text
stringlengths
4
267
ሀብታምንና ድሃን የሚያመሳስላቸው ነገር አለ፦ ሁለቱንም የፈጠረው ይሖዋ ነው።
ብልህ ሰው አደጋ ሲያይ ይሸሸጋል፤ተሞክሮ የሌለው ግን ዝም ብሎ ይሄዳል፤ መዘዙንም ይቀበላል።
ትሕትናና ይሖዋን መፍራትሀብት፣ ክብርና ሕይወት ያስገኛል።
በጠማማ ሰው መንገድ ላይ እሾህና ወጥመድ አለ፤ለሕይወቱ ትልቅ ግምት የሚሰጥ ሁሉ ግን ከእነዚህ ይርቃል።
ልጅን ሊሄድበት በሚገባው መንገድ አሠልጥነው፤በሚያረጅበት ጊዜም እንኳ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።
ሀብታም ድሃን ይገዛል፤ተበዳሪም የአበዳሪው ባሪያ ነው።
ክፋትን የሚዘራ ሁሉ ጥፋትን ያጭዳል፤የቁጣውም በትር ያከትማል።
ለጋስ ሰው ይባረካል፤ምግቡን ለድሃ ያካፍላልና።
ንቀት የሚያሳይን ሰው አባረው፤ጭቅጭቅም ይቀራል፤ጥልና ስድብ ያከትማል።
ንጹሕ ልብ የሚወድና ንግግሩ ለዛ ያለው ሰው፣የንጉሥ ወዳጅ ይሆናል።
የይሖዋ ዓይኖች እውቀትን ይጠብቃሉ፤የከዳተኛን ቃል ግን ይሽራል።
ሰነፍ “ውጭ አንበሳ አለ! አደባባይ ላይ እገደላለሁ!” ይላል።
የጋጠወጥ ሴት አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው። ይሖዋ ያወገዘው ሰው እዚያ ውስጥ ይወድቃል።
ሞኝነት በልጅ ልብ ውስጥ ታስሯል፤የተግሣጽ በትር ግን ከእሱ ያርቀዋል።
ሀብቱን ለመጨመር ድሃውን የሚያጭበረብርእንዲሁም ለባለጸጋ ስጦታ የሚሰጥ ሰውየኋላ ኋላ ይደኸያል።
እውቀቴን በሙሉ ልብ እንድትቀበልጆሮህን አዘንብል፤ የጥበበኞችንም ቃል አዳምጥ፤
ምንጊዜም ይህ ቃል ሙሉ በሙሉ በከንፈሮችህ ላይ እንዲሆንቃሉን በውስጥህ መያዝህ መልካም ነውና።
በይሖዋ እንድትተማመን፣ዛሬ እውቀት እሰጥሃለሁ።
ከዚህ ቀደም ምክርናእውቀት የያዙ ሐሳቦች አልጻፍኩልህም?
ይህን ያደረግኩት ለላከህ ትክክለኛ ወሬ ይዘህ እንድትመለስ፣እውነት የሆነውንና እምነት የሚጣልበትን ቃል ላስተምርህ አይደለም?
ድሃውን ድሃ ስለሆነ ብቻ አትዝረፈው፤ችግረኛውንም በከተማው በር ላይ ግፍ አትፈጽምበት፤
ይሖዋ ራሱ ይሟገትላቸዋልና፤የሚያጭበረብሯቸውንም ሰዎች ሕይወት ያጠፋል።
ከግልፍተኛ ሰው ጋር አትግጠም፤በቀላሉ ቱግ ከሚል ሰውም ጋር አትቀራረብ፤
አለዚያ መንገዱን ትማራለህ፤ለራስህም ወጥመድ ይሆናል።
ዋስ ለመሆን እጅ እንደሚመቱ፣ለብድር ተያዥ እንደሚሆኑ ሰዎች አትሁን።
የምትከፍለው ካጣህየተኛህበት አልጋ ከሥርህ ይወሰድብሃል!
አባቶችህ ያደረጉትንየጥንቱን የወሰን ምልክት ከቦታው አታንቀሳቅስ።
በሥራው የተካነን ሰው አይተሃል? በነገሥታት ፊት ይቆማል፤ተራ በሆኑ ሰዎች ፊት አይቆምም።
የለዘበ መልስ ቁጣን ያበርዳል፤ክፉ ቃል ግን ቁጣን ያነሳሳል።
የጥበበኞች ምላስ እውቀትን በሚገባ ይጠቀማል፤የሞኞች አፍ ግን ሞኝነትን ይገልጣል።
የይሖዋ ዓይኖች በሁሉም ቦታ ናቸው፤ክፉዎችንም ሆነ ጥሩ ሰዎችን ይመለከታሉ።
የረጋ አንደበት የሕይወት ዛፍ ነው፤ጠማማ ንግግር ግን ተስፋ ያስቆርጣል።
ሞኝ የአባቱን ተግሣጽ ይንቃል፤ብልህ ግን እርማትን ይቀበላል።
በጻድቅ ሰው ቤት ብዙ ሀብት አለ፤የክፉ ሰው ምርት ግን ችግር ያስከትልበታል።
የጥበበኞች ከንፈር እውቀትን ታስፋፋለች፤የሞኞች ልብ ግን እንዲህ አይደለም።
ይሖዋ የክፉዎችን መሥዋዕት ይጸየፋል፤የቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሰኘዋል።
ይሖዋ የክፉውን መንገድ ይጸየፋል፤ጽድቅን የሚከታተለውን ግን ይወደዋል።
ከመንገድ የሚወጣ ሰው፣ ተግሣጽ መጥፎ ነገር ይመስለዋል፤ወቀሳን የሚጠላ ሁሉ ግን ይሞታል።
መቃብርና የጥፋት ቦታ በይሖዋ ፊት ወለል ብለው ይታያሉ። የሰዎች ልብማ በፊቱ ምንኛ የተገለጠ ነው!
