text
stringlengths
4
267
እንቅልፍ አትውደድ፤ አለዚያ ድሃ ትሆናለህ። ዓይንህን ግለጥ፤ የተትረፈረፈ ምግብም ታገኛለህ።
ዕቃ የሚገዛ ሰው “የማይረባ ነው፣ የማይረባ ነው!” ይላል፤ከሄደ በኋላ ግን በራሱ ይኩራራል።
ወርቅ አለ፤ ዛጎልም ተትረፍርፏል፤እውቀትን የሚናገሩ ከንፈሮች ግን ውድ ናቸው።
አንድ ሰው ለማያውቀው ሰው ዋስ ከሆነ ልብሱን ውሰድበት፤ይህን ያደረገው ለባዕድ ሴት ብሎ ከሆነ መያዣውን ውሰድ።
ሰው በማጭበርበር ያገኘው ምግብ ያስደስተዋል፤በኋላ ግን አፉን ኮረት ይሞላዋል።
መመካከር ሲኖር የታቀደው ነገር ይሳካል፤ለውጊያም ስትወጣ ጥበብ ያለበት አመራር ተቀበል።
ስም የሚያጠፋ ሰው እየዞረ የሌሎችን ሚስጥር ይገልጣል፤ማማት ከሚወድ ሰው ጋር አትወዳጅ።
አባቱንና እናቱን የሚረግም ሁሉጨለማ ሲሆን መብራቱ ይጠፋበታል።
በመጀመሪያ በስግብግብነት የተገኘ ውርስ፣የኋላ ኋላ በረከት አይሆንም።
“ቆይ፣ ብድሬን ባልመልስ!” አትበል። ይሖዋን ተስፋ አድርግ፤ እሱም ያድንሃል።
አባይ ሚዛን በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው፤ለማጭበርበር የሚያገለግሉ መለኪያዎችንም መጠቀም ጥሩ አይደለም።
ይሖዋ የሰውን አካሄድ ይመራል፤ሰው የገዛ መንገዱን እንዴት ማስተዋል ይችላል?
ሰው ቸኩሎ “የተቀደሰ ነው!” ቢልና ከተሳለ በኋላ ስእለቱን መልሶ ማጤን ቢጀምር ወጥመድ ይሆንበታል።
ጥበበኛ ንጉሥ ክፉ ሰዎችን ያበጥራል፤የመውቂያ መንኮራኩርም በላያቸው ያስኬዳል።
የሰው እስትንፋስ የይሖዋ መብራት ነው፤ውስጣዊ ማንነቱን በሚገባ ይመረምራል።
ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ንጉሥን ይጠብቃሉ፤በታማኝ ፍቅርም ዙፋኑን ያጸናል።
የወጣቶች ክብር ጉልበታቸው ነው፤የአረጋውያንም ግርማ ሽበታቸው ነው።
ሰንበርና ቁስል ክፋትን ያስወግዳል፤ግርፋትም የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት ያጠራል።
ተግሣጽን የሚወድ እውቀትን ይወዳል፤ወቀሳን የሚጠላ ግን የማመዛዘን ችሎታ ይጎድለዋል።
ጥሩ ሰው የይሖዋን ሞገስ ያገኛል፤ክፋት የሚያሴርን ሰው ግን እሱ ይፈርድበታል።
በክፋት ጸንቶ መቆም የሚችል ሰው የለም፤ጻድቅ ግን ፈጽሞ አይነቀልም።
ጥሩ ሚስት ለባሏ ዘውድ ናት፤አሳፋሪ ሚስት ግን አጥንቱ ውስጥ እንዳለ ንቅዘት ናት።
የጻድቃን ሐሳብ ፍትሐዊ ነው፤የክፉዎች ምክር ግን አሳሳች ነው።
የክፉዎች ቃል ገዳይ ወጥመድ ነው፤የቅኖች አፍ ግን ይታደጋቸዋል።
ክፉዎች ሲገለበጡ ደብዛቸው ይጠፋል፤የጻድቃን ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል።
ሰው አስተዋይ በሆነ አንደበቱ ይመሰገናል፤ልቡ ጠማማ የሆነ ግን ይናቃል።
የሚበላው ሳይኖረው ራሱን ከፍ ከፍ ከሚያደርግ ሰው ይልቅአገልጋይ ኖሮት ራሱን ዝቅ አድርጎ የሚኖር ሰው ይሻላል።
ጻድቅ የቤት እንስሳቱን ይንከባከባል፤ክፉዎች ግን ርኅራኄያቸው እንኳ ጭካኔ ነው።
መሬቱን የሚያርስ ሰው የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፤ከንቱ ነገሮችን የሚያሳድድ ግን ማስተዋል ይጎድለዋል።
ክፉ ሰው፣ ሌሎች መጥፎ ሰዎች ባጠመዱት ነገር ይቀናል፤የጻድቃን ሥር ግን ፍሬ ያፈራል።
መጥፎ ሰው በክፉ ንግግሩ ይጠመዳል፤ጻድቅ ግን ከመከራ ያመልጣል።
ሰው ከአፉ ፍሬ መልካም ነገር ይጠግባል፤የእጁ ሥራም ብድራት ይከፍለዋል።
የሞኝ መንገድ በራሱ ዓይን ትክክል ነው፤ጥበበኛ ግን ምክር ይቀበላል።
ሞኝ ሰው ቁጣውን ወዲያውኑ ይገልጻል፤ብልህ ሰው ግን ስድብን ችላ ብሎ ያልፋል።
