text
stringlengths
0
200
ኮ/ል አብዲሳ አጋ ከዚህ አለም በሞት ከተለየ ዛሬ ጥቅምት 3 አርባ አንድ አመት ሞላዉ። ይሄን ታሪክ ከአፄ ቴወድሮስና ከበላይ ዘለቀ ታሪክ እኩል ስሰማዉ ያደኩት እዉነተኛ...
መንግሥት በተለየ መልኩ ትኩረት አድርጎበታል የሚባለውን የማኅበረ ቅዱሳን ሓላፊዎችን በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ባለመሳካቱ የማኅበሩን አስተያየት ማካተት አልቻልንም፡፡
ኤማላ አዲስ የምልክት (መታወቂያ ፥ መግለጫ) ቋንቋ መፍጠሪያ ነው። የኤማላ ሰነድ ደግሞ ፥ የሱ ምርት ነው።
የኢትዮጵያ ቀን በመባል ከእግር ኳሱ ሌላ ልዩ ልዩ የባህልና ትእይንቶች፡ የሥነ-ጽሑፍ ምንባቦችና የተጋበዙ እንግዶች ንግግር የሚያደርጉበት በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎሉና ታሪክን የሚያወቅሱ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ የስፖርትና የባህል ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ተስፋዬ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።
Mahmoud Ahmed ማህሙድ አህመድ - ሆይ ናና ጀግናው ና [Ethiopian Music Oldies أغاني حبشيه]
በ68 ደቂቃ አንበለሐ ዮሀንስ ኃይሉ በጥሩ ሁኔታ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ አንዱአለም ከጃኮ ፔንዜ ጋር 1ለ1 ተገናኝቶ በግሩም ሁኔታ ቺፕ በማድረግ ወሳኟን እና የጨዋታዋን ልየዩነት ፈጣሪ ጎል አስቆጥሯል።
"የአምነስቲ የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ አጥኚ የሆኑት አቶ ፍሰሐ ተክሌ፤ በኢትዮጵያ የተመሰረተው ልዩ ኃይል በ1998 ዓ.ም የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ መሆኑን ይናገራሉ። ""ከኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ጋር ከነበረውን የሽምቅ ውጊያ ጋር በተያያዘ ነበር ይህ ልዩ ኃይል የተደራጀው። ከዚያም
በኋላ በኦሮሚያና በአማራ እንዲሁም በሌሎች ክልሎችም ልምዱ ተስፋፍቶ ቀጥሏል” ይላሉ። ተጨማሪ የኦሮሚያ ልዩ ኃይልን ማደራጀት ለምን አስፈለገ?"
Oldies Day በከፍተኛ 23 (SOS) ተማሪ ቤት
ፍቅር የሚለውን ነገር ስናነብ ወይም ስንሰማ ወደ አእመሯችን ስንት ሃሳቦች መጥተው ይሆን? ብዙ ጊዜ በተለያየ መልኩ ከመጠራቱ የተነሣ ቀላልና ጣፋጭ የሚመስለው ይህ ቃል በዚሁ ምክንያት ለብዙ የተሳሳተ ትርጉሞች የተዳረገ ነው አንድ ካህን ሲጽፉ ስለፍቅር ትክክለኛ ትርጉም ከመናገራቸው በፊት ሦስት የተሳሳቱ የፍቅር ግንዛ
ቤዎችን ይጠቁማሉ።
አሁን, በዚህ ጥቁር ንቅሳ ላይ ጓደኞችዎን በቅናትዎ ላይ ይቀኑ.
የውጭ ፖሊሲ - ሲል ፒተር አቶ ኃይለማርያምን ስለ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ስምምነት የሚከተለውን ጠይቋል፡፡ የሁለቱ አገሮች መሪዎች ሰሞኑን አዲስ አበባ ላይ ሲደራደሩ ነበር፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ለድርድሩ ባደረጉት አስተዋጽዖ በጣም ሲመሰገኑ ነበር፡፡ እርስዎ ጉዳዩን ይከታተሉ ነበር?
