text stringlengths 4 267 |
|---|
ኢየሱስ በሰማይ ካሉት 144,000 ተባባሪ ገዢዎቹ ጋር በመሆን በምድር ላይ ያሉትን የአምላክ ሕዝቦች ይታደጋል። |
ወደ ክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ለጋበዘን አምላክ አክብሮት እንዳለን ጨዋነት በሚንጸባረቅበት ምግባራችን፣ በአለባበሳችንና በአጋጌጣችን ልናሳይ ይገባል። |
አክብሮት ካለን ከተለመደው ወጣ ያሉ ነገሮችን ከማድረግም እንቆጠባለን። |
ይሖዋ አገልጋዮቹም ሆነ ተጋባዦች በመንግሥት አዳራሽ ውስጥ ነፃነት እንዲሰማቸው ይፈልጋል። |
በሌላ በኩል ግን ወደ አዳራሾቻችን የሚመጡ ሰዎች በአለባበሳቸው ግዴለሽ የሚሆኑ፣ ስብሰባ እየተካሄደ በስልክ መልእክት የሚጽፉ፣ የሚያወሩ፣ የሚበሉ፣ የሚጠጡ ወይም የመሳሰሉትን ነገሮች የሚያደርጉ ከሆነ ለስብሰባው አክብሮት እንደጎደላቸው እያሳዩ ነው። |
በተጨማሪም የመንግሥት አዳራሹ ልጆች የሚሯሯጡበት ወይም የሚጫወቱበት ስፍራ እንዳልሆነ ወላጆቻቸው ሊያስገነዝቧቸው ይገባል። |
ኢየሱስ በአምላክ ቤተ መቅደስ ውስጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ያካሂዱ በነበሩት ሰዎች በጣም ስለተቆጣ አባርሯቸዋል። |
የመንግሥት አዳራሾቻችንም ንጹሕ አምልኮ የሚከናወንባቸውና መንፈሳዊ ትምህርት የምናገኝባቸው ቦታዎች ናቸው። |
በመሆኑም ንግድን ጨምሮ ከመንፈሳዊ ነገሮች ጋር ምንም ግንኙነት የሌለውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ በዚያ ማከናወን አይኖርብንም። |
— ጋር አወዳድር፤ |
አዘውትረው ይገኙ ነበር ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ሐሳብ በአንድ ነገር መጽናትን የሚያመለክት ሲሆን ይህም ከፍተኛ ጥረት ማድረግን ይጠይቃል። |
በሮም አገዛዝ ሥር ለሚኖሩትና በጊዜው ከነበሩት የሃይማኖት መሪዎች ተቃውሞ ለሚደርስባቸው ለጥንቶቹ ክርስቲያኖች በስብሰባዎች ላይ መገኘት ቀላል አልነበረም። |
ያም ቢሆን በስብሰባዎች ላይ አዘውትረው ይገኙ ነበር። |
በዛሬው ጊዜ የሚገኙ በርካታ የይሖዋ አገልጋዮች ለክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ጥልቅ አድናቆት እንዳላቸው አሳይተዋል። |
ከ22 ለሚበልጡ ዓመታት የበላይ አካል አባል ሆኖ ያገለገለው ወንድም ጆርጅ ጋንጋስ እንዲህ ብሏል፦ ከወንድሞች ጋር መሰብሰብ ማለት ለእኔ፣ በሕይወቴ ውስጥ ትልቅ ደስታና ማበረታቻ ከሚሰጡኝ ነገሮች አንዱ ነው። |
አክሎም የእኔም የዘወትር ሐሳብና ፍላጎት በስብሰባዎች ላይ መገኘት ነው ብሏል። |
አንተስ ይሖዋን ለማምለክ አንድ ላይ ስለ መሰብሰብ እንዲህ ይሰማሃል? |
ከሆነ በስብሰባዎች ላይ አዘውትረህ ለመገኘት የምታደርገውን ልባዊ ጥረት ግፋበት። |
