text stringlengths 4 267 |
|---|
የምትወዳቸው ሰዎች እንዲድኑበቀኝ እጅህ ታደገን፤ ደግሞም መልስ ስጠኝ። |
አምላክ በቅድስናው እንዲህ ብሏል፦ “ሐሴት አደርጋለሁ፤ ሴኬምን ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤የሱኮትንም ሸለቆ አከፋፍላለሁ። |
ጊልያድም ሆነ ምናሴ የእኔ ናቸው፤ኤፍሬምም የራስ ቁሬ ነው፤ይሁዳ በትረ መንግሥቴ ነው። |
ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው። በኤዶም ላይ ጫማዬን እጥላለሁ። በፍልስጤም ላይ በድል አድራጊነት እጮኻለሁ።” |
ወደተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል? እስከ ኤዶም ድረስ ማን ይመራኛል? |
አምላክ ሆይ፣ ገሸሽ ያደረግከን አንተ አይደለህም?አምላካችን ሆይ፣ ከሠራዊታችን ጋር አብረህ አትወጣም። |
ከጭንቅ እንድንገላገል እርዳን፤የሰው ማዳን ከንቱ ነውና። |
አምላክ ኃይል ይሰጠናል፤ጠላቶቻችንንም ይረጋግጣቸዋል። |
ዓለቴ ይሖዋ ሆይ፣ ሁልጊዜ ወደ አንተ እጣራለሁ፤አንተም ጆሮ አትንፈገኝ። ዝም ካልከኝ፣ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱ ሰዎች እሆናለሁ። |
ወደ መቅደስህ ውስጠኛ ክፍል እጆቼን አንስቼ፣እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ በምጮኽበት ጊዜ ልመናዬን ስማ። |
ከክፉዎችና መጥፎ ነገር ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ጎትተህ አትውሰደኝ፤እነሱ በልባቸው ክፋት እያለ ከባልንጀሮቻቸው ጋር የሰላም ቃል የሚያወሩ ናቸው። |
ለሠሩት ሥራ፣እንደ ክፉ ልማዳቸው ክፈላቸው። ለእጃቸው ሥራ መልሰህ ክፈላቸው፤እንዳደረጉትም መልስላቸው። |
ይሖዋ ላከናወናቸው ነገሮች፣ለእጆቹም ሥራ ትኩረት አይሰጡምና። እሱ ያፈርሳቸዋል፤ ደግሞም አይገነባቸውም። |
እርዳታ ለማግኘት ያቀረብኩትን ልመና ስለሰማይሖዋ የተመሰገነ ይሁን። |
ይሖዋ ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ልቤ በእሱ ይተማመናል። ከእሱ እርዳታ ስላገኘሁ ልቤ ሐሴት ያደርጋል፤በመዝሙሬም አወድሰዋለሁ። |
ይሖዋ ለሕዝቡ ብርታት ነው፤ለቀባው ታላቅ መዳን የሚያስገኝ መሸሸጊያ ነው። |
ሕዝብህን አድን፤ ርስትህንም ባርክ። ለዘላለም እረኛ ሁናቸው፤ በክንድህም ተሸከማቸው። |
አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውከኝ? እኔን ከማዳን፣ ከደረሰብኝም ሥቃይ የተነሳ የማሰማውን ጩኸት ከመስማትየራቅከው ለምንድን ነው? |
አምላኬ ሆይ፣ በቀን ደጋግሜ እጣራለሁ፤ አንተ ግን አትመልስልኝም፤በሌሊትም ዝም ማለት አልቻልኩም። |
አንተ ግን ቅዱስ ነህ፤እስራኤል በሚያቀርበው ውዳሴ ተከበሃል። |
አባቶቻችን እምነታቸውን በአንተ ላይ ጣሉ፤በአንተ ተማመኑ፤ አንተም ሁልጊዜ ትታደጋቸው ነበር። |
ወደ አንተ ጮኹ፤ ደግሞም ዳኑ፤በአንተ ተማመኑ፤ የጠበቁት ሳይፈጸም ቀርቶም አላዘኑም። |
እኔ ግን ትል እንጂ ሰው አይደለሁም፤ሰው ያፌዘብኝ፣ ሕዝብም የናቀኝ ነኝ። |
የሚያዩኝ ሁሉ ያላግጡብኛል፤በንቀትና በፌዝ ጭንቅላታቸውን እየነቀነቁ እንዲህ ይሉኛል፦ |
“ራሱን ለይሖዋ በአደራ ሰጥቷል። እስቲ እሱ ይታደገው! በእሱ እጅግ የተወደደ ስለሆነ እሱ ያድነው!” |
ከማህፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ፤በእናቴ ጡት ተማምኜ እንድኖር ያደረግከኝ አንተ ነህ። |
ስወለድ ጀምሮ ለአንተ በአደራ ተሰጠሁ፤ከእናቴ ማህፀን ጀምሮ አንተ አምላኬ ነህ። |
ችግር ሊደርስብኝ ስለሆነ ከእኔ አትራቅ፤ደግሞም ሌላ ረዳት የለኝም። |
ብዙ ወይፈኖች ከበውኛል፤የባሳን ኃይለኛ ኮርማዎችም በዙሪያዬ ናቸው። |
ያደነውን እንደሚቦጫጭቅ የሚያገሳ አንበሳአፋቸውን በእኔ ላይ ከፈቱ። |
እንደ ውኃ ፈሰስኩ፤አጥንቶቼ ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ። ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤በውስጤም ቀለጠ። |
ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ፤ምላሴ ከላንቃዬ ጋር ተጣበቀ፤እንድሞትም ወደ ጉድጓድ አወረድከኝ። |
ውሾች ከበውኛልና፤እንደ ክፉ አድራጊዎች ሸንጎ በዙሪያዬ ሰፍረዋል፤እንደ አንበሳ ሆነው እጆቼና እግሮቼ ላይ ተረባረቡ። |
አጥንቶቼን ሁሉ መቁጠር እችላለሁ። እነሱም አዩኝ፤ ትኩር ብለውም ተመለከቱኝ። |
መደረቢያዎቼን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ፤በልብሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ። |
አንተ ግን ይሖዋ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ። አንተ ብርታቴ ነህ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን። |
ከሰይፍ አድነኝ፤ውድ ሕይወቴን ከውሾች መዳፍ ታደጋት፤ |
ከአንበሳ አፍና ከዱር በሬዎች ቀንድ አድነኝ፤መልስ ስጠኝ፤ ታደገኝም። |
ስምህን ለወንድሞቼ አሳውቃለሁ፤በጉባኤ መካከልም አወድስሃለሁ። |
እናንተ ይሖዋን የምትፈሩ፣ አወድሱት! እናንተ የያዕቆብ ዘር ሁሉ፣ ከፍ ከፍ አድርጉት! እናንተ የእስራኤል ዘር ሁሉ፣ ለእሱ ታላቅ አክብሮት አሳዩ። |
እሱ የተጨቆነውን ሰው መከራ አልናቀምና፤ ደግሞም አልተጸየፈም፤ፊቱን ከእሱ አልሰወረም። ለእርዳታ ወደ እሱ በጮኸ ጊዜ ሰምቶታል። |
በታላቅ ጉባኤ መካከል አወድስሃለሁ፤እሱን በሚፈሩት ፊት ስእለቴን እፈጽማለሁ። |
የዋሆች በልተው ይጠግባሉ፤ይሖዋን የሚፈልጉት እሱን ያወድሱታል። ለዘላለም ተደስታችሁ ኑሩ። |
የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ይሖዋን አስታውሰው ወደ እሱ ይዞራሉ። የሕዝቦች ነገዶች ሁሉ በፊትህ ይሰግዳሉ። |
ንግሥና የይሖዋ ነውና፤ብሔራትን ይገዛል። |
በምድር ያሉ ባለጸጎች ሁሉ ይበላሉ፤ ይሰግዳሉም፤ወደ አፈር የሚወርዱ ሁሉ በእሱ ፊት ይንበረከካሉ፤ከእነሱ መካከል አንዳቸውም ሕይወታቸውን ማቆየት አይችሉም። |
ዘሮቻቸው ያገለግሉታል፤መጪው ትውልድ ስለ ይሖዋ ይነገረዋል። |
መጥተው ጽድቁን ያወራሉ። ገና ለሚወለድ ሕዝብ ያደረገውን ነገር ይናገራሉ። |
ይሖዋ ነገሠ! ምድር ደስ ይበላት። ብዙ ደሴቶችም ሐሴት ያድርጉ። |
ደመናና ድቅድቅ ጨለማ በዙሪያው አለ፤ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው። |
እሳት በፊቱ ይሄዳል፤ጠላቶቹንም በሁሉም አቅጣጫ ይፈጃል። |
የመብረቅ ብልጭታዎቹ በመሬት ላይ አበሩ፤ምድር ይህን አይታ ተንቀጠቀጠች። |
