text
stringlengths
4
267
የተዋጋላቸው እውነተኛው አምላክ ስለነበር ተገድለው የወደቁት ብዙ ነበሩ። በግዞት እስከተወሰዱበትም ጊዜ ድረስ በእነሱ ቦታ ላይ ኖሩ።
የምናሴ ነገድ እኩሌታ ዘሮች ከባሳን እስከ በዓልሄርሞን፣ እስከ ሰኒር እንዲሁም እስከ ሄርሞን ተራራ ድረስ ባለው ምድር ላይ ኖሩ። ቁጥራቸውም እጅግ ብዙ ነበር።
የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች እነዚህ ነበሩ፦ ኤፌር፣ ይሽኢ፣ ኤሊዔል፣ አዝርዔል፣ ኤርምያስ፣ ሆዳውያህ እና ያህዲኤል፤ እነዚህ ሰዎች ኃያላን ተዋጊዎችና ስመ ገናና ሲሆኑ የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች ነበሩ።
ሆኖም ለአባቶቻቸው አምላክ ታማኞች ሳይሆኑ ቀሩ፤ ደግሞም አምላክ ከፊታቸው ካጠፋቸው ከምድሪቱ ሕዝቦች አማልክት ጋር አመነዘሩ።
በመሆኑም የእስራኤል አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፑልን መንፈስ አነሳሳ (የአሦርን ንጉሥ የቴልጌልቴልፌልሶርን መንፈስ ማለት ነው)፤ እሱም ሮቤላውያንን፣ ጋዳውያንንና የምናሴ ነገድ እኩሌታን በግዞት ወደ ሃላህ፣ ወደ ሃቦር፣ ወደ ሃራ እና ወደ ጎዛን ወንዝ ወሰዳቸው፤ እስከ ዛሬም በዚያ ይገኛሉ።
የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤት እንዲሠሩለት መልእክተኞችን እንዲሁም የአርዘ ሊባኖስ ሳንቃዎችን፣ ድንጋይ ጠራቢዎችንና አናጺዎችን ላከ።
ዳዊትም ይሖዋ በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ እንዳጸናው አወቀ፤ ምክንያቱም አምላክ ስለ ሕዝቡ ስለ እስራኤል ሲል ንግሥናውን ከፍ ከፍ አድርጎለት ነበር።
ዳዊት በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ሚስቶች አገባ፤ ደግሞም ተጨማሪ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
በኢየሩሳሌም ሳለ የተወለዱለት ልጆች ስም ይህ ነው፦ ሻሙአ፣ ሾባብ፣ ናታን፣ ሰለሞን፣
ይብሃር፣ ኤሊሹዓ፣ ኤልፔሌት፣
ኖጋ፣ ኔፌግ፣ ያፊአ፣
ኤሊሻማ፣ ቤኤልያዳ እና ኤሊፌሌት።
ፍልስጤማውያንም በሙሉ ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን ሲሰሙ እሱን ፍለጋ ወጡ። ዳዊትም ይህን በሰማ ጊዜ ሊገጥማቸው ወጣ።
ከዚያም ፍልስጤማውያን መጥተው በረፋይም ሸለቆ ወረራ አካሄዱ።
ዳዊትም “ወጥቼ ፍልስጤማውያንን ልግጠም? በእጄ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህ?” ሲል አምላክን ጠየቀ። ይሖዋም “አዎ ውጣ፤ እኔም በእርግጥ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ” አለው።
