text
stringlengths
4
267
ሊቀብሯት ሲሄዱ ግን ከራስ ቅሏ፣ ከእግሮቿና ከእጆቿ መዳፍ በስተቀር ምኗንም አላገኙም።
እነሱም ተመልሰው በነገሩት ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ይህ እኮ ይሖዋ በአገልጋዩ በቲሽባዊው በኤልያስ አማካኝነት እንዲህ በማለት የተናገረው ቃል ፍጻሜ ነው፦ ‘በኢይዝራኤል በሚገኘው የእርሻ ቦታ ውሾች የኤልዛቤልን ሥጋ ይበላሉ።
ሰዎች “ይህች እኮ ኤልዛቤል ናት” እንዳይሉ የኤልዛቤል በድን በኢይዝራኤል የእርሻ ቦታ ላይ እንደ ፍግ ይሆናል።’”
በኢዮዓቄም ዘመን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ምድሪቱን ወረረ፤ ኢዮዓቄምም ለሦስት ዓመት የእሱ አገልጋይ ሆነ። ሆኖም ሐሳቡን ለውጦ ዓመፀበት።
ከዚያም ይሖዋ የከለዳውያንን፣ የሶርያውያንን፣ የሞዓባውያንንና የአሞናውያንን ወራሪ ቡድኖች ይልክበት ጀመር። ይሖዋ አገልጋዮቹ በሆኑት በነቢያት አማካኝነት በተናገረው ቃል መሠረት ይሁዳን እንዲያጠፉ እነዚህን ቡድኖች ይልክባቸው ነበር።
ይህ ነገር ይሖዋ ባዘዘው መሠረት በይሁዳ ላይ የደረሰው ይሁዳን ከፊቱ ለማጥፋት ነው፤ ይህም የሆነው ምናሴ በሠራቸው ኃጢአቶች ሁሉ የተነሳ ነው፤
ንጹሕ ደም በማፍሰስ ኢየሩሳሌም በንጹሕ ደም እንድትጥለቀለቅ በማድረጉ ነው፤ ይሖዋም ይቅር ለማለት ፈቃደኛ አልሆነም።
የቀረው የኢዮዓቄም ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉ በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?
በመጨረሻም ኢዮዓቄም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በእሱም ምትክ ልጁ ዮአኪን ነገሠ።
የባቢሎን ንጉሥ ከግብፅ ደረቅ ወንዝ አንስቶ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ የሚገኘውን የግብፅን ንጉሥ ምድር ሁሉ ወስዶ ስለነበር የግብፅ ንጉሥ ዳግመኛ ከምድሩ ለመውጣት አልደፈረም።
ዮአኪን በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 18 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሦስት ወር ገዛ። እናቱ ነሁሽታ ትባል ነበር፤ እሷም የኢየሩሳሌም ሰው የሆነው የኤልናታን ልጅ ነበረች።
አባቱ እንዳደረገው ሁሉ እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።
በዚህ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ የናቡከደነጾር አገልጋዮች በኢየሩሳሌም ላይ ዘመቱ፤ ከተማዋም ተከበበች።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር አገልጋዮቹ ከተማዋን ከበው ሳሉ ወደ ከተማዋ መጣ።
የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፣ ከአገልጋዮቹ፣ ከመኳንንቱና ከቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ ጋር ሆኖ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ዮአኪንን ማርኮ ወሰደው።
