text stringlengths 4 267 |
|---|
ለምሳሌ ያደግከው እውነት ቤት ውስጥ ሊሆን ይችላል። |
ባለፉት ዓመታት አንዳንድ እኩዮችህን አልፎ ተርፎም ወንድሞችህንና እህቶችህን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ሲጠመቁ ተመልከተህ ይሆናል። |
እንዲህ ያለ ሁኔታ አጋጥሞህ ከሆነ ምን ዓይነት ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብሃል? |
ጥምቀት፣ ይዋል ይደር እንጂ ሁሉም ወጣቶች የሆነ ዕድሜ ላይ ሲደርሱ በዘልማድ ሊወስዱት የሚገባ እርምጃ እንደሆነ አድርገህ እንዳታስብ ተጠንቀቅ። |
ታዲያ ይሖዋ ስላደረገው የጥምቀት ዝግጅት ተገቢ አመለካከት እንዲኖርህ ምን ይረዳሃል? |
መጠመቅ በጣም አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት ቆም ብሎ ማሰብን ልማድ አድርግ። |
አምላክ ሳኦልን ንጉሥ እንዲሆን የቀባው ቢሆንም ከጊዜ በኋላ ሳኦል ታዛዥ ሳይሆን በመቅረቱ ይሖዋ ተወው። |
አምላክ ሳኦልን ከሥልጣኑ ወዲያው ስላላወረደው፣ የእሱ መጥፎ ድርጊት ለተገዢዎቹም ሆነ በቅርቡ ለነበሩት ሰዎች ፈተና ሆኖባቸው ነበር። |
በይሖዋ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ንጉሥ የተከተለውን መጥፎ አካሄድ እየተመለከቱ ለአምላክ ታማኝ መሆን ተፈታታኝ ነበር። |
ሆኖም የሳኦል ልጅ ዮናታን ለይሖዋ ታማኝ መሆኑን አሳይቷል። |
እኛም አንዳንድ የበላይ ባለሥልጣናት ክብር ሊሰጣቸው እንደማይገባ ይሰማን ይሆናል፤ ሆኖም አምላክ ባዘዘው መሠረት ሁኔታው በሚፈቅድበት ጊዜ ሁሉ ለእነሱ በመገዛት ለይሖዋ ታማኝ መሆናችንን ማሳየት እንችላለን። |
ለምሳሌ ያህል፣ አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ምግባረ ብልሹ ሊሆን ይችላል፤ ያም ሆኖ ለበላይ ባለሥልጣናት በአንጻራዊ ሁኔታ መገዛት ስላለብን ሥልጣኑን እናከብራለን። |
ሁላችንም ይሖዋ ሥልጣን ለሰጣቸው ሰዎች አክብሮት በማሳየት ለእሱ ታማኝ መሆን እንችላለን። |
እንዴት? |
አንዳንድ ሽማግሌዎች ጊዜ መድበው ሌሎችን ማሠልጠን ከባድ ይሆንባቸዋል። |
እንዲህ ብለው ያስቡ ይሆናል፦ ሌሎችን ማሠልጠን አስፈላጊ ቢሆንም ጊዜ ከማይሰጡ ሌሎች የጉባኤ ሥራዎች አንጻር ሲታይ ያን ያህል አጣዳፊ አይደለም። |
ሥልጠናውን በሌላ ጊዜ ባደርገው ጉባኤው ላይ የሚያመጣው ጉዳት የለም። |
የአንድን ሽማግሌ ጊዜ የሚፈልጉ በርካታ ጉዳዮች መኖራቸው እውነት ቢሆንም ሥልጠናውን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ የጉባኤውን መንፈሳዊ ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥለው ይችላል። |
ሽማግሌዎች ሊያከናውኗቸው የሚገቡ በርካታ አጣዳፊ ጉዳዮች አሉ። |
ሆኖም ሽማግሌዎች ሥልጠናውን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፋቸውን ከቀጠሉ ይዋል ይደር እንጂ ጉባኤው አስፈላጊ ሥራዎችን የሚያከናውኑ ብቃት ያላቸው ወንድሞችን በማጣት መቸገሩ አይቀርም። |
