text stringlengths 4 267 |
|---|
ዳዊትም አማሌቃውያን የወሰዱትን ሁሉ አስጣለ፤ ሁለቱን ሚስቶቹንም አስመለሰ። |
ከትንሽ እስከ ትልቅ ምንም የጎደለ ነገር አልነበረም። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ሆነ ዘርፈው የወሰዱባቸውን ንብረት ሁሉ አስመለሱ፤ ዳዊት የወሰዱትን ሁሉ አስመለሰ። |
በመሆኑም ዳዊት መንጎቹንና ከብቶቹን በሙሉ ወሰደ፤ እነሱም ከራሳቸው ከብቶች ፊት ፊት ነዷቸው። እነሱም “ይህ የዳዊት ምርኮ ነው” አሉ። |
ከዚያም ዳዊት በጣም ከመድከማቸው የተነሳ አብረውት ሊሄዱ ወዳልቻሉትና በበሶር ሸለቆ ቀርተው ወደነበሩት 200 ሰዎች መጣ፤ እነሱም ዳዊትንና አብረውት የነበሩትን ሰዎች ለመቀበል ወጡ። ዳዊትም ወደ ሰዎቹ በቀረበ ጊዜ ስለ ደህንነታቸው ጠየቃቸው። |
ሆኖም ከዳዊት ጋር አብረው ከሄዱት መካከል ክፉ የሆኑትና የማይረቡት ሰዎች “እነዚህ ሰዎች አብረውን ስላልሄዱ እያንዳንዳቸው ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ይዘው ይሂዱ እንጂ ካመጣነው ምርኮ ላይ ምንም ነገር አንሰጣቸውም” አሉ። |
ዳዊት ግን እንዲህ አለ፦ “ወንድሞቼ ይሖዋ በሰጠን ነገርማ እንዲህ ማድረግ የለባችሁም። የጠበቀንና የመጣብንን ወራሪ ቡድን በእጃችን አሳልፎ የሰጠን እሱ ነው። |
ታዲያ አሁን ይህን የምትሉትን ማን ይሰማችኋል? ወደ ውጊያ የዘመተው ሰው የሚያገኘው ድርሻና ጓዝ የጠበቀው ሰው የሚያገኘው ድርሻ እኩል ነው። ሁሉም ድርሻ ይኖረዋል።” |
ዳዊትም ከዚያ ቀን ጀምሮ እስከዚህ ዕለት ድረስ ይህን ለእስራኤል ሥርዓትና ደንብ አድርጎ አጸደቀው። |
ዳዊትም ወደ ጺቅላግ በተመለሰ ጊዜ “ከይሖዋ ጠላቶች ከተገኘው ምርኮ የተሰጠ ስጦታ ይኸውላችሁ” በማለት ወዳጆቹ ለሆኑት የይሁዳ ሽማግሌዎች ከምርኮው ላይ የተወሰነውን ላከ። |
ስጦታውንም በቤቴል፣ በኔጌብ ራሞት፣ በያቲር፣ |
በአሮዔር፣ በሲፍሞት፣ በኤሽተሞዓ፣ |
በራካል፣ በየራህምኤል ከተሞች፣ በቄናውያን ከተሞች፣ |
በሆርማ፣ በቦርአሻን፣ በአታክ፣ |
በኬብሮን እንዲሁም ዳዊትና ሰዎቹ በሚያዘወትሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለነበሩት ላከ። |
የቢንያም ሰው የሆነ ቂስ የተባለ አንድ እጅግ ባለጸጋ ሰው ነበር፤ እሱም የቢንያማዊው የአፊያ ልጅ፣ የቤኮራት ልጅ፣ የጸሮር ልጅ፣ የአቢዔል ልጅ ነበር። |
ይህ ሰው ሳኦል የተባለ መልከ መልካም ወጣት ልጅ ነበረው፤ ከእስራኤላውያንም መካከል እንደ እሱ ያለ መልከ መልካም ወንድ አልነበረም፤ እሱም ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ ሲሆን ቁመቱ ከሌሎቹ ሁሉ ይበልጥ ነበር። |
የሳኦል አባት ቂስ አህዮቹ በጠፉበት ጊዜ ልጁን ሳኦልን “እባክህ ከአገልጋዮቹ መካከል አንዱን ይዘህ ሂድና አህዮቹን ፈልጋቸው” አለው። |
