text
stringlengths
4
267
ነገሥታታችን፣ መኳንንታችን፣ ካህናታችንም ሆኑ አባቶቻችን ሕግህን አልጠበቁም፤ ደግሞም እነሱን ለማስጠንቀቅ ብለህ ለሰጠሃቸው ትእዛዛትም ሆነ ማሳሰቢያዎች ትኩረት አልሰጡም።
ሌላው ቀርቶ በራሳቸው መንግሥት ሥር በሚተዳደሩበት፣ አትረፍርፈህ በሰጠሃቸው መልካም ነገሮች በሚደሰቱበት እንዲሁም ባዘጋጀህላቸው ሰፊና ለም ምድር በሚኖሩበት ጊዜም እንኳ አንተን አላገለገሉም፤ ከመጥፎ ተግባራቸውም አልተቆጠቡም።
በመሆኑም ይኸው ዛሬ እኛ ባሪያዎች ሆነናል፤ አዎ፣ አባቶቻችን ፍሬዋንና በረከቷን እንዲበሉ በሰጠሃቸው ምድር ላይ ባሪያዎች ሆነናል።
በምድሪቱ የተትረፈረፈ ምርት እየተጠቀሙ ያሉት በኃጢአታችን የተነሳ በላያችን እንዲነግሡ ያደረግካቸው ነገሥታት ናቸው። እነሱም በሰውነታችንና በቤት እንስሶቻችን ላይ እንዳሻቸው እየገዙ ነው፤ እኛም በከባድ መከራ ውስጥ እንገኛለን።
“በዚህም ሁሉ የተነሳ በጽሑፍ የሰፈረ ጽኑ ስምምነት እናደርጋለን፤ ስምምነቱም በመኳንንታችን፣ በሌዋውያናችንና በካህናታችን ማኅተም የጸደቀ ይሆናል።”
ንጉሥ አርጤክስስ በነገሠ በ20ኛው ዓመት በኒሳን ወር በንጉሡ ፊት የወይን ጠጅ ቀርቦ ነበር፤ እኔም እንደተለመደው የወይን ጠጁን አንስቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። ሆኖም ከዚህ ቀደም እሱ ጋ ስቀርብ በፊቴ ላይ ሐዘን ታይቶ አያውቅም ነበር።
በመሆኑም ንጉሡ “ሳትታመም ፊትህ እንዲህ በሐዘን የጠቆረው ለምንድን ነው? ይህ መቼም የልብ ሐዘን እንጂ ሌላ ነገር ሊሆን አይችልም” አለኝ። በዚህ ጊዜ በጣም ፈራሁ።
ከዚያም ንጉሡን እንዲህ አልኩት፦ “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር! አባቶቼ የተቀበሩባት ከተማ ፈራርሳ፣ በሮቿም በእሳት ተቃጥለው እያለ ለምን ፊቴ በሐዘን አይጠቁር?”
ንጉሡም መልሶ “ታዲያ ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” አለኝ። እኔም ወዲያውኑ ወደ ሰማይ አምላክ ጸለይኩ።
ከዚያም ንጉሡን እንዲህ አልኩት፦ “ንጉሡን ደስ የሚያሰኘው ከሆነና አገልጋይህ በፊትህ ሞገስ ካገኘ ከተማዋን መልሼ እንድገነባ አባቶቼ ወደተቀበሩባት ከተማ፣ ወደ ይሁዳ እንድሄድ ፍቀድልኝ።”
ንጉሡም ንግሥቲቱ አጠገቡ ተቀምጣ ሳለ “ጉዞህ ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል? መቼ ትመለሳለህ?” አለኝ። ንጉሡም ደስ ብሎት እንድሄድ ፈቀደልኝ፤ እኔም ጊዜውን ቆርጬ ነገርኩት።