በዚህ መንገድ የንጉሥ ዳዊት ዓይነት ስሜት እንዳለህ ታሳያለህ፤ ዳዊት እንዲህ ብሏል፦ ይሖዋ ሆይ፣ የምትኖርበትን ቤት እወዳለሁ። |
መጽናት የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሠራበት፣ ፈተናዎችን ወይም አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ከመቋቋም የበለጠ ነገርን ለማመልከት ነው። |
ጽናት ከአስተሳሰባችንና ከስሜታችን ማለትም መከራ ሲደርስብን ከምናደርገው ነገር ጋር የተያያዘ ነው። |
የሚጸና ሰው ድፍረትና ትዕግሥት እንዳለው እንዲሁም ከአቋሙ ፍንክች እንደማይል ያሳያል። |
አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ እንደገለጸው ጽናት አንድን ነገር ምርጫ ስለሌለን ብቻ መቀበልን ሳይሆን ብሩህ ተስፋ ይዞ የመቻልን መንፈስ ያመለክታል። |
ይኸው ጽሑፍ አክሎም እንዲህ ብሏል፦ ጽናት፣ አንድ ሰው ወደ እሱ የሚነፍሰውን ነፋስ ፊት ለፊት ተጋፍጦ ሳይንገዳገድ እንዲቆም የሚያስችለው ባሕርይ ነው። |
ከሥቃዩ ባሻገር ያለውን ግብ ለመመልከት ስለሚረዳ ከባዱን መከራ ወደ ክብር መለወጥ የሚያስችል ግሩም ባሕርይ ነው። |
ክርስቲያኖች እንዲጸኑ የሚያነሳሳቸው ፍቅር ነው። |
ለይሖዋ ያለን ፍቅር፣ እሱ የሚፈቅደውን ማንኛውንም ነገር በጽናት እንድንወጣ ያነሳሳናል። |
ለወንድሞቻችን ያለን ፍቅር፣ ፍጹማን ባለመሆናቸው ያለባቸውን ድክመት ችለን እንድናልፍ ይረዳናል። |
ለትዳር ጓደኛችን ያለን ፍቅር ደግሞ ደስተኛ ባለትዳሮች እንኳ የሚያጋጥማቸውን መከራ በጽናት እንድናሳልፍና የትዳር ጥምረታችንን እንድናጠናክር ያደርገናል። |
በታሪክ ዘመናት ሁሉ ይሖዋ ዝርዝር መመሪያዎች ወይም ትእዛዛት ሲሰጥ ቆይቷል። |
ለምሳሌ በኤደን ገነት የዘላለም ሕይወትና ዘላቂ ደስታ ሊያስገኝ የሚችል ግልጽ መመሪያ ለአዳምና ለሔዋን ሰጥቷቸው ነበር። |
እነዚህ ባልና ሚስት መመሪያውን ቢታዘዙ ኖሮ ችግር ላይ አይወድቁም ነበር፤ ባለመታዘዛቸው ምክንያት ግን በመከራ የተሞላ እንዲሁም ያለምንም ተስፋ በሞት የሚደመደም ሕይወት ለመምራት ተገደዋል። |
ሔዋን መመሪያውን በመታዘዝ ፋንታ ከአንድ ተራ እንስሳ የመጣ የሚመስለውን ምክር ተቀብላለች። |
አዳምም ቢሆን ሟች የሆነችው ሔዋን የነገረችውን ነገር ሰማ። |
ሁለቱም አፍቃሪ የሆነው አባታቸው የሰጣቸውን መመሪያ አልተቀበሉም። |
በዚህም የተነሳ የሰው ልጆች ወደ ሞት በሚመራ ጎዳና ላይ መጓዝ ጀመሩ። |
ይሖዋ በዛሬው ጊዜ ሕዝቦቹን እየመራ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስዳቸውንና አደጋ የሌለበትን መንገድ ይጠቁማቸዋል። |
ከዚህ በተጨማሪ አፍቃሪ እረኛ እንደመሆኑ መጠን በጎቹ አደገኛ የሆነ ጎዳና ከመከተል እንዲርቁ አስፈላጊውን መመሪያና ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል። |