አቶ አስራት ጣሴ መፅሔት ላይ ባወጡት ፅሁፍ ታሰሩ
ይህ ሞጁል የመልዕክት መላመድ ንድፍ እንዴት እንደሚሰራ እና ተግባራዊ እንደሚያደርግ ያብራራል.የምናገኘው ትምህርት
ይህ ከተሟላ ፓርቲዎች በእርስ በርስ የመሰራረግ ተንኮል ሳይጠቃቁ፣ በመከባበርና በቅንነት እየተወያዩና እየተራረሙ ለችግሮች መፍትሔ ለመፈለግና ለመቀባበል ይችላሉ፡፡ በውጭም ሆነ በጫካ ውስጥ ያሉ በፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ መሳተፍ የሚሹ ኃይሎችን ማሰባሰብ ቀላል ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ከመንግሥት የቃል መግለጫ
ይበልጥ ራሱ የሕጋዊ መድረኩ ሆደ ሰፊነት በጠመንጃ ጎዳና ውስጥ ያሉትን ወደ ሰላም የመጥራት ጉልበት ስለሚኖረው ነው፡፡ “የዴሞክራሲ ግንባታና መስፋፋት ማዕከል” ትርጉም ያለው ሥራ መሥራት የሚችለውም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውስጥ ከሚኒስትርነት የወረዱ ሹሞችን አዝሎ ሲፈጠር ሳይሆን፣ የፓርቲዎችን የጋራ ተልዕኮ
ተቆናጦ ሁሉንም ፓርቲዎችና የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎችን አካትቶ እስከ ታች ድረስ ከሕዝብ ጋር የሚሠሩ ቅርንጫፎች ሲኖሩት ነው፡፡
72ካሬ የሚሸጥ G+2 ቤት in Addis Ababa _ Qefira
አቶ በረከት ስምኦን በብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መታገዳቸውን ተከትሎ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ በሚሰጡት ቃለ ምልልስና ማስተባበያ፤ የማህበራዊ ሚዲያው መነጋገርያ ሆነው ሰንብተዋል፡፡ ከዚህ በኋላም አቶ በረከት በፖለቲካው እንደማይቀጥሉ መግለፃቸው ይታወቃል፡፡
#EBC ዛሬ የተሾሙት የካቢኔ አባላት ቀዳሙ ትኩረት ሙስናን መዋጋትና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሆኑ ተገለጸ
ኬንያውያን ተንታኞች በበኩላቸው ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ግዙፍ መንሳት አስተዋጽኦ አድርገዋል ያሏቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር መብዛት፣ የሕዝቡ መብዛትም ለአገር ውስጥ ገበያ የፈጠረው አቅም እንዲሁም ለውጭ ባለሀብቶች እንደልብ የቀረበው ርካሽ የሰው ኃይል ይገኙበታል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት ከኬንያ በእጥፍ ይበልጣል፡፡
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታ እንዲህ እንዲህ እያለ ዛሬ ላይ ደርሷል።በጎንደር ልዩ ልዩ ስፍራዎች በሕዝብ እና በሕወሓት መካከል ከፍተኛ ውግያ እየተደረገ ነው።ከሱዳን በኩል ዋስትና እስካለ...
(ይህ ጽሑፍ ለውጥ በፖለቲካዊ አብዮት ብቻ እንደማይመጣ፤ እንዲያውም አብዮት ለአንዳንዶች መጠቀሚያነት ሊውል እንደሚችል፣ ብሎም ዴሞክራሲ የሚገነባው “የክፍል አለቃ፣ የት/ቤት ዳይሬክተር፣ የቢሮ አለቃ፣ የዕድር ሊቀመንበር፣ የማኅበር ሙሴ የመሳሰሉት…” በሹመት፣ በሞገስ ሲሰየሙ ሳይሆን በዴሞክራሲያዊ መንገድ መመረጥ ሲጀ
ምሩ ነው የሚል ይዘት ያለው ነው፡፡)
oh holy night,oh silent night ነፍሴን የሚያርዳት መዝሙር ነው። በእርግጥም በዚያች ምሽት የሰማይ እና የምድር ፈጣሪ አምላክ ራሱን “በጠባብ ደረት እና በአጭር ቁመት” ወስኖ ተገልጧል። እንዲህ መዝሙር ደግሞ ያንን ጉልበት አምቆ የያዘ መዝሙር አላይሁም። ያልዘመረው አርቲስት አለ ብትሉኝ አማላምንም።
