text
stringlengths
4
267
ምሥራቹን ለሰዎች የመስበኩ ሥራ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ እንገነዘባለን።
የስብከቱ ሥራ ከአምላክ ጋር ለሚታረቁ ሰዎች የዘላለም ሕይወት ማግኘት የሚችሉበት መንገድ ይከፍታል።
ኢየሱስ ይሖዋን፣ የአምላክን ቃልና ሰዎችን ይወድ ስለነበር የሌሎችን ልብ በሚነካ መንገድ ማስተማር ችሏል።
ወላጆችም እንዲህ ዓይነት ፍቅር ካላቸው የልጆቻቸውን ልብ መንካት ይችላሉ።
ስለሆነም ወላጆች መጽሐፍ ቅዱስንና ጽሑፎቻችንን በትጋት አጥኑ።
ለፍጥረት ሥራዎች እንዲሁም በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በጽሑፎቻችን ላይ ለሚወጡ ርዕሶች ትኩረት ስጡ።
እንዲህ ማድረጋችሁ ግንዛቤያችሁን የሚያሰፋና ለይሖዋ ያላችሁን አድናቆት የሚያሳድግ ከመሆኑም ሌላ ልጆቻችሁን ለማስተማር ይበልጥ ዝግጁ እንድትሆኑ ይረዳችኋል።
የእናንተ ልብ በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ከተሞላ ያወቃችሁትን ነገር ከቤተሰባችሁ ጋር ለመወያየት ትነሳሳላችሁ።
ይህን የምታደርጉት ለጉባኤ ስብሰባዎች ስትዘጋጁ ወይም የቤተሰብ አምልኮ ስታከናውኑ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ጊዜ ሊሆን ይገባል።
በተጨማሪም ከልጆቻችሁ ጋር እንዲህ ዓይነት ውይይት የምታደርጉት ይህን የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባችሁ ስለሚሰማችሁ ብቻ መሆን የለበትም፤ ከዚህ ይልቅ በዕለታዊ ጭውውታችሁ ውስጥ ልታካትቱት የሚገባ ነገር ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ በባልና ሚስት መካከል ከሚፈጸም የፆታ ግንኙነት ጋር የተያያዙ የፍቅር መግለጫዎች ምን ዓይነት ሊሆኑ እንደሚገባ ወይም እስከ ምን ድረስ መሄድ እንደሚቻል ዝርዝር መመሪያ ባይሰጥም አንዳንድ የፍቅር መግለጫዎችን ይጠቅሳል።
ክርስቲያን ባለትዳሮች አንዳቸው ለሌላው አሳቢነት ማሳየት አለባቸው።
ለአምላክና ለሌሎች ጥልቅ ፍቅር ካለን ማንኛውም ሰው ወይም ነገር በትዳራችን ውስጥ ጣልቃ እንዲገባ አንፈቅድም።
አንዳንድ ባለትዳሮች የብልግና ምስሎችንና ጽሑፎችን ፖርኖግራፊ የማየት ወይም የማንበብ ልማድ ስለተጠናወታቸው፣ በትዳራቸው ውስጥ ችግሮች ከመፈጠራቸውም አልፎ ትዳራቸው እስከ መፍረስ ደርሷል።
ፖርኖግራፊ የማየት ጉጉትም ሆነ ከትዳር ጓደኛችን ውጭ በማንኛውም መንገድ የፆታ ስሜትን የማርካት ፍላጎት እንዲያድርብን ፈጽሞ መፍቀድ አይኖርብንም።
የትዳር ጓደኛችን ያልሆነን ሰው እያሽኮረመምን እንዳለን የሚያስመስል ነገር ማድረግ እንኳ ፍቅር የጎደለው ድርጊት ስለሆነ ልንርቀው ይገባል።
አምላክ የምናስበውንም ሆነ የምናደርገውን ነገር ሁሉ እንደሚያውቅ ማስታወሳችን፣ እሱን የሚያሳዝን ነገር ከማድረግ እንድንቆጠብ የሚረዳን ከመሆኑም ሌላ ሥነ ምግባራዊ ንጽሕናችንን ለመጠበቅ ያስችለናል።
የቆላስይስ ክርስቲያኖች እንዲህ ያለውን ትክክለኛ እውቀት መቅሰማቸው ለይሖዋ በሚገባ ሁኔታ እንዲመላለሱና እሱን ሙሉ በሙሉ እንዲያስደስቱ ያስችላቸዋል።
ይህም በመልካም ሥራ ሁሉ በተለይም ምሥራቹን በመስበኩ ሥራ ፍሬ ማፍራታቸውን እንዲቀጥሉ ያስችላቸዋል።
አንድ የይሖዋ አገልጋይ በአገልግሎቱ ውጤታማ መሆን ከፈለገ በግሉ መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ረገድ ጥሩ ልማድ ሊኖረው ይገባል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ይህን እውነታ እንዲገነዘቡ መርዳታችን አስፈላጊ ነው።
በቅድሚያ ግን እኛ ራሳችን እንዲህ ዓይነቱን ልማድ ማዳበር ያለውን ጥቅም መገንዘብ ይኖርብናል።
በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስን በግላችን የማጥናት ጥሩ ልማድ ሊኖረን ይገባል።
ስለሆነም እንደሚከተለው እያልን ራሳችንን መጠየቅ እንችላለን፦ በአገልግሎት የማገኛቸው ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጩ ሐሳቦችን ቢጠቅሱ ወይም ከባድ ጥያቄዎችን ቢጠይቁኝ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ መልስ መስጠት እችላለሁ?
