text
stringlengths
4
267
እነዚህ ንጉሡ በመላው ይሁዳ በተመሸጉ ከተሞች ውስጥ ካስቀመጣቸው ሌላ ንጉሡን ያገለግሉ የነበሩ ሰዎች ናቸው።
ከዚህ በኋላ በዚያ የተገኙት እስራኤላውያን በሙሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው በመላው ይሁዳና ቢንያም እንዲሁም በኤፍሬምና በምናሴ የነበሩትን የማምለኪያ ዓምዶች ሰባበሩ፤ የማምለኪያ ግንዶቹን ቆረጡ፤ ከፍ ያሉትንም የማምለኪያ ቦታዎችና መሠዊያዎቹን አፈራረሱ፤ ምንም ያስቀሩት ነገር አልነበረም፤ ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን በሙሉ ወደየከተሞቻቸው፣ እያንዳንዳቸውም ወደየርስታቸው ተመለሱ።
ከዚያም ሕዝቅያስ ካህናቱን በየምድባቸው፣ ሌዋውያኑንም በየምድባቸው ሾማቸው፤ እያንዳንዱን ካህንና ሌዋዊ በተሰጠው ሥራ መሠረት ደለደለ። እነሱም የሚቃጠለውን መባና የኅብረት መሥዋዕቶቹን ያቀርባሉ፣ ያገለግላሉ እንዲሁም በይሖዋ ቤተ መቅደስ ዙሪያ ባሉት የግቢዎቹ በሮች ለእሱ ምስጋናና ውዳሴ ያቀርባሉ።
በይሖዋ ሕግ ላይ በተጻፈው መሠረት ጠዋትና ማታ የሚቀርበውን መባ እንዲሁም በየሰንበቱ፣ በየወር መባቻውና በበዓላት ወቅት የሚቀርቡትን የሚቃጠሉ መባዎች ጨምሮ ለሚቃጠሉት መባዎች እንዲውል ከንጉሡ ንብረት ላይ የተወሰነ ድርሻ ይሰጥ ነበር።
በተጨማሪም ሕዝቅያስ የይሖዋን ሕግ በጥብቅ መከተል እንዲችሉ በኢየሩሳሌም የሚኖረው ሕዝብ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ ተገቢውን ድርሻ እንዲሰጥ አዘዘ።
ትእዛዙ እንደወጣ እስራኤላውያን የእህሉን፣ የአዲሱን የወይን ጠጅ፣ የዘይቱን፣ የማሩንና የእርሻውን ፍሬ ሁሉ በኩራት በብዛት ሰጡ፤ ከእያንዳንዱም ነገር ላይ አንድ አሥረኛውን አትረፍርፈው አመጡ።
በይሁዳ ከተሞች ይኖሩ የነበሩት የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብም ከከብቶቻቸውና ከበጎቻቸው አንድ አሥረኛውን እንዲሁም ለአምላካቸው ለይሖዋ ከተለዩት ቅዱስ የሆኑ ነገሮች ላይ አንድ አሥረኛውን አመጡ። ያመጡትንም ብዙ ቦታ ላይ ቆለሉት።
በሦስተኛው ወር ያመጡትን መዋጮ መከመር የጀመሩ ሲሆን በሰባተኛው ወር አጠናቀቁ።
ሕዝቅያስና መኳንንቱ መጥተው ክምሩን ባዩ ጊዜ ይሖዋን አወደሱ፤ ሕዝቡን እስራኤልንም ባረኩ።
ሕዝቅያስ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ስለ ክምሩ ሲጠይቃቸው
ከሳዶቅ ቤት የሆነው የካህናት አለቃው አዛርያስ እንዲህ አለው፦ “መዋጮውን ወደ ይሖዋ ቤት ማምጣት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ሕዝቡ እስኪጠግብ ድረስ ሲበላ ቆይቷል፤ ገና ያልተነካ ብዙ ነገር አለ፤ ይሖዋ ሕዝቡን ስለባረከ ይህን ያህል ብዛት ያለው ነገር ሊተርፍ ችሏል።”
በዚህ ጊዜ ሕዝቅያስ በይሖዋ ቤት ማከማቻ ክፍሎች እንዲያዘጋጁ አዘዘ፤ እነሱም አዘጋጁ።