ኦሕዴድ ጠቅላላ ጉባዔውን በመስከረም በጅማ ከተማ ያካሂዳል ዮሐንስ አንበርብር Sun, 09/09/2018 - 09:
በገዢው ስራዓት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ባለው ሰፊ የዓመቱ ግምገማ “የተቃዋሚዎች ሬድዮ መስማት” እንደዋነኛ መገምገሚያ ነጥብ ሆኖ መነሳቱን ተገለፀ።በምንጮቻችን መረጃ መሰረት- በሁሉም የስርዓቱ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ የዓመቱ ግምገማ ወታደሩ ያለማቋረጥ እየፈረሰ በመጥፋት ላይ
ያለው የትጥቅ ትግል እያካሄዱ በሚገኙ ድርጅቶች የሚሰራጨውን ሬድዮ መስማት ዋናው ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ስለሆነ ለምን ታዳምጣላችሁ፤ እነማን ናቸው የሚያዳምጡት መታወቅ አለባቸው በማለት እየተካሄደ ባለው ስብሰባ የሰራዊቱ አዛዦች ራሳቸው የስብሰባው መሪዎችና ገምጋሚዎች ሆነው በመቅረብ ለበርካታ የሰራዊቱ አባላት እያባ
ረሩና እያሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ መግለጫ “የአገሪቱ ችግር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ሆነ በኮማንድ ፖስት አስተዳደር አይፈታም”
Next Post ብሔርተኝነት የሰው-ልጅን ወደ አውሬነት ይቀይራል (ክፍል-2)
የአረብ ፖለቲካ ተንታኝና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ማህጁብ ዝዌሪ፣ ‹‹የኢራን ሕዝብ ከኑክሌር ድርድሩ መልካም ውጤት ይገኛል ብሎ ተስፋ አድርጎ የነበረው ስሌት የተሳሳተ ነበር፤ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን ከያዙ በኋላ ሕዝቡ የፕሬዚዳንቱን ፖሊሲዎች ከግምት ውስጥ አላስገባቸውም፤ ሲጀመርም ድርድሩ ለኢራን ጠቃሚ
አልነበረም›› ብለዋል፡፡
ከ400 በላይ ሙዚዬሞችና የኤግዚብሽን አዳራሾች፤ ከ182 በላይ ቲያትር ቤቶች፤ አምስት የሰርከስ አደራሾች፤ ከ16 በላይ ፓርኮች፤ በደን የበለፀጉ ከ118 በላይ የተፈጥሮ ክልሎች በከተማዋ ዙርያ ገብ ይገኛሉ፡፡
የ2005 ዓ.ም የቤተክርስቲያኒቱ ሀገራዊ ገቢ አንድ ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር ተጠጋ
4. ባጩ መርጋ – የ18 ዓመት ፍርድ ተፈርዶባት በቃሊቲ የምትገኝ።
ዳኒ የጠቀስኸው የደበበ ሰይፉ (1967) ተራኪ ግጥም ላይ ስለ አንድነት ሲያወራ እነዚህን ስንኞች ማሰቡ እኔን ያስደስተኛል- ፋንታሲ ቢሆንም (ቢመስልም) ቅሉ፡፡
በሰሜን ኢትዮጵያ ጠንክሮ የመጣው የወልቃይት ጥያቄም ቢሆን አስተዳደራዊ አከላለልን ብቻ የሚመለከት ሳይሆን የማንነት ጥያቄም ጭምር ነው፡፡ ኮሚቴው “ህዝባችን በስነ ልቦናው፣ አለባበሱ፣ ለቅሶ እና ሰርግ ስነ ስርዓተ የአማራ ብሄር አካል ሆኖ ሳለ ትግሬኛ ቋንቋ ስለተናገረ ብቻ በብሄሩ “ትግሬ ነህ” መባሉ ህገመንግስታዊ
አይደለም” በሚሉበት ሁኔታ ጥያቄው አስተዳደራዊ ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡ “ስነ ልቦናችን በፈቅደው አማርኛ ቋንቋ ትምህርት መማር እና ዳኝነትም ማግኘት እንፈልጋለን” የሚል ጥያቄ መሰረታዊ ህግ መንግስታዊ ጥያቄ እንጂ ወደ አስተዳደራዊ ጥያቄ የሚገፋ ተራ ጥያቄ አይሆንም፡፡
ጤናማ የወሲብ ግንኙነት እንዴት ማድረግ ይቻላል ትንሽ...
ጥቁር_ገበያው አቅሙን በማፈርጠም በአገሪቱ ኢኮኖሚና በዜጎች ህይወት ላይ...
