text
stringlengths
4
267
የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ27ኛው ዓመት ዚምሪ ገብቶ ኤላህን መትቶ ገደለው፤ በእሱም ምትክ ነገሠ።
እሱም ነግሦ ገና በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጠ የባኦስን ቤት ሁሉ መታ። ከዘመዶቹም ሆነ ከወዳጆቹ መካከል አንድም ወንድ አላስተረፈም።
በዚህ መንገድ ይሖዋ በነቢዩ ኢዩ አማካኝነት በባኦስ ላይ በተናገረው ቃል መሠረት ዚምሪ መላውን የባኦስን ቤት አጠፋ።
ይህም የሆነው ባኦስ እና ልጁ ኤላህ በፈጸሙት ኃጢአት እንዲሁም ከንቱ በሆኑት ጣዖቶቻቸው አማካኝነት የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን በማስቆጣት እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ባደረጉት ኃጢአት የተነሳ ነው።
የቀረው የኤላህ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?
የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ27ኛው ዓመት፣ ሠራዊቱ የፍልስጤማውያን የሆነችውን ጊበቶንን ከቦ በነበረበት ወቅት ዚምሪ በቲርጻ ለሰባት ቀን ነገሠ።
በኋላም ከተማዋን ከቦ የነበረው ሠራዊት “ዚምሪ ሴራ በመጠንሰስ ንጉሡን ገድሎታል” የሚል ወሬ ሰማ። በመሆኑም መላው እስራኤል የሠራዊቱ አለቃ የሆነውን ኦምሪን በዚያን ቀን በሰፈሩ ውስጥ በእስራኤል ላይ አነገሡት።
ኦምሪና ከእሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከጊበቶን ወጥተው ቲርጻን ከበቡ።
ዚምሪም ከተማዋ መያዟን ሲያይ በንጉሡ ቤት ወዳለው የማይደፈር ማማ ገብቶ በውስጡ እንዳለ ቤቱን በእሳት አቃጠለው፤ በዚህም የተነሳ ሞተ።
ይህም የሆነው የኢዮርብዓምን መንገድ በመከተል በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር በመፈጸም በሠራው በገዛ ኃጢአቱና እስራኤላውያን እንዲሠሩ ባደረገው ኃጢአት የተነሳ ነው።
የቀረው የዚምሪ ታሪክና የጠነሰሰው ሴራ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፎ ይገኝ የለም?
የእስራኤል ሕዝብ በሁለት አንጃ የተከፈለው በዚህ ጊዜ ነበር። አንደኛው ወገን የጊናትን ልጅ ቲብኒን ለማንገሥ ስለፈለገ የእሱ ተከታይ ሆነ፤ ሌላኛው ወገን ደግሞ ኦምሪን ተከተለ።
ሆኖም ኦምሪን የተከተለው ሕዝብ የጊናትን ልጅ ቲብኒን በተከተለው ሕዝብ ላይ አየለ። በመሆኑም ቲብኒ ሞተ፤ ኦምሪም ነገሠ።
የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ31ኛው ዓመት ኦምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለ12 ዓመትም ገዛ። በቲርጻም ሆኖ ለስድስት ዓመት ገዛ።
እሱም የሰማርያን ተራራ ከሼሜር ላይ በሁለት ታላንት ብር ገዛ፤ በተራራውም ላይ ከተማ ገነባ። የገነባትንም ከተማ የተራራው ጌታ በሆነው በሼሜር ስም ሰማርያ ብሎ ሰየማት።
ኦምሪም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ማድረጉን ቀጠለ፤ ከእሱ በፊት ከነበሩት ሁሉ የከፋ ድርጊት ፈጸመ።
የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በሄደበት መንገድ ሁሉ ሄደ፤ እንዲሁም ኢዮርብዓም እስራኤላውያን በከንቱ ጣዖቶቻቸው አማካኝነት የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን እንዲያስቆጡት በማድረግ በተከተለው የኃጢአት ጎዳና ተመላለሰ።
የቀረው የኦምሪ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮችና በኃያልነቱ የፈጸማቸው ጀብዱዎች በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?
