text stringlengths 4 267 |
|---|
እሱም ብሩን ለእናቱ ከመለሰላት በኋላ እናቱ 200 የብር ሰቅል ወስዳ ለብር አንጥረኛው ሰጠችው። እሱም የተቀረጸ ምስልና ከብረት የተሠራ ሐውልት ሠራበት፤ እነሱም በሚክያስ ቤት ተቀመጡ። |
ሚክያስ የተባለው ይህ ሰው የአማልክት ቤት ነበረው፤ እሱም ኤፉድና የተራፊም ቅርጻ ቅርጾች ሠራ፤ ከወንዶች ልጆቹም መካከል አንዱን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው ሾመው። |
በዚያ ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም። እያንዳንዱም ሰው ለራሱ ትክክል መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር። |
በዚያ ጊዜ በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም የሚኖር ከይሁዳ ቤተሰብ የሆነ አንድ ወጣት ነበር። እሱም ሌዋዊ ሲሆን በዚያ ለተወሰነ ጊዜ ተቀምጦ ነበር። |
ይህም ሰው የሚኖርበት ስፍራ ለመፈለግ በይሁዳ የምትገኘውን የቤተልሔምን ከተማ ለቆ ሄደ። እየተጓዘም ሳለ በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ ወደሚገኘው ወደ ሚክያስ ቤት ደረሰ። |
ከዚያም ሚክያስ “ከየት ነው የመጣኸው?” ሲል ጠየቀው። እሱም መልሶ “በይሁዳ ከምትገኘው ከቤተልሔም የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፤ የምኖርበት ስፍራ ለመፈለግ እየሄድኩ ነው” አለው። |
በመሆኑም ሚክያስ “እንግዲያው እኔ ጋ ተቀመጥ፤ እንደ አባትና እንደ ካህንም ሆነህ አገልግለኝ። እኔ ደግሞ በዓመት አሥር የብር ሰቅል እንዲሁም ልብስና ምግብህን እሰጥሃለሁ” አለው። ስለዚህ ሌዋዊው ገባ። |
በዚህ መንገድ ሌዋዊው ከሰውየው ጋር ለመኖር ተስማማ፤ ወጣቱም ከልጆቹ እንደ አንዱ ሆነለት። |
በተጨማሪም ሚክያስ ሌዋዊውን ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው ሾመው፤ እሱም በሚክያስ ቤት ኖረ። |
ከዚያም ሚክያስ “ሌዋዊ፣ ካህን ስለሆነልኝ ይሖዋ መልካም እንደሚያደርግልኝ አሁን ተረድቻለሁ” አለ። |
በእስራኤል ንጉሥ ባልነበረበት በዚያ ዘመን በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ ራቅ ብሎ በሚገኝ ስፍራ የሚኖር አንድ ሌዋዊ በይሁዳ ካለችው ከቤተልሔም አንዲት ቁባት አገባ። |
ቁባቱ ግን ለእሱ ታማኝ አልነበረችም፤ ከዚያም ትታው በይሁዳ ባለችው ቤተልሔም ወደሚገኘው ወደ አባቷ ቤት ሄደች። እሷም በዚያ ለአራት ወር ተቀመጠች። |
ባሏም እንድትመለስ ሊያግባባት ተነስቶ ወደ እሷ ሄደ፤ ወደዚያም የሄደው አገልጋዩንና ሁለት አህዮቹን ይዞ ነበር። እሷም ወደ አባቷ ቤት አስገባችው። አባቷም ባየው ጊዜ እሱን በማግኘቱ ተደሰተ። |
