text stringlengths 4 267 |
|---|
እንዲህ ዓይነቱ ምርጫ ግን ውጤቱ አስከፊ ነው። |
ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ሌሎች ውሳኔ እንዲያደርጉልን መፍቀድ ያለውን አደጋ በተመለከተ በገላትያ ለነበሩት ክርስቲያኖች ግልጽ የሆነ ማሳሰቢያ ሰጥቷቸዋል። |
በጉባኤ ውስጥ የነበሩ አንዳንዶች ለሌሎች ውሳኔ ማድረግ ይፈልጉ ነበር። |
ሐዋርያው ዮሐንስ፣ አንድ ሰው በዓለም ውስጥ ያሉትን ነገሮች የሚወድ ከሆነ ይኸውም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ካለው እንዲሁም ኑሮዬ ይታይልኝ የሚል ከሆነ የአብ ፍቅር በውስጡ የለም ሲል ተናግሯል። |
በመሆኑም በዓለም ላይ ያለው መዝናኛና አለባበስ እንዲሁም ዓለማዊ ጓደኞች ልባችንን እየማረኩት መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ አዘውትረን ራሳችንን መመርመር ይኖርብናል። |
በሌላ በኩል ደግሞ ከፍተኛ ትምህርት በመከታተል ታላላቅ ነገሮችን ለማግኘት የምንጥር ከሆነ ዓለምን እንደምንወድ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል። |
አምላክ ቃል በገባልን አዲስ ዓለም ደፍ ላይ ነን። |
እንግዲያው ሙሴ ላይ የሰጠውን ጠንከር ያለ ምክር ማስታወሳችን በጣም አስፈላጊ ነው! አምላካችን ይሖዋ አንድ ይሖዋ መሆኑን ከተገነዘብንና ከልባችን ካመንን እሱን ብቻ እናመልከዋለን፤ እንዲሁም ተቀባይነት ባለው መንገድ እናገለግለዋለን። |
ማግባት የሚፈልጉ ክርስቲያኖች ጓደኝነትን በተመለከተ ይበልጥ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ የትዳር ጓደኛ የሚፈልጉ የአምላክ አገልጋዮች በጌታ ብቻ እንዲያገቡ ይኸውም ራሱን ወስኖ የተጠመቀና በመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርቶች የሚመራ የይሖዋ አገልጋይ ብቻ እንዲያገቡ ይመክራል። |
ክርስቲያኖች ከእምነት ባልንጀራቸው ጋር በትዳር ሲጣመሩ፣ ራሱን ለይሖዋ የወሰነና ንጹሕ አቋማቸውን ጠብቀው እንዲመላለሱ የሚያግዛቸው አጋር ያገኛሉ። |
ይሖዋ ለአገልጋዮቹ የተሻለው ነገር ምን እንደሆነ ያውቃል፤ በተጨማሪም ጋብቻን በተመለከተ ያለው አመለካከት ምንጊዜም አይለወጥም። |
በሙሴ አማካኝነት ለእስራኤላውያን የሰጠውን የማያሻማ መመሪያ እንመልከት። |
እስራኤላውያን፣ በዙሪያቸው ያሉ ሕዝቦችን ይኸውም ይሖዋን የማያገለግሉ ሰዎችን በተመለከተ የሚከተለው መመሪያ ተሰጥቷቸው ነበር፦ ከእነሱ ጋር በጋብቻ አትዛመድ። |
ምክንያቱም ልጆችህ ሌሎች አማልክትን ያገለግሉ ዘንድ እኔን ከመከተል ዞር እንዲሉ ያደርጓቸዋል። |
ሕሊናችንን ማሠልጠን የምንችለው እንዴት ነው? |
ዘወትር መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት፣ ባነበብነው ነገር ላይ ማሰላሰልና ያገኘነውን እውቀት በሥራ ላይ ማዋል ይህን ለማድረግ የሚያስችሉን ቁልፍ ነገሮች ናቸው። |
ይህ ሲባል ግን መረጃዎችን መሰብሰብና ደንቦችን ማጥናት ማለት ብቻ አይደለም። |
መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናታችን ስለ ይሖዋ፣ ስለ ማንነቱ፣ ስለ ባሕርያቱ እንዲሁም ስለሚወዳቸውና ስለሚጠላቸው ነገሮች ያለን ግንዛቤ ከዕለት ወደ ዕለት እያደገ እንዲሄድ ሊረዳን ይገባል። |
