text
stringlengths
0
200
‹‹የሴቶች ተሳትፎ የምርጫ ጉዳይ አይደለም። የግድ ነው። እኛም ማብቃት አለብን። እውቀት ያላቸውም አሉ። ትንሽ ድጋፍ እና እድል የሚፈልጉ እነሱን ወደዚህ ማምጣት ይኖርብናል።›› በማለትም ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማምጣት አስላጊነቱን ገልጸዋል።
ቆይ! ቆይ! ቆይ! በፊት እኮ ወዳጅ ስለነበርን የምታመጣልኝ መስሎኝ?
ኢትዮጵያ ዉስጥ አሁን በእስር ላይ ያሉ ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር እንደሌላቸው ነገር ግን በሺህዎች እንደሚቆጠሩ ጠቁመዋል፡፡ “ባለመረጋጋቱ እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች ታስረው እንደነበር የሚያሳዩ ዘገባዎች አሉን፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ተለቅቀዋል ነገር ግን አሁንም ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆ
ነ ሰዎች በእስር ላይ እንዳሉ እናምናለን” ሲሉም አክለዋል፡፡
3ኛ) አለሙ አምሃ የ25 አመት (አብሮ ተጓዝ)
አፋን ኦሮሞ የኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ የመሆን ግዴታነትና የእራሱ በሆነው በኢትዮጵያ ፊደል የመገልገል ተገቢነት _ ዛጎል ዜና - ZAGGOLE NEWS
ስደት የፍርሃት ውጤት ነው - ፕ/ሮ መስፍን ወልደ ማርያም - ETHIOFORUM-ኢትዮፎረም
በተለይም ደግሞ በእየሩሳሌም ከተማ ውስጥ በጥንታዊነት በሚታወቀው ስፍራ ላይ የሚገኘው እና በተባበሩት መንግስታት የባህልና የቅርስ ተቋም በሆነ UNESCO ተመዝግቦ የሚገኘው እና 35 ሄክታር ያህል ስፋት ያለው ስፍራ ይገኝበታል፣ በዚሁ ስፍራ የእመነት አባት በመባል የሚታወቀው አብራሃም የእመነታችን ስር መስረት ነው የ
ሚሉ የክርስትና፣ የአይሁድ እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ቅዱስት ሥፍራዎች ይገኛሉ። በእንግልዜኛው “dome of the Rock” በማባል የሚታወቀው የአይሁድ ቤተ መቅደስ የሚገኝበት እንዲሁም አል አክሳ በመባል የሚታወቅ መስጊድ የሚገኝበት ስፍራ ነው፣ ከዚያም ባሻገር የተለያዩ የክርስትና እምነት ማካሄጃ ቅዱስን የሆ
ኑ ስፍራዎችንም አቅፎ የያዘ ስፍራ ነው።
[የመልካም አስተዳደር እጦት በወሎ] የዘረፈ፣ እግር የቆረጠ፣ ሕዝብን በጥይት እየገደለ ያለ ስልጣን ላይ ሆኖ ይንደላቀቃል _ AdisZena.com
ተመዝጋቢው በሚኖርበት ከተማም ይሁን በገጠር በሚገኙ ቀበሌዎች የሚሰጥ የነዋሪነት መታወቂያ፣ የሠራተኛነት መታወቂያ፣ የተማሪነት መታወቂያ፣ ፓስፖርት ከላይ የተጠቀሰው መታወቂያ በሌለበት ወቅት በቅርቡ ፎቶግራፍ ተደርጐበት የተሰጠው እንደ መንጃ ፍቃድ፣ የመኖሪያ ምስክር ወረቀት፣ ከውትድርና የተገለለበት ሰነድ ወይም በተባ
በሩት መንግሥታት የተሰጠ የስደተኞች ካርድ የመሳሰሉት የመለያ ማስረጃ ናቸው፡፡ ፓስፖርቱ ወይም መታወቂያው ጊዜ ያለፈበት ቢሆንም እንኳን በመራጭነት ለመመዝገብ ሊያገለግል ይችላል፡፡ ከላይ የተገለፁት ማስረጃዎች በማይኖሩበት ወቅት መዝጋቢዎች መራጩን ለይተው የሚያውቁ ከሆነ በገጠር አካባቢ ሲሆን በባህላዊና በልማዳዊ ዘዴ
ተመዝጋቢውን ለመለየት የሚቻልበት ካለ በመራጭነት ሊመዘገብ ይችላል፡፡
LTV Sport _ ጋቶች ፓኖም ከሩስያ መልስ – ክፍል አንድ
ተድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ በቅርብ ከአማራ ቴሌቭዥን ጣቢያ ጋር ያደረገውን ቃለ መጠይቅ ይመልከቱየሊቨርፑልና የቶትነሀም የኧንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታዎቹን ጎሎች መመልከት…የዩቲዩብ አጠቃቀማችን ቀላል እና ፈጣን የሚያደርጉ አጭጭር ስልቶችቼልሲ የ2016/2017 ዓ.ም የኧንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ባለቤት የሆነበትን የጨዋ
ታ…በተበዳዮችና...
