text stringlengths 4 267 |
|---|
ጨለማው ለአንተ አይጨልምብህም፤ይልቁንም ሌሊቱ እንደ ቀን ብሩህ ይሆናል፤ጨለማ ለአንተ እንደ ብርሃን ነው። |
አንተ ኩላሊቴን ሠርተሃልና፤በእናቴ ማህፀን ውስጥ ጋርደህ አስቀመጥከኝ። |
በሚያስደምም ሁኔታ ግሩምና ድንቅ ሆኜ ስለተፈጠርኩ አወድስሃለሁ። ሥራዎችህ አስደናቂ ናቸው፤ይህን በሚገባ አውቃለሁ። |
በስውር በተሠራሁ ጊዜ፣በማህፀን ውስጥ እያደግኩ በነበረበት ወቅት፣አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም ነበር። |
ፅንስ እያለሁ እንኳ ዓይኖችህ አዩኝ፤የአካሌ ክፍሎች በሙሉ በመጽሐፍህ ተጻፉ፤አንዳቸውም ወደ ሕልውና ከመምጣታቸው በፊት፣የተሠሩባቸውን ቀኖች በተመለከተ በዝርዝር ተጻፈ። |
ሐሳቦችህ ለእኔ ምንኛ ውድ ናቸው! አምላክ ሆይ፣ ቁጥራቸው ምንኛ ብዙ ነው! |
ልቆጥራቸው ብሞክር ከአሸዋ ይልቅ ይበዛሉ። ከእንቅልፌ ስነቃም ገና ከአንተው ጋር ነኝ። |
አምላክ ሆይ፣ ምነው ክፉውን በገደልከው! በዚያን ጊዜ ጨካኞች ከእኔ ይርቁ ነበር፤ |
እነሱ በተንኮል ተነሳስተው በአንተ ላይ ክፉ ነገር ይናገራሉ፤ስምህን በከንቱ የሚያነሱ ጠላቶችህ ናቸው። |
ይሖዋ ሆይ፣ አንተን የሚጠሉትን እጠላ የለም?በአንተ ላይ የሚያምፁትንስ እጸየፍ የለም? |
እጅግ ጠላኋቸው፤ለእኔ የለየላቸው ጠላቶች ሆነዋል። |
አምላክ ሆይ፣ በሚገባ ፈትሸኝ፤ ልቤንም እወቅ። መርምረኝ፤ የሚያስጨንቁኝንም ሐሳቦች እወቅ። |
በውስጤ ጎጂ የሆነ ዝንባሌ ካለ እይ፤በዘላለምም መንገድ ምራኝ። |
እነሆ፣ ወንድሞች በአንድነት አብረው ቢኖሩምንኛ መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል! |
በራስ ላይ ፈስሶ እስከ ጢም እንደሚዘልቅ፣በአሮን ጢም ላይ እንደሚወርድ፣እስከ ልብሱ ኮሌታ ድረስ እንደሚፈስጥሩ ዘይት ነው። |
በጽዮን ተራሮች ላይ እንደሚወርድ፣እንደ ሄርሞን ጤዛ ነው። በዚያ ይሖዋ በረከቱን ይኸውምየዘላለም ሕይወትን አዟል። |
ይሖዋ ሆይ፣ ልቤ አይኩራራም፤ዓይኖቼም አይታበዩም፤እጅግ ታላላቅ ነገሮችን ወይምከአቅሜ በላይ የሆኑ ነገሮችን አልመኝም። |
ይልቁንም እናቱ ላይ እንደተቀመጠ ጡት የጣለ ሕፃንነፍሴን አረጋጋኋት፤ ደግሞም ጸጥ አሰኘኋት።ጡት እንደጣለ ሕፃን ረካሁ። |
እስራኤል ከአሁን ጀምሮ ለዘላለምይሖዋን በትዕግሥት ይጠባበቅ። |
ይሖዋ ሆይ፣ በድንኳንህ ውስጥ በእንግድነት የሚስተናገድ ማን ነው? በተቀደሰ ተራራህ የሚኖር ማን ነው? |
ያለነቀፋ የሚመላለስ፣ትክክል የሆነውን የሚያደርግ፣በልቡም እውነትን የሚናገር ሰው ነው። |
በአንደበቱ ስም አያጠፋም፤በባልንጀራው ላይ መጥፎ ነገር አይሠራም፤የወዳጆቹንም ስም አያጎድፍም። |
ነውረኛ የሆነን ሰው ሁሉ ይንቃል፤ይሖዋን የሚፈሩትን ግን ያከብራል። ጉዳት ላይ ሊጥለው ቢችልም እንኳ ቃሉን አያጥፍም። |
