text
stringlengths
4
267
በዚህ ጊዜ ሳሙኤል እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ የእስራኤልን ንጉሣዊ አገዛዝ በዛሬው ዕለት ከአንተ ቀዶታል፤ ከአንተ ለሚሻል ባልንጀራህም አሳልፎ ይሰጠዋል።
ደግሞም የእስራኤል ክቡር አይዋሽም ወይም ሐሳቡን አይቀይርም፤ ምክንያቱም እሱ ሐሳቡን ይቀይር ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም።”
እሱም “ኃጢአት ሠርቻለሁ። ሆኖም እባክህ በሕዝቤ ሽማግሌዎችና በእስራኤል ፊት አክብረኝ። አብረኸኝ ተመለስ፤ እኔም ለአምላክህ ለይሖዋ እሰግዳለሁ” አለው።
በመሆኑም ሳሙኤል ሳኦልን ተከትሎት ተመለሰ፤ ሳኦልም በይሖዋ ፊት ሰገደ።
ሳሙኤልም “የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ” አለ። አጋግም “መቼም የሞትን መራራ ጽዋ የምቀምስበት ጊዜ አልፏል” ብሎ ስላሰበ ፈራ ተባ እያለ ወደ እሱ ሄደ።
ሆኖም ሳሙኤል “በአንተ ሰይፍ የተነሳ ልጆቻቸውን ያጡ ሴቶች እንዳዘኑ ሁሉ የአንተም እናት ከሴቶች ሁሉ ይበልጥ ታዝናለች” አለው። ከዚያም ሳሙኤል በጊልጋል በይሖዋ ፊት አጋግን ቆራረጠው።
ሳሙኤል ወደ ራማ ሄደ፤ ሳኦልም በጊብዓ ወደሚገኘው ቤቱ አቀና።
ሳሙኤልም ለሳኦል እጅግ አዘነ፤ እስከ ዕለተ ሞቱም ድረስ ሳኦልን ዳግመኛ አላየውም። ይሖዋም ሳኦልን በእስራኤል ላይ ንጉሥ በማድረጉ ተጸጸተ።
የሳሙኤልም ቃል ለእስራኤላውያን ሁሉ ደረሰ። ከዚያም እስራኤላውያን ከፍልስጤማውያን ጋር ለመዋጋት ወጡ፤ ኤቤንዔዘርም አጠገብ ሰፈሩ፤ ፍልስጤማውያን ደግሞ በአፌቅ ሰፍረው ነበር።
ፍልስጤማውያን እስራኤላውያንን ለመግጠም ተሰልፈው ወጡ፤ ውጊያውም እየተፋፋመ ሄደ፤ እስራኤላውያንም ውጊያው በተደረገበት ግንባር 4,000 ሰው በገደሉባቸው በፍልስጤማውያን ድል ተመቱ።
ሠራዊቱ ወደ ሰፈሩ በተመለሰ ጊዜ የእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህ አሉ፦ “ይሖዋ በዛሬው ዕለት በፍልስጤማውያን ፊት ድል እንድንመታ የፈቀደው ለምንድን ነው? አብሮን እንዲሆንና ከጠላቶቻችን እጅ እንዲያድነን የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ከሴሎ ይዘነው እንሂድ።”
በመሆኑም ሕዝቡ ሰዎችን ወደ ሴሎ ላከ፤ እነሱም ከኪሩቤል በላይ ዙፋን ላይ የተቀመጠውን የሠራዊት ጌታ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ከዚያ ተሸክመው መጡ። ሁለቱ የኤሊ ልጆች ሆፍኒ እና ፊንሃስም ከእውነተኛው አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት ጋር አብረው ነበሩ።
የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ሰፈሩ ሲገባ እስራኤላውያን ሁሉ ምድር እስክትናወጥ ድረስ ጮኹ።
ፍልስጤማውያንም ጩኸቱን ሲሰሙ “በዕብራውያን ሰፈር የሚሰማው ይህ ሁሉ ጩኸት ምንድን ነው?” አሉ። በመጨረሻም የይሖዋ ታቦት ወደ ሰፈሩ እንደገባ አወቁ።
ፍልስጤማውያንም “አምላክ ወደ ሰፈሩ ገብቷል!” በማለት በፍርሃት ተዋጡ። በመሆኑም እንዲህ አሉ፦ “ወየው ጉዳችን! እንዲህ ዓይነት ነገር ሆኖ አያውቅም!