ከዚያም ንጉሡን እንዲህ አልኩት፦ “ንጉሡን ደስ የሚያሰኘው ከሆነ ከወንዙ ባሻገር ያለው ክልል ገዢዎች ይሁዳ እስክደርስ ድረስ በሰላም ምድራቸውን አቋርጬ እንዳልፍ እንዲፈቅዱልኝ ደብዳቤ ይሰጠኝ፤
በተጨማሪም የንጉሡ መናፈሻ ቦታ ጠባቂ የሆነው አሳፍ ለቤቱ የግንብ አጥር በሮች፣ ለከተማዋ ቅጥሮችና ለምሄድበት ቤት የሚያገለግሉ ሳንቃዎች እንዲሰጠኝ ደብዳቤ ይጻፍልኝ።” በዚህ ጊዜ መልካም የሆነው የአምላኬ እጅ በእኔ ላይ ስለነበር ንጉሡ እነዚህን ሰጠኝ።
በመጨረሻም ከወንዙ ባሻገር ወዳለው ክልል ገዢዎች ሄጄ የንጉሡን ደብዳቤዎች ሰጠኋቸው። በተጨማሪም ንጉሡ የጦር አለቆችና ፈረሰኞች አብረውኝ እንዲሄዱ አድርጎ ነበር።
ሆሮናዊው ሳንባላጥና አሞናዊው ባለሥልጣን ጦብያ ይህን ነገር ሲሰሙ ለእስራኤላውያን መልካም ነገር የሚያደርግ ሰው በመምጣቱ በጣም ተበሳጩ።
በመጨረሻም ኢየሩሳሌም ደረስኩ፤ እዚያም ሦስት ቀን ቆየሁ።
ከዚያም በሌሊት ተነሳሁ፤ ከእኔም ጋር ጥቂት ሰዎች ነበሩ፤ አምላኬ ለኢየሩሳሌም እንዳደርግ በልቤ ያኖረውን ነገር ለማንም ሰው አልተናገርኩም፤ ከተቀመጥኩበት እንስሳም በስተቀር ሌላ እንስሳ ከእኔ ጋር አልነበረም።
በሌሊትም በሸለቆ በር ከወጣሁ በኋላ በትልቁ እባብ ምንጭ ፊት ለፊት በማለፍ ወደ አመድ ቁልል በር ሄድኩ፤ የፈራረሱትን የኢየሩሳሌም ቅጥሮችና በእሳት የተቃጠሉትን በሮቿንም አንድ በአንድ መረመርኩ።
ከዚያም አልፌ ወደ ምንጭ በርና ወደ ንጉሡ ኩሬ ሄድኩ፤ በዚያም የተቀመጥኩበትን እንስሳ ማሳለፍ የሚያስችል በቂ ቦታ አልነበረም።
ሆኖም ሌሊቱን ሸለቆውን ይዤ ሽቅብ ወጣሁ፤ ቅጥሩንም መመርመሬን ቀጠልኩ፤ ከዚያም ተመልሼ በሸለቆ በር ገባሁ፤ በኋላም ወደመጣሁበት ተመለስኩ።
ለአይሁዳውያኑ፣ ለካህናቱ፣ ለተከበሩት ሰዎች፣ ለበታች ገዢዎቹና ለቀሩት ሠራተኞች ገና ምንም የነገርኳቸው ነገር ስላልነበር የበታች ገዢዎቹ የት እንደሄድኩና ምን እያደረግኩ እንደነበር አላወቁም።
በመጨረሻም እንዲህ አልኳቸው፦ “መቼም ያለንበት ሁኔታ ምን ያህል አሳዛኝ እንደሆነ ሳትመለከቱ አትቀሩም፤ ኢየሩሳሌም ፈራርሳለች፣ በሮቿም በእሳት ተቃጥለዋል። እንግዲህ ተዋርደን እንዳንቀር ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥሮች መልሰን እንገንባ።”
ከዚያም የአምላኬ መልካም እጅ ምን ያህል በእኔ ላይ እንደነበርና ንጉሡም ምን እንዳለኝ ነገርኳቸው። እነሱም “እንነሳና እንገንባ” አሉ። በመሆኑም መልካሙን ሥራ ለመሥራት ራሳቸውን አበረቱ።
ሆሮናዊው ሳንባላጥና አሞናዊው ባለሥልጣን ጦብያ እንዲሁም የዓረብ ተወላጅ የሆነው ጌሼም ይህን ሲሰሙ ያፌዙብንና በንቀት ዓይን ይመለከቱን ጀመር፤ እንዲህም አሉን፦ “ምን እያደረጋችሁ ነው? በንጉሡ ላይ ልታምፁ ነው?”
