text stringlengths 4 267 |
|---|
የስብከቱ ሥራ፣ ከቤት ወደ ቤት በመሄድ መልእክቱን መስማት የሚገባውን ሰው መፈለግን ይጨምራል። |
እንዲህ ያለው የተደራጀ አሠራር ያለ አድልዎ ለመመሥከር ያስችላል። |
የይሖዋ ምሥክሮችስ በዚህ ረገድ ምን ታሪክ አስመዝግበዋል? |
ኢየሱስ ከ1914 ጀምሮ ንጉሥ ሆኖ እየገዛ መሆኑን የሚሰብኩት እነሱ ብቻ ናቸው። |
ኢየሱስ ባዘዘው መሠረት ለስብከቱ ሥራ ትልቅ ቦታ ይሰጣሉ። |
ፒለርስ ኦቭ ፌዝ—አሜሪካን ኮንግርጌሽንስ ኤንድ ዜር ፓርትነርስ የተባለው መጽሐፍ የይሖዋ ምሥክሮች ተቀዳሚ ሥራቸው፣ ስለ መጪው የዓለም ፍጻሜና ለመዳን ስለሚያስፈልገው ነገር የሚገልጸውን መንፈሳዊ መልእክት ማዳረስ መሆኑን ፈጽሞ አይዘነጉም ብሏል። |
የይሖዋ ምሥክሮች ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ የተጠቀሙባቸውን ዘዴዎች በመከተል ይህን መልእክት ማድረሳቸውን ቀጥለዋል። |
በይሖዋ አስተሳሰብ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ስናደርግ ይበልጥ ወደ እሱ እንቀርባለን። |
የእሱን ሞገስና በረከት እናገኛለን። |
ይህ ደግሞ በሰማይ ባለው አባታችን ላይ ያለንን እምነት ያጠናክርልናል። |
እንግዲያው የመጽሐፍ ቅዱስ ሕጎችና መሠረታዊ ሥርዓቶች አምላክ ስለ አንድ ጉዳይ ያለውን አመለካከት እንድናውቅ ስለሚረዱን በእነሱ ለመመራት ጥረት እናድርግ። |
እርግጥ ነው፣ ምንጊዜም ስለ ይሖዋ የምንማራቸው አዳዲስ ነገሮች ይኖራሉ። |
ያም ቢሆን ትጋት የተሞላበት ጥረት በማድረግ በዛሬው ጊዜም እንኳ ጥሩ ውሳኔ ለመወሰን የሚረዳንን ጥበብ፣ እውቀትና ማስተዋል ማግኘት እንችላለን። |
ፍጽምና የጎደላቸው ሰዎች የሚያመነጯቸው ሐሳቦችና የሚያወጧቸው ዕቅዶች በየጊዜው ይለዋወጣሉ፤ ከዚህ በተቃራኒ መዝሙራዊው የይሖዋ ውሳኔዎች ለዘላለም ይጸናሉ፤ የልቡ ሐሳብ ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል በማለት ተናግሯል። |
ከዚህ በግልጽ ማየት እንደሚቻለው አስተሳሰባችንና ድርጊታችን፣ እጅግ ጥበበኛ ከሆነው ከይሖዋ አምላክ አስተሳሰብ ጋር የሚስማማ ከሆነ ከሁሉ የተሻለ ውሳኔ ማድረግ እንችላለን። |
ወደ ይሖዋ ቅረብ የተባለው መጽሐፍ በአብዛኞቹ ጉባኤዎች ውስጥ ወደ ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ ተጠንቷል። |
በዚህ ዝግጅት አማካኝነት የአምላክን ባሕርያት ማጥናታችን እንዲሁም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የሰጧቸውን ከልብ የመነጩ ሐሳቦች መስማታችን በሰማይ የሚኖረውን አባታችንን ይበልጥ እንድንወደው አላደረገንም? |
በተጨማሪም በጉባኤ ለሚቀርቡ ንግግሮችና ሠርቶ ማሳያዎች እንዲሁም ለመጽሐፍ ቅዱስ ንባቡ ትኩረት መስጠታችን ስለ አምላክ ቃል ያለን እውቀት እንዲጨምር ያደርጋል። |
በስብሰባዎች ላይ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች በሁሉም የሕይወታችን ዘርፎች ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንማራለን። |
