text stringlengths 4 267 |
|---|
በመጨረሻም ኢዮዓስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ኢዮርብዓምም በዙፋኑ ተቀመጠ። ኢዮዓስም ከእስራኤል ነገሥታት ጋር በሰማርያ ተቀበረ። |
ኤልሳዕ ለሞት በዳረገው በሽታ ተይዞ በነበረበት ወቅት የእስራኤል ንጉሥ ኢዮዓስ ወደ እሱ ወርዶ “አባቴ፣ አባቴ! የእስራኤል ሠረገላና ፈረሰኞች!” በማለት ላዩ ላይ ተደፍቶ አለቀሰ። |
ኤልሳዕም “በል ደጋንና ቀስቶች አምጣ” አለው። እሱም ደጋንና ቀስቶች አመጣ። |
ከዚያም ኤልሳዕ የእስራኤልን ንጉሥ “ደጋኑን በእጅህ ያዝ” አለው። ንጉሡም ደጋኑን በእጁ ያዘ፤ በመቀጠልም ኤልሳዕ እጆቹን በንጉሡ እጆች ላይ ጫነ። |
ከዚያም “በምሥራቅ በኩል ያለውን መስኮት ክፈት” አለው። እሱም ከፈተ። ኤልሳዕም “አስፈንጥር!” አለው። እሱም አስፈነጠረ። ኤልሳዕም “የይሖዋ የድል ቀስት፤ በሶርያ ላይ የሚወነጨፍ የድል ቀስት! ሶርያውያንን ድምጥማጣቸውን እስክታጠፋ ድረስ አፌቅ ላይ ትመታቸዋለህ” አለው። |
ኤልሳዕ በመቀጠል “ቀስቶቹን ያዝ” አለው፤ እሱም ያዘ። ከዚያም የእስራኤልን ንጉሥ “መሬቱን ውጋ” አለው። እሱም መሬቱን ሦስት ጊዜ ወግቶ አቆመ። |
በዚህ ጊዜ የእውነተኛው አምላክ ሰው በእሱ ላይ ተቆጥቶ እንዲህ አለው፦ “መሬቱን አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መውጋት ነበረብህ! እንደዚያ ብታደርግ ኖሮ ሶርያውያንን ሙሉ በሙሉ ድምጥማጣቸውን ታጠፋ ነበር፤ አሁን ግን ሶርያን የምትመታው ሦስት ጊዜ ብቻ ነው” አለው። |
ከዚያም ኤልሳዕ ሞተ፤ ተቀበረም። በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ወደ ምድሪቱ ዘልቀው የሚገቡ የሞዓባውያን ወራሪ ቡድኖች ነበሩ። |
የተወሰኑ ሰዎች አንድ ሰው ሊቀብሩ ሲሉ ወራሪውን ቡድን ተመለከቱ፤ ስለዚህ ሰውየውን ኤልሳዕ የተቀበረበት ቦታ ውስጥ ወርውረው እየሮጡ ሄዱ። ሰውየውም የኤልሳዕን አፅም በነካ ጊዜ ሕያው ሆነ፤ በእግሩም ቆመ። |
የሶርያ ንጉሥ ሃዛኤል በኢዮዓካዝ ዘመን ሁሉ እስራኤልን ይጨቁን ነበር። |
ሆኖም ይሖዋ ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር ስለገባው ቃል ኪዳን ሲል ሞገስና አሳቢነት አሳያቸው፤ ምሕረትም አደረገላቸው። ሊያጠፋቸው አልፈለገም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከፊቱ አላስወገዳቸውም። |
የሶርያ ንጉሥ ሃዛኤል በሞተ ጊዜ ልጁ ቤንሃዳድ በእሱ ምትክ ነገሠ። |
ከዚያም የኢዮዓካዝ ልጅ ኢዮዓስ፣ ሃዛኤል ከአባቱ ከኢዮዓካዝ ላይ በጦርነት የወሰዳቸውን ከተሞች ከሃዛኤል ልጅ ከቤንሃዳድ አስመለሰ። ኢዮዓስ ሦስት ጊዜ መታው፤ የእስራኤልንም ከተሞች መልሶ ያዘ። |
ምናሴ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 12 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ55 ዓመት ገዛ። የእናቱ ስም ሄፍጺባ ነበር። |
እሱም ይሖዋ ከእስራኤል ሕዝብ ፊት ያባረራቸው ብሔራት ይፈጽሟቸው የነበሩትን አስጸያፊ ልማዶች በመከተል በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ። |