እኔም እንዲህ ብዬ መለስኩላቸው፦ “ሥራችንን የሚያሳካልን የሰማይ አምላክ ነው፤ እኛ አገልጋዮቹም ተነስተን እንገነባለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ምንም ዓይነት ድርሻም ሆነ መብት ወይም መታሰቢያ የላችሁም።”
በስምምነቱ ላይ ማኅተማቸውን በማተም ያጸደቁት እነዚህ ናቸው፦ የሃካልያህ ልጅ የሆነው ገዢው ነህምያ፣ ሴዴቅያስ፣
ሰራያህ፣ አዛርያስ፣ ኤርምያስ፣
ጳስኮር፣ አማርያህ፣ ማልኪያህ፣
ሃጡሽ፣ ሸባንያህ፣ ማሉክ፣
ሃሪም፣ መሬሞት፣ አብድዩ፣
ዳንኤል፣ ጊነቶን፣ ባሮክ፣
መሹላም፣ አቢያህ፣ ሚያሚን፣
ማአዝያህ፣ ቢልጋይ እና ሸማያህ፤ ካህናቱ እነዚህ ናቸው።
ሌዋውያኑ ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፦ የአዛንያህ ልጅ የሹዋ፣ ከሄናዳድ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው ቢኑይ፣ ቃድሚኤል፣
እንዲሁም ወንድሞቻቸው የሆኑት ሸባንያህ፣ ሆዲያህ፣ ቀሊጣ፣ ፐላያህ፣ ሃናን፣
ሚካ፣ ሬሆብ፣ ሃሻብያህ፣
ዛኩር፣ ሸረበያህ፣ ሸባንያህ፣
ሆዲያህ፣ ባኒ እና ቤኒኑ።
የሕዝቡ መሪዎች የሚከተሉት ናቸው፦ ፓሮሽ፣ ፓሃትሞአብ፣ ኤላም፣ ዛቱ፣ ባኒ፣
ቡኒ፣ አዝጋድ፣ ቤባይ፣
አዶንያስ፣ ቢግዋይ፣ አዲን፣
አጤር፣ ሕዝቅያስ፣ አዙር፣
ሆዲያህ፣ ሃሹም፣ ቤጻይ፣
ሃሪፍ፣ አናቶት፣ ነባይ፣
ማግፒአሽ፣ መሹላም፣ ሄዚር፣
መሺዛቤል፣ ሳዶቅ፣ ያዱአ፣
ጰላጥያህ፣ ሃናን፣ አናያ፣
ሆሺአ፣ ሃናንያህ፣ ሃሹብ፣
ሃሎሔሽ፣ ፒልሃ፣ ሾቤቅ፣
ረሁም፣ ሃሻብናህ፣ ማአሴያህ፣
አኪያህ፣ ሃናን፣ አናን፣
ማሉክ፣ ሃሪም እና ባአናህ።
የቀረው ሕዝብ ማለትም ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ ዘማሪዎቹ፣ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ እንዲሁም የእውነተኛውን አምላክ ሕግ ለመጠበቅ በምድሪቱ ካሉት ሕዝቦች ራሳቸውን የለዩ ሁሉ ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶች ልጆቻቸውንና ሴቶች ልጆቻቸውን ጨምሮ እውቀትና ማስተዋል ያለው ማንኛውም ሰው
ከወንድሞቻቸውና ታዋቂ ከሆኑት ሰዎቻቸው ጋር በመሆን የእውነተኛው አምላክ አገልጋይ በሆነው በሙሴ እጅ በተሰጠው የእውነተኛው አምላክ ሕግ መሠረት ለመሄድ እንዲሁም የጌታችንን የይሖዋን ትእዛዛት፣ ፍርዶችና ሥርዓቶች ሁሉ በጥንቃቄ ለመጠበቅ በእርግማንና በመሐላ ራሳቸውን ግዴታ ውስጥ አስገቡ።
