text
stringlengths
4
267
የይሖዋም መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ፤ እሱም የእስራኤል መስፍን ሆነ። ለጦርነት በወጣም ጊዜ ይሖዋ የሜሶጶጣሚያውን ንጉሥ ኩሻንሪሻታይምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እሱም በኩሻንሪሻታይም ላይ በረታበት።
ከዚያ በኋላ ምድሪቱ ለ40 ዓመት አረፈች። ከዚያም የቀናዝ ልጅ ኦትኒኤል ሞተ።
እስራኤላውያንም እንደገና በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር ማድረግ ጀመሩ። ስለዚህ ይሖዋ የሞዓብ ንጉሥ ኤግሎን በእስራኤላውያን ላይ እንዲበረታባቸው አደረገ፤ ምክንያቱም በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አድርገው ነበር።
በተጨማሪም አሞናውያንንና አማሌቃውያንን በእነሱ ላይ አመጣባቸው። እነሱም በእስራኤላውያን ላይ ጥቃት በመሰንዘር የዘንባባ ዛፎች ከተማን ያዙ።
እስራኤላውያንም የሞዓብን ንጉሥ ኤግሎንን 18 ዓመት አገለገሉ።
ከዚያም እስራኤላውያን ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ ጮኹ፤ ይሖዋም ግራኝ የሆነውን ቢንያማዊውን የጌራን ልጅ ኤሁድን አዳኝ አድርጎ አስነሳላቸው። ከጊዜ በኋላ እስራኤላውያን በእሱ በኩል ለሞዓብ ንጉሥ ለኤግሎን ግብር ላኩ።
በዚህ ጊዜ ኤሁድ ርዝመቱ አንድ ክንድ የሆነ በሁለት በኩል ስለት ያለው ሰይፍ ሠርቶ ከልብሱ ሥር በቀኝ ጭኑ ላይ አሰረው።
ከዚያም ግብሩን ለሞዓብ ንጉሥ ለኤግሎን አቀረበ። ኤግሎን በጣም ወፍራም ነበር።
ኤሁድ ግብሩን ሰጥቶ እንደጨረሰ ግብሩን ተሸክመው የመጡትን ሰዎች አሰናበታቸው።
እሱ ግን በጊልጋል የሚገኙት የተቀረጹ ምስሎች ጋ ሲደርስ ተመልሶ በመሄድ “ንጉሥ ሆይ፣ በሚስጥር የምነግርህ አንድ መልእክት አለኝ” አለ። ንጉሡም “እስቲ አንዴ ጸጥታ!” አለ። በዚህ ጊዜ አገልጋዮቹ ሁሉ ጥለውት ወጡ።
ንጉሡ፣ ሰገነት ላይ በሚገኘው ቀዝቀዝ ያለ የግል ክፍሉ ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ ሳለ ኤሁድ ወደ እሱ ቀረበ። ከዚያም ኤሁድ “ከአምላክ ዘንድ ለአንተ የመጣ መልእክት አለኝ” አለው። በዚህ ጊዜ ንጉሡ ከዙፋኑ ተነሳ።
ስለዚህ ኤሁድ ግራ እጁን ሰዶ በቀኝ ጭኑ በኩል የነበረውን ሰይፍ በመምዘዝ በንጉሡ ሆድ ውስጥ ሻጠው።
ከስለቱ በኋላም እጀታው ሆዱ ውስጥ ገባ፤ ኤሁድ ሰይፉን ከሆዱ መልሶ ስላላወጣው ስለቱ በስብ ተሸፈነ፤ ፈርሱም ተዘረገፈ።
ኤሁድም በበረንዳው በኩል ወጣ፤ ሰገነት ላይ ያለውን ክፍል በሮች ግን ዘግቶ ቆልፏቸው ነበር።
እሱም ከሄደ በኋላ አገልጋዮቹ መጥተው ሲያዩ ሰገነት ላይ ያለው ክፍል በሮች ተቆልፈው ነበር። በመሆኑም “ቀዝቀዝ ባለው ውስጠኛ ክፍል እየተጸዳዳ ይሆናል” አሉ።
እነሱም እስኪያፍሩ ድረስ ጠበቁ፤ ሆኖም ሰገነት ላይ የሚገኘውን ክፍል በሮች እንዳልከፈተ ባዩ ጊዜ ቁልፉን ወስደው በሮቹን ከፈቱ፤ በዚያም ጌታቸው ሞቶ ወለል ላይ ተዘርሮ ተመለከቱ!