አባቱ ሕዝቅያስ አስወግዷቸው የነበሩትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች መልሶ ገነባ፤ እንዲሁም የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ እንዳደረገው ለባአል መሠዊያዎችን አቆመ፤ የማምለኪያ ግንድም ሠራ። ለሰማይ ሠራዊትም ሁሉ ሰገደ፤ እነሱንም አገለገለ። |
በተጨማሪም ይሖዋ “ስሜን በኢየሩሳሌም አኖራለሁ” ብሎ በተናገረለት በይሖዋ ቤት ውስጥ መሠዊያዎችን ሠራ። |
ደግሞም በይሖዋ ቤት በሚገኙት በሁለቱ ግቢዎች ውስጥ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ መሠዊያዎችን ሠራ። |
የገዛ ልጁን ለእሳት አሳልፎ ሰጠ፤ አስማተኛና መተተኛም ሆነ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ቀጠረ። ይሖዋን ያስቆጣው ዘንድ በእሱ ፊት በጣም ብዙ መጥፎ ነገሮችን ሠራ። |
የሠራውንም የማምለኪያ ግንድ የተቀረጸ ምስል ይሖዋ ለዳዊትና ለልጁ ለሰለሞን እንዲህ ብሎ በተናገረለት ቤት ውስጥ አስቀመጠው፦ “በዚህ ቤትና ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ በመረጥኳት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘለቄታው አኖራለሁ። |
እነሱ ያዘዝኳቸውን ሁሉ ይኸውም አገልጋዬ ሙሴ እንዲከተሉት ያዘዛቸውን ሕግ በሙሉ በጥንቃቄ ይጠብቁ እንጂ ከእንግዲህ የእስራኤላውያን እግር ለአባቶቻቸው ከሰጠሁት ምድር ወጥቶ እንዲንከራተት አላደርግም።” |
እነሱ ግን አልታዘዙም፤ ምናሴም ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት ካጠፋቸው ብሔራት የበለጠ ክፉ ነገር እንዲሠሩ አሳታቸው። |
ይሖዋ አገልጋዮቹ በሆኑት ነቢያት አማካኝነት በተደጋጋሚ እንዲህ ይላቸው ነበር፦ |
“የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ እነዚህን ሁሉ አስጸያፊ ነገሮች አድርጓል፤ ከእሱ በፊት ከነበሩት አሞራውያን ሁሉ ይበልጥ ክፉ ድርጊት ፈጽሟል፤ አስጸያፊ በሆኑ ጣዖቶቹም ይሁዳ ኃጢአት እንዲሠራ አድርጓል። |
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለሚሰማው ሰው ሁሉ ጆሮ የሚሰቀጥጥ ጥፋት በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ አመጣለሁ። |
በሰማርያ ላይ ተጠቅሜበት የነበረውን የመለኪያ ገመድ በኢየሩሳሌም ላይ እዘረጋለሁ፤ እንዲሁም በአክዓብ ቤት ላይ ተጠቅሜበት የነበረውን ውኃ ልክ በእሷ ላይ እጠቀማለሁ፤ አንድ ሰው ሳህኑን እንደሚወለውል ሁሉ እኔም ኢየሩሳሌምን ከወለወልኩ በኋላ እገለብጣታለሁ። |
የርስቴን ቀሪዎች እተዋቸዋለሁ፤ በጠላቶቻቸውም እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እነሱም በጠላቶቻቸው ሁሉ ይበዘበዛሉ፤ እንዲሁም ለጠላቶቻቸው ምርኮ ይሆናሉ፤ |
ይህን የማደርገው አባቶቻቸው ከግብፅ ከወጡበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ በፊቴ መጥፎ የሆነውን ነገር ስላደረጉና በተደጋጋሚ ስላስቆጡኝ ነው።’” |
