text stringlengths 4 267 |
|---|
እነዚህ መመሪያዎች የተሰጡት ለሁሉም ክርስቲያኖች ስለሆነ ተስፋቸው በሰማይ መኖርም ይሁን በምድር በዛሬው ጊዜ ያሉ የአምላክ አገልጋዮችን በሙሉ ይመለከታሉ። |
እነዚህ ሐሳቦች ማርያም በመንፈስ መሪነት የተጻፉትን ቅዱሳን መጻሕፍት በሚገባ እንደምታውቅ ይጠቁማል። |
የማርያም ሐሳብ፣ የነቢዩ ሳሙኤል እናት የሆነችው ሐና ከተናገረችው ነገር ጋር በተወሰነ መጠን ይመሳሰላል። |
ማርያም 20 ጊዜ ያህል ከቅዱሳን መጻሕፍት ጠቅሳ እንደተናገረች ይገመታል። |
በግልጽ ማየት እንደሚቻለው ስለ መንፈሳዊ ነገሮች መናገር የምትወድ ሴት ነበረች። |
ማርያም በልቧ ካስቀመጠችው ውድ ሀብት ይኸውም ከታላቁ ወዳጇ ከይሖዋ አምላክ በተማረቻቸው ውድ እውነቶች ከተሞላው ጎተራ እያወጣች የተናገረች ያህል ነው። |
እንደ ማርያም ሁሉ እኛም አንዳንድ ጊዜ ይሖዋ የሚሰጠን ኃላፊነት ከባድ ሊመስለን ይችላል። |
ልክ እንደ እሷ፣ ይሖዋ የሚጠቅመንን ነገር እንደሚያደርግልን በመተማመን የሚሰጠንን ኃላፊነት በትሕትና እንቀበል። |
ስለ ይሖዋና ስለ ዓላማዎቹ የምንማረውን ነገር በጥሞና በማዳመጥ፣ በመንፈሳዊ እውነቶች ላይ በማሰላሰል እንዲሁም የተማርናቸውን ነገሮች ለሌሎች በደስታ በማካፈል ማርያምን በእምነቷ መምሰል እንችላለን። |
አንድ ወዳጅህ ወይም የቤተሰብህ አባል በተናገረው ተስፋ አስቆራጭ ነገር ስሜትህ ተደቁሶ አሊያም በከባድ ሕመም እየተሠቃየህ ወይም የምትወደውን ሰው በሞት አጥተህ ከሆነ ኢዮብ ከተወው ምሳሌ ማጽናኛ ማግኘት ትችላለህ። |
ኢዮብ መከራ እንዲደርስበት ያደረገው ማን መሆኑን ባያውቅም እንኳ ተስፋ አልቆረጠም። |
እንዲጸና የረዳው ምንድን ነው? |
አንደኛ ነገር አምላክን የሚፈራ ሰው ነበር። |
ኢዮብ አመቺ በሆነ ወቅትም ሆነ በአስቸጋሪ ጊዜ ይሖዋን ለማስደሰት ቁርጥ ውሳኔ አድርጎ ነበር። |
በተጨማሪም ይሖዋ፣ በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት ባከናወናቸው አስደናቂ ነገሮች ላይ እንዲያሰላስል ኢዮብን ረድቶታል። |
ይህም መከራዎቹን ይሖዋ በትክክለኛው ጊዜ እንደሚያስወግዳቸው ይበልጥ እንዲተማመን አድርጎታል። |
ደግሞም የሆነው ይህ ነው። |
መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋ በኢዮብ ላይ የደረሰው መከራ እንዲያበቃ አደረገ፤ ደግሞም ብልጽግናውን መለሰለት። |
ይሖዋ ለኢዮብ ቀድሞ የነበረውን እጥፍ አድርጎ ሰጠው ይላል። |
ኢዮብም ሸምግሎና ዕድሜ ጠግቦ ሞተ። |
አደገኛ ሁኔታዎችን አስቀድመን በማስተዋል ጠንቃቆች መሆናችንን እናሳያለን፤ በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ የገለልተኝነት አቋማችንን በመጠበቅ ደግሞ የዋሆች መሆናችንን እናሳያለን። |
