text
stringlengths
4
267
እኔ “በምላሴ ኃጢአት እንዳልፈጽምአካሄዴን እጠብቃለሁ። ክፉ ሰው ከእኔ ጋር እስካለ ድረስአፌን ለመጠበቅ ልጓም አስገባለሁ” አልኩ።
ዱዳ ሆንኩ፤ ደግሞም ዝም አልኩ፤መልካም ነገር ከመናገር እንኳ ታቀብኩ፤ይሁንና ሥቃዬ ከባድ ነበር።
ልቤ በውስጤ ነደደ። ሳወጣ ሳወርድ እንደ እሳት ነደድኩ። በዚህ ጊዜ በአንደበቴ እንዲህ አልኩ፦
“ይሖዋ ሆይ፣ መጨረሻዬ ምን እንደሚሆን፣የዕድሜዬም ርዝማኔ ምን ያህል እንደሆነ እንዳውቅ እርዳኝ፤ይህም ሕይወቴ ምን ያህል አጭር እንደሆነ አውቅ ዘንድ ነው።
በእርግጥም ቀኖቼን ጥቂት አደረግካቸው፤የሕይወት ዘመኔም በፊትህ ከምንም አይቆጠርም። አዎ፣ ሰው ሁሉ ምንም ነገር የማይነካው ቢመስልም እንኳ እንደ እስትንፋስ ነው። (ሴላ)
በእርግጥም ሰው ሁሉ የሚመላለሰው እንደ ጥላ ነው። ላይ ታች የሚለው በከንቱ ነው። ማን እንደሚጠቀምበት ሳያውቅ ንብረት ያከማቻል።
ይሖዋ ሆይ፣ ታዲያ ተስፋዬ ምንድን ነው? ተስፋዬ አንተ ብቻ ነህ።
ከፈጸምኩት በደል ሁሉ አድነኝ። ሞኝ ሰው እንዲሳለቅብኝ አትፍቀድ።
ዱዳ ሆንኩ፤ይህን ያደረግከው አንተ ስለሆንክአፌን መክፈት አልቻልኩም።
በእኔ ላይ ያመጣኸውን መቅሰፍት ከእኔ አርቅ። እጅህ ስለመታኝ ዛልኩ።
ሰውን በሠራው ስህተት የተነሳ በመቅጣት ታርመዋለህ፤እንደ ውድ ሀብት የሚመለከታቸውን ነገሮች እንደ ብል ትበላበታለህ። በእርግጥም ሰው ሁሉ እንደ እስትንፋስ ነው። (ሴላ)
ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤ለእርዳታ የማሰማውን ጩኸት አዳምጥ። እንባዬን ችላ አትበል። እኔ በአንተ ዘንድ የባዕድ አገር ሰው ነኝና፤እንደ አባቶቼ አልፌ የምሄድ ተጓዥ ነኝ።
ከመሞቴና ከሕልውና ውጭ ከመሆኔ በፊት፣ፊቴ እንዲፈካ በክፉ ዓይን አትየኝ።”
በጭንቀት ቀን ይሖዋ ይስማህ። የያዕቆብ አምላክ ስም ይጠብቅህ።
ከቅዱሱ ስፍራ እርዳታ ይላክልህ፤ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ።
በስጦታ የምታቀርበውን መባ ሁሉ ያስብልህ፤የሚቃጠል መባህን በሞገስ ዓይን ይቀበልህ። (ሴላ)
የልብህን ፍላጎት ያሟላልህ፤ዕቅድህንም ሁሉ ያሳካልህ።
በማዳን ሥራህ በደስታ እልል እንላለን፤በአምላካችን ስም ዓርማችንን ወደ ላይ ከፍ እናደርጋለን። ይሖዋ የለመንከውን ሁሉ ይፈጽምልህ።
ይሖዋ የቀባውን እንደሚያድን አሁን አወቅኩ። በቀኝ እጁ በሚያከናውነው ታላቅ የማዳን ሥራ፣ቅዱስ ከሆኑት ሰማያቱ ይመልስለታል።
አንዳንዶች በሠረገሎች፣ ሌሎች ደግሞ በፈረሶች ይታመናሉ፤እኛ ግን የአምላካችንን የይሖዋን ስም እንጠራለን።
እነሱ ተዝለፍልፈው ወድቀዋል፤እኛ ግን ተነስተን ቀጥ ብለን ቆመናል።
ይሖዋ ሆይ፣ ንጉሡን አድን! እርዳታ ለማግኘት በተጣራን ቀን ይመልስልናል።
ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ። መላዋ ምድር ለይሖዋ ትዘምር!