ከዚያም በይሖዋ ቤትና በንጉሡ ቤት የነበሩትን ውድ ዕቃዎች ሁሉ ወሰደ። የእስራኤል ንጉሥ የነበረው ሰለሞን ለይሖዋ ቤተ መቅደስ የሠራቸውን የወርቅ ዕቃዎች በሙሉ ይሖዋ አስቀድሞ በተናገረው መሠረት አደቀቃቸው።
ኢየሩሳሌምን በሙሉ፣ መኳንንቱን በሙሉ፣ ኃያላን ተዋጊዎቹን ሁሉ፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችንና አንጥረኞችን በአጠቃላይ 10,000 ሰዎችን በግዞት ወሰደ። በጣም ድሃ ከሆኑት የምድሪቱ ነዋሪዎች በስተቀር በዚያ የቀረ አልነበረም።
በዚህ መንገድ ዮአኪንን ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደው፤ በተጨማሪም የንጉሡን እናት፣ የንጉሡን ሚስቶች፣ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱንና በምድሪቱ ውስጥ ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደ።
ደግሞም የባቢሎን ንጉሥ ኃያላን የሆኑና ለጦርነት የሠለጠኑ ወንዶችን በሙሉ ይኸውም 7,000 ተዋጊዎችን እንዲሁም 1,000 የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችንና አንጥረኞችን ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደ።
ከዚያም የዮአኪንን አጎት ማታንያህን በእሱ ምትክ አነገሠው፤ ስሙንም ቀይሮ ሴዴቅያስ አለው።
ሴዴቅያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 21 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ11 ዓመት ገዛ። እናቱ ሀሙጣል ትባል ነበር፤ እሷም የሊብና ሰው የሆነው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።
ኢዮዓቄም እንዳደረገው ሁሉ እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።
እነዚህ ነገሮች በኢየሩሳሌምና በይሁዳ የተፈጸሙት ከይሖዋ ቁጣ የተነሳ ነው፤ በመጨረሻም ከፊቱ አስወገዳቸው። ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዓመፀ።
ይሖዋ ኤልያስን በአውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ የሚወስድበት ጊዜ ሲደርስ ኤልያስና ኤልሳዕ ከጊልጋል ተነስተው ጉዞ ጀመሩ።
ኤልያስም ኤልሳዕን “ይሖዋ ወደ ቤቴል እንድሄድ ስለላከኝ እባክህ አንተ እዚህ ቆይ” አለው። ኤልሳዕ ግን “ሕያው በሆነው በይሖዋና በሕያውነትህ እምላለሁ፣ ከአንተ አልለይም” አለው። በመሆኑም አብረው ወደ ቤቴል ወረዱ።
ከዚያም በቤቴል የነበሩት የነቢያት ልጆች ወጥተው ኤልሳዕን “ይሖዋ በአንተ ላይ ራስ የነበረውን ጌታህን ዛሬ ሊወስደው እንደሆነ አውቀሃል?” አሉት። እሱም “አዎ፣ አውቄአለሁ። ዝም በሉ” አለ።