በመጨረሻም ኦምሪ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእሱም ምትክ ልጁ አክዓብ ነገሠ።
የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በ38ኛው ዓመት የኦምሪ ልጅ አክዓብ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ የኦምሪ ልጅ አክዓብ በሰማርያ ሆኖ በእስራኤል ላይ ለ22 ዓመት ገዛ።
የኦምሪ ልጅ አክዓብ ከእሱ በፊት የነበሩት ሁሉ ከፈጸሙት የከፋ ድርጊት በይሖዋ ፊት ፈጸመ።
አክዓብ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በተከተለው የኃጢአት ጎዳና መመላለሱ ሳያንሰው የሲዶናውያን ንጉሥ የኤትባዓል ልጅ የሆነችውን ኤልዛቤልን አገባ፤ እንዲሁም ባአልን ማገልገልና ለእሱ መስገድ ጀመረ።
እንዲሁም በሰማርያ ለባአል በሠራው ቤት ውስጥ ለባአል መሠዊያ አቆመ።
በተጨማሪም አክዓብ የማምለኪያ ግንድ ሠራ። እንዲሁም ከእሱ በፊት ከነበሩት የእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን የሚያስቆጣ ድርጊት ፈጸመ።
በአክዓብ ዘመን የቤቴል ሰው የሆነው ሂኤል ኢያሪኮን መልሶ ገነባ። ይሖዋ በነዌ ልጅ በኢያሱ አማካኝነት በተናገረው ቃል መሠረት የከተማዋን መሠረት ሲጥል የበኩር ልጁ አቤሮን ሞተ፤ በሮቿን ሲያቆም ደግሞ የመጨረሻ ልጁ ሰጉብ ሞተ።
የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ሰለሞን በአባቱ ምትክ ንጉሥ ሆኖ እንደተቀባ ሲሰማ አገልጋዮቹን ወደ እሱ ላከ፤ ምክንያቱም ኪራም ምንጊዜም የዳዊት ወዳጅ ነበር።
ሰለሞንም በምላሹ እንዲህ የሚል መልእክት ወደ ኪራም ላከ፦
“አባቴ ዳዊት ከተለያየ አቅጣጫ ጦርነት ይከፈትበት ስለነበር ይሖዋ ጠላቶቹን ከእግሩ በታች እስኪያደርግለት ድረስ ለአምላኩ ለይሖዋ ስም የሚሆን ቤት መሥራት እንዳልቻለ በሚገባ ታውቃለህ።
አሁን ግን አምላኬ ይሖዋ በዙሪያዬ ካሉ ጠላቶቼ ሁሉ እረፍት ሰጥቶኛል። የሚቃወመኝም ሆነ እየተፈጸመ ያለ ምንም መጥፎ ነገር የለም።
በመሆኑም ይሖዋ ለአባቴ ለዳዊት ‘ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ በአንተ ምትክ በዙፋንህ ላይ የማስቀምጠው ልጅህ ነው’ ሲል በገባው ቃል መሠረት ለአምላኬ ለይሖዋ ስም ቤት ለመሥራት አስቤአለሁ።
ስለሆነም አገልጋዮችህ አርዘ ሊባኖስ እንዲቆርጡልኝ ትእዛዝ ስጥ። አገልጋዮቼም ከአገልጋዮችህ ጋር ይሠራሉ፤ የአገልጋዮችህንም ደሞዝ አንተ በወሰንከው መሠረት እከፍላለሁ፤ መቼም ከመካከላችን እንደ ሲዶናውያን ዛፍ መቁረጥ የሚችል አንድም ሰው እንደሌለ ታውቃለህ።”
ኪራም የሰለሞንን መልእክት ሲሰማ እጅግ በመደሰቱ “ይህን ታላቅ ሕዝብ እንዲመራ ለዳዊት ጥበበኛ ልጅ ስለሰጠው ዛሬ ይሖዋ ይወደስ!” አለ።
ስለዚህ ኪራም እንዲህ የሚል መልእክት ወደ ሰለሞን ላከ፦ “የላክብኝ መልእክት ደርሶኛል። የአርዘ ሊባኖስና የጥድ ሳንቃዎች በማቅረብ ረገድ የፈለግከውን ሁሉ አደርጋለሁ።
አገልጋዮቼ ሳንቃዎቹን ከሊባኖስ ወደ ባሕሩ ያወርዷቸዋል፤ እኔም በባሕር ላይ ተንሳፈው አንተ ወደምትለኝ ቦታ እንዲደርሱ አንድ ላይ አስሬ እልካቸዋለሁ። እዚያም ሲደርሱ እንዲፈቱ አደርጋለሁ፤ ከዚያ ልትወስዳቸው ትችላለህ። አንተ ደግሞ በምላሹ የጠየቅኩህን ቀለብ ለቤተሰቤ ታቀርባለህ።”