ከዚያም መዋጮውን፣ አንድ አሥረኛውንና ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች በታማኝነት ማምጣታቸውን ቀጠሉ፤ ሌዋዊው ኮናንያ የእነዚህ ሁሉ ነገሮች ተቆጣጣሪ ሆኖ ተሹሞ የነበረ ሲሆን ወንድሙ ሺምአይ ደግሞ የእሱ ምክትል ነበር።
የሂኤል፣ አዛዝያ፣ ናሃት፣ አሳሄል፣ የሪሞት፣ ዮዛባድ፣ ኤሊዔል፣ ይስማክያ፣ ማሃት እና በናያህ በንጉሥ ሕዝቅያስ ትእዛዝ ኮናንያን እና ወንድሙን ሺምአይን የሚረዱ ሹሞች ነበሩ፤ አዛርያስም የእውነተኛው አምላክ ቤት ተቆጣጣሪ ነበር።
የምሥራቁ በር ጠባቂ የሆነው ሌዋዊው የይምናህ ልጅ ቆረ ለእውነተኛው አምላክ በበጎ ፈቃድ የሚቀርቡትን መባዎች ይቆጣጠር ነበር፤ ደግሞም ለይሖዋ የተሰጠውን መዋጮና እጅግ ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች ያከፋፍል ነበር።
በእሱም አመራር ሥር ኤደን፣ ሚንያሚን፣ የሹዋ፣ ሸማያህ፣ አማርያህ እና ሸካንያህ የነበሩ ሲሆን በየምድቦቹ ውስጥ ላሉት ወንድሞቻቸው፣ ለትልቁም ሆነ ለትንሹ ድርሻቸውን እኩል ለማከፋፈል በካህናቱ ከተሞች ታማኝነት በሚጠይቅ ቦታ ላይ ተሹመው ነበር።
ይህም ስማቸው በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ ለሰፈሩት ሦስት ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆናቸው ወንዶች የሚከፋፈለውን ሳይጨምር ነው፤ እነሱም በይሖዋ ቤት ለማገልገል በየዕለቱ ይመጡና እንደየምድባቸው ያሉባቸውን ኃላፊነቶች ይፈጽሙ ነበር።
ካህናቱ፣ 20 ዓመትና ከዚያ በላይ እንደሆናቸው ሌዋውያን ሁሉ በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ የሰፈሩት በየአባቶቻቸው ቤት እንደየምድብ ሥራቸው ነበር።
የትውልድ ሐረግ መዝገቡ ልጆቻቸውን፣ ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በሙሉ፣ መላውን የሌዋውያን ማኅበረሰብ ይጨምራል፤ እነሱ በተሾሙበት ታማኝነት የሚጠይቅ ቦታ የተነሳ ቅዱስ ለሆነው ነገር ራሳቸውን ቀድሰዋል፤
በተጨማሪም መዝገቡ ላይ በከተሞቻቸው ዙሪያ ባሉ የግጦሽ መሬቶች ላይ የሚኖሩት የአሮን ዘሮች የሆኑት ካህናትም ይገኛሉ። በሁሉም ከተሞች ውስጥ በካህናት ቤተሰብ ውስጥ ላሉት ወንዶች ሁሉና በሌዋውያን የትውልድ ሐረግ መዝገብ ላይ ለተጻፉት በሙሉ እንዲያከፋፍሉ በስም ተጠቅሰው ኃላፊነት የተሰጣቸው ወንዶች ነበሩ።
ሕዝቅያስ በመላው ይሁዳ ይህን አደረገ፤ በአምላኩ በይሖዋም ፊት ጥሩና ትክክል የሆነውን አደረገ፤ ለእሱም ታማኝ ነበር።
ከእውነተኛው አምላክ ቤት አገልግሎት ጋርም ሆነ ከሕጉና ከትእዛዙ ጋር በተያያዘ አምላኩን ይፈልግ ዘንድ የጀመረውን ሥራ ሁሉ፣ በሙሉ ልቡ አከናወነ፤ ደግሞም ተሳካለት።
ከዚያም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤቱ በደህና ተመለሰ።
ባለ ራእዩ የሃናኒ ልጅ ኢዩ ከንጉሥ ኢዮሳፍጥ ጋር ለመገናኘት ሄደ፤ እንዲህም አለው፦ “ለክፉ ሰው እርዳታ መስጠት ይገባሃል? ይሖዋን የሚጠሉትንስ መውደድ ይገባሃል? በዚህ ምክንያት ይሖዋ በአንተ ላይ ተቆጥቷል።
ይሁንና የማምለኪያ ግንዶቹን ከምድሪቱ ስላስወገድክና እውነተኛውን አምላክ ለመፈለግ ልብህን ስላዘጋጀህ መልካም ነገር ተገኝቶብሃል።”