ገንዘቡን በወለድ አያበድርም፤ንጹሕ የሆነውን ሰው ለመወንጀልም ጉቦ አይቀበልም። እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ሁሉ ፈጽሞ አይናወጥም። |
ሕዝቤ ሆይ፣ ሕጌን አዳምጥ፤ከአፌ ወደሚወጣው ቃል ጆሮህን አዘንብል። |
አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ። በጥንት ዘመን የተነገሩትን እንቆቅልሾች አቀርባለሁ። |
የሰማናቸውንና ያወቅናቸውን ነገሮች፣አባቶቻችን ለእኛ የተረኩልንን፣ |
ከልጆቻቸው አንደብቀውም፤ይሖዋ ያከናወናቸውን የሚያስመሰግኑ ሥራዎችና ብርታቱን፣ደግሞም የሠራቸውን አስደናቂ ነገሮችለመጪው ትውልድ እንተርካለን። |
እሱ ለያዕቆብ ማሳሰቢያ ሰጠ፤በእስራኤልም ሕግ ደነገገ፤እነዚህን ነገሮች ለልጆቻቸው እንዲያሳውቁአባቶቻችንን አዘዛቸው፤ |
ይህም ቀጣዩ ትውልድ፣ገና የሚወለዱት ልጆች እነዚህን ነገሮች እንዲያውቁ ነው። እነሱም በተራቸው ለልጆቻቸው ይተርካሉ። |
በዚህ ጊዜ እነሱ ትምክህታቸውን በአምላክ ላይ ይጥላሉ። የአምላክን ሥራዎች አይረሱም፤ይልቁንም ትእዛዛቱን ይጠብቃሉ። |
ያን ጊዜ እንደ አባቶቻቸውእልኸኛና ዓመፀኛ ትውልድ፣ደግሞም ልቡ የሚወላውልናመንፈሱ ለአምላክ ታማኝ ያልሆነ ትውልድ አይሆኑም። |
ኤፍሬማውያን ቀስት የታጠቁ ነበሩ፤ይሁንና በጦርነት ቀን ወደ ኋላ አፈገፈጉ። |
የአምላክን ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤በሕጉም ለመመላለስ ፈቃደኛ አልሆኑም። |
በተጨማሪም ያደረጋቸውን ነገሮች፣ያሳያቸውን ድንቅ ሥራዎች ረሱ። |
በአባቶቻቸው ፊት በግብፅ አገር፣በጾዓን ምድር አስደናቂ ነገሮች አከናውኖ ነበር። |
በዚያ አቋርጠው እንዲሄዱ ባሕሩን ከፈለው፤ውኃዎቹንም እንደ ግድብ አቆመ። |
ቀን በደመና፣ ሌሊቱን ሙሉ ደግሞበእሳት ብርሃን መራቸው። |
በምድረ በዳ ዓለቶችን ሰነጠቀ፤ከጥልቅ ውኃ የሚጠጡ ያህል እስኪረኩ ድረስ አጠጣቸው። |
ከቋጥኝ ውስጥ ወራጅ ውኃ አወጣ፤ውኃዎችም እንደ ወንዝ እንዲፈስሱ አደረገ። |
እነሱ ግን በበረሃ፣ በልዑሉ አምላክ ላይ በማመፅበእሱ ላይ ኃጢአት መሥራታቸውን ቀጠሉ፤ |
እንዲሁም የተመኙትን ምግብ እንዲሰጣቸው በመጠየቅአምላክን በልባቸው ተገዳደሩት። |
“አምላክ በምድረ በዳ ማዕድ ማዘጋጀት ይችላል?” በማለትበአምላክ ላይ አጉረመረሙ። |
እነሆ፣ ውኃ እንዲፈስና ጅረቶች እንዲንዶለዶሉዓለትን መታ። ይሁንና “ዳቦስ ሊሰጠን ይችላል?ወይስ ለሕዝቡ ሥጋ ሊያቀርብ ይችላል?” አሉ። |
ይሖዋ በሰማቸው ጊዜ እጅግ ተቆጣ፤በያዕቆብ ላይ እሳት ተቀጣጠለ፤በእስራኤልም ላይ ቁጣው ነደደ፤ |
ምክንያቱም በአምላክ ላይ እምነት አልጣሉም፤እነሱን የማዳን ችሎታ እንዳለው አላመኑም። |
ስለዚህ በላይ ያሉትን በደመና የተሸፈኑ ሰማያት አዘዘ፤የሰማይንም በሮች ከፈተ። |
የሚበሉት መና አዘነበላቸው፤የሰማይንም እህል ሰጣቸው። |
