text stringlengths 4 267 |
|---|
ልቡ ጥበበኛ የሆነ ሰው አስተዋይ ይባላል፤በደግነት የሚናገርም የማሳመን ችሎታ አለው። |
ጥልቅ ማስተዋል ለባለቤቱ የሕይወት ምንጭ ነው፤ሞኞች ግን በገዛ ሞኝነታቸው ይቀጣሉ። |
የጥበበኛ ሰው ልብ፣ አንደበቱ ጥልቅ ማስተዋል እንዲኖረው ያደርጋል፤ለንግግሩም የማሳመን ችሎታ ይጨምርለታል። |
ደስ የሚያሰኝ ቃል እንደ ማር እንጀራ ነው፤ለነፍስ ጣፋጭ፣ ለአጥንትም ፈውስ ነው። |
ለሰው ትክክለኛ መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ይመራል። |
ሠራተኛን የምግብ ፍላጎቱ ተግቶ እንዲሠራ ያደርገዋል፤ረሃቡ እንዲህ እንዲያደርግ ያስገድደዋልና። |
የማይረባ ሰው ክፋትን ይምሳል፤ንግግሩ እንደሚለበልብ እሳት ነው። |
ነገረኛ ሰው ጭቅጭቅ ያስነሳል፤ስም አጥፊም የልብ ጓደኛሞችን ይለያያል። |
ዓመፀኛ ሰው ባልንጀራውን ክፉ ነገር እንዲሠራ ያግባባዋል፤ወደተሳሳተ መንገድም ይመራዋል። |
በዓይኑ እየጠቀሰ ተንኮል ይሸርባል። ከንፈሮቹን ነክሶ ሸር ይሠራል። |
ሽበት በጽድቅ መንገድ ሲገኝየውበት ዘውድ ነው። |
ቶሎ የማይቆጣ ሰው ከኃያል ሰው፣ስሜቱን የሚቆጣጠርም ከተማን ድል ከሚያደርግ ሰው ይሻላል። |
ዕጣ ጭን ላይ ይጣላል፤ውሳኔውን በሙሉ የሚያስተላልፈው ግን ይሖዋ ነው። |
ልጄ ሆይ፣ ጥበቤን ልብ በል። ማስተዋልን በተመለከተ የምሰጠውን ትምህርት በጥሞና አዳምጥ፤ |
ይህም የማመዛዘን ችሎታህን እንድትጠብቅ፣በከንፈሮችህም እውቀትን በጥንቃቄ እንድትይዝ ነው። |
የጋጠወጥ ሴት ከንፈር እንደ ማር እንጀራ ያንጠባጥባልና፤አፏም ከዘይት ይለሰልሳል። |
በመጨረሻ ግን እንደ ጭቁኝ ትመርራለች፤ደግሞም በሁለት በኩል እንደተሳለ ሰይፍ ትሆናለች። |
እግሮቿ ወደ ሞት ይወርዳሉ። እርምጃዎቿ በቀጥታ ወደ መቃብር ይመራሉ። |
ስለ ሕይወት መንገድ ግድ የላትም። በጎዳናዎቿ ላይ ትባዝናለች፤ ወዴት እንደሚወስዱም አታውቅም። |
እንግዲህ ልጆቼ ሆይ፣ አዳምጡኝ፤ከምናገረውም ቃል አትራቁ። |
ከእሷ ራቅ፤ወደ ቤቷም ደጃፍ አትቅረብ፤ |
ይህም ክብርህን ለሌሎች አሳልፈህ እንዳትሰጥ ነው፤ቀሪ የሕይወት ዘመንህም በመከራ የተሞላ እንዳይሆን ነው፤ |
ደግሞም እንግዳ የሆኑ ሰዎች ጥሪትህን እንዳያሟጥጡ፣የለፋህበትንም ነገር የባዕድ አገር ሰው እንዳይወርሰው ነው። |
አለዚያ በሕይወትህ ማብቂያሥጋህና መላ ሰውነትህ እየመነመነ ሲሄድ ትቃትታለህ፤ |
ደግሞም እንዲህ ትላለህ፦ “ምነው ተግሣጽን ጠላሁ! ልቤስ ምነው ወቀሳን ናቀ! |
የአስተማሪዎቼን ቃል አላዳመጥኩም፤መምህሮቼንም በጥሞና አልሰማሁም። |
በመላው ጉባኤ መካከልሙሉ በሙሉ ልጠፋ ምንም አልቀረኝም ነበር።” |