ምናሴ፣ ይሁዳ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር በመፈጸም ኃጢአት እንዲሠራ በማድረግ ከሠራው ኃጢአት በተጨማሪ ኢየሩሳሌም ከዳር እስከ ዳር በደም እስክትሞላ ድረስ እጅግ ብዙ ንጹሕ ደም አፍስሷል። |
የቀረው የምናሴ ታሪክና ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ እንዲሁም የሠራው ኃጢአት በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? |
በመጨረሻም ምናሴ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በቤቱም በሚገኘው የአትክልት ስፍራ ይኸውም በዑዛ የአትክልት ስፍራ ተቀበረ፤ ልጁም አምዖን በእሱ ምትክ ነገሠ። |
አምዖን በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 22 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሁለት ዓመት ገዛ። እናቱ ሜሹሌሜት ትባል ነበር፤ እሷም የዮጥባ ሰው የሆነው የሃሩጽ ልጅ ነበረች። |
አምዖን አባቱ ምናሴ እንዳደረገው በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ። |
አባቱ በሄደበት መንገድ ሁሉ ተመላለሰ፤ ደግሞም አባቱ ያገለግላቸው የነበሩትን አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶች አገለገለ፤ ለእነሱም ሰገደ። |
የአባቶቹንም አምላክ ይሖዋን ተወ፤ በይሖዋም መንገድ አልሄደም። |
ከጊዜ በኋላም የንጉሥ አምዖን አገልጋዮች በእሱ ላይ አሲረው በገዛ ቤቱ ውስጥ ገደሉት። |
ሆኖም የምድሪቱ ሕዝብ በንጉሥ አምዖን ላይ ያሴሩትን ሁሉ ገደላቸው፤ በእሱም ምትክ ልጁን ኢዮስያስን አነገሠው። |
የቀረው የአምዖን ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም? |
እሱንም በዑዛ የአትክልት ስፍራ በሚገኘው መቃብሩ ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮስያስ በምትኩ ነገሠ። |
የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ በነገሠ በ18ኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በሰማርያ ሆኖ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ እሱም ለ12 ዓመት ገዛ። |
ኢዮራም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ፤ ሆኖም አባቱ ወይም እናቱ ያደረጉትን ያህል ክፉ ድርጊት አልፈጸመም፤ አባቱ የሠራውን የባአል የማምለኪያ ዓምድ አስወግዶ ነበርና። |
ይሁንና የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤላውያን ኃጢአት እንዲሠሩ በማድረግ የተከተለውን የኃጢአት ጎዳና የሙጥኝ አለ። ከዚያ ፈቀቅ አላለም። |
የሞዓብ ንጉሥ ሜሻ በግ አርቢ ነበር፤ እሱም ለእስራኤል ንጉሥ 100,000 የበግ ጠቦቶችንና 100,000 ያልተሸለቱ አውራ በጎችን ይገብር ነበር። |
አክዓብ እንደሞተ የሞዓብ ንጉሥ በእስራኤል ንጉሥ ላይ ዓመፀ። |
