text stringlengths 4 267 |
|---|
ሥራ ፈት የሆኑ የማይረቡ ሰዎችም ወደ እሱ ተሰበሰቡ። የሰለሞን ልጅ ሮብዓም ለጋ ወጣት በነበረበትና ልቡ በቀላሉ ይሸበር በነበረበት ጊዜም በእሱ ላይ በረቱበት፤ ሊቋቋማቸውም አልቻለም። |
“አሁንም እናንተ እጅግ ብዙ ስለሆናችሁና ኢዮርብዓም አማልክት አድርጎ የሠራላችሁን የወርቅ ጥጃዎች ስለያዛችሁ በዳዊት ልጆች እጅ ያለውን የይሖዋን መንግሥት መቋቋም እንደምትችሉ ተሰምቷችኋል። |
የአሮን ዘሮች የሆኑትን የይሖዋን ካህናትና ሌዋውያንን አላባረራችሁም? ደግሞስ እንደ ሌሎቹ አገሮች ሕዝቦች የራሳችሁን ካህናት አልሾማችሁም? አንድ ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ይዞ የሚመጣ ማንኛውም ሰው አማልክት ላልሆኑት ጣዖቶች ካህን መሆን ይችላል። |
እኛ ግን አምላካችን ይሖዋ ነው፤ እሱንም አልተውነውም፤ የአሮን ዘሮች የሆኑት ካህናት ይሖዋን እያገለገሉ ሲሆን ሌዋውያንም በሥራው ይረዷቸዋል። |
በየጠዋቱና በየማታው ለይሖዋ የሚቃጠል መባ እንዲሁም ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን ያቀርባሉ፤ የሚነባበረውም ዳቦ ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው ጠረጴዛ ላይ ይቀመጣል፤ የወርቁን መቅረዝና መብራቶቹን በየማታው ያበራሉ፤ ምክንያቱም እኛ በአምላካችን በይሖዋ ፊት ያለብንን ኃላፊነት እየተወጣን ነው፤ እናንተ ግን እሱን ትታችሁታል። |
እነሆ፣ እውነተኛው አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤ እሱም በእናንተ ላይ ጦርነት መታወጁን የሚያመለክት ድምፅ ለማሰማት መለከት ከያዙ ካህናቱ ጋር ሆኖ እየመራን ነው። የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ስለማይሳካላችሁ ከአባቶቻችሁ አምላክ ከይሖዋ ጋር አትዋጉ።” |
ኢዮርብዓም ግን ከበስተ ጀርባቸው አድፍጠው ጥቃት የሚሰነዝሩ ተዋጊዎችን ላከ፤ ዋናው ሠራዊት ከፊት፣ ያደፈጡትም ተዋጊዎች ከበስተ ጀርባ ይሁዳን እንዲገጥሙ አደረገ። |
የይሁዳ ሰዎች ዙሪያቸውን ሲመለከቱ ከፊትና ከኋላ መከበባቸውን አዩ። በዚህ ጊዜ ወደ ይሖዋ ጮኹ፤ ካህናቱም መለከቶቹን በኃይል ነፉ። |
የይሁዳ ሰዎች ቀረርቶ አሰሙ፤ የይሁዳ ሰዎች ቀረርቶ ባሰሙ ጊዜም እውነተኛው አምላክ ኢዮርብዓምንና እስራኤላውያንን ሁሉ በአቢያህና በይሁዳ ፊት ድል አደረጋቸው። |
እስራኤላውያን ከይሁዳ ፊት ሸሹ፤ አምላክም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። |
አቢያህና ሕዝቡም ፈጇቸው፤ ከእስራኤላውያንም መካከል 500,000 የሠለጠኑ ተዋጊዎች ተገደሉ። |
በዚህ ጊዜ የእስራኤል ሰዎች ተዋረዱ፤ የይሁዳ ሰዎች ግን በአባቶቻቸው አምላክ በይሖዋ በመታመናቸው ድል ነሱ። |
አቢያህ ኢዮርብዓምን አሳደደው፤ ከተሞቹን ይኸውም ቤቴልንና በሥሯ ያሉትን ከተሞች፣ የሻናንና በሥሯ ያሉትን ከተሞች እንዲሁም ኤፍራይንንና በሥሯ ያሉትን ከተሞች ወሰደበት። |