መጽሐፍ ቅዱስን በግላችን በማጥናታችን ምን ያህል እንደተጠቀምን ለሌሎች ከነገርናቸው፣ እነሱም ተመሳሳይ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ቅዱሳን መጻሕፍትን በትጋት ለማጥናት ሊነሳሱ ይችላሉ።
ይሖዋ ቅቡዓንን መምረጥ የጀመረው ኢየሱስ ሞቶ ከተነሳ በኋላ ነው፤ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረው የክርስቲያን ጉባኤ አባላት በሙሉ ቅቡዓን ሳይሆኑ አይቀሩም።
ከመጀመሪያው መቶ ዘመን በኋላ እስከ መጨረሻዎቹ ቀናት መባቻ ባለው ጊዜ ውስጥ፣ የክርስቶስ ተከታዮች ነን ይሉ የነበሩት አብዛኞቹ ሰዎች ሐሰተኛ ክርስቲያኖች ነበሩ፤ ኢየሱስ እነዚህን ሰዎች ከእንክርዳድ ጋር አመሳስሏቸዋል።
ያም ሆኖ ይሖዋ በዚያ ጊዜ ውስጥ ታማኝ የሆኑ አንዳንዶችን መቀባቱን የቀጠለ ሲሆን እነዚህ ሰዎች ኢየሱስ እንደጠቀሰው ስንዴ ሆነው ተገኝተዋል።
በመጨረሻዎቹ ቀናትም ይሖዋ የ144,000ዎቹን አባላት መቀባቱን ቀጥሏል።
ይሖዋ ለዚህ መብት ብቁ የሚሆኑ አንዳንድ ሰዎችን ለመምረጥ እስከ መጨረሻዎቹ ቀናት መገባደጃ ለመቆየት ከፈለገ በእሱ ጥበብ ላይ ጥያቄ ለማንሳት እኛ ማን ነን?
በ11ኛው ሰዓት ለተቀጠሩት ሠራተኞች ጌታው ባደረገው ነገር ቅር ተሰኝተው እንዳጉረመረሙት ሰዎች እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን።
በዛሬው ጊዜ አምላክ እንዲህ ያለ ጥያቄ አያቀርብልንም።
ሆኖም ትእዛዛቱን መፈጸም ከባድ በሚሆንብን ወይም አንድ ዓይነት መመሪያ የተሰጠበትን ምክንያት ሙሉ በሙሉ በማንረዳበት ጊዜም እንኳ እንድንታዘዘው ይጠብቅብናል።
ከአምላክ ትእዛዛት መካከል ለመታዘዝ የሚከብድህ አለ?
አንዳንዶች የስብከቱ ሥራ ከባድ ይሆንባቸዋል።
ዓይናፋር በመሆናቸው ለማያውቁት ሰው ምሥራቹን መንገር ይጨንቃቸው ይሆናል።
ሌሎች ደግሞ በትምህርት ቤት አሊያም በሥራ ቦታ አብረዋቸው ካሉት ሰዎች የተለዩ መሆን ተፈታታኝ ሊሆንባቸው ይችላል።
አንተም ልክ እንደ አብርሃም የሞሪያን ተራራ እየወጣህ ያለ ያህል፣ የተሰጠህ ሥራ ከአቅምህ በላይ እንደሆነ ይሰማሃል?