እነሱም የኤፍሬምን ተራራማ አካባቢና የሻሊሻን ምድር አቋርጠው ሄዱ፤ ሆኖም አህዮቹን አላገኟቸውም። ከዚያም የሻአሊምን ምድር አቋርጠው ተጓዙ፤ አህዮቹ ግን በዚያ አልነበሩም። እነሱም መላውን የቢንያማውያንን ምድር አቋርጠው ሄዱ፤ ይሁንና አህዮቹን አላገኟቸውም። |
እነሱም ወደ ጹፍ ምድር መጡ፤ ሳኦልም አብሮት የነበረውን አገልጋዩን “አባቴ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ ስለ እኛ መጨነቅ እንዳይጀምር፣ ና እንመለስ” አለው። |
አገልጋዩ ግን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፣ በዚህ ከተማ የሚኖር አንድ የተከበረ የአምላክ ሰው አለ። የሚናገረው ነገር በሙሉ መሬት ጠብ አይልም። ስለዚህ ወደዚያ እንሂድ። ምናልባት በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን ሊነግረን ይችላል።” |
በዚህ ጊዜ ሳኦል አገልጋዩን እንዲህ አለው፦ “መሄዱንስ እንሂድ፤ ግን ለሰውየው ምን ይዘንለት እንሄዳለን? በከረጢታችን ውስጥ የያዝነው ዳቦ እንደሆነ አልቋል፤ ለእውነተኛው አምላክ ሰው ስጦታ አድርገን የምንሰጠው ምንም ነገር የለንም። ታዲያ ምን ብናደርግ ይሻላል?” |
አገልጋዩም መልሶ ሳኦልን “እንግዲህ ሩብ ሰቅል ብር በእጄ አለ። ይህን ለእውነተኛው አምላክ ሰው እሰጠዋለሁ፤ እሱም በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለብን ይነግረናል” አለው። |
(ቀደም ባሉት ጊዜያት በእስራኤል ውስጥ አንድ ሰው አምላክን ለመፈለግ ሲሄድ “ኑ፣ ወደ ባለ ራእዩ እንሂድ” ይል ነበር። ምክንያቱም በዛሬው ጊዜ ነቢይ የሚባለው ቀደም ባሉት ጊዜያት ባለ ራእይ ይባል ነበር።) |
ከዚያም ሳኦል አገልጋዩን “የተናገርከው ነገር መልካም ነው። በል ና፣ እንሂድ” አለው። በመሆኑም የእውነተኛው አምላክ ሰው ወደሚገኝበት ከተማ ሄዱ። |
እነሱም ወደ ከተማዋ የሚወስደውን አቀበት እየወጡ ሳለ ውኃ ለመቅዳት የወጡ ልጃገረዶችን አገኙ። በመሆኑም “ባለ ራእዩ እዚህ ነው ያለው?” አሏቸው። |
እነሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦ “አዎ እዚህ ነው። እነሆ፣ ከፊታችሁ ነው ያለው! ፈጠን ብላችሁ ሂዱ፣ በዛሬው ዕለት ሕዝቡ ከፍ ባለው ቦታ ላይ መሥዋዕት ስለሚያቀርብ ወደ ከተማዋ መጥቷል። |
ልክ ወደ ከተማዋ እንደገባችሁ ለመብላት ወደ ኮረብታው ከመውጣቱ በፊት ታገኙታላችሁ። መሥዋዕቱን የሚባርከው እሱ ስለሆነ ሕዝቡ እሱ ካልመጣ መብላት አይጀምርም። ከዚያ በኋላ የተጋበዙት ይበላሉ። በሉ አሁኑኑ ውጡ፤ ታገኙታላችሁ።” |
ስለዚህ ወደ ከተማዋ ወጡ። ከተማዋ መሃል ሲደርሱም ሳሙኤል ከእነሱ ጋር ተገናኝቶ ወደ ኮረብታው ለመውጣት ወደ እነሱ እየመጣ ነበር። |
ይሖዋ፣ ሳኦል ከመምጣቱ ከአንድ ቀን በፊት ለሳሙኤል እንዲህ ብሎት ነበር፦ |
“ነገ በዚህ ጊዜ ገደማ ከቢንያም ምድር የመጣ አንድ ሰው ወደ አንተ እልካለሁ። አንተም በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ አድርገህ ቀባው፤ እሱም ሕዝቤን ከፍልስጤማውያን እጅ ያድናቸዋል። ምክንያቱም የሕዝቤን መከራ አይቻለሁ፤ ጩኸታቸውም ወደ እኔ ደርሷል።” |