ከዚህ በግልጽ ማየት እንደሚቻለው ሥልጠና መስጠት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም የሚለውን አስተሳሰብ ማስወገድ ይኖርብናል። |
ልምድ የሌላቸውን ወንድሞች ለማሠልጠን ጊዜያቸውን መሥዋዕት የሚያደርጉና አርቆ አሳቢ የሆኑ ሽማግሌዎች ጥበበኛ መጋቢዎች ከመሆናቸውም በላይ ለጉባኤው በረከት ናቸው። |
በጥንት ዘመን የነበሩት እስራኤላውያን ዓመታዊ በዓል በሚከበርበት ወቅት ኢየሩሳሌም በሚገኘው ቤተ መቅደስ ተገኝተው ይሖዋን ሲያወድሱ ይታይህ። |
ለጉዞ መዘጋጀት፣ በጉዞ ወቅት እርስ በርስ መረዳዳት ከዚያም ቤተ መቅደስ ውስጥ ይሖዋን በአንድነት ማምለክ ነበረባቸው። |
ይህ ሁሉ ትብብር የሚጠይቅ ነገር ነው። |
እኛም ወደ አዲሱ ዓለም በምናደርገው ጉዞ ላይ እርስ በርስ መስማማትና መተባበር ያስፈልገናል። |
እስቲ ስለሚጠብቁን በረከቶች አስብ! በአሁኑ ጊዜ እንኳ በዓለም ውስጥ ከሚታየው መከፋፈልና ግራ መጋባት ተገላግለናል። |
ኢሳይያስና ሚክያስ የተናገሩት ትንቢት ሲፈጸም እየተመለከትን ነው፤ የአምላክ ሕዝቦች አንድ ላይ ሆነው ወደ ይሖዋ ተራራ እየወጡ ነው። |
በእርግጥም በዘመኑ መጨረሻ ለይሖዋ የምናቀርበው አምልኮ እጅግ የላቀ ነው። |
አንድ የመንግሥት አዳራሽ ተገንብቶ ከተጠናቀቀ በኋላ ደግሞ የምናመልከውን አምላክ ባሕርያትና ማንነት ይኸውም የሥርዓት አምላክ መሆኑን የሚያንጸባርቅ እንዲሆን በንጽሕና መያዝ አለበት። |
መጽሐፍ ቅዱስ ቅድስናን እንዲሁም መንፈሳዊ ንጽሕናን ከአካላዊ ንጽሕና ጋር ያያይዘዋል። |
በመሆኑም አንድ ሰው በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት ከፈለገ ንጽሕናውንም መጠበቅ አለበት። |
ከእነዚህ መሠረታዊ ሥርዓቶች አንጻር የአዳራሹ ሁኔታ ከምንሰብከው ምሥራች ጋር የሚስማማ መሆን አለበት፤ ይህም ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ምንጊዜም ወደ ስብሰባዎቻችን ለመጋበዝ ነፃነት እንዲሰማን ያደርጋል። |
የምንጋብዛቸው ሰዎች አምላካችን ቅዱስ እንደሆነ መመልከት እንዲሁም በቅርቡ ምድርን በመለወጥ ከብክለት የጸዳች ገነት እንደሚያደርጋት መገንዘብ ይችላሉ። |
በአካባቢው ያለው ሁኔታ ምንም ይሁን ምን፣ የመንግሥት አዳራሾቻችን ንጹሕና ሥርዓታማ በመሆን ረገድ አርዓያ ሊሆኑ ይገባል፤ ምክንያቱም የይሖዋ ስም የሚጠራባቸው ከመሆኑም ሌላ የንጹሕ አምልኮ ማዕከል ናቸው። |
ኢየሱስ ስለ ዕለት ምግባችን ሲጠቅስ በየቀኑ ስለሚያስፈልገን ነገር መናገሩ እንደሆነ ግልጽ ነው። |
አምላክ፣ አበቦችን እንደሚያለብስ ከገለጸ በኋላ እንዲህ አለ፦ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፣ እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁም? |
ከዚያም ስለ ነገ ፈጽሞ አትጨነቁ የሚለውን ጠቃሚ ምክር በድጋሚ በመናገር ሐሳቡን ደመደመ። |