ሴቶች ልጆቻችንን በምድሪቱ ለሚኖሩ ሰዎች አንሰጥም፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችን አንወስድም።
በምድሪቱ የሚኖሩት ሕዝቦች በሰንበት ቀን ሸቀጣ ሸቀጦቻቸውንና የተለያዩ ጥራጥሬዎችን ለመሸጥ ቢያመጡ በሰንበት ወይም ቅዱስ በሆነ ቀን ከእነሱ ላይ ምንም ነገር አንገዛም። በተጨማሪም በሰባተኛው ዓመት ምርት ከማምረት እንቆጠባለን፤ ያልተከፈለን ዕዳም ሁሉ እንሰርዛለን።
በተጨማሪም እያንዳንዳችን በአምላካችን ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት በየዓመቱ አንድ ሦስተኛ ሰቅል ለመስጠት ራሳችንን ግዴታ ውስጥ እናስገባለን፤
ይህም በሰንበት ቀናትና በአዲስ ጨረቃ ወቅት ለሚቀርበው የሚነባበር ዳቦ እንዲሁም በእነዚህ ጊዜያት ዘወትር ለሚቀርበው የእህል መባና የሚቃጠል መባ፣ በተጨማሪም በተወሰኑ ጊዜያት ለሚከበሩት በዓላት፣ ቅዱስ ለሆኑት ነገሮች፣ እስራኤልን ለማስተሰረይ ለሚቀርቡት የኃጢአት መባዎችና በአምላካችን ቤት ለሚከናወኑ ሥራዎች ሁሉ ይውላል።
ከዚህም ሌላ ካህናቱ፣ ሌዋውያኑና ሕዝቡ በሕጉ ላይ በተጻፈው መሠረት በየዓመቱ በተወሰነው ጊዜ በአምላካችን በይሖዋ መሠዊያ ላይ እንዲቃጠል በየአባቶቻችን ቤት በየተራ ወደ አምላካችን ቤት ሊያመጡ የሚገባውን እንጨት በተመለከተ ዕጣ ጣልን።
እንዲሁም መሬታችን የሚያፈራውን መጀመሪያ የደረሰውን ፍሬና ማንኛውም ዓይነት የፍራፍሬ ዛፍ የሚያፈራውን መጀመሪያ የደረሰውን ፍሬ ሁሉ በየዓመቱ ወደ ይሖዋ ቤት እናመጣለን፤
በተጨማሪም በሕጉ ላይ በተጻፈው መሠረት ከወንዶች ልጆቻችንና ከእንስሶቻችን በኩሩን እንዲሁም ከከብቶቻችንና ከመንጎቻችን በኩሩን እናመጣለን። ወደ አምላካችን ቤት ይኸውም በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት እናመጣለን።
ከዚህም በተጨማሪ የተፈጨውን የእህላችንን በኩር፣ መዋጮዎቻችንን፣ ማንኛውም ዛፍ የሚያፈራውን ፍሬ፣ አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት ወደ አምላካችን ቤት ግምጃ ቤቶች ወደ ካህናቱ እናመጣለን፤ እንዲሁም ከእርሻ ከተሞቻችን ሁሉ አንድ አሥረኛውን የሚቀበሉት ሌዋውያኑ ስለሆኑ የመሬታችንን አንድ አሥረኛ ለሌዋውያኑ እናመጣለን።