ስለሆነም አማቱ ማለትም የወጣቷ አባት ሰውየውን ለሦስት ቀን እሱ ጋ እንዲቆይ አግባባው፤ እነሱም በሉ፣ ጠጡም፤ እሱም እዚያው አደረ። |
በአራተኛው ቀን በማለዳ ለመሄድ ሲነሱ የወጣቷ አባት አማቹን “ብርታት እንድታገኙ ትንሽ እህል ቅመሱ፤ ከዚያ በኋላ ትሄዳላችሁ” አለው። |
በመሆኑም ተቀመጡ፤ እነሱም አብረው በሉ፤ ጠጡም፤ ከዚያም የወጣቷ አባት ሰውየውን “እባክህ እዚሁ እደር፤ ልብህም ደስ ይበለው” አለው። |
ሰውየውም ለመሄድ ሲነሳ አማቱ ይለምነው ነበር፤ ስለዚህ ዳግመኛ እዚያው አደረ። |
በአምስተኛውም ቀን ለመሄድ በማለዳ ሲነሳ የወጣቷ አባት “ብርታት እንድታገኝ እባክህ ትንሽ እህል ቅመስ” አለው። እነሱም ቀኑ እስኪገባደድ ድረስ እዚያው ዋሉ፤ አብረውም ሲበሉ ቆዩ። |
ሰውየውም ከቁባቱና ከአገልጋዩ ጋር ለመሄድ ሲነሳ አማቱ ማለትም የወጣቷ አባት እንዲህ አለው፦ “አሁን እኮ እየመሸ ነው! እባካችሁ እዚሁ እደሩ። ቀኑ እየተገባደደ ነው። እዚሁ እደሩና ልባችሁ ደስ ይበለው። ነገ በማለዳ ተነስታችሁ ትጓዛላችሁ፤ ወደ ቤታችሁም ትሄዳላችሁ።” |
ሆኖም ሰውየው እዚያ ለማደር አልፈለገም፤ ስለሆነም ተነስቶ እስከ ኢያቡስ ማለትም እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ተጓዘ። ከእሱም ጋር ጭነት የተጫኑት ሁለቱ አህዮች፣ ቁባቱና አገልጋዩ ነበሩ። |
ወደ ኢያቡስም በቀረቡ ጊዜ ቀኑ መሸትሸት ብሎ ነበር። በመሆኑም አገልጋዩ ጌታውን “ወደዚህች የኢያቡሳውያን ከተማ ጎራ ብለን ብናድር አይሻልም?” አለው። |
ጌታው ግን “እስራኤላውያን ወዳልሆኑ ባዕድ ሰዎች ከተማ መግባት የለብንም። ከዚህ ይልቅ እስከ ጊብዓ ድረስ እንሂድ” አለው። |
ከዚያም አገልጋዩን “ና፣ ከእነዚህ ስፍራዎች ወደ አንዱ ለመድረስ እንሞክር፤ ጊብዓ ወይም ራማ እናድራለን” አለው። |
በመሆኑም ጉዟቸውን ቀጠሉ፤ የቢንያም ወደሆነችው ወደ ጊብዓ በተቃረቡም ጊዜ ፀሐይዋ መጥለቅ ጀመረች። |
ስለዚህ በጊብዓ ለማደር ወደዚያ ጎራ አሉ። ገብተውም በከተማዋ አደባባይ ተቀመጡ፤ ሆኖም ሊያሳድራቸው ወደ ቤቱ የወሰዳቸው ማንም ሰው አልነበረም። |
በመጨረሻም ምሽት ላይ ከእርሻ ሥራው እየተመለሰ ያለ አንድ አረጋዊ ሰው መጣ። ይህ ሰው የኤፍሬም ተራራማ አካባቢ ሰው ነበር፤ በጊብዓም መኖር ከጀመረ የተወሰነ ጊዜ ሆኖታል፤ የከተማዋ ነዋሪዎች ግን ቢንያማውያን ነበሩ። |
አረጋዊውም ቀና ብሎ መንገደኛውን ሰው በከተማዋ አደባባይ ሲያየው “ወዴት ነው የምትሄደው? የመጣኸውስ ከየት ነው?” አለው። |
እሱም መልሶ እንዲህ አለው፦ “እኛ በይሁዳ ከምትገኘው ቤተልሔም ተነስተን በኤፍሬም ተራራማ አካባቢዎች ራቅ ብሎ ወደሚገኝ ስፍራ እየተጓዝን ነው፤ እኔ የዚያ አካባቢ ሰው ነኝ። በይሁዳ ወደምትገኘው ቤተልሔም ሄጄ ነበር፤ አሁን ወደ ይሖዋ ቤት እየሄድኩ ነው፤ ይሁንና ወደ ቤቱ የሚያስገባኝ ሰው አላገኘሁም። |