ለምሳሌ ያህል፣ የመጠበቂያ ግንብ የጥናት ርዕሶች የሚዘጋጁት የአምላክ ሕዝቦች የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ግምት ውስጥ በማስገባት ነው። |
ግቦችህን መለስ ብለህ እንድትገመግም፣ የእምነት ባልንጀሮችህን ይቅር እንድትል ወይም የጸሎትህን ይዘት እንድታሻሽል ያነሳሳህ የመጠበቂያ ግንብ ጥናት አለ? |
በሳምንቱ መሃል በሚደረገው ስብሰባ ላይ ለአገልግሎታችን ሥልጠና እናገኛለን። |
ምሥራቹን መስበክና ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ማስተማር የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንማራለን። |
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግበው ስለሚገኙት በግለሰቦች መካከል ስለተፈጠሩ ግጭቶች አስበህ ታውቃለህ? |
እስቲ በዘፍጥረት መጽሐፍ የመጀመሪያዎቹ ምዕራፎች ላይ የተገለጹትን ብቻ እንመልከት። |
ቃየን አቤልን ገድሎታል ፤ ላሜህም የመታውን አንድ ወጣት ገድሏል ፤ በአብርሃም በአብራም እና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተፈጥሯል ፤ ሣራ ሦራ አጋር ስለናቀቻት በአብርሃም ላይ ተቆጥታለች ፤ እስማኤል ባገኘው ሰው ሁሉ ላይ እጁን ያነሳል፤ ያገኘውም ሰው ሁሉ እጁን ያነሳበታል። |
እነዚህ ግጭቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰፈሩት ለምንድን ነው? |
አንዱ ምክንያት ፍጽምና የሚጎድላቸው የሰው ልጆች፣ በመካከላቸው ያለው ሰላም እንዳይደፈርስ መጠንቀቅ ያለባቸው ለምን እንደሆነ እንዲማሩ ለመርዳት ነው። |
በተጨማሪም ይህን ማድረግ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያስገነዝበናል። |
በገሃዱ ዓለም የነበሩ ሰዎች ስለገጠሟቸው ችግሮች የሚያወሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎችን በማንበብ ጥቅም ማግኘት እንችላለን። |
ያጋጠሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ያደረጉት ጥረት ያስገኘላቸውን ውጤት መመልከታችን እኛም በሕይወታችን ውስጥ ተመሳሳይ ሁኔታ ሲያጋጥመን የእነሱን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያስተምረናል። |
በእርግጥም እነዚህ ዘገባዎች እንዲህ ያሉ ችግሮች ሲያጋጥሙን ምን ማድረግ እንዳለብንና እንደሌለብን ለመወሰን ይረዱናል። |
ዮፍታሔ እስራኤላውያንን ከአሞናውያን እጅ ነፃ ለማውጣት የአምላክ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ያውቅ ነበር። |
በመሆኑም ይሖዋ ድል ካቀዳጀው፣ ከጦርነት ሲመለስ ሊቀበለው መጀመሪያ የሚወጣውን ሰው ለይሖዋ የሚቃጠል መባ አድርጎ እንደሚያቀርብ ቃል ገባ። |
ዮፍታሔ የገባው ቃል ምን ትርጉም አለው? |
ሰውን መሥዋዕት አድርጎ ማቅረብ በይሖዋ ዘንድ አስጸያፊ ድርጊት ነው። |