21፤ እርሱም ያለውን ሁሉ ይዞ ኮበለለ፤ ተነሥቶም ወንዙን ተሻገረ፥ ፊቱንም ወደ ገለዓድ ተራራ አቀና።
ከሌሎች ነገሮች ሁሉ በላይ ጽሑፉ የሚያነሳሳው በግለሰቡ ውስጥ ያሉትን ልዩነቶች ሁሉ፣ የአኗኗር አርአያነት፣ የአተገባባራቸው ደረጃ ልዩነት ቢኖርም ባህላዊ አመለካካቶችን፣የፆታና የግብረ ሥጋ ግንኙነት ግንዛቤ፣ እንዲከበሩ ነው፡፡ አባባሉ ዘርፈ ብዙ አተረጓጐም ሊያስከትል የሚችል አገላለጽ ይሁን እንጂ እንዲጎላ የተፈለገው
ሐሳብ ግን ‹‹የፆታ ግንዛቤን እናክብር›› የሚል ነው፡፡‹‹ ኢንፎርሜሽን ቱ ዘ ፓብሊክ›› ና ‹‹ጋይዳንስ ሪጋርዲንግ ኮምፕሊየንትስ አባውት ሳይኮሎጅስትስ›› ከሚለው ጋር ሲያያዝ በልጆቻቸው ህይወት ውስጥ ግብረሰዶማዊነትን ለመከላከል ለሚፈልጉ ወላጆችን ለመርዳት ለሚፈልግ ማንኛውም ሳይኮሎጅስት ብዙ ዓይነት ትርጉም አለ
ው፡፡
ከስደተኞች መካከል አንዷ በሰጠችው አስተያየት፣ በጦርነት ውስጥ ተወልዳ በጦርነት ውስጥ ማደጓን፤ አሁን ግን የጥይት ድምፅ የማይሰማበት አካባቢ መኖር የምትፈልግ መሆኗን ገልፃለች።
“ልማት፣ ህዳሴ፣ …” እያላችሁ እውነታውን ለመደበቅ ብትሞክሩም ውጥረት ከነገሠ ግን ቆይቷል። በትግሬዎችና በሌሎች ኢትዮጵያውያን መካከል ያለው ልዩነት በተለይ ከውጭ ለሚመጡ ኢትዮጵያውያንም ሆነ ሌሎች በግልጽ የሚታይ ነው፤ ልዩነቱ የሚታየውም ከቦሌ ኤርፖርት ጀምሮ ነው። ወደ አገር ሲገቡ ትግሬ በመሆናቸው ብቻ የተለየ
መስተንግዶና አገልግሎት ሲሰጣቸው ማየት ለብዙዎች አዲስ አይደለም። በኤርፖርቱ ውስጥ ያሉት የጉምሩክ ሠራተኞች ትግሬዎች መሆናቸው አንዱ ማረጋገጫ ነው። (በነገራችን ላይ ይህ በራሱ ወደ አገር ውስጥ ማን እንደሚገባ ማን ከአገር እንደሚወጣ በታማኞች ለመቆጣጠር ሆን ተብሎ የተደረገ ነው።)
አንድ የቀረችኝ ትንሽ ተስፋ ቢትኖር፣ ይህ ሁሉ የመከራ ዘመን አንድ ቀን አልፎ እኛ ጋዜጠኞች ነፃ ሆነን የፕሬስ ነፃነቱንም ተቀዳጅተን አላንዳች ቁጥጥርና ፍረሃት ለአገራችን ዕድገትና ብልፅግና፣ ለሕዝቡም ድህንነትና መልካም ኑሮ፣ ለእናት አገራችንም ሕልውና የተለያዩ፣ የሚጻረሩና የሚፎካከሩ አስተሳሰቦችን አንስተን በመል
ክ በመልኩ እያፈረጥን እነሱን የምናስተናግድበት ጊዜ አይቀርም፣ ይመጣል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፤ እሱንም እጠብቃለሁ።
“የተሻሻለ ጎረቤት” – በተሳካ በገጠር አካባቢዎች
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 11/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ካደረጉት የመጽሐፍ ቅዱስ አስተንትኖ በመቀጠል ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙት “የእግዚኣ
ብሔር መልእክ ማርያምን አበሰራት” የሚለውን የመልእከ እግዚኣብሔር ጸሎት ከምዕመና ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 11/2011 ዓ.ም ዓለማቀፍ የተልዕኮ ቀን መከበሩን አስታውሰው ይህም ዓለማቀፍ የተልዕኮ ቀን “ከወጣቶች ጋር
በጋራ በመሆን ቅዱስ ወንጌልን ለዓለም አናዳርስ” በሚል መሪ ቃል መከበሩን ቅዱስነታቸው ገለጸዋል።
መግለጫው በጣም የወቀሳቸው ባለስልጣናት እነማን ይሆኑ? ለምን?
