text stringlengths 4 267 |
|---|
እንዲህ ያለውን መመሪያ በፈቃደኝነት በመቀበልና ተግባራዊ በማድረግ አመስጋኝ መሆናችንን እንዲሁም ይሖዋን ከልባችን እንደምንወደው እናሳያለን። |
ሐዋርያው ዮሐንስ ያሰፈረውን ይህን ሐሳብ በጥልቀትና በአድናቆት ልናስብበት ይገባል። |
ዮሐንስ አብ ምን ያህል ታላቅ ፍቅር እንዳሳየን ተመልከቱ ሲል ክርስቲያኖች አምላክ ለእነሱ ያለው ፍቅር ምን ያህል ጥልቅና ሰፊ እንደሆነ እንዲሁም ፍቅሩን ያሳየበትን መንገድ እንዲያስቡ ማበረታታቱ ነበር። |
ከዚህ አንጻር የይሖዋን ፍቅር መረዳት ከቻልን ለእሱ ያለን ፍቅር ያድጋል፤ እንዲሁም ከእሱ ጋር ያለን ዝምድና ይጠናከራል። |
ይሁንና አንዳንዶች አምላክ ሰዎችን ይወዳል የሚለው ሐሳብ አይዋጥላቸውም። |
አምላክ፣ ሰዎች እንዲፈሩትና እንዲታዘዙት ብቻ የሚፈልግ አካል እንደሆነ አድርገው ያስባሉ። |
አሊያም በውስጣቸው ሥር ከሰደደ የተሳሳተ ትምህርት የተነሳ ሊሆን ይችላል አምላክ አፍቃሪ እንዳልሆነና እነሱም ሊወዱት እንደማይችሉ ይሰማቸዋል። |
በአንጻሩ ደግሞ የፈለጉትን ነገር ቢያደርጉም ወይም የሚጠበቅባቸውን ነገር ሳያደርጉ ቢቀሩም እንኳ አምላክ እንደሚወዳቸው የሚያምኑ ሰዎች አሉ። |
መጽሐፍ ቅዱስን ስታጠና ፍቅር የይሖዋ ዋነኛ ባሕርይ እንደሆነና ለእኛ ሲል ልጁን ቤዛ አድርጎ እንዲሰጥ ያነሳሳውም ፍቅር መሆኑን ተምረሃል። |
ጮክ ብሎ ማንበብ ያነበቡትን ነገር በቀላሉ ለማስታወስ እንደሚረዳ ሳይንሳዊ የምርምር ውጤቶች አረጋግጠዋል። |
አእምሯችንን የፈጠረው አምላክ ደግሞ ይህን ያውቃል። |
በመሆኑም ኢያሱን የሕጉን መጽሐፍ በለሆሳስ አንብበው በማለት አዞታል። |
መጽሐፍ ቅዱስን ዝቅ ባለ ድምፅ ወይም በለሆሳስ ማንበብ የምታነበው ነገር አእምሮህ ላይ በሚገባ እንዲቀረጽ ያደርጋል። |
ይህም በተሻለ ሁኔታ አእምሮህን መሰብሰብ እንድትችል ይረዳሃል። |
ማንበብ ብዙ ጥረት የሚጠይቅ ባይሆንም ማሰላሰል ግን ትኩረትን ማሰባሰብ ይጠይቃል። |
ፍጽምና የሚጎድለው የሰው አእምሮ ብዙ ማሰብ በማይጠይቁና እምብዛም አድካሚ ባልሆኑ ሥራዎች በቀላሉ የመወሰድ አዝማሚያ ያለው ከዚህ የተነሳ ነው። |
በመሆኑም ለማሰላሰል ይበልጥ አመቺ የሆነው ጊዜ ዘና የምትልበት እንዲሁም ትኩረትህን የሚሰርቁና የሚያስጨንቁ ነገሮች የሌሉበት ወቅት ነው። |
መዝሙራዊው፣ ሌሊት ከእንቅልፉ የሚነቃበት ጊዜ ለማሰላሰል ጥሩ ሰዓት እንደሆነ ተረድቷል። |
ፍጹም አእምሮ የነበረው ኢየሱስ ጸጥ ባለ ቦታ ማሰላሰልና መጸለይ ምን ያህል ጥቅም እንዳለው ተገንዝቦ ነበር። |
በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረው የክርስቲያን ጉባኤ አይሁዳውያንን፣ ግሪካውያንን፣ ሮማውያንንና ሌሎች ዜጎችን ያቀፈ ነበር። |
እነዚህ ሰዎች የተለያየ ሃይማኖት፣ ባሕልና ምርጫ ነበራቸው። |
በዚህም የተነሳ አንዳንዶች አዲሱን የአምልኮ ሥርዓት መከተል ወይም የቀድሞ ልማዶቻቸውን ሙሉ በሙሉ መተው ከብዷቸው ነበር። |
በመሆኑም ሐዋርያው ጳውሎስ፣ እነዚህ ክርስቲያኖች አንድ አምላክ ብቻ እንዳላቸው ይኸውም ይሖዋን ብቻ ማምለክ እንደሚገባቸው ማሳሰብ አስፈላጊ እንደሆነ ተሰምቶታል። |