ከሆነ ስለ አብርሃምና ስላሳየው እምነት ማሰብህ ደፋር እንድትሆን ይረዳሃል! ታማኝ ወንዶችና ሴቶች በተዉት ምሳሌ ላይ ማሰላሰላችን እነሱን ለመምሰልና ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዲኖረን ለማድረግ ያነሳሳናል።
ሳኦል ዳዊትን ለመግደል ቆርጦ ስለተነሳ ዮናታን ለማን ታማኝ መሆን እንዳለበት ግራ ተጋብቶ ነበር።
ዮናታን ከዳዊት ጋር ቃል ኪዳን የተጋባ ቢሆንም ለአባቱም ታዛዥ ነበር።
ሆኖም ዮናታን፣ አምላክ ከዳዊት እንጂ ከሳኦል ጋር እንዳልሆነ ያውቅ ነበር።
በመሆኑም ዮናታን ከሳኦል ይበልጥ ለዳዊት ታማኝ ሆኗል።
ዳዊትን እንዲደበቅ ካስጠነቀቀው በኋላ ስለ እሱ ለአባቱ መልካም ነገር ተናግሯል።
እኛም ካልተጠነቀቅን ለአንድ አገር፣ ትምህርት ቤት ወይም የስፖርት ቡድን ያለን ታማኝነት ቀስ በቀስ ለአምላክ ካለን ታማኝነት ሊበልጥብን ይችላል።
ቼዝ መጫወት ይወድ የነበረውን የሄንሪን ሁኔታ እንደ ምሳሌ እንመልከት።
ትምህርት ቤቱ በቼዝ ውድድር ሁልጊዜ ያሸንፍ ስለነበር እሱም ለማሸነፍ የተቻለውን ጥረት ማድረግ እንዳለበት ይሰማው ነበር።
እንዲህ ብሏል፦ ለትምህርት ቤቴ የማሳየው ታማኝነት ለአምላክ ከማሳየው ታማኝነት ቀስ በቀስ እየበለጠ ሄደ።
ቅዳሜና እሁድ የሚደረጉት የቼዝ ጨዋታዎች ለመንግሥቱ አገልግሎት የማውለውን ጊዜ እየተሻሙብኝ መጡ።
በመሆኑም ከቼዝ ቡድኑ ለመውጣት ወሰንኩ።
በጉባኤ ውስጥ ለማገልገል እየሠለጠኑ ያሉ ወንድሞች ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር እንዲያስቡ መማር ይኖርባቸዋል።
ለምሳሌ ያህል፣ አንድ ሽማግሌ የመንግሥት አዳራሹን መግቢያ ለእይታ ማራኪ እንዲያደርግና እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮችን ከአካባቢው እንዲያስወግድ አንድን ወንድም ይጠይቀዋል።
በዚህ ጊዜ በመጥቀስ ወንድም በመንግሥት አዳራሹ የተሰጠውን ይህን ኃላፊነት መወጣቱ አዳኛችን የሆነው አምላክ ትምህርት በሁሉም መንገድ ውበት እንዲጎናጸፍ የሚያደርገው እንዴት እንደሆነ ይገልጽለታል።
በተጨማሪም ተማሪው የተሰጠውን ኃላፊነት መወጣቱ በጉባኤ ውስጥ ያሉትን አረጋውያን የሚጠቅመው እንዴት እንደሆነ ሊነግረው ይችላል።
ከተማሪው ጋር እንዲህ ያለ ውይይት ማድረጉ ሕግ በመፈጸም ላይ ሳይሆን ለሰዎች በማሰብ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ያሠለጥነዋል።
እሱ የሚያከናውነው አገልግሎት በጉባኤ ውስጥ ያሉ ወንድሞችንና እህቶችን ምን ያህል እየጠቀማቸው እንደሆነ ሲመለከት ይደሰታል።
በተጨማሪም ሽማግሌው ተማሪው የተሰጠውን ሐሳብ ተግባራዊ ለማድረግ ሲጥር ማመስገን እንዳለበት መርሳት አይኖርበትም።
አንድ አትክልት ውኃ ማግኘቱ እንዲለመልም እንደሚያደርገው ሁሉ ተማሪውም ልባዊ ምስጋና ማግኘቱ መንፈሳዊ እድገት እንዲያደርግ ይረዳዋል።
እውነተኛ ክርስቲያኖች የተዘረጋላቸው ተስፋ ምንኛ ግሩም ነው! ቅቡዓንም ሆንን ሌሎች በጎች ሁላችንም የአምላክ ዓላማ ሲፈጸምና የይሖዋ ስም ሲቀደስ ለማየት እንጓጓለን።