በመሆኑም ዳዊት ወደ በዓልጰራጺም ወጥቶ በዚያ መታቸው። ከዚያም ዳዊት “እውነተኛው አምላክ፣ ውኃ እንደጣሰው ግድብ ጠላቶቼን በእጄ ደረማመሳቸው” አለ። ከዚህም የተነሳ ያን ቦታ በዓልጰራጺም ብለው ጠሩት።
ፍልስጤማውያንም አማልክታቸውን በዚያ ጥለው ሸሹ፤ ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረትም በእሳት አቃጠሏቸው።
ከጊዜ በኋላ ፍልስጤማውያን ሸለቆውን እንደገና ወረሩ።
ዳዊት ዳግመኛ አምላክን ጠየቀ፤ ሆኖም እውነተኛው አምላክ እንዲህ አለው፦ “እነሱን ለመግጠም በቀጥታ አትውጣ። ይልቁንም ከኋላቸው ዙርና በባካ ቁጥቋጦዎቹ ፊት መጥተህ ግጠማቸው።
ደግሞም በባካ ቁጥቋጦዎቹ አናት ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማ ጥቃት ሰንዝር፤ ምክንያቱም ይህ በሚሆንበት ጊዜ እውነተኛው አምላክ የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ለመምታት በፊትህ ወጥቷል ማለት ነው።”
ስለዚህ ዳዊት ልክ እውነተኛው አምላክ እንዳዘዘው አደረገ፤ የፍልስጤማውያንንም ሠራዊት ከገባኦን አንስቶ እስከ ጌዜር ድረስ መቷቸው።
የዳዊትም ዝና በአገሩ ሁሉ ተሰማ፤ ይሖዋም ብሔራት ሁሉ እንዲፈሩት አደረገ።
ዳዊት የእስራኤልን መኳንንት ሁሉ ይኸውም የነገዶቹን አለቆች፣ ንጉሡን በሚያገለግሉት ምድቦች ላይ የተሾሙትን አለቆች፣ የሺህ አለቆቹን፣ የመቶ አለቆቹን እንዲሁም በንጉሡና በልጆቹ ንብረትም ሆነ መንጋ ሁሉ ላይ የተሾሙትን አለቆች ከቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ፣ ከኃያላኑና ብቃት ካላቸው ሰዎች ሁሉ ጋር በኢየሩሳሌም ሰበሰባቸው።
ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ተነስቶ እንዲህ አለ፦ “ወንድሞቼና ወገኖቼ ሆይ፣ ስሙኝ። እኔ ለይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ማረፊያና ለአምላካችን የእግር ማሳረፊያ የሚሆን ቤት ለመሥራት ከልቤ ተመኝቼ ነበር፤ ደግሞም ይህን ቤት ለመሥራት ዝግጅት አድርጌ ነበር።
እውነተኛው አምላክ ግን ‘ብዙ ጦርነት ስላካሄድክና ደም ስላፈሰስክ ለስሜ የሚሆን ቤት አትሠራም’ አለኝ።
ይሁንና የእስራኤል አምላክ ይሖዋ በእስራኤል ላይ ለዘላለም ንጉሥ እንድሆን ከአባቴ ቤት ሁሉ መረጠኝ፤ መሪ እንዲሆን የመረጠው ይሁዳን ነውና፤ ከይሁዳም ቤት የአባቴን ቤት፣ ከአባቴም ወንዶች ልጆች መካከል በመላው እስራኤል ላይ እንድነግሥ እኔን መረጠ።
ይሖዋ ከሰጠኝ ብዙ ወንዶች ልጆች መካከል ደግሞ በይሖዋ የንግሥና ዙፋን ላይ ተቀምጦ እስራኤልን እንዲገዛ ልጄን ሰለሞንን መርጦታል።
“እንዲህም አለኝ፦ ‘ቤቴንና ቅጥር ግቢዎቼን የሚሠራው ልጅህ ሰለሞን ነው፤ እሱን እንደ ልጄ አድርጌ መርጬዋለሁና፤ እኔም አባቱ እሆናለሁ።