ኢዮሳፍጥ በኢየሩሳሌም መኖሩን ቀጠለ፤ ወደ አባቶቻቸው አምላክ ወደ ይሖዋ ይመልሳቸውም ዘንድ ከቤርሳቤህ አንስቶ እስከ ተራራማው የኤፍሬም ምድር ድረስ ወዳለው ሕዝብ ዳግመኛ ወጣ።
በተጨማሪም በመላ ምድሪቱ ይኸውም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ፣ በእያንዳንዱ ከተማ ፈራጆችን መደበ።
ፈራጆቹንም እንዲህ አላቸው፦ “የምትፈርዱት ለሰው ሳይሆን ለይሖዋ ስለሆነ የምታደርጉትን ነገር በጥንቃቄ አከናውኑ፤ እሱም በምትፈርዱበት ጊዜ ከእናንተ ጋር ነው።
አሁንም ይሖዋን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን። በአምላካችን በይሖዋ ዘንድ ፍትሕ ማዛባት፣ አድልዎ ወይም ጉቦ መቀበል ስለሌለ የምታደርጉትን ነገር በጥንቃቄ አከናውኑ።”
ኢዮሳፍጥ በኢየሩሳሌምም የተወሰኑ ሌዋውያንንና ካህናትን እንዲሁም ከእስራኤል የአባቶች ቤት መሪዎች መካከል አንዳንዶቹን ፈራጆች ሆነው ይሖዋን እንዲያገለግሉና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ሙግት እንዲቋጩ መደበ።
እንዲህም ሲል አዘዛቸው፦ “ይሖዋን በመፍራት በታማኝነትና በሙሉ ልብ ይህን ልታደርጉ ይገባል፦
በየከተሞቻቸው የሚኖሩት ወንድሞቻችሁ ከደም መፋሰስ ጋር የተያያዘ ክስ አሊያም ከሕግ፣ ከትእዛዝ፣ ከሥርዓት ወይም ከድንጋጌዎች ጋር የተያያዘ ጥያቄ ይዘው በሚመጡበት ጊዜ ሁሉ በይሖዋ ፊት በደለኛ እንዳይሆኑ ልታስጠነቅቋቸው ይገባል፤ ይህ ካልሆነ ግን በእናንተም ሆነ በወንድሞቻችሁ ላይ ቁጣው ይመጣል። በደለኛ እንዳትሆኑ ይህን ልታደርጉ ይገባል።
እነሆ፣ የይሖዋ በሆነው ነገር ሁሉ ላይ በእናንተ ላይ የተሾመው የካህናቱ አለቃ አማርያህ አለ። የእስማኤል ልጅ ዘባድያህ ከንጉሡ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ሁሉ የይሁዳ ቤት መሪ ነው። ሌዋውያኑ ደግሞ አለቆች ሆነው ያገለግሏችኋል። በርቱ፤ ሥራችሁንም በትጋት አከናውኑ፤ ይሖዋም መልካም የሆነውን ነገር ከሚያደርጉት ጋር ይሁን።”
ምናሴ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 12 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ 55 ዓመት ገዛ።
እሱም ይሖዋ ከእስራኤል ሕዝብ ፊት ያባረራቸው ብሔራት ይፈጽሟቸው የነበሩትን አስጸያፊ ልማዶች በመከተል በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።
አባቱ ሕዝቅያስ አፍርሷቸው የነበሩትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች መልሶ ገነባ፣ ለባአል አማልክት መሠዊያዎችን አቆመ፣ የማምለኪያ ግንዶች ሠራ እንዲሁም ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ ሰገደ፤ እነሱንም አገለገለ።
በተጨማሪም ይሖዋ “ኢየሩሳሌም ለዘላለም በስሜ ትጠራለች” ብሎ በተናገረለት በይሖዋ ቤት ውስጥ መሠዊያዎችን ሠራ።