የትምህርትን ጥቅም የሚያውቁ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በትምህርት የተጠቀሙ ሰዎች ናቸው፡፡ ትምህርት እንደማንም የፋብሪካ ውጤት የሚሸጥ፣ የሚለወጥና የሚሸመት አይደለም፡፡ ትምህርት የአንድ ግለሰብ ሕይወትን ለዓመታት የሚያገለግል፣ ጊዜ የማይለውጠውና ጥሎ የማይጠፋ ልዩ የስብዕና መገለጫ አጋርና ኃብት ነው፡፡ ትም
ህርት ከግለሰብ አልፎ የማሕበረሰብና የሀገር ልዩ ኃብት ነው፡፡ ለዚህም ነው ትምህርት የሕዝብ ኃብት (Public good) የሚባለው፡፡ በመሆኑም ዩኒቲ ዩኒቨርስቲና ሌሎችም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በመማር ማስተማር ሂደቱ ብቁ ኢትዮጵያውያን፣ ዕውቀትና የሥራ ጥበብ ይዘው እንዲመረቁና ሀገር እንዲያገለግሉ የማድረ
ግ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለባቸው፡፡ ይህን ከፍተኛ ኃላፊነትና ተግባር ለመወጣት ትርፍ ላይ ከፍተኛ ትኩረት በማድረግ ጥራት የሌለው ትምህርት እንዳይሰጥ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ዩኒቲን ጨምሮ፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡
ኦባንግ ሜቶ በመኪና አደጋ ከሞት መትረፉ ተነገረ _ Freedom4Ethiopian
አዲስ አበባን የሚያዘምን ፕሮጀክት እየተዘጋጀ ነው
ሱኑካለም, ኢንተርኔይ kasasını oluşturan aùlgisayarlardır. በድረ ገጹ ላይ በድረ-ገፃችን ላይ ያተኩራል. በ
"dr.fone ሮጦ በፊት, iTunes የቅርብ ጊዜውን ስሪት ለማውረድ መስሎአቸው ነው. Dr.fone የመሳሪያ ስብስብ በሚሰራበት ጊዜ iTunes ለማስነሳት እንጂ, በራስ-ሰር ማመሳሰያ ያለውን ማስወገድ. ""በራስ ሰር ማመሳሰል ከ ለመከላከል አይፖድ, iPhones እና iPads"" ይፈትሹ iTunes> Preference
s> መሣሪያዎች ለማስነሳት:"
የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በዞኑ ስር ለሚተዳደሩ ሴክተሮች ለአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት በልማታዊ ሴፍትኔት ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:
(አትሮንስ ሕዳር 1 ቀን 2007 ዓ.ም) ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ፤ የአራቱ ጉባኤ ምስክር እና መምህር፤ የመንበረ መንግስት መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ በሆኑት ከቀድሞ አባ...