ሳሙኤል፣ ሳኦልን ባየው ጊዜ ይሖዋ “‘ሕዝቤን የሚገዛው እሱ ነው’ ብዬ የነገርኩህ ሰው ይህ ነው” አለው። |
ከዚያም ሳኦል በሩ መሃል ላይ ወደነበረው ወደ ሳሙኤል ቀርቦ “እባክህ፣ የባለ ራእዩ ቤት የት እንደሆነ ትነግረኛለህ?” አለው። |
ሳሙኤልም ለሳኦል እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ባለ ራእዩ እኔ ነኝ። ከእኔ ቀድመህ ወደ ኮረብታው ውጣ፤ ዛሬ አብራችሁኝ ትበላላችሁ። በማለዳም አሰናብትሃለሁ፤ ማወቅ የምትፈልገውንም ነገር ሁሉ እነግርሃለሁ። |
ከሦስት ቀን በፊት ስለጠፉብህ አህዮች አትጨነቅ፤ ምክንያቱም ተገኝተዋል። በእስራኤል ውስጥ ያለው ምርጥ ነገር ሁሉ የማን ነው? የአንተና የመላው የአባትህ ቤት አይደለም?” |
በዚህ ጊዜ ሳኦል እንዲህ አለው፦ “እኔ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ አነስተኛ ከሆነው ከቢንያም ነገድ የተገኘሁ ቢንያማዊ አይደለሁም? ቤተሰቤስ ቢሆን ከቢንያም ነገድ ቤተሰቦች መካከል እዚህ ግባ የሚባል ሆኖ ነው? ታዲያ እንዲህ የምትለኝ ለምንድን ነው?” |
ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልንና አገልጋዩን ወደ መመገቢያ አዳራሹ ይዟቸው ሄደ፤ እነሱንም በተጋበዙት ሰዎች ፊት በክብር ቦታ አስቀመጣቸው፤ ተጋባዦቹም 30 ገደማ ነበሩ። |
ሳሙኤልም ምግብ የሚያበስለውን ሰው “‘ለይተህ አስቀምጠው’ ብዬ የሰጠሁህን ድርሻ አምጣው” አለው። |
በዚህ ጊዜ ምግብ የሚያበስለው ሰው ጭኑንና ላዩ ላይ የነበረውን አንስቶ ሳኦል ፊት አስቀመጠው። ሳሙኤልም እንዲህ አለው፦ “ተለይቶ ተቀምጦ የነበረው ፊትህ ቀርቦልሃል። ይህ ለዚህ ጊዜ ብለው ለይተው ያስቀመጡልህ ስለሆነ ብላ። ምክንያቱም ‘እንግዶች ጋብዣለሁ’ ብዬ ነግሬያቸዋለሁ።” በመሆኑም ሳኦል በዚያ ቀን ከሳሙኤል ጋር በላ። |
ከዚያም ከኮረብታው ወደ ከተማው ወረዱ፤ ሳሙኤልም ከሳኦል ጋር በቤቱ ሰገነት ላይ ሲነጋገር ቆየ። |
እነሱም በማለዳ ተነሱ፤ ጎህ እንደቀደደም ሳሙኤል ሳኦልን ወደ ቤቱ ሰገነት ጠርቶ “በል ተዘጋጅና ላሰናብትህ” አለው። ስለዚህ ሳኦል ተዘጋጀ፤ ከዚያም እሱና ሳሙኤል ወደ ውጭ ወጡ። |
እነሱም በከተማዋ ዳርቻ ቁልቁል እየወረዱ ሳሉ ሳሙኤል ሳኦልን “አገልጋይህ ቀድሞን እንዲሄድ ንገረው” አለው፤ እሱም ቀድሞ ሄደ። ሳሙኤልም “አንተ ግን የአምላክን ቃል እንዳሰማህ እዚሁ ቁም” አለው። |
ሳኦል ፍልስጤማውያንን አሳዶ እንደተመለሰ “ዳዊት በኤንገዲ ምድረ በዳ ይገኛል” ብለው ነገሩት። |
ስለዚህ ሳኦል ከመላው እስራኤል የተመረጡ 3,000 ሰዎችን ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ የተራራ ፍየሎች ወደሚገኙበት ዓለታማ ገደላ ገደል ሄደ። |