ኤልያስም “ኤልሳዕ፣ ይሖዋ ወደ ኢያሪኮ እንድሄድ ስለላከኝ እባክህ አንተ እዚህ ቆይ” አለው። ኤልሳዕ ግን “ሕያው በሆነው በይሖዋና በሕያውነትህ እምላለሁ፣ ከአንተ አልለይም” አለው። በመሆኑም አብረው ወደ ኢያሪኮ መጡ።
ከዚያም በኢያሪኮ የነበሩት የነቢያት ልጆች ወደ ኤልሳዕ ቀርበው “ይሖዋ በአንተ ላይ ራስ የነበረውን ጌታህን ዛሬ ሊወስደው እንደሆነ አውቀሃል?” አሉት። እሱም “አዎ፣ አውቄአለሁ። ዝም በሉ” አለ።
ኤልያስም ኤልሳዕን “ይሖዋ ወደ ዮርዳኖስ እንድሄድ ስለላከኝ እባክህ አንተ እዚህ ቆይ” አለው። ኤልሳዕ ግን “ሕያው በሆነው በይሖዋና በሕያውነትህ እምላለሁ፣ ከአንተ አልለይም” አለው። በመሆኑም አብረው ሄዱ።
ከነቢያት ልጆች መካከል 50ዎቹ ተከትለዋቸው በመሄድ ራቅ ብለው ቆመው ያዩአቸው ነበር፤ በዚህ ጊዜ ሁለቱ ዮርዳኖስ አጠገብ ቆመው ነበር።
ከዚያም ኤልያስ የነቢይ ልብሱን አውልቆ በመጠቅለል ውኃውን መታው፤ ውኃውም ግራና ቀኝ ተከፈለ፤ ሁለቱም በደረቅ መሬት ተሻገሩ።
ዮርዳኖስን እንደተሻገሩ ኤልያስ ኤልሳዕን “ከአንተ ከመወሰዴ በፊት እንዳደርግልህ የምትፈልገውን ጠይቀኝ” አለው። ኤልሳዕም “እባክህ፣ መንፈስህ በእጥፍ ይሰጠኝ” አለው።
ኤልያስም “የጠየቅከው አስቸጋሪ ነገር ነው። ከአንተ ስወሰድ ካየኸኝ እንዳልከው ይሆንልሃል፤ አለዚያ ግን አይሆንልህም” አለው።
ሁለቱ እየተጨዋወቱ በመሄድ ላይ ሳሉ የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረሶች ድንገት መጥተው ለያዩአቸው፤ ኤልያስም በአውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ወደ ሰማይ ወጣ።
ኤልሳዕ ይህን ሲመለከት “አባቴ፣ አባቴ፣ እነሆ የእስራኤል ሠረገላና ፈረሰኞቹ!” በማለት ጮኸ። ኤልያስ ከዓይኑ ሲሰወርበትም የራሱን ልብስ ይዞ ለሁለት ቀደደው።
ከዚያም ከኤልያስ ላይ የወደቀውን የነቢይ ልብስ አነሳ፤ ተመልሶም በዮርዳኖስ ዳርቻ ቆመ።
እሱም ከኤልያስ ላይ በወደቀው የነቢይ ልብስ ውኃውን መታና እንዲህ አለ፦ “የኤልያስ አምላክ ይሖዋ የት አለ?” ውኃውንም ሲመታው ግራና ቀኝ ተከፈለ፤ ኤልሳዕም ተሻገረ።
በኢያሪኮ የሚኖሩ የነቢያት ልጆች ኤልሳዕን ከሩቅ ሲመለከቱት “የኤልያስ መንፈስ በኤልሳዕ ላይ አርፏል” አሉ። በመሆኑም እሱን ለማግኘት ሄዱ፤ በፊቱም መሬት ላይ ተደፍተው እጅ ነሱት።
እነሱም እንዲህ አሉት፦ “እነሆ፣ ከአገልጋዮችህ ጋር ብቁ የሆኑ 50 ሰዎች አሉ። እባክህ ይሂዱና ጌታህን ይፈልጉት። ምናልባት የይሖዋ መንፈስ ወደ ላይ አንስቶት ከተራሮቹ በአንዱ ላይ ወይም ከሸለቆዎቹ በአንዱ ውስጥ ጥሎት ይሆናል።” እሱ ግን “አትላኳቸው” አላቸው።
ሆኖም እነሱ እስኪያፍር ድረስ ወተወቱት፤ እሱም “እሺ፣ ላኳቸው” አለ። እነሱም 50ዎቹን ሰዎች ላኩ፤ ሰዎቹም ለሦስት ቀን ያህል ፈለጉት፤ ሆኖም ሊያገኙት አልቻሉም።
ወደ ኤልሳዕ በተመለሱም ጊዜ ኤልሳዕ በኢያሪኮ ነበር። እሱም “‘አትሂዱ’ ብያችሁ አልነበረም?” አላቸው።
ከጊዜ በኋላም የከተማዋ ሰዎች ኤልሳዕን “ጌታዬ፣ ይኸው እንደምታየው ከተማዋ የምትገኘው ጥሩ ቦታ ላይ ነው፤ ሆኖም ውኃው መጥፎ ነው፤ ምድሪቱም ፍሬ አትሰጥም” አሉት።