በዛሬው ጊዜ በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ያለው ሁኔታስ ምን ይመስላል? |
ነቢዩ ኢሳይያስ በዘመኑ መጨረሻ ላይ ከብሔራት ሁሉ የተውጣጡ ሰዎች በተራራ ወደተመሰለው ወደ እውነተኛው አምልኮ እንደሚጎርፉ ትንቢት ተናግሮ ነበር። |
እነዚህ ሰዎች ይሖዋ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤ በጎዳናዎቹም እንሄዳለን ይላሉ። |
ይህ ትንቢት ሲፈጸም የማየት አጋጣሚ በማግኘታችን እንዴት ታድለናል! ትንቢቱ በመፈጸሙ ጉባኤዎቻችን የተለያየ ዘር፣ ባሕልና ቋንቋ ያላቸውን ወንድሞችና እህቶች ያቀፉ ሆነዋል፤ ይህም ለይሖዋ ውዳሴ ያመጣል። |
ሰይጣን፣ በሕይወታችን ደስተኛ መሆን ከፈለግን መሠረታዊ ከሆኑት ቁሳዊ ነገሮች ባሻገር ሌሎች ተጨማሪ ነገሮች እንደሚያስፈልጉን ሊያሳምነን ይሞክራል፤ ይህን ለማድረግም የንግዱን ዓለም ይጠቀማል። |
የዓይን አምሮት እንዲያድርብን በማድረግ ረገድ የተካነ ነው። |
ይህ ዓለም፣ ምርጥ ከሚባሉት አንስቶ እርባና ቢስ እስከሆኑት ነገሮች ድረስ በርካታ ቁሳዊ ነገሮችን ያቀርባል፤ ከእነዚህ አንዳንዶቹ በጣም የሚያጓጉ ሊሆኑ ይችላሉ። |
አንድን ዕቃ በማስታወቂያ ስላየኸው ወይም ሱቅ ውስጥ የተቀመጠበት መንገድ ቀልብህን ስለሳበው ብቻ ገዝተህ ታውቃለህ? |
በኋላ ላይ ስታስበው ግን የገዛኸው ነገር ጨርሶ እንደማያስፈልግህ ተገንዝበህ ይሆናል። |
እንዲህ ያሉት አላስፈላጊ ነገሮች ሕይወታችንን ከማወሳሰብና ጫና ከመፍጠር ባለፈ የሚፈይዱልን ነገር አይኖርም። |
መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ማጥናት፣ ለስብሰባዎች እንደ መዘጋጀትና በስብሰባዎች ላይ እንደ መገኘት እንዲሁም በአገልግሎት ላይ አዘውትሮ እንደ መካፈል የመሳሰሉ መንፈሳዊ ልማዶቻችንን ሊያስተጓጉሉብንና ወጥመድ ሊሆኑብን ይችላሉ። |
ሐዋርያው ዮሐንስ ዓለምም ሆነ ምኞቱ ያልፋሉ በማለት የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ማስታወሳችን ተገቢ ነው። |
የአምላክ ሕዝቦች በተቻለ መጠን ምሥራቹን ለብዙ ሰዎች ለማድረስ የተለያዩ ዘዴዎችን ተጠቅመዋል። |
በተለይ ሠራተኞቹ ጥቂት በነበሩበት ወቅት ይህ በጣም አስፈላጊ ነበር። |
በ20ኛው መቶ ዘመን መባቻ አካባቢ የይሖዋ ሕዝቦች ቁጥር ጥቂት በሆነባቸው ቦታዎች ምሥራቹን ለብዙ ሰዎች ለማድረስ ጋዜጦች ጥቅም ላይ ውለዋል። |
ወንድም ቻርልስ ቴዝ ራስል፣ ስብከቶቹን ለአንድ የጋዜጣ ድርጅት በየሳምንቱ ይልክ ነበር። |
ድርጅቱም ስብከቶቹን በዩናይትድ ስቴትስ፣ በካናዳና በአውሮፓ ባሉ ጋዜጦች ላይ እንዲወጡ በቴሌግራፍ ይልካል። |
በ1913 የወንድም ራስል ስብከቶች በ2,000 ጋዜጦች ላይ ይታተሙ የነበረ ሲሆን 15,000,000 የሚያህሉ አንባቢዎች ዘንድ ይደርሱ እንደነበር ይገመታል። |
ወንድም ራስል ከሞተ በኋላ ምሥራቹን ለማዳረስ የሚያስችል ሌላ ውጤታማ ዘዴ ጥቅም ላይ ዋለ። |
