text stringlengths 4 267 |
|---|
የአምላካችንን ስም ረስተን፣ወይም ወደ ባዕድ አምላክ ለመጸለይ እጃችንን ዘርግተን ከሆነ፣ |
አምላክ ይህን አይደርስበትም? እሱ በልብ ውስጥ ያለውን ሚስጥር ያውቃል። |
ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ ሞትን እንጋፈጣለን፤እንደ እርድ በጎችም ተቆጠርን። |
ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ። ለምንስ ትተኛለህ? ንቃ! ለዘላለም አትጣለን። |
ፊትህን ለምን ትሰውራለህ? የደረሰብንን ጉስቁልናና ጭቆና የምትረሳው ለምንድን ነው? |
ወደ አፈር ተጥለናልና፤ሰውነታችን ከመሬት ጋር ተጣብቋል። |
እኛን ለመርዳት ተነስ! ስለ ታማኝ ፍቅርህ ስትል ታደገን። |
ዝም ብዬ አምላክን እጠባበቃለሁ። መዳን የማገኘው ከእሱ ዘንድ ነው። |
በእርግጥም እሱ ዓለቴና አዳኜ እንዲሁም አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው፤ከልክ በላይ አልናወጥም። |
አንድን ሰው ለመግደል ጥቃት የምትሰነዝሩበት እስከ መቼ ነው? ሁላችሁም እንዳዘመመ ግንብ፣ ሊወድቅ እንደተቃረበም የድንጋይ ቅጥር አደገኛ ናችሁ። |
ካለበት ከፍ ያለ ቦታ ሊጥሉት እርስ በርሳቸው ይማከራሉና፤በመዋሸት ደስ ይሰኛሉ። በአፋቸው ይባርካሉ፤ በልባቸው ግን ይራገማሉ። (ሴላ) |
ዝም ብዬ አምላክን እጠባበቃለሁ፤ምክንያቱም ተስፋዬ የሚመጣው ከእሱ ዘንድ ነው። |
በእርግጥም እሱ ዓለቴና አዳኜ እንዲሁም አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው፤በምንም ዓይነት አልናወጥም። |
የእኔ መዳንና ክብር የተመካው በአምላክ ላይ ነው። እሱ ጠንካራ ዓለቴና መጠጊያዬ ነው። |
ሰዎች ሆይ፣ ሁልጊዜ በእሱ ታመኑ። ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ። አምላክ መጠጊያችን ነው። (ሴላ) |
የሰው ልጆች እስትንፋስ ናቸው፤ሰዎች ከንቱ መመኪያ ናቸው። አንድ ላይ ሆነው በሚዛን ሲመዘኑ ከአየር እንኳ ይቀልላሉ። |
በዝርፊያ አትታመኑ፤ወይም በስርቆት እጠቀማለሁ ብላችሁ በከንቱ ተስፋ አታድርጉ። ሀብታችሁ ቢበዛ ልባችሁን በእሱ ላይ አትጣሉ። |
አምላክ አንድ ጊዜ ተናገረ፤ እኔም ይህን ሁለት ጊዜ ሰማሁ፦ ብርታት የአምላክ ነው። |
ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርም የአንተ ነው፤ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ትከፍላለህና። |
የመዳኔ አምላክ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣በቀን እጮኻለሁ፤በሌሊትም በፊትህ እቀርባለሁ። |
ጸሎቴ ወደ አንተ ይድረስ፤እርዳታ ለማግኘት የማሰማውን ጩኸት ለማዳመጥ ጆሮህን አዘንብል። |
ነፍሴ በመከራ ተሞልታለችና፤ሕይወቴም በመቃብር አፋፍ ላይ ነች። |
አሁንም እንኳ ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ሰዎች ጋር ተቆጥሬአለሁ፤ምስኪን ሰው ሆንኩ፤ |