ደግሞም በይሖዋ ቤት በሚገኙት በሁለቱ ግቢዎች ውስጥ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ መሠዊያዎችን ሠራ።
በሂኖም ልጅ ሸለቆም የገዛ ልጆቹን ለእሳት አሳልፎ ሰጠ፤ አስማተኛ፣ ሟርተኛና መተተኛ ሆነ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ቀጠረ። ይሖዋን ያስቆጣው ዘንድ በእሱ ፊት በጣም ብዙ መጥፎ ነገሮችን ሠራ።
ምናሴም የሠራውን የተቀረጸ ምስል አምላክ ለዳዊትና ለልጁ ለሰለሞን እንዲህ ብሎ በተናገረለት በእውነተኛው አምላክ ቤት ውስጥ አስቀመጠው፦ “በዚህ ቤትና ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ በመረጥኳት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘለቄታው አኖራለሁ።
እነሱ በሙሴ በኩል የሰጠኋቸውን ሕግ ሁሉ እንዲሁም ሥርዓቶቹንና ድንጋጌዎቹን በጥንቃቄ ይጠብቁ እንጂ የእስራኤላውያን እግር ለአባቶቻቸው ከሰጠሁት ምድር ዳግመኛ እንዲወጣ አላደርግም።”
ምናሴም ይሖዋ ከእስራኤላውያን ፊት ካጠፋቸው ብሔራት የባሰ ክፉ ነገር እንዲሠሩ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች አሳተ።
ይሖዋ ለምናሴና ለሕዝቡ በተደጋጋሚ ቢናገርም እነሱ ለመስማት ፈቃደኛ አልሆኑም።
ስለዚህ ይሖዋ የአሦርን ንጉሥ ሠራዊት አለቆች አመጣባቸው፤ እነሱም ምናሴን በመንጠቆ ያዙት፤ ከመዳብ በተሠሩ ሁለት የእግር ብረቶች አስረው ወደ ባቢሎን ወሰዱት።
በተጨነቀም ጊዜ ሞገስ እንዲያሳየው አምላኩን ይሖዋን ለመነ፤ በአባቶቹም አምላክ ፊት ራሱን እጅግ አዋረደ።
ወደ እሱ አጥብቆ ጸለየ፤ እሱም ተለመነው፤ በእሱ ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ያቀረበውንም ልመና ሰማው፤ ወደ ኢየሩሳሌም፣ ወደ ንግሥናው መለሰው። ከዚያም ምናሴ፣ ይሖዋ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ አወቀ።
ከዚህ በኋላ በሸለቆው ውስጥ ከሚገኘው ከግዮን በስተ ምዕራብ አንስቶ እስከ ዓሣ በር ድረስ ለዳዊት ከተማ በውጭ በኩል ቅጥር ሠራ። ቅጥሩ ከዚያ ተነስቶ ከተማዋን በመዞር እስከ ኦፌል የሚደርስ ሲሆን እጅግ ከፍ አድርጎ ሠራው። በተጨማሪም በተመሸጉ የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ የጦር አለቆች ሾመ።
ከዚያም ባዕዳን አማልክቱንና የጣዖቱን ምስል ከይሖዋ ቤት አስወገደ፤ ደግሞም በይሖዋ ቤት ተራራ ላይና በኢየሩሳሌም የሠራቸውን መሠዊያዎች ሁሉ አፍርሶ ከከተማዋ ውጭ እንዲጣሉ አደረገ።
በተጨማሪም የይሖዋን መሠዊያ አድሶ በላዩ ላይ የኅብረት መሥዋዕቶችና የምስጋና መሥዋዕቶች ያቀርብ ጀመር፤ የይሁዳም ሰዎች የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን እንዲያገለግሉ አዘዘ።
ያም ሆኖ ሕዝቡ ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎቹ ላይ መሠዋታቸውን አልተዉም፤ የሚሠዉት ግን ለአምላካቸው ለይሖዋ ነበር።