በዚህ ጊዜ ንጉሥ ኢዮራም ከሰማርያ ወጥቶ በመሄድ እስራኤልን ሁሉ አሰለፈ። |
በተጨማሪም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ኢዮሳፍጥ “የሞዓብ ንጉሥ ዓምፆብኛል። ሞዓብን ለመውጋት አብረኸኝ ትሄዳለህ?” የሚል መልእክት ላከበት። እሱም “አብሬህ እሄዳለሁ። እኔ ማለት እኮ አንተ ማለት ነህ። ሕዝቤ፣ ሕዝብህ ነው። ፈረሶቼም ፈረሶችህ ናቸው” አለው። |
ከዚያም “ታዲያ በየትኛው መንገድ ብንወጣ ይሻላል?” ብሎ ጠየቀው። እሱም “ወደ ኤዶም ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ” አለው። |
በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ ከይሁዳ ንጉሥና ከኤዶም ንጉሥ ጋር አብሮ ሄደ። ለሰባት ቀን ያህል በሌላ አቅጣጫ ዞረው ከሄዱ በኋላ ለሠራዊቱም ሆነ እየተከተሏቸው ለነበሩት የቤት እንስሳት የሚሆን ውኃ አጡ። |
ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ “በጣም አስደንጋጭ ነው! ይሖዋ እነዚህን ሦስት ነገሥታት የጠራው ለሞዓብ አሳልፎ ለመስጠት ነው!” አለ። |
በዚህ ጊዜ ኢዮሳፍጥ “በእሱ አማካኝነት ይሖዋን ልንጠይቅ የምንችልበት የይሖዋ ነቢይ እዚህ የለም?” አለ። ከእስራኤል ንጉሥ አገልጋዮች አንዱ “ኤልያስን እጅ ያስታጥብ የነበረው የሻፋጥ ልጅ ኤልሳዕ እዚህ አለ” ሲል መለሰ። |
ከዚያም ኢዮሳፍጥ “የይሖዋ ቃል እሱ ዘንድ ይገኛል” አለ። በዚህም መሠረት የእስራኤል ንጉሥ፣ ኢዮሳፍጥና የኤዶም ንጉሥ ወደ እሱ ወረዱ። |
ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ “እኔና አንተን ምን የሚያገናኘን ነገር አለ? ወደ አባትህ ነቢያትና ወደ እናትህ ነቢያት ሂድ” አለው። የእስራኤል ንጉሥ ግን “ይሄማ አይሆንም፤ ይሖዋ እኮ እነዚህን ሦስት ነገሥታት ጠርቶ በሞዓብ እጅ አሳልፎ ሊሰጣቸው ነው” አለው። |
በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ እንዲህ አለ፦ “በማገለግለውና ሕያው በሆነው በሠራዊት ጌታ በይሖዋ እምላለሁ፣ ለማከብረው ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮሳፍጥ ብዬ ነው እንጂ ዓይንህን አላይም፣ ጉዳዬም አልልህም ነበር። |
በሉ አሁን በገና የሚደረድር ሰው አምጡልኝ።” በገና የሚደረድረውም ሰው መጫወት ሲጀምር የይሖዋ እጅ በኤልሳዕ ላይ መጣ። |
እሱም እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በዚህ ሸለቆ ውስጥ ብዙ ቦዮች ቆፍሩ፤ |
ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ነፋስም ሆነ ዝናብ አታዩም፤ ይሁንና ይህ ሸለቆ በውኃ ይሞላል፤ እናንተም ሆናችሁ ከብቶቻችሁ እንዲሁም ሌሎች እንስሶቻችሁ ከዚያ ትጠጣላችሁ።”’ |
ይህ ለይሖዋ በጣም ቀላል ነገር ነው፤ ሞዓብንም በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣችኋልና። |
እናንተም እያንዳንዱን የተመሸገ ከተማና እያንዳንዱን የተመረጠ ከተማ ትመታላችሁ፤ ጥሩውንም ዛፍ ሁሉ ትቆርጣላችሁ፤ የውኃ ምንጮችን በሙሉ ትደፍናላችሁ፤ ጥሩውንም መሬት ሁሉ በድንጋይ ታበላሻላችሁ።” |