እንዲህ ከሆነ ሕሊናችን ይሖዋ አምላክ ካወጣቸው መሥፈርቶች ጋር የሚስማማ ይሆናል። |
ይህ ደግሞ ይበልጥ እሱን እየመሰልን እንድንሄድ ያነሳሳናል። |
ይሁንና አንድ የእምነት ባልንጀራችን በሕሊናው ተመርቶ ያደረገው የግል ውሳኔ ባይገባን ቸኩለን በእሱ ላይ መፍረድም ሆነ አስተሳሰቡን እንዲለውጥ መጫን አይገባንም። |
ምናልባት ሕሊናው አሁንም ደካማ ሊሆንና ተጨማሪ ሥልጠና ሊያስፈልገው ይችላል፤ አሊያም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ በጣም ጥብቅ ሊሆን ይችላል። |
እያንዳንዱ ግለሰብ ፈተና ውስጥ መግባት አለመግባቱ በራሱ ላይ የተመካ ነው። |
ኢየሱስ፣ ሰይጣን ያቀረበለትን እያንዳንዱን ፈተና ከአምላክ ቃል ውስጥ ተስማሚ ጥቅስ በመጥቀስ ወዲያውኑ ተቃውሟል። |
በዚህ መንገድ ኢየሱስ የአምላክን ሉዓላዊነት ደግፏል። |
ሰይጣን ግን ተስፋ አልቆረጠም። |
ሌላ አመቺ ጊዜ እስኪያገኝ ድረስ ጠበቀ። |
ኢየሱስም ቢሆን ንጹሕ አቋሙን እንዲያጎድፍ ሰይጣን ባደረገበት ተጽዕኖ አልተሸነፈም። |
ያም ቢሆን ሰይጣን አንተን ጨምሮ የኢየሱስን ተከታዮች ለማጥመድ ጥረት ያደርጋል። |
ከአምላክ ሉዓላዊነት ጋር በተያያዘ የተነሳው ጥያቄ መልስ ስላላገኘ ፈታኙ በዚህ ዓለም ተጠቅሞ እንዲፈትነን ይሖዋ ፈቅዶለታል። |
ወደ ፈተና የሚያስገባን አምላክ አይደለም። |
ከዚህ በተቃራኒ በእኛ የሚተማመን ከመሆኑም ሌላ ሊረዳን ይፈልጋል። |
ይሁንና ይሖዋ የመምረጥ ነፃነታችንን ሊጋፋ ስለማይፈልግ ወደ ፈተና እንዳንገባ አይከለክለንም። |
እኛ ሁለት ነገሮችን ማድረግ ይኸውም በመንፈሳዊ ንቁ መሆንና በጸሎት መጽናት አለብን። |
ክርስቲያኖች ከገለልተኝነት ጋር የተያያዘ ጉዳይ ሲነሳ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት አእምሯቸውንና ሕሊናቸውን ማሠልጠን ይኖርባቸዋል። |
በቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ ክልል ውስጥ የምትኖረውን ሚሪዬታን እንደ ምሳሌ እንውሰድ። |
ያደገችው ሰርቦችን በሚጠላ ማኅበረሰብ ውስጥ ነው። |
ይሖዋ የማያዳላ አምላክ እንደሆነና በዘር ልዩነት ምክንያት ለሚፈጠሩ ችግሮች ተጠያቂው ሰይጣን መሆኑን ስታውቅ ብሔራዊ ስሜትን ከውስጧ ለማጥፋት ትግል ማድረግ ጀመረች። |
በአካባቢዋ ከዘር ጋር የተያያዘ ግጭት ሲቀሰቀስ ግን ቀደም ሲል ለሰርቦች የነበራት ጥላቻ ማገርሸት ጀመረ፤ በመሆኑም ለሰርቦች መስበክ ከበዳት። |
ይሁንና እንዲህ ያለው ተገቢ ያልሆነ ስሜት በራሱ እንደሚጠፋ በማሰብ እጇን አጣጥፋ አልተቀመጠችም። |
ይሖዋ ይህንን ችግሯን ለመወጣት እንዲረዳት በጸሎት ለመነችው። |
ሚሪዬታ እንዲህ ብላለች፦ ከሁሉ በላይ የረዳኝ በአገልግሎቱ ላይ ትኩረት ማድረጌ ነው። |
በአገልግሎት ላይ የይሖዋን ፍቅር ለማንጸባረቅ እጥራለሁ፤ ይህም አሉታዊ ስሜትን ለማስወገድ ረድቶኛል። |
እዚህ ላይ መጣጣር ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ግስ፣ አንድን ነገር ምናልባትም በቀላሉ የማይደረስበትን ነገር ለመያዝ መንጠራራት የሚል መልእክት ያስተላልፋል። |
ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን ቃል የተጠቀመው መንፈሳዊ እድገት ማድረግ ጥረት እንደሚጠይቅ ለማጉላት ነው። |
በጉባኤው ውስጥ ወደፊት ሊያከናውን ስለሚችለው ነገር እያሰበ ያለን አንድ ወንድም ወደ አእምሯችን እናምጣ። |
በአሁኑ ጊዜ የጉባኤ አገልጋይ ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን ክርስቲያናዊ ባሕርያት ማዳበር እንዳለበት ይገነዘባል። |
መጀመሪያ፣ የጉባኤ አገልጋይ ለመሆን የሚያስፈልጉትን ብቃቶች ለማሟላት ይጥራል። |
ከጊዜ በኋላ ደግሞ የበላይ ተመልካች ለመሆን የሚያስፈልጉትን ብቃቶች ለማሟላት ግብ ያወጣል። |
ይህ ወንድም፣ የጉባኤ አገልጋይም ሆነ ሽማግሌ ለመሆን ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ በጉባኤ ውስጥ ተጨማሪ ኃላፊነት ለመሸከም የሚያስፈልጉትን ብቃቶች ለማሟላት ተግቶ ይሠራል። |
በተመሳሳይም አቅኚ፣ ቤቴላዊ እንዲሁም የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ፈቃደኛ ሠራተኛ ሆነው ማገልገል የሚፈልጉ ወንድሞችና እህቶች፣ ግባቸው ላይ ለመድረስ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው አስፈላጊ ነው። |
ይሖዋ በጸጋው ከሰጠን ግሩም በረከቶች አንዱ ልባችን ሲጨነቅ ማጽናኛ ማግኘት መቻላችን ነው። |
ጳውሎስ ስደት እየደረሰባቸው ለነበሩት በተሰሎንቄ የሚገኙ ክርስቲያኖች በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ ያለውን ሐሳብ ጽፏል። |
ይሖዋ በልግስና በሰጠን ጸጋ አማካኝነት በፍቅር እንደሚንከባከበን ማወቁ እንዴት ያበረታታል! ኃጢአተኞች በመሆናችን፣ ይሖዋ ባይረዳን ኖሮ ተስፋ አይኖረንም ነበር። |
ይሁንና ይሖዋ አስደናቂ ተስፋ ሰጥቶናል። |
ኢየሱስ ለተከታዮቹ የአባቴ ፈቃድ ወልድን የሚያውቅና በእሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው ብሏቸዋል። |
በእርግጥም የዘላለም ሕይወት ተስፋ፣ የአምላክ ጸጋ የተገለጸበት ግሩም ስጦታ ነው። |
ለዚህ ስጦታ አድናቆት የነበረው ጳውሎስ የአምላክ ጸጋ ተገልጧልና፤ ጸጋው ለሁሉም ዓይነት ሰዎች መዳን ያስገኛል ብሏል። |
ሐዋርያው ጴጥሮስ፣ አይሁዳዊ ላልሆኑ ሰዎች መሠረተ ቢስ ጥላቻ ነበረው፤ ውሎ አድሮ ግን እንዲህ ያለውን አሉታዊ አመለካከት ማስወገድ ችሏል። |
እኛም በተመሳሳይ ለሌሎች መሠረተ ቢስ ጥላቻ እንዳለን ወይም በዘራችን የመኩራት ዝንባሌ በውስጣችን እያቆጠቆጠ እንደሆነ ካስተዋልን፣ ይህን አመለካከት ከሥሩ ነቅለን ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ አለብን። |
ሁላችንም ለመዳን የማንበቃ ሰዎች መሆናችንን እንዲሁም ዜግነታችን ምንም ይሁን ምን ፍጽምና የጎደለን ሰዎች እንደሆንን ማስታወስ ይኖርብናል። |
ታዲያ ከሌሎች እንደምንበልጥ እንዲሰማን የሚያደርግ ምን ምክንያት አለን? |
ይልቁንም ሐዋርያው ጳውሎስ የነበረው ዓይነት አመለካከት ልናዳብር ይገባል፤ ጳውሎስ እንደ እሱ ቅቡዓን የሆኑትን የእምነት ባልንጀሮቹን ከዚህ በኋላ እንግዶችና ባዕዳን አይደላችሁም፤ ከዚህ ይልቅ የአምላክ ቤተሰብ አባላት ናችሁ በማለት አሳስቧቸዋል። |