አሁን እያደረገ እንዳለው ትእዛዛቴንና ድንጋጌዎቼን ሳያወላውል የሚፈጽም ከሆነ ንግሥናውን ለዘላለም አጸናለሁ።’
በመሆኑም የይሖዋ ጉባኤ በሆነው በእስራኤል ሁሉ ፊት፣ አምላካችን እየሰማ ይህን እነግራችኋለሁ፦ መልካሚቱን ምድር እንድትወርሱና ከእናንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆቻችሁ ቋሚ ርስት አድርጋችሁ እንድታወርሱ የአምላካችሁን የይሖዋን ትእዛዛት በሙሉ በጥብቅ ተከተሉ፤ ደግሞም ፈልጉ።
“አንተም ልጄ ሰለሞን ሆይ፣ የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በሙሉ ልብና በደስተኛ ነፍስ አገልግለው፤ ይሖዋ ልብን ሁሉ ይመረምራልና፤ ሐሳብንና ውስጣዊ ዝንባሌን ሁሉ ይረዳል። ብትፈልገው ይገኝልሃል፤ ከተውከው ግን ለዘላለም ይተውሃል።
አሁንም ለመቅደስ የሚሆን ቤት እንድትሠራ ይሖዋ እንደመረጠህ ልብ በል። እንግዲህ ደፋር ሁን፤ ሥራህንም ጀምር።”
ከዚያም ዳዊት የበረንዳውን፣ የመቅደሱን ክፍሎች፣ የግምጃ ቤቶቹን፣ ሰገነት ላይ ያሉትን ክፍሎች፣ የውስጠኛዎቹን ክፍሎችና የስርየት መክደኛው የሚቀመጥበትን ክፍል ንድፍ ለልጁ ለሰለሞን ሰጠው።
ዳዊት በመንፈስ የተገለጠለትን የይሖዋን ቤት ቅጥር ግቢዎች፣ በዙሪያው ያሉትን የመመገቢያ ክፍሎች ሁሉ፣ የእውነተኛውን አምላክ ቤት ግምጃ ቤቶችና የተቀደሱት ነገሮች የሚቀመጡባቸውን ግምጃ ቤቶች ንድፍ ሁሉ ለሰለሞን ሰጠው፤
እንዲሁም የካህናቱንና የሌዋውያኑን ምድብ፣ በይሖዋ ቤት አገልግሎት የሚከናወነውን ሥራ ሁሉና በይሖዋ ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች ሁሉ በተመለከተ መመሪያ ሰጠው፤
በተጨማሪም የወርቁን ይኸውም ለተለያዩ አገልግሎቶች ለሚውሉት ዕቃዎች ሁሉ የሚያስፈልገውን ወርቅ መጠን፣ የብር ዕቃዎቹን ሁሉ መጠንና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉትን ዕቃዎች ሁሉ መጠን አሳወቀው፤
ደግሞም እንደየመቅረዙ አገልግሎት ዓይነት፣ ለወርቅ መቅረዞቹና ለወርቅ መብራቶቻቸው ይኸውም ለተለያዩ ዓይነት መቅረዞችና መብራቶቻቸው የሚያስፈልገውን ወርቅ መጠን እንዲሁም ለብር መቅረዞቹ ማለትም ለእያንዳንዱ መቅረዝና ለመብራቶቹ የሚያስፈልገውን ብር መጠን ገለጸለት፤
በተጨማሪም የሚነባበረው ዳቦ ለሚቀመጥበት ለእያንዳንዱ ጠረጴዛ የሚያስፈልገውን ወርቅ መጠንና ለብር ጠረጴዛዎቹ የሚያስፈልገውን ብር መጠን አሳወቀው፤
ከንጹሕ ወርቅ ለሚሠሩት ሹካዎች፣ ጎድጓዳ ሳህኖችና ማንቆርቆሪያዎች እንዲሁም ለእያንዳንዱ ትንሽ የወርቅ ጎድጓዳ ሳህን የሚያስፈልገውን ወርቅ መጠንና ለእያንዳንዱ ትንሽ የብር ጎድጓዳ ሳህን የሚያስፈልገውን ብር መጠን ገለጸለት።
ደግሞም ለዕጣኑ መሠዊያ የሚያስፈልገውን እንዲሁም ለሠረገላው ምስል ይኸውም ክንፋቸውን ለሚዘረጉትና የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ለሚሸፍኑት የወርቅ ኪሩቦች የሚያስፈልገውን የጠራ ወርቅ መጠን አሳወቀው።