ሳኦልም በመንገዱ ዳር ወዳለ ከድንጋይ የተሠራ የበጎች ጉረኖ ደረሰ፤ በዚያም አንድ ዋሻ ነበር፤ በመሆኑም ሳኦል ለመጸዳዳት ወደ ዋሻው ገባ፤ በዚህ ጊዜ ዳዊትና ሰዎቹ በዋሻው ውስጠኛ ክፍል ተቀምጠው ነበር። |
ከዚያም የዳዊት ሰዎች “ይሖዋ ‘ጠላትህን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ አንተም ደስ ያለህን ታደርግበታለህ’ ያለህ ቀን ይህ ነው” አሉት። ስለሆነም ዳዊት ተነሳ፤ የሳኦልንም ልብስ ጫፍ በቀስታ ቆርጦ ወሰደ። |
በኋላ ላይ ግን ዳዊት የሳኦልን ልብስ ጫፍ በመቁረጡ ልቡ ወቀሰው። |
አብረውት የነበሩትንም ሰዎች “ይሖዋ በቀባው በጌታዬ ላይ እጄን በማንሳት እንዲህ ያለውን ድርጊት መፈጸም በይሖዋ ዓይን ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው፤ ምክንያቱም እሱ ይሖዋ የቀባው ነው” አላቸው። |
ስለዚህ ዳዊት ይህን በማለት ሰዎቹን ከለከላቸው፤ በሳኦል ላይ ጉዳት እንዲያደርሱበትም አልፈቀደላቸውም። ሳኦልም ተነስቶ ከዋሻው ወጥቶ ሄደ። |
ከዚያም ዳዊት ከዋሻው በመውጣት “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” በማለት ሳኦልን ጠራው። ሳኦልም ወደኋላው ዞር ብሎ ሲመለከት ዳዊት በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ ሰገደ። |
ዳዊትም ሳኦልን እንዲህ አለው፦ “‘ዳዊት የአንተን ክፉ ማየት ይፈልጋል’ የሚሉትን ሰዎች ወሬ ለምን ትሰማለህ? |
በዛሬዋ ዕለት በዋሻው ውስጥ ይሖዋ አንተን እንዴት አድርጎ በእጄ ሰጥቶኝ እንደነበር በገዛ ዓይንህ አይተሃል። አንድ ሰው እንድገድልህ ገፋፍቶኝ የነበረ ቢሆንም እኔ ግን ለአንተ በማዘን ‘ይሖዋ የቀባው ስለሆነ በጌታዬ ላይ እጄን አላነሳም’ አልኩ። |
አሁንም አባቴ ሆይ፣ ተመልከት፣ በእጄ የያዝኩትን የልብስህን ቁራጭ እይ፤ የልብስህን ጫፍ በቆረጥኩ ጊዜ ልገድልህ እችል ነበር፤ ግን አልገደልኩህም። እንግዲህ አንተን ለመጉዳትም ሆነ በአንተ ላይ ለማመፅ ፈጽሞ እንዳላሰብኩ ከዚህ ማየትና መረዳት ትችላለህ፤ ምንም እንኳ ሕይወቴን ለማጥፋት እያሳደድከኝ ቢሆንም እኔ በአንተ ላይ ምንም የፈጸምኩት በደል የለም። |
ይሖዋ በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ፤ ይሖዋ አንተን ይበቀልልኝ እንጂ እኔ በምንም ዓይነት እጄን በአንተ ላይ አላነሳም። |
‘ከክፉ ሰው ክፉ ነገር ይወጣል’ የሚል የጥንት አባባል አለ፤ እኔ ግን በምንም ዓይነት እጄን በአንተ ላይ አላነሳም። |
ለመሆኑ የእስራኤል ንጉሥ የወጣው ማንን ፍለጋ ነው? የምታሳድደውስ ማንን ነው? አንድን የሞተ ውሻ? ወይስ አንዲትን ቁንጫ? |
አሁንም ይሖዋ ዳኛ ሆኖ በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ፤ ጉዳዩንም ተመልክቶ ስለ እኔ ይሟገትልኝ፤ እሱ ይፍረድልኝ፣ ከእጅህም ያድነኝ።” |