በመሆኑም ኪራም፣ ሰለሞን የፈለገውን ያህል የአርዘ ሊባኖስና የጥድ ሳንቃ አቀረበለት።
ሰለሞን ደግሞ ለኪራም ቤተሰብ ቀለብ እንዲሆን 20,000 የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴና 20 የቆሮስ መስፈሪያ ምርጥ የወይራ ዘይት ለኪራም ሰጠው። ሰለሞን ለኪራም በየዓመቱ ይህን ይሰጠው ነበር።
ይሖዋም ቃል በገባለት መሠረት ለሰለሞን ጥበብ ሰጠው። በኪራምና በሰለሞን መካከል ሰላም ነበር፤ እንዲሁም የስምምነት ውል ተዋዋሉ።
ሰለሞንም ከመላው እስራኤል የግዳጅ ሥራ የሚሠሩ ሰዎችን መለመለ፤ የተመለመሉትም ሰዎች ብዛታቸው 30,000 ነበር።
እነሱንም በየወሩ አሥር አሥር ሺህ እያደረገ በየተራ ወደ ሊባኖስ ይልካቸው ነበር። እነሱም ለአንድ ወር በሊባኖስ፣ ለሁለት ወር ደግሞ ቤታቸው ይቀመጡ ነበር፤ የግዳጅ ሥራ እንዲሠሩ የተመለመሉት ሰዎች አለቃ አዶኒራም ነበር።
ሰለሞን በተራሮቹ ላይ 70,000 ተራ የጉልበት ሠራተኞችና 80,000 ድንጋይ ጠራቢዎች ነበሩት፤
በተጨማሪም ከሰለሞን መኳንንት መካከል አስተዳዳሪዎች ሆነው የሚያገለግሉት 3,300 ሰዎች ሠራተኞቹን ይቆጣጠሩ ነበር።
የቤቱን መሠረት በተጠረቡ ድንጋዮች ለመጣል በንጉሡ ትእዛዝ መሠረት ውድ የሆኑ ትላልቅ ድንጋዮችን ፈልፍለው አወጡ።
ስለዚህ የሰለሞን ግንበኞች፣ የኪራም ግንበኞችና ጌባላውያን ድንጋዮቹን ጠረቡ፤ እንዲሁም ቤቱን ለመገንባት የሚያስፈልጉትን ሳንቃዎችና ድንጋዮች አዘጋጁ።
በዚህ ጊዜ የኢዮርብዓም ልጅ አቢያህ ታመመ።
በመሆኑም ኢዮርብዓም ሚስቱን እንዲህ አላት፦ “እባክሽ፣ ተነሺና የኢዮርብዓም ሚስት መሆንሽን እንዳያውቁ ራስሽን ለውጠሽ ወደ ሴሎ ሂጂ። ነቢዩ አኪያህ ያለው እዚያ ነው። እኔ በዚህ ሕዝብ ላይ ንጉሥ እንደምሆን የተናገረው እሱ ነው።
አሥር ዳቦና የተቀቡ ቂጣዎች እንዲሁም አንድ ገንቦ ማር ይዘሽ ወደ እሱ ሂጂ። እሱም በልጁ ላይ የሚደርሰውን ነገር ይነግርሻል።”
የኢዮርብዓምም ሚስት እንዳላት አደረገች። ተነስታ ወደ ሴሎ በመሄድ ወደ አኪያህ ቤት መጣች። አኪያህ ከማርጀቱ የተነሳ ማየት ተስኖት የነበረ ቢሆንም ዓይኖቹ ፊት ለፊት ትኩር ብለው ይመለከቱ ነበር።
ይሖዋ ግን አኪያህን እንዲህ አለው፦ “የኢዮርብዓም ሚስት ልጇ ስለታመመ ስለ እሱ ልትጠይቅህ እየመጣች ነው። እኔም ምን እንደምትላት እነግርሃለሁ። እሷም እዚህ ስትደርስ ማንነቷ እንዳይታወቅ ራሷን ትለውጣለች።”
አኪያህም በሩ ጋ ስትደርስ የእግሯን ኮቴ ሰምቶ እንዲህ አላት፦ “የኢዮርብዓም ሚስት ግቢ። ማንነትሽ እንዳይታወቅ ራስሽን የለወጥሽው ለምንድን ነው? መጥፎ ዜና እንድነግርሽ ታዝዣለሁ።
ሂጂና ኢዮርብዓምን እንዲህ በዪው፦ ‘የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን ከሕዝብህ መካከል አስነሳሁህ።
ከዚያም መንግሥቱን ከዳዊት ቤት ላይ ቀድጄ ለአንተ ሰጠሁህ። አንተ ግን በፊቴ ትክክል የሆነውን ነገር ብቻ በማድረግ ትእዛዛቴን እንደጠበቀውና በሙሉ ልቡ እንደተከተለኝ እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት አልሆንክም።
ከዚህ ይልቅ ከአንተ በፊት ከነበሩት ሁሉ የከፋ ድርጊት ፈጸምክ፤ እኔንም ለማስቆጣት ለራስህ ሌላ አምላክና ከብረት የተሠሩ ምስሎችን ሠራህ፤ ጀርባህንም ሰጠኸኝ።