ተገድለው በመቃብር ውስጥ እንደተጋደሙ፣ከእንግዲህ ፈጽሞ እንደማታስታውሳቸውናየአንተ እንክብካቤ እንደተቋረጠባቸው ሰዎች፣በሙታን መካከል ተተውኩ። |
አዘቅት ውስጥ ከተትከኝ፤በጨለማ በተዋጠ ስፍራ፣ ጥልቅ በሆነ ጉድጓድ ውስጥ አኖርከኝ። |
በላዬ ላይ ያረፈው ቁጣህ እጅግ ከብዶኛል፤በኃይለኛ ማዕበልህም አጥለቀለቅከኝ። (ሴላ) |
የሚያውቁኝን ሰዎች ከእኔ አራቅክ፤በእነሱ ፊት አስጸያፊ ነገር አደረግከኝ። ወጥመድ ውስጥ ገብቻለሁ፤ ማምለጥም አልቻልኩም። |
ከደረሰብኝ ጉስቁልና የተነሳ ዓይኔ ፈዘዘ። ይሖዋ ሆይ፣ ቀኑን ሙሉ አንተን እጣራለሁ፤እጆቼንም ወደ አንተ እዘረጋለሁ። |
ለሙታን ድንቅ ሥራዎች ታከናውናለህ? በሞት የተረቱትስ ተነስተው ሊያወድሱህ ይችላሉ? (ሴላ) |
ታማኝ ፍቅርህ በመቃብር፣ታማኝነትህስ በጥፋት ቦታ ይታወጃል? |
ያከናወንከው ድንቅ ሥራ በጨለማ፣ጽድቅህስ በተረሱ ሰዎች ምድር ይታወቃል? |
ይሖዋ ሆይ፣ እኔ ግን እርዳታ ለማግኘት አሁንም ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ጸሎቴም በየማለዳው ወደ አንተ ትደርሳለች። |
ይሖዋ ሆይ፣ ፊት የምትነሳኝ ለምንድን ነው? ፊትህንስ ከእኔ የምትሰውረው ለምንድን ነው? |
እኔ ከልጅነቴ ጀምሮየተጎሳቆልኩና ለመጥፋት የተቃረብኩ ነኝ፤እንዲደርሱብኝ ከፈቀድካቸው አስከፊ ነገሮች የተነሳ ደንዝዣለሁ። |
የሚነደው ቁጣህ በላዬ ላይ ወረደ፤አንተ ያመጣህብኝ ሽብር አጠፋኝ። |
ቀኑን ሙሉ እንደ ውኃ ከበበኝ፤በሁሉም አቅጣጫ ከቦ መውጫ አሳጣኝ። |
ወዳጆቼንና ባልንጀሮቼን ከእኔ አራቅክ፤ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ርቀህ የምትቆመው ለምንድን ነው? በመከራ ጊዜ ራስህን የምትሰውረው ለምንድን ነው? |
ክፉ ሰው በእብሪት ተነሳስቶ ምስኪኑን ያሳድዳል፤ይሁንና በወጠነው ሴራ ይያዛል። |
ክፉው ሰው በራስ ወዳድነት ምኞቱ ይኩራራልና፤ስግብግብ የሆነውንም ሰው ይባርካል፤נ [ኑን] ይሖዋንም ያቃልላል። |
ክፉው ሰው ከትዕቢቱ የተነሳ ምንም ምርምር አያደርግም፤“አምላክ የለም” ብሎ ያስባል። |
መንገዱ ሁልጊዜ የተሳካ ነው፤ሆኖም ፍርድህ እሱ ሊገነዘበው ከሚችለው በላይ ነው፤በጠላቶቹ ሁሉ ላይ ያፌዛል። |
በልቡ እንዲህ ይላል፦ “ፈጽሞ አልናወጥም፤ከትውልድ እስከ ትውልድምንም መከራ አይደርስብኝም።” |
አፉ በእርግማን፣ በውሸትና በዛቻ የተሞላ ነው፤ከምላሱ ሥር ችግርና ጉዳት የሚያስከትል ነገር አለ። |
በመንደሮቹ አጠገብ አድብቶ ይጠብቃል፤ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ ንጹሑን ሰው ይገድላል። ע [አይን] ዓይኖቹ ያልታደለውን ሰለባ ይጠባበቃሉ። |
በጎሬው ውስጥ እንዳለ አንበሳ በተደበቀበት ቦታ አድፍጦ ይጠብቃል። ምስኪኑን ሰው ለመያዝ ይጠባበቃል። ምስኪኑን ሰው መረቡ ውስጥ አስገብቶ ይይዘዋል። |
ሰለባው ይደቅቃል፤ ደግሞም ይወድቃል፤ያልታደሉ ሰዎች መዳፉ ውስጥ ይወድቃሉ። |