በነጋታውም የጠዋት የእህል መባ በሚቀርብበት ጊዜ በድንገት ውኃ ከኤዶም አቅጣጫ መጣ፤ ምድሪቱም በውኃው ተጥለቀለቀች። |
ሞዓባውያንም ነገሥታቱ ሊወጓቸው እንደመጡ ሲሰሙ የጦር መሣሪያ መታጠቅ የሚችሉ ሰዎችን ሁሉ ሰብስበው ድንበሩ ላይ ቆሙ። |
በማለዳ ሲነሱም ፀሐይዋ በውኃው ላይ ታንጸባርቅ ነበር፤ ማዶ ለነበሩት ሞዓባውያንም ውኃው እንደ ደም ቀልቶ ታያቸው። |
እነሱም “ይሄማ ደም ነው! ነገሥታቱ ያለጥርጥር እርስ በርሳቸው በሰይፍ ተራርደዋል። ስለዚህ ሞዓብ ሆይ፣ ወደ ምርኮህ ሂድ!” አሉ። |
እነሱም ወደ እስራኤል ሰፈር ሲመጡ እስራኤላውያን ተነስተው ሞዓባውያንን መምታት ጀመሩ፤ እነሱም ከፊታቸው ሸሹ። እስራኤላውያንም ሞዓባውያንን እየመቱ ወደ ሞዓብ ገሰገሱ። |
ከተሞቹንም ደመሰሱ፤ እያንዳንዱም ሰው ድንጋይ እየጣለ ጥሩውን መሬት ሁሉ በድንጋይ ሞላው፤ የውኃ ምንጮቹን በሙሉ ደፈኑ፤ ጥሩውንም ዛፍ ሁሉ ቆረጡ። በመጨረሻም የቂርሃረሰት የድንጋይ ግንቦች ብቻ ቆመው ቀሩ፤ ወንጭፍ የሚወነጭፉትም ዙሪያዋን ከበው መቷት። |
የሞዓብ ንጉሥ በውጊያው እንደተሸነፈ ባየ ጊዜ ወደ ኤዶም ንጉሥ ጥሶ ለመግባት ሰይፍ የታጠቁ 700 ሰዎችን ወሰደ፤ ሆኖም አልተሳካላቸውም። |
ስለዚህ በእሱ ምትክ የሚነግሠውን የበኩር ልጁን ወስዶ ቅጥሩ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበው። በእስራኤልም ላይ ታላቅ ቁጣ ሆነ፤ በመሆኑም አካባቢውን ለቀው ወደ ምድራቸው ተመለሱ። |
ከዚያም ነቢዩ ኤልሳዕ ከነቢያት ልጆች አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ልብስህን በወገብህ ታጠቅና ይህን የዘይት ዕቃ ይዘህ ወደ ራሞትጊልያድ በፍጥነት ሂድ። |
እዚያም ስትደርስ የኒምሺን ልጅ፣ የኢዮሳፍጥን ልጅ ኢዩን ፈልገው፤ ከዚያም ገብተህ ከወንድሞቹ መካከል አስነሳውና ወደ ውስጠኛው ክፍል ውሰደው። |
የዘይቱንም ዕቃ ወስደህ ዘይቱን በራሱ ላይ አፍስ፤ እንዲህም በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንተን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጌ ቀብቼሃለሁ።”’ ከዚያም በሩን ከፍተህ በፍጥነት ሽሽ።” |
በመሆኑም የነቢዩ አገልጋይ ወደ ራሞትጊልያድ አቀና። |
እዚያም ሲደርስ የሠራዊቱ አለቆች ተቀምጠው አገኛቸው። እሱም “አለቃ ሆይ፣ የምነግርህ መልእክት አለኝ” አለ። ኢዩም “ለማናችን ነው?” ሲል ጠየቀው። እሱም “አለቃ ሆይ፣ ለአንተ ነው” አለው። |
በመሆኑም ኢዩ ተነስቶ ወደ ቤት ገባ፤ አገልጋዩም ዘይቱን በኢዩ ራስ ላይ በማፍሰስ እንዲህ አለው፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘አንተን በይሖዋ ሕዝብ፣ በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጌ ቀብቼሃለሁ። |
አንተም የጌታህን የአክዓብን ቤት ትመታለህ፤ እኔም የአገልጋዮቼን የነቢያትን ደምና በኤልዛቤል እጅ የሞቱትን የይሖዋን አገልጋዮች ሁሉ ደም እበቀላለሁ። |
የአክዓብም ቤት በጠቅላላ ይጠፋል፤ ደግሞም በእስራኤል ውስጥ ያለውን ምስኪኑንም ሆነ ደካማውን ጨምሮ ከአክዓብ ቤት ወንድ የተባለውን ሁሉ ጠራርጌ አጠፋለሁ። |
