text stringlengths 4 267 |
|---|
ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤አምላክ ራሱ ፈራጅ ነውና። (ሴላ) |
“ሕዝቤ ሆይ፣ ስማ፤ እኔም እናገራለሁ፤እስራኤል ሆይ፣ በአንተ ላይ እመሠክርብሃለሁ። እኔ አምላክ፣ አዎ አምላክህ ነኝ። |
በመሥዋዕቶችህም ሆነዘወትር በፊቴ ባሉት የሚቃጠሉ መባዎችህ የተነሳ አልወቅስህም። |
ከቤትህ ኮርማ፣ከጉረኖህም ፍየሎች መውሰድ አያስፈልገኝም። |
በጫካ ውስጥ ያሉ የዱር እንስሳት ሁሉ፣በሺህ ተራሮች ላይ ያሉ አራዊትም እንኳ የእኔ ናቸውና። |
በተራሮች ላይ የሚኖሩትን ወፎች ሁሉ አውቃለሁ፤በመስክ ያሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው እንስሳት የእኔ ናቸው። |
ብራብ እንኳ ለአንተ አልነግርህም፤ፍሬያማ የሆነችው ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የእኔ ነውና። |
የኮርማዎችን ሥጋ እበላለሁ?የፍየሎችንስ ደም እጠጣለሁ? |
ምስጋናን ለአምላክ መሥዋዕት አድርገህ አቅርብ፤ስእለትህንም ለልዑሉ አምላክ ስጥ፤ |
በጭንቅ ቀን ጥራኝ። እኔ እታደግሃለሁ፤ አንተም ታወድሰኛለህ።” |
ክፉውን ግን አምላክ እንዲህ ይለዋል፦ “ስለ ሥርዓቴ ለማውራት፣ወይም ደግሞ ስለ ቃል ኪዳኔ ለመናገር ምን መብት አለህ? |
ተግሣጼን ትጠላለህና፤ለቃሌም ጀርባህን ትሰጣለህ። |
ሌባ ስታይ ትደግፈዋለህ፤ከአመንዝሮችም ጋር ትወዳጃለህ። |
አንደበትህን ክፉ ወሬ ለመንዛት ትጠቀምበታለህ፤ማታለያም ከምላስህ አይጠፋም። |
ከሌሎች ጋር ተቀምጠህ ወንድምህን ታማለህ፤የገዛ እናትህን ልጅ ድክመት ታወራለህ። |
እነዚህን ሁሉ ነገሮች ስታደርግ፣ ዝም አልኩ፤በመሆኑም እንደ አንተ የምሆን መስሎህ ነበር። አሁን ግን እወቅስሃለሁ፤ከአንተ ጋር ያለኝንም ሙግት አሳውቃለሁ። |
እናንተ አምላክን የምትረሱ፣ እባካችሁ ይህን ልብ በሉ፤አለዚያ ብትንትናችሁን አወጣለሁ፤ የሚታደጋችሁም አይኖርም። |
ምስጋናን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብልኝ ያከብረኛል፤ደግሞም ትክክለኛውን መንገድ በጥብቅ የሚከተልን ሰው፣የአምላክን ማዳን እንዲያይ አደርገዋለሁ።” |
ምድርና በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ፣ፍሬያማ የሆነችው ምድርና በእሷ ላይ የሚኖር ሁሉ የይሖዋ ነው። |
እሱ በባሕሮች ላይ መሥርቷታልና፤በወንዞችም ላይ አጽንቶ አስቀምጧታል። |
ወደ ይሖዋ ተራራ መውጣት የሚችል ማን ነው?በቅዱስ ስፍራውስ ሊቆም የሚችል ማን ነው? |
ከክፋት የጸዱ እጆችና ንጹሕ ልብ ያለው፣በእኔ ሕይወት በሐሰት ያልማለ፣በማታለልም መሐላ ያልፈጸመ። |
እሱ በረከትን ከይሖዋ ያገኛል፤ጽድቅንም አዳኝ ከሆነው አምላኩ ይቀበላል። |
እሱን የሚፈልጉ ሰዎች ትውልድ ይህ ነው፤የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ ፊትህን የሚፈልጉ ሰዎች ትውልድ እንዲህ ያለ ነው። (ሴላ) |