ለአህዮቻችን የሚሆን በቂ ገለባና ገፈራ አለን፤ በተጨማሪም ለእኔም ሆነ ለሴትየዋ እንዲሁም ለአገልጋያችን የሚሆን ምግብና የወይን ጠጅ አለን። ምንም የጎደለ ነገር የለም።” |
ሆኖም አረጋዊው ሰው “ሰላም ለአንተ ይሁን! የሚያስፈልጋችሁን ማንኛውንም ነገር እኔ አሟላላችኋለሁ። ብቻ እዚህ አደባባይ ላይ አትደሩ” አለው። |
ስለዚህ ወደ ቤቱ ይዞት ገባ፤ ለአህዮቹም ገፈራ ሰጣቸው። ሰዎቹም እግራቸውን ታጠቡ፤ በሉ፣ ጠጡም። |
እነሱም እየተደሰቱ ሳለ በከተማዋ ውስጥ የሚኖሩ የተወሰኑ ጋጠወጥ ወንዶች ቤቱን ከበው እርስ በርስ እየተገፈታተሩ በሩን ይደበድቡ ጀመር፤ የቤቱ ባለቤት የሆነውንም አረጋዊ “ከእሱ ጋር የፆታ ግንኙነት እንድንፈጽም ቤትህ የገባውን ሰው ወደ ውጭ አውጣልን” ይሉት ነበር። |
በዚህ ጊዜ የቤቱ ባለቤት ወደ እነሱ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “ወንድሞቼ ተዉ፤ ይህን መጥፎ ድርጊት አትፈጽሙ። እባካችሁ ይህ ሰው የእኔ እንግዳ ነው። እንዲህ ያለውን አሳፋሪ ድርጊት አትፈጽሙ። |
ይኸው ድንግል የሆነች ልጄና የሰውየው ቁባት አሉ። እንግዲህ አሻፈረኝ ካላችሁ እነሱን ላውጣላችሁና ልታዋርዷቸው ትችላላችሁ። በዚህ ሰው ላይ ግን እንዲህ ያለውን አሳፋሪ ድርጊት አትፈጽሙ።” |
ሰዎቹ ግን ሊሰሙት ፈቃደኞች አልሆኑም፤ በመሆኑም ሰውየው ቁባቱን ይዞ ወደ ውጭ አወጣላቸው። እነሱም ደፈሯት፤ እስኪነጋም ድረስ ሌሊቱን ሙሉ ሲጫወቱባት አደሩ። ከዚያም ጎህ ሲቀድ ለቀቋት። |
ሴትየዋም በማለዳ መጥታ ጌታዋ ባለበት የሰውየው ቤት በር ላይ ተዘረረች፤ ብርሃን እስኪሆንም ድረስ እዚያው ወድቃ ቀረች። |
በኋላም ጌታዋ ጉዞውን ለመቀጠል በጠዋት ተነስቶ የቤቱን በሮች ሲከፍት ሴትየዋ ማለትም ቁባቱ እጇ ደፉ ላይ ተዘርግቶ የቤቱ በር ላይ ወድቃ ተመለከተ። |
እሱም “ተነሽ፤ እንሂድ” አላት። ነገር ግን ምንም መልስ አልነበረም። ከዚያም ሰውየው እሷን በአህያው ላይ አድርጎ ወደ ቤቱ ሄደ። |
ቤቱም እንደደረሰ ቢላ አንስቶ ቁባቱን በአጥንቶቿ መገጣጠሚያ ላይ 12 ቦታ ቆራረጣት፤ ከዚያም ወደ እያንዳንዱ የእስራኤል ክልል አንድ ቁራጭ ላከ። |
ይህን ያየ ሰው ሁሉ እንዲህ ይል ነበር፦ “እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ ታይቶም፣ ተሰምቶም አያውቅም። ይህን ጉዳይ በቁም ነገር አስቡበት፤ ተመካከሩበት፤ ከዚያም ምን መደረግ እንዳለበት ንገሩን።” |
ጊልያዳዊው ዮፍታሔ ኃያል ተዋጊ ነበር፤ እሱም የአንዲት ዝሙት አዳሪ ልጅ የነበረ ሲሆን አባቱ ጊልያድ ነበር። |
ይሁንና የጊልያድ ሚስትም ለጊልያድ ወንዶች ልጆች ወለደችለት። የዚህችኛዋ ሚስቱ ልጆች ሲያድጉም ዮፍታሔን “አንተ ከሌላ ሴት የተወለድክ ስለሆንክ በአባታችን ቤት ምንም ውርሻ አይኖርህም” በማለት አባረሩት። |