አሁን ፋብሪካው የጀመረው የአፈር ብናኙን የመቆጣጠር ስራ ዘላቂ እንዲሆን ይፈልጋሉ፡፡
ህዝባችንን እና አገራችንን ከወደድን ኦሮሞን ለኦሮሞ አማራን ለአማራ የሚለውን ተረት ትተን በአንድነት ለአንዲት ኢትዮጵያ መቆም አለብን። ዛሬ እየተገደልን ያለው ስለተለያየን ነው ዛሬ አገር እየተዘረፈች ያለችው ተከፋፍለን ስላለን ነው ተከፋፍለን የምናደርገው የግል ትግል አሸናፊው እና ተሸናፊው ወደማይታወቅበት አዘቅት
ውስጥ የሚከተን በመሆኑ እና ለወያኔም አመቺ ስለሆነ አንደነታችንን በግልጽ አውጀን ኢትዮጵያኖች እንደማንለያይ አንድ እንደሆንን አውጀን እውነተኛ ነጻነት ለማምጣት በጋራ እንታገል። አንድነት አሸናፊ ነው፣ አንድነት ፍቅር ነው፣ አንድነት ነጻነት ነው፣ አንድነት ኃይል ነው። አንድነት አንድነት አንድነት ለኢትዮጵያዊነት።
አዝናኝ እና አወያይ ዝግጅት በአስፋዉ መሸሻ እና ራኬብ አለማየሁ/Sunday WIth EBS Asfaw And Rakeb
ሳይንስ ሚረጋገጠው ነገሮችን በመሰብሰብ ፣ በመለካት ፣ በማየት እና ሙከራዎችን በማድረግ ሲሆን ጥበብ ግን የሚረጋገጠው በሰው ልጅ ውስጣዊ ሚስጥር በመፈተሸ ነው፡፡ ፍቅር ፣ ሐዘን፣ ደስታ ፣ ስቃይ እና መሰል ነገሮችን በመዳሰስ ……
Bitcoin ጎልድ cryptocurrency ወደ የማገጃ ላይ hardfork ምክንያት ጥቅምት 24 ላይ ታየ 491,407 የሆንግ ኮንግ ውስጥ ኩባንያ መብረቅ ASIC የሙስናና. የፕሮጀክቱ ግብ የመጀመሪያው Bitcoin ይልቅ ያልሆኑ ሙያዊ ቆፋሪዎች አንድ ይበልጥ ማራኪ ምንዛሬ ለመሆን ነው. በዚህ ረገድ, የአውታረ መረብ
ተጠቃሚዎች ይበልጥ ቁጥር Bitcoin ወርቅ እና cryptocurrency መፈክር ነው ማዕድን ይችላሉ “እንደገና ባልተማከለ Bitcoin ማድረግ.” ይልቅ አሮጌውን ማስረጃ-መካከል-የስራ ፕሮቶኮል hardfork initiators አዲስ አንዱን ይጠቀሙ, Equihash. ይህ ስልተ የዘፈቀደ መዳረሻ ትውስታ መጠን የበለጠ
ስሜታዊ ነው (ራንደም አክሰስ ሜሞሪ) cryptocurrency Zcash የማዕድን ጊዜ ደግሞ ጥቅም ላይ ነው. ዛሬ, 13 ታህሳስ, Bitcoin ጎልድ ምንዛሬ ተመን ነው $276.88 እና የገበያ አቢይ በላይ ነው $4.5 ቢሊዮን.
በዛሬው መዝናኛ ዲጂታል ቪዲዮዎች ከባቢ, ኢ-መጽሐፍት, እና ኦዲዮ
የባለሙያዎቹ ቡድን ሐኪሞችን፣ ነርሶችን፣ የፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ባለሙያዎችን፣ የአካባቢ ጤና ባለሙያዎችንና የህብረተሰብ ጤና ስፔሻሊስቶችን ያካተተ ነው፡፡
This entry was posted on April 5, 2015, in Uncategorized and tagged ወቅታዊ መርህ ሊሆን የሚገባው ‹‹ያገባኛል›› ባይነት! (ኢ-ሰብዓዊነትን መቃወም በራስ ሲደርስ ብቻ አይደለም) ኤልያስ ገብሩ. Leave a comment
ይህ ጭፍን ወገንተኝነት ወይም ምክንያት አልባ አቋም አይደለም። ይልቁንም ከግልብ አመለካከት የራቀ ውስጣዊ እሳቤንና ፍላጎትን የሚዳስስ እይታ እንጂ። እነዚህ እሳቤዎችና ፍላጎቶች ናቸው አንድ ህዝብ ከሌላው የሚለዩት። ይህ ሚዛን ነው አንድን አስተሳሰብ፣ አመለካከት፣ የህይወት እይታ ከሌላው የሚለየው።
ኦሕዴድ አምስት አዳዲስ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መርጧል፡፡ በድርጅቱ ታሪክ ሦስት ሴቶች ማለትም ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ ወ/ሮ ሎሚ በዶ፣ ወ/ሮ አዚዛ አብዲ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሆነዋል፡፡ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬና አቶ ፍቃዱ ተሰማም ተካተዋል፡፡ ወ/ሮ ብርቱካን አያኖ (አምባሳደር) የክልሉ የሥነ ምግባርና ፀ
ረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነዋል፡፡
በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ስርዓት መሰረት በ አንድ ቀን ውስጥ የተመደቡ የጸሎት ጊዜያት ሲኖሩ እነርሱም ሰባት (፯)ናቸው። አንድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሰው ቢችል በ አንድ ቀን ዉስጥ ሰባቱንም ጸሎታት ማድረስ ይኖርበታል፣ በስራ ወይም በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ሳይመቸው ቢቀር
ቢያንስ በጸሎቱ ሠዓታት ሚታሰቡትን ነገሮች አስቦ ማሳለፍ ይኖርበታል። ነገር ግን እናመሰግነው ዘንድ ለፈጠረን አምላክ በስራስ ቦታ ቢሆን የሁለት እና የሦስት ደቂቃ ጊዜ እነዴት እናጣለታለን? እና ከቻልን አቡነ ዘበሰማያት (አባታችን ሆይ) የምትለዋን አጭር ጸሎት ብናደርስ ይመረጣል። ያንንም እናደርግ ዘንድ እግዚአብሄር
ይርዳን !