የቀረው የምናሴ ታሪክ፣ ለአምላኩ ያቀረበው ጸሎትና በእስራኤል አምላክ በይሖዋ ስም ያናገሩት ባለ ራእዮች ቃል ስለ እስራኤል ነገሥታት በተጻፈው ታሪክ ውስጥ ተመዝግበዋል።
በተጨማሪም ያቀረበው ጸሎት፣ ልመናው እንዴት እንደተሰማለት፣ የሠራው ኃጢአት ሁሉና ታማኝነት በማጉደል የፈጸመው ድርጊት በባለ ራእዮቹ ዘገባዎች ውስጥ ተካተዋል፤ ደግሞም ራሱን ከማዋረዱ በፊት ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች የሠራባቸው እንዲሁም የማምለኪያ ግንዶችና የተቀረጹ ምስሎች ያቆመባቸው ስፍራዎች በእነዚህ ዘገባዎች ላይ ተጽፈዋል።
በመጨረሻም ምናሴ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ እነሱም በቤቱ ቀበሩት፤ ልጁም አምዖን በእሱ ምትክ ነገሠ።
አምዖን በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 22 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሁለት ዓመት ገዛ።
እሱም አባቱ ምናሴ እንዳደረገው በይሖዋ ፊት መጥፎ ነገር አደረገ፤ አምዖን አባቱ ምናሴ ለሠራቸው የተቀረጹ ምስሎች ሁሉ ሠዋ፤ ያገለግላቸውም ነበር።
ይሁንና አባቱ ምናሴ ራሱን እንዳዋረደ፣ በይሖዋ ፊት ራሱን አላዋረደም፤ ይልቁንም በበደል ላይ በደል እየጨመረ ሄደ።
ከጊዜ በኋላም አገልጋዮቹ በእሱ ላይ አሲረው በገዛ ቤቱ ውስጥ ገደሉት።
ሆኖም የምድሪቱ ሕዝብ በንጉሥ አምዖን ላይ ያሴሩትን ሁሉ ገደላቸው፤ በእሱም ምትክ ልጁን ኢዮስያስን አነገሠው።
ሮብዓም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከእስራኤል ጋር ተዋግተው መንግሥቱን ለሮብዓም እንዲያስመልሱ ከይሁዳ ቤትና ከቢንያም ነገድ የተውጣጡ 180,000 የሠለጠኑ ተዋጊዎች ወዲያውኑ ሰበሰበ።
ከዚያም የይሖዋ ቃል የእውነተኛው አምላክ ሰው ወደሆነው ወደ ሸማያህ እንዲህ ሲል መጣ፦
“ለይሁዳ ንጉሥ ለሰለሞን ልጅ ለሮብዓም እንዲሁም በይሁዳና በቢንያም ላሉት እስራኤላውያን ሁሉ እንዲህ ብለህ ተናገር፦
‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ከወንድሞቻችሁ ጋር ለመዋጋት አትውጡ። ይህ እንዲሆን ያደረግኩት እኔ ስለሆንኩ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ።”’” ስለዚህ የይሖዋን ቃል ሰምተው ተመለሱ፤ በኢዮርብዓምም ላይ አልዘመቱም።
ሮብዓም መኖሪያውን በኢየሩሳሌም አድርጎ በይሁዳ የተመሸጉ ከተሞችን ገነባ።
ቤተልሔምን፣ ኤጣምን፣ ተቆአን፣
ቤትጹርን፣ ሶኮን፣ አዱላምን፣
ጌትን፣ ማሬሻህን፣ ዚፍን፣
አዶራይምን፣ ለኪሶን፣ አዜቃን፣
ጾራን፣ አይሎንንና ኬብሮንን ገነባ፤ እነዚህ በይሁዳና በቢንያም የነበሩ የተመሸጉ ከተሞች ናቸው።
በተጨማሪም የተመሸጉትን ከተሞች አጠናከረ፤ በከተሞቹም ላይ አዛዦችን ሾመ፤ በእነዚህ ከተሞች ምግብ፣ ዘይትና የወይን ጠጅ አከማቸ፤
በከተሞቹም ሁሉ ትላልቅ ጋሻዎችና ጦር አስቀመጠ፤ ከተሞቹንም እጅግ አጠናከራቸው። ይሁዳንና ቢንያምንም መግዛቱን ቀጠለ።
በመላው እስራኤል ያሉት ካህናትና ሌዋውያንም የነበሩበትን ክልል በሙሉ ለቀው በመሄድ ከእሱ ጎን ቆሙ።