ኤሁድ ግን እነሱ ቆመው ሲጠባበቁ ሳለ አመለጠ፤ በተቀረጹት ምስሎች በኩል አድርጎም በሰላም ወደ ሰኢራ ደረሰ።
እዚያም እንደደረሰ በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ ቀንደ መለከት ነፋ፤ እስራኤላውያንም ከተራራማው አካባቢ ወጥተው በእሱ መሪነት አብረውት ወረዱ።
ከዚያም “ይሖዋ ጠላቶቻችሁን ሞዓባውያንን በእጃችሁ አሳልፎ ስለሰጣችሁ ተከተሉኝ” አላቸው። እነሱም ተከትለውት በመሄድ ሞዓባውያን እንዳይሻገሩ የዮርዳኖስን መልካዎች ያዙባቸው፤ አንድም ሰው እንዲሻገር አልፈቀዱም።
በዚያን ጊዜም ጠንካራና ጀግና የሆኑ 10,000 ሞዓባውያንን ገደሉ፤ አንድም ሰው አላመለጠም።
በዚያ ቀን ሞዓብ በእስራኤል እጅ ተንበረከከ፤ ምድሪቱም ለ80 ዓመት አረፈች።
ከእሱ በኋላ፣ 600 ፍልስጤማውያንን በከብት መውጊያ የገደለው የአናት ልጅ ሻምጋር ተነሳ፤ እሱም እስራኤልን አዳነ።
ከጊዜ በኋላ የየሩባአል ልጅ አቢሜሌክ በሴኬም ወደሚገኙት የእናቱ ወንድሞች ሄዶ እነሱንና የአያቱን ቤተሰብ በሙሉ እንዲህ አላቸው፦
“እባካችሁ የሴኬምን መሪዎች ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ጠይቋቸው፦ ‘70ዎቹ የየሩባአል ልጆች በሙሉ ቢገዟችሁ ይሻላችኋል ወይስ አንድ ሰው ቢገዛችሁ? ደግሞም እኔ የአጥንታችሁ ፍላጭ፣ የሥጋችሁ ቁራጭ መሆኔን አስታውሱ።’”
በመሆኑም የእናቱ ወንድሞች እሱን ወክለው ለሴኬም መሪዎች በሙሉ ይህንኑ ነገሯቸው፤ እነሱም “እሱ እኮ የገዛ ወንድማችን ነው” በማለት ልባቸው አቢሜሌክን ወደመከተል አዘነበለ።
እነሱም ከባአልበሪት ቤት 70 የብር ሰቅል ሰጡት፤ አቢሜሌክም ተከታዮቹ እንዲሆኑ በዚህ ገንዘብ ሥራ ፈቶችንና ወሮበሎችን ቀጠረበት።
ከዚያም በኦፍራ ወደሚገኘው ወደ አባቱ ቤት ሄዶ ወንድሞቹን ማለትም 70ዎቹን የየሩባአል ልጆች በአንድ ድንጋይ ላይ ገደላቸው። በሕይወት የተረፈው የሁሉም ታናሽ የሆነው የየሩባአል ልጅ ኢዮዓታም ብቻ ነበር፤ ምክንያቱም እሱ ተደብቆ ነበር።
ከዚያም የሴኬም መሪዎች ሁሉ እንዲሁም የቤትሚሎ ሰዎች በሙሉ በአንድነት ተሰብስበው በመሄድ አቢሜሌክን በትልቁ ዛፍ አጠገብ ይኸውም በሴኬም በነበረው ዓምድ አጠገብ አነገሡት።
ኢዮዓታምም ይህን በነገሩት ጊዜ ወዲያውኑ ሄዶ በገሪዛን ተራራ አናት ላይ ቆመ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የሴኬም መሪዎች እኔን ስሙኝ፤ ከዚያም አምላክ ይሰማችኋል።
“ከዕለታት አንድ ቀን ዛፎች በላያቸው የሚነግሥ ንጉሥ ለመቀባት ሄዱ። በመሆኑም የወይራ ዛፍን ‘በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት።
ሆኖም የወይራ ዛፍ ‘ሄጄ ከሌሎች ዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል አምላክንና ሰዎችን ለማክበር የሚጠቀሙበትን ዘይቴን መስጠት ልተው?’ አላቸው።
ከዚያም ዛፎቹ የበለስን ዛፍ ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት።
የበለስ ዛፍ ግን ‘ሄጄ ከሌሎች ዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል ጣፋጭና መልካም ፍሬዬን መስጠት ልተው?’ አላቸው።
በመቀጠልም ዛፎቹ የወይን ተክልን ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት።
የወይን ተክልም መልሶ ‘ሄጄ ከሌሎች ዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል አምላክንና ሰዎችን የሚያስደስተውን አዲስ የወይን ጠጅ መስጠቴን ልተው?’ አላቸው።
በመጨረሻም ሌሎቹ ዛፎች ሁሉ የእሾህ ቁጥቋጦን ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት።
በዚህ ጊዜ የእሾህ ቁጥቋጦው ዛፎቹን እንዲህ አላቸው፦ ‘በእናንተ ላይ ንጉሥ እንድሆን የምትቀቡኝ እውነት ከልባችሁ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ። ካልሆነ ግን እሳት ከእሾህ ቁጥቋጦው ወጥቶ አርዘ ሊባኖሶችን ያቃጥል።’
“ለመሆኑ አቢሜሌክን ንጉሥ ያደረጋችሁት በየዋህነትና በቅንነት ነው? ለየሩባአልና ለቤተሰቡ ጥሩነት አሳይታችኋል? የሚገባውን ውለታስ መልሳችሁለታል?