ድምጻዊት አበበች ደራራ ከዚህ አለም በሞት ተለየች
አዎ የኔ ወንድም ብዙ ብለንም ደክመንም ነበር በውነቱ። የኒህ አብይ ሰውዬ ጉዳይ እጅግ በጣም የሚገርምና እውነትም ኢትዮጵያ መከራዋ ያበቃ መስሎ ይታየኛል። ተመልከት ወንድሜ፣ ጅቦች መሃል ሆኖ ጅብን ጅብ የሚል ደፋር መሪ፣ ያውም ዝምታ ወርቅ ሆኖ እንጂ ብዙ ግልገል ጅቦችም መኖራችሁ አልጠፋኝም የሚል ጀግና!!! አይኔን
እስኪያመኝ ድረስ የዛሬውን የፓርላማ ንግግር ከአንዴም ሁለቴ በዩቱብ መስኮት ሰማሁት! አጃኢባ ረቢ ያሰኛል በውነቱ! እንደው የወለዱት እናቱና በመፈጠሩ የታደለችው የኢትዮጵያ አምላክ ከክፉ አይን ይጠብቀው አቦ! እንዲህ አይነቱን አይምሮ ለመሪነት ህይወቴ ሳያልፍ ማየቴ ምነኛ እድለኛ መሆኔን እገምታለሁ! እንዴት አይነቱ
አንጀት አርስ ሰው ነው እባካችሁ!!!! አንዲት የወያኔ ሴትወይዘሮ የፓርላማ አባል(በገጽታቸው እንደማየው፣ ከይቅርታ ጋር) እንደው አወኩ ብለው ከባድ ጥያቄ የጠየቁት መስሎዋቸው ደህና አድርጎ እሳቸውን ተገን አድርጎ ጅቦቹን ደቁሶአቸው አንጀቴን አራሰው!! ቅቅቅቅቅ
Home»ንግድና ኢኮኖሚ»በበልግ አብቃይ አካባቢዎች የዝናብ እጥረት ሊያጋጥም እንደሚችል ተገለጸ
በዚያ ዘመን ነቢዩና ተከታዮቻቸው በግልጽ የተዋጉት ከአይሁዶች ጋር ነው። ይህም በሀይማኖታቸው ምክንያት አይደለም። አይሁዶቹ የመዲና ከተማን ደንብ አክብረው ለመኖር የገቡትን ቃል-ኪዳን አፍርሰው ከነቢዩ ጠላቶች ጋር በወገን ስለተዋጓቸው ነው። በዚህም የተነሳ አይሁዶቹ ለጥፋታቸው ተመጣጣኝ ቅጣት ከፍለው በከተማዋ እንዲኖ
ሩ፤ አሊያም ከተማዋን ለቀው እንዲሄዱ ምርጫ ተሰጣቸው። ጥቂቶች ቅጣቱን ለመክፈል ተስማማሙ። አብዛኞቹ ግን ከተማዋን ለቀው ወደ ተቡክ (አሁን ሳዑዲና ዮርዳኖስ ድንበር) ተሰደዱ።
በድሕረ-ደርግ ኢትዮጵያ ሃሳብን በነፃነት ከመግለፅ አንጻር የተገኙትን ትርፍና ኪሳራ ሂሣብ ስናወራርድ ከፕሬሱ ይልቅ በስነ ፅሁፉ መስክ መጠነኛ ትርፍ እያገኘን የመጣን ይመስለኛል። ስለተሸነፈ ስርዓት መናገርም ሆነ መፃፍ ቀላል ስለሆነ ከማንኛውም ጉዳይ በላይ ስለደርግ ስርዓት ብዙ እየተፃፈ ነው። የፕረስ ነፃነትን ዕውን
ለማድረግ ግን ብዙ ፈታኝ ትግል ቢደረግም “ያለ ዲሞክራሲ የፕረስ ነፃነት” ያለ ፕረስ ነፃነትም ዲሞክራሲ” ሊኖር አይችልም እንደሚባለው ሙከራው የሚደገፍ ቢሆንም ወደ ግቡ ለመድረስ ግን ጉዞው ገና ረጅም ነው። የማይካደው ዕውነት ግን በፕረሱም ሆነ በስነፅሁፉ እስካሁን እየተሄደ ያለው ሂደት ፈረንጆች ዘመነ አብርሆት (
Age of Enlightenment) ያሉት የ18ኛው ክፍለ ዘመን ወቅት የሚመስል ክስተት ዘግይቶም ቢሆን ወደ አገራችን እየገባ ይመስላል።
በኢትዮጵያ የአራቱም ሃይማኖቶች መሪዎች ኅዳር 19 ቀን 2004 ዓ.ም. በ4 ሰዓት ሊሰጡ ያቀዱትን መግለጫ ለመዘገብ ይጠባበቁ ለነበሩ ጋዜጠኞች ‹‹ብርቱ ማሳሰቢያ›› በሚል ርእስ ከታደለው ጽሑፍ ለመረዳት እንደተቻለው፣ ራሱን ዘ አፍሪካን ሜን ፎር ሴክሿል ሄልዝ ኤንድ ራይትስ (አምሸር) ‹‹The African Men fo
r Sexual Health and Rights (AMSHeR)›› ብሎ የሚጠራ የዚህ ቡድን/ድርጅት ዓላማ በአፍሪካ የሚገኙ ግብረሰዶማዊ ወንዶች የተሻለ ሕይወትና ተቀባይነት የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት ነው፡፡