በዚህም የተነሳ በኢዮርብዓም ቤት ላይ ጥፋት አመጣለሁ፤ በእስራኤል ውስጥ የሚገኘውን ምስኪኑንና ደካማውን ጨምሮ የኢዮርብዓም የሆነውን ወንድ ሁሉ ጠራርጌ አጠፋለሁ፤ አንድ ሰው ፋንድያን ሙልጭ አድርጎ በመጥረግ እንደሚያስወግድ ሁሉ እኔም የኢዮርብዓምን ቤት ሙልጭ አድርጌ እጠርጋለሁ!
ከኢዮርብዓም ወገን የሆነውን በከተማ ውስጥ የሚሞተውን ሁሉ ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳ ላይ የሚሞተውን ደግሞ የሰማይ አሞሮች ይበሉታል፤ ይሖዋ ይህን ተናግሯልና።”’
“እንግዲህ አሁን ተነስተሽ ወደ ቤትሽ ሂጂ። እግርሽ ከተማዋን እንደረገጠ ልጁ ይሞታል።
ከኢዮርብዓም ቤተሰብ መካከል በመቃብር ቦታ የሚቀበረው እሱ ብቻ ስለሆነ እስራኤል ሁሉ አልቅሰው ይቀብሩታል፤ ምክንያቱም የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ከኢዮርብዓም ቤት ሁሉ አንድ መልካም ነገር ያገኘበት እሱን ብቻ ነው።
ይሖዋም ከዚያን ቀን ጀምሮ እንዲያውም አሁኑኑ፣ የኢዮርብዓምን ቤት የሚያስወግድ በእስራኤል ላይ የሚነግሥ ንጉሥ ለራሱ ያስነሳል።
ይሖዋ በውኃ ውስጥ እንደሚወዛወዝ ሸምበቆ እስራኤልን ይመታል፤ እንዲሁም እስራኤላውያንን ለአባቶቻቸው ከሰጣቸው ከዚህ መልካም ምድር ላይ ይነቅላቸዋል፤ ከወንዙም ማዶ ይበትናቸዋል፤ ምክንያቱም የማምለኪያ ግንዶችን ለራሳቸው በማቆም ይሖዋን አስቆጥተውታል።
እሱም ኢዮርብዓም በሠራው ኃጢአትና እስራኤላውያን እንዲሠሩ ባደረገው ኃጢአት የተነሳ እስራኤልን ይተዋል።”
በዚህ ጊዜ የኢዮርብዓም ሚስት ተነስታ በመሄድ ወደ ቲርጻ መጣች። ቤቱ ደጃፍ ላይ ስትደርስም ልጁ ሞተ።
ይሖዋ በአገልጋዩ በነቢዩ አኪያህ አማካኝነት በተናገረውም መሠረት ቀበሩት፤ እስራኤልም ሁሉ አለቀሰለት።
ኢዮርብዓም ስላደረገው ውጊያና ስለ አገዛዙ የሚናገረው የቀረው ታሪኩ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፏል።
ኢዮርብዓም የገዛበት የጊዜ ርዝመት 22 ዓመት ነበር፤ ከዚያም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በእሱም ምትክ ልጁ ናዳብ ነገሠ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰለሞን ልጅ ሮብዓም በይሁዳ ላይ ነግሦ ነበር። ሮብዓም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 41 ዓመት ነበር፤ እሱም ይሖዋ ስሙ እንዲኖርባት ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል በመረጣት ከተማ በኢየሩሳሌም ሆኖ ለ17 ዓመት ገዛ። እናቱም ናዕማ የተባለች አሞናዊት ነበረች።
ይሁዳም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ፤ እነሱም በፈጸሙት ኃጢአት የተነሳ ከአባቶቻቸው ይበልጥ አስቆጡት።
እነሱም ቢሆኑ በእያንዳንዱ ኮረብታ ላይና በእያንዳንዱ የለመለመ ዛፍ ሥር ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችን፣ የማምለኪያ ዓምዶችንና የማምለኪያ ግንዶችን ለራሳቸው ሠሩ።