ዳዊት ይህን ተናግሮ ሲጨርስ ሳኦል “ልጄ ዳዊት፣ ይህ የአንተ ድምፅ ነው?” አለው። ከዚያም ሳኦል ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ። |
ዳዊትንም እንዲህ አለው፦ “አንተ መልካም ስታደርግልኝ እኔ ግን ክፉ መለስኩልህ፤ ስለሆነም አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ። |
አዎ፣ ይሖዋ እኔን በእጅህ አሳልፎ ቢሰጥህም ሳትገድለኝ በመቅረት ለእኔ ያደረግከውን መልካም ነገር ይኸው ዛሬ ነገርከኝ። |
ለመሆኑ ጠላቱን አግኝቶ ጉዳት ሳያደርስበት የሚለቀው ሰው ይኖራል? ዛሬ አንተ ለእኔ መልካም ስላደረግክልኝ ይሖዋም ለአንተ መልካም በማድረግ ወሮታህን ይመልስልህ። |
ደግሞም አንተ በእርግጥ ንጉሥ ሆነህ እንደምትገዛ አውቃለሁ፤ የእስራኤልም መንግሥት በእጅህ ይጸናል። |
በመሆኑም አሁን ከእኔ በኋላ የሚመጡትን ዘሮቼን እንደማታጠፋና ስሜንም ከአባቴ ቤት እንደማትደመስስ በይሖዋ ማልልኝ።” |
ስለዚህ ዳዊት ለሳኦል ማለለት፤ ከዚያም ሳኦል ወደ ቤቱ ሄደ። ዳዊትና ሰዎቹ ግን ወደ ምሽጉ ወጡ። |
ሆኖም ዳዊት በልቡ እንዲህ አለ፦ “አንድ ቀን በሳኦል እጅ መጥፋቴ አይቀርም። የሚያዋጣኝ ወደ ፍልስጤማውያን ምድር መሸሽ ነው፤ ሳኦልም ተስፋ ቆርጦ በእስራኤል ግዛት ሁሉ እኔን መፈለጉን ያቆማል፤ እኔም ከእጁ አመልጣለሁ።” |
በመሆኑም ዳዊት አብረውት ከነበሩት 600 ሰዎች ጋር ተነስቶ የጌት ንጉሥ ወደሆነው ወደ ማኦክ ልጅ ወደ አንኩስ ተሻገረ። |
ዳዊትና ሰዎቹም እያንዳንዳቸው ከነቤተሰባቸው ጌት ውስጥ አንኩስ ዘንድ ተቀመጡ። ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ማለትም ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪኖዓም እና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢጋኤል ጋር ነበር። |
ሳኦልም ዳዊት ወደ ጌት መሸሹ ሲነገረው እሱን መፈለጉን ተወ። |
ከዚያም ዳዊት አንኩስን “በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ በገጠር ካሉ ከተሞች በአንዱ እንድኖር ቦታ እንዲሰጡኝ አድርግ። አገልጋይህ ለምን በንጉሥ ከተማ ከአንተ ጋር ይኖራል?” አለው። |
በመሆኑም አንኩስ በዚያ ቀን ጺቅላግን ሰጠው። ጺቅላግ እስካሁንም ድረስ የይሁዳ ነገሥታት ይዞታ የሆነችው በዚህ ምክንያት ነው። |
ዳዊት በፍልስጤማውያን ገጠራማ አካባቢ የኖረበት ጊዜ አንድ ዓመት ከአራት ወር ነበር። |
ዳዊትም ከሰዎቹ ጋር በመሆን ገሹራውያንን፣ ጊዝራውያንን እና አማሌቃውያንን ለመውረር ይወጣ ነበር፤ ምክንያቱም እነዚህ ሕዝቦች ከቴላም አንስቶ እስከ ሹር እና እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ባለው አካባቢ ይኖሩ ነበር። |
ዳዊት በምድሪቱ ላይ ጥቃት በሚሰነዝርበት ጊዜ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አያስቀርም ነበር፤ ሆኖም መንጎችን፣ ከብቶችን፣ አህዮችን፣ ግመሎችንና ልብሶችን ወስዶ ወደ አንኩስ ይመለስ ነበር። |