ፖለቲካዊ ጉዳዮች ሲነሱ ስለምንናገረው ነገር ጠንቃቃ መሆን አለብን። |
ለምሳሌ ያህል፣ የአምላክን መንግሥት ምሥራች ስንሰብክ የአንድን መሪ ወይም የፖለቲካ ፓርቲ ፖሊሲዎች፣ ከማወደስም ሆነ ከመንቀፍ መቆጠብ ይኖርብናል። |
ከሰዎች ጋር ስንነጋገር ትኩረት ማድረግ ያለብን መሠረታዊ በሆነው ችግር ላይ እንጂ በማንኛውም ፖለቲካዊ መፍትሔ ላይ ሊሆን አይገባም፤ በዚህ መንገድ የሚያግባቡንን ነጥቦች ለማንሳት ጥረት ማድረግ አለብን። |
ከዚያም የአምላክ መንግሥት የሰው ልጆች ያሉባቸውን ችግሮች ለዘለቄታው ጠራርጎ የሚያስወግደው እንዴት እንደሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ እናሳያቸው። |
በውይይቱ መሃል፣ ተመሳሳይ ፆታ ባላቸው ሰዎች መካከል የሚፈጸመውን ጋብቻ ወይም ፅንስ ማስወረድን የመሳሰሉ አወዛጋቢ ጉዳዮች ከተነሱ የአምላክ መሥፈርቶች ምን እንደሆኑ እናስረዳቸው፤ እንዲሁም እነዚህን መሥፈርቶች በሕይወታችን ተግባራዊ ለማድረግ የምንጥረው እንዴት እንደሆነ ልንገልጽላቸው ይገባል። |
ከእነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የየትኛውንም የፖለቲካ ፓርቲ አቋም ደግፈን መናገር አይኖርብንም። |
በተጨማሪም አንዳንድ ሕጎች ሊወጡ፣ ሊሻሩ ወይም ሊለወጡ እንደሚገባ የሚገልጽ ሐሳብ ቢሰነዘር እኛ ከየትኛውም ወገን ልንሆን አይገባም፤ ሌሎች የእኛን አመለካከት እንዲቀበሉም ጫና አናሳድርም። |
አንድ ሽማግሌ ለአንድ ወንድም ሥልጠና ከመጀመሩ በፊት ዘና ያለ ሁኔታ እንዲኖርና ከእሱ ጋር ጥሩ ወዳጅነት ለመመሥረት ጥረት ማድረግ ይኖርበታል። |
ሽማግሌዎች የሚወስዷቸው እርምጃዎች እንደ አካባቢው ሁኔታና ባሕል ሊለያዩ ይችላሉ። |
ይሁንና የምትኖረው የትም ይሁን የት እንዲሁም ምንም ያህል ሥራ የሚበዛብህ ሽማግሌ ብትሆን ከተማሪው ጋር ጊዜ ማሳለፍህ በእኔ ዘንድ ትልቅ ቦታ አለህ የሚል መልእክት ያስተላልፋል። |
በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኝ ለመማር ፈቃደኛ የሆነ ተማሪ ይህን መልእክት በሚገባ እንደሚያስተውልና በጥልቅ እንደሚነካው ጥርጥር የለውም። |
አንድ አስተማሪ ውጤታማ የሚባለው ሌሎችን የማሠልጠን ፍቅር ስላለው ብቻ ሳይሆን ለሚያሠለጥነው ሰው ጭምር ፍቅር ሲኖረው ነው። |
ጋር አወዳድር። |
አንድ አስተማሪ ለተማሪው ፍቅር ካለው ተማሪው ይህን በቀላሉ ሊያስተውል ይችላል፤ እንዲሁም ለሥልጠናው ጥሩ ምላሽ እንዲሰጥ ያነሳሳዋል። |
በመሆኑም ውድ ሽማግሌዎች፣ ሌሎችን ስታሠለጥኑ አስተማሪ ብቻ ሳይሆን ጓደኛም ሁኗቸው። |