ተራሮች በይሖዋ ፊት፣በምድርም ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ። |
ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤ሕዝቦችም ሁሉ ክብሩን ያያሉ። |
ማንኛውንም የተቀረጸ ምስል የሚያመልኩ ሁሉ፣ከንቱ በሆኑ አማልክታቸው የሚኩራሩ ይፈሩ። እናንተ አማልክት ሁሉ፣ ለእሱ ስገዱ። |
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ስላስተላለፍካቸው የፍርድ ውሳኔዎች፣ጽዮን ሰምታ ሐሴት አደረገች፤የይሁዳ ከተሞች ደስ አላቸው። |
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ በመላው ምድር ላይ ልዑል ነህና፤ከሌሎች አማልክት ሁሉ በላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለሃል። |
እናንተ ይሖዋን የምትወዱ፣ ክፉ የሆነውን ነገር ጥሉ። እሱ የታማኝ አገልጋዮቹን ሕይወት ይጠብቃል፤ከክፉዎች እጅ ይታደጋቸዋል። |
ብርሃን ለጻድቃን ወጣ፤ደስታም ለልበ ቅኖች ተዳረሰ። |
እናንተ ጻድቃን፣ በይሖዋ ሐሴት አድርጉ፤ለቅዱስ ስሙም ምስጋና አቅርቡ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ ደግሞም መልስልኝ፤ጎስቋላና ድሃ ነኝና። |
እኔ ታማኝ ስለሆንኩ ሕይወቴን ጠብቃት። በአንተ የሚታመነውን አገልጋይህን አድነው፤አንተ አምላኬ ነህና። |
ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየኝ፤ቀኑን ሙሉ አንተን እጣራለሁና። |
አገልጋይህን ደስ አሰኘው፤ይሖዋ ሆይ፣ የአንተን እርዳታ እሻለሁና። |
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ጥሩ ነህና፤ ይቅር ለማለትም ዝግጁ ነህ፤አንተን ለሚጠሩ ሁሉ የምታሳየው ታማኝ ፍቅር ወሰን የለውም። |
ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን አዳምጥ፤እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውንም ልመና በትኩረት ስማ። |
አንተ መልስ ስለምትሰጠኝ፣በተጨነቅኩ ቀን አንተን እጣራለሁ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ የለም፤ከአንተ ሥራ ጋር የሚወዳደር አንድም ሥራ የለም። |
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ የሠራሃቸው ብሔራት ሁሉ ይመጣሉ፤በፊትህም ይሰግዳሉ፤ለስምህም ክብር ይሰጣሉ። |
አንተ ታላቅ ነህና፤ ድንቅ ነገሮችም ትሠራለህ፤አንተ አምላክ ነህ፤ ከአንተ ሌላ የለም። |
ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረኝ። በእውነትህ እሄዳለሁ። ስምህን እፈራ ዘንድ ልቤን አንድ አድርግልኝ። |
ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ በሙሉ ልቤ አወድስሃለሁ፤ስምህንም ለዘላለም ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤ |
ለእኔ የምታሳየው ታማኝ ፍቅር ታላቅ ነውና፤ሕይወቴንም ጥልቅ ከሆነው መቃብር አድነሃል። |
አምላክ ሆይ፣ እብሪተኛ ሰዎች በእኔ ላይ ተነስተዋል፤የጨካኞች ቡድን ሕይወቴን ይሻታል፤አንተንም ከምንም አልቆጠሩም። |