ለይሖዋ ዘምሩ፤ ስሙንም አወድሱ። የማዳኑን ምሥራች በየቀኑ አውጁ።
ክብሩን በብሔራት፣አስደናቂ ሥራዎቹንም በሕዝቦች ሁሉ መካከል አስታውቁ።
ይሖዋ ታላቅ ነው፤ ደግሞም እጅግ ሊወደስ ይገባዋል። ከሌሎች አማልክት ሁሉ በላይ እጅግ የሚፈራ ነው።
የሌሎች ሕዝቦች አማልክት ሁሉ ከንቱ ናቸው፤ይሖዋ ግን ሰማያትን የሠራ አምላክ ነው።
ሞገስና ግርማ በፊቱ ናቸው፤ብርታትና ውበት በመቅደሱ ውስጥ አሉ።
እናንተ የሕዝብ ነገዶች፣ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ፤ከክብሩና ከብርታቱ የተነሳ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ።
ለስሙ የሚገባውን ክብር ለይሖዋ ስጡ፤ስጦታ ይዛችሁ ወደ ቅጥር ግቢዎቹ ግቡ።
ያጌጠ የቅድስና ልብስ ለብሳችሁ ለይሖዋ ስገዱ፤ምድር ሁሉ በፊቱ ተንቀጥቀጪ!
በብሔራት መካከል እንዲህ ብላችሁ አስታውቁ፦ “ይሖዋ ነገሠ! ምድር በጽኑ ተመሥርታለች፤ ከቦታዋ ልትንቀሳቀስ አትችልም። እሱ ለሕዝቦች በትክክል ይፈርዳል።”
ሰማያት ሐሴት ያድርጉ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤ባሕሩና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰማ፤
መስኩና በላዩ ላይ ያለው ሁሉ ሐሴት ያድርግ። የዱር ዛፎችም ሁሉ በይሖዋ ፊት እልል ይበሉ።
እሱ እየመጣ ነውና፤በምድር ላይ ለመፍረድ እየመጣ ነው። በዓለም ላይ በጽድቅ፣በሕዝቦችም ላይ በታማኝነት ይፈርዳል።
ይሖዋ ሆይ፣ አንድም ታማኝ ሰው ስለሌለ አድነኝ፤ከሰው ልጆች መካከል ታማኞች ጠፍተዋል።
እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤በከንፈራቸው ይሸነግላሉ፤ አታላይ በሆነ ልብም ይናገራሉ።
ይሖዋ የሚሸነግልን ከንፈር ሁሉ፣ጉራ የሚነዛውንም ምላስ ይቆርጣል፤
እነሱ “በምላሳችን እንረታለን። አንደበታችንን እንዳሻን እንጠቀምበታለን፤በእኛ ላይ ጌታ ሊሆን የሚችል ማን ነው?” ይላሉ።
“የተጎሳቆሉት ሰዎች በመጨቆናቸው፣ድሆችም በመቃተታቸው፣እርምጃ ለመውሰድ እነሳለሁ” ይላል ይሖዋ። “በንቀት ዓይን ከሚመለከቷቸው ሁሉ እታደጋቸዋለሁ።”
የይሖዋ ቃል የጠራ ነው፤ከሸክላ በተሠራ ምድጃ እንደተጣራ ብር ሰባት ጊዜ የነጠረ ነው።
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ትጋርዳቸዋለህ፤እያንዳንዳቸውን ከዚህ ትውልድ ለዘላለም ትጠብቃቸዋለህ።
የሰው ልጆች ብልሹ ምግባርን ስለሚያስፋፉ፣ክፉዎች እንዳሻቸው ይፈነጫሉ።
ሞኝ ሰው በልቡ “ይሖዋ የለም” ይላል። የዓመፅ ድርጊታቸው ብልሹና አስጸያፊ ነው፤መልካም የሚሠራ ማንም የለም።
ሆኖም ጥልቅ ማስተዋል ያለውና ይሖዋን የሚፈልግ ሰው ይኖር እንደሆነ ለማየትአምላክ ከሰማይ ሆኖ ወደ ሰው ልጆች ይመለከታል።
ሁሉም ወደ ሌላ ዞር ብለዋል፤ሁሉም ብልሹ ናቸው። መልካም የሚሠራ ማንም የለም፤አንድ እንኳ የለም።
ከክፉ አድራጊዎቹ መካከል አንዳቸውም አያስተውሉም? ምግብ እንደሚበሉ ሕዝቤን ይውጣሉ። ይሖዋን አይጠሩም።