አንኩስም “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” ይለው ነበር። ዳዊትም “በይሁዳ ደቡባዊ ክፍል ላይ ዘምተን ነበር” ወይም “በየራህምኤላውያን ምድር ደቡባዊ ክፍል ላይ ዘምተን ነበር” አሊያም “በቄናውያን ምድር ደቡባዊ ክፍል ላይ ዘምተን ነበር” በማለት ይመልስለት ነበር። |
ዳዊት “‘እሱ እንዲህ አደረገ’ በማለት ስለ እኛ ሊነግሯቸው ይችላሉ” ብሎ ስላሰበ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አስተርፎ ወደ ጌት አያመጣም ነበር። (ዳዊት በፍልስጤም ገጠራማ አካባቢ በኖረበት ዘመን ሁሉ እንዲህ የማድረግ ልማድ ነበረው።) |
ስለዚህ አንኩስ ‘በእርግጥም ይህ ሰው በገዛ ሕዝቦቹ በእስራኤላውያን ዘንድ እንደ ጥንብ ተቆጥሯል፤ ስለሆነም ዕድሜ ልኩን አገልጋዬ ይሆናል’ ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው። |
ከዚያም ሐና እንዲህ ስትል ጸለየች፦ “ልቤ በይሖዋ ሐሴት አደረገ፤ቀንዴም በይሖዋ ከፍ ከፍ አለ። አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፣በማዳን ሥራዎችህ ደስ ብሎኛልና። |
እንደ ይሖዋ ያለ ቅዱስ ማንም የለም፣ያለአንተ ማንም የለም፤እንደ አምላካችን ያለ ዓለት የለም። |
በትዕቢት መናገራችሁን ተዉ፤የእብሪት ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፣ይሖዋ ሁሉን የሚያውቅ አምላክ ነውና፣ተግባርን ሁሉ በትክክል የሚመዝን እሱ ነው። |
የኃያላን ቀስቶች ተሰባብረዋል፣የተንገዳገዱት ግን ብርታት አግኝተዋል። |
ጠግበው የነበሩት ለምግብ ሲሉ ተቀጥረው ለመሥራት ተገደዱ፤የተራቡት ግን ከእንግዲህ አይራቡም። መሃን የነበረችው ሴት ሰባት ልጆች ወለደች፤ብዙ ወንዶች ልጆች የነበሯት ግን ብቻዋን ቀረች። |
ይሖዋ ይገድላል፤ ሕይወትንም ያድናል፤ወደ መቃብር ያወርዳል፤ ከዚያም ያወጣል። |
ይሖዋ ያደኸያል፤ እንዲሁም ያበለጽጋል፤እሱ ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍም ያደርጋል። |
ችግረኛውን ከአቧራ ላይ ያነሳል፤ድሃውንም ከአመድ ቁልል ላይ ያነሳል፤ከመኳንንትም ጋር ያስቀምጣቸዋል፤የክብር ወንበርም ይሰጣቸዋል። የምድር ምሰሶዎች የይሖዋ ናቸው፤ፍሬያማ የሆነችውን ምድር በእነሱ ላይ አስቀምጧል። |
እሱ የታማኞቹን እርምጃ ይጠብቃል፤ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ጸጥ እንዲሉ ይደረጋሉ፤ሰው የበላይ የሚሆነው በኃይሉ አይደለምና። |
ይሖዋ ከእሱ ጋር የሚዋጉትን ያደቃቸዋል፤እሱም ከሰማይ ነጎድጓድ ይለቅባቸዋል። ይሖዋ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይፈርዳል፤ለንጉሡ ኃይል ይሰጣል፤የእሱ ቅቡዕ የሆነውንም ቀንዱን ከፍ ከፍ ያደርጋል።” |