የአክዓብንም ቤት እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም ቤትና እንደ አኪያህ ልጅ እንደ ባኦስ ቤት አደርገዋለሁ። |
ኤልዛቤልን ደግሞ ኢይዝራኤል ውስጥ በሚገኝ የእርሻ ቦታ ውሾች ይበሏታል፤ የሚቀብራትም አይኖርም።’” ይህን ከተናገረም በኋላ በሩን ከፍቶ ሸሸ። |
ኢዩ ወጥቶ ወደ ጌታው አገልጋዮች ሲሄድ “ሁሉም ነገር ደህና ነው? ይህ እብድ ወደ አንተ የመጣው ለምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት። እሱም “መቼም ሰውየውንም ሆነ የሚናገረውን ነገር ታውቁታላችሁ” አላቸው። |
እነሱ ግን “ይሄ እንኳ ትክክል አይደለም! ይልቅስ እውነቱን ንገረን” አሉት። ከዚያም ኢዩ “እንግዲህ የነገረኝ ይህ ነው፤ ደግሞም እንዲህ ብሏል፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጌ ቀብቼሃለሁ።”’” |
በዚህ ጊዜ እያንዳንዳቸው ቶሎ ብለው ልብሳቸውን በማውለቅ ደረጃዎቹ ላይ አነጠፉለት፤ ቀንደ መለከትም ነፍተው “ኢዩ ነግሦአል!” አሉ። |
ከዚያም የኒምሺ ልጅ፣ የኢዮሳፍጥ ልጅ ኢዩ በኢዮራም ላይ አሴረ። ኢዮራም ከሶርያ ንጉሥ ከሃዛኤል የተነሳ ከእስራኤል ሁሉ ጋር ሆኖ ራሞትጊልያድን እየጠበቀ ነበር። |
በኋላም ንጉሥ ኢዮራም ከሶርያ ንጉሥ ከሃዛኤል ጋር በተዋጋበት ጊዜ ሶርያውያን ካደረሱበት ቁስል ለማገገም ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ። ኢዩም “እንግዲህ ከተስማማችሁ ወደ ኢይዝራኤል ሄዶ ይህን ወሬ የሚያቀብል ሰው እንዳይኖር ማንም ሰው ከከተማዋ ሾልኮ እንዳይወጣ ጠብቁ” አለ። |
ከዚያም ኢዩ ሠረገላው ላይ ወጥቶ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤ ምክንያቱም ኢዮራም ቆስሎ በዚያ ተኝቶ ነበር፤ የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስም ኢዮራምን ለመጠየቅ ወደዚያ ወርዶ ነበር። |
ጠባቂውም በኢይዝራኤል ማማ ላይ ቆሞ ሳለ የኢዩ ሰዎች ግር ብለው ሲመጡ አየ። ወዲያውኑም “ሰዎች ግር ብለው ሲመጡ ይታየኛል” አለ። ኢዮራምም “አንድ ፈረሰኛ ጠርተህ ወደ እነሱ ላክ፤ እሱም ‘የመጣችሁት በሰላም ነው?’ ይበላቸው” አለ። |
ስለሆነም አንድ ፈረሰኛ ወደ ኢዩ ሄዶ “ንጉሡ ‘የመጣችሁት በሰላም ነው?’ ይላል” አለው። ኢዩ ግን “አንተ ስለ ‘ሰላም’ ምን ይመለከትሃል? ይልቅስ ከኋላዬ ተሰለፍ!” አለው። ጠባቂውም “መልእክተኛው እነሱ ጋ ደርሷል፤ ሆኖም አልተመለሰም” በማለት ተናገረ። |
በመሆኑም ሁለተኛ ፈረሰኛ ላከ፤ እሱም እነሱ ጋ ሲደርስ “ንጉሡ ‘የመጣችሁት በሰላም ነው?’ ይላል” አለ። ኢዩ ግን “አንተ ስለ ‘ሰላም’ ምን ይመለከትሃል? ይልቅስ ከኋላዬ ተሰለፍ!” አለው። |
ጠባቂውም “መልእክተኛው እነሱ ጋ ደርሷል፤ ሆኖም አልተመለሰም፤ ሰውየው ሠረገላ አነዳዱ የኒምሺን የልጅ ልጅ የኢዩን ይመስላል፤ የሚነዳው ልክ እንደ እብድ ነውና” በማለት ተናገረ። |