ዳዊትም “የይሖዋ እጅ በእኔ ላይ ነበረ፤ የግንባታ ንድፉንም ዝርዝር በሙሉ በጽሑፍ እንዳሰፍር ማስተዋል ሰጠኝ” አለ።
ከዚያም ዳዊት ልጁን ሰለሞንን እንዲህ አለው፦ “ደፋርና ብርቱ ሁን፤ ሥራህንም ጀምር። አትፍራ ወይም አትሸበር፤ አምላኬ፣ ይሖዋ አምላክ ከአንተ ጋር ነውና። በይሖዋ ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት አስፈላጊ የሆነው ሥራ በሙሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከአንተ ጋር ይሆናል እንጂ አይጥልህም ወይም አይተውህም።
እነሆ፣ በእውነተኛው አምላክ ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት ሁሉ የሚያስፈልጉት የካህናትና የሌዋውያን ምድቦች ተዘጋጅተዋል። ማንኛውንም ዓይነት አገልግሎት ለማከናወን ፈቃደኛ የሆኑና የተካኑ ሠራተኞች አሉልህ፤ መኳንንቱና ሕዝቡም ሁሉ መመሪያህን በሙሉ ይፈጽማሉ።”
ከዚያም ዳዊት “የእውነተኛው አምላክ የይሖዋ ቤት በዚህ ይሆናል፤ ለእስራኤል የሚቃጠል መባ የሚቀርብበት መሠዊያም በዚሁ ይቆማል” አለ።
ዳዊት በእስራኤል ምድር የሚኖሩትን የባዕድ አገር ሰዎች እንዲሰበስቡ አዘዘ፤ የእውነተኛውን አምላክ ቤት ለመገንባት የሚያስፈልጉትንም ድንጋዮች እንዲጠርቡ ድንጋይ ጠራቢዎች አድርጎ መደባቸው።
በተጨማሪም ዳዊት ለመግቢያዎቹ በሮች የሚያስፈልጉ ምስማሮችንና ማጠፊያዎችን ለመሥራት የሚያገለግል ከፍተኛ መጠን ያለው ብረት አዘጋጀ፤ ደግሞም ከብዛቱ የተነሳ ሊመዘን የማይችል መዳብ አከማቸ፤
ከዚህም ሌላ ስፍር ቁጥር የሌለው ከአርዘ ሊባኖስ የተሠራ ሳንቃ አዘጋጀ፤ ሲዶናውያንና ጢሮሳውያን ከአርዘ ሊባኖስ የተዘጋጀ ብዛት ያለው ሳንቃ ለዳዊት አምጥተውለት ነበርና።
ዳዊትም እንዲህ አለ፦ “ልጄ ሰለሞን ገና ወጣት ነው፤ ተሞክሮም የለውም፤ ለይሖዋ የሚሠራው ቤት ደግሞ እጅግ የሚያምር ከመሆኑ የተነሳ ዝናውም ሆነ ውበቱ በመላው ምድር የታወቀ ይሆናል። ስለዚህ የሚያስፈልገውን ነገር አዘጋጅለታለሁ።” በመሆኑም ዳዊት ከመሞቱ በፊት ለሥራው የሚያስፈልጉትን ነገሮች በብዛት አዘጋጀ።
በተጨማሪም ልጁን ሰለሞንን ጠርቶ ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ፣ ቤት እንዲሠራ አዘዘው።
ዳዊት ልጁን ሰለሞንን እንዲህ አለው፦ “እኔ በበኩሌ ለአምላኬ ለይሖዋ ስም፣ ቤት ለመሥራት ከልብ ተመኝቼ ነበር።
ሆኖም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ ‘አንተ እጅግ ብዙ ደም አፍስሰሃል፤ ታላላቅ ጦርነቶችንም አድርገሃል። በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም ስላፈሰስክ አንተ ለስሜ ቤት አትሠራልኝም።