አባቴ ለእናንተ ሲል በተዋጋ ጊዜ እናንተን ከምድያማውያን እጅ ለመታደግ ሕይወቱን አደጋ ላይ ጥሏል።
እናንተ ግን ዛሬ በአባቴ ቤተሰብ ላይ ተነሳችሁ፤ 70 ልጆቹንም በአንድ ድንጋይ ላይ ገደላችኋቸው። ወንድማችሁ ስለሆነ ብቻ ከባሪያይቱ የወለደውን ልጁን አቢሜሌክን በሴኬም መሪዎች ላይ አነገሣችሁት።
በዛሬው ዕለት ለየሩባአልና ለቤተሰቡ ይህን ያደረጋችሁት በየዋህነትና በቅንነት ከሆነ በአቢሜሌክ ደስ ይበላችሁ፤ እሱም በእናንተ ደስ ይበለው።
ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቢሜሌክ ወጥቶ የሴኬምን መሪዎችና ቤትሚሎን ያቃጥል፤ እንዲሁም እሳት ከሴኬም መሪዎችና ከቤትሚሎ ወጥቶ አቢሜሌክን ያቃጥል።”
ከዚያም ኢዮዓታም ወደ በኤር ሸሽቶ አመለጠ፤ በወንድሙ በአቢሜሌክ የተነሳም በዚያ ኖረ።
አቢሜሌክም በእስራኤል ላይ ሦስት ዓመት ገዛ።
ከዚያም አምላክ በአቢሜሌክና በሴኬም መሪዎች መካከል ቅራኔ እንዲፈጠር አደረገ፤ እነሱም በአቢሜሌክ ላይ ተንኮል አሴሩበት።
ይህም የሆነው ወንድሞቹን የገደለውን አቢሜሌክንና ወንድሞቹን እንዲገድል የረዱትን የሴኬምን መሪዎች በሞቱት ሰዎች ደም ተጠያቂ በማድረግ በ70ዎቹ የየሩባአል ልጆች ላይ የተፈጸመውን ግፍ ለመበቀል ነው።
በመሆኑም የሴኬም መሪዎች አድብተው እሱን የሚጠባበቁ ሰዎችን በተራሮች አናት ላይ መደቡ፤ እነሱም በአጠገባቸው የሚያልፈውን መንገደኛ ሁሉ ይዘርፉ ነበር። በኋላም ሁኔታው ለአቢሜሌክ ተነገረው።
ከዚያም የኤቤድ ልጅ ገአል ከወንድሞቹ ጋር ወደ ሴኬም ተሻገረ፤ የሴኬምም መሪዎች እምነት ጣሉበት።
እነሱም ወደ እርሻ ወጥተው የወይን ፍሬያቸውን ከሰበሰቡ በኋላ ጨመቁት፤ በዓልም አከበሩ፤ ከዚያም ወደ አምላካቸው ቤት ገብተው በሉ፤ ጠጡም፤ አቢሜሌክንም ረገሙ።
ከዚያም የኤቤድ ልጅ ገአል እንዲህ አለ፦ “ለመሆኑ አቢሜሌክ ማን ነው? እናገለግለውስ ዘንድ ሴኬም ማን ነው? እሱ የየሩባአል ልጅ አይደለም? የእሱ ተወካይስ ዘቡል አይደለም? የሴኬምን አባት የኤሞርን ሰዎች አገልግሉ! አቢሜሌክን የምናገለግለው ለምንድን ነው?