ይህም ለቁሳዊ ነገሮች ፍቅር ከማዳበር ይልቅ መሠረታዊ ስለሆኑት በየዕለቱ የሚያስፈልጉን ነገሮች ብቻ ማሰብ እንዳለብን ያሳያል። |
ከእነዚህ ፍላጎቶች መካከል ተስማሚ መኖሪያ፣ ቤተሰባችንን ለማስተዳደር የሚያስችለን ሥራ እንዲሁም የጤና ችግሮችን ለመወጣት የሚረዳን ጥበብ ይገኙበታል። |
ይሁንና የምንጸልየው ከአካላዊ ፍላጎታችን ጋር ስለተያያዙት ስለ እነዚህ ነገሮች ብቻ ከሆነ ይህ ሚዛናዊ እንዳልሆንን የሚጠቁም ነው። |
ምክንያቱም ከዚህ ይበልጥ ትልቅ ቦታ ልንሰጠው የሚገባ መንፈሳዊ ፍላጎት አለን። |
ጌታችን ሰው ከይሖዋ አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በምግብ ብቻ አይኖርም ብሏል። |
እንግዲያው ይሖዋ በጊዜው መንፈሳዊ ምግብ ማቅረቡን እንዲቀጥል ምንጊዜም ልንጸልይ ይገባል። |
ፈተና ሲያጋጥመን ንጹሕ አቋማችንን ለመጠበቅ እንዲረዳን አምላክን አዘውትረን እንለምነዋለን? |
አስተዳደጋችን ወይም የቀድሞ አኗኗራችን ይሖዋ የሚጠላቸውን ነገሮች እንድንወድ ተጽዕኖ ያደርግብን ይሆናል። |
ያም ቢሆን ይሖዋ፣ እሱን ተቀባይነት ባለው መንገድ ማገልገላችንን እንድንቀጥል የሚያስፈልጉትን ለውጦች ለማድረግ ይረዳናል። |
ንጉሥ ዳዊት ይህን ተገንዝቦ ነበር። |
ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር ምንዝር ከፈጸመ በኋላ ይሖዋን ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤ በውስጤም ጽኑ የሆነ አዲስ መንፈስ አኑር በማለት ተማጽኖታል። |
ደካማው ሥጋችን በኃጢአት ድርጊቶች በቀላሉ ሊማረክ ይችላል፤ ይሁንና ይሖዋ የፈቃደኝነት መንፈስ ይኸውም እሱን የመታዘዝ ፍላጎት በውስጣችን እንዲቀሰቀስ ሊረዳን ይችላል። |
መጥፎ ምኞቶች በውስጣችን ሥር ሰደው ንጹሕ ሐሳቦችን ገፍተው ለማውጣት ቢሞክሩም እንኳ ይሖዋ የእሱን መመሪያዎች በመታዘዝ በዚያ መሠረት መኖር እንድንችል አካሄዳችንን ይመራልናል። |
ይሖዋ ማንኛውም ጎጂ ነገር በእኛ ላይ እንዳይሠለጥን ሊከላከልልን ይችላል። |
የመጀመሪያው ሰው የአዳም ልጆች በመሆናችን ሁላችንም ኃጢአትንና የኃጢአት ደሞዝ የሆነውን ሞትን ወርሰናል። |
ማናችንም ብንሆን ቤዛው አያስፈልገኝም ማለት አንችልም። |
በጣም ታማኝ የሆነ የአምላክ አገልጋይም እንኳ ይሖዋ በክርስቶስ በኩል ያሳየን ጸጋ የግድ ያስፈልገዋል። |
ሁላችንም ከፍተኛ ዕዳ እንደተሰረዘልን መገንዘብ ይኖርብናል። |
ታዲያ የይሖዋ ፍቅርና ምሕረት ምን እንድናደርግ ሊያነሳሳን ይገባል? |
በወንድሞቻችን ወይም በእህቶቻችን ላይ ቂም ይዘን ከሆነ ይቅር ለማለት ዝግጁ የሆነውን ይሖዋን መምሰል ይኖርብናል። |
ይሖዋ ከፍተኛ መጠን ያለውን ዕዳችንን በመሰረዝ ላደረገልን ነገር አድናቆት ካለን እኛም ሌሎችን ከልባችን ይቅር ለማለት እንነሳሳለን። |
ለሌሎች ፍቅርና ምሕረት የማናሳይ ከሆነ አምላክ ሊወደን ወይም ይቅር ሊለን አይችልም። |
ይቅር ማለታችን የደረሰብንን በደል ባያስቀረውም በወደፊት ሕይወታችን ላይ በጎ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ጥርጥር የለውም። |