እነሆ፣ የሰላም ሰው የሚሆን ወንድ ልጅ ትወልዳለህ፤ በዙሪያውም ካሉት ጠላቶቹ በሙሉ እረፍት እሰጠዋለሁ፤ ስሙ ሰለሞን ይባላልና፤ በእሱም ዘመን ለእስራኤል ሰላምና ጸጥታ እሰጣለሁ።
ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ እሱ ነው። እሱ ልጄ ይሆናል፤ እኔም አባቱ እሆናለሁ። የንግሥናውን ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።’
“አሁንም ልጄ ሆይ፣ ይሖዋ ከአንተ ጋር ይሁን፤ ስለ አንተም በተናገረው መሠረት ተሳክቶልህ የአምላክህን የይሖዋን ቤት ለመሥራት ያብቃህ።
ብቻ ይሖዋ በእስራኤል ላይ ሲሾምህ የአምላክህን የይሖዋን ሕግ እንድትጠብቅ የማመዛዘንና የማስተዋል ችሎታ ይስጥህ።
ደግሞም ይሖዋ እስራኤልን በተመለከተ ሙሴን ያዘዘውን ሥርዓትና ድንጋጌ በጥንቃቄ ብትጠብቅ ይሳካልሃል። ደፋርና ብርቱ ሁን። አትፍራ ወይም አትሸበር።
እነሆ፣ እኔ ለይሖዋ ቤት 100,000 ታላንት ወርቅና 1,000,000 ታላንት ብር እንዲሁም ከብዛቱ የተነሳ ሊመዘን የማይችል መዳብና ብረት ለማዘጋጀት ብዙ ደክሜአለሁ፤ ደግሞም ሳንቃና ድንጋይ አዘጋጅቻለሁ፤ አንተም በዚያ ላይ ትጨምርበታለህ።
ከአንተም ጋር ብዙ ሠራተኞች፣ ድንጋይ ጠራቢዎች፣ ግንበኞች፣ አናጺዎችና በተለያዩ ሙያዎች የተካኑ ሠራተኞች አሉ።
ወርቁ፣ ብሩ፣ መዳቡና ብረቱ ስፍር ቁጥር የለውም። በል ሥራውን ጀምር፤ ይሖዋም ከአንተ ጋር ይሁን።”
ከዚያም ዳዊት የእስራኤል መኳንንት ሁሉ ልጁን ሰለሞንን እንዲረዱት እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦
“አምላካችሁ ይሖዋ ከእናንተ ጋር አይደለም? በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ ሁሉስ እረፍት አልሰጣችሁም? የምድሪቱን ነዋሪዎች በእጄ አሳልፎ ሰጥቷቸዋልና፤ ምድሪቱም በይሖዋና በሕዝቡ ፊት ተገዝታለች።
አሁንም በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ አምላካችሁን ይሖዋን ጠይቁ፤ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦትና የእውነተኛውን አምላክ የተቀደሱ ዕቃዎች ለይሖዋ ስም ወደሚሠራው ቤት እንድታመጡ የእውነተኛውን አምላክ የይሖዋን መቅደስ መሥራት ጀምሩ።”
ዳዊትም፣ በገዛ ከተማው ለራሱ ቤቶችን መገንባት ቀጠለ፤ ደግሞም የእውነተኛው አምላክ ታቦት የሚቀመጥበትን ስፍራ አዘጋጀ፤ ድንኳንም ተከለ።
በዚያን ጊዜም ዳዊት እንዲህ አለ፦ “ከሌዋውያን በስተቀር ማንም ሰው የእውነተኛውን አምላክ ታቦት መሸከም የለበትም፤ የይሖዋን ታቦት እንዲሸከሙና ምንጊዜም እንዲያገለግሉት ይሖዋ የመረጠው እነሱን ነውና።”
ከዚያም ዳዊት የይሖዋን ታቦት ወዳዘጋጀለት ስፍራ እንዲያመጡ መላውን የእስራኤል ሕዝብ በኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