ይህ፣ ማንኛውም ሰው ሊኖረው ከሚችለው ሁሉ የላቀ ተስፋ ነው።
በተጨማሪም አምላክ ቃል የገባው አዲስ ሰማያት ወይም አዲስ ምድር ክፍል ሆነን የዘላለም ሕይወት ለማግኘት እንጠባበቃለን።
እስከዚያው ድረስ ደግሞ የአምላክ ሕዝቦች በመንፈሳዊ ይበልጥ እየበለጸጉ ሲሄዱ ለማየት እንናፍቃለን።
የሰይጣን ዓለም ክፍል የሆኑ ሰዎችም ተስፋ የሚያደርጓቸው ነገሮች አሉ፤ ሆኖም ተስፋቸው መፈጸም መቻሉን ይጠራጠሩ ይሆናል።
ለምሳሌ ያህል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቁማርተኞች ሎተሪ እንደሚያሸንፉ ተስፋ ያደርጋሉ፤ ይሁንና ማሸነፋቸውን እርግጠኞች መሆን አይችሉም።
በሌላ በኩል ግን እውነተኛ እምነት ሲባል ለክርስቲያኖች የተሰጠውን ተስፋ በእርግጠኝነት መጠበቅ ማለት ነው።
ዳዊት ልጁ ሰለሞን እንዲህ ያለውን ከባድ ሥራ ማለትም የአምላክን ቤት የመገንባቱን ሥራ ለመምራት ብቁ እንዳልሆነ ሊያስብ ይችል ነበር።
ምክንያቱም ቤተ መቅደሱ እጅግ የሚያምር መሆን ይኖርበታል፤ ሰለሞን ደግሞ በዚያ ወቅት ገና ወጣትና ተሞክሮ የሌለው ነበር።
ሆኖም ዳዊት፣ ሰለሞን የተሰጠውን ሥራ መወጣት እንዲችል ይሖዋ እንደሚረዳው ተገንዝቦ ነበር።
በመሆኑም ግንባታውን ለመደገፍ ማከናወን በሚችለው ነገር ላይ ትኩረት በማድረግ ለግንባታው የሚያስፈልገውን ቁሳቁስ በብዛት ማሰባሰብ ጀመረ።
በተመሳሳይም በዛሬው ጊዜ የሚገኙ በዕድሜ የገፉ ወንድሞች ኃላፊነታቸውን ለወጣት ወንድሞች ሲያስረክቡ ቅር ሊሰኙ አይገባም።
ምክንያቱም ወጣቶች ኃላፊነት ለመሸከም ብቁ እንዲሆኑ መሠልጠናቸው ሥራው በተሻለ መንገድ እንዲከናወን ያስችላል።
የተሾሙ ወንድሞች፣ እነሱ ያሠለጠኗቸው ወጣት ወንድሞች የእነሱን ሥራ ለመረከብ ብቁ ሆነው ሲገኙ ከፍተኛ እርካታ ሊሰማቸው ይገባል።
ይሖዋን እንድናመሰግነው የሚያነሳሱን በርካታ ምክንያቶች አሉን! ሕይወት ያገኘነው፣ የምንንቀሳቀሰውና የምንኖረው በእሱ ነው።
ውድ የሆነ ስጦታ ይኸውም ቃሉን መጽሐፍ ቅዱስን ሰጥቶናል።
በተሰሎንቄ እንደነበሩት ክርስቲያኖች እኛም የይሖዋን መልእክት እንደ አምላክ ቃል አድርገን በመቀበል አድናቆታችንን እናሳያለን።
በጽሑፍ የሰፈረው የአምላክ ቃል በእጃችን ስላለ ወደ ይሖዋ መቅረብ ችለናል፤ እሱም ወደ እኛ ቀርቧል።
በሰማይ ያለው አባታችን የድርጅቱ አባል የመሆን ውድ መብት ሰጥቶናል።
ከይሖዋ ያገኘናቸውን እንዲህ ያሉ በረከቶች በጣም እናደንቃለን! ይሖዋ ጥሩ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤ ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል በማለት እንደዘመረው መዝሙራዊ ይሰማናል።
ላይ ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል የሚለው አገላለጽ 26 ጊዜ ተጠቅሷል።
በፍጹም።
የበላይ አካሉ አባላት በመጀመሪያው መቶ ዘመን በነበረው ጉባኤ ላይ ሥልጣን ቢኖራቸውም መሪያቸው ኢየሱስ መሆኑን ያውቁ ነበር።
ሐዋርያው ጳውሎስ በሁሉም ነገር ወደ እሱ ይኸውም የአካሉ ራስ ወደሆነው ወደ ክርስቶስ በፍቅር እንደግ ሲል ጽፏል።