ይሖዋ ለበላይ ተመልካቾች የሚሆኑ ብቃቶች በዝርዝር እንዲሰፍሩ ማድረጉ፣ ኃላፊነት ያላቸው ወንድሞች ላቅ ያሉ መሥፈርቶችን እንዲያሟሉ የሚፈልግ መሆኑን ያሳያል። |
ይሖዋ፣ ሽማግሌዎች ጥሩ ምሳሌ እንዲሆኑ ይጠብቅባቸዋል፤ እንዲሁም በገዛ ልጁ ደም የዋጀውን ጉባኤ የሚይዙበትን መንገድ በተመለከተ ይጠይቃቸዋል። |
አምላክ፣ በተሾሙት የበታች እረኞች እንክብካቤ ሥር ሆነን ያለ ስጋት እንድንኖር ይፈልጋል። |
ከእነዚህ ነጥቦች አንጻር፣ ክርስቲያን ሽማግሌዎች እንዲያሟሉ የሚጠበቁባቸው ቅዱስ ጽሑፋዊ ብቃቶች መኖራቸው ይሖዋ ምን ያህል በጥልቅ እንደሚያስብልን እንድንገነዘብ ያደርገናል። |
ለነገሩ በዚህ ጥቅስ ላይ ከተዘረዘሩት ብቃቶች መካከል አብዛኞቹ፣ ይሖዋ ከሁሉም ክርስቲያኖች የሚጠብቃቸው ስለሆኑ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከዚህ ጥቅስ ትምህርት ሊያገኝ ይችላል። |
ለምሳሌ፣ ሁላችንም ምክንያታዊ ልንሆንና ጤናማ አስተሳሰብ ሊኖረን ይገባል። |
ሽማግሌዎች ለመንጋው ምሳሌ ለመሆን ሲጥሩ እኛም ከእነሱ ትምህርት ልንወስድና በእምነታቸው ልንመስላቸው ይገባል። |
በዚህ ጥቅስ ላይ ማሰላሰልህ ይሖዋ ስለ አንተ በግለሰብ ደረጃ እንደሚያስብና እንደሚወድህ እንድትገነዘብ ሊያደርግህ ይችላል። |
በይሖዋ ፊት ውድ እንደሆንክ እርግጠኛ ሁን። |
አምላክ እኛን ለማነጋገር በዋነኝነት የሚጠቀመው በመጽሐፍ ቅዱስ ስለሆነ ለቃሉ ጥልቅ አክብሮት ሊኖረን ይገባል። |
ወላጆችም ሆኑ ልጆች አንዳቸው ለሌላው ፍቅር እንዳላቸው እንዲሰማቸው እንዲሁም በመካከላቸው የመተማመን ስሜት እንዲኖር፣ ትርጉም ያለውና ደግነት የሚንጸባረቅበት የሐሳብ ልውውጥ ማድረጋቸው ወሳኝ ነው። |
ከይሖዋ ጋር በተያያዘስ ምን መጠበቅ ይኖርብናል? |
ይሖዋን አይተነውም ሆነ ድምፁን ሰምተን ባናውቅም እንኳ በመንፈስ መሪነት ባስጻፈው ቃሉ አማካኝነት ያነጋግረናል፤ እኛም ልናዳምጠው ይገባል። |
ራሳችንን ለእሱ የወሰንን ሕዝቦቹ በመሆናችን ይሖዋ ሊመራን እንዲሁም ከጉዳት ሊጠብቀን ይፈልጋል። |
በተጨማሪም እንድናውቀውና እንድንተማመንበት ይሻል። |
የፆታ ብልግና ለመፈጸም የምትፈተን ከሆነ ምን ማድረግ ይኖርብሃል? |
ድክመት እንዳለብህ አምነህ ተቀበል። |
አምላክ ጥንካሬ እንዲሰጥህ ጸልይ። |
የሥነ ምግባር ብልግና ወደመፈጸም ሊመሩህ ከሚችሉ ሁኔታዎች ራቅ። |
እንዲሁም ፈተና ሲያጋጥምህ ከፆታ ብልግና በመሸሽ ወዲያውኑ እርምጃ ውሰድ። |
ኢየሱስ ፈተናን በመቃወም ረገድ ጥሩ ምሳሌ ትቶልናል። |
በሰይጣን ማማለያዎች አልተታለለም፤ እንዲሁም በቀረበለት ግብዣ ላይ ማሰብ ብሎም ጥቅምና ጉዳቱን ማመዛዘን አላስፈለገውም። |
ከዚህ ይልቅ ተብሎ ተጽፏል በማለት ወዲያውኑ ምላሽ ሰጠ። |