ከዚያም ሕልቃና በራማ ወደሚገኘው ቤቱ ሄደ፤ ልጁ ግን በካህኑ በኤሊ ፊት የይሖዋ አገልጋይ ሆነ። |
የኤሊ ወንዶች ልጆች ምግባረ ብልሹ ነበሩ፤ ለይሖዋ አክብሮት አልነበራቸውም። |
ከሕዝቡ ላይ የካህናቱን ድርሻ በሚቀበሉበት ጊዜ እንዲህ ያደርጉ ነበር፦ ማንኛውም ሰው መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ሥጋው እየተቀቀለ ሳለ የካህኑ አገልጋይ ሦስት ጣት ያለው ሹካ ይዞ ይመጣና |
ሹካውን ወደ ሰታቴው ወይም ወደ ምንቸቱ ወይም ወደ አፍላሉ ወይም ወደ ባለ አንድ ጆሮው ድስት ይከተዋል። መንሹ ይዞ የሚወጣውንም ካህኑ ለራሱ ይወስድ ነበር። ወደ ሴሎ በሚመጡት እስራኤላውያን ሁሉ ላይ እንዲሁ ያደርጉ ነበር። |
ሌላው ቀርቶ መሥዋዕቱን የሚያቀርበው ሰው ስቡን ከማቃጠሉ በፊት የካህኑ አገልጋይ መጥቶ “ለካህኑ የሚጠበስ ሥጋ ስጠው። ጥሬ ሥጋ ብቻ እንጂ የተቀቀለ ሥጋ ከአንተ አይቀበልም” ይለው ነበር። |
ሰውየውም “በመጀመሪያ ስቡን ያቃጥሉ፤ ከዚያ በኋላ የፈለግከውን ውሰድ” ይለው ነበር። እሱ ግን “አይሆንም፤ አሁኑኑ ስጠኝ፤ ካልሆነ ግን ነጥቄ እወስዳለሁ!” ይለዋል። |
ሰዎቹ የይሖዋን መባ ያቃልሉ ስለነበር የአገልጋዮቹ ኃጢአት በይሖዋ ፊት እጅግ ታላቅ ሆነ። |
በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ገና አንድ ፍሬ ልጅ የነበረ ቢሆንም ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ በይሖዋ ፊት ያገለግል ነበር። |
እናቱም ዓመታዊውን መሥዋዕት ለማቅረብ ከባሏ ጋር ስትወጣ እጅጌ የሌለው ትንሽ ቀሚስ እየሠራች በየዓመቱ ታመጣለት ነበር። |
ኤሊም ሕልቃናንና ሚስቱን እንዲህ ሲል ባረካቸው፦ “ለይሖዋ በተሰጠው ልጅ ምትክ ይሖዋ ከዚህች ሚስትህ ልጅ ይስጥህ” አለው። እነሱም ወደ ቤታቸው ተመለሱ። |
ይሖዋም ሐናን አሰባት፤ እሷም ፀነሰች፤ ሌሎች ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ልጆችም ወለደች። ብላቴናው ሳሙኤልም በይሖዋ ፊት እያደገ ሄደ። |
በዚህ ጊዜ ኤሊ በጣም አርጅቶ ነበር፤ ሆኖም ወንዶች ልጆቹ በሁሉም እስራኤላውያን ላይ ምን እንደሚያደርጉ እንዲሁም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር እንደሚተኙ አንድም ሳይቀር ሰምቶ ነበር። |
እሱም እንዲህ ይላቸው ነበር፦ “እንዲህ ያለ ነገር ለምን ታደርጋላችሁ? ሰዎች ሁሉ ስለ እናንተ መጥፎ ነገር ሲናገሩ እሰማለሁ። |
ልጆቼ፣ ትክክል አይደላችሁም፤ በይሖዋ ሕዝቦች መካከል ሲናፈስ የምሰማው ወሬ ጥሩ አይደለም። |
አንድ ሰው ሌላውን ቢበድል ሌላ ሰው ይሖዋን ይለምንለት ይሆናል፤ ሆኖም አንድ ሰው ይሖዋን ቢበድል ማን ሊጸልይለት ይችላል?” እነሱ ግን የአባታቸውን ቃል ለመስማት ፈቃደኞች አልሆኑም፤ ምክንያቱም ይሖዋ ሊገድላቸው ወስኖ ነበር። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.