ምግብ ቤቱ ስያሜውን ያገኘው እንደ የባለቤቶቹ ማንነት ከስኮትላንድ እና የኢትዮጵያ ቃላት ጥምር ነው። ቤን በስኮቲሽ ቋንቋ ኮረብታ የሚል ትርጓሜ ሲኖረው አበባ ደግ ያው አበባ ነው። ቤን አበባ የኢትዮጵያዊው ሐብታሙ ባዬ እና ስኮትላንዳዊቷ ሱዛን ኤይቸሰን ጥምረት ውጤት ነው። ሱዛን ጡረታ የወጡ መምህር ናቸው። ከአመታት
በፊት ወደ ላሊበላ ያቀኑት በጎረቤታቸው ግብዣ ድንገት ነበር።
ይልቁንም ደግሞ የኢትዮጵያን ነፃነትና የኢትዮትያን ክርስቲያንነት ከብዙ ዘመን አስቀድሞ መሆኑን አስረድታችሁ ታሪኳን በመናገራችሁ ደስታዬ ከልክ ያለፈ ሆነ፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ የውጭ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን አስተላላፊዎች
የተንቀሳቃሽ ስልኮች ከሚያደርሱት ከፍተኛ ጥልቀት ያለው እና የማይታየው የግላዊነት ስጋት ቀዳሚው ያሉበትን አድራሻ ሌት ተቀን በሚልኩት ሲግናል አማካኝነት ማሳወቃቸው ነው። የግለሰቦች የተንቀሳቃሽ ስልክ አድራሻ በሌሎች ሰዎች ክትትል ውስጥ ሊወድቅ የሚችልባቸው ቢያንስ አራት መንገዶች አሉ።
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ዘመን የፓርላማ አባል የነበሩት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ አሁንም ቢሮ መግባታቸውን አላቆሙም።
Previous Articleሰው ለጥያቄው መልስ የሚያገኘው ሲያምፅ ከሆነ፥ ኑ እናምፅ (ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ)
እስቲ እነዚህን ሐቆች በጥቂቱ ብቻ ለማየት እንሞከር፡፡ በመሠረቱ የአገሪቱን ታሪክ ወደ መቶ ዓመት አውርዶ ለሚተነትነው፣ ጥንታዊው የሆነው ፊደላችን፣ ሦስት ሺሕ ዘመንን ያስቆጠረውን የሥነ-መንግሥት ታሪክ ‹‹የአቢሲኒያውያን/የነፍጠኞች ቅኝ ገዢዎች ታሪክ›› አድርጎ የኢትዮጵያን ሕዝቦች ታሪክ በብሔር ብሔረሰቦች ማዕቀፍ
ቀንብቦ ዳግም ለመፍጠር ለሚውተረተረው፤ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሚመሩት የኢሕአዴግ መንግሥት በምን ሞራልና ተጠየቅ፡- ‹‹ከአፍሪካ አገራት ሺሕ ዘመናትን ያስቆጠረ የራሳችን ፊደልና የዘመን አቆጣጠር ያለን ኩሩ ሕዝቦች …፡፡›› ተብሎ በአደባባይ ሊነግሩን እንደደፈሩ አይገባኝም፡፡ የታሪክ እውነት/ሐቅ ሲያሻን የምንደ
ርበው እንዲያ ሲል ደግሞ አውልቀንና አሽቀንጥረን የምንጥለው የበረሃ ሽርጥ ኾነ እንዴ ጎበዝ …?! ይሄ በእውነት ያስተዛዝባል፡፡ ወይስ ደግሞ እንደው ሳንሰማ ኢሕአዴግ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያለውን አቋም አስተካክሎ ይሆን እንዴ … እ…እ…እ… አይመስለኝም፡፡
ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሮባቸዋል፡፡
በአንፃሩ ደግሞ በ200 ሺ ብር የገንዘብ ክፍያና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ተደልለው በወልቃይት የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባላት ላይ ለመመስከር በህወሃት የተዘጋጁት
ተጨዋቹም ከጥር 1 ጀምሮ አዲሱን ክለቡን ይቀላቀላል።