በመሆኑም ዮፍታሔ ከወንድሞቹ ሸሽቶ በጦብ ምድር መኖር ጀመረ። ሥራ ፈት ሰዎችም ከእሱ ጋር በመተባበር ተከተሉት። |
ከተወሰነ ጊዜ በኋላም አሞናውያን ከእስራኤላውያን ጋር ተዋጉ። |
አሞናውያን ከእስራኤላውያን ጋር በሚዋጉበት ጊዜ የጊልያድ ሽማግሌዎች ዮፍታሔን ከጦብ ምድር መልሰው ለማምጣት ወዲያውኑ ወደዚያ ሄዱ። |
ዮፍታሔንም “አሞናውያንን መውጋት እንድንችል መጥተህ አዛዣችን ሁን” አሉት። |
ዮፍታሔ ግን የጊልያድን ሽማግሌዎች “እኔን እጅግ ከመጥላታችሁ የተነሳ ከአባቴ ቤት ያባረራችሁኝ እናንተ አይደላችሁም? ታዲያ አሁን ጭንቅ ውስጥ ስትገቡ ወደ እኔ የምትመጡት ለምንድን ነው?” አላቸው። |
በዚህ ጊዜ የጊልያድ ሽማግሌዎች ዮፍታሔን እንዲህ አሉት፦ “አሁን ወደ አንተ ተመልሰን የመጣነውም ለዚህ ነው። ከእኛ ጋር አብረኸን በመሄድ ከአሞናውያን ጋር የምትዋጋ ከሆነ ለጊልያድ ነዋሪዎች በሙሉ መሪ ትሆናለህ።” |
ዮፍታሔም የጊልያድን ሽማግሌዎች “እንግዲህ ከአሞናውያን ጋር እንድዋጋ ወደዚያ ብትመልሱኝና ይሖዋ እነሱን ድል ቢያደርግልኝ በእርግጥ እኔ መሪያችሁ እሆናለሁ!” አላቸው። |
የጊልያድ ሽማግሌዎችም ዮፍታሔን “እንዳልከው ካላደረግን ይሖዋ በመካከላችን ምሥክር ይሁን” አሉት። |
በመሆኑም ዮፍታሔ ከጊልያድ ሽማግሌዎች ጋር ሄደ፤ ሕዝቡም መሪና አዛዥ አደረገው። ዮፍታሔም የተናገረውን ነገር ሁሉ በምጽጳ በይሖዋ ፊት ደገመው። |
ከዚያም ዮፍታሔ ለአሞናውያን ንጉሥ “ምድሬን ልትወጋ የመጣኸው ከእኔ ጋር ምን ጠብ ቢኖርህ ነው?” ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞች ላከ። |
የአሞናውያን ንጉሥም የዮፍታሔን መልእክተኞች እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ያደረግኩት እስራኤል ከግብፅ በወጣበት ጊዜ ከአርኖን አንስቶ እስከ ያቦቅና እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ያለውን መሬቴን ስለወሰደብኝ ነው። አሁንም መሬቴን በሰላም መልሱልኝ።” |
ዮፍታሔ ግን መልእክተኞቹን እንደገና ወደ አሞናውያን ንጉሥ በመላክ |
እንዲህ አለው፦ “ዮፍታሔ እንዲህ ይላል፦ ‘እስራኤል የሞዓባውያንን ምድርና የአሞናውያንን ምድር አልወሰደም፤ |
ምክንያቱም እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡ ጊዜ በምድረ በዳው አልፈው እስከ ቀይ ባሕርና እስከ ቃዴስ ድረስ መጡ። |
ከዚያም እስራኤል ለኤዶም ንጉሥ “እባክህ ምድርህን አቋርጠን እንድናልፍ ፍቀድልን” ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞችን ላከ፤ የኤዶም ንጉሥ ግን ለመስማት ፈቃደኛ አልሆነም። ለሞዓብም ንጉሥ መልእክት ላኩ፤ እሱም ቢሆን በዚህ ሐሳብ አልተስማማም። ስለዚህ እስራኤል በቃዴስ ተቀመጠ። |