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን መሐሪና ሩኅሩኅ፣ለቁጣ የዘገየህ እንዲሁም ታማኝ ፍቅርህና ታማኝነትህ የበዛ አምላክ ነህ። |
ወደ እኔ ተመልከት፤ ሞገስም አሳየኝ። ለአገልጋይህ ብርታትህን ስጠው፤የሴት ባሪያህንም ልጅ አድን። |
እኔን የሚጠሉ አይተው እንዲያፍሩ፣የጥሩነትህን ምልክት አሳየኝ። ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ረዳቴና አጽናኜ ነህና። |
ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና አዳምጥ። እንደ ታማኝነትህና እንደ ጽድቅህ መጠን መልስልኝ። |
ሕያው የሆነ ማንኛውም ሰው በፊትህ ጻድቅ ሊሆን ስለማይችል፣አገልጋይህን ለፍርድ አታቅርበው። |
ጠላት ያሳድደኛልና፤ሕይወቴንም አድቆ ከአፈር ደባልቋታል። ከረጅም ጊዜ በፊት እንደሞቱ ሰዎች በጨለማ ቦታ እንድኖር አድርጎኛል። |
መንፈሴ በውስጤ ዛለ፤ልቤ በውስጤ ደነዘዘ። |
የጥንቱን ዘመን አስታውሳለሁ፤ባከናወንካቸው ነገሮች ሁሉ ላይ አሰላስላለሁ፤የእጆችህን ሥራ በታላቅ ጉጉት አውጠነጥናለሁ። |
እጆቼን ወደ አንተ እዘረጋለሁ፤እንደ ደረቅ ምድር አንተን ተጠማሁ። (ሴላ) |
ይሖዋ ሆይ፣ ፈጥነህ መልስልኝ።ጉልበቴ ተሟጠጠ። ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤አለዚያ ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱ ሰዎች እሆናለሁ። |
በአንተ ታምኛለሁና፣በማለዳ ታማኝ ፍቅርህን ልስማ። ፊቴን ወደ አንተ አዞራለሁና፣ልሄድበት የሚገባውን መንገድ አሳውቀኝ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ከጠላቶቼ ታደገኝ። የአንተን ጥበቃ እሻለሁ። |
አንተ አምላኬ ስለሆንክ፣ፈቃድህን እንድፈጽም አስተምረኝ። መንፈስህ ጥሩ ነው፤በደልዳላ መሬት ይምራኝ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ለስምህ ስትል በሕይወት አቆየኝ። በጽድቅህ ከጭንቅ ታደገኝ። |
በታማኝ ፍቅርህ ጠላቶቼን አስወግዳቸው፤አገልጋይህ ነኝና፣የሚያጎሳቁሉኝን ሰዎች ሁሉ አጥፋቸው። |
ይሖዋ ሆይ፣ በሚገባ መርምረኸኛል፤ ደግሞም ታውቀኛለህ። |
አንተ ስቀመጥም ሆነ ስነሳ ታውቃለህ። ሐሳቤን ከሩቅ ታስተውላለህ። |
ስጓዝም ሆነ ስተኛ በሚገባ ታየኛለህ፤መንገዶቼን ሁሉ ታውቃለህ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ገና ቃል ከአፌ ሳይወጣ፣እነሆ፣ አንተ ሁሉን ነገር አስቀድመህ በሚገባ ታውቃለህ። |
ከኋላም ከፊትም ከበብከኝ፤እጅህንም በላዬ ላይ ታደርጋለህ። |
እንዲህ ያለው እውቀት እኔ ልረዳው ከምችለው በላይ ነው። በጣም ከፍ ያለ ከመሆኑ የተነሳ ልደርስበት አልችልም። |
ከመንፈስህ ወዴት ላመልጥ እችላለሁ?ከፊትህስ ወዴት ልሸሽ እችላለሁ? |
ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ አለህ፤በመቃብር አልጋዬን ባነጥፍም እነሆ፣ አንተ በዚያ ትኖራለህ። |
እጅግ ርቆ በሚገኝ ባሕር አቅራቢያ ለመኖር፣በንጋት ክንፍ ብበር፣ |
በዚያም እንኳ እጅህ ትመራኛለች፤ቀኝ እጅህም ትይዘኛለች። |
“በእርግጥ ጨለማ ይሰውረኛል!” ብል፣ በዚያን ጊዜ በዙሪያዬ ያለው ሌሊት ብርሃን ይሆናል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.