እናንተ ደጆች፣ ራሳችሁን ቀና አድርጉ፤እናንተ ጥንታዊ በሮች፣ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ ይገባ ዘንድ ተከፈቱ! |
ይህ ክብር የተጎናጸፈ ንጉሥ ማን ነው? ብርቱና ኃያል የሆነው ይሖዋ ነው፤በውጊያ ኃያል የሆነው ይሖዋ ነው። |
እናንተ ደጆች፣ ራሳችሁን ቀና አድርጉ፤እናንተ ጥንታዊ በሮች፣ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ ይገባ ዘንድ ተከፈቱ! |
ይህ ክብር የተጎናጸፈ ንጉሥ ማን ነው? የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ነው፤ ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ እሱ ነው። (ሴላ) |
እናንተ ሕዝቦች ሁሉ፣ እጆቻችሁን አጨብጭቡ። በድል አድራጊነት ለአምላክ እልል በሉ። |
ልዑሉ ይሖዋ እጅግ የሚያስፈራ ነውና፤በመላው ምድር ላይ ታላቅ ንጉሥ ነው። |
ሕዝቦችን ለእኛ ያስገዛል፤ብሔራትም ከእግራችን በታች እንዲሆኑ ያደርጋል። |
የሚወደውን የያዕቆብን መመኪያርስታችን አድርጎ ይመርጥልናል። (ሴላ) |
አምላክ በእልልታ አረገ፤ይሖዋ በቀንደ መለከት ድምፅ ወደ ላይ ወጣ። |
ለአምላክ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ። ለንጉሣችን የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ። |
አምላክ የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ ማስተዋልም ይኑራችሁ። |
አምላክ በብሔራት ላይ ነግሦአል። በቅዱስ ዙፋኑ ላይ ተቀምጧል። |
የሕዝቡ መሪዎች ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋርአንድ ላይ ተሰብስበዋል። የምድር ገዢዎች የአምላክ ናቸውና። እሱ እጅግ ከፍ ከፍ ብሏል። |
“ከወጣትነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ ያጠቁኝ ነበር”፤ እስራኤል እንዲህ ይበል፦ |
“ከወጣትነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ ያጠቁኝ ነበር፤ሆኖም ሊያሸንፉኝ አልቻሉም። |
አራሾች ጀርባዬን አረሱት፤ትልማቸውንም አስረዘሙት።” |
ይሖዋ ግን ጻድቅ ነው፤የክፉዎችን ገመድ በጣጥሷል። |
ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ፣ኀፍረት ይከናነባሉ፤ ተዋርደውም ወደኋላቸው ይመለሳሉ። |
ከመነቀሉ በፊት እንደሚጠወልግ፣በጣሪያ ላይ እንደበቀለ ሣር ይሆናሉ፤ |
እንዲህ ዓይነቱ ሣር የአጫጁን እጅ፣ነዶ የሚሰበስበውንም ሰው ክንዶች ሊሞላ አይችልም። |
በዚያ የሚያልፉ ሰዎች “የይሖዋ በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤በይሖዋ ስም እንባርካችኋለን” አይሉም። |
በይሖዋ የሚታመኑ፣ፈጽሞ ሳይናወጥ ለዘላለም ጸንቶ እንደሚኖረውእንደ ጽዮን ተራራ ናቸው። |
ተራሮች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንዳሉ ሁሉ፣ይሖዋም ከአሁን ጀምሮ ለዘላለምበሕዝቡ ዙሪያ ይሆናል። |