በሁለተኛነት የቀረበባቸውን ክስ አስመልክቶ በሰጡት ቃል ደግሞ በኢትዮጵያ ሕግና የዳኝነት ሥርዓት ቢኖርም፣ የ1997 ዓ.ም. ምርጫን ተከትሎ የተፈጠረውን ግርግር በተመለከተ ያለፈው አልፏል ለወደፊት በድጋሚ ቢከሰት ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት (ICC) አባል መሆኗ ሊጠቅም እንደሚችል መጠቆማቸውን ለጉባዔው እንደገ
ለጹ የቀረበው ሪፖርት ያስረዳል፡፡ የ1997 ዓ.ም. ምርጫ ክስተት የአንድን ብሔር ጥቅም ለማስጠበቅ የተደረገ ነው ወይም ይህ ቡድን ይህን ፈጽሟል አለማለታቸውን፣ የተባለው በመንግሥት ደረጃ የተፈጸመ ነገር አለ ወደፊት ቢደገም የሚዳኝ ገለልተኛ አካል ያስፈልጋል ማለታቸውን፣ ክስተቱ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተቋቋመ
አጣሪ ኮሚቴ ተጣርቶ መንግሥት የወሰደው ዕርምጃ ተመጣጣኘ ነው ቢባልም፣ ወደፊት ሌላ ተመጣጣኘ ያልሆነ ነገር ቢከሰት ይህንን በገለልተኝነት የሚዳኝ አካል ያስፈልጋል ማለታቸውን ለጉባዔው ገልጸዋል ተብሎ ሪፖርት ተደርጓል፡፡ የተቀሩት ክሶችን በአግባቡ በማስተባበላቸው ጉባዔው ከላይ የተጠቀሱትን ሁለት ክሶች በጭብጥነት ይ
ዞ የማጣራት ሥራ ማከናወኑን ይገልጻል፡፡
የመጀመሪያ ብቸኛ ልጄ ነበርና በህይወቱ ውስጥ የሚጨምር እያንዳንዷየእድገት ደረጃ የእኔንም ህይወት ትጨምር ነበር፡፡ማንኛዋም እናት ከወለደች በኋላ የእርምጃዋን ልክ በልጅዋ እርምጃ እንደሚወሰን ሁሉ የእኔም እንደዚያው ነበር፡፡
የዝቋላን ቃጠሎ ለመከላከል ዓለም አቀፍ ድጋፍ ተጀምሯል
አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዱቄት አንድ ማንኪያ የእኸሊ ቅጠል ከአንድ ስኒ ንጹሕ ማር ጋር ለውሶ በባዶ ሆድ መብላት፡፡
በመሆኑም ሰዎች በሞባይል ስልክ በሚነጋገሩበት ወቅት ጉንጫቸውን የሚነካው የሞባይል ስክሪን ላይ የሚገኙ ባክቴሪያዎች ቆዳችንን ማበላሸት ብቻ ሳይሆን ለሆድ እና ጨጓራ ህመም በማጋለጥ በአጠቃላይ ጤንነታችን ላይ ከባድ አደጋን ሊያስከትሉ ይችላሉ ነው የሚሉት።
መንግሥት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን የሚያሳውቅ በትን ሰረዘ
እርሱ ደግሞ ይሄን ሲያስተላልፈ ያውም በጨዋ መንገድ ፤‹‹አሁን በኢትዮጵያ ባለው ነባራዊ ሁኔታ የጋዜጠኝነት ሞያ በራሱ ነጻ አልወጣም፡፡‹‹ተቃዋሚዎች ሞያውን እንደነርሱ ፍላጎት ይስቡታል፣ባለሃብቶችም እንደሚመቻቸው ሊያሽከረክሩት ይፈልጋሉ፡፡ አንባቢውም ማንበብ የሚፈልገው ብቻ እንዲጻፍለት ይፈልጋል፡፡›› የሚለውን ብቻ
ወስዶ እንደሚኾን በእርግጠኝነት ነገርኩት፡፡ እርሱም ከዛ በላይ ብዙ ሊለልኝ ስላልፈለገ ለስንብት ተነሳ፡፡እናም ከወራት በኋላ እኔን በጠየቀኝ ጋዜጠኛ ስምም ባይኾን በሌላ አዘጋጆች ስም በዚህ ሓሳብ ዙሪያ የሚያጠነጥን ‹‹መንታ መንገድ›› የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ባለፈው ሣምንት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ቀርቦ ታየ፡፡ ስለ ፊልሙ