ሰዎች የኃያላንን ምግብ በሉ፤እስኪጠግቡ ድረስ እንዲበሉ በቂ ምግብ አቀረበላቸው። |
የምሥራቁን ነፋስ በሰማይ አስነሳ፤በኃይሉም የደቡብ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ። |
ሥጋንም እንደ አፈር፣ወፎችንም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አዘነበላቸው። |
በሰፈሩ መካከል፣በድንኳኖቹም ሁሉ ዙሪያ እንዲወድቁ አደረገ። |
እነሱም በሉ፤ ከልክ በላይም ጠገቡ፤የተመኙትን ነገር ሰጣቸው። |
ሆኖም ምኞታቸውን ሙሉ በሙሉ ከማርካታቸው በፊት፣ምግባቸው ገና በአፋቸው ውስጥ እያለ |
የአምላክ ቁጣ በእነሱ ላይ ነደደ። ኃያላን ሰዎቻቸውን ገደለ፤የእስራኤልን ወጣቶች ጣለ። |
ይህም ሆኖ በኃጢአታቸው ገፉበት፤አስደናቂ በሆኑ ሥራዎቹም አላመኑም። |
ስለዚህ ዘመናቸው እንደ እስትንፋስ እንዲያበቃ፣ዕድሜያቸውም በድንገተኛ ሽብር እንዲያከትም አደረገ። |
ሆኖም በገደላቸው ቁጥር እሱን ይሹ ነበር፤ተመልሰው አምላክን ይፈልጉ ነበር፤ |
ይህን የሚያደርጉት አምላክ ዓለታቸው እንደሆነ፣ልዑሉ አምላክም እንደሚዋጃቸው በማስታወስ ነበር። |
እነሱ ግን በአፋቸው ሊያታልሉት ሞከሩ፤በምላሳቸውም ዋሹት። |
ልባቸው ለእሱ የጸና አልነበረም፤ለቃል ኪዳኑም ታማኞች አልነበሩም። |
እሱ ግን መሐሪ ነው፤በደላቸውን ይቅር ይል ነበር፤ ደግሞም አላጠፋቸውም። ቁጣውን ሁሉ ከመቀስቀስ ይልቅብዙ ጊዜ ስሜቱን ይገታ ነበር። |
ነፍሶ ዳግመኛ የማይመለስ ነፋስ፣ሥጋ መሆናቸውንም አስታውሷልና። |
በምድረ በዳ ስንት ጊዜ በእሱ ላይ ዓመፁ!በበረሃ ሳሉም ብዙ ጊዜ ስሜቱን ጎዱት! |
ደግመው ደጋግመው አምላክን ተፈታተኑት፤የእስራኤልንም ቅዱስ እጅግ አሳዘኑት። |
እነሱን ከጠላት የታደገበትን ቀን፣ኃይሉንም አላስታወሱም፤ |
በግብፅ አስደናቂ ምልክቶችን፣በጾዓን ምድርም ተአምራቱን እንዴት እንዳሳየ አላሰቡም፤ |
እንዲሁም ከጅረቶቻቸው መጠጣት እንዳይችሉየአባይን የመስኖ ቦዮች እንዴት ወደ ደም እንደለወጠ ዘነጉ። |
ይበሏቸው ዘንድ የተናካሽ ዝንቦችን መንጋ ሰደደባቸው፤ያጠፏቸውም ዘንድ እንቁራሪቶችን ላከባቸው። |
ሰብላቸውን ለማይጠግብ አንበጣ፣የድካማቸውን ፍሬ ለአንበጣ መንጋ ሰጠ። |
የወይን ተክላቸውን በበረዶ፣የሾላ ዛፎቻቸውንም በበረዶ ድንጋይ አጠፋ። |
የጋማ ከብቶቻቸውን ለበረዶ፣መንጎቻቸውንም ለመብረቅ ብልጭታ ዳረገ። |
የሚነድ ቁጣውን፣ንዴቱን፣ መዓቱንና መቅሰፍቱንእንዲሁም ጥፋት የሚያመጡ የመላእክት ሠራዊትን ላከባቸው። |
ለቁጣው መንገድ ጠረገ። ከሞት አላተረፋቸውም፤ለቸነፈርም አሳልፎ ሰጣቸው። |
በመጨረሻም የግብፅን በኩሮች በሙሉ፣በካም ድንኳኖች ውስጥ ከሚገኙትም መካከል የፍሬያቸው መጀመሪያ የሆኑትን መታ። |
ከዚያም ሕዝቡን እንደ በጎች እንዲወጡ አደረገ፤በምድረ በዳም እንደ መንጋ መራቸው። |