ሌዋውያኑ የይሖዋ ካህናት ሆነው እንዳያገለግሉ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አባረዋቸው ስለነበር የግጦሽ መሬታቸውንና ርስታቸውን ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ነበር።
በዚህ ጊዜ ኢዮርብዓም ከፍ ላሉት የማምለኪያ ቦታዎች፣ ፍየል ለሚመስሉት አጋንንትና ለሠራቸው የጥጃ ምስሎች የራሱን ካህናት ሾመ።
የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን ለመፈለግ ከልባቸው ቆርጠው የተነሱ ከሁሉም የእስራኤል ነገዶች የተውጣጡ ሰዎች ለአባቶቻቸው አምላክ ለይሖዋ መሥዋዕት ለማቅረብ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ለሦስት ዓመት በዳዊትና በሰለሞን መንገድ ይመላለሱ ስለነበር በእነዚህ ሦስት ዓመታት የይሁዳን መንግሥት አጠናከሩ፤ ደግሞም ለሰለሞን ልጅ ለሮብዓም ድጋፍ ሰጡ።
ከዚያም ሮብዓም የዳዊት ልጅ የሆነውን የየሪሞትን ሴት ልጅ ማሃላትን አገባ። ማሃላት የእሴይ ልጅ፣ የኤልያብ ሴት ልጅ የሆነችው የአቢሃይል ልጅ ነበረች።
ከጊዜ በኋላም የኡሽ፣ ሸማርያህ እና ዛሃም የተባሉ ወንዶች ልጆች ወለደችለት።
ከእሷ በኋላ የአቢሴሎም የልጅ ልጅ የሆነችውን ማአካን አገባ። እሷም አቢያህን፣ አታይን፣ ዚዛን እና ሸሎሚትን ወለደችለት።
ሮብዓም የአቢሴሎም የልጅ ልጅ የሆነችውን ማአካን ከሌሎቹ ሚስቶቹና ቁባቶቹ ሁሉ አስበልጦ ይወዳት ነበር፤ እሱም 18 ሚስቶችና 60 ቁባቶች ነበሩት፤ ደግሞም 28 ወንዶች ልጆችና 60 ሴቶች ልጆች ወለደ።
ሮብዓምም የማአካን ልጅ አቢያህን ሊያነግሠው ስለፈለገ በወንድሞቹ ላይ ራስና መሪ አድርጎ ሾመው።
ይሁን እንጂ ማስተዋል የታከለበት እርምጃ በመውሰድ ከወንዶች ልጆቹ መካከል አንዳንዶቹን በይሁዳና በቢንያም ምድር ሁሉ ወደሚገኙት ወደተመሸጉት ከተሞች ሁሉ ላካቸው፤ የሚያስፈልጓቸውንም ነገሮች በብዛት ሰጣቸው፤ ብዙ ሚስቶችም አጋባቸው።
ከዚያም የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ የ16 ዓመት ልጅ የነበረውን ዖዝያን ወስደው በአባቱ በአሜስያስ ምትክ አነገሡት።
እሱም፣ ንጉሡ ከአባቶቹ ጋር ካንቀላፋ በኋላ ኤሎትን መልሶ በመገንባት ወደ ይሁዳ መለሳት።
ዖዝያ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 16 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለ52 ዓመት ገዛ። እናቱ ይኮልያ የተባለች የኢየሩሳሌም ተወላጅ ነበረች።
እሱም አባቱ አሜስያስ እንዳደረገው ሁሉ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ።
እውነተኛውን አምላክ መፍራት ባስተማረው በዘካርያስ ዘመን አምላክን ይፈልግ ነበር። ይሖዋን ይፈልግ በነበረበት ዘመን እውነተኛው አምላክ አበለጸገው።
እሱም ወጥቶ ከፍልስጤማውያን ጋር በመዋጋት የጌትን ቅጥር፣ የያብነህን ቅጥርና የአሽዶድን ቅጥር አፈረሰ። ከዚያም በአሽዶድና በፍልስጤማውያን ክልል ከተሞችን ገነባ።