ቅድመ ዝግጅት በማወቄ ሳይኾን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ስለ ሕትመት ሚዲያው ስርጭት የቀረበው መረጃ እውነተኛውን ስዕል የሚያሳይ አይደለም ብዬ ስለማምን አስተያየቴን እንዲህ ጻፍኩ፡፡
2.ኣምላኽ ኢዩ ዓቢ ንጉስ ፈጣሪ ኩሉ ዓለም፡
በሲንጉሃ ዩኒቨርሲቲ የኬሚካል ኢንጂነሪንግ ምሩቅ የሆኑት ጂንፒንግ፣ ከድምፃዊቷ ባለቤታቸው ፔንግ ሊዩዋን አንዲት ሴት ልጅ ወልደዋል፡፡ ልጃቸው ሺ ሚንግዜ ሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የተማረች ሲሆን፣ ብዙም ስለርሷ የሚታወቅ መረጃ የለም፡፡ ጂንፒንግ በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ለቅቀው ለሚያስጠጉት ተተኪ ያስተላልፉ ይሆን የሚለው
ጥያቄ አሁን የብዙዎች ሆኗል፡፡
አሁን የለበስከውን ልብስ ለብሰህ እስከ ተከዜ ትሄዳለህ። ተከዜን ከተሻገርክ በኋላ የለበስከውን ልብስ አውልቀህ ሙሉ የቄስ ልብስህን ትለብሳለህ። የዱሮው ልብስህን ተመልሰህ እኛን ለመገናኘት ስትመጣ የቄስ ልብስህን ደብቀህ የዱሮ ልብስህን ለብሰህ እንገናኛለን። ሰው በማያገኘው ጥሩ ቦታ ደብቀው ተባብለው በዚሁ ተለያዩ።
አባ ገ/ሥላሴም ዋልድባ ገዳም ገቡ። ታጋይ በርሄ መብራህቱ (አባ ገ/ሥላሴ) ገዳም ገብተው ሰፈሩ። ከ1975 እስከ ሐምሌ 1983 ለ8 ዓመታት ዋልድባ ገዳም የኖረው ታጋይ በርሄ መብራህቱ ሰላዩ በዋልድባ ገዳም የሚታወቀው አባ ገ/ሥላሴ ሲሆን የተሰጣቸውን የስለላ ተግባር በተሳካ ሁኔታ ቀጠሉበት። በዋልድባ ገዳም አባ ገ/
ሥላሴን የሚያውቋቸው የገዳሙ አባላት በርካታ ናቸው። ቢሆንም፣ ገዳሙን ለማጥቃት በህወሓት የተላኩ ሰላይ መሆናቸውን ግን አያውቁም። ስምንት ዓመት በገዳሙ ሲኖር ማንነቱ እንዳይታወቅ በጥንቃቄ የኖረ ሰላይና መልእክተኛ ነው። ታጋይ በርሄ መብራህቱ (አባ ገ/ሥላሴ) በዋልድባ ገዳም ባካሄደው የስለላ ጥናቱ ለስብሃት ነጋና ለ
ግደይ ዘርአጽዮን በማስተላለፍ ዋልድባ ገዳምን ለካባድ ጥፋትና ውድመት የዳረገ ሰው ነው። ከግደይ ዘርአጽዮን በማለሊት ምስረታ ጉባኤ በሃሐምሌ 1977 ቢባረርም፣ ሰላዩን በተገቢው መንገድ አሰጥኖታል። አባ ገ/ሥላሴ (ታጋይ በርሄ መብራህቱ) በሚያስተላልፈው የስለላ መልእክቶች በብስራት አማረ እጅ በመላክ ለስብሃት ነጋና
ለውውይት ለዘርአጽዮን ይደርሳል። ከዚሁ በመነሳት የሚፈለገውን ጥቃት ሁሉ በስምንት ዓመታት ቆይታው ገዳሙ ከሚጠቀምባቸው የምንጭ ውሃ እስከ እርሻ መሬት፣ በብዛት የጋማ ከብትና ማንኛውንም ሃብት በዝርዝር አሳልፈው የሰጡና ያስተላለፉ ሰላይ ዛሬ ገዳሙ እየደረሰበት ያለው መፍትሄ የሌለው ውድቀትና ችግር የአባ ገ/ሥላሴ (ታ