እሱም “አነስ ባለ አዲስ ጎድጓዳ ሳህን ጨው ጨምራችሁ አምጡልኝ” አለ። እነሱም አመጡለት።
ከዚያም ውኃው ወደሚመነጭበት ቦታ ሄዶ ጨው ረጨበትና “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ይህን ውኃ ፈውሼዋለሁ። ከእንግዲህ ለሞት ምክንያት አይሆንም፤ ምድሪቱንም ፍሬ እንዳትሰጥ አያደርጋትም’” አለ።
ኤልሳዕ በተናገረውም ቃል መሠረት ውኃው እስከ ዛሬ ድረስ እንደተፈወሰ ነው።
እሱም ከዚያ ተነስቶ ወደ ቤቴል ወጣ። በዚህ ጊዜ ከከተማዋ የወጡ ልጆች “አንተ መላጣ፣ ውጣ! አንተ መላጣ፣ ውጣ!” እያሉ ያፌዙበት ጀመር።
በመጨረሻም ዞር ብሎ ተመለከታቸውና በይሖዋ ስም ረገማቸው። ከዚያም ሁለት እንስት ድቦች ከጫካው ወጥተው 42 ልጆችን ቦጫጨቁ።
እሱም ጉዞውን በመቀጠል ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሄደ፤ ከዚያ ደግሞ ወደ ሰማርያ ተመለሰ።
አክዓብ በሰማርያ 70 ወንዶች ልጆች ነበሩት። በመሆኑም ኢዩ ደብዳቤዎች ጽፎ በሰማርያ ወደሚገኙት የኢይዝራኤል መኳንንትና ሽማግሌዎች እንዲሁም ወደ አክዓብ ልጆች ሞግዚቶች ላከ፤ መልእክቱ እንዲህ የሚል ነበር፦
“አሁን ይህ ደብዳቤ ሲደርሳችሁ የጌታችሁ ወንዶች ልጆች ከእናንተ ጋር ይሆናሉ፤ እንዲሁም የጦር ሠረገሎች፣ ፈረሶች፣ የተመሸገች ከተማና የጦር መሣሪያ ይኖራችኋል።
በመሆኑም ከጌታችሁ ወንዶች ልጆች መካከል የተሻለውንና ብቃት ያለውን መርጣችሁ በአባቱ ዙፋን ላይ አስቀምጡት። ከዚያም ለጌታችሁ ቤት ተዋጉ።”
እነሱ ግን በፍርሃት ተውጠው “ሁለት ነገሥታት በፊቱ ሊቆሙ ካልቻሉ እኛ እንዴት ልንቆም እንችላለን?” አሉ።
በመሆኑም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ፣ የከተማዋ ገዢ፣ ሽማግሌዎቹና ሞግዚቶቹ “እኛ የአንተ አገልጋዮች ነን፤ አንተ ያልከንን ሁሉ እናደርጋለን። ማንንም አናነግሥም። አንተ ራስህ መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” በማለት ወደ ኢዩ መልእክት ላኩ።
ከዚያም ኢዩ “የእኔ ከሆናችሁና እኔን ለመታዘዝ ፈቃደኛ ከሆናችሁ የጌታችሁን ወንዶች ልጆች ራስ ቆርጣችሁ ነገ በዚህ ሰዓት ወደ ኢይዝራኤል ይዛችሁልኝ ኑ” የሚል ሁለተኛ ደብዳቤ ጻፈላቸው። በዚህ ጊዜ 70ዎቹ የንጉሡ ልጆች አሳዳጊዎቻቸው ከሆኑት ታዋቂ የከተማዋ ሰዎች ጋር ነበሩ።
እነሱም ደብዳቤው እንደደረሳቸው 70ዎቹን የንጉሡን ልጆች ወስደው አረዷቸው፤ ከዚያም ጭንቅላታቸውን በቅርጫቶች ውስጥ አድርገው ወደ ኢይዝራኤል ላኩለት።
መልእክተኛውም ገብቶ “የንጉሡን ልጆች ጭንቅላት አምጥተዋል” አለው። እሱም “በከተማዋ መግቢያ በር ላይ ሁለት ቦታ ቆልላችሁ እስከ ጠዋት ድረስ አቆዩአቸው” አለ።
ከዚያም ጠዋት ላይ ሲወጣ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ቆሞ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ንጹሐን ናችሁ። በጌታዬ ላይ ያሴርኩትና የገደልኩት እኔ ነኝ፤ እነዚህን ሁሉ ግን የገደላቸው ማን ነው?