ኢዮርብዓምም በአቢያህ ዘመን እንደገና ሊያንሰራራ አልቻለም፤ ከዚያም ይሖዋ ስለቀሰፈው ሞተ። |
አቢያህ ግን እየበረታ ሄደ። ከጊዜ በኋላም 14 ሚስቶችን አግብቶ 22 ወንዶች ልጆችና 16 ሴቶች ልጆች ወለደ። |
የቀረው የአቢያህ ታሪክ፣ የሠራውና የተናገረው ነገር ሁሉ በነቢዩ ኢዶ ጽሑፎች ላይ ሰፍሯል። |
በመጨረሻም ኢዮሳፍጥ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ በእሱም ምትክ ልጁ ኢዮራም ነገሠ። |
የኢዮሳፍጥ ልጆች የሆኑት ወንድሞቹ አዛርያስ፣ የሂኤል፣ ዘካርያስ፣ አዛርያስ፣ ሚካኤል እና ሰፋጥያህ ነበሩ፤ እነዚህ ሁሉ የእስራኤል ንጉሥ የኢዮሳፍጥ ወንዶች ልጆች ናቸው። |
አባታቸውም ብዙ ብር፣ ወርቅና ውድ የሆኑ ነገሮች ስጦታ አድርጎ የሰጣቸው ከመሆኑም በላይ በይሁዳ የተመሸጉ ከተሞችን ሰጣቸው፤ መንግሥቱን ግን የበኩር ልጁ ለነበረው ለኢዮራም ሰጠው። |
ኢዮራም በአባቱ መንግሥት ላይ ተደላድሎ በተቀመጠ ጊዜ ወንድሞቹን በሙሉ እንዲሁም ከእስራኤል መኳንንት መካከል የተወሰኑትን በሰይፍ በመግደል ሥልጣኑን አጠናከረ። |
ኢዮራም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 32 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ስምንት ዓመት ገዛ። |
የአክዓብን ልጅ አግብቶ ስለነበር ከአክዓብ ቤት የሆኑት እንዳደረጉት ሁሉ እሱም በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ በይሖዋም ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ። |
ሆኖም ይሖዋ ከዳዊት ጋር ለገባው ቃል ኪዳን ሲል የዳዊትን ቤት ማጥፋት አልፈለገም፤ ምክንያቱም ለእሱና ለልጆቹ ለሁልጊዜ የሚኖር መብራት እንደሚሰጥ ቃል ገብቶ ነበር። |
በእሱ ዘመን ኤዶም በይሁዳ ላይ ዓምፆ የራሱን ንጉሥ አነገሠ። |
በመሆኑም ኢዮራም ከአዛዦቹ ጋር ሠረገሎቹን ሁሉ ይዞ ተሻገረ፤ በሌሊትም ተነስቶ እሱንና የሠረገሎቹን አዛዦች ከበው የነበሩትን ኤዶማውያን ድል አደረገ። |
ሆኖም ኤዶም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ላይ እንዳመፀ ነው። ሊብናም በዚሁ ጊዜ በእሱ ላይ ዓመፀ፤ ምክንያቱም ኢዮራም የአባቶቹን አምላክ ይሖዋን ትቶ ነበር። |
ደግሞም በይሁዳ ተራሮች ላይ ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችን ሠርቶ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች መንፈሳዊ ምንዝር እንዲፈጽሙ አደረገ፤ ይሁዳንም አሳተ። |
በመጨረሻም ነቢዩ ኤልያስ እንዲህ የሚል መልእክት በጽሑፍ ላከለት፦ “የአባትህ የዳዊት አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በአባትህ በኢዮሳፍጥ ወይም በይሁዳ ንጉሥ በአሳ መንገድ አልሄድክም። |