ለሌላ አገር ሰዎች መሠረተ ቢስ ጥላቻ እንዳይኖረን ልባዊ ጥረት ማድረጋችን አዲሱን ስብዕና ለመልበስ ይረዳናል። |
ይሖዋ፣ እምነታችን ምንጊዜም ጠንካራ እንዲሆን እኛን ለመርዳት ሲል ቃሉን መጽሐፍ ቅዱስን በደግነት ሰጥቶናል። |
ደስተኛ እና ስኬታማ ለመሆን ከፈለግን የአምላክን ቃል አዘውትረን ከተቻለም በየዕለቱ ማንበብ አለብን። |
በተጨማሪም በቅድመ ክርስትና ዘመን እንደኖሩት የይሖዋ አገልጋዮች፣ አምላክ ቃል በገባቸው ነገሮች ላይ ማሰላሰል እንዲሁም የእሱን ትእዛዛት መጠበቅ አለብን። |
ይሖዋ በታማኝና ልባም ባሪያ አማካኝነት የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ምግብ ይሰጠናል። |
ይሖዋ ከሚያቀርብልን መንፈሳዊ ማዕድ የምንመገብ ከሆነ የመንግሥቱን ተስፋ በእርግጠኝነት እንደጠበቁት በጥንት ዘመን የኖሩ የእምነት ምሳሌዎች እንሆናለን። |
በቅድመ ክርስትና ዘመን የነበሩ የአምላክ ምሥክሮች እምነታቸው ምንጊዜም ጠንካራ እንዲሆን የረዳቸው ሌላው ነገር ደግሞ ጸሎት ነው። |
አምላክ ለጸሎታቸው የሚሰጠውን መልስ መመልከታቸው እምነታቸውን አጠናክሮታል። |
አንድ የደች ጋዜጣ፣ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ባደረጉት ስብሰባ ላይ የነበረውን ሁኔታ አስመልክቶ ሲዘግብ እንዲህ ብሏል፦ አየሩ ሞቃት በመሆኑ የብዙዎቹ አለባበስ በመዝናኛ ቦታ እንደሚታየው ዓይነት ነው። |
ጋዜጣው አክሎም እንዲህ ብሏል፦ በይሖዋ ምሥክሮች ትልቅ ስብሰባ ላይ ግን ሁኔታው ከዚህ የተለየ ነው። |
በእርግጥም የይሖዋ ምሥክሮች ልከኝነትና ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ የሚንጸባረቅበት እንዲሁም የሚያስከብርና ለአምላክ ያደርን ነን ለሚሉ ሰዎች የሚገባ አለባበስ ስላላቸው ብዙዎች ያደንቋቸዋል። |
ግርጌ ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን የጻፈው ስለ ሴቶች ቢሆንም መሠረታዊ ሥርዓቱ ለክርስቲያን ወንዶችም ይሠራል። |
የይሖዋ ሕዝቦች እንደመሆናችን መጠን ተገቢ አለባበስ ያለን መሆኑ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነገር ሲሆን የምናመልከው አምላክም ቢሆን ይህን ጉዳይ ከፍ አድርጎ ይመለከተዋል። |
ቅዱሳን መጻሕፍት ስለ አለባበስና አጋጌጥ የያዙት ሐሳብ፣ የአጽናፈ ዓለሙ ሉዓላዊ ገዢ እውነተኛ አገልጋዮቹ በአለባበስ ረገድ የላቀ መሥፈርት እንዲከተሉ እንደሚፈልግ በግልጽ ያሳያል። |
በመሆኑም ከአለባበስና ከአጋጌጥ ጋር በተያያዘ የምናደርገው ምርጫ ሉዓላዊውን ጌታ ይሖዋን የሚያስደስተውን ነገር ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ይኖርበታል። |
አንዳንዶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሰፈሩት ትንቢቶች ወይም መጽሐፍ ቅዱስ ከታሪክ፣ ከአርኪኦሎጂና ከሳይንስ አንጻር ትክክል ስለመሆኑ ለማጥናት ግብ አውጥተዋል። |
ምርምር ልታደርጉባቸው ከምትችሏቸው ትኩረት የሚስቡ ትንቢቶች አንዱ ላይ ይገኛል። |
ይህ ጥቅስ የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና ጭብጥ ምን እንደሆነ ይኸውም በአምላክ መንግሥት አማካኝነት የይሖዋ አገዛዝ ትክክለኛነት እንደሚረጋገጥና ስሙ እንደሚቀደስ ይጠቁመናል። |
