text
stringlengths
4
267
ይልቁንም በዚያ ከነበሩት ብሔራት ጋር ተቀላቀሉ፤የእነሱንም መንገድ ተከተሉ።
ጣዖቶቻቸውን አመለኩ፤እነሱም ወጥመድ ሆኑባቸው።
ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንለአጋንንት መሥዋዕት አድርገው ያቀርቡ ነበር።
ንጹሕ ደም፣ይኸውም ለከነአን ጣዖቶች የሠዉአቸውንየገዛ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ደም አፈሰሱ፤ምድሪቱም በደም ተበከለች።
በሥራቸው ረከሱ፤በድርጊታቸውም መንፈሳዊ ምንዝር ፈጸሙ።
በመሆኑም የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፤ርስቱንም ተጸየፈ።
በተደጋጋሚ ጊዜያት በብሔራት እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ይህም የሚጠሏቸው ሰዎች እንዲገዟቸው ነው።
ጠላቶቻቸው ጨቆኗቸው፤ለእነሱም ሥልጣን ተገዢ ሆኑ።
ብዙ ጊዜ ታደጋቸው፤እነሱ ግን ያምፁና ለመታዘዝ አሻፈረኝ ይሉ ነበር፤ከሠሩት ጥፋት የተነሳም ተዋረዱ።
እሱ ግን ጭንቀታቸውን ይመለከት፣እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትንም ጩኸት ይሰማ ነበር።
ለእነሱ ሲል ቃል ኪዳኑን ያስታውስ ነበር፤ታላቅ በሆነው ታማኝ ፍቅሩ ተገፋፍቶ ያዝንላቸው ነበር።
የማረኳቸው ሰዎች ሁሉበሐዘኔታ እንዲይዟቸው ያደርግ ነበር።
ይሖዋ አምላካችን ሆይ፣ አድነን፤ደግሞም ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እንድናቀርብ፣አንተንም በማወደስ ሐሴት እንድናደርግ፣ከብሔራት ሰብስበን።
የእስራኤል አምላክ ይሖዋከዘላለም እስከ ዘላለም ይወደስ፤ ሕዝቦችም ሁሉ “አሜን!” ይበሉ። ያህን አወድሱ!
ከታማኝ ፍቅርህና ከታማኝነትህ የተነሳለእኛ ሳይሆን፣ ይሖዋ ሆይ፣ ለእኛ ሳይሆን፣ለስምህ ክብር ስጥ።
ብሔራት “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?
አምላካችን ያለው በሰማያት ነው፤እሱ የወደደውን ሁሉ ያደርጋል።
የእነሱ ጣዖቶች ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣የሰው እጅ ሥራ ናቸው።
አፍ አላቸው፤ መናገር ግን አይችሉም፤ዓይን አላቸው፤ ማየት ግን አይችሉም፤
ጆሮ አላቸው፤ መስማት ግን አይችሉም፤አፍንጫ አላቸው፤ ማሽተት ግን አይችሉም፤
እጅ አላቸው፤ መዳሰስ ግን አይችሉም፤እግር አላቸው፤ መራመድ ግን አይችሉም፤በጉሮሯቸው የሚያሰሙት ድምፅ የለም።
የሚሠሯቸውም ሆኑ የሚታመኑባቸው ሁሉ፣እንደ እነሱ ይሆናሉ።
እስራኤል ሆይ፣ በይሖዋ ታመኑ፤እሱ ረዳታቸውና ጋሻቸው ነው።
የአሮን ቤት ሆይ፣ በይሖዋ ታመኑ፤እሱ ረዳታቸውና ጋሻቸው ነው።
እናንተ ይሖዋን የምትፈሩ፣ በይሖዋ ታመኑ፤እሱ ረዳታቸውና ጋሻቸው ነው።
ይሖዋ ያስታውሰናል፤ ደግሞም ይባርከናል፤የእስራኤልን ቤት ይባርካል፤የአሮንን ቤት ይባርካል።
ይሖዋ እሱን የሚፈሩትን፣ታናናሾችንም ሆነ ታላላቆችን ይባርካል።
ይሖዋ እናንተን፣አዎ፣ እናንተንና ልጆቻችሁን ያበዛል።
ሰማይንና ምድርን የሠራውይሖዋ ይባርካችሁ።
ሰማያት የይሖዋ ናቸው፤ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።
ሙታንም ሆኑ ወደ ዝምታው ዓለም የሚወርዱ ሁሉ፣ያህን አያወድሱም።
እኛ ግን ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣ያህን እናወድሳለን። ያህን አወድሱ!