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 24/2010)የአሜሪካው የስለላ ተቋም ሲ አይ ኤ እስካሁን ይፋ ያልሆኑና የቢን ላደንን ልጅ የቅርብ ጊዜ መልክ የሚያሳዩ የቪዲዮ ምስሎችን ይፋ አደረገ።
በአገራችን ሕዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነት በመቻቻልና በእኩልነት መርሆዎች ላይ እንዲሆን ብዙ ገድሎች ተካሂደዋል። በዲያስፖራው ውስጥ የሚገኙ ፅንፈኛው ወገኖችም ቢሆኑ እነዚህ እሴቶች የአገራችን የፖለቲካ ባህል እንዲሆኑ ድጋፍ መስጠት አለባቸው። ከዴሞክራሲያዊ እኩልነትና ከመቻቻል ውጪ ኢትዮጵያን ማሰብ እንደማይቻል መ
ገንዘብ ያስፈልጋል።
በመላው ኢትዮጵያ የስኳር እጥረት ባለበት ባሁኑ ወቅት በውጭ ምንዛሬ ተገዝቶ ወደ አገር ቤት ከገባ በኋላ ተበላሽቶ ተቀብርዋል ለተባለው ስኳርና ከ77 ቢሊዮን በላይ ወጥቶባቸው በጅምር ለቀሩ የስኳር ፕሮጀክቶች እስካሁን በሕግ የተጠየቀ አካል የለም።
"እውነታኛ የእግዚኣብሄር ኣገልጋይ የጌታችን የብርሃን ቃል በሁሉም ጥግ የሰው ልጅ ልብ የሚያበራ ነው እነዛ ሃጥያት የሚወዱ እንደዚ ብሎ ይጦሩታል የሃስት ነቢይ ፥ የሰህተት መምህር እንደዚ ሊሉት የቻሉት ሃጥያታቸው ስላ ጋለጣቸው ነው። ሆኖም እነዚ ከጨለማ ሊወጡ የሚፈልጉት ዋስትና ያለው መውጪያ ለሚፈልጉት ለዚህ እውነ
ተኛ የእግዚኣብሄር አገልጋይ ያመስጉኑታል ኣሁን መውጪ ስላሳያቸው ። ስለዚህ ሁለት መልሰ ተግባር ኣሉ ለዚህ ብርሃን የጌታ ቃል ኣንዳንዶቹ ይጠሉታል ፥ ሌሎችም ያመስግናሉ ስለ ብርሃኑ የጌታ ቃል ።ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስ ለኛ ሞልቶ ሃይሉ ድሉ በሁሉ ቦታ ነው የሚገልጸው ስለዚህ ኣንዳንዶቹ ስለኛ ጌታ ያመስግናሉ
ሌሎቹም ሊጠሉን ነው ""የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንምና፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን"" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:"
18) ታዲያ ይሖዋ ኤድዋርዶ ያደረገውን ጥረት ባርኮለታል? አና ውጤቱን ስትገልጽ እንዲህ ብላለች፦ “ጥሩ አባት ለመሆን እንዲሁም ከእኛ ጋር ለመቀራረብ ያደረገው ጥረት ትልቅ ለውጥ አምጥቷል። በጉባኤ ውስጥ መንፈሳዊ እድገት ሲያደርግ ስንመለከት ደስ አለን። ይህ ዓለም ከይሖዋ ሊያርቀን እየሞከረ ነበር። ይሁን እንጂ ወላ
ጆቻችን በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ እንደሚያተኩሩ ስንመለከት እኛም ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ጀመርን። አባዬ ሁለተኛ ከእኛ እንደማይለይ ቃል ገባልን፤ ደግሞም ቃሉን ጠብቋል። እንዲህ ባያደርግ ኖሮ ዛሬ በይሖዋ ድርጅት ውስጥ ላልገኝ እችል ነበር።”
ስልጠናው ትኩረት ያደረገው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለተውጣጡ ሴት ሰራተኞች መሆኑን የጠቆሙት አሰተባባሪው ሴቶችን ማስተማር ህብረተሰቡን ማስተማር እንደሆነ በመገንዘብ፣ ሴቶች ለልጆቻቸውና ለቤተሰቦቻቸው ቅርብ በመሆናቸው ያገኙትን እውቀት ማካፈል እንደሚችሉ ታሳቢ ተደርጎ ነው ብለዋል፡፡
am-3 ይህ/ቾ አባል በ ከፍተኛ ደረጃ አማርኛ ማቀነባበር ይችላሉ።.