በመሆኑም ዮፍታሔ ማንንም ሰው ቃል በቃል መሥዋዕት ለማድረግ እንዳላሰበ ግልጽ ነው። |
በሙሴ ሕግ መሠረት የሚቃጠል መባ ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቀርብ መሥዋዕት ነው፤ ስለሆነም ዮፍታሔ፣ ግለሰቡን ሙሉ በሙሉ ለይሖዋ አገልግሎት እንደሚሰጥ መናገሩ መሆን አለበት። |
ዮፍታሔ የገባው ቃል፣ ግለሰቡ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ በማደሪያው ድንኳን ውስጥ እንዲያገለግል መስጠትን ያመለክታል። |
ይሖዋ የዮፍታሔን ስእለት የተቀበለው ሲሆን በምላሹም ታላቅ ድል እንዲቀዳጅ አደረገው። |
ዮፍታሔ ከጦርነት ሲመለስ እሱን ለመቀበል የወጣችው የሚወዳት አንድያ ልጁ ነበረች! እንግዲህ ፈተናው እዚህ ላይ ነው። |
አንዳንድ የበሽታ ዓይነቶች ፈውስ የሌላቸው ሊሆኑ ይችላሉ። |
በመሆኑም አንዳንድ የሕክምና ዓይነቶች በጣም ውጤታማ እንደሆኑ ሲወራ ብንሰማና ወሬው እንዲሁ የስሚ ስሚ ቢሆን እንዲህ ያሉትን የሕክምና ዓይነቶች በመጠቀም ረገድ ጥንቃቄ ማድረጋችን የጥበብ አካሄድ ነው። |
ጳውሎስ ምክንያታዊነታችሁ በሰው ሁሉ ዘንድ የታወቀ ይሁን ሲል በመንፈስ መሪነት ጽፏል። |
ምክንያታዊ መሆናችን መንፈሳዊ ጉዳዮችን ቸል እስክንል ድረስ ስለ ጤናችን ከሚገባው በላይ ከመጨነቅ እንድንቆጠብ ይረዳናል። |
የጤንነታችን ጉዳይ በሕይወታችን ውስጥ የመጀመሪያውን ቦታ ከያዘ ራስ ወዳድ የመሆን አዝማሚያ እየታየብን ሊሆን ይችላል። |
በሕይወታችን ውስጥ ትልቁን ቦታ ሊይዝ የሚገባው መንፈሳዊ ነገር ነው፤ በመሆኑም ስለ ጤንነታችን ያለን አመለካከት ምክንያታዊነት የሚንጸባረቅበት ሊሆን ይገባል። |
ከጤና ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በተመለከተ እያንዳንዳችን የራሳችንን ውሳኔ ለማድረግና የሚያስከትልብንን ኃላፊነት ለመቀበል ፈቃደኛ መሆን ይኖርብናል። |
ሰለሞን መጥፎ ጓደኝነት መመሥረቱ፣ የነበረውን ጥበብ እያደር እንዲያጣና ከእውነተኛው አምልኮ እንዲርቅ አድርጎታል። |
ይሖዋን የማይወድ ሰው ማግባት ለሚያስቡ ክርስቲያኖች ይህ ጥሩ ማስጠንቀቂያ ይሆናቸዋል! አንድ ሰው የአምላክ አገልጋይ የሆነው ከማያምን ሰው ጋር ትዳር ከመሠረተ በኋላ ቢሆንስ? |
መጽሐፍ ቅዱስ እናንተ ሚስቶች፣ ለቃሉ የማይታዘዙ ባሎች ካሉ ያለ ቃል በሚስቶቻቸው ምግባር እንዲማረኩ ለባሎቻችሁ ተገዙ ይላል። |
ይህ ሐሳብ የተጻፈው ለክርስቲያን ሚስቶች ቢሆንም ከጊዜ በኋላ ይሖዋን ማምለክ ለጀመሩና የማያምኑ ሚስቶች ላሏቸው ባሎችም ይሠራል። |
የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር ግልጽ ነው፦ ጥሩ የትዳር አጋር ሁኑ፤ እንዲሁም አምላክ ለጋብቻ ያወጣቸውን የላቁ መሥፈርቶች ተግባራዊ አድርጉ። |
በርካታ የማያምኑ ሰዎች፣ የትዳር ጓደኛቸው የአምላክን መመሪያዎች መከተል ከጀመረ በኋላ ምን ያህል ለውጥ እንዳደረገ ሲመለከቱ እነሱም እውነትን ተቀብለዋል። |
የሐሰት ሃይማኖት ድርጅቶች ከጠፉ በኋላ ምን ይሆናል? |
በዚያን ጊዜ የልባችን እውነተኛ ዝንባሌ ይገለጣል። |