ይልቁንም በእስራኤል ነገሥታት መንገድ በመሄድ፣ ይሁዳና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የአክዓብ ቤት የፈጸመውን ምንዝር የሚመስል መንፈሳዊ ምንዝር እንዲፈጽሙ አድርገሃል፤ ከዚህም በላይ ከአንተ ይሻሉ የነበሩትን የአባትህ ቤት ልጆች የሆኑትን የገዛ ወንድሞችህን ገድለሃል። |
ስለዚህ ይሖዋ ሕዝብህን፣ ልጆችህን፣ ሚስቶችህንና ንብረትህን ሁሉ በታላቅ መቅሰፍት ይመታል። |
አንተም የአንጀት በሽታን ጨምሮ በብዙ ሕመም ትሠቃያለህ፤ ከበሽታው የተነሳ አንጀትህ እስኪወጣ ድረስ ሕመሙ ዕለት ተዕለት እየጠናብህ ይሄዳል።’” |
ከዚያም ይሖዋ ፍልስጤማውያንና በኢትዮጵያውያን አቅራቢያ የሚኖሩት ዓረቦች በኢዮራም ላይ እንዲነሱ አደረገ። |
እነሱም ይሁዳን ወረሩ፤ በኃይል ጥሰው በመግባትም በንጉሡ ቤት ያገኙትን ንብረት ሁሉ እንዲሁም ልጆቹንና ሚስቶቹን ማርከው ወሰዱ፤ ከመጨረሻው ልጁ ከኢዮዓካዝ በቀር አንድም ልጅ አልቀረለትም። |
ከዚህ ሁሉ በኋላ ይሖዋ በማይድን የአንጀት በሽታ ቀሰፈው። |
ድፍን ሁለት ዓመት ከታመመ በኋላም ሕመሙ ጠንቶበት አንጀቱ ወጣ፤ በበሽታውም እጅግ ሲሠቃይ ቆይቶ በመጨረሻ ሞተ፤ ሕዝቡም ለአባቶቹ ያደርጉት እንደነበረው ለእሱ ክብር እሳት አላነደዱም። |
በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 32 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ለስምንት ዓመት ገዛ። ሲሞት ማንም አላዘነለትም። በመሆኑም በነገሥታቱ የመቃብር ስፍራ ሳይሆን በዳዊት ከተማ ቀበሩት። |
ከዚያም ሰለሞን በኢየሩሳሌም፣ ይሖዋ ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ይኸውም ዳዊት በኢያቡሳዊው በኦርናን አውድማ ላይ ባዘጋጀው ቦታ የይሖዋን ቤት መሥራት ጀመረ። |
በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ በሁለተኛው ቀን የግንባታውን ሥራ ጀመረ። |
ሰለሞን የእውነተኛውን አምላክ ቤት ለመሥራት የጣለው መሠረት በቀድሞው መለኪያ ርዝመቱ 60 ክንድ፣ ወርዱም 20 ክንድ ነበር። |
ከቤቱ ፊት ያለው በረንዳ ርዝመቱ 20 ክንድ ሲሆን ይህም ከቤቱ ወርድ ጋር እኩል ነው፤ ከፍታው ደግሞ 120 ነው፤ ውስጡንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው። |
ዋናውን ክፍል በጥድ እንጨት አልብሶ በጥሩ ወርቅ ለበጠው፤ ከዚያም በዘንባባ ዛፍ ምስሎችና በሰንሰለቶች አስጌጠው። |
በተጨማሪም ቤቱን ባማሩና በከበሩ ድንጋዮች ለበጠው፤ የተጠቀመበትም ወርቅ ከፓርዋይም የመጣ ነበር። |
እሱም ቤቱን፣ ወራጆቹን፣ ደፎቹን፣ ግድግዳዎቹንና በሮቹን በወርቅ ለበጣቸው፤ በግድግዳዎቹም ላይ የኪሩቦችን ምስል ቀረጸ። |
ከዚያም የቅድስተ ቅዱሳኑን ክፍል ሠራ፤ ርዝመቱ ከቤቱ ወርድ ጋር እኩል የነበረ ሲሆን 20 ክንድ ነበር፤ ወርዱም 20 ክንድ ነበር። ከዚያም 600 ታላንት በሚሆን ጥሩ ወርቅ ለበጠው። |
ለምስማሮቹ የዋለው ወርቅ 50 ሰቅል ይመዝን ነበር፤ ሰገነት ላይ ያሉትንም ክፍሎች በወርቅ ለበጣቸው። |