ብርታታችን ለሆነው አምላክ እልል በሉ። ለያዕቆብ አምላክ በድል አድራጊነት ስሜት ጩኹ።
ሙዚቃውን መጫወት ጀምሩ፤ አታሞም ምቱ፤ደስ የሚያሰኘውን በገና ከባለ አውታር መሣሪያ ጋር ተጫወቱ።
አዲስ ጨረቃ በምትታይበት፣ሙሉ ጨረቃም ወጥታ በዓል በምናከብርበት ዕለት ቀንደ መለከት ንፉ።
ይህ ለእስራኤል የተሰጠ ድንጋጌ፣የያዕቆብም አምላክ ያስተላለፈው ውሳኔ ነውና።
በግብፅ ምድር ላይ ባለፈ ጊዜ፣ይህን ለዮሴፍ ማሳሰቢያ አድርጎ ሰጠው። እኔም የማላውቀውን ድምፅ ሰማሁ፦
“ሸክሙን ከትከሻው ላይ አነሳሁለት፤እጆቹ ቅርጫት ከመያዝ አረፉ።
በጨነቀህ ጊዜ ጠራኸኝ፤ እኔም ታደግኩህ፤ከነጎድጓዳማው ደመና መለስኩልህ። የመሪባ ውኃዎች ባሉበት ስፍራ ፈተንኩህ። (ሴላ)
ሕዝቤ ሆይ፣ ስማኝ፤ እኔም እመሠክርብሃለሁ። እስራኤል ሆይ፣ ምነው ብታዳምጠኝ!
በመካከልህ እንግዳ አምላክ አይኖርም፤ለባዕድ አምላክም አትሰግድም።
ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ፣እኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ። አፍህን በሰፊው ክፈት፤ እኔም በምግብ እሞላዋለሁ።
ሕዝቤ ግን ድምፄን አልሰማም፤እስራኤል ለእኔ አይገዛም።
በመሆኑም እልኸኛ ልባቸውን እንዲከተሉ ተውኳቸው፤ትክክል መስሎ የታያቸውን አደረጉ።
ምነው ሕዝቤ ቢያዳምጠኝ ኖሮ!ምነው እስራኤል በመንገዴ ቢመላለስ ኖሮ!