ጋይ በርሄ መብራህቱ) የስለላ ውጤቶች ናቸው። በወቅቱም ቢሆን በብስራት አማረ የሚመራው አፋኝና ሽብርተኛ ገዳይ ቡድን አድፍጠው በመጠባበቅ ብዙ ብፁአን አባቶችን፣ ቀሳውስቶችን፣ በርካታ ዲያቆናትን ደብዛቸውን አጥፍቷል። ሙታኖችን ገዳሙ ይቁጠራቅቸው። ለዚህ ሁሉ ወንጀል ተጠያዎቹ ስብሃት ነጋና ግደይ ዘርአጽዮን ናቸው።
እ.ኤ.አ በዴሴምበር 2013 አጋማሽ የኢትዮጵያ ወጣቶች ቃልኪዳናቸውን አድሰዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ የኃይማኖት ነጻነት እንዲከበር፣ ሰብአዊ መብቶች እንዲጠበቁ እና የህገ መንግስት እና ህዝባዊ ተጠያቂነት መኖርን በመጠየቅ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በአገሪቱ ማዕከል በሆነችው በ
አዲስ አበባ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡ በወጣቱ ስራ አጥነት፣ በዋጋ ግሽበት እና በተንሰራፋው ሙስና ላይ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ ገዥውን አካል ጠይቋል፡፡ እኔ በዚህ ሁኔታ በጣም ተመስጫለሁ፡፡ “በኢትዮጵያ ወጣቶች ረዥሙ የነጻነት እና የክብር ጉዞ ተጀምሯል፡፡ በጣም ቆንጆ ነገር ነው፡፡ በጣም ቆንጆ ነገር
ነው፣ ምክንያቱም ሰላማዊ ነው፡፡ በጣም ቆንጆ ነገር ነው፣ ምክንያቱም የአንዲት አገር ኢትዮጵያ ውድ ልጆች እርስ በእርሳቸው በመዋደድ እና በአገር ፍቅር ስሜት ሆ ብለው በአንድነት ሆነው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንዲህ እያሉ ሲጮሁ ነበር፣ “ከዚህ በኋላ ምንም ዓይነት ትዕግስት የለንም! ለውጥ እንፈልጋለን!”
ከክርስቶስ ልደት በኋላ ፡ በአንደኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በንግሥት ህንደኬ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የገባው የጥምቀት ዜና በአራት ኛው ክፍለ ዘመን በኦብርሃና አጽብሐ ዘመነ መንግሥት በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ስብከት ተስፋፍቶ አብዛኛው... Read more
«እርግጥ ነዉ እዚያ የሚገኙ አንዳንድ ጋዜጠኞችን አነጋግሬያለሁ፤ አንዳንዶቹ አዲስ አበባ ናቸዉ ሌሎቹ ደግሞ ስደት ላይ ይገኛሉ። በመሠረቱ በጣም ሰግተዋል፤ ምክንያቱም በበርካታ ሰበቦች በኢንተርኔት የቀጥታ ግንኙነት መገንገያዎች ላይ እጅግ የተመረኮዙ ናቸዉና። አንደኛዉ ከዋጋ አንፃር ወጪ ይቆጥባል፤ ምክንያቱም ምስራቅ
አፍሪቃና የአፍሪቃዉ ቀንድ ሀገሮች መካከል ስልክ ለመደወል በጣም ዉድ ነዉ፤ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከእነዚህ ስልቶች በአንዱ ብትጠቀሚ ደህንነቱ በጣም አስተማማኝ ነዉ፤ ግለሶቦች ግንኙነቱን ለመጥለፍም ያዳግታቸዋል፤ እናም በዚህ ምክንያት እኔ ያነጋገርኳቸዉ በርካታ ጋዜጠኞች እንዲህ ያለዉ ይፋዊ እገዳ የመገናኛ መንገዶችን