ከዚያም በቅድስተ ቅዱሳኑ ክፍል ውስጥ ሁለት የኪሩቦች ቅርጽ ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። |
የኪሩቦቹ ክንፎች አጠቃላይ ርዝመት 20 ክንድ ነበር፤ የመጀመሪያው ኪሩብ አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ ርዝመት ያለው ሲሆን የቤቱን ግድግዳ ይነካ ነበር፤ ሌላኛው ክንፉም አምስት ክንድ ርዝመት ያለው ሲሆን የሁለተኛውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር። |
የሁለተኛውም ኪሩብ አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ ርዝመት ያለው ሲሆን በአንጻሩ ያለውን የቤቱን ግድግዳ ይነካ ነበር፤ ሌላኛው ክንፉም አምስት ክንድ ርዝመት ያለው ሲሆን የመጀመሪያውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር። |
የተዘረጉት የእነዚህ ኪሩቦች ክንፎች 20 ክንድ ነበሩ፤ ኪሩቦቹም ፊታቸውን ወደ ውስጥ አዙረው በእግራቸው ቆመው ነበር። |
በተጨማሪም ከሰማያዊ ክር፣ ከሐምራዊ ሱፍ፣ ከደማቅ ቀይ ክርና ጥራት ካለው ጨርቅ መጋረጃ ሠርቶ የኪሩቦችን ምስል ጠለፈበት። |
ከቤቱ ፊት ለፊትም 35 ክንድ ርዝመት ያላቸው ሁለት ዓምዶችን ሠራ፤ በእያንዳንዱ ዓምድ ላይ ያለው የዓምድ ራስ አምስት ክንድ ነበር። |
እንደ ሐብል ያሉ ሰንሰለቶች ሠርቶም በዓምዶቹ አናት ላይ አደረጋቸው፤ እንዲሁም 100 የሮማን ፍሬዎችን ሠርቶ ከሰንሰለቶቹ ጋር አያያዛቸው። |
ዓምዶቹንም አንዱን በቀኝ ሌላውን በግራ አድርጎ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በስተ ቀኝ ያለውን ያኪን፣ በስተ ግራ ያለውን ደግሞ ቦዔዝ ብሎ ሰየማቸው። |
ሕዝቅያስ ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ፋሲካን ለማክበር በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ ይሖዋ ቤት እንዲመጡ ለእስራኤልና ለይሁዳ ሁሉ መልእክት ላከ፤ ለኤፍሬምና ለምናሴም እንኳ ሳይቀር ደብዳቤ ጻፈ። |
ይሁን እንጂ ንጉሡና መኳንንቱ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ያለው መላው ጉባኤ ፋሲካን በሁለተኛው ወር ለማክበር ወሰኑ፤ |
በቂ ካህናት ራሳቸውን ስላልቀደሱና ሕዝቡ ገና በኢየሩሳሌም ስላልተሰበሰበ ፋሲካውን በመደበኛው ጊዜ ማክበር አልቻሉም ነበር። |
ይህ ዝግጅት በንጉሡና በመላው ጉባኤ ፊት ተቀባይነት አገኘ። |
ስለዚህ ሕዝቡ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ለእስራኤል አምላክ ለይሖዋ ፋሲካን እንዲያከብር በመላው እስራኤል፣ ከቤርሳቤህ አንስቶ እስከ ዳን ድረስ አዋጅ እንዲነገር ወሰኑ፤ በተጻፈው መሠረት በዓሉን በጋራ አክብረው አያውቁም ነበር። |