በልቡ እንዲህ ይላል፦ “አምላክ ረስቷል። ፊቱን አዙሯል። ፈጽሞ ልብ አይልም።” |
ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ። አምላክ ሆይ፣ እጅህን አንሳ። ምስኪኖችን አትርሳ። |
ክፉው ሰው አምላክን ያቃለለው ለምንድን ነው? በልቡ “ተጠያቂ አታደርገኝም” ይላል። |
አንተ ግን ችግርንና መከራን ትመለከታለህ። ደግሞም አይተህ እርምጃ ትወስዳለህ። ያልታደለው ሰለባ ወደ አንተ ይጮኻል፤አንተ አባት ለሌለው ልጅ ረዳቱ ነህ። |
ክፉና መጥፎ የሆነውን ሰው ክንድ ስበር፤ከዚያ በኋላ ክፋቱን በምትፈልግበት ጊዜጨርሶ አታገኘውም። |
ይሖዋ ለዘላለም ንጉሥ ነው። ብሔራት ከምድር ጠፍተዋል። |
ይሖዋ ሆይ፣ የዋሆች የሚያቀርቡትን ልመና ግን ትሰማለህ። ልባቸውን ታጸናለህ፤ ደግሞም ትኩረት ትሰጣቸዋለህ። |
በምድር ላይ ያለ ሟች የሆነ ሰው ከእንግዲህ እንዳያሸብራቸው፣አባት ለሌለው ልጅና ለተደቆሱ ሰዎች ፍትሕ ታሰፍናለህ። |
እናንተ የሰው ልጆች፣ ዝም ብላችሁ እያለ ስለ ጽድቅ ልትናገሩ ትችላላችሁ? በቅንነትስ መፍረድ ትችላላችሁ? |
ይልቁንም በልባችሁ ክፋት ትጠነስሳላችሁ፤እጆቻችሁም በምድሪቱ ላይ ዓመፅ ያስፋፋሉ። |
ክፉዎች፣ ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ መንገድ ስተዋል፤ከተወለዱበት ጊዜ አንስቶ ሥርዓት የሌላቸውና ውሸታሞች ናቸው። |
መርዛቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤ጆሮውን እንደ ደፈነ ጉበና ደንቆሮ ናቸው። |
ድግምተኞቹ ምንም ያህል ችሎታ ቢኖራቸውጉበናው ድምፃቸውን አይሰማም። |
አምላክ ሆይ፣ ጥርሳቸውን ከአፋቸው አርግፍ! ይሖዋ ሆይ፣ የእነዚህን አንበሶች መንጋጋ ሰባብር! |
ፈስሶ እንደሚያልቅ ውኃ ይጥፉ። አምላክ ደጋኑን ወጥሮ በቀስቶቹ ይጣላቸው። |
ሲሄድ እንደሚቀልጥ ቀንድ አውጣ ይሁኑ፤ፀሐይን ፈጽሞ እንደማያይ ከሴት የተወለደ ጭንጋፍ ይሁኑ። |
በእሳት የተቀጣጠለው እሾህ ድስታችሁን ሳያሞቀው፣አምላክ እርጥቡንም ሆነ የሚነደውን ቅርንጫፍ እንደ አውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስደዋል። |
ጻድቅ ሰው በክፉዎች ላይ የተወሰደውን የበቀል እርምጃ በማየቱ ደስ ይለዋል፤እግሮቹ በእነሱ ደም ይርሳሉ። |
በዚህ ጊዜ ሰዎች እንዲህ ይላሉ፦ “በእርግጥ ጻድቁ ብድራት ይቀበላል። በእውነትም በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ።” |
ያህን አወድሱ! ይሖዋ ጥሩ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። |
የይሖዋን ታላላቅ ሥራዎች ሙሉ በሙሉ ሊያስታውቅ የሚችለው ማን ነው?ወይስ የሚያስመሰግኑ ተግባሮቹን ሁሉ ሊያውጅ የሚችለው ማን ነው? |
ፍትሐዊ ድርጊት የሚፈጽሙ፣ምንጊዜም ትክክል የሆነውን የሚያደርጉ ደስተኞች ናቸው። |
ይሖዋ ሆይ፣ ለሕዝብህ ሞገስ በምታሳይበት ጊዜ እኔንም አስታውሰኝ። ተንከባከበኝ፤ ደግሞም አድነኝ፤ |