እንግዲህ ይሖዋ በአክዓብ ቤት ላይ ከተናገረው የይሖዋ ቃል አንዱም እንኳ ሳይፈጸም እንደማይቀር እወቁ፤ ይሖዋ በአገልጋዩ በኤልያስ አማካኝነት የተናገረውን ቃል ፈጽሟል።”
በተጨማሪም ኢዩ በኢይዝራኤል ከአክዓብ ቤት የቀሩትን ሁሉ እንዲሁም ታዋቂ የሆኑ ሰዎቹን፣ ወዳጆቹንና ካህናቱን አንድም ሳያስቀር ገደላቸው።
ከዚያም ተነስቶ ወደ ሰማርያ አቀና። በመንገዱ ላይም የእረኞች ማቆያ ቤት ይገኝ ነበር።
በዚያም ኢዩ የይሁዳን ንጉሥ የአካዝያስን ወንድሞች አገኛቸው፤ እሱም “እናንተ እነማን ናችሁ?” ሲላቸው “እኛ የአካዝያስ ወንድሞች ነን፤ የንጉሡን ልጆችና የንጉሡን እናት ልጆች ደህንነት ለመጠየቅ እየወረድን ነው” አሉት።
እሱም ወዲያውኑ “በሕይወት እንዳሉ ያዟቸው!” አለ። በመሆኑም በሕይወት እንዳሉ ያዟቸው፤ በእረኞች ማቆያው ቤት አጠገብ በሚገኘው የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ 42ቱን ሰዎች አረዷቸው። ከመካከላቸው አንድም ሰው አላስተረፈም።
ከዚያ ተነስቶ ሲሄድ የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን ወደ እሱ ሲመጣ አገኘው። ኢዩም ሰላምታ ሰጥቶት “የእኔ ልብ ከልብህ ጋር እንደሆነው ሁሉ የአንተስ ልብ ሙሉ በሙሉ ከእኔ ጋር ነው?” አለው። ኢዮናዳብም “አዎ ነው” ሲል መለሰለት። ኢዩም “እንደዚያ ከሆነ እጅህን ስጠኝ” አለው። እሱም እጁን ሰጠው፤ ኢዩም ጎትቶ ወደ ሠረገላው አወጣው።
ከዚያም “አብረኸኝ ሂድና ይሖዋን የሚቀናቀንን ማንኛውንም ነገር እንደማልታገሥ እይ” አለው። እነሱም በጦር ሠረገላው አብሮት እንዲሄድ አደረጉ።
ከዚያም ወደ ሰማርያ መጣ፤ ደግሞም ይሖዋ ለኤልያስ በነገረው ቃል መሠረት ኢዩ በሰማርያ የሚገኙትን ከአክዓብ ቤት የቀሩትን በሙሉ ጠራርጎ እስኪያጠፋቸው ድረስ መታቸው።
በተጨማሪም ኢዩ ሕዝቡን ሁሉ አንድ ላይ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፦ “አክዓብ ባአልን ያመለከው በትንሹ ነው፤ ኢዩ ግን በላቀ ሁኔታ ያመልከዋል።
በመሆኑም የባአልን ነቢያት ሁሉ፣ አምላኪዎቹን ሁሉና ካህናቱን ሁሉ ጥሩልኝ። ለባአል ታላቅ መሥዋዕት ስለማቀርብ አንድም ሰው እንዳይቀር። የሚቀር ካለ በሕይወት አይኖርም።” ሆኖም ኢዩ ይህን ያለው የባአልን አምላኪዎች ለማጥፋት ተንኮል አስቦ ነው።
በመቀጠልም ኢዩ “ለባአል የተቀደሰ ጉባኤ አውጁ” አለ። እነሱም ይህንኑ አወጁ።
ከዚያም ኢዩ በመላው እስራኤል መልእክት ላከ፤ የባአል አምላኪዎችም በሙሉ መጡ። ሳይመጣ የቀረ አንድም ሰው አልነበረም። እነሱም ወደ ባአል ቤት ገቡ፤ የባአልም ቤት ከአፍ እስከ ገደፉ ሞላ።
ኢዩም የልብስ ቤቱን ኃላፊ “ለባአል አምላኪዎች ሁሉ ልብስ አውጣላቸው” አለው። እሱም ልብሶቹን አወጣላቸው።