ወየው ጉዳችን! ከዚህ ባለ ግርማ አምላክ እጅ ማን ያድነናል? ግብፃውያንን በምድረ በዳ በተለያዩ መቅሰፍቶች የመታቸው አምላክ እኮ ይህ ነው።
እናንተ ፍልስጤማውያን አይዟችሁ፣ ወንድነታችሁን አሳዩ፤ አለዚያ ዕብራውያን የእናንተ አገልጋዮች እንደነበሩ ሁሉ እናንተም የእነሱ አገልጋዮች ትሆናላችሁ። ወንድነታችሁን አሳዩ፤ ተዋጉ!”
በመሆኑም ፍልስጤማውያን ተዋጉ፤ እስራኤላውያንም ድል ተመቱ፤ እያንዳንዱም ሰው ወደየድንኳኑ ሸሸ። በጣም ብዙ ሕዝብ አለቀ፤ ከእስራኤላውያንም ወገን 30,000 እግረኛ ወታደር ሞተ።
የአምላክም ታቦት ተማረከ፤ ሁለቱ የኤሊ ልጆች ሆፍኒ እና ፊንሃስም ሞቱ።
አንድ ቢንያማዊ ልብሱን ቀዶና በራሱ ላይ አቧራ ነስንሶ ከጦር ግንባሩ እየሮጠ በዚያው ቀን ሴሎ ደረሰ።
ሰውየውም ሲደርስ ኤሊ በእውነተኛው አምላክ ታቦት የተነሳ ልቡ ስለተረበሸ መንገድ ዳር ወንበር ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር። ሰውየውም ወሬውን ለመንገር ወደ ከተማዋ ገባ፤ መላ ከተማዋም በጩኸት ትናወጥ ጀመር።
ኤሊም ጩኸቱን ሲሰማ “ይህ ሁሉ ጩኸት ምንድን ነው?” በማለት ጠየቀ። ሰውየውም በፍጥነት ወደ እሱ ሄዶ ወሬውን ነገረው።
(በዚህ ወቅት ኤሊ ዕድሜው 98 ዓመት ነበር፤ ኤሊ ማየት ተስኖት የነበረ ቢሆንም ዓይኖቹ ፊት ለፊት ትኩር ብለው ይመለከቱ ነበር።)
ከዚያም ሰውየው ኤሊን “ከጦር ግንባሩ የመጣሁት ሰው እኔ ነኝ! ከጦር ግንባሩ ሸሽቼ የመጣሁትም ዛሬ ነው” አለው። በዚህ ጊዜ ኤሊ “ልጄ፣ ለመሆኑ የተከሰተው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።
ወሬውን ያመጣውም ሰው እንዲህ አለው፦ “እስራኤላውያን ከፍልስጤማውያን ፊት ሸሽተዋል፤ ሕዝቡም ከፍተኛ ሽንፈት ደርሶበታል፤ ሁለቱ ልጆችህ ሆፍኒ እና ፊንሃስም ሞተዋል፤ የእውነተኛው አምላክ ታቦትም ተማርኳል።”
ሰውየው ስለ እውነተኛው አምላክ ታቦት በተናገረበት ቅጽበት ኤሊ በሩ አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ወደኋላው ወደቀ፤ በዕድሜ የገፋ ከመሆኑም ሌላ ሰውነቱ ከባድ ስለነበር አንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እሱም ለ40 ዓመት በእስራኤል ላይ ፈራጅ ሆኖ አገልግሏል።
የኤሊ ምራት የፊንሃስ ሚስት ነፍሰ ጡር ነበረች፤ የምትወልድበትም ጊዜ ተቃርቦ ነበር። እሷም የእውነተኛው አምላክ ታቦት እንደተማረከ እንዲሁም አማቷና ባሏ እንደሞቱ ስትሰማ ሆዷን ይዛ ጎንበስ አለች፤ ድንገትም ምጥ ያዛትና ወለደች።
እሷም ልትሞት በምታጣጥርበት ጊዜ አጠገቧ ቆመው የነበሩት ሴቶች “አይዞሽ፣ ወንድ ልጅ ወልደሻል” አሏት። እሷ ግን መልስ አልሰጠችም፤ ልብም አላለችውም።
ሆኖም የእውነተኛው አምላክ ታቦት በመማረኩ እንዲሁም በአማቷና በባሏ ላይ በደረሰው ነገር የተነሳ “ክብር ከእስራኤል በግዞት ተወሰደ” ስትል ለልጁ ኢካቦድ የሚል ስም አወጣችለት።