ከራስህ ጉድጓድ እንዲሁምከገዛ ምንጭህ የሚፈልቀውን ውኃ ጠጣ። |
ምንጮችህ ወደ ውጭ፣ጅረቶችህም በአደባባይ ሊፈሱ ይገባል? |
ለአንተ ብቻ ይሁኑ፤ከአንተ ጋር ላሉ እንግዶችም አይሁኑ። |
ምንጭህ የተባረከ ይሁን፤ከወጣትነት ሚስትህም ጋር ደስ ይበልህ፤ |
እሷ እንደምትወደድ ሚዳቋና እንደምታምር የተራራ ፍየል ናት። ጡቶቿ ምንጊዜም ያርኩህ። ፍቅሯ ምንጊዜም ይማርክህ። |
ልጄ ሆይ፣ ጋጠወጥ ሴት ለምን ትማርክሃለች?ባለጌ ሴትንስ ለምን ታቅፋለህ? |
የሰው መንገድ በይሖዋ ዓይኖች ፊት ነውና፤እሱ መንገዱን ሁሉ ይመረምራል። |
ክፉ ሰው የገዛ ጥፋቱ ወጥመድ ይሆንበታል፤ኃጢአቱም እንደ ገመድ ተብትቦ ይይዘዋል። |
ተግሣጽ ከማጣቱ የተነሳ ይሞታል፤በጣም ሞኝ ከመሆኑም የተነሳ መንገድ ይስታል። |
ጥበበኛ ሴት ቤቷን ትገነባለች፤ሞኝ ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች። |
አካሄዱ ቅን የሆነ ሰው ይሖዋን ይፈራል፤መንገዱ መሠሪ የሆነ ግን ይንቀዋል። |
በሞኝ ሰው አፍ የትዕቢት በትር አለ፤የጥበበኞች ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች። |
ከብት በሌለበት ግርግሙ ንጹሕ ይሆናል፤የበሬ ጉልበት ግን ብዙ ምርት ያስገኛል። |
ሐቀኛ ምሥክር አይዋሽም፤ሐሰተኛ ምሥክር ግን ባወራ ቁጥር ይዋሻል። |
ፌዘኛ ጥበብን ይፈልጋል፤ ሆኖም አያገኛትም፤አስተዋይ ሰው ግን እውቀትን በቀላሉ ያገኛል። |
ከሞኝ ሰው ራቅ፤ከከንፈሮቹ ምንም ዓይነት እውቀት አታገኝምና። |
ብልህ ሰው የሚሄድበትን መንገድ በጥበብ ያስተውላል፤ሞኞች ግን በቂልነታቸው ይታለላሉ። |
ሞኞች በደል ፈጽመው ያፌዛሉ፤ቅኖች ግን እርቅ ለመፍጠር ፈቃደኞች ናቸው። |
ልብ የራሱን ምሬት ያውቃል፤ደስታውንም ሌላ ሰው ሊጋራው አይችልም። |
የክፉዎች ቤት ይወድማል፤የቅኖች ድንኳን ግን ይበለጽጋል። |
ለሰው ትክክለኛ መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ይመራል። |
አንድ ሰው እየሳቀ እንኳ ልቡ ሊያዝን ይችላል፤ደስታም በሐዘን ሊቋጭ ይችላል። |
በልቡ ጋጠወጥ የሆነ ሰው አካሄዱ የሚያስከትለውን መዘዝ ይቀበላል፤ጥሩ ሰው ግን የሥራውን ውጤት ያገኛል። |
ተላላ ቃልን ሁሉ ያምናል፤ብልህ ግን አካሄዱን አንድ በአንድ ያጤናል። |
ጥበበኛ ሰው ጠንቃቃ ነው፤ ከክፉም ይርቃል፤ሞኝ ግን ደንታ ቢስ ነው፤ ደግሞም ከልክ በላይ በራሱ ይመካል። |
ለቁጣ የሚቸኩል ሰው የሞኝነት ተግባር ይፈጽማል፤በጥሞና የሚያስብ ሰው አይወደድም። |
ተላሎች ሞኝነትን ይወርሳሉ፤ብልሆች ግን እውቀትን እንደ አክሊል ይጎናጸፋሉ። |