ከዚያም መልእክተኞቹ የንጉሡንና የመኳንንቱን ደብዳቤዎች ይዘው ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ሄዱ፤ ንጉሡም እንዲህ የሚል ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የእስራኤል አምላክ ወደሆነው ወደ ይሖዋ ተመለሱ፤ እሱም ከአሦር ነገሥታት እጅ ወዳመለጡት ቀሪዎች ይመለሳል። |
አሁን እንደምታዩት፣ መቀጣጫ እስኪያደርጋቸው ድረስ በአባቶቻቸው አምላክ በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት እንደፈጸሙት እንደ አባቶቻችሁና እንደ ወንድሞቻችሁ አትሁኑ። |
አሁንም እንደ አባቶቻችሁ አንገታችሁን አታደንድኑ። የሚነድ ቁጣው ከእናንተ እንዲመለስ ለይሖዋ ተገዙ፤ ለዘላለም ወደቀደሰው መቅደሱ ኑ፤ አምላካችሁን ይሖዋን አገልግሉ። |
ወደ ይሖዋ ስትመለሱ ወንድሞቻችሁና ልጆቻችሁ በማረኳቸው ዘንድ ምሕረት ያገኛሉ፤ ወደዚህች ምድር እንዲመለሱም ይለቋቸዋል፤ አምላካችሁ ይሖዋ ሩኅሩኅና መሐሪ ነውና፤ ወደ እሱም ከተመለሳችሁ ፊቱን አያዞርባችሁም።” |
ስለዚህ መልእክተኞቹ ከከተማ ወደ ከተማ እየተዘዋወሩ የኤፍሬምንና የምናሴን እንዲሁም የዛብሎንን አገር ሁሉ አዳረሱ፤ ሕዝቡ ግን ያፌዝባቸውና ይሳለቅባቸው ነበር። |
ይሁን እንጂ ከአሴር፣ ከምናሴና ከዛብሎን ምድር የተወሰኑ ሰዎች ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። |
በተጨማሪም የእውነተኛው አምላክ እጅ ከይሁዳ ሰዎች ጋር ስለነበር ንጉሡና መኳንንቱ በይሖዋ ቃል መሠረት ያስተላለፉትን ትእዛዝ እንዲፈጽሙ አንድ ልብ ሰጣቸው። |
በሁለተኛው ወር የቂጣን በዓል ለማክበር እጅግ ብዙ ሕዝብ በኢየሩሳሌም ተሰበሰበ፤ ጉባኤው እጅግ ታላቅ ነበር። |
እነሱም ተነስተው በኢየሩሳሌም የነበሩትን መሠዊያዎችና የዕጣን መሠዊያዎች ከነቃቀሉ በኋላ በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ ጣሏቸው። |
ከዚያም በሁለተኛው ወር በ14ኛው ቀን የፋሲካን መሥዋዕት አረዱ። ካህናቱና ሌዋውያኑ አፍረው ስለነበር ራሳቸውን ቀደሱ፤ ወደ ይሖዋም ቤት የሚቃጠል መባ አመጡ። |
በእውነተኛው አምላክ ሰው በሙሴ ሕግ መሠረት የተሰጣቸውን መመሪያ ተከትለው መደበኛ ቦታቸውን ያዙ፤ ከዚያም ካህናቱ ከሌዋውያኑ እጅ የተቀበሉትን ደም ረጩ። |
በጉባኤው መካከል ራሳቸውን ያልቀደሱ ብዙ ሰዎች ስለነበሩ ሌዋውያኑ ያልነጹትን ሰዎች ለይሖዋ ለመቀደስ የፋሲካን መሥዋዕት የማረድ ኃላፊነት ተጥሎባቸው ነበር። |
እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በተለይም ከኤፍሬም፣ ከምናሴ፣ ከይሳኮርና ከዛብሎን የመጡ ሰዎች ራሳቸውን ያላነጹ ቢሆንም የተጻፈውን መመሪያ ተላልፈው ፋሲካውን በሉ። ይሁንና ሕዝቅያስ እንዲህ ሲል ጸለየላቸው፦ “ጥሩ የሆነው ይሖዋ ይቅር ይበል፤ |
የቅድስናውን መሥፈርት አሟልተው ራሳቸውን ባያነጹም እንኳ እውነተኛ አምላክ የሆነውን የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን ለመፈለግ ልባቸውን ያዘጋጁትን ሁሉ ይቅር ይበላቸው።” |