ይሁንና በታላቅ ሽብር፣ከዚህ በፊት ተሰምቷቸው በማያውቅ ታላቅ ፍርሃት ይዋጣሉ፤በአንተ ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩትን ሰዎች አጥንት አምላክ ይበታትነዋልና። ይሖዋ ስላልተቀበላቸው አንተ ታዋርዳቸዋለህ።
የእስራኤል መዳን ምነው ከጽዮን በመጣ! ይሖዋ የተማረከውን ሕዝቡን በሚመልስበት ጊዜ፣ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤል ሐሴት ያድርግ።
ይሖዋ ታላቅ ነው፤በአምላካችን ከተማ፣ በቅዱስ ተራራው እጅግ ሊወደስ ይገባዋል።
በከፍታ ቦታ ላይ ተውባ የምትታየው፣ የምድር ሁሉ ደስታ፣በስተ ሰሜን ርቃ የምትገኘው የጽዮን ተራራ ነች፤ደግሞም የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነች።
አምላክ በማይደፈሩ ማማዎቿ ውስጥአስተማማኝ መጠጊያ መሆኑን አስመሥክሯል።
እነሆ፣ ነገሥታት ተሰብስበዋልና፤አንድ ላይ ሆነው ገሰገሱ።
ከተማዋን ባዩአት ጊዜ ተገረሙ። ደንግጠውም ፈረጠጡ።
በዚያም በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤እንደምትወልድ ሴት ጭንቅ ያዛቸው።
የተርሴስን መርከቦች በምሥራቅ ነፋስ ሰባበርክ።
የሰማነውን ነገር፣ በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ከተማይኸውም በአምላካችን ከተማ አሁን በገዛ ዓይናችን አይተናል። አምላክ ለዘላለም ያጸናታል። (ሴላ)
አምላክ ሆይ፣ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነንስለ ታማኝ ፍቅርህ እናሰላስላለን።
አምላክ ሆይ፣ እንደ ስምህ ሁሉ ውዳሴህምእስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳል። ቀኝ እጅህ በጽድቅ ተሞልቷል።
ከፍርድህ የተነሳ የጽዮን ተራራ ደስ ይበላት፤የይሁዳ ከተሞችም ሐሴት ያድርጉ።
በጽዮን ዙሪያ ሂዱ፤ በዙሪያዋም ተጓዙ፤ማማዎቿን ቁጠሩ።
የመከላከያ ግንቦቿን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ። ለመጪዎቹ ትውልዶች መናገር ትችሉ ዘንድ፣የማይደፈሩ ማማዎቿን በሚገባ አጢኑ።
ይህ አምላክ፣ ለዘላለም አምላካችን ነውና። እስከ ወዲያኛው ይመራናል።
ብርታቴ ይሖዋ ሆይ፣ እወድሃለሁ።
ይሖዋ ቋጥኜ፣ ምሽጌና ታዳጊዬ ነው። አምላኬ የምሸሸግበት ዓለቴ ነው፤ጋሻዬ፣ የመዳኔ ቀንድና አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው።
ውዳሴ የሚገባውን ይሖዋን እጠራለሁ፤ከጠላቶቼም እድናለሁ።
የሞት ገመዶች ተተበተቡብኝ፤የማይረቡ ሰዎች የለቀቁት ድንገተኛ ጎርፍ አሸበረኝ።
የመቃብር ገመድ ተጠመጠመብኝ፤የሞት ወጥመድ ተጋረጠብኝ።
በጭንቅ ውስጥ ሳለሁ ይሖዋን ጠራሁት፤እርዳታ ለማግኘት አምላኬን አጥብቄ ተማጸንኩት። በመቅደሱ ሆኖ ድምፄን ሰማ፤እርዳታ ለማግኘት የማሰማውም ጩኸት ወደ ጆሮው ደረሰ።
ምድርም ትንቀጠቀጥና ትናወጥ ጀመር፤የተራሮች መሠረቶች ተንቀጠቀጡ፤እሱ ስለተቆጣም ራዱ።