በአስተማማኝ ሁኔታ መራቸው፤አንዳች ፍርሃትም አልተሰማቸውም፤ባሕሩም ጠላቶቻቸውን ዋጠ። |
ደግሞም ቅዱስ ወደሆነው ምድሩ፣ቀኝ እጁ የራሱ ወዳደረገው ወደዚህ ተራራማ ክልል አመጣቸው። |
ብሔራቱን ከፊታቸው አባረረ፤በመለኪያ ገመድም ርስት አከፋፈላቸው፤የእስራኤልን ነገዶች በቤቶቻቸው እንዲኖሩ አደረገ። |
እነሱ ግን ልዑሉን አምላክ ተገዳደሩት፤ በእሱም ላይ ዓመፁ፤ማሳሰቢያዎቹን ችላ አሉ። |
በተጨማሪም ጀርባቸውን ሰጡ፤ እንደ አባቶቻቸውም ከሃዲዎች ሆኑ። ጅማቱ እንደረገበ ደጋን እምነት የማይጣልባቸው ነበሩ። |
ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎቻቸው ብዙ ጊዜ አሳዘኑት፤በተቀረጹ ምስሎቻቸውም ለቁጣ አነሳሱት። |
አምላክ ሰምቶ በጣም ተቆጣ፤በመሆኑም እስራኤልን እርግፍ አድርጎ ተወው። |
በመጨረሻም በሴሎ የሚገኘውን የማደሪያ ድንኳን፣በሰው ልጆች መካከል ይኖርበት የነበረውን ድንኳን ተወው። |
የብርታቱ ምልክት ተማርኮ እንዲወሰድ ፈቀደ፤ግርማ ሞገሱን በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ። |
ሕዝቡን ለሰይፍ አሳልፎ ሰጠ፤በርስቱም ላይ እጅግ ተቆጣ። |
ወጣቶቹን እሳት በላቸው፤ለደናግሎቹም የሠርግ ዘፈን አልተዘፈነላቸውም። |
ካህናቱ በሰይፍ ወደቁ፤የገዛ መበለቶቻቸውም አላለቀሱላቸውም። |
ከዚያም ይሖዋ፣ የወይን ጠጅ ስካሩ እንደለቀቀው ኃያል ሰውከእንቅልፍ እንደነቃ ሆኖ ተነሳ። |
ጠላቶቹንም አሳዶ ወደ ኋላ መለሳቸው፤ለዘለቄታው ውርደት አከናነባቸው። |
የዮሴፍን ድንኳን ናቀ፤የኤፍሬምን ነገድ አልመረጠም። |
ከዚህ ይልቅ የይሁዳን ነገድ፣የሚወደውን የጽዮንን ተራራ መረጠ። |
መቅደሱን እንደ ሰማያት ጽኑ አድርጎ ሠራው፤ለዘላለምም እንደመሠረታት ምድር አድርጎ ገነባው። |
አገልጋዩን ዳዊትን መረጠ፤ከበጎች ጉረኖ ወስዶ፣ |
የሚያጠቡ በጎችን ከመጠበቅም አንስቶበሕዝቡ በያዕቆብ፣ በርስቱም በእስራኤል ላይእረኛ እንዲሆን ሾመው። |
እሱም በንጹሕ ልብ ጠበቃቸው፤በተካኑ እጆቹም መራቸው። |
አምላክ ይነሳ፤ ጠላቶቹ ይበታተኑ፤የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ። |
ጭስ በኖ እንደሚጠፋ ሁሉ እነሱንም አጥፋቸው፤ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፣ክፉዎችም ከአምላክ ፊት ይጥፉ። |
ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው፤በአምላክ ፊት ሐሴት ያድርጉ፤በደስታም ይፈንጥዙ። |
ለአምላክ ዘምሩ፤ ለስሙም የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ። በበረሃማ ሜዳዎች እየጋለበ ለሚያቋርጠው ለእሱ ዘምሩ። ስሙ ያህ ነው! በፊቱ እጅግ ደስ ይበላችሁ! |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.