ጴጥሮስና ሌሎች ደቀ መዛሙርት የወደፊቱን ጊዜ በአእምሯቸው እንዲስሉ ለመርዳት ኢየሱስ በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ ያለውን ሐሳብ ነገራቸው። |
እነሱም ምድርን በሚያስተዳድረውና ታዛዥ ለሆኑ የሰው ልጆች አስደናቂ በረከቶችን በሚያመጣው የአምላክ መንግሥት ውስጥ በሚኖራቸው ድርሻ ላይ ማሰላሰል ይችሉ ነበር። |
በየትኛውም ጊዜ በምድር ላይ የኖሩ የአምላክ አገልጋዮች፣ አምላክ ቃል ስለገባቸው ነገሮች ፍጻሜ በማሰባቸው ተጠቅመዋል። |
አቤል ስለ አምላክ ዓላማ ያወቀው ነገር የተሻለ የወደፊት ሕይወት እንደሚመጣ ለማሰብ፣ እምነት ለማዳበርና አስተማማኝ ተስፋ እንዳለው ለማመን አስችሎታል። |
አብርሃም ታላቅ እምነት እንዳለው የሚያሳዩ ነገሮችን ያከናወነው፣ ተስፋ ከተሰጠበት ዘር ጋር በተያያዘ አምላክ ስለተናገረው ትንቢት ፍጻሜ በዓይነ ሕሊናው በማየቱ ነው። |
ሙሴ የሚከፈለውን ወሮታ በትኩረት ተመልክቷል፤ በመሆኑም እምነትና ለይሖዋ ፍቅር ማዳበር ችሏል። |
በአምላክ ላይ ያለን እምነትና ለእሱ ያለን ፍቅር ይሖዋ ቃል የገባቸውን ነገሮች በዓይነ ሕሊናችን እንድንመለከት ሊረዳን ይችላል። |
ክርስቲያኖች በጦርነት ጊዜ ብቻ ሳይሆን መቼም ቢሆን ታማኝ የመሆናቸውና የገለልተኝነት አቋማቸውን የመጠበቃቸው ጉዳይ ያሳስባቸዋል። |
ለምን? |
ምክንያቱም ራሳቸውን ለይሖዋ የወሰኑ ሁሉ እሱን ሊወዱት፣ ታማኝ ሊሆኑለትና ሊታዘዙት ቃል ገብተዋል። |
የምንኖረው የትም ይሁን የት እንዲሁም አስተዳደጋችን፣ ዜግነታችን ወይም ባሕላችን ምንም ይሁን ምን በአምላክ የጽድቅ መሥፈርቶች ለመመራት እንፈልጋለን። |
ለይሖዋና ለመንግሥቱ ያለንን ታማኝነት ለሌላ ለማንኛውም ነገር ካለን ፍቅር እናስበልጣለን። |
ክርስቲያኖች እንዲህ ዓይነት ታማኝነት ለማሳየት በዚህ ዓለም ላይ በሚፈጠር በየትኛውም ግጭት ወይም ውዝግብ ውስጥ ከመግባት መቆጠብ አለባቸው። |
የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ ሰዎች ለአገራቸው፣ ለዘራቸው ወይም ለባሕላቸው አልፎ ተርፎም ለብሔራዊ የስፖርት ቡድናቸው ልዩ ታማኝነት ማሳየት እንዳለባቸው ይሰማቸው ይሆናል። |
እንዲህ ያለው ታማኝነት የውድድርና የፉክክር መንፈስ እንዲኖር ይባስ ብሎም ደም መፋሰስና የጅምላ ጭፍጨፋ እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል። |
እኛም በዓለም ላይ ባሉ ውዝግቦች ረገድ ሳናስበው ከአንዱ ወገን እንቆም እንዲሁም በቀላሉ ውዝግቡ ውስጥ እንገባ ይሆናል። |
የአምላክ ቃል፣ ከበድ ያለ ውሳኔ በምናደርግበት ጊዜ እንዳንቸኩል ያሳስበናል። |
ከምናደርገው ውሳኔ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ወይም ሁኔታዎችን በሙሉ ጊዜ ወስደን በሚገባ መመርመራችን ጥሩ ውሳኔ እንድናደርግ ይረዳናል። |