ከአፍንጫው ጭስ ወጣ፤የሚባላም እሳት ከአፉ ወጣ፤ፍምም ከእሱ ፈለቀ።
ወደ ታች ሲወርድ ሰማያት እንዲያጎነብሱ አደረገ፤ከእግሮቹም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበር።
በኪሩብ ላይ ተቀምጦ እየበረረ መጣ። በመንፈስ ክንፎች በፍጥነት ወረደ።
ከዚያም በጨለማ ራሱን ሸፈነ፤ጥቁር ውኃና ጥቅጥቅ ያለ ደመናእንደ መጠለያ በዙሪያው ነበር።
በፊቱ ካለው ብርሃን፣ከደመናቱ መካከል በረዶና ፍም ወጣ።
ከዚያም ይሖዋ በሰማያት ያንጎደጉድ ጀመር፤ልዑሉ አምላክ ድምፁን አሰማ፤ደግሞም በረዶና ፍም ነበር።
ፍላጻዎቹን አስፈንጥሮ በታተናቸው፤መብረቁን አዥጎድጉዶ ግራ አጋባቸው።
ይሖዋ ሆይ፣ ከተግሣጽህ፣ ከአፍንጫህም ከሚወጣው ኃይለኛ እስትንፋስ የተነሳየጅረቶች ወለል ታየ፤የምድር መሠረቶችም ተገለጡ።
ከላይ ሆኖ እጁን ሰደደ፤ከጥልቅ ውኃ ውስጥም አወጣኝ።
ከብርቱ ጠላቴ አዳነኝ፤ከእኔ ይበልጥ ብርቱዎች ከሆኑት፣ ከሚጠሉኝ ሰዎች ታደገኝ።
ችግር ላይ በወደቅኩበት ቀን ተነሱብኝ፤ይሖዋ ግን ድጋፍ ሆነልኝ።
ከዚያም ደህንነት ወደማገኝበት ስፍራ አመጣኝ፤በእኔ ስለተደሰተ ታደገኝ።
ይሖዋ እንደ ጽድቄ ወሮታ ይከፍለኛል፤እንደ እጄ ንጽሕና ብድራት ይመልስልኛል።
የይሖዋን መንገድ ጠብቄአለሁና፤አምላኬን በመተው ክፉ ድርጊት አልፈጸምኩም።
ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነው፤ደንቦቹን ቸል አልልም።
በፊቱ እንከን የለሽ ሆኜ እኖራለሁ፤ራሴንም ከስህተት እጠብቃለሁ።
ይሖዋ እንደ ጽድቄ፣በፊቱ ንጹሕ እንደሆኑት እጆቼ ብድራት ይመልስልኝ።
ታማኝ ለሆነ ሰው ታማኝ ትሆናለህ፤እንከን የለሽ ለሆነ ሰው እንከን የለሽ ትሆናለህ፤
ከንጹሕ ሰው ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ጠማማ ለሆነ ሰው ግን ብልህ መሆንህን ታሳያለህ።
ችግረኞችን ታድናለህና፤ትዕቢተኛውን ግን ታዋርዳለህ።
ይሖዋ ሆይ፣ መብራቴን የምታበራው አንተ ነህና፤አምላኬ ሆይ፣ ጨለማዬን ብርሃን የምታደርገው አንተ ነህ።
በአንተ እርዳታ ወራሪውን ቡድን መጋፈጥ እችላለሁ፤በአምላክ ኃይል ቅጥር መውጣት እችላለሁ።
የእውነተኛው አምላክ መንገድ ፍጹም ነው፤የይሖዋ ቃል የነጠረ ነው። እሱ መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻቸው ነው።
ደግሞስ ከይሖዋ ሌላ አምላክ ማን ነው? ከአምላካችንስ ሌላ ዓለት ማን ነው?
ብርታትን የሚያስታጥቀኝ እውነተኛው አምላክ ነው፤መንገዴንም ፍጹም ያደርግልኛል።
እግሮቼን እንደ ዋልያ እግሮች ያደርጋል፤በከፍታ ቦታዎች ላይ ያቆመኛል።
እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፤ክንዶቼ የመዳብ ደጋን ማጠፍ ይችላሉ።
የመዳን ጋሻህን ትሰጠኛለህ፤ቀኝ እጅህ ይደግፈኛል፤ትሕትናህም ታላቅ ያደርገኛል።
ለእርምጃዬ መንገዱን ታሰፋልኛለህ፤እግሮቼ አያዳልጣቸውም።
ጠላቶቼን አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ፤ተጠራርገው እስኪጠፉ ድረስ ወደ ኋላ አልመለስም።