ከዚያም ኢዩና የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ወደ ባአል ቤት ገቡ። የባአልንም አምላኪዎች “ከባአል አምላኪዎች በስተቀር አንድም የይሖዋ አምላኪ እዚህ አለመኖሩን በሚገባ አረጋግጡ” አላቸው።
በመጨረሻም መሥዋዕቶችንና የሚቃጠሉ መባዎችን ለማቅረብ ገቡ። ኢዩም የራሱ የሆኑ 80 ሰዎችን ውጭ አቁሞ “በእጃችሁ አሳልፌ ከምሰጣችሁ ሰዎች መካከል አንድ ሰው ቢያመልጥ የእናንተ ሕይወት በዚያ ሰው ሕይወት ይተካል” አላቸው።
ኢዩም የሚቃጠለውን መባ አቅርቦ እንደጨረሰ ጠባቂዎቹንና የጦር መኮንኖቹን “ግቡና ጨፍጭፏቸው! አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” አላቸው። ጠባቂዎቹና የጦር መኮንኖቹም በሰይፍ ጨፈጨፏቸው፤ ሬሳቸውንም ወደ ውጭ ጣሉ፤ እስከ ባአል ቤት ውስጠኛ መቅደስም ድረስ ዘልቀው ገቡ።
ከዚያም የባአልን ቤት የማምለኪያ ዓምዶች አውጥተው አንድ በአንድ አቃጠሉ።
የባአልን የማምለኪያ ዓምድ ፈረካከሱ፤ የባአልንም ቤት በማፈራረስ መጸዳጃ ቦታ እንዲሆን አደረጉ፤ እስከ ዛሬም ድረስ እንደዚያው ነው።
በዚህ መንገድ ኢዩ ባአልን ከእስራኤል አስወገደ።
ሆኖም የናባጥን ልጅ የኢዮርብዓምን ኃጢአት ይኸውም በቤቴልና በዳን ከነበሩት የወርቅ ጥጆች ጋር በተያያዘ እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ያደረገውን ኃጢአት ከመከተል ዞር አላለም።
ስለሆነም ይሖዋ ኢዩን “በአክዓብ ቤት ላይ በልቤ ያሰብኩትን ሁሉ በመፈጸም በፊቴ መልካምና ትክክል የሆነውን ነገር ስላደረግክ ልጆችህ እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ በእስራኤል ዙፋን ላይ ይቀመጣሉ” አለው።
ኢዩ ግን በሙሉ ልቡ በእስራኤል አምላክ በይሖዋ ሕግ ይሄድ ዘንድ አልተጠነቀቀም። ኢዮርብዓም እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ካደረጋቸው ኃጢአቶች ዞር አላለም።
በዚያ ዘመን ይሖዋ የእስራኤልን ግዛት መቆራረስ ጀመረ። ሃዛኤል በሁሉም የእስራኤል ግዛት ጥቃት ይሰነዝር ነበር፤
ይህም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያለውን የጊልያድ ምድር ሁሉ ማለትም ጋዳውያን፣ ሮቤላውያንና ምናሴያውያን የሚኖሩበትን ምድር እንዲሁም ከአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለው ከአሮዔር አንስቶ እስከ ጊልያድና እስከ ባሳን ድረስ ያለውን አካባቢ ያጠቃልላል።
የቀረው የኢዩ ታሪክ፣ ያደረጋቸው ነገሮች በሙሉና ኃያልነቱ ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ዘመን ስለተፈጸሙት ነገሮች በሚተርከው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፈው ይገኙ የለም?