ፌዘኛ የሚያርመውን ሰው አይወድም። ጥበበኞችን አያማክርም።
ደስተኛ ልብ ፊትን ያፈካል፤የልብ ሐዘን ግን መንፈስን ይደቁሳል።
አስተዋይ ልብ እውቀትን ይፈልጋል፤የሞኞች አፍ ግን ቂልነትን ይመገባል።
ጎስቋላ ሰው ዘመኑ ሁሉ አስከፊ ነው፤ደስተኛ ልብ ያለው ሰው ግን ሁልጊዜ ግብዣ ላይ ያለ ያህል ነው።
ከጭንቀት ጋር ከሚገኝ ብዙ ሀብት ይልቅይሖዋን በመፍራት የሚገኝ ጥቂት ነገር ይሻላል።
ጥላቻ ባለበት የሰባ ፍሪዳ ከመብላት ይልቅፍቅር ባለበት አትክልት መብላት ይሻላል።
ግልፍተኛ ሰው ጭቅጭቅ ይፈጥራል፤ቶሎ የማይቆጣ ሰው ግን ጠብን ያበርዳል።
የሰነፍ መንገድ እንደ እሾህ አጥር ነው፤የቅኖች መንገድ ግን እንደተስተካከለ አውራ ጎዳና ነው።
ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ሞኝ ግን እናቱን ያቃልላል።
ማስተዋል የጎደለው ሰው ሞኝነት ያስደስተዋል፤ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰው ግን ቀጥተኛውን መንገድ ተከትሎ ይሄዳል።
መመካከር ከሌለ የታቀደው ነገር ሳይሳካ ይቀራል፤በብዙ አማካሪዎች ግን ይሳካል።
ሰው ትክክለኛውን መልስ በመስጠት ሐሴት ያደርጋል፤በትክክለኛው ጊዜ የተነገረ ቃልም ምንኛ መልካም ነው!
ጥልቅ ማስተዋል ያለው ሰው ወደ መቃብር ከመውረድ ይድን ዘንድየሕይወት መንገድ ወደ ላይ ይመራዋል።
ይሖዋ የትዕቢተኞችን ቤት ያፈርሳል፤የመበለቲቱን ወሰን ግን ያስከብራል።
ይሖዋ የክፉውን ሰው ሐሳብ ይጸየፋል፤ያማረ ቃል ግን በፊቱ ንጹሕ ነው።
በማጭበርበር የተገኘ ትርፍ የሚያጋብስ ሰው በቤተሰቡ ላይ ችግር ያመጣል፤ጉቦን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል።
የጻድቅ ልብ፣ መልስ ከመስጠቱ በፊት ያሰላስላል፤የክፉዎች አፍ ግን መጥፎ ነገር ይዘከዝካል።
ይሖዋ ከክፉዎች እጅግ የራቀ ነው፤የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።
ብሩህ ዓይን ልብን ደስ ያሰኛል፤መልካም ዜናም አጥንትን ያበረታል።
ሕይወት የሚያስገኝ ወቀሳን የሚሰማ፣በጥበበኛ ሰዎች መካከል ይኖራል።
ተግሣጽን ገሸሽ የሚያደርግ ሰው ሁሉ ሕይወቱን ያቃልላል፤ወቀሳን የሚሰማ ሁሉ ግን ማስተዋል ያገኛል።
ይሖዋን መፍራት ጥበብን ያስተምራል፤ትሕትናም ክብርን ትቀድማለች።
ልጆቼ ሆይ፣ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፤ማስተዋል እንድታገኙ በትኩረት አዳምጡ፤
ጥሩ መመሪያ እሰጣችኋለሁና፤ትምህርቴን አትተዉ።
እኔ ለአባቴ ጥሩ ልጅ ነበርኩ፤እናቴም ለእኔ ልዩ ፍቅር ነበራት።
አባቴ እንዲህ ሲል አስተማረኝ፦ “ልብህ ቃሌን አጥብቆ ይያዝ። ትእዛዛቴን ጠብቅ፤ በሕይወትም ትኖራለህ።
ጥበብን አግኝ፤ ማስተዋልንም አዳብር። የምናገረውን ነገር አትርሳ፤ ከእሱም ፈቀቅ አትበል።
ጥበብን አትተዋት፤ እሷም ትጠብቅሃለች። ውደዳት፤ እሷም ትከልልሃለች።
ጥበብ በጣም አስፈላጊ ነገር ናት፤ ስለዚህ ጥበብን አግኝ፤ደግሞም ባለህ ነገር ሁሉ ማስተዋልን ለማግኘት ጥረት አድርግ።