“የእውነተኛው አምላክ ታቦት ስለተማረከ ክብር ከእስራኤል በግዞት ተወሰደ” አለች።
ከዚያም ዳዊት በራማ ከምትገኘው ከናዮት ሸሸ። ሆኖም ወደ ዮናታን መጥቶ “ምን አደረግኩ? የፈጸምኩትስ በደል ምንድን ነው? አባትህ ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልገው በእሱ ላይ ምን ኃጢአት ሠርቼ ነው?” አለው።
ዮናታንም እንዲህ አለው፦ “ይሄማ የማይታሰብ ነው! ፈጽሞ አትሞትም! አባቴ እንደሆነ ትልቅም ሆነ ትንሽ፣ ለእኔ ሳይነግረኝ ምንም ነገር አያደርግም። ታዲያ አባቴ ይህን ነገር ከእኔ የሚደብቅበት ምን ምክንያት አለው? እንዲህማ አይሆንም።”
ዳዊት ግን እንደገና ማለለት፤ እንዲህም አለው፦ “አባትህ በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን በሚገባ ስለሚያውቅ ‘ዮናታን ሊያዝን ስለሚችል ይህን ነገር ማወቅ የለበትም’ ብሎ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ሕያው በሆነው በይሖዋና በሕያውነትህ እምላለሁ፣ በእኔና በሞት መካከል ያለው አንድ እርምጃ ብቻ ነው!”
ከዚያም ዮናታን ዳዊትን “የምትለውን ማንኛውንም ነገር አደርግልሃለሁ” አለው።
በዚህ ጊዜ ዳዊት ዮናታንን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፣ ነገ አዲስ ጨረቃ የምትወጣበት ቀን ነው፤ እኔም ከንጉሡ ጋር ለመመገብ በማዕድ መቀመጥ ይጠበቅብኛል፤ አንተ ካሰናበትከኝ ግን እስከ ሦስተኛው ቀን ምሽት ድረስ ወደ ሜዳ ሄጄ እደበቃለሁ።
ምናልባት አባትህ አለመኖሬን አስተውሎ ከጠየቀ ‘ዳዊት በከተማው በቤተልሔም ለመላ ቤተሰቡ የሚቀርብ ዓመታዊ መሥዋዕት ስላለ ቶሎ ወደዚያ ይሄድ ዘንድ እንድፈቅድለት ለመነኝ’ በለው።
እሱም ‘ጥሩ ነው!’ ካለ አገልጋይህን የሚያሰጋው ነገር የለም ማለት ነው። ከተቆጣ ግን በእኔ ላይ ጉዳት ለማድረስ እንደቆረጠ እወቅ።
አገልጋይህ ከአንተ ጋር በይሖዋ ፊት ቃል ኪዳን እንዲገባ ያደረግከው አንተ ስለሆንክ ለአገልጋይህ ታማኝ ፍቅር አሳየው። በእኔ ላይ ጥፋት ከተገኘ ግን አንተው ራስህ ግደለኝ። ለምን ለአባትህ አሳልፈህ ትሰጠኛለህ?”
በዚህ ጊዜ ዮናታን “እንዲህ ብለህ ማሰብማ የለብህም! አባቴ በአንተ ላይ ጉዳት ለማድረስ መቁረጡን ባውቅ እንዴት ሳልነግርህ ዝም እላለሁ?” አለው።
ከዚያም ዳዊት ዮናታንን “ታዲያ አባትህ ክፉ ቃል ቢመልስልህ ማን ይነግረኛል?” አለው።
ዮናታንም ዳዊትን “ና፣ ወደ ሜዳ እንውጣ” አለው። በመሆኑም ተያይዘው ወደ ሜዳ ወጡ።
ከዚያም ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ነገ በዚህ ጊዜ ወይም ከነገ ወዲያ አባቴ ያለውን አመለካከት ባላጣራ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ምሥክር ይሁንብኝ። እሱ ለዳዊት ጥሩ አመለካከት ካለው ወደ አንተ ልኬ የማላሳውቅህ ይመስልሃል?