በምሳሌያዊ አነጋገር የተቀመጠው ይህ ጥቅስ፣ ከኤደን ጀምሮ በሰው ልጆች ላይ የደረሱትን መከራዎች በሙሉ ይሖዋ እንዴት እንደሚያስወግድ ይገልጻል። |
ታዲያ ላይ ምርምር ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው? |
ይህን ማድረግ የምትችሉበት አንዱ መንገድ ክንውኖቹን በዘመን ቅደም ተከተል ማስፈር ሊሆን ይችላል። |
አምላክ፣ በዚህ ጥቅስ ላይ ከተገለጸው ዝግጅትና ከተጠቀሱት ግለሰቦች ጋር የተያያዙ እውነታዎችን ቀስ በቀስ እንዴት እንደገለጠ የሚጠቁሙ እንዲሁም ትንቢቱ እንዴት እንደሚፈጸም የሚያሳዩ ቁልፍ ጥቅሶችን በቅደም ተከተል ማስፈር ትችላላችሁ። |
ከዚያም ጥቅሶቹን አንድ ላይ ስትመለከቷቸው እርስ በርሱ የሚስማማ መልእክት እንደሚያስተላልፉ ታስተውላላችሁ፤ ይህን ስታዩ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ነቢያትና ጸሐፊዎች ሐሳቡን ያሰፈሩት በመንፈስ ቅዱስ ተገፋፍተው እንደሆነ መገንዘባችሁ አይቀርም። |
ጳውሎስ በጻፋቸው ደብዳቤዎች ላይ ለእምነት ባልንጀሮቹ ያለውን አድናቆት ገልጿል። |
ከአንዳንዶቹ ጋር ለዓመታት አብሮ ስለተጓዘ ያሉባቸውን ድክመቶች እንደሚያውቅ ጥርጥር የለውም፤ ያም ቢሆን ስለ እነሱ መልካም ነገር ተናግሯል። |
ለምሳሌ ያህል፣ ጳውሎስ ስለ ጢሞቴዎስ ሲናገር በጌታ ልጄ የሆነው የምወደውና ታማኝ የሆነው በማለት ገልጾታል፤ በተጨማሪም ጳውሎስ፣ ጢሞቴዎስ ለሌሎች ክርስቲያኖች ከልቡ እንደሚያስብ ተናግሯል። |
ሐዋርያው ስለ ቲቶ ለቆሮንቶስ ጉባኤ ሲጽፍ ደግሞ ለእናንተ ጥቅም አብሮኝ የሚሠራ ባልደረባዬ በማለት ለእሱ ያለውን አድናቆት ገልጿል። |
ጢሞቴዎስና ቲቶ፣ ጳውሎስ ለእነሱ ያለውን አመለካከት ሲያውቁ ምንኛ ተበረታተው ይሆን! ጳውሎስና በርናባስ፣ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ በመጣል ከዚያ ቀደም ጥቃት ተሰንዝሮባቸው ወደነበሩ ቦታዎች ተመልሰው ሄደዋል። |
ለምሳሌ ያህል፣ በልስጥራ ከባድ ተቃውሞ አጋጥሟቸው የነበረ ቢሆንም ወደዚያ ተመልሰው በመሄድ አዳዲስ ደቀ መዛሙርትን በእምነት ጸንተው እንዲኖሩ አበረታተዋል። |
ጳውሎስ በኤፌሶን በቁጣ የተሞሉ ሰዎች ከተነሱበት በኋላ በዚያ የነበሩትን ደቀ መዛሙርት አበረታቷቸዋል። |
ኢየሱስ ከአባቱ ጋር አብሮ በደስታ ይሠራ የነበረ ሲሆን ባከናወነው ነገር እንዲሁም ይሖዋ በእሱ ደስ እንደሚሰኝ በማወቁ ሐሴት ያደርግ ነበር። |
ስለ እኛስ ምን ማለት ይቻላል? |
ኢየሱስ መቀበልም ሆነ መስጠት ደስታ እንደሚያስገኝ ተናግሯል። |
እውነትን ማግኘታችን አስደስቶናል፤ እውነትን ለሌሎች ማካፈላችንም ደስታ ያስገኝልናል። |
የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች የምንነግራቸው በመንፈሳዊ የተራቡ ሰዎች፣ ስለ አምላካችን ሲያውቁና በቃሉ ውስጥ የሰፈሩትን ውድ እውነቶች ሲገነዘቡ ልባቸው በደስታ ይሞላል። |
እኛም እነዚህ ሰዎች በአስተሳሰባቸው ብቻ ሳይሆን በሕይወታቸው ውስጥም ለውጦች ሲያደርጉ ስንመለከት ልባችን ሐሴት ያደርጋል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.