በምድረ በዳው በተጓዙበት ጊዜ በኤዶም ምድርና በሞዓብ ምድር ዳርቻ አልፈው ሄዱ። ከሞዓብ ምድር በስተ ምሥራቅ ተጉዘውም በአርኖን ክልል ሰፈሩ፤ ወደ ሞዓብ ወሰንም አልገቡም፤ ምክንያቱም አርኖን የሞዓብ ወሰን ነበር። |
“‘ከዚያም እስራኤል ወደ አሞራውያን ንጉሥ ማለትም ወደ ሃሽቦን ንጉሥ ወደ ሲሖን መልእክተኞችን ላከ፤ እስራኤልም “እባክህ ምድርህን አቋርጠን ወደ ገዛ ስፍራችን እንድናልፍ ፍቀድልን” አለው። |
ሲሖን ግን በግዛቱ አቋርጦ እንዲያልፍ ለመፍቀድ እስራኤልን አላመነውም፤ በመሆኑም ሕዝቡን ሁሉ በአንድነት ሰብስቦ በያሃጽ ሰፈረ፤ ከእስራኤልም ጋር ውጊያ ገጠመ። |
በዚህ ጊዜ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሲሖንንና ሕዝቡን ሁሉ ለእስራኤላውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ በመሆኑም ድል አደረጓቸው፤ እስራኤላውያንም በዚያ የሚኖሩትን የአሞራውያንን ምድር በሙሉ ወረሱ። |
በዚህ መንገድ ከአርኖን አንስቶ እስከ ያቦቅ እንዲሁም ከምድረ በዳው አንስቶ እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ያለውን የአሞራውያንን ግዛት በሙሉ ወረሱ። |
“‘እንግዲህ አሞራውያንን ከሕዝቡ ከእስራኤላውያን ፊት ያባረራቸው የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ነው፤ እና አሁን አንተ ደግሞ እነሱን ልታባርራቸው ነው? |
አንተስ ብትሆን አምላክህ ከሞሽ እንድትወርሰው የሰጠህን ሁሉ አትወርስም? ስለዚህ እኛም አምላካችን ይሖዋ ከፊታችን ያባረራቸውን ሁሉ እናባርራለን። |
ደግሞስ አንተ የሞዓብ ንጉሥ ከሆነው ከሴፎር ልጅ ከባላቅ ትበልጣለህ? ለመሆኑ እሱ እስራኤልን ለመገዳደር ሞክሮ ያውቃል? ወይስ ከእነሱ ጋር ውጊያ ገጥሞ ያውቃል? |
እስራኤል በሃሽቦንና በሥሯ ባሉት ከተሞች፣ በአሮዔርና በሥሯ ባሉት ከተሞች እንዲሁም በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ በሚገኙት ከተሞች ሁሉ ለ300 ዓመት ተቀምጦ በነበረበት ጊዜ እነዚያን ቦታዎች መልሳችሁ ለመውሰድ ያልሞከራችሁት ለምንድን ነው? |
እንግዲህ እኔ ምንም የበደልኩህ ነገር የለም፤ አንተም ብትሆን በእኔ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መነሳትህ ተገቢ አይደለም። ፈራጁ ይሖዋ በእስራኤል ሕዝብና በአሞን ሕዝብ መካከል ዛሬ ይፍረድ።’” |
የአሞናውያን ንጉሥ ግን ዮፍታሔ የላከበትን መልእክት ለመስማት ፈቃደኛ አልሆነም። |
የይሖዋ መንፈስ በዮፍታሔ ላይ ወረደ፤ እሱም በጊልያድ ወደምትገኘው ወደ ምጽጳ ለመሄድ ጊልያድንና ምናሴን አቋርጦ አለፈ፤ በጊልያድ ከምትገኘው ምጽጳም ተነስቶ ወደ አሞናውያን ሄደ። |