ኢየሱስ የአምላክን ቃል ያውቅ ስለነበር ፈተና ሲያጋጥመው ፈጣን እርምጃ መውሰድና ከቅዱሳን መጻሕፍት ጠቅሶ መልስ መስጠት ችሏል። |
እኛም ከሰይጣን ጋር ተዋግተን ማሸነፍ እንድንችል የፆታ ብልግና ፈተና እንዲሆንብን መፍቀድ የለብንም። |
አንድ አረጋዊ ሰው እያዘገመ ተራራ ሲወጣ በዓይነ ሕሊናህ ይታይህ። |
በሕይወቱ ውስጥ ካደረጋቸው ጉዞዎች ሁሉ ይህ ከባዱ ሳይሆን አይቀርም። |
ጉዞውን ከባድ ያደረገበት የዕድሜው መግፋት አይደለም። |
አብርሃም 125 ዓመት ገደማ ቢሆነውም ጉልበቱ አሁንም ጠንካራ ነው። |
አብሮት የሚጓዘው ወጣት 25 ዓመት ገደማ ይሆነዋል። |
ይህ ወጣት፣ የአብርሃም ልጅ ይስሐቅ ሲሆን የማገዶ እንጨት ተሸክሟል። |
አብርሃም ደግሞ ቢላ እንዲሁም እሳት ለማቀጣጠል የሚያስፈልገውን ነገር ይዟል። |
አብርሃም የገዛ ልጁን መሥዋዕት አድርጎ እንዲያቀርብ ይሖዋ ጠይቆት ነበር! አብርሃም በሕይወቱ ካጋጠሙት ሁሉ ከባድ የሆነ የእምነት ፈተና ተደቅኖበታል። |
አብርሃም አምላክን የታዘዘው በጭፍን አይደለም። |
ከዚህ ይልቅ የታዘዘው ነገሮችን በእምነት ዓይን ስለተመለከተ ነው። |
አብርሃም የእምነት ዓይን ስለነበረው በሰማይ ያለው አባቱ ይሖዋ፣ ታማኝ አገልጋዮቹ ዘላቂ ጉዳት የሚያመጣባቸውን ነገር እንዲፈጽሙ እንደማይጠይቃቸው መመልከት ችሏል። |
ይሖዋን ከታዘዘ፣ አምላኩ እሱንም ሆነ የሚወደውን ልጁን እንደሚባርካቸው ያውቅ ነበር። |
ይሁንና ለእምነቱ መሠረት የሆነው ምን ነበር? |
እውቀትና ተሞክሮ ነው። |
ወደ ይሖዋ ለመቅረብ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ነገሮች አንዱ ከእሱ ጋር አዘውትረን የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ ነው። |
ለመሆኑ ከአምላክ ጋር መነጋገር የምትችለው እንዴት ነው? |
ይሖዋን የምታነጋግረው ወደ እሱ አዘውትረህ በመጸለይ ነው። |
በተጨማሪም በጽሑፍ የሰፈረውን የአምላክ ቃል ዘወትር በማንበብና ባነበብከው ላይ በማሰላሰል ይሖዋ ሲያነጋግርህ ማዳመጥ ትችላለህ። |
ስትጸልይ የምትፈልገውን ነገር ለይተህ የምትጠቅስ ከሆነ ይሖዋ የሚሰጥህ ምላሽ በግልጽ የሚታይ ባይሆንም እንኳ አንተ ለጸሎትህ መልስ እንዳገኘህ በቀላሉ ታስተውላለህ። |
ጸሎትህ ምላሽ ማግኘቱ ደግሞ ይሖዋ ይበልጥ እውን እንዲሆንልህ ያደርጋል። |
በተጨማሪም የሚያሳስቡህን ነገሮች ለይሖዋ ግልጥልጥ አድርገህ በነገርከው መጠን እሱ ወደ አንተ ይበልጥ እየቀረበ ይሄዳል። |
ከይሖዋ ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖረን የምናደርገው ጥረት በሕይወታችን ሙሉ የሚቀጥል ነው። |
ይሖዋ ወደ እኛ እንዲቀርብ የምንፈልግ ከሆነ እኛም ወደ እሱ ለመቅረብ እርምጃ መውሰድ ይኖርብናል። |