ጻድቃን ትክክል ያልሆነ ነገር መሥራት እንዳይጀምሩ፣የክፋት በትር ለጻድቃን በተሰጠ ምድር ላይ አይኖርም። |
ይሖዋ ሆይ፣ ለጥሩ ሰዎች፣ለልበ ቅኖች መልካም ነገር አድርግ። |
ወደ ጠማማ መንገዳቸው ዞር የሚሉትን፣ይሖዋ ከክፉ አድራጊዎች ጋር ያስወግዳቸዋል። በእስራኤል ሰላም ይስፈን። |
ይሖዋ ነገሠ! ግርማ ተጎናጽፏል፤ይሖዋ ብርታት ለብሷል፤እንደ ቀበቶ ታጥቆታል። ምድር በጽኑ ተመሥርታለች፤ልትናወጥ አትችልም። |
ዙፋንህ ከብዙ ዘመናት በፊት ጸንቶ የተመሠረተ ነው፤አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ወንዞቹ ጎረፉ፤ወንዞቹ ጎረፉ፤ አስገመገሙም፤ወንዞቹ ይጎርፋሉ፤ ደግሞም በኃይል ይላተማሉ። |
ከብዙ ውኃዎች ድምፅ፣ኃይለኛ ከሆነው የባሕር ማዕበልም በላይ፣ይሖዋ ከፍ ባለ ቦታ ግርማ ተጎናጽፏል። |
ማሳሰቢያዎችህ እጅግ አስተማማኝ ናቸው። ይሖዋ ሆይ፣ ቤትህ ለዘላለሙ በቅድስና ያጌጠ ነው። |
ይሖዋ ብርሃኔና አዳኜ ነው። ማንን እፈራለሁ? ይሖዋ የሕይወቴ ተገን ነው። ማን ያሸብረኛል? |
ክፉዎች ሥጋዬን ለመብላት ባጠቁኝ ጊዜ፣ተሰናክለው የወደቁት ባላጋራዎቼና ጠላቶቼ ናቸው። |
ሠራዊት በዙሪያዬ ቢሰፍርም፣ልቤ በፍርሃት አይዋጥም። ጦርነት ቢከፈትብኝም እንኳበልበ ሙሉነት እመላለሳለሁ። |
ይሖዋን አንድ ነገር ለመንኩት፤ምኞቴም ይኸው ነው፦በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በይሖዋ ቤት እኖር ዘንድ፣ይሖዋ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን በትኩረት እመለከት ዘንድ፣ቤተ መቅደሱንም በአድናቆት አይ ዘንድ ነው። |
በመዓት ቀን በመጠለያው ይሸሽገኛል፤ሚስጥራዊ ቦታ በሆነው ድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛል፤ከፍ ባለ ዓለት ላይ ያስቀምጠኛል። |
በመሆኑም ራሴ በዙሪያዬ ካሉ ጠላቶቼ በላይ ከፍ ብሏል፤በድንኳኑ ውስጥ በእልልታ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ። |
ይሖዋ ሆይ፣ በምጮኽበት ጊዜ ስማኝ፤ሞገስ አሳየኝ፤ መልስም ስጠኝ። |
ልቤ በአንተ ቦታ ሆኖ ሲናገር “ፊቴን ፈልጉ” ብሏል። ይሖዋ ሆይ፣ ፊትህን እሻለሁ። |
ፊትህን ከእኔ አትሰውር። አገልጋይህን ተቆጥተህ ፊት አትንሳው። አንተ ረዳቴ ነህ፤አዳኝ አምላኬ ሆይ፣ ከእኔ አትለይ፤ አትተወኝም። |
የገዛ አባቴና እናቴ ቢተዉኝ እንኳይሖዋ ራሱ ይቀበለኛል። |
ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረኝ፤ከጠላቶቼ ጥበቃ እንዳገኝ ቀና በሆነ መንገድ ምራኝ። |
ለጠላቶቼ አሳልፈህ አትስጠኝ፤ሐሰተኛ ምሥክሮች በእኔ ላይ ተነስተዋልና፤ደግሞም እኔን ለማጥቃት ይዝቱብኛል። |
በሕያዋን ምድር የይሖዋን ጥሩነት አያለሁ የሚል እምነት ባይኖረኝ ኖሮምን ይውጠኝ ነበር! |
ይሖዋን ተስፋ አድርግ፤ደፋር ሁን፤ ልብህም ይጽና። አዎ፣ ይሖዋን ተስፋ አድርግ። |
ብሔራት የታወኩት ለምንድን ነው?ሕዝቦችስ ከንቱ ነገር የሚያጉተመትሙት ለምንድን ነው? |