ከዚያም ዮፍታሔ እንዲህ ሲል ለይሖዋ ስእለት ተሳለ፦ “አሞናውያንን በእጄ አሳልፈህ ከሰጠኸኝ |
ከአሞናውያን ዘንድ በሰላም በምመለስበት ጊዜ ሊቀበለኝ ከቤቴ በር የሚወጣው ማንኛውም ሰው የይሖዋ ይሆናል፤ እኔም የሚቃጠል መባ አድርጌ አቀርበዋለሁ።” |
በመሆኑም ዮፍታሔ ከአሞናውያን ጋር ለመዋጋት ሄደ፤ ይሖዋም እነሱን በእጁ አሳልፎ ሰጠው። |
እሱም ከአሮዔር አንስቶ እስከ ሚኒት ድረስ ማለትም 20 ከተሞችን፣ ከዚያም አልፎ እስከ አቤልከራሚም ድረስ ፈጽሞ ደመሰሳቸው። በዚህ መንገድ አሞናውያን ለእስራኤላውያን ተገዙ። |
በመጨረሻም ዮፍታሔ በምጽጳ ወደሚገኘው ቤቱ መጣ፤ በዚህ ጊዜ ሴት ልጁ አታሞ እየመታችና እየጨፈረች ልትቀበለው ወጣች! ልጁ እሷ ብቻ ነበረች። ከእሷ ሌላ ወንድም ሆነ ሴት ልጅ አልነበረውም። |
እሱም ባያት ጊዜ ልብሱን ቀደደ፤ እንዲህም አለ፦ “ወዮ፣ ልጄ! ልቤን ሰበርሽው፤ እንግዲህ ከቤት የማስወጣው አንቺን ነው። አንዴ ለይሖዋ ቃል ገብቻለሁ፤ ልመልሰውም አልችልም።” |
እሷም እንዲህ አለችው፦ “አባቴ ሆይ፣ ለይሖዋ ቃል ከገባህ፣ የገባኸውን ቃል በእኔ ላይ ፈጽምብኝ፤ ምክንያቱም ይሖዋ ጠላቶችህን አሞናውያንን ተበቅሎልሃል።” |
እሷም በመቀጠል አባቷን እንዲህ አለችው፦ “እንዲህ ይደረግልኝ፦ ለሁለት ወር ያህል ብቻዬን ልሁን፤ ወደ ተራሮቹም ልሂድ፤ ከሴት ባልንጀሮቼም ጋር ሆኜ ስለ ድንግልናዬ ላልቅስ።” |
በዚህ ጊዜ “እሺ ሂጂ!” አላት፤ ለሁለት ወርም አሰናበታት፤ እሷም ስለ ድንግልናዋ ለማልቀስ ከባልንጀሮቿ ጋር ወደ ተራሮቹ ሄደች። |
ከሁለት ወር በኋላም ወደ አባቷ ተመለሰች፤ አባቷም እሷን በተመለከተ የተሳለውን ስእለት ፈጸመ። እሷም ከወንድ ጋር ግንኙነት ፈጽማ አታውቅም ነበር። ይህም በእስራኤል ውስጥ ልማድ ሆነ፦ |
የእስራኤል ወጣት ሴቶች የጊልያዳዊውን የዮፍታሔን ሴት ልጅ ለማመስገን በየዓመቱ ለአራት ቀን ያህል ይሄዱ ነበር። |
ኢያሱ ከሞተ በኋላ እስራኤላውያን “ከከነአናውያን ጋር ለመዋጋት ከመካከላችን ማን ቀድሞ ይውጣ?” በማለት ይሖዋን ጠየቁ። |
ይሖዋም “ይሁዳ ይውጣ። እኔም ምድሪቱን በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ” አለ። |
ከዚያም ይሁዳ ወንድሙን ስምዖንን “ከከነአናውያን ጋር ለመዋጋት ወደተመደበልኝ ርስት አብረኸኝ ውጣ። እኔም ደግሞ በዕጣ ወደደረሰህ ርስት አብሬህ እሄዳለሁ” አለው። ስለዚህ ስምዖን አብሮት ሄደ። |
ይሁዳም በወጣ ጊዜ ይሖዋ ከነአናውያንንና ፈሪዛውያንን በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ በመሆኑም ቤዜቅ ላይ 10,000 ሰዎችን ድል አደረጉ። |
አዶኒቤዜቅን ቤዜቅ ላይ ባገኙት ጊዜ በዚያ ከእሱ ጋር ተዋጉ፤ ከነአናውያንንና ፈሪዛውያንንም ድል አደረጉ። |