ይህን ሕዝብ የማዘው እኔ ብሆን ኖሮ አቢሜሌክን አስወግደው ነበር።” ከዚያም አቢሜሌክን “ብዙ ሠራዊት አሰባስበህ ና ውጣ” አለው።
የከተማዋ ገዢ የሆነው ዘቡል የኤቤድ ልጅ ገአል የተናገረውን ነገር በሰማ ጊዜ ቁጣው ነደደ።
በመሆኑም ለአቢሜሌክ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት በሚስጥር መልእክተኞችን ላከ፦ “እነሆ፣ የኤቤድ ልጅ ገአልና ወንድሞቹ ወደ ሴኬም መጥተዋል፤ ከተማዋም በአንተ ላይ እንድታምፅ እያነሳሱ ነው።
በመሆኑም አንተም ሆንክ አብረውህ ያሉት ሰዎች በሌሊት ወጥታችሁ ሜዳው ላይ አድፍጡ።
ጠዋት ላይ ልክ ፀሐይ ስትወጣ፣ ማልደህ በመነሳት በከተማዋ ላይ ጥቃት ሰንዝር፤ እሱና አብረውት ያሉት ሰዎች አንተን ለመውጋት ሲወጡም እሱን ድል ለመምታት የቻልከውን ሁሉ አድርግ።”
በመሆኑም አቢሜሌክና አብረውት ያሉት ሰዎች በሙሉ በሌሊት ተነሱ፤ በአራት ቡድንም ሆነው በሴኬም ላይ አደፈጡ።
የኤቤድ ልጅ ገአል ወጥቶ በከተማዋ መግቢያ በር ላይ በቆመ ጊዜ አቢሜሌክና አብረውት ያሉት ሰዎች ካደፈጡበት ቦታ ተነሱ።
ገአልም ሰዎቹን ባያቸው ጊዜ ዘቡልን “ተመልከት፣ ከተራሮቹ አናት ላይ ሰዎች እየወረዱ ነው” አለው። ዘቡል ግን “ሰው መስሎ የታየህ የተራሮቹ ጥላ ነው” አለው።
በኋላም ገአል “ተመልከት፤ ከምድሩ መሃል ሰዎች እየወረዱ ነው፤ አንደኛው ቡድን በመኦነኒም ትልቅ ዛፍ በኩል አድርጎ እየመጣ ነው” አለ።
ዘቡልም “‘እናገለግለው ዘንድ አቢሜሌክ ማን ነው?’ እያልክ ጉራህን ስትነዛ አልነበረም? የናቅከው ሕዝብ ይህ አይደለም? እስቲ አሁን ውጣና ግጠማቸው” ሲል መለሰለት።
በመሆኑም ገአል ከሴኬም መሪዎች ፊት ፊት በመሄድ ከአቢሜሌክ ጋር ተዋጋ።
አቢሜሌክም አሳደደው፤ ገአልም ከፊቱ ሸሸ፤ እስከ ከተማዋም መግቢያ በር ድረስ ብዙ ሰው ተረፈረፈ።
አቢሜሌክም በአሩማ መኖሩን ቀጠለ፤ ዘቡልም ገአልንና ወንድሞቹን ከሴኬም አስወጣቸው።
በማግስቱም ሕዝቡ ከከተማዋ ወጣ፤ ይህም ለአቢሜሌክ ተነገረው።
እሱም ሰዎቹን ወስዶ በሦስት ቡድን በመክፈል ሜዳ ላይ አድፍጦ ይጠባበቅ ጀመር። ሕዝቡም ከከተማዋ መውጣቱን ተመለከተ፤ በዚህ ጊዜም በእነሱ ላይ ጥቃት ሰነዘረ፤ መታቸውም።
አቢሜሌክና አብረውት የነበሩት ቡድኖች በፍጥነት ወደ ፊት በመገስገስ በከተማዋ መግቢያ በር ላይ ቆሙ፤ ሁለቱ ቡድኖች ደግሞ ከከተማዋ ውጭ ባሉት ሰዎች ሁሉ ላይ ጥቃት ሰነዘሩ፤ መቷቸውም።