አብዛኛው የሰው ዘር ተራራ ላይ ባሉ ዓለቶች የተመሰሉትን ሰብዓዊ ድርጅቶች መሸሸጊያ ለማድረግ ይሞክራል። |
የአምላክ ሕዝቦች ግን ይሖዋ ወዳዘጋጀው መጠለያ በምሳሌያዊ ሁኔታ ይሸሻሉ። |
በመጀመሪያው መቶ ዘመን ለተወሰነ ጊዜ ያህል ክፍተት የተገኘው ብዙ አይሁዳውያን ወደ ክርስትና እንዲለወጡ አልነበረም። |
ከዚህ በተለየ፣ ቀድሞውንም ክርስቲያን የነበሩት ሰዎች በታዛዥነት እርምጃ የሚወስዱበት ጊዜ ነበር። |
በተመሳሳይም ወደፊት ታላቁ መከራ ለተወሰነ ጊዜ ሲቋረጥ አዳዲስ አማኞች ወደ ክርስትና እንደሚጎርፉ አንጠብቅም። |
ከዚህ ይልቅ በዚህ ጊዜ እውነተኛ ክርስቲያኖች በሙሉ ይሖዋን እንደሚወዱና የክርስቶስን ወንድሞች እንደሚደግፉ ለማሳየት አጋጣሚ ያገኛሉ። |
ይሖዋ ከፍተኛ ኃይል ያለውን ቅዱስ መንፈሱን በመስጠት ጥንካሬ እንድናገኝና ፈተናን መቋቋም እንድንችል ይረዳናል። |
በተጨማሪም አምላክ ልንርቃቸው ስለሚገቡ ሁኔታዎች በቃሉና በጉባኤው አማካኝነት አስቀድሞ ያስጠነቅቀናል፤ ከማስጠንቀቂያዎቹ መካከል እምብዛም አስፈላጊ ባልሆኑ ቁሳዊ ነገሮች ላይ ብዙ ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት ማጥፋትን አስመልክቶ የሚሰጠን ምክር ይገኝበታል። |
ቀደም ሲል አቅኚ የነበሩት ኢስፔንና ያኒ ሁለት ልጆቻቸውን እያሳደጉ ነው። |
ኢስፔን እንዲህ ብሏል፦ ቀደም ሲል እናደርገው እንደነበረው አሁን በቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች ረዘም ያለ ጊዜ ማሳለፍ አንችልም፤ በመሆኑም ፈተና ውስጥ እንዳንወድቅ አዘውትረን ወደ ይሖዋ እንጸልያለን። |
መንፈሳዊነታችንንና ለአገልግሎቱ ያለንን ቅንዓት ጠብቀን ለመኖር እንዲረዳን ይሖዋን እንጠይቀዋለን። |
በዘመናችን የተስፋፋው ሌላው ፈተና ደግሞ ፖርኖግራፊ ማየት ነው። |
አንዳንዶች፣ መጥፎ በሆኑ ነገሮች ላይ በማሰላሰላቸው በዚህ ፈተና ወድቀዋል። |
ሆኖም በሺዎች የሚቆጠሩ ወንድሞቻችን እንዳደረጉት እኛም ይህን ፈተና መቋቋም እንችላለን። |
ብዙ ሰዎች የጌታን ጸሎት በቃላቸው መድገም ይችላሉ። |
ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል የአምላክ መንግሥት እውን መስተዳድር እንደሆነና በምድር ላይ አስደናቂ የሆኑ ለውጦችን እንደሚያመጣ ለሰዎች ለማስረዳት ብዙውን ጊዜ ይህን ጸሎት እንጠቅሳለን። |
አሊያም ደግሞ አምላክ የግል ስም እንዳለውና ይህ ስም መቀደስ ወይም ብሩክ መሆን እንዳለበት ለማጉላት በጸሎቱ ላይ ያለውን የመጀመሪያ ልመና አውጥተን እናሳያቸው ይሆናል። |
የግርጌ ማስታወሻ ኢየሱስ ይህን ጸሎት ያስተማረን በሕዝበ ክርስትና ውስጥ በርካታ ሰዎች እንደሚያደርጉት በጸለይን ቁጥር ቃል በቃል እንድንደግመው አስቦ ነው? |
በፍጹም። |
ኢየሱስ ይህን ናሙና ከማስተማሩ በፊት በምትጸልዩበት ጊዜ አንድ ዓይነት ነገር ደጋግማችሁ አታነብንቡ ብሎ ነበር። |
ከጊዜ በኋላም ይህን ጸሎት በድጋሚ ሲያስተምር ለየት ያለ አገላለጽ ተጠቅሟል። |
ኢየሱስ፣ ስለ የትኞቹ ነገሮች መለመን እንዳለብንና በጸሎታችን ላይ ቅድሚያ መስጠት የሚገባን ለምን ነገሮች እንደሆነ አስገንዝቦናል። |