ዳዊት የአሮንን ዘሮችና ሌዋውያኑን ሰበሰበ፦
ከቀአታውያን መካከል አለቃውን ዑሪኤልንና 120 ወንድሞቹን፣
ከሜራራውያን መካከል አለቃውን አሳያህንና 220 ወንድሞቹን፣
ከጌርሳማውያን መካከል አለቃውን ኢዩኤልንና 130 ወንድሞቹን፣
ከኤሊጻፋን ዘሮች መካከል አለቃውን ሸማያህንና 200 ወንድሞቹን፣
ከኬብሮን ዘሮች መካከል አለቃውን ኤሊዔልንና 80 ወንድሞቹን፣
ከዑዚኤል ዘሮች መካከል አለቃውን አሚናዳብንና 112 ወንድሞቹን ሰበሰበ።
በተጨማሪም ዳዊት ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን እንዲሁም ሌዋውያኑን ዑሪኤልን፣ አሳያህን፣ ኢዩኤልን፣ ሸማያህን፣ ኤሊዔልን እና አሚናዳብን ጠራ፤
እንዲህም አላቸው፦ “እናንተ የሌዋውያን አባቶች ቤት መሪዎች ናችሁ። እናንተና ወንድሞቻችሁ ራሳችሁን ቀድሱ፤ የእስራኤልን አምላክ የይሖዋን ታቦትም ወዳዘጋጀሁለት ስፍራ አምጡ።
በመጀመሪያው ጊዜ ታቦቱን ሳትሸከሙ በመቅረታችሁ የአምላካችን የይሖዋ ቁጣ በእኛ ላይ ነድዶ ነበር፤ ይህ የሆነው ትክክለኛውን መመሪያ ባለመከተላችን ነው።”
ስለዚህ ካህናቱና ሌዋውያኑ የእስራኤልን አምላክ የይሖዋን ታቦት ለማምጣት ራሳቸውን ቀደሱ።
ከዚያም ሌዋውያኑ ሙሴ በይሖዋ ቃል መሠረት እንዳዘዘው የእውነተኛውን አምላክ ታቦት በመሎጊያዎቹ አድርገው በትከሻቸው ላይ ተሸከሙ።
ከዚያም ዳዊት በሙዚቃ መሣሪያዎች ይኸውም በባለ አውታር መሣሪያዎች፣ በበገና እና በሲምባል ታጅበው በደስታ ይዘምሩ ዘንድ ዘማሪ የሆኑትን ወንድሞቻቸውን እንዲሾሙ ለሌዋውያኑ አለቆች ነገራቸው።
በመሆኑም ሌዋውያኑ የኢዩኤልን ልጅ ሄማንን፣ ከወንድሞቹም መካከል የቤራክያህን ልጅ አሳፍን፣ እንዲሁም ወንድሞቻቸው ከሆኑት ከሜራራውያን መካከል የቁሻያህን ልጅ ኤታንን ሾሙ።
ከእነሱ ጋር በሁለተኛው ምድብ ያሉት ወንድሞቻቸው ይገኙ ነበር፤ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፦ ዘካርያስ፣ ቤን፣ ያአዚዔል፣ ሸሚራሞት፣ የሂኤል፣ ዑኒ፣ ኤልያብ፣ በናያህ፣ ማአሴያህ፣ ማቲትያህ፣ ኤሊፌሌሁ፣ ሚቅኔያህ፣ በር ጠባቂዎቹ ኦቤድዔዶም እና የኢዔል።
ዘማሪዎቹ ሄማን፣ አሳፍ እና ኤታን ከመዳብ በተሠራ ሲምባል እንዲጫወቱ ተመደቡ፤
ዘካርያስ፣ አዚዔል፣ ሸሚራሞት፣ የሂኤል፣ ዑኒ፣ ኤልያብ፣ ማአሴያህ እና በናያህ ደግሞ በአላሞት ቅኝት በባለ አውታር መሣሪያዎች ይጫወቱ ነበር፤
ማቲትያህ፣ ኤሊፌሌሁ፣ ሚቅኔያህ፣ ኦቤድዔዶም፣ የኢዔል እና አዛዝያ ደግሞ በሸሚኒት ቅኝት በገና ይጫወቱና የሙዚቀኞች ቡድን መሪ ሆነው ያገለግሉ ነበር።
የሌዋውያን አለቃ የሆነው ኬናንያ ሥራውን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ታቦቱን የማጓጓዙን ሥራ በበላይነት ይከታተል ነበር፤
ቤራክያህ እና ሕልቃና ታቦቱ የተቀመጠበትን ቦታ በር ይጠብቁ ነበር።