ጠላቶቻቸውን ወዲያውኑ ባንበረከክኋቸው፣እጄን በባላጋራዎቻቸው ላይ በሰነዘርኩ ነበር።
ይሖዋን የሚጠሉ በፊቱ ይሸማቀቃሉ፤የሚደርስባቸውም ነገር ዘላለማዊ ነው።
እሱ ግን ምርጡን ስንዴ ይመግባችኋል፤ከዓለት በሚገኝ ማርም ያጠግባችኋል።”
አምላክ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁና ጠብቀኝ።
ይሖዋን እንዲህ አልኩት፦ “አንተ ይሖዋ ነህ፤ ለእኔ የጥሩ ነገሮች ምንጭ አንተ ነህ።
ደግሞም በምድር ላይ ያሉት ቅዱሳን፣ክብር የተላበሱት አገልጋዮች እጅግ ደስ ያሰኙኛል።”
ሌሎች አማልክትን የሚከተሉ ሐዘናቸውን ያበዛሉ። እንደ እነሱ ደምን የመጠጥ መባ አድርጌ አላቀርብም፤በከንፈሬም ስማቸውን አላነሳም።
ይሖዋ ድርሻዬ፣ ዕጣ ፋንታዬና ጽዋዬ ነው። ርስቴን ትጠብቅልኛለህ።
ለእኔ ርስት አድርገህ ለመስጠት የለካኸው ቦታ ያማረ ነው። አዎ፣ ባገኘሁት ርስት ረክቻለሁ።
ምክር የሰጠኝን ይሖዋን አወድሳለሁ። በሌሊትም እንኳ በውስጤ ያለው ሐሳብ ያርመኛል።
ይሖዋን ሁልጊዜ በፊቴ አደርገዋለሁ። እሱ በቀኜ ስላለ ፈጽሞ አልናወጥም።
ስለዚህ ልቤ ሐሴት ያደርጋል፤ ሁለንተናዬ ደስ ይለዋል። ያለ ስጋትም እኖራለሁ።
መቃብር ውስጥ አትተወኝምና። ታማኝ አገልጋይህ ጉድጓድ እንዲያይ አትፈቅድም።
የሕይወትን መንገድ አሳወቅከኝ። በፊትህ ብዙ ደስታ አለ፤በቀኝህ ለዘላለም ደስታ አለ።
ይሖዋ ጥሩ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
ይሖዋ የዋጃቸው፣አዎ፣ ከጠላት እጅ የዋጃቸው ይህን ይበሉ፤
ከምሥራቅና ከምዕራብ፣ከሰሜንና ከደቡብ፣ከየአገሩ አንድ ላይ የሰበሰባቸው ይህን ይናገሩ።
በምድረ በዳ፣ በበረሃም ተቅበዘበዙ፤ሊኖሩ ወደሚችሉበት ከተማ የሚወስድ መንገድ አላገኙም።
ተርበውና ተጠምተው ነበር፤ኃይላቸው ከመሟጠጡ የተነሳ ተዝለፈለፉ።
በተጨነቁ ጊዜ ወደ ይሖዋ ይጮኹ ነበር፤እሱም ከደረሰባቸው መከራ ታደጋቸው።
መኖር ወደሚችሉበት ከተማ እንዲደርሱበትክክለኛው መንገድ መራቸው።
ሕዝቦች ስለ ታማኝ ፍቅሩናለሰው ልጆች ስላደረጋቸው አስደናቂ ሥራዎች ይሖዋን ያመስግኑት።
እሱ የተጠማውን አርክቷልና፤የተራበውንም በመልካም ነገሮች አጥግቧል።
አንዳንዶች በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የሚኖሩ፣በመከራ ውስጥ ያሉና በሰንሰለት የተጠፈሩ እስረኞች ነበሩ።
በአምላክ ቃል ላይ ዓምፀዋልና፤የልዑሉን አምላክ ምክር ንቀዋል።
ስለዚህ በደረሰባቸው መከራ ልባቸው እንዲለሰልስ አደረገ፤ተሰናከሉ፤ የሚረዳቸውም አንዳች ሰው አልነበረም።
በተጨነቁ ጊዜ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ተጣሩ፤እሱም ከደረሰባቸው መከራ አዳናቸው።