ይሖዋ በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ቀጥተኛ የሆኑ በርካታ መመሪያዎችን ሰጥቶናል። |
ለምሳሌ የፆታ ብልግናን፣ የጣዖት አምልኮን፣ ስርቆትንና ስካርን ያወግዛል። |
በተጨማሪም የአምላክ ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የሚከተለውን ከባድ ሆኖም አስደሳች ትእዛዝ ሰጥቷቸዋል፦ ሂዱና ከሁሉም ብሔራት ሰዎችን ደቀ መዛሙርት አድርጉ፤ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፣ ያዘዝኳችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው። |
እነሆም እኔ እስከ ሥርዓቱ መደምደሚያ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። |
በእርግጥም መለኮታዊ ሕጎችና ትእዛዛት ለእኛ ጥበቃ ሆነውልናል! እነዚህን መመሪያዎች መታዘዛችን ለራሳችን ያለን አክብሮት እንዲጨምር፣ ጥሩ ጤንነት እንዲኖረንና ቤተሰባችን ይበልጥ ደስተኛ እንዲሆን አድርጓል። |
በስብከቱ ሥራ እንድንካፈል የተሰጠንን ትእዛዝ ጨምሮ የይሖዋን መመሪያዎች በሙሉ በታማኝነት መታዘዛችን ከሁሉም በላይ የእሱን ሞገስና በረከት አስገኝቶልናል። |
የአምላክ ቅዱስ መንፈስ እንዲመራን ስንፈቅድ እንዲሁም በአምላክ ቃል ውስጥ ከሰፈረው የይሖዋ አመለካከት ጋር የሚስማማ አመለካከት ስናዳብር አስተሳሰባችን፣ ንግግራችንና ድርጊታችን አምላክን የሚያስደስት ይሆናል። |
እርግጥ ነው፣ እንዲህ እያደረግንም ቢሆን በድክመቶቻችን ላለመሸነፍ መጠንቀቅ ያስፈልገናል። |
መንፈሳዊ እድገትህ አዝጋሚ እንደሆነ ከተሰማህ እንዲህ ያለ እድገት ማድረግ ጊዜ እንደሚወስድ ማስታወስህ ጠቃሚ ነው። |
መንፈሳዊ ባሕርያትን ማዳበር ቀጣይነት ያለው ሂደት ነው። |
መጽሐፍ ቅዱስ ምንጊዜም በሕይወታችን ውስጥ ጠቃሚ ለውጦች ለማድረግ እንዲረዳን ስንጥር ትዕግሥተኞች መሆን አለብን። |
ከቅዱሳን መጻሕፍት ጋር የሚስማማ ነገር ለማድረግ መጀመሪያ ላይ ራሳችንን መገሠጽ ያስፈልገን ይሆናል። |
ውሎ አድሮ በአስተሳሰባችንና በድርጊታችን ይሖዋ አምላክን መምሰል ስንችል ግን አምላክን በሚያስደስት መንገድ ማሰብና መመላለስ ይበልጥ ቀላል ሊሆንልን ይችላል። |
ምሥራቹን የመስበኩ ሥራ ይሖዋ ለሰው ልጆች ካለው ፍቅር የተንጸባረቀበት ዓላማ ጋር እንዴት እንደሚያያዝ አስብ። |
የአምላክ ዓላማ የሰው ልጆች ፈጽሞ ሞትን ሳያዩ በምድር ላይ እንዲኖሩ ነው፤ አዳም ኃጢአት ቢሠራም ይሖዋ ይህን ዓላማውን አልቀየረም። |
እንዲያውም የሰው ልጆች ከኃጢአትና ከሞት ኩነኔ ነፃ የሚወጡበትን ዝግጅት አደረገ። |
ይህንን ዓላማ ከዳር ማድረስ እንዲቻል ኢየሱስ ወደ ምድር መጥቶ ታዛዥ ለሆኑ ሰዎች ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ ሰጥቷል። |