የምድር ነገሥታት ተሰለፉ፤ከፍተኛ ባለሥልጣናትም በአንድነት ተሰብስበውበይሖዋና እሱ በቀባው ላይ ተነሱ። |
“ሰንሰለታቸውን እንበጥስ፤ገመዳቸውንም እናስወግድ!” ይላሉ። |
በሰማያት በዙፋን ላይ የተቀመጠው ይስቃል፤ይሖዋ ይሳለቅባቸዋል። |
በዚያን ጊዜ በቁጣ ይናገራቸዋል፤በሚነድ ቁጣውም ያሸብራቸዋል፤ |
እንዲህም ይላቸዋል፦ “እኔ ራሴ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይንጉሤን ሾምኩ።” |
የይሖዋን ድንጋጌ ልናገር፤እንዲህ ብሎኛል፦ “አንተ ልጄ ነህ፤እኔ ዛሬ ወለድኩህ። |
ጠይቀኝ፤ ብሔራትን ርስትህ፣የምድርንም ዳርቻዎች ግዛትህ አድርጌ እሰጥሃለሁ። |
በብረት በትረ መንግሥት ትሰብራቸዋለህ፤እንደ ሸክላ ዕቃም ታደቃቸዋለህ።” |
እንግዲህ እናንተ ነገሥታት አስተውሉ፤እናንተ የምድር ፈራጆች እርማት ተቀበሉ። |
ይሖዋን በፍርሃት አገልግሉ፤ለእሱ በመንቀጥቀጥም ሐሴት አድርጉ። |
ልጁን አክብሩ፤ አለዚያ አምላክ ይቆጣል፤ከመንገዱም ትጠፋላችሁ፤ቁጣው ፈጥኖ ይነድዳልና። እሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ደስተኞች ናቸው። |
አምላክ ሆይ፣ በገዛ ጆሯችን ሰምተናል፤ከረጅም ጊዜ በፊት፣በእነሱ ዘመን ያከናወንካቸውን ተግባሮች፣አባቶቻችን ተርከውልናል። |
በእጅህ ብሔራትን አባረርክ፤በዚያም አባቶቻችንን አሰፈርክ። ብሔራትን ድል አድርገህ አባረርካቸው። |
ምድሪቱን የወረሱት በገዛ ሰይፋቸው አይደለም፤ድል ያጎናጸፋቸውም የገዛ ክንዳቸው አይደለም። ከዚህ ይልቅ በእነሱ ደስ ስለተሰኘህቀኝ እጅህ፣ ክንድህና የፊትህ ብርሃን ይህን አድርጓል። |
አምላክ ሆይ፣ አንተ ንጉሤ ነህ፤ለያዕቆብ ፍጹም ድል እዘዝ። |
በአንተ ኃይል ጠላቶቻችንን እንመክታለን፤በእኛ ላይ የተነሱትን በስምህ እንረግጣለን። |
በቀስቴ አልታመንምና፤ሰይፌም ሊያድነኝ አይችልም። |
ከጠላቶቻችን ያዳንከን፣የሚጠሉንን ሰዎች ያዋረድካቸው አንተ ነህ። |
ቀኑን ሙሉ ለአምላክ ውዳሴ እናቀርባለን፤ስምህንም ለዘላለም እናመሰግናለን። (ሴላ) |
አሁን ግን ትተኸናል፤ ደግሞም አዋርደኸናል፤ከሠራዊታችንም ጋር አብረህ አትወጣም። |
ከጠላታችን ፊት እንድንሸሽ ታደርገናለህ፤የሚጠሉን ሰዎች የፈለጉትን ሁሉ ይወስዱብናል። |
እንደ በግ እንዲበሉን ለጠላቶቻችን አሳልፈህ ሰጠኸን፤በብሔራት መካከል በተንከን። |
ሕዝብህን በማይረባ ዋጋ ሸጥክ፤ከሽያጩ ያገኘኸው ትርፍ የለም። |
በጎረቤቶቻችን ዘንድ መሳለቂያ አደረግከን፤በዙሪያችን ያሉት ሁሉ እንዲያላግጡብንና እንዲዘብቱብን አደረግክ። |
በብሔራት መካከል መቀለጃ እንድንሆን፣ሕዝቦችም ራሳቸውን እንዲነቀንቁብን አደረግክ። |
ቀኑን ሙሉ በኀፍረት ተውጫለሁ፤ውርደትም ተከናንቤአለሁ፤ |
ይህም ከሚሳለቁና ከሚሳደቡ ሰዎች ድምፅ፣እንዲሁም ከሚበቀለን ጠላታችን የተነሳ ነው። |
ይህ ሁሉ በእኛ ላይ ደርሷል፤ እኛ ግን አልረሳንህም፤ቃል ኪዳንህንም አላፈረስንም። |
ልባችን አልሸፈተም፤እግራችንም ከመንገድህ አልወጣም። |
ይሁንና ቀበሮዎች በሚኖሩበት ቦታ ሰባብረኸናል፤በድቅድቅ ጨለማም ሸፍነኸናል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.