ለጥበብ የላቀ ዋጋ ስጥ፤ እሷም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች። ብታቅፋት ታከብርሃለች።
በራስህ ላይ የሚያምር የአበባ ጉንጉን ትደፋልሃለች፤በውበት አክሊልም ታስጌጥሃለች።”
ልጄ ሆይ፣ አዳምጥ፤ የምናገረውንም ተቀበል፤የሕይወትህም ዘመን ይረዝማል።
በጥበብ መንገድ እንድትሄድ አስተምርሃለሁ፤ቀና በሆነ ጎዳና እመራሃለሁ።
በምትጓዝበት ጊዜ እርምጃህ አይስተጓጎልም፤ብትሮጥም አትሰናከልም።
ተግሣጽን ያዛት፤ አትልቀቃትም። ጠብቃት፤ ሕይወትህ ናትና።
ወደ ክፉዎች መንገድ አትግባ፤በመጥፎ ሰዎች ጎዳናም አትሂድ።
ከእሱ ራቅ፤ በዚያም አትሂድ፤ከዚያ ጎዳና ፈቀቅ በል፤ ደግሞም አልፈኸው ሂድ።
እነሱ ክፋት ካልሠሩ አይተኙምና። ሰውን ለውድቀት ካልዳረጉ እንቅልፍ በዓይናቸው አይዞርም።
የክፋት ምግብ ይበላሉ፤የዓመፅም ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።
የጻድቃን መንገድ ግን ፍንትው ብሎ እንደሚወጣ የማለዳ ብርሃን ነው፤እንደ ቀትር ብርሃን ቦግ ብሎ እስኪበራም ድረስ እየደመቀ ይሄዳል።
የክፉዎች መንገድ እንደ ጨለማ ነው፤ምን እንደሚያሰናክላቸው አያውቁም።
ልጄ ሆይ፣ ቃሌን በትኩረት ተከታተል፤ንግግሬን በጥሞና አዳምጥ።
ከእይታህ አይራቅ፤በልብህ ውስጥ አስቀምጠው፤
ለሚያገኙት ሕይወት ነውና፤ለመላ አካላቸውም ጤና ነው።
ከምንም ነገር በላይ ልብህን ጠብቅ፤የሕይወት ምንጭ ከእሱ ዘንድ ነውና።
ጠማማ አንደበትን ከአንተ አስወግድ፤አታላይ የሆነን ንግግርም ከአንተ አርቅ።
ዓይኖችህ በቀጥታ ይዩ፤አዎ፣ ፊት ለፊት በትኩረት ተመልከት።
የእግርህን መንገድ ደልዳላ አድርግ፤መንገድህም ሁሉ አስተማማኝ ይሆናል።
ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አትበል። እግርህን ከክፉ ነገር መልስ።
የወይን ጠጅ ፌዘኛ፣ የሚያሰክር መጠጥም ሥርዓት አልበኛ ያደርጋል፤በዚህ ምክንያት ከትክክለኛው መንገድ የሚወጣ ሁሉ ጥበበኛ አይደለም።
ንጉሥ የሚፈጥረው ሽብር እንደ አንበሳ ግሳት ነው፤የእሱን ቁጣ የሚያነሳሳ ሁሉ ሕይወቱን ለአደጋ ያጋልጣል።
ሰው ከጠብ መራቁ ያስከብረዋል፤ሞኝ የሆነ ሁሉ ግን ጥል ውስጥ ይዘፈቃል።
ሰነፍ ሰው በክረምት አያርስም፤በመሆኑም በመከር ወራት ባዶውን ሲቀር ይለምናል።
በሰው ልብ ውስጥ ያለ ሐሳብ እንደ ጥልቅ ውኃ ነው፤አስተዋይ ሰው ግን ቀድቶ ያወጣዋል።
ብዙ ሰዎች ስለ ራሳቸው ታማኝ ፍቅር ያወራሉ፤ይሁንና ታማኝ የሆነን ሰው ማን ሊያገኘው ይችላል?
ጻድቅ ንጹሕ አቋሙን ጠብቆ ይመላለሳል። ከእሱ በኋላ የሚመጡት ልጆቹ ደስተኞች ናቸው።
ንጉሥ ለመፍረድ በዙፋን ላይ ሲቀመጥ፣ክፋትን ሁሉ በዓይኖቹ ያበጥራል።
“ልቤን አንጽቻለሁ፤ከኃጢአቴም ነጽቻለሁ” ሊል የሚችል ማን ነው?
አባይ ሚዛንና የሐሰት መለኪያ፣ሁለቱም በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ናቸው።
ሕፃን እንኳ ባሕርይው ንጹሕና ትክክል መሆኑበአድራጎቱ ይታወቃል።
የሚሰማ ጆሮንና የሚያይ ዓይንን፣ሁለቱንም የሠራው ይሖዋ ነው።