ይህም ለተመረጡ አገልጋዮችህ የምታሳየውን ጥሩነት እንድቀምስ፣ከሕዝብህ ጋር ሐሴት እንዳደርግ፣ከርስትህም ጋር አንተን በኩራት እንዳወድስ ነው። |
እኛም እንደ አባቶቻችን ኃጢአት ሠርተናል፤በድለናል፤ ክፉ ነገርም አድርገናል። |
አባቶቻችን በግብፅ በነበሩበት ጊዜ፣ ድንቅ ሥራዎችህን በአድናቆት አልተመለከቱም። የታማኝ ፍቅርህን ብዛት አላስታወሱም፤ከዚህ ይልቅ በባሕሩ አጠገብ ይኸውም ቀይ ባሕር አጠገብ ዓመፁ። |
ይሁንና ኃያልነቱ እንዲታወቅ ሲል፣ለስሙ ብሎ አዳናቸው። |
ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ ባሕሩም ደረቀ፤በበረሃ የሚሄዱ ያህል በጥልቅ ውኃው መካከል መራቸው፤ |
ከባላጋራዎቻቸው እጅ አዳናቸው፤ከጠላቶቻቸውም እጅ ታደጋቸው። |
ውኃው ጠላቶቻቸውን ዋጠ፤ከእነሱ አንድ ሰው እንኳ አልዳነም። |
በዚያን ጊዜ በገባው ቃል አመኑ፤የውዳሴ መዝሙር ይዘምሩለት ጀመር። |
ይሁን እንጂ ያደረገውን ነገር ወዲያውኑ ረሱ፤እሱ የሚሰጣቸውን ምክር በትዕግሥት አልጠበቁም። |
በምድረ በዳ በራስ ወዳድነት ምኞት ተሸነፉ፤በበረሃ አምላክን ተፈታተኑት። |
እሱም የለመኑትን ሰጣቸው፤ነገር ግን በሚያመነምን በሽታ መታቸው። |
በሰፈር ውስጥ በሙሴ፣ደግሞም የይሖዋ ቅዱስ አገልጋይ በሆነው በአሮን ቀኑ። |
በዚህ ጊዜ ምድር ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤ከአቤሮንም ጋር ያበሩትን ሰለቀጠች። |
እሳትም በማኅበራቸው መካከል ነደደች፤ነበልባልም ክፉዎችን በላች። |
በኮሬብ ጥጃ ሠሩ፤ከብረት ለተሠራም ሐውልት ሰገዱ፤ |
ሣር በሚበላ ኮርማ ምስልክብሬን ለወጡ። |
በግብፅ ታላላቅ ነገሮች ያደረገውን፣አዳኛቸው የሆነውን አምላክ ረሱ፤ |
በካም ምድር አስደናቂ ሥራዎች፣በቀይ ባሕር የሚያስፈሩ ነገሮች ያከናወነውን አምላክ ዘነጉ። |
እንዲጠፉ ሊያዝዝ ምንም አልቀረውም ነበር፤ሆኖም እሱ የመረጠው አገልጋዩ ሙሴ፣አጥፊ ቁጣውን እንዲመልስ አምላክን ተማጸነ። |
ከዚያም የተወደደችውን ምድር ናቁ፤በገባው ቃል ላይ እምነት አልነበራቸውም። |
በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው ማጉረምረማቸውን ቀጠሉ፤የይሖዋን ድምፅ አልሰሙም። |
በመሆኑም በምድረ በዳ ሊጥላቸው፣ስለ እነሱ እጁን አንስቶ ማለ፤ |
ዘራቸውን በብሔራት መካከል እንደሚጥል፣በየአገሩ እንደሚበትናቸውም ማለ። |
ከዚያም በፌጎር የነበረውን ባአል አመለኩ፤ለሙታን የቀረቡትን መሥዋዕቶችም በሉ። |
በሥራቸው አምላክን አስቆጡት፤በመካከላቸውም መቅሰፍት ተነሳ። |
ሆኖም ፊንሃስ ተነስቶ እርምጃ በወሰደ ጊዜ፣መቅሰፍቱ ተገታ። |
ይህም በትውልዶች ሁሉ፣ ለዘላለምጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት። |
በመሪባ ውኃ አጠገብ አምላክን አስቆጡት፤በእነሱም የተነሳ ሙሴ ችግር ላይ ወደቀ። |
መንፈሱን አስመረሩት፤እሱም በከንፈሮቹ በችኮላ ተናገረ። |
ይሖዋ ባዘዛቸው መሠረት፣ሕዝቦቹን ከማጥፋት ወደኋላ አሉ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.