ጸሎት እና ህይወት ማዳን ቪኜት (ከልጆች ጋር እትም)
ቀደም ሲል በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ከኦሮሚያ ክልል ገዥ ፓርቲ ኦዴፓ ጋር ውህደት የፈፀመ ሲሆን ከሰሞኑ ደግሞ ከተመሰረተ 22 ዓመታት ያስቆጠረው የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ)
ግድቡ በመጀመሪያ በሚሞላበት ጊዜ በሰከንድ በ25 እና በመቶ ሜትር ኩብ አካባቢ የሆነ በጣም ትንሽ መጠን ያለው አንድ የውኃ መልቀቂያ ይኖረዋል፡፡ ይህ የውኃ ፍሰት መጠን ከወንዙ ትንሹ ዓመታዊ የውኃ ፍሰት መጠን ጋር እኩል በመሆን ቢያንስ ከ7 እስከ 9 ወራት በዚሁ የፍሰት መጠን በመፍሰስ ይቀጥላል ተብሎ ይገመታል፡፡
ይህም ማለት በታችኛው የወንዙ ሸለቆ የሚኖረው ህዝብ እና አጠቃላይ የአካባቢው ብዝኃ ሕይወት የአንድ ዓመት ክረምት ወቅት የውኃ ፍሰት መጠን ያጣሉ ማለት ነው፡፡ የውኃ ማጠራቀሚያ ግድቡ ሲሞላ እና የኤሌክትሪክ ማመንጫ ተርባይኖች በሚሽከረከሩበት ጊዜ የጊቤ ሶስት የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ የታችኛው ሸለቆ የውኃ ፍሰት መ
ጠን ከፍ ማለት ይጀምራል፡፡
የኢትዮጵያ ሃገራችን የህዝብ ሃብትም ዕጣ ፈንታችን ለቻይና መንግሥት በእዳ ጫና ምክንያት መሸጡ አይቀሬ መሆኑ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ቻይና ቻይና የሸተተ ልማት፣ ለቅኝ ተገዥነት!!! የአቴንስ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት፣ ሄለኒክ ሪፓብሊክ አሴት ዲቨሎፕመንት ፈንድ አቴንስ ዓለም አቀፍ ኤርፖርትን ለአቪአልያንስ የጀርመን ኤ
ርፖርት ማኔጅመንት ካንፓኒ በ45 በመቶ ድርሻ በ672 ሚሊዮን ዶላር በጨረታ ተሸጦል፡፡ በ2016እኤአ ጀርመን ካንፓኒ ሆነው ፍራፖርት ስሌንቴል 14 የግሪክ የአይሮፕላኖች ማኮብኮቢያና ማረፍያዎች፣ በ1.3 ቢሊዮን ዶላር ገዝተዋል፡፡ ስምምነቱ የዓለም ዓቀፍ አበዳሪዎች ፍላጎት የመንግሥታዊ ኃብቶች ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዘዋወ
ር ብሎም የ86 ቢሊዩን ፓውንድ እዳ ለመክፈል የተደረሰ የአቴንስ ስምምነት ነበር፡፡ የፍራንክ ፈርት ኤርፖርት ኦፕሬተር ፍራፖርት በ1.23 ቢሊዮን ፓውንድ የ40 ዓመታት ሊዝ ኮንትራት ፈፅመዋል፡፡3 ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ይነሳ!!! የህግ ልዕልና በኢትዮጵያ ይስፈን!!! የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!
"← ከአሮጌ ""ውሃ"" ሞተር ጋር መገናኘት"
2 - በመንገዶች ላይ፣ሰዎች በሚጠለሉበት ጥላ ቦታና በመሰብሰቢያ ቦታዎች መጸዳዳት፤ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ሁለቱን መርገምት ተጠንቀቁ ሲሉ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሁለቱ መርገምት ምንድነው? ተብለው ሲጠየቁ በሰው መንገድ ወይም በሚያርፉበት ጥላ ቦታ የሚጸዳዳ ሰው ነው፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ]ብለዋል፡፡
ገጸባህሪያት, ብራናና ብእር አገናኝቶ ቀለም እፍ በማለት ብቻ አይፈጠሩም። ወይም ስም ብቻ የሰጠነው ምናባዊ አካል ገጸባህሪ አይሆንም። ገጽባህሪያት ልክ በውኑ አለም እንዳለነው ሰዎች የህይወት ታሪክ አላቸው። ያሳለፉት ታሪክ ይገዛቸዋል። በልብወለድ ታሪከ ውስጥ ገጽባህሪያት ከገጻት ውስጥ ወጥተው እንዲታዬ ማንነታቸውን
በሚገባ መግለጽ ያስፈልጋል። ገጸባህሪያት የሚናገሩትን የምናምነው ወይም ቃሉ ከራሳቸው አፍ የወጣ መሆኑን የምንቀበለው ያ ያሳለፉት ታሪክ፣ ያ አሁን ለሚናገሩት ምክንያት የሆነው ጉዳይ በዚያው በልቦለዱ አለም ትረካ ውስጥ ሲገለጽ ብቻ ነው።
• አዎ፣ከዚህ በእግር የአምስት ደቂቃ መንገድ ነው።
የፖለቲካ ተንታኙ አቶ አብዲዋሳ፣ ኢሳያስ ብቸኝነት የማያዋጣ መሆኑን የሚገነዘቡ ይመስለኛል፡፡ ማዕቀቡ በበዛ ቁጥር የኤርትራ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን አመራሩን ጭምር ነው ከአካባቢውም ከዓለምም የሚነጥለው፡፡ ኢሳያስ ይኼ ደግሞ ከተሳካላቸው በአልሸባብ ተጠቂ ከሆነችው ኡጋንዳ በኩል ያለው ግፊት ይቀንስላቸዋል፡፡ በእርግጥ ከገፉ
በት ደግሞ መልካም ጉርብትና መጀመር ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው፤›› ሲሉ ያስረዳሉ፡፡
የእርስ በእርስ ጦርነት ያደቀቃት ሶማሊያ አንገቷን ቀና ማድረግ ከጎረቤቶቿ እና ከዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ጋር መቀላቀል ጀምራ ነበር፡፡ በመስከረም ወር ልታካሂደው አቅዳ የነበረው የተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የፕሬዝዳንት ምርጫ ሀገሪቱ ወደ ተረጋጋ ህይወት ለመመለሷ ማመላከቻ ልታደርገው አስባም ነበር፡፡ እርሱም ቢ
ሆን ግን በሰበብ አሰባቡ እየተደነቃቀፈ ከአንድም አራት ጊዜ መራዘሙ ግድ ሆኗል፡፡ ሶማሊያ ፕሬዝደንቷን እንዳትመርጥ ሲጎትታት የነበረው የነበረው የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምርጫ በተያዘለት ጊዜ አለመጠናቀቅ ነበር፡፡ የፌደራላዊ አወቃቀርን መተግበር የጀመረችው ሶማሊያ የምክር ቤት...