መጥፎ ሰዎች በጥሩ ሰዎች ፊት፣ክፉዎችም በጻድቅ ደጃፍ ይሰግዳሉ። |
ድሃ በባልንጀሮቹ ዘንድ እንኳ የተጠላ ነው፤የባለጸጋ ወዳጆች ግን ብዙ ናቸው። |
ባልንጀራውን የሚንቅ ኃጢአት ይሆንበታል፤ለችግረኞች የሚራራ ግን ደስተኛ ነው። |
ተንኮል የሚሸርቡ ሰዎች መንገድ ይስቱ የለም? መልካም ነገር ለመሥራት የሚያስቡ ሰዎች ግን ታማኝ ፍቅርንና ታማኝነትን ያተርፋሉ። |
በትጋት ያከናወኑት ነገር ሁሉ ጥቅም ያስገኛል፤እንዲሁ ማውራት ግን ችግር ላይ ይጥላል። |
የጥበበኞች ዘውድ ሀብታቸው ነው፤የሞኞች ቂልነት ግን ለከፋ ሞኝነት ይዳርጋል። |
እውነተኛ ምሥክር ሕይወትን ይታደጋል፤አታላይ ግን ባወራ ቁጥር ይዋሻል። |
ይሖዋን የሚፈራ ሁሉ በማንኛውም ነገር በእሱ ይታመናል፤ልጆቹም መጠጊያ ያገኛሉ። |
ይሖዋን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፤ሰውን ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጥ ይረዳዋል። |
የሕዝብ ብዛት የንጉሥ ግርማ ነው፤ተገዢዎች የሌሉት ገዢ ግን ይጠፋል። |
ቶሎ የማይቆጣ ሰው ትልቅ ማስተዋል አለው፤ትዕግሥት የሌለው ሰው ግን ሞኝነቱን ይገልጣል። |
የሰከነ ልብ ለሰውነት ሕይወት ይሰጣል፤ቅናት ግን አጥንትን ያነቅዛል። |
ችግረኛን የሚያጭበረብር ፈጣሪውን ይሰድባል፤ለድሃ የሚራራ ሁሉ ግን አምላክን ያከብራል። |
ክፉ ሰው በገዛ ክፋቱ ይወድቃል፤ጻድቅ ግን ንጹሕ አቋሙ መጠጊያ ያስገኝለታል። |
ጥበብ በአስተዋይ ልብ ውስጥ በጸጥታ ታርፋለች፤በሞኞች መካከል ግን ራሷን ትገልጣለች። |
ጽድቅ አንድን ብሔር ከፍ ከፍ ታደርጋለች፤ኃጢአት ግን ሕዝብን ታዋርዳለች። |
ንጉሥ አስተውሎ በሚሠራ አገልጋይ ደስ ይሰኛል፤አሳፋሪ ድርጊት በሚፈጽም አገልጋይ ላይ ግን ይቆጣል። |
ክፉዎች ማንም ሳያሳድዳቸው ይሸሻሉ፤ጻድቃን ግን እንደ አንበሳ ልበ ሙሉ ናቸው። |
በአንድ አገር ውስጥ ሕግ ተላላፊነት ሲነግሥ ብዙ ገዢዎች ይፈራረቁበታል፤ይሁንና ጥልቅ ግንዛቤና እውቀት ያለው ሰው በሚያበረክተው እርዳታ ገዢ ለረጅም ዘመን ይቆያል። |
ችግረኞችን የሚበዘብዝ ድሃ፣እህሉን ሁሉ ጠራርጎ እንደሚወስድ ዝናብ ነው። |
ሕግን የሚተዉ ሰዎች ክፉዎችን ያወድሳሉ፤ሕግን የሚጠብቁ ሰዎች ግን በእነሱ ላይ ይቆጣሉ። |
ክፉዎች ፍትሕን መረዳት አይችሉም፤ይሖዋን የሚፈልጉ ግን ሁሉን ነገር መረዳት ይችላሉ። |
መንገዱ ብልሹ ከሆነ ሀብታም ይልቅንጹሕ አቋም ይዞ የሚመላለስ ድሃ ይሻላል። |
አስተዋይ ልጅ ሕግን ይጠብቃል፤ከሆዳሞች ጋር የሚወዳጅ ግን አባቱን ያዋርዳል። |
ወለድና አራጣ በማስከፈል ሀብት የሚያካብት፣ለድሆች ሞገስ ለሚያሳይ ሰው ያከማችለታል። |