ይሖዋም ሕዝቅያስን ሰምቶ ሕዝቡን ይቅር አለ። |
በመሆኑም በኢየሩሳሌም የተገኙት እስራኤላውያን የቂጣን በዓል ለሰባት ቀናት በታላቅ ደስታ አከበሩ፤ ሌዋውያኑና ካህናቱም ከፍ ባለ ድምፅ ለይሖዋ የሙዚቃ መሣሪያዎቻቸውን በመጫወት በየዕለቱ ይሖዋን ያወድሱ ነበር። |
በተጨማሪም ሕዝቅያስ ይሖዋን በማስተዋል ያገለግሉ የነበሩትን ሌዋውያን ሁሉ በማነጋገር አበረታታቸው። እነሱም የኅብረት መሥዋዕቶች በማቅረብና ለአባቶቻቸው አምላክ ለይሖዋ ምስጋና በማቅረብ በዓሉ ተጀምሮ እስኪያበቃ ድረስ ለሰባት ቀናት በሉ። |
ከዚያም መላው ጉባኤ ለተጨማሪ ሰባት ቀናት በዓሉን ለማክበር ወሰነ፤ በመሆኑም እንደገና ለሰባት ቀናት በዓሉን በታላቅ ደስታ አከበሩ። |
የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስም 1,000 በሬዎችና 7,000 በጎች ለጉባኤው ሰጥቶ ነበር፤ መኳንንቱ ደግሞ 1,000 በሬዎችና 10,000 በጎች ለጉባኤው አበረከቱ፤ እጅግ ብዙ ካህናትም ራሳቸውን ቀደሱ። |
መላው የይሁዳ ጉባኤ፣ ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ ከእስራኤል የመጣው መላው ጉባኤ እንዲሁም ከእስራኤል ምድር የመጡትና በይሁዳ የሚኖሩት የባዕድ አገር ሰዎች እጅግ ተደሰቱ። |
ከእስራኤል ንጉሥ ከዳዊት ልጅ ከሰለሞን ዘመን አንስቶ በኢየሩሳሌም እንዲህ ያለ ነገር ሆኖ ስለማያውቅ በኢየሩሳሌም ታላቅ ደስታ ሆነ። |
በመጨረሻም ሌዋውያኑ ካህናት ተነስተው ሕዝቡን ባረኩ፤ አምላክም ድምፃቸውን ሰማ፤ ጸሎታቸውም ወደ ቅዱሱ መኖሪያው ወደ ሰማያት ደረሰ። |
የሳባ ንግሥት ስለ ሰለሞን ዝና በሰማች ጊዜ አስቸጋሪ በሆኑ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች። እሷም እጅግ ታላቅ አጀብ አስከትላ እንዲሁም የበለሳን ዘይት፣ በጣም ብዙ ወርቅና የከበሩ ድንጋዮች በግመል አስጭና ነበር። ወደ ሰለሞንም ገብታ በልቧ ያለውን ሁሉ ነገረችው። |
ሰለሞንም ጥያቄዎቿን ሁሉ መለሰላት። ሰለሞን ሊያብራራላት ያልቻለው ምንም ነገር አልነበረም። |
የሳባ ንግሥት የሰለሞንን ጥበብና የሠራውን ቤት ስትመለከት፣ |
በገበታው ላይ የሚቀርበውን ምግብ፣ የአገልጋዮቹን አቀማመጥ፣ አስተናጋጆቹ በማዕድ ላይ የሚያስተናግዱበትን መንገድና አለባበሳቸውን፣ መጠጥ አሳላፊዎቹንና አለባበሳቸውን እንዲሁም በይሖዋ ቤት ዘወትር የሚያቀርባቸውን የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ስታይ በመገረም ፈዛ ቀረች። |
በመሆኑም ንጉሡን እንዲህ አለችው፦ “ስላከናወንካቸው ነገሮችና ስለ ጥበብህ በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ነገር እውነት ነው። |
ይሁንና እኔ ራሴ መጥቼ በገዛ ዓይኔ እስከማይ ድረስ የተነገረኝን ነገር አላመንኩም ነበር። እንደዚያም ሆኖ ታላቅ ከሆነው ጥበብህ ግማሹ እንኳ አልተነገረኝም! እኔ ስለ አንተ ከሰማሁት እጅግ የላቅክ ነህ። |