አባቴ በአንተ ላይ ጉዳት ለማድረስ አስቦ ቢሆንና እኔ ግን ይህን ሳላሳውቅህ ብቀር እንዲሁም በሰላም እንድትሄድ ባላደርግ ይሖዋ በዮናታን ላይ ይህን ያድርግበት፤ ከዚህ የከፋም ነገር ያምጣበት። ይሖዋ ከአባቴ ጋር እንደነበር ሁሉ ከአንተም ጋር ይሁን።
አንተስ ብትሆን በሕይወት ሳለሁም ሆነ ስሞት የይሖዋን ታማኝ ፍቅር አታሳየኝም?
ይሖዋ የዳዊትን ጠላቶች በሙሉ ከምድር ገጽ ጠራርጎ በሚያጠፋበት ጊዜም ለቤተሰቤ ታማኝ ፍቅርህን ከማሳየት ፈጽሞ ወደኋላ አትበል።”
ስለዚህ ዮናታን “ይሖዋ የዳዊትን ጠላቶች ይፋረዳቸዋል” በማለት ከዳዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን ገባ።
በመሆኑም ዮናታን ዳዊት ለእሱ ባለው ፍቅር እንደገና እንዲምልለት አደረገ፤ ምክንያቱም ዳዊትን እንደ ራሱ ይወደው ነበር።
ዮናታንም ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ነገ አዲስ ጨረቃ የምትወጣበት ቀን ነው፤ የምትቀመጥበት ቦታ ባዶ ስለሚሆን አለመኖርህ ይታወቃል።
በሦስተኛውም ቀን፣ አለመኖርህ ይበልጥ ግልጽ ይሆናል፤ አንተም ያን ቀን ተደብቀህበት ወደነበረው ቦታ ሂድ፤ እዚህ ድንጋይ አጠገብም ቆይ።
እኔም ዒላማ የምመታ አስመስዬ በድንጋዩ አጠገብ ሦስት ቀስቶችን አስፈነጥራለሁ።
አገልጋዩንም ‘ሂድ፣ ፍላጻዎቹን አምጣቸው’ ብዬ እልከዋለሁ። አገልጋዩን ‘ፍላጻዎቹ ከአንተ በዚህኛው በኩል ናቸው፤ አምጣቸው’ ካልኩት ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ ሁሉ ነገር ሰላም ስለሆነና ምንም የሚያሰጋህ ነገር ስለሌለ ተመልሰህ መምጣት ትችላለህ።
ሆኖም ልጁን ‘ፍላጻዎቹ ከአንተ ወዲያ ናቸው’ ካልኩት ይሖዋ አሰናብቶሃልና ሂድ።
እኔና አንተ የተጋባነውን ቃል በተመለከተም ይሖዋ በእኔና በአንተ መካከል ለዘላለም ምሥክር ይሁን።”
በመሆኑም ዳዊት ወደ ሜዳ ሄዶ ተደበቀ። አዲስ ጨረቃ ስትወጣም ንጉሡ ለመብላት በማዕድ ተቀመጠ።
ንጉሡ እንደተለመደው በግድግዳው በኩል ባለው መቀመጫው ላይ ተቀምጦ ነበር። ዮናታን ከፊት ለፊቱ፣ አበኔር ደግሞ ከሳኦል ጎን ተቀምጠው ነበር፤ የዳዊት ቦታ ግን ባዶ ነበር።
ሳኦል ‘መቼም ዳዊት እንዳይነጻ የሚያደርገው የሆነ ነገር ገጥሞት መሆን ይኖርበታል። አዎ፣ ረክሶ መሆን አለበት’ ብሎ ስላሰበ በዚያን ቀን ምንም አልተናገረም።
አዲስ ጨረቃ በወጣችበት ቀን ማግስት ይኸውም በሁለተኛው ቀን የዳዊት ቦታ ክፍት እንደሆነ ነበር። ከዚያም ሳኦል ልጁን ዮናታንን “የእሴይ ልጅ ትናንትም፣ ዛሬም ማዕድ ላይ ያልተገኘው ለምንድን ነው?” አለው።
ዮናታንም ለሳኦል እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ዳዊት ወደ ቤተልሔም ይሄድ ዘንድ እንድፈቅድለት ለመነኝ።