አቢሜሌክም ያን ቀን ሙሉ ከተማዋን ሲወጋ ዋለ፤ በመጨረሻም በቁጥጥሩ ሥር አዋላት። በከተማዋም ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ገደለ፤ ከዚያም ከተማዋን አፈራረሳት፤ በላይዋም ጨው ዘራባት።
የሴኬም ግንብ መሪዎች በሙሉ ይህን ሲሰሙ ወዲያውኑ በኤልበሪት ቤት ወደሚገኘው መሸሸጊያ ቦታ ሄዱ።
የሴኬም ግንብ መሪዎች በሙሉ አንድ ላይ እንደተሰባሰቡ ለአቢሜሌክ በተነገረውም ጊዜ
አቢሜሌክና አብረውት የነበሩት ሰዎች በሙሉ ወደ ጻልሞን ተራራ ወጡ። አቢሜሌክም መጥረቢያ ይዞ የዛፍ ቅርንጫፍ ከቆረጠ በኋላ አንስቶ በትከሻው ተሸከመው፤ አብረውት የነበሩትንም ሰዎች “እኔ ሳደርግ ያያችሁትን ፈጥናችሁ አድርጉ!” አላቸው።
በመሆኑም ሰዎቹ ሁሉ ቅርንጫፎች ቆርጠው በመያዝ አቢሜሌክን ተከተሉት። ከዚያም ቅርንጫፎቹን መሸሸጊያ ቦታው ላይ በመቆለል መሸሸጊያ ቦታውን በእሳት አያያዙት። በዚህም የተነሳ የሴኬም ግንብ ሰዎች በሙሉ ይኸውም 1,000 ገደማ የሚሆኑ ወንዶችና ሴቶች ሞቱ።
ከዚያም አቢሜሌክ ወደ ቴቤጽ ሄደ፤ ቴቤጽንም ከቦ በቁጥጥር ሥር አዋላት።
በከተማዋ መሃል ጠንካራ ግንብ ስለነበር ወንዶችና ሴቶች በሙሉ እንዲሁም የከተማዋ መሪዎች በሙሉ ወደዚያ ሸሹ። እነሱም ከውስጥ ሆነው በሩን ከዘጉት በኋላ የግንቡ አናት ላይ ወጡ።
አቢሜሌክም ወደ ግንቡ ሄደ፤ ጥቃትም ሰነዘረበት። ግንቡንም በእሳት ለማቃጠል ወደ መግቢያው ተጠጋ።
ከዚያም አንዲት ሴት በአቢሜሌክ ራስ ላይ የወፍጮ መጅ በመልቀቅ ጭንቅላቱን ፈረከሰችው።
እሱም ጋሻ ጃግሬውን ወዲያውኑ ጠርቶ “‘ሴት ገደለችው’ እንዳይሉኝ ሰይፍህን ምዘዝና ግደለኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬውም ወጋው፤ እሱም ሞተ።
የእስራኤል ሰዎች አቢሜሌክ መሞቱን ሲያዩ ሁሉም ወደቤታቸው ተመለሱ።
በዚህ መንገድ አምላክ፣ አቢሜሌክ 70 ወንድሞቹን በመግደል በአባቱ ላይ ለፈጸመው ክፉ ነገር የእጁን እንዲያገኝ አደረገ።
በተጨማሪም አምላክ የሴኬም ሰዎች ክፋት ሁሉ በራሳቸው ላይ እንዲደርስ አደረገ። በመሆኑም የየሩባአል ልጅ የኢዮዓታም እርግማን ደረሰባቸው።
የይሖዋም መልአክ ከጊልጋል ወደ ቦኪም ወጣ፤ እንዲህም አለ፦ “ከግብፅ አውጥቼ ለአባቶቻችሁ ወደማልኩላቸው ምድር አስገባኋችሁ። በተጨማሪም እንዲህ አልኩ፦ ‘እኔ ከእናንተ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ፈጽሞ አላፈርስም።
እናንተም ከዚህች ምድር ነዋሪዎች ጋር ቃል ኪዳን አትግቡ፤ መሠዊያዎቻቸውንም አፈራርሱ።’ እናንተ ግን ቃሌን አልሰማችሁም። እንዲህ ያደረጋችሁት ለምንድን ነው?