ሌላው ቀርቶ በምድሪቱ ላይ የቤተ መቅደስ ቀላጮች ነበሩ። ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት አባሮ ያስወጣቸው ብሔራት ይፈጽሟቸው የነበሩትን አስጸያፊ ነገሮች በሙሉ አደረጉ።
ንጉሥ ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብፁ ንጉሥ ሺሻቅ ኢየሩሳሌምን ለመውጋት መጣ።
እሱም በይሖዋ ቤት የነበሩትን ውድ ንብረቶችና በንጉሡ ቤት የነበሩትን ውድ ንብረቶች ወሰደ። ሰለሞን የሠራቸውን የወርቅ ጋሻዎች ጨምሮ ሁሉንም ነገር ወሰደ።
በመሆኑም ንጉሥ ሮብዓም በእነሱ ምትክ የመዳብ ጋሻዎችን ሠርቶ የንጉሡን ቤት በር ለሚጠብቁት የዘብ አለቆች ሰጣቸው።
ዘቦቹም ንጉሡ ወደ ይሖዋ ቤት በመጣ ቁጥር ጋሻዎቹን ያነግቡ ነበር፤ ከዚያም ወደ ዘቦቹ ክፍል ይመልሷቸው ነበር።
የቀረው የሮብዓም ታሪክና ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?
በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከል የማያቋርጥ ጦርነት ነበር።
በመጨረሻም ሮብዓም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ። እናቱ ናዕማ የተባለች አሞናዊት ነበረች። በእሱም ምትክ ልጁ አብያም ነገሠ።
በሶርያና በእስራኤል መካከል ለሦስት ዓመት ጦርነት አልነበረም።
በሦስተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወረደ።
የእስራኤልም ንጉሥ አገልጋዮቹን “ራሞትጊልያድ የእኛ እንደሆነች ታውቃላችሁ አይደል? ሆኖም እሷን ከሶርያ ንጉሥ እጅ ለማስመለስ እያመነታን ነው” አላቸው።
ከዚያም ኢዮሳፍጥን “በራሞትጊልያድ ለመዋጋት ከእኔ ጋር አብረህ ትሄዳለህ?” አለው። በዚህ ጊዜ ኢዮሳፍጥ ለእስራኤል ንጉሥ “እኔ ማለት እኮ አንተ ማለት ነህ። ሕዝቤ ሕዝብህ ነው። የእኔ ፈረሶችም የአንተ ፈረሶች ናቸው” በማለት መለሰለት።
ሆኖም ኢዮሳፍጥ የእስራኤልን ንጉሥ “እባክህ፣ በመጀመሪያ ይሖዋ ምን እንደሚል ጠይቅ” አለው።
በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ 400 ገደማ የሚሆኑ ነቢያትን አንድ ላይ ሰብስቦ “ራሞትጊልያድን ለመውጋት ልዝመት ወይስ ይቅርብኝ?” አላቸው። እነሱም “ዝመት፤ ይሖዋ በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል” አሉት።
ከዚያም ኢዮሳፍጥ “በዚህ ቦታ የይሖዋ ነቢይ የለም? ካለ በእሱም አማካኝነት እንጠይቅ” አለ።
በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥን “በእሱ አማካኝነት ይሖዋን ልንጠይቅ የምንችልበት አንድ ሰው ይቀራል፤ ሆኖም ስለ እኔ መጥፎ ነገር ብቻ እንጂ መልካም ነገር ፈጽሞ ስለማይተነብይ በጣም እጠላዋለሁ። እሱም የይምላ ልጅ ሚካያህ ነው” አለው። ኢዮሳፍጥ ግን “ንጉሡ እንዲህ ሊል አይገባም” አለ።
ስለሆነም የእስራኤል ንጉሥ አንድ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣን ጠርቶ “የይምላን ልጅ ሚካያህን በአስቸኳይ ይዘኸው ና” አለው።
በዚህ ጊዜ የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ የንግሥና ልብሳቸውን ለብሰው በሰማርያ መግቢያ በር ላይ በሚገኘው አውድማ ላይ በየዙፋናቸው ተቀምጠው ነበር፤ ነቢያቱም ሁሉ በፊታቸው ትንቢት ይናገሩ ነበር።