እንዲህም አለኝ፦ ‘ቤተሰባችን በከተማዋ ውስጥ መሥዋዕት ስለሚያቀርብና ወንድሜም በዚያ እንድገኝ ስለጠራኝ እባክህ እንድሄድ ፍቀድልኝ። እንግዲህ በፊትህ ሞገስ ካገኘሁ እባክህ ወንድሞቼን አይ ዘንድ ሹልክ ብዬ ልሂድ።’ ዳዊት በንጉሡ ማዕድ ላይ ያልተገኘው ለዚህ ነው።”
በዚህ ጊዜ ሳኦል በዮናታን ላይ እጅግ ተቆጣ፤ እንዲህም አለው፦ “አንተ የዚያች ዓመፀኛ ሴት ልጅ፣ በራስህም ሆነ በእናትህ ላይ ውርደት ለማምጣት ከእሴይ ልጅ ጋር መወገንህን የማላውቅ መሰለህ?
የእሴይ ልጅ በምድር ላይ በሕይወት እስካለ ድረስ አንተም ሆንክ መንግሥትህ አትጸኑም። እሱ መሞት ስላለበት በል አሁኑኑ ልከህ አስመጣልኝ።”
ዮናታን ግን አባቱን ሳኦልን “ለምን ይገደላል? ጥፋቱስ ምንድን ነው?” አለው።
በዚህ ጊዜ ሳኦል እሱን ለመግደል ጦሩን ወረወረበት፤ ስለሆነም ዮናታን አባቱ፣ ዳዊትን ለመግደል ቆርጦ መነሳቱን አወቀ።
ዮናታንም ወዲያውኑ በታላቅ ቁጣ ከማዕዱ ላይ ተነሳ፤ በዳዊት ምክንያት በጣም ስላዘነና የገዛ አባቱም ስላዋረደው አዲስ ጨረቃ በወጣች በሁለተኛው ቀን ምንም ምግብ አልቀመሰም።
ዮናታንም በማለዳ ተነስቶ ከዳዊት ጋር ወደተቀጣጠሩበት ቦታ ሄደ፤ አንድ ወጣት አገልጋይም አብሮት ነበር።
እሱም አገልጋዩን “ሂድ፣ ሩጥ፤ የምወነጭፋቸውንም ፍላጻዎች ፈልግ” አለው። ከዚያም አገልጋዩ ሮጠ፤ ዮናታንም ፍላጻውን ከእሱ አሳልፎ ወነጨፈው።
አገልጋዩም ዮናታን የወነጨፈው ፍላጻ ያረፈበት ቦታ ሲደርስ ዮናታን አገልጋዩን ጠርቶ “ፍላጻው ያለው ከአንተ ወዲያ አይደለም?” አለው።
ዮናታንም በድጋሚ አገልጋዩን ጠርቶ “ፍጠን እንጂ! ቶሎ በል! አትዘግይ!” አለው። የዮናታን አገልጋይም ፍላጻዎቹን አንስቶ ወደ ጌታው ተመለሰ።
አገልጋዩ ስለ ጉዳዩ የሚያውቀው ነገር አልነበረም፤ የዚህ ትርጉም ምን እንደሆነ የሚያውቁት ዮናታንና ዳዊት ብቻ ነበሩ።
ከዚያም ዮናታን የጦር መሣሪያዎቹን ለአገልጋዩ ሰጥቶ “ሂድ፣ ወደ ከተማ ይዘሃቸው ተመለስ” አለው።
አገልጋዩም ሲሄድ ዳዊት በስተ ደቡብ በኩል ከሚገኝ በአቅራቢያው ካለ ስፍራ ተነስቶ መጣ። ሦስት ጊዜም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ እጅ ነሳ፤ ከዚያም ተሳሳሙ፤ ተላቀሱ፤ ይበልጥ ያለቀሰው ግን ዳዊት ነበር።
ዮናታንም ዳዊትን “ሁለታችንም ‘ይሖዋ በእኔና በአንተ፣ በዘሮቼና በዘሮችህ መካከል ለዘላለም ይሁን’ ብለን በይሖዋ ስም ስለተማማልን በሰላም ሂድ” አለው። ከዚያም ዳዊት ተነስቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማዋ ተመለሰ።