አዶኒቤዜቅም በሸሸ ጊዜ አሳደው ያዙት፤ ከዚያም የእጆቹንና የእግሮቹን አውራ ጣቶች ቆረጡ። |
አዶኒቤዜቅም እንዲህ አለ፦ “የእጃቸውና የእግራቸው አውራ ጣቶች የተቆረጡባቸው ከገበታዬ ሥር ሆነው ፍርፋሪ የሚለቃቅሙ 70 ነገሥታት ነበሩ። አምላክም ልክ እኔ እንዳደረግኩት አደረገብኝ።” ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፤ እሱም በዚያ ሞተ። |
በተጨማሪም የይሁዳ ሰዎች ኢየሩሳሌምን ወግተው በቁጥጥር ሥር አዋሏት፤ ከተማዋንም በሰይፍ መትተው በእሳት አቃጠሏት። |
ከዚያም የይሁዳ ሰዎች በተራራማው አካባቢ፣ በኔጌብና በሸፌላ ከሚኖሩት ከነአናውያን ጋር ለመዋጋት ወረዱ። |
በመሆኑም ይሁዳ በኬብሮን ይኖሩ በነበሩት ከነአናውያን ላይ ዘመተ (ኬብሮን ቀደም ሲል ቂርያትአርባ ተብላ ትጠራ ነበር)፤ እነሱም ሸሻይን፣ አሂማንን እና ታልማይን መቱ። |
ከዚያም ተነስተው በደቢር ነዋሪዎች ላይ ዘመቱ። (ደቢር ቀደም ሲል ቂርያትሰፈር ትባል ነበር።) |
ካሌብም “ቂርያትሰፈርን መትቶ በቁጥጥር ሥር ላደረጋት ሰው ሴት ልጄን አክሳን እድርለታለሁ” አለ። |
የካሌብ ታናሽ ወንድም የሆነው የቀናዝ ልጅ ኦትኒኤልም ከተማዋን በቁጥጥር ሥር አደረጋት። ስለሆነም ካሌብ ሴት ልጁን አክሳን ዳረለት። |
እሷም ወደ ባሏ ቤት እየሄደች ሳለ ባሏን ከአባቷ መሬት እንዲጠይቅ ወተወተችው። ከዚያም ከአህያዋ ላይ ወረደች። በዚህ ጊዜ ካሌብ “ምን ፈለግሽ?” ሲል ጠየቃት። |
እሷም “የሰጠኸኝ በስተ ደቡብ ያለ ቁራሽ መሬት ስለሆነ እባክህ ባርከኝ፤ ጉሎትማይምንም ስጠኝ” አለችው። በመሆኑም ካሌብ ላይኛውን ጉሎት እና ታችኛውን ጉሎት ሰጣት። |
የቄናዊው የሙሴ አማት ዘሮች ከይሁዳ ሰዎች ጋር በመሆን ከዘንባባ ዛፎች ከተማ ወጥተው ከአራድ በስተ ደቡብ ወደሚገኘው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ አቀኑ። እነሱም ወደዚያ ሄደው ከሕዝቡ ጋር መኖር ጀመሩ። |
ይሁዳም ከወንድሙ ከስምዖን ጋር በመዝመት በጸፋት በሚኖሩት ከነአናውያን ላይ ጥቃት ሰነዘሩ፤ ከተማዋንም ሙሉ በሙሉ ደመሰሱ። በመሆኑም ከተማዋን ሆርማ ብለው ሰየሟት። |
ከዚያም ይሁዳ ጋዛንና ግዛቶቿን፣ አስቀሎንንና ግዛቶቿን እንዲሁም ኤቅሮንንና ግዛቶቿን ተቆጣጠረ። |
ይሖዋ ከይሁዳ ጋር ስለነበር ይሁዳ ተራራማውን አካባቢ ወረሰ፤ በሜዳው ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ግን ማባረር አልቻሉም፤ ምክንያቱም እነሱ የብረት ማጭድ የተገጠመላቸው የጦር ሠረገሎች ነበሯቸው። |
ሙሴ ቃል በገባው መሠረት ኬብሮንን ለካሌብ ሰጡት፤ እሱም ሦስቱን የኤናቅ ልጆች ከዚያ አባረራቸው። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.