ካህናቱ ሸባንያህ፣ ዮሳፍጥ፣ ናትናኤል፣ አማሳይ፣ ዘካርያስ፣ በናያህ እና ኤሊዔዘር በእውነተኛው አምላክ ታቦት ፊት ከፍ ባለ ድምፅ መለከት ይነፉ ነበር፤ ኦቤድዔዶም እና የሂያህ ታቦቱ የተቀመጠበትን ቦታ በር በመጠበቅም ያገለግሉ ነበር።
ከዚያም ዳዊትና የእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲሁም የሺህ አለቆቹ የይሖዋን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከኦቤድዔዶም ቤት በታላቅ ደስታ ለማምጣት ሄዱ።
የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙትን ሌዋውያን፣ እውነተኛው አምላክ ስለረዳቸው ሰባት ወይፈኖችንና ሰባት አውራ በጎችን ሠዉ።
ዳዊት፣ ታቦቱን የተሸከሙት ሌዋውያን ሁሉ፣ ዘማሪዎቹ እንዲሁም ታቦቱን የማጓጓዙ ሥራ ኃላፊና የዘማሪዎቹ አለቃ የሆነው ኬናንያ እጅጌ የሌለው ምርጥ ልብስ ለብሰው ነበር፤ በተጨማሪም ዳዊት ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ ነበር።
መላው የእስራኤል ሕዝብ በቀንደ መለከት፣ በመለከትና በሲምባል ድምፅ ታጅቦ ባለ አውታር መሣሪያዎችንና በገናን ከፍ ባለ ድምፅ እየተጫወተ በእልልታ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት አመጣ።
ይሁንና የይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በመጣ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ወደ ታች ተመለከተች፤ ንጉሥ ዳዊት ሲዘልና በደስታ ሲጨፍር አይታ በልቧ ናቀችው።
የይሁዳ ወንዶች ልጆች ፋሬስ፣ ኤስሮን፣ ካርሚ፣ ሁር እና ሾባል ነበሩ።
የሾባል ልጅ ረአያህ ያሃትን ወለደ፤ ያሃት አሁማይን እና ላሃድን ወለደ። እነዚህ የጾራውያን ቤተሰቦች ናቸው።
የኤጣም አባት ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ ኢይዝራኤል፣ ይሽማ፣ ይድባሽ (የእህታቸውም ስም ሃጽሌልጶኒ ይባል ነበር)፤
ጰኑኤል የጌዶር አባት ነው፤ ኤጼር ደግሞ የሁሻ አባት ነው። እነዚህ የኤፍራታ የበኩር ልጅና የቤተልሔም አባት የሆነው የሁር ወንዶች ልጆች ነበሩ።
የተቆአ አባት አሽሁር፣ ሄላ እና ናዕራ የሚባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት።
ናዕራ አሁዛምን፣ ሄፌርን፣ ተመናይን እና ሃሽታሪን ወለደችለት። እነዚህ የናዕራ ወንዶች ልጆች ናቸው።
የሄላ ወንዶች ልጆች ደግሞ ጸረት፣ ይጽሃር እና ኤትናን ናቸው።
ቆጽ አኑብን እና ጾበባን ወለደ፤ ደግሞም የሃሩም ልጅ የሆነው የአሃርሔል ቤተሰቦች የተገኙት ከእሱ ነው።
ያቤጽ ከወንድሞቹ ይበልጥ የተከበረ ሰው ነበር፤ እናቱም “በሥቃይ ወለድኩት” ስትል ያቤጽ የሚል ስም አወጣችለት።