በመጨረሻም ሳሙኤል እስራኤላውያንን ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “እንግዲህ እኔ ያላችሁኝን ሁሉ አድርጌአለሁ፤ የሚገዛችሁም ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ።
የሚመራችሁ ንጉሥ ይኸው! እኔ ዕድሜዬ ገፍቷል፤ ፀጉሬም ሸብቷል፤ እነሆ፣ ልጆቼ አብረዋችሁ ናቸው፤ እኔ እንደሆንኩ ከልጅነቴ ጀምሮ እስከዚህ ቀን ድረስ ስመራችሁ ቆይቻለሁ።
አሁንም ያለሁት በፊታችሁ ነው። እስቲ የምከሰስበት ነገር ካለ በይሖዋና እሱ በቀባው ፊት ንገሩኝ፦ የማንን በሬ ወይም የማንን አህያ ወስጃለሁ? ወይስ ማንን አታልያለሁ? ደግሞስ በማን ላይ ግፍ ፈጽሜአለሁ? አይቼ እንዳላየሁ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀብያለሁ? እንዲህ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”
በዚህ ጊዜ እነሱ “አታለኸንም ሆነ ግፍ ፈጽመህብን ወይም ደግሞ ከማንም ሰው እጅ ምንም ነገር ተቀብለህ አታውቅም” አሉት።
በመሆኑም ሳሙኤል “እኔን የምትከሱበት ምንም ነገር እንዳላገኛችሁ ይሖዋም ሆነ እሱ የቀባው ዛሬ በእናንተ ላይ ምሥክሮች ናቸው” አላቸው። እነሱም “እሱ ምሥክር ነው” አሉ።
ሳሙኤልም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “ሙሴንና አሮንን የመረጠው እንዲሁም አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር ያወጣው ይሖዋ ምሥክር ነው።
እንግዲህ እናንተ ባላችሁበት ቁሙ፤ እኔም ይሖዋ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ባደረጋቸው የጽድቅ ሥራዎች መሠረት በይሖዋ ፊት እፋረዳችኋለሁ።
“ያዕቆብ ወደ ግብፅ በገባና አባቶቻችሁም ይሖዋ እንዲረዳቸው በጮኹ ጊዜ ይሖዋ አባቶቻችሁን ከግብፅ መርተው እንዲያወጧቸውና በዚህ ስፍራ እንዲያኖሯቸው ሙሴንና አሮንን ላከ።
እነሱ ግን አምላካቸውን ይሖዋን ረሱ፤ እሱም የሃጾር ሠራዊት አለቃ ለነበረው ለሲሳራ፣ ለፍልስጤማውያንና ለሞዓብ ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሸጣቸው፤ እነሱም ወጓቸው።
በዚህ ጊዜ ይሖዋ እንዲረዳቸው ጮኹ፤ እንዲህም አሉ፦ ‘ባአልንና የአስታሮትን ምስሎች ለማገልገል ስንል ይሖዋን ስለተውን ኃጢአት ሠርተናል፤ ስለሆነም እንድናገለግልህ አሁን ከጠላቶቻችን እጅ ታደገን።’
ከዚያም ይሖዋ ያለስጋት መኖር እንድትችሉ የሩባአልን፣ ቤዳንን፣ ዮፍታሔንና ሳሙኤልን ልኮ በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ ሁሉ እጅ ታደጋችሁ።