በዚህም የተነሳ ‘እነሱን ከፊታችሁ አላስወጣቸውም፤ ለእናንተም ወጥመድ ይሆኑባችኋል፤ አማልክታቸውም ያታልሏችኋል’ አልኩ።”
የይሖዋም መልአክ ለእስራኤላውያን በሙሉ ይህን በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ።
ስለሆነም የዚያን ስፍራ ስም ቦኪም አሉት፤ በዚያም ለይሖዋ መሥዋዕት አቀረቡ።
ኢያሱ ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ እያንዳንዱ እስራኤላዊ ምድሪቱን ለመውረስ ወደየርስቱ ሄደ።
ሕዝቡም ኢያሱ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ እንዲሁም ከኢያሱ በኋላ በሕይወት በኖሩትና ይሖዋ ለእስራኤል ሲል ያደረገውን ታላቅ ነገር በሙሉ በተመለከቱት ሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ ይሖዋን አገለገለ።
ከዚያም የይሖዋ አገልጋይ የሆነው የነዌ ልጅ ኢያሱ በ110 ዓመቱ ሞተ።
እነሱም ከጋአሽ ተራራ በስተ ሰሜን በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ በሚገኘው ርስቱ በቲምናትሄረስ ቀበሩት።
ያም ትውልድ ሁሉ ወደ አያቶቹ ተሰበሰበ፤ ከእነሱም በኋላ ይሖዋንም ሆነ እሱ ለእስራኤል ያደረገውን ነገር የማያውቅ ሌላ ትውልድ ተነሳ።
በመሆኑም እስራኤላውያን በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አደረጉ፤ ባአልንም አገለገሉ።
በዚህ መንገድ ከግብፅ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን ተዉ። በዙሪያቸው ያሉት ሕዝቦች የሚያመልኳቸውን ሌሎች አማልክት ተከተሉ፤ ለእነሱም በመስገድ ይሖዋን አስቆጡት።
ይሖዋን ትተው ባአልንና የአስታሮትን ምስሎች አገለገሉ።
በዚህ ጊዜ የይሖዋ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ በመሆኑም ለሚዘርፏቸው ዘራፊዎች አሳልፎ ሰጣቸው። በዙሪያቸው ላሉ ጠላቶቻቸው ሸጣቸው፤ ከዚያ ወዲህ ጠላቶቻቸውን መቋቋም አልቻሉም።
ይሖዋ አስቀድሞ በተናገረውና ይሖዋ ለእነሱ በማለው መሠረት በሄዱበት ቦታ ሁሉ ጥፋት ያመጣባቸው ዘንድ የይሖዋ እጅ በእነሱ ላይ ነበር፤ እነሱም በከባድ ጭንቀት ተውጠው ነበር።
በመሆኑም ይሖዋ ከዘራፊዎቻቸው እጅ የሚያድኗቸውን መሳፍንት አስነሳላቸው።
እነሱ ግን መሳፍንቱን እንኳ ለመስማት ፈቃደኞች አልሆኑም፤ እንዲያውም ከሌሎች አማልክት ጋር አመነዘሩ፤ ለእነሱም ሰገዱ። የይሖዋን ትእዛዛት ያከብሩ የነበሩ አባቶቻቸው ከሄዱበት መንገድ ፈጥነው ዞር አሉ። እነሱ እንዳደረጉት ማድረግ ሳይችሉ ቀሩ።
ይሖዋ መሳፍንትን በሚያስነሳላቸው ጊዜ ሁሉ ይሖዋ ከመስፍኑ ጋር ይሆን ነበር፤ በመስፍኑም ዘመን ሁሉ ከጠላቶቻቸው እጅ ያድናቸው ነበር፤ ምክንያቱም ይሖዋ በሚጨቁኗቸውና በሚያንገላቷቸው ሰዎች የተነሳ ሲቃትቱ ያዝናል።
መስፍኑ በሚሞትበት ጊዜ ግን ሌሎች አማልክትን በመከተልና በማገልገል እንዲሁም ለእነሱ በመስገድ በድጋሚ ከአባቶቻቸው ይበልጥ መጥፎ ድርጊት ይፈጽማሉ። መጥፎ ሥራቸውን ያልተዉ ከመሆኑም ሌላ በእንቢተኝነታቸው ገፍተውበታል።
በመጨረሻም የይሖዋ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ እንዲህም አለ፦ “ይህ ብሔር ከአባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ስላፈረሰና ቃሌን ስላልሰማ
እኔም ኢያሱ በሞተ ጊዜ ሳያጠፋ ከተዋቸው ብሔራት መካከል አንዳቸውንም ከፊቱ አላባርርም።