ከዚያም የኬናአና ልጅ ሴዴቅያስ የብረት ቀንዶች ሠርቶ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሶርያውያንን እስክታጠፋቸው ድረስ በእነዚህ ትወጋቸዋለህ’” አለ።
ሌሎቹ ነቢያትም ሁሉ “ወደ ራሞትጊልያድ ውጣ፤ ይሳካልሃል፤ ይሖዋም እሷን በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል” በማለት ተመሳሳይ ትንቢት ይናገሩ ነበር።
ሚካያህን ለመጥራት የሄደው መልእክተኛም “እነሆ፣ ነቢያቱ ሁሉ በአንድ ድምፅ ለንጉሡ የተናገሩት ነገር ጥሩ ነው። እባክህ፣ የአንተም ቃል እንደ እነሱ ይሁን፤ አንተም ጥሩ ነገር ተናገር” አለው።
ሚካያህ ግን “ሕያው በሆነው በይሖዋ እምላለሁ፣ የምናገረው ይሖዋ የሚለኝን ብቻ ነው” አለ።
ከዚያም ወደ ንጉሡ ገባ፤ ንጉሡም “ሚካያህ፣ ራሞትጊልያድን ለመውጋት እንዝመት ወይስ ይቅርብን?” ሲል ጠየቀው። እሱም ወዲያውኑ “ውጡ፤ ይቀናችኋል፤ ይሖዋ በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል” በማለት መለሰለት።
በዚህ ጊዜ ንጉሡ “በይሖዋ ስም ከእውነት በስተቀር ሌላ አንዳች ነገር እንዳትነግረኝ የማስምልህ ስንት ጊዜ ነው?” አለው።
በመሆኑም ሚካያህ እንዲህ በማለት ተናገረ፦ “እስራኤላውያን ሁሉ እረኛ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበታትነው አያለሁ። ይሖዋም ‘እነዚህ ጌታ የላቸውም። እያንዳንዳቸው በሰላም ወደየቤታቸው ይመለሱ’ ብሏል።”
ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥን “‘ስለ እኔ መጥፎ ነገር ብቻ እንጂ ጥሩ ነገር አይተነብይም’ ብዬህ አልነበረም?” አለው።
በዚህ ጊዜ ሚካያህ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስማ፦ ይሖዋ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ የሰማያት ሠራዊትም ሁሉ በቀኙና በግራው አጠገቡ ቆመው አየሁ።
ከዚያም ይሖዋ ‘በራሞትጊልያድ ላይ ዘምቶ እዚያው እንዲሞት አክዓብን ማን ያሞኘዋል?’ አለ። በዚህ ጊዜ አንዱ አንድ ነገር፣ ሌላው ደግሞ ሌላ ነገር ተናገረ።
ከዚያም አንድ መንፈስ ወደ ፊት ወጥቶ ይሖዋ ፊት በመቆም ‘እኔ አሞኘዋለሁ’ አለ። ይሖዋም ‘እንዴት አድርገህ?’ አለው።
‘እኔ እወጣና በነቢያቱ ሁሉ አፍ ላይ አሳሳች መንፈስ እሆናለሁ’ አለ። እሱም ‘እንግዲያው ታሞኘዋለህ፤ ደግሞም ይሳካልሃል። ውጣና እንዳልከው አድርግ’ አለው።
ይሖዋም በእነዚህ ነቢያትህ ሁሉ አፍ ላይ አሳሳች መንፈስ አኑሯል፤ ሆኖም ይሖዋ ጥፋት እንደሚመጣብህ ተናግሯል።”
የኬናአና ልጅ ሴዴቅያስም ወደ ሚካያህ ቀርቦ በጥፊ መታውና “ለመሆኑ የይሖዋ መንፈስ እኔን በየት በኩል አልፎ ነው አንተን ያናገረህ?” አለው።
ሚካያህም “በየት በኩል እንዳለፈማ፣ ለመደበቅ ወደ ውስጠኛው ክፍል በምትገባበት ቀን ታውቀዋለህ” አለው።
ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ እንዲህ አለ፦ “ሚካያህን ወስዳችሁ ለከተማው አለቃ ለአምዖን እና የንጉሡ ልጅ ለሆነው ለዮአስ አስረክቡት።