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ሮሜ 8፡28
- ኪራይ ለ ሆቴል ሕንፃ, Lancha, አዲስ አበባ, የተሟላ እና ተግባራዊ 32 መኝታ ክፍሎች,.
በጣም ጥሩ እይታ ነው፣ ሀሳብህን እጋራለሁ፣ ትምህርቱ ራሱ በአማርኛ ቢሆን ምንኛ ተማሪና አስተማሪ በተግባባ ነበር ብዬ አስባለሁ፣ በአንድ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮሙኒኬሽንና ጆርናሊዝም የማስተርስ ትምህርቴን ስከታተል ያጋጠመኝን ላካፍላችሁ፣ የዩኒቨርሲቲው ምሁራን ያው እንደተለመደው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ያስተም
ሩና አስተያየት ጥያቄ ካለ መድረኩን ለተማሪዎቹ ክፍት ያደርጋሉ፣ ታዲያ ውይይቱ በእንግሊዘኛ ከሆነ ብዙም ተሳታፊ አይኖርም፣ ወዲያው ግን አንድ ተማሪ አስተያየቱንና ጥያቄውን በአማርኛ ማቅረብ ከጀመረና አስተማሪው እንዲቀጥል ከፈቀዱለት በተከታታይ ብዙ ተማሪዎች በጣም አስገራሚ፣ ሙያዊ ትንታኔዎች እና የሥራ ገጠመኞች፣ ል
ምዶችን የሚያካፍሉበት ጊዜ ይሆናል፣ ውይይቱንም በጊዜ ለመገደብ እስከሚያስቸግር ድረስ በጣም የሚስብ ይሆን ነበር፣ ታዲያ አስተማሪዎቹም የተማሪዎቻቸውን የልብ ትርታ የሚያዳምጡ ነበሩና ትምህርቱን በእንግሊዘኛ ውይይቱን በአማርኛ ያደርጉት ነበረ፣ በዚህ ሁሌም አመሰግናቸዋለሁ፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ ፈተናው በእንግሊዘኛ መሰጠቱ
ስለማይቀር ስለትምህርቱ እውቀቱና ግንዛቤው ኖሯቸው ነገር ግን እንግሊዘኛ የሚያጥራቸው ተማሪዎች በውጤታቸው ወደኋላ ሲቀሩ “ወይኔ አማርኛ ቢሆን ኖሮ” ያሰኛል!!!