ከድቅድቅ ጨለማ አወጣቸው፤የታሰሩበትንም ሰንሰለት በጠሰ።
ሕዝቦች ስለ ታማኝ ፍቅሩናለሰው ልጆች ስላደረጋቸው አስደናቂ ሥራዎች ይሖዋን ያመስግኑት።
እሱ የመዳብ በሮችን ሰብሯልና፤የብረት መወርወሪያዎችንም ቆርጧል።
ከጥፋታቸውና ከበደላቸው የተነሳሞኝ ሆኑ፤ ለመከራም ተዳረጉ።
የምግብ ፍላጎታቸው ሙሉ በሙሉ ጠፋ፤ወደ ሞት ደጆች ቀረቡ።
በተጨነቁ ጊዜ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ይጣሩ ነበር፤እሱም ከደረሰባቸው መከራ ያድናቸው ነበር።
ቃሉን ልኮ ይፈውሳቸው፣ከተያዙበትም ጉድጓድ ይታደጋቸው ነበር።
ሕዝቦች ስለ ታማኝ ፍቅሩናለሰው ልጆች ስላደረጋቸው አስደናቂ ሥራዎች ይሖዋን ያመስግኑት።
የምስጋና መሥዋዕት ያቅርቡ፤በእልልታም ሥራዎቹን ያስታውቁ።
በባሕር ላይ በመርከቦች የሚጓዙ፣በሰፋፊ ውኃዎች ላይ ንግድ የሚያካሂዱ፣
እነሱ የይሖዋን ሥራዎች፣በጥልቁም ውስጥ ያከናወናቸውን አስደናቂ ነገሮች ተመልክተዋል፤
እሱ በቃሉ አውሎ ነፋስ ሲያስነሳ፣የባሕሩንም ማዕበል ሲያናውጥ አይተዋል።
ወደ ሰማይ ይወጣሉ፣ወደ ጥልቆችም ይወርዳሉ። እየመጣባቸው ካለው መከራ የተነሳ ሐሞታቸው ፈሰሰ።
እንደሰከረ ሰው ይንገዳገዳሉ፤ ደግሞም ይወላገዳሉ፤ችሎታቸውም ሁሉ የፈየደላቸው ነገር የለም።
በዚህ ጊዜ ከጭንቀታቸው የተነሳ ወደ ይሖዋ ይጮኻሉ፤እሱም ከደረሰባቸው መከራ ይታደጋቸዋል።
አውሎ ነፋሱ እንዲቆም ያደርጋል፤የባሕሩም ሞገዶች ጸጥ ይላሉ።
ሞገዶቹ ጸጥ ሲሉ ሰዎቹ ሐሴት ያደርጋሉ፤እሱም ወዳሰቡት ወደብ ይመራቸዋል።
ሕዝቦች ስለ ታማኝ ፍቅሩናለሰው ልጆች ስላደረጋቸው አስደናቂ ሥራዎች ይሖዋን ያመስግኑት።
በሕዝብ ጉባኤ መካከል ከፍ ከፍ ያድርጉት፤በሽማግሌዎችም ሸንጎ ያወድሱት።
እሱ ወንዞችን ወደ በረሃ፣የውኃ ምንጮችንም ወደ ደረቅ መሬት ይለውጣል፤
ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሳፍሬያማዋን አገር ጨዋማ የሆነ ጠፍ ምድር ያደርጋታል።
በረሃውን ቄጠማ የሞላበት ኩሬ፣ደረቁንም ምድር የውኃ ምንጭ ያደርጋል።
ሊኖሩ የሚችሉበትን ከተማ እንዲመሠርቱ፣የተራቡ ሰዎችን በዚያ ያኖራል።
መሬት ላይ ዘሩ፤ ወይንም ተከሉ፤መሬቱም ብዙ ምርት ሰጠ።
እሱ ይባርካቸዋል፤ እነሱም እጅግ ይበዛሉ፤የከብቶቻቸው ብዛት እንዲያንስ አያደርግም።
ሆኖም ከደረሰባቸው ጭቆና፣ መከራና ሐዘን የተነሳዳግመኛ ቁጥራቸው ተመናመነ፤ ተዋረዱም።
በታላላቅ ሰዎች ላይ የውርደት መዓት ያዘንባል፤መንገድ በሌለበት ጠፍ መሬትም እንዲቅበዘበዙ ያደርጋል።
ድሆችን ግን ከጭቆና ይጠብቃል፤ቤተሰባቸውንም እንደ መንጋ ያበዛል።