ሌዋውያኑ አንድ አሥረኛውን በሚቀበሉበት ጊዜ ካህኑ የአሮን ልጅ ከሌዋውያኑ ጋር አብሮ መሆን አለበት፤ ሌዋውያኑም የአንድ አሥረኛውን አንድ አሥረኛ ወደ አምላካችን ቤት ይኸውም በግምጃ ቤቱ ውስጥ ወደሚገኙት ክፍሎች መውሰድ ይኖርባቸዋል።
ምክንያቱም እስራኤላውያንም ሆኑ የሌዋውያኑ ልጆች የእህሉን፣ የአዲሱን ወይን ጠጅና የዘይቱን መዋጮ ማምጣት ያለባቸው ወደ ግምጃ ቤቶቹ ነው፤ ደግሞም የመቅደሱ ዕቃዎች የሚቀመጡትም ሆነ የሚያገለግሉት ካህናት፣ በር ጠባቂዎቹና ዘማሪዎቹ የሚገኙት በዚያ ነው። እኛም የአምላካችንን ቤት ቸል አንልም።
ሆኖም ወንዶቹም ሆኑ ሚስቶቻቸው በአይሁዳውያን ወንድሞቻቸው ላይ ታላቅ ጩኸት አሰሙ።
አንዳንዶቹ “የእኛም ሆነ የወንዶች ልጆቻችንና የሴቶች ልጆቻችን ቁጥር ብዙ ነው። በሕይወት ለመቆየት የምንበላው እህል ማግኘት ይኖርብናል” ይሉ ነበር።
ሌሎቹም “የምግብ እጥረት በተከሰተበት ወቅት እህል ለማግኘት ስንል ማሳችንን፣ የወይን እርሻችንንና ቤታችንን መያዣ አድርገን ሰጥተናል” አሉ።
የተቀሩት ደግሞ እንዲህ ይሉ ነበር፦ “የንጉሡን ግብር ለመክፈል ስንል ማሳችንንና የወይን እርሻችንን አስይዘን ገንዘብ ተበድረናል።
እንግዲህ ወንድሞቻችን የአጥንታችን ፍላጭ፣ የሥጋችን ቁራጭ ናቸው፤ ልጆቻችንም እንደ ልጆቻቸው ናቸው፤ ሆኖም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንን ለባርነት አሳልፈን ለመስጠት ተገደናል፤ እንዲያውም ከሴቶች ልጆቻችን መካከል አንዳንዶቹ አሁንም በባርነት ላይ ናቸው። ያም ሆኖ ማሳችንና የወይን እርሻችን በሌሎች እጅ ስለሆነ ይህን ለማስቆም የሚያስችል አቅም የለንም።”
እኔም ጩኸታቸውንና ይህን አቤቱታቸውን ስሰማ በጣም ተናደድኩ።
ስለዚህ ነገሩን በልቤ ካጤንኩ በኋላ የተከበሩትን ሰዎችና የበታች ገዢዎቹን “እያንዳንዳችሁ ከገዛ ወንድማችሁ ላይ ወለድ እየተቀበላችሁ ነው” በማለት ወቀስኳቸው። በተጨማሪም በእነሱ የተነሳ ታላቅ ስብሰባ ጠራሁ።
እንዲህም አልኳቸው፦ “ለብሔራት ተሸጠው የነበሩትን አይሁዳውያን ወንድሞቻችንን በተቻለን መጠን መልሰን ገዝተናቸው ነበር፤ ታዲያ እናንተ አሁን የገዛ ወንድሞቻችሁን መልሳችሁ ትሸጣላችሁ? ደግሞስ እንደገና ለእኛ መሸጥ ይኖርባቸዋል?” በዚህ ጊዜ የሚመልሱት ስለጠፋቸው ዝም አሉ።
ከዚያም እንዲህ አልኳቸው፦ “የምትሠሩት ሥራ ጥሩ አይደለም። ጠላቶቻችን የሆኑት ብሔራት መሳለቂያ እንዳያደርጉን አምላካችንን በመፍራት መመላለስ አልነበረባችሁም?