የቤተሰብ ራሶች አንድ ውሳኔ ላይ ከመድረሳቸው በፊት በአምላክ ቃልና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በተመሠረቱ ጽሑፎች ላይ ምርምር ማድረጋቸው እንዲሁም ሌሎች የቤተሰባቸው አባላት ያላቸውን አመለካከት ግምት ውስጥ ማስገባታቸው አስፈላጊ ነው። |
አምላክ፣ አብርሃምን የሚስቱን ሐሳብ እንዲሰማ እንዳሳሰበው አስታውስ። |
ሽማግሌዎችም ጊዜ ወስደው ምርምር ማድረግ አለባቸው። |
ምክንያታዊና ትሑት ከሆኑ፣ ውሳኔያቸውን እንደገና ማጤን እንዳለባቸው የሚያሳይ ጠቃሚ የሆነ አዲስ መረጃ ሲያገኙ፣ ሌሎች ለእነሱ ያላቸው አክብሮት እንዳይቀንስ በመፍራት ይህን ከማድረግ ወደኋላ አይሉም። |
አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ አመለካከታቸውንና ውሳኔያቸውን ለማስተካከል ፈቃደኞች መሆን አለባቸው፤ ሁላችንም ብንሆን የእነሱን ምሳሌ መከተላችን ጠቃሚ ነው። |
ይህም በጉባኤ ውስጥ ሰላምና ሥርዓት እንዲሰፍን አስተዋጽኦ ያደርጋል። |
ኢዮስያስ አምላክን የሚያስደስተውን ነገር በቅንዓት አከናውኗል። |
እንደ ኢዮስያስ ሁሉ በዛሬው ጊዜ ያሉ ልጆችም ከትንሽነታቸው አንስቶ ይሖዋን መፈለግ አለባቸው። |
ንጉሥ ምናሴ ንስሐ ከገባ በኋላ ኢዮስያስን ስለ አምላክ ምሕረት አስተምሮት ሊሆን ይችላል። |
ልጆች የሆናችሁ፣ በቤተሰባችሁና በጉባኤያችሁ ውስጥ ካሉ ታማኝ የሆኑ ትላልቅ ወንድሞችና እህቶች ጋር ብትቀራረቡ ይሖዋ ስላደረገላቸው በርካታ መልካም ነገሮች ሊነግሯችሁ ይችላሉ። |
በተጨማሪም ኢዮስያስ ቅዱሳን መጻሕፍት ምን እንደሚሉ ማወቁ ልቡ እንዲነካና እርምጃ እንዲወስድ እንዳነሳሳው አስታውሱ። |
እናንተም የአምላክን ቃል ማንበባችሁ ደስታችሁ እንዲጨምር፣ ከአምላክ ጋር ያላችሁ ወዳጅነት እንዲጠናከር እንዲሁም ሌሎች አምላክን እንዲፈልጉ ለመርዳት እንድትነሳሱ ሊያደርግ ይችላል። |
ከዚህም ሌላ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናታችሁ ለአምላክ በምታቀርቡት አገልግሎት ረገድ ማሻሻያ ማድረግ የምትችሉባቸውን መንገዶች እንድታስተውሉ ይረዳችኋል። |
ማሻሻያ ማድረግ እንደሚያስፈልጋችሁ ከተሰማችሁ ልክ እንደ ኢዮስያስ ለውጥ ለማድረግ የተቻላችሁን ጥረት አድርጉ። |
ውሳኔ ማድረግ የእያንዳንዳችን ኃላፊነት ነው፤ በተጨማሪም ጥበብ የሚንጸባረቅበትና ትክክለኛ ውሳኔ ማድረግ የምንችለው ቅዱስ ጽሑፋዊ እውቀት ሲኖረን ነው። |
ሌላ ሰው ውሳኔ እንዲያደርግልን ኃላፊነቱን ልንሰጠው አይገባም። |
ከዚህ ይልቅ በአምላክ ዓይን ትክክል የሆነውን ነገር ራሳችን ለይተን ማወቅና ይህን ለመከተል መምረጥ ይኖርብናል። |
ሌሎች ሰዎች ውሳኔ እንዲያደርጉልን በመፍቀድ አደገኛ የሆነ አካሄድ ልንከተል የምንችለው እንዴት ነው? |
የእኩዮች ተጽዕኖ መጥፎ ውሳኔዎችን እንድናደርግ ሊገፋፋን ይችላል። |
ሌሎች ሰዎች ምንም ያህል ተጽዕኖ ሊያደርጉብን ቢሞክሩም በመጽሐፍ ቅዱስ የሠለጠነውን ሕሊናችንን መከተል የእኛ ኃላፊነት ነው። |
ሌሎች ውሳኔ እንዲያደርጉልን የምንፈቅድ ከሆነ እነሱን ለመከተል መርጠናል ማለት ነው። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.