ደቀ መዛሙርቱ በአንድ ታዋቂ ሐዋርያ ስም ከመጠራት ይልቅ በመለኮታዊ አመራር ክርስቲያኖች ተብለው ተጠርተዋል።
እርግጥ ነው፣ ጳውሎስ ሐዋርያትና አመራር የሚሰጡ ሌሎች ወንዶች ያስተላለፏቸውን ወጎች ወይም በቅዱሳን መጻሕፍት ላይ የተመሠረቱ ልማዶች አጥብቆ መያዝ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁሟል።
ይሁንና እያንዳንዱን የበላይ አካል አባል ጨምሮ የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፣ የክርስቶስ ራስ ደግሞ አምላክ እንደሆነ እንድታውቁ እወዳለሁ በማለት አክሎ ተናግሯል።
በሰማይ ያለውና ክብር የተጎናጸፈው ክርስቶስ ኢየሱስ፣ በይሖዋ አምላክ ሥር ሆኖ ጉባኤውን እየመራ ነበር።
ይሖዋ እኛን በግለሰብ ደረጃ ለመቅረጽ በክርስቲያን ጉባኤና በሽማግሌዎች ይጠቀማል።
ለምሳሌ ያህል፣ ሽማግሌዎች ከመንፈሳዊነታችን ጋር በተያያዘ የሆነ ችግር እንዳለብን ካስተዋሉ እርዳታ ሊያደርጉልን ይሞክራሉ፤ ይህን የሚያደርጉት ግን በሰብዓዊ ጥበብ ላይ ተመርኩዘው አይደለም።
ይልቁንም ትሑት በመሆን አምላክ ማስተዋልና ጥበብ እንዲሰጣቸው ይጠይቃሉ።
ከዚያም የእኛን ሁኔታ ግምት ውስጥ አስገብተው በአምላክ ቃልና በክርስቲያናዊ ጽሑፎቻችን ላይ ምርምር በማድረግ ከጸሎታቸው ጋር የሚስማማ እርምጃ ይወስዳሉ።
ይህም በግለሰብ ደረጃ የሚያስፈልገንን እርዳታ ለመስጠት ያስችላቸዋል።
አምላክ እንዴት እንደሚቀርጸን መገንዘባችን፣ ከእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረን እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችንን ጨምሮ በክልላችን ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖረን ይረዳናል።
አምላክ ለውጥ እንዲያደርጉ ሰዎችን አያስገድድም፤ ይሁንና በፈቃዳቸው ሕይወታቸውን ለመለወጥና ማስተካከያዎችን ለማድረግ እንዲነሳሱ የጽድቅ መሥፈርቶቹን ያሳውቃቸዋል።
ጳውሎስ እንዲህ ብሎ ሲናገር የተግሣጽን አስፈላጊነት ወይም ዋጋማነት ማቃለሉ አልነበረም፤ ምክንያቱም ከዚያ በመቀጠል በኋላ ግን በተግሣጽ ሥልጠና ላገኙ ሰዎች የጽድቅን ሰላማዊ ፍሬ ያፈራላቸዋል ብሏል።
ይሖዋን የምንወደው ከሆነ ምክር ሲሰጠን ሰምተን እንዳልሰማን ከመሆን ወይም ቅር ከመሰኘት እንቆጠባለን።
ዛሬ ባለው ራስ ወዳድና እኔ ልቅደም ባይ በሆነ ትውልድ ውስጥ ምክርና ተግሣጽ መቀበል ይቅርና ስለ እነዚህ ነገሮች ማንሳት በራሱ አስቸጋሪ ነው።
አንዳንዶች ደግሞ ምክር ወይም ተግሣጽ ሲሰጣቸው ቢቀበሉም እንኳ ይህን የሚያደርጉት እያጉረመረሙ ነው።
ክርስቲያኖች ግን ይህ ሥርዓት እንዲቀርጻችሁ አትፍቀዱ የሚል ምክር ተሰጥቷቸዋል።
ከዚህ ይልቅ ፍጹም የሆነውን የአምላክ ፈቃድ መገንዘብና መፈጸም ይኖርብናል።
ይሖዋ በድርጅቱ አማካኝነት የተለያየ ወቅታዊ ምክር ይሰጠናል፤ ለምሳሌ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ሊኖረን ስለሚገባው ግንኙነት፣ ስለ ጓደኛ ምርጫና ስለ መዝናኛ ምክር እናገኛለን።