ሚያዝያ 16, 1922 ወንድም ጆሴፍ ፍራንክሊን ራዘርፎርድ በሬዲዮ የሚተላለፍ ንግግር አቀረበ፤ ወንድም ራዘርፎርድ በሬዲዮ ካስተላለፋቸው የመጀመሪያ ንግግሮች አንዱ የሆነውን ይህን ንግግር 50,000 ያህል ሰዎች እንዳዳመጡት ይገመታል። |
ከዚያም የካቲት 24, 1924 የድርጅቱ የመጀመሪያ የሬዲዮ ጣቢያ ይኸውም ደብልዩ ቢ ቢ አር ስርጭት ጀመረ። |
እርግጥ ነው፣ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መጀመሪያ የተጻፉት ለአንድ ግለሰብ ወይም ለተወሰኑ ሰዎች ነው። |
የአምላክን ቃል ማንበብ ከመጀመራችን በፊት፣ ለመማር ዝግጁ እንድንሆንና ይሖዋ ሊያስተምረን የሚፈልገውን ትምህርት ለማስተዋል የሚያስችል ጥበብ እንድናገኝ መጸለያችን አስፈላጊ የሆነው ለዚህ ነው። |
መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ ቆም እያልክ እንደሚከተሉት ያሉ ጥያቄዎችን ራስህን ጠይቅ፦ ይህ ዘገባ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረኛል? |
ትምህርቱን በሕይወቴ ተግባራዊ ማድረግ የምችለው እንዴት ነው? |
ይህን ሐሳብ ሌሎችን ለመርዳት ልጠቀምበት የምችለው እንዴት ነው? |
እንደነዚህ ባሉ ጥያቄዎች ላይ ስናሰላስል ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን ይበልጥ ጥቅም ማግኘት እንደምንችል የታወቀ ነው። |
ለምሳሌ ያህል፣ ክርስቲያን ሽማግሌዎች እንዲያሟሉ የሚጠበቁባቸውን ቅዱስ ጽሑፋዊ ብቃቶች እንመልከት። |
አብዛኞቻችን የጉባኤ ሽማግሌዎች ስላልሆንን ይህ ጥቅስ በሕይወታችን ውስጥ ልንጠቀምበት የምንችል ትምህርት እንዳልያዘ ይሰማን ይሆናል። |
ይሁንና ከዚህ ጥቅስ ሁላችንም የተለያዩ ጥቅሞች ልናገኝ እንደምንችል እንገነዘባለን። |
‘የሰው ልጅ፣ በሕይወት ለመኖር የሚያስፈልጉት ነገሮች ጥቂት ሲሆኑ የሚፈልጋቸው ነገሮች ግን ስፍር ቁጥር የላቸውም ሲባል እንሰማለን። |
ብዙዎች፣ በሚያስፈልጓቸው ቁሳዊ ነገሮችና እነሱ በሚፈልጓቸው ነገሮች መካከል ያለውን ልዩነት የሚያስተውሉ አይመስልም። |
ይሁንና ልዩነቱ ምንድን ነው? |
የሚያስፈልገን ነገር የሚባለው በሕይወት ለመኖር የግድ አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው። |
ምግብ፣ ልብስና መጠለያ ለሰው ልጅ አስፈላጊ የሆኑ መሠረታዊ ነገሮች ናቸው። |
የምንፈልገው ነገር የሚባለው ግን ቢኖረን ደስ የሚለን ሆኖም ለዕለት ተዕለት ሕይወታችን የግድ አስፈላጊ ያልሆነ ነገር ነው። |
ሰዎች የሚፈልጉት ነገር፣ እንደሚኖሩበት አካባቢ ሊለያይ ይችላል። |
በማደግ ላይ ባሉ አገሮች የሚኖሩ ብዙ ሰዎች የሚፈልጉት ሞባይል ስልክ፣ ሞተር ብስክሌት ወይም አነስ ያለ መሬት መግዛት ሊሆን ይችላል። |
በበለጸጉ አገሮች የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ ውድ የሆኑ ልብሶች፣ ትልቅ ቤት ወይም ውድ መኪና መግዛት ይፈልጋሉ። |
የምንኖረው የትም ይሁን የት፣ አደገኛ በሆነው የፍቅረ ንዋይ ወጥመድ ልንወድቅ እንችላለን፤ ይህ ደግሞ የመግዛት አቅሙ ቢኖረንም ባይኖረንም፣ የምንገዛው ነገር ቢያስፈልገንም ባያስፈልገንም ተጨማሪ ቁሳዊ ነገሮችን የመመኘት አባዜ እንዲጠናወተን ሊያደርግ ይችላል። |