ይሁንና የሰው ልጆች ታዛዥ እንዲሆኑ አምላክ ከእነሱ ምን እንደሚጠብቅባቸው ማወቅ ያስፈልጋቸዋል። |
በመሆኑም ኢየሱስ የአምላክን መሥፈርቶች ለሰዎች አስተምሯል፤ ደቀ መዛሙርቱም እንዲህ እንዲያደርጉ ትእዛዝ ሰጥቷል። |
እኛም ሰዎች ከአምላክ ጋር እንዲታረቁ ስንረዳ የሰው ልጆችን ከኃጢአትና ከሞት ለማዳን ይሖዋ ባደረገው ፍቅራዊ ዝግጅት ውስጥ ቀጥተኛ ተሳትፎ ይኖረናል። |
በተጨማሪም እንዲህ ማድረጋችን ለእነሱም ሆነ ለይሖዋ ያለንን ፍቅር ያሳያል፤ የይሖዋ ፈቃድ ሁሉም ዓይነት ሰዎች እንዲድኑና የእውነትን ትክክለኛ እውቀት እንዲያገኙ ነው። |
ስለምታምንበት ነገር እርግጠኛ ከሆንክ ይህ በምግባርህ ላይ መንጸባረቁ አይቀርም። |
ወጣቶችም ቢሆኑ ቅዱስ ሥነ ምግባር ሊኖራቸው ይገባል። |
ይህን ለማድረግ ደግሞ ከሥነ ምግባር አኳያ ንጹሕ መሆን አለባቸው። |
በዚህ ረገድ የአንተ ሁኔታ ምን ይመስላል? |
ለምሳሌ ያለፉትን ስድስት ወራት መለስ ብለህ አስብ። |
ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ለመለየት የሠለጠነ የማስተዋል ችሎታ እንዳለህ ያሳየኸው እንዴት ነው? |
ፈተናዎችን ወይም የእኩዮችን ተጽዕኖ የተቋቋምክባቸውን አጋጣሚዎች ታስታውሳለህ? |
በትምህርት ቤት የምታሳየው ምግባር ስለምታምንበት ነገር ጥሩ ምሥክርነት ይሰጣል? |
ሌሎች እንዳያሾፉብህ ስትል ብቻ አብረውህ ከሚማሩ ልጆች ጋር ለመመሳሰል ከመሞከር ይልቅ ለምታምንበት ነገር ጥብቅና ትቆማለህ? |
እርግጥ ነው፣ ፍጹም የሆነ ሰው የለም። |
ይሖዋን ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ሰዎችም እንኳ አንዳንድ ጊዜ በሕዝብ ፊት ስለሚያምኑበት ነገር በይፋ መናገር ሊያስፈራቸው ይችላል። |
ይሁንና ራሱን ለይሖዋ የወሰነ አንድ ሰው የአምላክን ስም በመሸከሙ ኩራት ይሰማዋል፤ ይህንንም በምግባሩ ያሳያል። |
ኢየሱስ አስቀድሞ እንደተናገረው ኢየሩሳሌም በጦር ሠራዊት ተከባ ሲመለከቱ በይሁዳ በተለይ ደግሞ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ክርስቲያኖች ቆራጥ እርምጃ መውሰድ ነበረባቸው። |
ኢየሱስ፣ እነዚህ ነገሮች መፈጸም ሲጀምሩ በፍጥነት መሸሽ እንዳለባቸው አስጠንቅቋቸዋል። |
ኢየሱስ ይህን ትንቢት ከተናገረ በኋላ በነበሩት 28 ዓመታት ውስጥ በእስራኤል የሚኖሩ ታማኝ አይሁዳውያን ክርስቲያኖች ብዙ ተቃውሞና ስደት የደረሰባቸው ቢሆንም ተቋቁመውታል። |
ይሁን እንጂ ጳውሎስ ከእምነታቸው ጋር በተያያዘ በቅርቡ በጣም ከባድ ፈተና እንደሚያጋጥማቸው ያውቃል። |
ስለዚህ ከፊታቸው ለሚጠብቃቸው ማንኛውም ነገር እንዲዘጋጁ ፈልጓል። |
የሚያጋጥማቸውን ነገር ለመቋቋም የተለየ ጽናት ብሎም በሕይወት የሚያኖር ጠንካራ እምነት ያስፈልጋቸዋል። |