ይህ ሁሉ እነ አሸናፊ ተሰላችተው የአንዳርጋቸውን ምስክርነት እንዲተውት ነው። እንደማይተውት ሲታወቅ ዐቃቤ ሕግ ፍርድቤቱ አቶ አንዳርጋቸው ምስክር ሆኖ እንዳይቀርብ ይታገድልኝ አለ። ታገደለት። እነ አሸናፊ አካሉ ይግባኝ ጠየቁ። አቶ አንዳርጋቸው ፍርድ ቤት ቀርቦ ይመስክር ተባለ። ቃሊቲ እንዲያቀርበው ትዕዛዝ ተፃፈ። ቃ
ሊቲ እስር ቤት ተከታታይ ቀጠሮዎችን የማይረባ ምክንያት አቅርቦ አንዳርጋቸው ሳይቀርብ ቀረ።
ሁኔታ ከ40 ዶላር በታች የወረደበትም ጊዜ ነበር ። በነዳጅ ዋጋ መቀነስ ምክንያት ለኤኮኖሚ ክስረት የተዳረገችው ሳውዲ አረቢያ የነዳጅ ዋጋ እስኪጨምር ድረስ መጠበቅ እንደሌለባት በያዝነው በታህሳስ ወር የወጣ አንድ ጥናት አመልክቷል ። ከዚያ ይልቅ ጥናቱ ሃገሪቱ በተቻለ ፍጥነት የተሃድሶ እርምጃዎችን እንድትወስድ ሃሳብ
ያቀርባል ።እንደ ጥናቱ እስካሁን ሲሠራበት የቆየው ውሃ የማጠጣት ዓይነት አሠራር የትም የሚያደርስ ሆኖ አልተገኘም ።ንጉሣዊው አገዛዝ የአገልግሎት ሰጭና የፍጆታ ዘርፎችን ይደጉማል። በዚህ ረገድ የኃይል የጋዝና የውሐ አገልግሎት ክፍያዎች ዝቅተኛ ናቸው ።መንግሥት የገቢ ግብር አይቀበልም ። በዚህ የተነሳም የሳውዲ ዜጎ
ች አባካኝ ሆነዋል ይላሉ የውጭ ጉዳዮችን የሚያጠናው የጀርመን ማህበረሰብ በተባለው ተቋም የምሥራቅ አፍሪቃ ጉዳዮች አጥኚ ዜባስቲያን ዞንስ ። ሆኖም በርሳቸው አስተያየት ድንገተኛ ለውጥን ተግባራዊ ማድረጉ በፖለቲካው አካሄድ የሚቻል አይደለም ።
164 ጌታቸው ተረፈ ወ 16 አይታወቅም
ምክንያቱም መንግስት ድንገት የነዳጅ ዋጋ ያሻቀበ እንደሆን በሚል ስሌት ያስቀመጠውን አንድ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በማዞር ለድርቁ እርዳታ ሊያውለው ችሏልና፡፡
አጀብ! ባዳራሹ ሙሉ ሰው በሰው ሲጠበብ ተግባር መሬት ወድቆ ላፍ እንዴት ይጨብጨብ! (“የዘመን ቀለማት” ከተሰኘውና የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ካሳተመው “ቅጽ ሁለት” የግጥም መድብል የተወሰደ) እንደምን ሰነበታችሁ ወዳጆቼ? . . . እንደዘበትም ሱቅ እንደመዝጋትም...
ዶክተር ብርሐኑ ነጋና ዶክተር መረራ ጉዲና በበርሊን _ ኢትዮጵያ _ DW _ 16.03.2011
3ኛ፦ በግሉ ሚዲያ ላይ የሚደረገው ማስፈራሪትና አፈና በአስቸኳይ እንዲቆምና የፕሬስ ነፃነት ሳይሸራረፍ እንዲከበር፣
በኮሪያ ልሳነ ምድር ያለው ፍጥጫ ደግሞ ሁለቱን ባላንጣ ኮሪያዎች የሳይበር ደህንነት ጉዳይ ላይ በእጅጉ የመጠቀ ፖሊሲና አደረጃጀት እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡ ሰሜን ኮሪያ በዚህ በኩል ቀደም ያለ እርምጃ ላይ የደረሰች ሲሆን፤ ራስን በመከላከል ረገድ አሉ የሚባሉ ባለሙያዎቿን አሰማርታ ትገኛለች፡፡ የሠለጠኑ 3000 የሚደር
ሱ የዲጂታል ምስጢሮችን ፈልቃቂ ኃይሎች እንዳላት ይገለጻል፡፡ እንደውም በመጋቢት ወር 2013 ላይ ሠላሳ ሺሕ የሚደርሱ ኮምፒዩተሮችን ያወከ ጥቃት በደቡብ ኮሪያ ላይ ሲደርስ KBS, YTN and MBC የተባሉት የመገናኛ ብዙኃን ጣቢያዎች ሰለባ ሲሆኑ ሰሜን ኮሪያ በዚህ ረገድ የደረሰችበትን አቅም ጠቋሚ ሆኗል ይባላል፡፡
ስለዚህ ደቡብ ኮሪያም በዚያ አንጻር የሳይበር ደህንነት ላይ እየሠራች መሆኗ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ እስከ አሁን በየዲጂታል መረጃዎችና ምስጢሮችን ፈልቃቂና ጥቃት አድራሽ የሠለጠነ የሰው ኃይሏ ከ400 እንደማይበልጥ ይነገራል፡፡ ስለዚህም ለጊዜው ከአሜሪካ ጋር የሚደረጉ ወታደራዊ የጋራ ልምምዶች ለሰሜን ኮሪያ ማስፈራ
ሪያ እና ማስጠንቀቂያ ሆነው እየተወሰዱ ነው፡፡