የአሞናውያን ንጉሥ የሆነው ናሃሽ በእናንተ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እንደመጣ ስታዩ ምንም እንኳ አምላካችሁ ይሖዋ ንጉሣችሁ ቢሆንም ‘አይሆንም፣ ንጉሥ እንዲነግሥልን እንፈልጋለን!’ አላችሁኝ።
እንግዲህ የመረጣችሁትና የጠየቃችሁት ንጉሥ ይኸውላችሁ። እነሆ፣ ይሖዋ በላያችሁ ንጉሥ አንግሦአል።
ይሖዋን ብትፈሩና ብታገለግሉ፣ ቃሉን ብትታዘዙና በይሖዋ ትእዛዝ ላይ ባታምፁ እንዲሁም እናንተም ሆናችሁ በላያችሁ የሚገዛው ንጉሥ አምላካችሁን ይሖዋን ብትከተሉ መልካም ይሆንላችኋል።
ሆኖም የይሖዋን ቃል ባትታዘዙና በይሖዋ ትእዛዝ ላይ ብታምፁ የይሖዋ እጅ በእናንተና በአባቶቻችሁ ላይ ይሆናል።
ስለሆነም አሁን ባላችሁበት ቆማችሁ ይሖዋ ዓይናችሁ እያየ የሚፈጽመውን ይህን ታላቅ ነገር ተመልከቱ።
ዛሬ የስንዴ መከር የሚታጨድበት ጊዜ አይደለም? ይሖዋን ነጎድጓድና ዝናብ እንዲልክ እጠይቀዋለሁ፤ እናንተም ንጉሥ እንዲነግሥላችሁ በመጠየቅ በይሖዋ ፊት ምን ያህል ታላቅ በደል እንደፈጸማችሁ ታውቃላችሁ፤ ደግሞም ታስተውላላችሁ።”
ከዚያም ሳሙኤል ይሖዋን ጠየቀ፤ ይሖዋም በዚያ ቀን ነጎድጓድና ዝናብ ላከ፤ በመሆኑም ሕዝቡ ሁሉ ይሖዋንና ሳሙኤልን እጅግ ፈራ።
ሕዝቡም ሳሙኤልን “ሌላው ኃጢአታችን ሳያንሰን ንጉሥ እንዲነግሥልን በመለመን ተጨማሪ በደል ስለፈጸምን እንዳንሞት ስለ አገልጋዮችህ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ጸልይልን” አለው።
በመሆኑም ሳሙኤል ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ “አትፍሩ። እርግጥ ይህን ሁሉ ክፋት ፈጽማችኋል። ብቻ ይሖዋን ከመከተል ዞር አትበሉ፤ ይሖዋንም በሙሉ ልባችሁ አገልግሉት።
ምንም ዋጋ የሌላቸውንና ማዳን የማይችሉ ከንቱ ነገሮችን ወደ መከተል ዞር አትበሉ፤ ምክንያቱም እነሱ ከንቱ ነገሮች ናቸው።
ይሖዋ ስለ ታላቁ ስሙ ሲል ሕዝቡን አይተውም፤ ምክንያቱም ይሖዋ እናንተን የራሱ ሕዝብ ሊያደርጋችሁ ፈልጓል።
እኔም ብሆን ስለ እናንተ መጸለዬን በመተው በይሖዋ ላይ ኃጢአት መሥራት ፈጽሞ የማላስበው ነገር ነው፤ እንዲሁም መልካምና ትክክለኛ የሆነውን መንገድ እናንተን ማስተማሬን እቀጥላለሁ።
ብቻ እናንተ ይሖዋን ፍሩ፤ በሙሉ ልባችሁም በታማኝነት አገልግሉት፤ ለእናንተ ያደረጋቸውን ታላላቅ ነገሮች አስታውሱ።
ሆኖም በግትርነት መጥፎ ነገር ማድረጋችሁን ብትቀጥሉ እናንተም ሆናችሁ ንጉሣችሁ ተጠራርጋችሁ ትጠፋላችሁ።”
ዳዊት ከሳኦል ጋር ተነጋግሮ እንደጨረሰ ዮናታንና ዳዊት የጠበቀ ወዳጅነት መሠረቱ፤ ዮናታንም እንደ ራሱ ወደደው።
ከዚያን ቀን ጀምሮ ሳኦል ዳዊት ከእሱ ጋር እንዲኖር አደረገ፤ ወደ አባቱም ቤት እንዲመለስ አልፈቀደለትም።
ዮናታንም ዳዊትን እንደ ራሱ ስለወደደው ከዳዊት ጋር ቃል ኪዳን ተጋቡ።