ከዚህም በላይ እኔም ሆንኩ ወንድሞቼና አገልጋዮቼ ገንዘብና እህል አበድረናቸዋል። እባካችሁ ይህን በወለድ ማበደር የሚባል ነገር እንተው።
ደግሞም እባካችሁ ማሳዎቻቸውን፣ የወይን እርሻዎቻቸውን፣ የወይራ ዛፎቻቸውንና ቤቶቻቸውን እንዲሁም ከገንዘብ፣ ከእህል፣ ከአዲስ የወይን ጠጅና ከዘይት ወለድ አድርጋችሁ የተቀበላችሁትን ከመቶ አንድ እጅ ዛሬውኑ መልሱላቸው።”
እነሱም “እነዚህን ነገሮች እንመልስላቸዋለን፤ በምላሹም ምንም ነገር እንዲያደርጉልን አንጠይቅም። ልክ እንዳልከው እናደርጋለን” አሉ። እኔም ካህናቱን ጠርቼ ሰዎቹን ይህን ቃል እንዲጠብቁ አስማልኳቸው።
በተጨማሪም የልብሴን እጥፋት አራግፌ እንዲህ አልኳቸው፦ “ይህን ቃል የማይፈጽመውን ማንኛውንም ሰው እውነተኛው አምላክ ከቤቱና ከንብረቱ እንዲህ አራግፎ ያስወጣው፤ ልክ እንደዚህ ተራግፎም ባዶውን ይቅር።” በዚህ ጊዜ መላው ጉባኤ “አሜን!” አለ። ይሖዋንም አመሰገኑ፤ ሕዝቡም ቃል እንደገቡት አደረጉ።
ከዚህም በላይ ንጉሡ በይሁዳ ምድር ገዢያቸው አድርጎ ከሾመኝ ጊዜ አንስቶ ማለትም ንጉሥ አርጤክስስ ከነገሠ ከ20ኛው ዓመት አንስቶ እስከ 32ኛው ዓመት ድረስ ይኸውም ለ12 ዓመት ያህል እኔም ሆንኩ ወንድሞቼ ለገዢው የሚገባውን ቀለብ አልበላንም።
ከእኔ በፊት የነበሩት የቀድሞዎቹ ገዢዎች ግን በሕዝቡ ላይ ሸክም ጭነውበት የነበረ ከመሆኑም ሌላ ከሕዝቡ ላይ ለምግብና ለወይን በየቀኑ 40 የብር ሰቅል ይወስዱ ነበር። በተጨማሪም አገልጋዮቻቸው ሕዝቡን ይጨቁኑ ነበር። እኔ ግን አምላክን ስለምፈራ እንዲህ አላደረግኩም።
ከዚህም በላይ ይህን ቅጥር በመገንባቱ ሥራ ተሳትፌያለሁ፤ አገልጋዮቼም በሙሉ ሥራውን ለመሥራት እዚያ ተሰባስበው ነበር፤ የራሳችንም መሬት አልነበረንም።
በተጨማሪም 150 አይሁዳውያንና የበታች ገዢዎች እንዲሁም ከሌሎች ብሔራት ወደ እኛ የመጡ ሰዎች ከማዕዴ ይበሉ ነበር።
በየቀኑ አንድ በሬ፣ ስድስት ምርጥ በጎች እንዲሁም ወፎች ይዘጋጁልኝ ነበር፤ በየአሥር ቀኑ ደግሞ የተለያየ ዓይነት የወይን ጠጅ በብዛት ይቀርብልን ነበር። እንደዚያም ሆኖ ሕዝቡ የራሱ የአገልግሎት ቀንበር ከብዶት ስለነበር ለገዢው የሚገባው ቀለብ እንዲሰጠኝ ጠይቄ አላውቅም።
አምላኬ ሆይ፣ ለዚህ ሕዝብ ስላደረግኩት ነገር ሁሉ በመልካም አስበኝ።
ሳንባላጥ ቅጥሩን መልሰን እየገነባን መሆናችንን ሲሰማ በጣም ተናደደ፤ እጅግም ተበሳጨ፤ በአይሁዳውያንም ላይ ያፌዝ ነበር።
በወንድሞቹና በሰማርያ ጦር ሠራዊት ፊትም እንዲህ ይል ጀመር፦ “እነዚህ አቅመ ቢስ አይሁዳውያን ምን እያደረጉ ነው? ለመሆኑ ይህን ሥራ ራሳቸው ሊሠሩት ነው? መሥዋዕትስ ሊያቀርቡ ነው? ደግሞስ በአንድ ቀን ሠርተው ሊጨርሱ ያስባሉ? በእሳት ተቃጥለው የአመድ ቁልል የሆኑትን ድንጋዮች ሕይወት ሊዘሩባቸው ነው?”