ሕግን ለመስማት አሻፈረኝ የሚል ሰው፣ጸሎቱ እንኳ አስጸያፊ ነው። |
ቅኖችን አሳስቶ ወደ መጥፎ መንገድ የሚመራ፣ እሱ ራሱ በቆፈረው ጉድጓድ ይገባል፤ነቀፋ የሌለባቸው ሰዎች ግን መልካም ነገርን ይወርሳሉ። |
ሀብታም ሰው በገዛ ዓይኖቹ ፊት ጥበበኛ ነው፤ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ድሃ ግን ማንነቱን ይደርስበታል። |
ጻድቃን ድል ሲያደርጉ ታላቅ ክብር ይሆናል፤ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ግን ሰዎች ይሸሸጋሉ። |
የሠራውን በደል የሚሸፋፍን አይሳካለትም፤የሚናዘዝና የሚተወው ሁሉ ግን ምሕረት ያገኛል። |
ምንጊዜም ተጠንቅቆ የሚኖር ሰው ደስተኛ ነው፤ልቡን የሚያደነድን ሁሉ ግን ለጥፋት ይዳረጋል። |
ምስኪን በሆነ ሕዝብ ላይ የተሾመ ክፉ ገዢ፣እንደሚያገሳ አንበሳና ተንደርድሮ እንደሚመጣ ድብ ነው። |
ጥልቅ ግንዛቤ የሌለው መሪ ሥልጣኑን አላግባብ ይጠቀማል፤በማጭበርበር የሚገኝን ትርፍ የሚጠላ ግን ዕድሜውን ያራዝማል። |
የሰው ሕይወት በማጥፋቱ የደም ባለ ዕዳ የሆነ ሰው መቃብር እስኪገባ ድረስ ሲሸሽ ይኖራል። እንዲህ ያለውን ሰው ማንም አይርዳው። |
እንከን የለሽ በሆነ መንገድ የሚመላለስ ሰው ይድናል፤መንገዱ ጠማማ የሆነ ግን ድንገት ይወድቃል። |
መሬቱን የሚያርስ ሰው የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፤ከንቱ የሆኑ ነገሮችን የሚያሳድድ ግን እጅግ ይደኸያል። |
ታማኝ ሰው ብዙ በረከት ያገኛል፤ሀብት ለማግኘት የሚጣደፍ ግን ንጽሕናውን ማጉደፉ አይቀርም። |
አድልዎ ማድረግ መልካም አይደለም፤ሆኖም ሰው ለቁራሽ ዳቦ ብሎ ስህተት ሊፈጽም ይችላል። |
ቀናተኛ ሰው ሀብት ለማግኘት ይጓጓል፤ድህነት ላይ እንደሚወድቅ አያውቅም። |
በምላሱ ከሚሸነግል ይልቅሰውን የሚወቅስ የኋላ ኋላ ይበልጥ ሞገስ ያገኛል። |
አባቱንና እናቱን እየዘረፈ “ምንም ጥፋት የለበትም” የሚል ሁሉ የአጥፊ ተባባሪ ነው። |
ስግብግብ ሰው ጠብ ያነሳሳል፤በይሖዋ የሚታመን ግን ይበለጽጋል። |
በገዛ ልቡ የሚታመን ሁሉ ሞኝ ነው፤በጥበብ የሚመላለስ ግን ክፉ አያገኘውም። |
ለድሃ የሚሰጥ ሁሉ አይቸገርም፤እነሱን ላለማየት ዓይኖቹን የሚከድን ግን ብዙ እርግማን ይደርስበታል። |
ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ሰው ራሱን ይሸሽጋል፤ክፉዎች ሲጠፉ ግን ጻድቃን ይበዛሉ። |
መልካም ስም ከብዙ ሀብት ይመረጣል፤መከበር ከብርና ከወርቅ ይሻላል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.