እንግዲያው በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና በጸሎት አማካኝነት ከአምላካችን ጋር አዘውትረን የሐሳብ ልውውጥ ማድረጋችንን እንቀጥል። |
እንዲህ የምናደርግ ከሆነ ከይሖዋ ጋር ያለን ግንኙነት እየተጠናከረ ስለሚሄድ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ለመወጣት ያስችለናል። |
አምላክ በሚያመጣው አዲስ ዓለም ውስጥ የምንወዳቸውንና የሚያስደስቱንን ነገሮች ለማከናወን አጋጣሚ እናገኛለን። |
ደግሞም ይሖዋ እነዚህን ፍላጎቶች እንድናሟላ ባይፈልግ ኖሮ በሥራችን የመርካትና ጤናማ በሆኑ መዝናኛዎች የመደሰት ፍላጎት በውስጣችን ይፈጥር ነበር? |
በዚህም ሆነ በሌሎች መንገዶች ይሖዋ ምንጊዜም የሕያዋን ፍጥረታትን ሁሉ ፍላጎት ያሟላል። |
እረፍትና መዝናኛ የራሳቸው ቦታ አላቸው፤ ሆኖም ከእነዚህ ነገሮች የበለጠ ደስታ ማግኘት የምንችለው ከይሖዋ ጋር ላለን ግንኙነት ቅድሚያ ስንሰጥ ነው። |
ምድር ገነት ስትሆንም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። |
እንግዲያው አስቀድመን መንግሥቱን በመፈለግና የይሖዋ ሕዝቦች አሁን በሚያገኟቸው መንፈሳዊ በረከቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ለግል ፍላጎቶቻችን ሁለተኛ ቦታ መስጠትን መልመዳችን ምንኛ ጥበብ ነው! ምድር ገነት ስትሆን ከዚህ በፊት አይተን በማናውቀው መጠን ደስታ እናገኛለን። |
ለእውነተኛው ሕይወት ከአሁኑ በመዘጋጀት ይህን ሕይወት ለማግኘት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለን እናሳይ። |
በሕይወታችን የይሖዋን እጅ ማየት የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው? |
እስቲ ይህን አስብ፦ ምናልባት እውነትን የሰማህበት መንገድ በቀጥታ የአምላክ እጅ እንዳለበት እንድታምን ያደርግህ ይሆናል። |
በጉባኤ ስብሰባ ላይ አንድ ክፍል ሲቀርብ አዳምጠህ ይሄ በቀጥታ እኔን የሚመለከት ነው ያልክበት ጊዜ አለ? |
ወይም ደግሞ ስለ አንድ ጉዳይ ጸልየህ መልስ አግኝተህ ይሆናል። |
ምናልባትም አገልግሎትህን ለማስፋት ከወሰንክ በኋላ ይሖዋ ነገሮችን እንዴት እንዳሳካልህ ስታይ ተገርመህ ሊሆን ይችላል። |
አሊያም ለመንፈሳዊ ነገሮች ስትል ሥራህን ከለቀቅክ በኋላ አምላክ በምንም ዓይነት አልጥልህም ሲል የገባው ቃል ሲፈጸም ተመልክተህ ይሆን? |
እንግዲያው በመንፈሳዊ ንቁ ከሆንንና ልባችን ንጹሕ ከሆነ ይሖዋ እኛን በተለያዩ መንገዶች እንዴት እየረዳን እንዳለ መገንዘብ እንችላለን። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.