በመጨረሻም ኢዩ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ እነሱም በሰማርያ ቀበሩት፤ ልጁ ኢዮዓካዝም በምትኩ ነገሠ።
ኢዩ በሰማርያ ሆኖ በእስራኤል ላይ የገዛበት ዘመን ርዝመት 28 ዓመት ነበር።
የረማልያህ ልጅ ፋቁሄ በነገሠ በ17ኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የኢዮዓታም ልጅ አካዝ ነገሠ።
አካዝ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 20 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ16 ዓመት ገዛ። አባቱ ዳዊት እንዳደረገው በአምላኩ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አላደረገም።
ከዚህ ይልቅ የእስራኤልን ነገሥታት መንገድ ተከተለ፤ ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት ያባረራቸው ብሔራት ይፈጽሙ የነበረውን አስጸያፊ ድርጊት በመከተል የገዛ ልጁን እንኳ ሳይቀር ለእሳት አሳልፎ ሰጠ።
ደግሞም ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች፣ በኮረብቶቹና በእያንዳንዱ የለመለመ ዛፍ ሥር ይሠዋ እንዲሁም የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርብ ነበር።
የሶርያ ንጉሥ ረጺንና የእስራኤል ንጉሥ የሆነው የረማልያህ ልጅ ፋቁሄ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ የመጡት በዚህ ጊዜ ነበር። አካዝንም ከበቡት፤ ሆኖም ከተማዋን መያዝ አልቻሉም።
በዚህ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ ረጺን አይሁዳውያንን ከኤላት ካባረረ በኋላ ኤላትን ለኤዶም መለሰ። ኤዶማውያንም ወደ ኤላት ገቡ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ይኖራሉ።
በመሆኑም አካዝ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ቴልጌልቴልፌልሶር መልእክተኞች ልኮ “እኔ አገልጋይህና ልጅህ ነኝ። መጥተህ በእኔ ላይ ጥቃት ከሚሰነዝሩት ከሶርያ ንጉሥ እጅና ከእስራኤል ንጉሥ እጅ አድነኝ” አለው።
ከዚያም አካዝ በይሖዋ ቤትና በንጉሡ ቤት ግምጃ ቤቶች ያለውን ብርና ወርቅ በመውሰድ ለአሦር ንጉሥ ጉቦ ሰጠ።
የአሦርም ንጉሥ ልመናውን በመስማት ወደ ደማስቆ ወጥቶ ከተማዋን ያዛት፤ ሕዝቧንም ወደ ቂር በግዞት ወሰደ፤ ረጺንንም ገደለው።
ከዚያም ንጉሥ አካዝ የአሦርን ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶርን ለማግኘት ወደ ደማስቆ ሄደ። በደማስቆ የነበረውን መሠዊያ ባየ ጊዜ ንጉሥ አካዝ የመሠዊያውን ንድፍና እንዴት እንደተሠራ የሚያሳይ መግለጫ ለካህኑ ለዑሪያህ ላከለት።
ካህኑ ዑሪያህ ንጉሥ አካዝ ከደማስቆ በላከለት መመሪያ መሠረት መሠዊያውን ሠራ። ካህኑ ዑሪያህ ንጉሥ አካዝ ከደማስቆ ከመመለሱ በፊት ሠርቶ አጠናቀቀ።
ንጉሡ ከደማስቆ በተመለሰ ጊዜ መሠዊያውን አየው፤ ወደ መሠዊያውም ቀርቦ በላዩ ላይ መባ አቀረበ።
እንዲሁም በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል መባውና የእህል መባው እንዲጨስ አደረገ፤ የመጠጥ መባውንም አፈሰሰ፤ የኅብረት መሥዋዕቶቹንም ደም ረጨ።
ከዚያም በይሖዋ ፊት የነበረውን የመዳብ መሠዊያ ከቤቱ ፊት ለፊት ከነበረበት ቦታ ይኸውም እሱ ከሠራው መሠዊያና ከይሖዋ ቤት መሃል አንስቶ ከእሱ መሠዊያ በስተ ሰሜን አስቀመጠው።
ንጉሥ አካዝም ካህኑን ዑሪያህን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ጠዋት ላይ የሚቀርበውን የሚቃጠል መባ፣ ማታ ላይ የሚቀርበውን የእህል መባ፣ የንጉሡን የሚቃጠል መባና የእህል መባ እንዲሁም የሕዝቡን ሁሉ የሚቃጠል መባ፣ የእህል መባና የመጠጥ መባ በታላቁ መሠዊያ ላይ አቅርብ። በተጨማሪም የሚቃጠለውን መባ ደም ሁሉና የሌሎቹን መሥዋዕቶች ደም ሁሉ በመሠዊያው ላይ እርጭ። የመዳቡን መሠዊያ በተመለከተ ግን ምን እንደማደርግ እወስናለሁ።”
ካህኑ ዑሪያህም ንጉሥ አካዝ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።