ሐዋርያው ጴጥሮስ፣ ክርስቲያኖች ሰይጣን የሚያመጣባቸውን አስቸጋሪ ሁኔታዎች በጽናት እንዲወጡ ለማበረታታት ከላይ ያለውን ጽፏል። |
የጸኑት የአምላክ አገልጋዮች የተዉት ምሳሌ ጽኑ አቋማችንን መጠበቅ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያስተምረናል፤ ሊሳካልን እንደሚችል ማረጋገጫ ይሰጠናል፤ እንዲሁም ታማኞች ከሆንን ሽልማት እንደምናገኝ ያስታውሰናል። |
ከእውነተኛው አምልኮ ጠላቶች፣ መራራ ተቃውሞ ሌላው ቀርቶ ስደት እየደረሰብህ ነው? |
ያሉብህ ከባድ ኃላፊነቶች ከአቅምህ በላይ እንደሆኑ የሚሰማህ የጉባኤ ሽማግሌ ወይም የወረዳ የበላይ ተመልካች ነህ? |
ከሆነ ጳውሎስ በተወው ምሳሌ ላይ አሰላስል። |
ጳውሎስ ብዙ ውጫዊ ችግሮች የደረሱበት ይኸውም ጨካኝ አሳዳጆች ያስጨነቁት ከመሆኑም ሌላ የጉባኤዎች ሐሳብ በየዕለቱ ጫና ይፈጥርበት ነበር። |
ይህ ሁሉ ቢደርስበትም ተስፋ አልቆረጠም፤ የተወው ምሳሌም ለሌሎች የብርታት ምንጭ ነው። |
አንተም አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በጽናት ስትቋቋም የአንተ ምሳሌነት ሌሎችም እንዲጸኑ እንደሚያበረታታቸው አስታውስ። |
ቅቡዓን ክርስቲያኖች በሰማይ ከክርስቶስ ጋር ዙፋን ላይ ተቀምጠው በሚገዙበት ጊዜ ይሖዋ ምን ዓይነት አስደናቂ ነገሮች እንደሚሰጣቸው መገመት ያዳግታል። |
ቅቡዓኑ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ይኸውም የክርስቶስ ሙሽራ ይሆናሉ። |
እነዚህ ቅቡዓን፣ ታዛዥ የሆኑ የሰው ልጆች ከኃጢአትና ከሞት ባርነት ነፃ ወጥተው ወደ ፍጽምና እንዲደርሱ በመርዳት ከኢየሱስ ጋር ሆነው ሕዝቦችን ይፈውሳሉ። |
የይሖዋ ጸጋ በምድር ላይ ከሚገለጽባቸው አስደናቂ መንገዶች አንዱ በመቃብር ያሉ ሰዎች ከሞት መነሳታቸው ይሆናል። |
ክርስቶስ መሥዋዕት ሆኖ ከመሞቱ በፊት በነበሩት ዘመናት የሞቱ ታማኝ ወንዶችና ሴቶች እንዲሁም በመጨረሻዎቹ ቀናት በታማኝነት የሚያንቀላፉ ሌሎች በጎች ሁሉ ትንሣኤ አግኝተው ይሖዋን ማገልገላቸውን ይቀጥላሉ። |
ይሖዋ፣ ፍጥረታቱ እሱ የሚፈልገውን እንዲሆኑም ያደርጋል። |
አምላክ ከስሙ ትርጉም ጋር በሚስማማ መንገድ ኖኅን መርከብ ሠሪ፣ ባስልኤልን የተዋጣለት የእጅ ጥበብ ባለሙያ፣ ጌድዮንን ኃያል ተዋጊ እንዲሁም ጳውሎስን የአሕዛብ ሐዋርያ አድርጓቸዋል። |
በእርግጥም የአምላክ ሕዝቦች መለኮታዊው ስም ትልቅ ትርጉም እንዳለው ይገነዘባሉ። |
የአዲስ ዓለም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ኮሚቴም ቢሆን መለኮታዊውን ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በማውጣት ለአምላክ ስም አክብሮት እንደጎደለው የሚያሳይ ድርጊት አይፈጽምም። |
ከ130 በሚበልጡ ቋንቋዎች የተዘጋጁ አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱሶች የአምላክ ስም በቅዱስ ጽሑፉ ውስጥ በትክክለኛው ቦታ ላይ እንዲገባ በማድረግ ለስሙ አክብሮት አሳይተዋል። |