ይህ ጸሎት፣ የጸሎት ናሙና ተብሎ የሚጠራውም ለዚህ ነው። |
ጽንፈ ዓለም የተደራጀው በእርግጥም አስገራሚ በሆነ መንገድ ነው። |
ከዚህ አንጻር ይሖዋ፣ አገልጋዮቹ በሚገባ የተደራጁ እንዲሆኑ መፈለጉ የሚያስገርም አይደለም። |
እንዲያውም ይህን ማድረግ እንድንችል አምላክ መጽሐፍ ቅዱስን ሰጥቶናል። |
የአምላክ ድርጅት የሚሰጠንን መመሪያዎችና የይሖዋን መሥፈርቶች ችላ ማለት ሕይወታችን ደስታ የራቀውና በመከራ የተሞላ እንዲሆን ያደርጋል። |
የጥንቶቹ እስራኤላውያን፣ በመደራጀት ረገድ ግሩም ምሳሌ ይሆናሉ። |
ለአብነት ያህል፣ በሙሴ ሕግ ሥር በተደራጀ መልክ የሚያገለግሉ ሴት አገልጋዮች ነበሩ። |
ከጊዜ በኋላ ደግሞ ንጉሥ ዳዊት ሌዋውያኑንና ካህናቱን ሥራቸውን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማከናወን በሚያስችል ሁኔታ አደራጅቷቸዋል። |
በአንደኛው መቶ ዘመን የነበረው የክርስቲያን ጉባኤ የተደራጀ ነበር፤ መጀመሪያ ላይ በሐዋርያት የተዋቀረው የበላይ አካል ለጉባኤው አመራር ይሰጥ ነበር። |
ለጉባኤዎች ምክርና መመሪያ የሚተላለፈው በመንፈስ መሪነት በተጻፉ ደብዳቤዎች አማካኝነት ነበር። |
ይሖዋ በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት እውነትን ስለገለጠልንና በምሥራቹ እንድናምን ስላስቻለን ምንኛ አመስጋኞች ነን! ይሖዋ፣ የእምነታችን ዋና ወኪል እና ፍጹም አድራጊ በሆነው በልጁ በኩል ወደ ራሱ ስለሳበን ምንጊዜም ልናመሰግነው ይገባል። |
እንዲህ ላለው ጸጋ ያለንን አመስጋኝነት ለማሳየት በጸሎትና የአምላክን ቃል በማጥናት እምነታችንን ማጠናከራችንን መቀጠል ይኖርብናል። |
ይሖዋ ቃል በገባቸው ተስፋዎች ላይ እምነት እንዳለን ምንጊዜም ማሳየት ይኖርብናል። |
ይህንንም የምናደርገው ሌሎች በግልጽ ሊያዩት በሚችሉት መንገድ ሊሆን ይገባል። |
ለምሳሌ ያህል፣ የአምላክን መንግሥት ምሥራች በመስበኩና ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ ሁልጊዜ እንሳተፋለን። |
በተጨማሪም ለሁሉም፣ በተለይ ደግሞ በእምነት ለሚዛመዱን ሰዎች መልካም ማድረጋችንን አናቋርጥም። |
ከዚህም ሌላ አሮጌውን ስብዕና ከነልማዶቹ ገፍፈን ለመጣል ብርቱ ጥረት እናደርጋለን። |
የጥንቱ የክርስቲያን ጉባኤ እያደገ ሲሄድ መድልዎ እንዳለ የሚጠቁም ሁኔታ መታየት ጀመረ። |
ግሪክኛ ተናጋሪ የሆኑ አይሁዳውያን መበለቶቻቸው ቸል ስለተባሉባቸው ቅሬታ አሰሙ። |
ሐዋርያት ይህን ችግር ለመፍታትና ማንም ቸል እንዳይባል ለማድረግ ሲሉ ሰባት ወንዶች ሾሙ። |
ሰባቱም ወንዶች የግሪክኛ ስም ያላቸው መሆኑ ትኩረት የሚስብ ነው፤ ምናልባትም ሐዋርያት ይህን ያደረጉት በዜግነት ምክንያት በጥንቶቹ ክርስቲያኖች መካከል ሊፈጠር የሚችለውን አለመግባባት ለማብረድ አስበው ሊሆን ይችላል። |
ሁላችንም፣ አናስተውለው ይሆናል እንጂ ያደግንበት ባሕል ከፍተኛ ተጽዕኖ ያደርግብናል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.