ስለሆነም ጳውሎስ እነዚህ ውድ ወንድሞችና እህቶች የሚያስፈልጋቸውን ለየት ያለ እርዳታ ለመስጠት የሚያስችል ደብዳቤ እንዲጽፍላቸው ይሖዋ በመንፈሱ መርቶታል። |
ይህ ደብዳቤ በአሁኑ ወቅት የዕብራውያን መጽሐፍ ተብሎ ይጠራል። |
የሌሎች በጎች አባላት በዛሬው ጊዜ የሚገኙትን የሁሉንም ቅቡዓን ስም ማወቅ ያስፈልጋቸዋል? |
አያስፈልጋቸውም። |
ለምን? |
ምክንያቱም አንድ ሰው ሰማያዊ ጥሪ ቢያገኝ እንኳ ግለሰቡ የተቀበለው ግብዣ እንጂ ሽልማቱን እንደሚያገኝ የሚያሳይ የመጨረሻ ማረጋገጫ አይደለም። |
ሰይጣን ቢቻላቸው የተመረጡትን እንኳ እንዲያስቱ ሐሰተኛ ነቢያትን የሚያስነሳው ለዚህ ነው። |
አንድ ቅቡዕ ክርስቲያን፣ ሰማያዊ ሽልማት ማግኘት ይገባው እንደሆነ ይሖዋ እስኪወስን ድረስ ግለሰቡ ይህን ሽልማት ማግኘቱን ማንም ሰው ማወቅ አይችልም። |
ይሖዋ ይህን ውሳኔ የሚያስተላልፈውና የመጨረሻውን ማኅተም የሚያደርግበት፣ ግለሰቡ በታማኝነት ከመሞቱ ትንሽ ቀደም ብሎ አሊያም ታላቁ መከራ ከመጀመሩ ጥቂት ቀደም ብሎ ነው። |
እንግዲያው በዛሬው ጊዜ በምድር ላይ ያለ ማንኛውም ሰው ከአምላክ አገልጋዮች መካከል የ144,000ዎቹ አባል የሚሆኑትን በእርግጠኝነት ለማወቅ መሞከሩ ምንም ትርጉም የለውም። |
አምላክ እንዲወደን ከፈለግን ወንድሞቻችንን የመውደድ ግዴታ እንዳለብን አምነን መቀበል ይኖርብናል። |
ታዲያ ፍቅራችንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? |
ኢየሱስ የተወውን ምሳሌ እንመልከት። |
በምድር ላይ ባከናወነው አገልግሎቱ ወቅት፣ ዝቅ ተደርገው ለሚታዩ ሰዎች ልዩ ትኩረት ይሰጥ ነበር። |
የአካል ጉዳተኛ የሆኑትን ለምሳሌ አንካሶችን፣ ዓይነ ስውሮችን፣ መስማት የተሳናቸውንና ዱዳዎችን ፈውሷል። |
በጊዜው የነበሩት የሃይማኖት መሪዎች የተረገሙ አድርገው የሚመለከቷቸውን በመንፈሳዊ የተራቡ ሰዎች ማስተማር ያስደስተው ነበር። |
ዝቅ ተደርገው የሚታዩትን እነዚህን ሰዎች ይወዳቸውና እነሱን ለማገልገል በትጋት ይሠራ ነበር። |
እናንተስ በጉባኤያችሁ ስላሉት ወንድሞችና እህቶች ጊዜ ወስዳችሁ ታስባላችሁ? |
ይህን ስታደርጉ ፍቅር ብታሳዩአቸው የሚጠቀሙ ሰዎች እንዳሉ ማስተዋላችሁ አይቀርም። |
ምናልባትም እርዳታ የሚያሻቸው አረጋውያን ወንድሞችና እህቶች ይኖሩ ይሆናል። |
የአምላክ ፍቅር ለወንድሞቻችን ፍቅራችንን ለማሳየት ሊያነሳሳን ይገባል። |
ከልጆቻችሁ ጋር ሆናችሁ በትሕትና ስትጸልዩ ልጆቻችሁ በይሖዋ መታመንን ይማራሉ። |
በብራዚል የምትኖረው አና እንዲህ ብላለች፦ በቤተሰባችን ውስጥ ችግሮች በሚኖሩበት ጊዜ ለምሳሌ አያቶቼ በታመሙበት ወቅት ወላጆቼ ሁኔታውን ለመቋቋም የሚያስችላቸው ጥንካሬና ጥሩ ውሳኔ ለማድረግ የሚረዳቸው ጥበብ እንዲሰጣቸው ወደ ይሖዋ ይጸልዩ ነበር። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.