ከዚህ በተቃራኒ በአሁኑ ጊዜ ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች መለኮታዊውን ስም በማውጣት በምትኩ ጌታ የሚለውን ማዕረግ ወይም በአካባቢው የሚታወቀውን አምላክ መጠሪያ የማስገባት ልማድ አላቸው። |
የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል፣ የአምላክን ስም የሚያስከብር የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በተቻለ መጠን ለብዙ ሰዎች እንዲደርስ ለማድረግ ቅድሚያ የሰጠበት ዋነኛ ምክንያት ይህ ነው። |
ሌሎች ባከናወኑት ነገር መደሰት ሌላው ቀርቶ በተወሰነ መጠን በራሳችን መኩራት እንኳ ስህተት አይደለም። |
በቤተሰባችን፣ በባሕላችን ወይም ባደግንበት አካባቢ ማፈር አይኖርብንም። |
በሌላ በኩል ግን ከሌሎች ጋር ያለንን ግንኙነትም ሆነ ከይሖዋ ጋር ያለንን ወዳጅነት ቀስ ቀስ የሚያበላሽ ኩራት አለ። |
እንዲህ ያለው ኩራት አስፈላጊ የሆነ ምክር ሲሰጠን በትሕትና ከመቀበል ይልቅ ቅር እንድንሰኝ ወይም ምክሩን እንዳንቀበል ሊያደርገን ይችላል። |
ይህ ዓይነቱ ኩራት ራስን ከሚገባው በላይ ከፍ አድርጎ መመልከት የሚል ፍቺ ተሰጥቶታል፤ ወይም ደግሞ ከሌሎች የተሻሉ እንደሆኑ የሚሰማቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ እንዲህ ለማሰብ የሚያበቃ ምክንያት ባይኖራቸውም የሚያሳዩት የትዕቢት ዝንባሌ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል። |
ይሖዋ ከልክ ያለፈ ኩራትን ይጠላል። |
ሰይጣን ግን እንዲህ ያለው አስተሳሰብ የእሱን የእብሪት ዝንባሌ የሚያንጸባርቅ በመሆኑ ሰዎች ሲታበዩ ማየት ያስደስተዋል። |
እንደ ናምሩድ፣ ፈርዖንና አቢሴሎም ያሉት ሰዎች በመታበይ ተገቢ ያልሆነ ኩራት ሲያሳዩ ምንኛ ፈንጥዞ ይሆን!—፤ |
ጎግ፣ ቀሪዎቹ የ144,000 አባላት ወደ ሰማይ ከመወሰዳቸው ትንሽ ቀደም ብሎ በአምላክ ሕዝቦች ላይ ጥቃት ይሰነዝራል። |
ታዲያ ይህ ጥቃት ምን ያስከትላል? |
በምድር ላይ ያሉት የአምላክ ሕዝቦች ለጥቃት የተጋለጡ ይመስላሉ። |
እነዚህ የአምላክ ሕዝቦች በንጉሥ ኢዮሳፍጥ ዘመን የተሰጠውን መመሪያ ይታዘዛሉ፦ እናንተ ይህን ጦርነት መዋጋት አያስፈልጋችሁም። |
ቦታ ቦታችሁን ይዛችሁ ዝም ብላችሁ ቁሙ፤ ይሖዋ ለእናንተ ሲል የሚወስደውን የማዳን እርምጃ ተመልከቱ። |
ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አትፍሩ ወይም አትሸበሩ። |
በሰማይ ግን ሁኔታው ከዚህ የተለየ ነው። |
ቅቡዓን በሙሉ ወደ ሰማይ ከሄዱ በኋላ የአምላክ ሕዝቦች ጠላቶች ስለሚያደርጉት ነገር ሲናገር እንዲህ ይላል፦ እነዚህ ከበጉ ጋር ይዋጋሉ፤ ሆኖም በጉ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለሆነ ድል ይነሳቸዋል። |
ከእሱ ጋር ያሉት የተጠሩት፣ የተመረጡትና የታመኑትም ድል ያደርጋሉ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.