
### Text: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕገወጥ እንደሆነ ገልጻ እንዲቆም ያሳሰበችው የትግራይ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ተፈፀመ። የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት ዛሬ ሃምሌ 15 2015 ዓም0 በአክሱም ከተማ የኤጲስ ቆጶሳት በአለ ሲመት አከናውኗል።በዚህም 1 ንቡረ ዕድ መሓሪ አቡነ ሊባኖስ2 ቆሞስ አባ ዘሥላሴ አቡነ ናትናኤል3 ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ አቡነ ኣረጋዊ4 ቆሞስ አባ ኃሚካኤል አቡነ ዮሐንስ5 ቆሞስ አ...
### Text: አሳዛኝ ዜና በወላይታ ዞን በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አንድ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብስ ተገልብጦ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ20 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድርሱን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።በጽህፈት ቤቱ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ ሳጂን አዳነ አሰፋ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሱ በወረዳው ዋሙራ በሚትባል የገጠር ቀበሌ አካባቢ ተገልብጦ ወንዝ ውስጥ በመግባቱ ነው።የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ...
### Text: የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎች ምልመላ ያወጣው ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ህዳር 2012 ዓም ለሚያካሂው የሲዳማ የክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ 6000 የሚሆኑ የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎችን በበጎ ፍቃደኝነነት ለአንድ ወር ማሰራት ይፈልጋል፡፡ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውን ና ኮፒ በመያዝ ንፋስ ስልክ ቡና ቦርድ ፊትለፊት በሚገኘው የቦርዱ ማሰልጠኛ ማእከል በአካል በመገኘት ...
### Text: ተማሪዎች የእርስ በእርስ የዩኒቨርሲቲ ቅያሬ ሙከራ አይቻልም ወሮ አመለወርቅ ሕዝቅኤልየኢትዮጵያ ቴሌቪዥንአዲስ የተመደቡ ተማሪዎች በግል የሚያደርጉት የእርስ በእርስ የዩኒቨርሲቲ ቅያሬ ሙከራ ህገወጥ እንደሆነ እና እንደማይቻል የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲ በግል ለመቀያየር እየተቀመጡ ያሉ መልዕክቶች ተገቢ ያልሆኑ እና ህጋዊ አለመሆናቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።ዘንድሮ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ...
### Text: ዘራፊዎቹ ተይዘዋል በአዲስ አበባ የአቢሲኒያ ባንክ ቴሌ መድሃኒዓለም ቅርንጫፍን ለመዝረፍ የሞከሩ ግለሰቦች ተያዙ፡፡ትናንት ምሽት አስራ ሁለት ሰዓት ተኩል ገደማ በተለምዶ ቦሌ መድሃኒዓም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ የአቢሲኒያ ባንክ ቅርንጫፍ ላይ የዘረፋ ሙከራ ያደረጉ ግለሰቦች መያዛቸው ተነግሯል፡፡እነዚህ የተደራጁ ዘራፊዎች መኪና ይዘው ያደረጉት የዘረፋ ሙከራ በባንኩ ሠራተኛ እና ፖሊስ ብርቱ ጥረት ከሽፏል ተብሏል፡፡የአቢሲኒያ ባንክ የማርኬቲንግ ኮሙኒኬሽን እና ኦፕሬሽን ስራ አስኪያጅ ...
### Text: አብዱል ጃባርበደቡባዊ ተገደሉ️በአፍጋኒስታን የምርጫ እጩ ተወዳዳሪ ከታሊባን በተሰነዘረው ጥቃት ተገደሉ።እጩ ተወዳዳሪ አብዱልጃባርበደቡባዊ አፍጋኒስታን የሄልማንድ ግዛት በፈነዳው ቦንብ ጥቃት ነው ከሌሎች አራት ሰዎች ጋር የተገደሉት፡፡አብዱል ጃባር ቅዳሜ ለሚካሄደው የምክርቤት ምርጫ ዝግጅት በማድረግ ላይ እያሉ በላሽካርጋህ ከተማ ተገድለው መገኘታቸውን የሄልማንድ አስተዳዳሪ አስታውቀዋል፡፡የሄልማንድ አስተዳዳሪ ቃል አቀባይ ኦማር ዝዋክ ከሟቾቹ በተጨማሪ ሰባት ሰዎች በ...
### Text: የጥላቻ ንግግርየፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከል ያረቀቀዉ አዋጅ «በተለይ በማኅበረሰቡና በሕዝቡ መካከል እኩልነት እንዲሰፍን» ለማጎልበት የወጣ ነው አለ። የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ «በጥንቃቄ ከሕገመንግሥቱም አጠቃላይ ከዜጎች መሠረታዊ መብቶች ጋር በማይጋጭ መልኩ አዋጁን ለማዘጋጀት ጥረት» መደረጉን ተናግረዋል። ረቂቁ በውይይት ላይ እንዳለ የገለጡት ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ «በሕጉ ውስጥ የወንጀ...
### Text: የጎርፍ እና የእሳት አደጋዎች በአዲስአበባ በአዲስ አበባ ከተማ ቅዳሜና እሁድ ሁለት የእሳት እንዲሁም ሶስት የጎርፍ አደጋዎች እንደተከሰቱ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ በአደጋዎቹ ሳብያም የሰው ሂወት አለመጥፋቱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያው አቶ ሲለሺ ተስፋዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ራድዮ ገልጸዋል፡፡የእሳት አደጋዎቹ የደረሱት በአዲስ ከታማ ክፍለ ከተማ መርካቶ በርበሬ በረንዳ ላይ በሚገኙ የንግድ ሱቆች ላይ ሲሆን በአደጋው ሳቢያም አንድ...
### Text: ቲክቫህ ቤተሰቦች ቄለም ወለጋከደቂቃዎች በፊት በቄለም ወለጋ አንፊሎሙጊ ከተማ ቤተሰቦቻቸው የሚኖሩ የዩዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በስልክ ለማግኘት ችለናል። ተማሪዎቹ እንደሚሉት ከሆነ በወለጋ የሰው ህይወት እየጠፋ ነው መንግስት ግልፅ መረጃ ለህዝብ እየሰጠ አይደለም የኢተርኔት እና ስልክ መቋረጥ ከቤተሰቦቻቸው እንዲርቁ እንዳደረጋቸውም ተናግረዋል። በሙጊ ከተማ በያዝነው ሳምንት የሰዎች ህወይት አልፏል የንግድ እንቅስቃሴ፣ ትምህርትም ቆማል፣ በከተማይቱ እጅግ ከፍተ...
### Text: አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች አርጀንቲና ግዙፉን የኢግዚቢሽን ማዕከል ወደ ኮቪድ19 የህክምና ማዕከል ቀይራለች። እስከ 2ሺህ 5መቶ የሚጠጉ የኮቪድ 19 ታማሚዎችን ለማከም እንዲውልና ማዕከሉ በሆስፒታሎች የሚኖረውን ጫና ለማገዝ እንደሚረዳ ተገልጿል በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 888 ሰዎች ሞተዋል። ቁጥሩ ባለፉት 7 ቀናት ከተመዘገበው ከፍተኛው ነው። በሌላ በኩል 5526 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ አጠቅላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 114217 ደርሷል። በጃፓን በኮ...
### Text: የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው አቶ ዘሪሁን አበበ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲፕሎማት፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ኮሚቴ አባል አቶ ዘሪሁን አበበ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው ሲሉ ገለፁ።አቶ ዘሪሁን ይህን ያሉት ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ነው።የግብፅ ጩኸት አጠቃላይ ዓላማ ኢትዮጵያ ለምን የዓባይን ውሃ...