ኢዮራምም “ሠረገላዬን አዘጋጁልኝ!” አለ። በመሆኑም የጦር ሠረገላው ተዘጋጀለት፤ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮራምና የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስም በየራሳቸው የጦር ሠረገላ ሆነው ኢዩን ለመገናኘት ወጡ። በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ የእርሻ ቦታ ላይ ከእሱ ጋር ተገናኙ። |
ኢዮራምም ኢዩን እንዳየው “ኢዩ፣ የመጣኸው በሰላም ነው?” አለው። እሱ ግን “የእናትህ የኤልዛቤል ምንዝርና መተት እያለ ምን ሰላም አለ?” አለው። |
ኢዮራምም ለመሸሽ ወዲያውኑ ሠረገላውን አዙሮ አካዝያስን “አካዝያስ ተታለናል!” አለው። |
ኢዩም ቀስቱን አስፈንጥሮ ኢዮራምን በትከሻዎቹ መካከል ወጋው፤ ቀስቱም በልቡ በኩል ወጣ፤ ኢዮራምም እዚያው ጦር ሠረገላው ውስጥ ወደቀ። |
ኢዩም የጦር መኮንኑን ቢድቃርን እንዲህ አለው፦ “አንስተህ በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ የእርሻ ቦታ ላይ ጣለው። እኔና አንተ በሠረገሎች ሆነን አባቱን አክዓብን እንከተለው በነበረ ጊዜ ይሖዋ ራሱ በእሱ ላይ ይህን ፍርድ እንዳስተላለፈ አስታውስ፦ |
‘“ትናንት የናቡቴን ደምና የልጆቹን ደም እንዳየሁ ሁሉ” ይላል ይሖዋ፣ “በዚህ የእርሻ ቦታ ላይ ዋጋህን እከፍልሃለሁ” ይላል ይሖዋ።’ በመሆኑም ይሖዋ በተናገረው ቃል መሠረት አንስተህ እርሻው ላይ ጣለው።” |
የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ይህን ሲያይ በአትክልት ቤቱ በኩል ባለው መንገድ ሸሸ። (በኋላም ኢዩ እሱን እያሳደደው “እሱንም ግደሉት!” አለ። እነሱም በይብለአም አጠገብ ወደምትገኘው ወደ ጉር ሽቅብ በሚያስወጣው መንገድ ላይ ሠረገላው ውስጥ እንዳለ አቆሰሉት። እሱ ግን ወደ መጊዶ ሸሸ፤ በዚያም ሞተ። |
ከዚያም አገልጋዮቹ በሠረገላ ጭነው ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፤ በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር በራሱ መቃብር ቀበሩት። |
አካዝያስ በይሁዳ ላይ የነገሠው የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በ11ኛው ዓመት ነበር።) |
ከዚያም ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል መጣ፤ ኤልዛቤልም ይህን ሰማች። በመሆኑም ዓይኖቿን ተኩላና ፀጉሯን አሰማምራ በመስኮት ቁልቁል ትመለከት ጀመር። |
ኢዩም በቅጥሩ በር በኩል ሲገባ ኤልዛቤል “ጌታውን የገደለው ዚምሪ ምን እንደደረሰበት አታውቅም?” አለችው። |
እሱም ወደ መስኮቱ ቀና ብሎ በመመልከት “ከእኔ ጎን የቆመ ማን ነው? ማን ነው?” አለ። ወዲያውኑ ሁለት ወይም ሦስት የሚሆኑ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት ቁልቁል ተመለከቱት። |
እሱም “ወደ ታች ወርውሯት!” አላቸው። እነሱም ወረወሯት፤ ደሟም በግድግዳውና በፈረሶቹ ላይ ተረጨ፤ ኢዩም በፈረሶቹ ረጋገጣት። |
ከዚያም ገብቶ በላ፤ ጠጣም። በኋላም “እባካችሁ ይህችን የተረገመች ሴት አንስታችሁ ቅበሯት። ምንም ቢሆን የንጉሥ ልጅ ናት” አላቸው። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.