እውነተኛው አምላክ በፍልስጤማውያን ላይ፣ በጉርባዓል በሚኖሩት ዓረቦች ላይ እንዲሁም በመኡኒም ላይ ድል እንዲቀዳጅ ረዳው።
አሞናውያን ለዖዝያ ግብር ይገብሩለት ጀመር። እጅግ እየበረታ ስለሄደም ዝናው እስከ ግብፅ ድረስ ናኘ።
በተጨማሪም ዖዝያ በኢየሩሳሌም በማዕዘን በር፣ በሸለቆ በርና የቅጥሩ ማጠናከሪያ በሚገኝበት ስፍራ ጠንካራ ማማዎችን ሠራ።
ከዚህም ሌላ በምድረ በዳው ማማዎችን ገነባ፤ ብዙ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓዶችንም ቆፈረ (ብዙ ከብቶች ነበሩትና)፤ በሸፌላና በሜዳውም ላይ እንዲሁ አደረገ። ግብርና ይወድ ስለነበር በተራሮቹ ላይና በቀርሜሎስ፣ ገበሬዎችና የወይን አትክልት ሠራተኞች ነበሩት።
በተጨማሪም ዖዝያ ለውጊያ ዝግጁ የሆነ ሠራዊት ነበረው። በቡድን በቡድን ተደራጅተው ለጦርነት ይወጡ ነበር። እነዚህ ሰዎች ከንጉሡ መኳንንት አንዱ በሆነው በሃናንያህ አመራር ሥር ሆነው በሚያገለግሉት በጸሐፊው የኢዔል እና በአለቃው ማአሴያህ አማካኝነት ተቆጥረው ተመዘገቡ።
በእነዚህ ኃያላን ተዋጊዎች ላይ የተሾሙት የአባቶች ቤት መሪዎች አጠቃላይ ቁጥር 2,600 ነበር።
በእነሱ አመራር ሥር 307,500 ወታደሮችን ያቀፈ ሠራዊት ነበር፤ ይህም ንጉሡ በጠላት ላይ በሚያደርገው ዘመቻ ድጋፍ የሚሰጡ ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ሰዎችን የያዘ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል ነው።
ዖዝያ መላው ሠራዊት ጋሻ፣ ጦር፣ የራስ ቁር፣ ጥሩር፣ ቀስትና የወንጭፍ ድንጋይ እንዲታጠቅ አደረገ።
በተጨማሪም ባለሙያዎች ባወጡት ንድፍ የተሠሩ የጦር መሣሪያዎችን በኢየሩሳሌም አዘጋጀ፤ መሣሪያዎቹ በየማማውና በቅጥሩ ማዕዘናት ላይ የተተከሉ ሲሆን ቀስትና ትላልቅ ድንጋዮች ለማስወንጨፍ ያገለግሉ ነበር። ዖዝያ ከፍተኛ እርዳታ በማግኘቱና እየበረታ በመሄዱ ዝናው በሩቅ ቦታ ሁሉ ተሰማ።
ይሁን እንጂ ዖዝያ በበረታ ጊዜ ለጥፋት እስኪዳረግ ድረስ ልቡ ታበየ፤ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ለማጠን ወደ ይሖዋ ቤተ መቅደስ በመግባት በአምላኩ በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ፈጸመ።
ወዲያውኑም ካህኑ አዛርያስና ደፋር የሆኑ ሌሎች 80 የይሖዋ ካህናት ተከትለውት ገቡ።
ከዚያም ንጉሥ ዖዝያን ፊት ለፊት በመጋፈጥ እንዲህ አሉት፦ “ዖዝያ ሆይ፣ አንተ ለይሖዋ ዕጣን ማጠንህ ተገቢ አይደለም! ዕጣን ማጠን ያለባቸው ካህናቱ ብቻ ናቸው፤ እነሱ የተቀደሱ የአሮን ዘሮች ናቸውና። ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ስለፈጸምክ ከመቅደሱ ውጣ፤ እንዲህ ማድረግህ በይሖዋ አምላክ ዘንድ ምንም ዓይነት ክብር አያስገኝልህም።”
ዕጣን ለማጠን በእጁ ጥና ይዞ የነበረው ዖዝያ ግን እጅግ ተቆጣ፤ ካህናቱን እየተቆጣ ሳለም በይሖዋ ቤት በዕጣን መሠዊያው አጠገብ ካህናቱ ባሉበት ግንባሩ ላይ የሥጋ ደዌ ወጣበት።