አብረውህ ያሉ ሰዎች ደስተኞች ናቸው፤ ዘወትር በፊትህ ቆመው ጥበብህን የሚሰሙት አገልጋዮችህም እጅግ ደስተኞች ናቸው! |
ለአምላክህ ለይሖዋ ንጉሥ ሆነህ እንድትገዛ አንተን በዙፋኑ ላይ በማስቀመጥ በአንተ ደስ የተሰኘው አምላክህ ይሖዋ ይወደስ። አምላክህ እስራኤልን ስለወደደውና ለዘላለም ያጸናው ዘንድ ስለፈለገ፣ ፍትሕንና ጽድቅን እንድታሰፍን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ ሾሞሃል።” |
ከዚያም ለንጉሡ 120 ታላንት ወርቅ እንዲሁም እጅግ ብዙ የበለሳን ዘይትና የከበሩ ድንጋዮችን ሰጠችው። የሳባ ንግሥት ለንጉሥ ሰለሞን የሰጠችውን ያህል የበለሳን ዘይት ከዚያ በኋላ መጥቶ አያውቅም። |
ከዚህ በተጨማሪ ከኦፊር ወርቅ ጭነው የመጡት የኪራም አገልጋዮችና የሰለሞን አገልጋዮች የሰንደል ዛፍ ሳንቃዎችና የከበሩ ድንጋዮች አመጡ። |
ንጉሡም ከሰንደል ዛፍ ሳንቃዎቹ ለይሖዋ ቤትና ለንጉሡ ቤት ደረጃዎችን እንዲሁም ለዘማሪዎቹ የሚሆኑ በገናዎችንና ሌሎች ባለ አውታር መሣሪያዎችን ሠራ። ከዚያ በፊት እንዲህ ያለ ነገር በይሁዳ ምድር ታይቶ አያውቅም። |
ንጉሥ ሰለሞን ደግሞ የሳባ ንግሥት የፈለገችውንና የጠየቀችውን ነገር ሁሉ፣ ካመጣችለት ስጦታ የሚበልጥ ነገር ሰጣት። ከዚያም ተነስታ አገልጋዮቿን በማስከተል ወደ አገሯ ተመለሰች። |
ሰለሞን በየዓመቱ 666 ታላንት ወርቅ ይመጣለት ነበር፤ |
ይህም ነጋዴዎችና ሻጮች የሚያስገቡትን ገቢ እንዲሁም የዓረብ ነገሥታት ሁሉና አገረ ገዢዎች ለሰለሞን የሚያመጡትን ወርቅና ብር ሳይጨምር ነው። |
ንጉሥ ሰለሞን ከቅይጥ ወርቅ 200 ትላልቅ ጋሻዎችን ሠራ፤ (እያንዳንዱ ጋሻ በ600 ሰቅል ቅይጥ ወርቅ ተለብጦ ነበር)፤ |
እንዲሁም ከቅይጥ ወርቅ 300 ትናንሽ ጋሻዎችን ሠራ፤ (እያንዳንዱ ትንሽ ጋሻ በሦስት ምናን ወርቅ ተለብጦ ነበር)። ከዚያም ንጉሡ የሊባኖስ ደን በተባለው ቤት አስቀመጣቸው። |
በተጨማሪም ንጉሡ ከዝሆን ጥርስ ትልቅ ዙፋን ሠርቶ በንጹሕ ወርቅ ለበጠው። |
ወደ ዙፋኑ የሚያስወጡ ስድስት ደረጃዎች ነበሩ፤ ከዙፋኑም ጋር የተያያዘ ከወርቅ የተሠራ የእግር ማሳረፊያ ነበር፤ መቀመጫውም በጎንና በጎኑ የእጅ መደገፊያዎች ያሉት ሲሆን ከእጅ መደገፊያዎቹም አጠገብ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር። |
በስድስቱ ደረጃዎች ዳርና ዳር አንድ አንድ አንበሳ፣ በአጠቃላይ 12 አንበሶች ቆመው ነበር። እንዲህ ያለ ዙፋን የሠራ አንድም ሌላ መንግሥት አልነበረም። |
የንጉሥ ሰለሞን የመጠጫ ዕቃዎች በሙሉ ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ፤ የሊባኖስ ደን በተባለው ቤት የነበሩት ዕቃዎችም በሙሉ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ። ከብር የተሠራ ምንም ነገር አልነበረም፤ በሰለሞን ዘመን ብር እንደ ተራ ነገር ይቆጠር ነበር። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.