በዚህ ጊዜ አጠገቡ ቆሞ የነበረው አሞናዊው ጦብያ “የሚገነቡት የድንጋይ ቅጥር እኮ ቀበሮ እንኳ ቢወጣበት ይፈርሳል” አለ።
አምላካችን ሆይ፣ መሳለቂያ ሆነናልና ስማ፤ ስድባቸውን በራሳቸው ላይ መልስባቸው፤ እንዲበዘበዙና ተማርከው ወደ ሌላ አገር እንዲወሰዱ አድርጋቸው።
የግንባታውን ሥራ የሚሠሩትን ሰዎች ስለተሳደቡ በደላቸውን አትሸፍን፤ ኃጢአታቸውም ከፊትህ እንዲደመሰስ አታድርግ።
እኛም ቅጥሩን መገንባታችንን ቀጠልን፤ ዙሪያውን ያለው ቅጥርም ክፍተቱ እየተደፈነ እስከ ቁመቱ እኩሌታ ድረስ ተጠገነ፤ ሕዝቡም ሥራውን ከልቡ መሥራቱን ቀጠለ።
ሳንባላጥ፣ ጦብያ፣ ዓረቦች፣ አሞናውያንና አሽዶዳውያን የኢየሩሳሌምን ቅጥሮች የመጠገኑ ሥራ እየተፋጠነና ክፍተቶቹም እየተደፈኑ መሆናቸውን ሲሰሙ እጅግ ተናደዱ።
እነሱም መጥተው ኢየሩሳሌምን ለመውጋትና በውስጧ ሁከት ለመፍጠር በአንድነት አሴሩ።
እኛ ግን ወደ አምላካችን ጸለይን፤ ከእነሱ ጥቃት ሌት ተቀን የሚጠብቁን ጠባቂዎችም አቆምን።
የይሁዳ ሰዎች ግን እንዲህ ይሉ ነበር፦ “የሠራተኞቹ አቅም እየተሟጠጠ ነው፤ ፍርስራሹ ደግሞ በጣም ብዙ ነው፤ ፈጽሞ ቅጥሩን መገንባት አንችልም።”
ጠላቶቻችንም “ምንም ሳያውቁ ወይም ሳያዩን መካከላቸው ገብተን እንገድላቸዋለን፤ ሥራውንም እናስቆማለን” ይሉ ነበር።
በእነሱ አቅራቢያ የሚኖሩት አይሁዳውያንም በመጡ ቁጥር “በሁሉም አቅጣጫ ይዘምቱብናል” እያሉ ደጋግመው ይነግሩን ነበር።
ስለዚህ ከቅጥሩ ጀርባ በሚገኘው ገላጣ በሆነው ዝቅተኛ ቦታ ላይ ሰዎችን አቆምኩ፤ እነሱም ሰይፋቸውን፣ ጦራቸውንና ቀስታቸውን ይዘው በየቤተሰቦቻቸው እንዲቆሙ አደረግኩ።
ሰዎቹ መፍራታቸውን ሳይም ወዲያውኑ ተነስቼ የተከበሩትን ሰዎች፣ የበታች ገዢዎቹንና የቀረውን ሕዝብ እንዲህ አልኳቸው፦ “አትፍሯቸው። ታላቁንና የተፈራውን ይሖዋን አስቡ፤ ለወንድሞቻችሁ፣ ለወንዶች ልጆቻችሁ፣ ለሴቶች ልጆቻችሁ፣ ለሚስቶቻችሁና ለቤታችሁ ተዋጉ።”
ጠላቶቻችንም ሴራቸውን እንዳወቅንባቸውና እውነተኛው አምላክ ዕቅዳቸውን እንዳከሸፈባቸው ሰሙ፤ ከዚያም ሁላችንም ቅጥሩን ወደ መገንባቱ ሥራችን ተመለስን።
ከዚያን ቀን ጀምሮ አብረውኝ ካሉት ሰዎች መካከል ግማሾቹ ሥራውን ሲሠሩ ግማሾቹ ደግሞ ጦር፣ ጋሻና ቀስት ይዘው እንዲሁም ጥሩር ለብሰው ይቆሙ ነበር። መኳንንቱ ከአይሁዳውያኑ ኋላ ቆመው ድጋፍ ሲሰጧቸው
እነሱ ደግሞ ቅጥሩን ይገነቡ ነበር። ሸክም የሚሸከሙት ሰዎች እያንዳንዳቸው በአንድ እጃቸው ሥራውን ሲሠሩ በሌላ እጃቸው ደግሞ የጦር መሣሪያ ይይዙ ነበር።