ታማኝ ምሥክር እውነቱን ይናገራል፤ውሸታም ምሥክር ግን ያታልላል።
ሳይታሰብበት የሚነገር ቃል እንደ ሰይፍ ይወጋል፤የጥበበኞች ምላስ ግን ፈውስ ነው።
እውነት የሚናገሩ ከንፈሮች ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ፤ሐሰተኛ ምላስ ግን የሚቆየው ለቅጽበት ብቻ ነው።
ተንኮል በሚሸርቡ ሰዎች ልብ ውስጥ ማታለያ አለ፤ሰላምን የሚያራምዱ ግን ደስተኞች ናቸው።
ጻድቅ ምንም ዓይነት ጉዳት አያገኘውም፤የክፉዎች ሕይወት ግን በመከራ የተሞላ ይሆናል።
ይሖዋ ውሸታም ከንፈሮችን ይጸየፋል፤በታማኝነት የሚመላለሱ ግን ደስ ያሰኙታል።
ብልህ ሰው እውቀቱን ይሰውራል፤የሞኝ ልብ ግን ሞኝነቱን ይዘከዝካል።
የትጉ ሰዎች እጅ ገዢ ትሆናለች፤ሥራ ፈት እጆች ግን ለባርነት ይዳረጋሉ።
በሰው ልብ ውስጥ ያለ ጭንቀት ልቡ እንዲዝል ያደርገዋል፤መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል።
ጻድቅ የግጦሽ መሬቱን በሚገባ ይቃኛል፤የክፉዎች መንገድ ግን እንዲባዝኑ ያደርጋቸዋል።
ሰነፍ ሰው አደኑን አሳድዶ አይዝም፤ትጋት ግን የሰው ውድ ሀብት ነው።
የጽድቅ ጎዳና ወደ ሕይወት ይመራል፤በጎዳናው ላይ ሞት የለም።
ራሱን የሚያገል ሰው ሁሉ የራስ ወዳድነት ምኞቱን ያሳድዳል፤ጥበብንም ሁሉ ይቃወማል።
ሞኝ ሰው ማስተዋል አያስደስተውም፤ይልቁንም በልቡ ያለውን ሐሳብ ይገልጣል።
ክፉ ሰው ሲመጣ ንቀትም ይመጣል፤ከውርደትም ጋር ኀፍረት ይመጣል።
ከሰው አፍ የሚወጣ ቃል ጥልቅ ውኃ ነው። የጥበብ ምንጭ የሚንዶለዶል ጅረት ነው።
ለክፉ ሰው ማድላት፣ጻድቁንም ፍትሕ መንፈግ መልካም አይደለም።
የሞኝ ሰው ንግግር ጠብ ያስነሳል፤አፉም ዱላ ይጋብዛል።
የሞኝ አንደበት መጥፊያው ነው፤ከንፈሮቹም ለሕይወቱ ወጥመድ ናቸው።
ስም አጥፊ የሚናገረው ቃል ጣፋጭ እንደሆነ ቁራሽ ምግብ ነው፤በፍጥነት ተውጦ በቀጥታ ወደ ሆድ ይገባል።
በሥራው ታካች የሆነ ሰው ሁሉ፣የአጥፊ ወንድም ነው።
የይሖዋ ስም ጽኑ ግንብ ነው። ጻድቅ ወደዚያ በመሮጥ ጥበቃ ያገኛል።
የባለጸጋ ሰው ሀብት የተመሸገ ከተማው ነው፤በሐሳቡም ጥበቃ እንደሚያስገኝ ግንብ አድርጎ ይመለከተዋል።
ሰው ለውድቀት ከመዳረጉ በፊት ልቡ ይታበያል፤ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች።
እውነታውን ከመስማቱ በፊት መልስ የሚሰጥ ሰው፣ሞኝነት ይሆንበታል፤ ውርደትም ይከናነባል።
ጠንካራ መንፈስ ያለው ሰው ሕመሙን መቋቋም ይችላል፤የተደቆሰን መንፈስ ግን ማን ሊቋቋም ይችላል?
የአስተዋይ ሰው ልብ እውቀትን ያገኛል፤የጥበበኛም ጆሮ እውቀትን ለማግኘት ይጥራል።
ስጦታ ለሰጪው መንገዱን ይከፍትለታል፤በታላላቅ ሰዎችም ፊት መቅረብ ያስችለዋል።
ክሱን አስቀድሞ ያሰማ ትክክለኛ ይመስላል፤ይህም ሌላው ወገን መጥቶ እስኪመረምረው ድረስ ነው።
ዕጣ መጣል ጭቅጭቅ እንዲያበቃ ያደርጋል፤ኃይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል።
የተበደለ ወንድም ከተመሸገች ከተማ ይበልጥ የማይበገር ነው፤እንደ ግንብ በሮች መቀርቀሪያም የጠነከረ ጠብ አለ።
ሰው በአፉ ፍሬ ሆዱ ይሞላል፤ከንፈሩም በሚያስገኘው ምርት ይረካል።
አንደበት የሞትና የሕይወት ኃይል አላት፤ሊጠቀምባት የሚወድ ፍሬዋን ይበላል።
ጥሩ ሚስት ያገኘ ጥሩ ነገር አግኝቷል፤የይሖዋንም ሞገስ ያገኛል።
ድሃ እየተለማመጠ ይናገራል፤ሀብታም ግን በኃይለ ቃል ይመልሳል።
እርስ በርስ ከመጠፋፋት ወደኋላ የማይሉ ጓደኛሞች አሉ፤ነገር ግን ከወንድም ይበልጥ የሚቀርብ ጓደኛ አለ።
ከንጉሥ ጋር ለመመገብ ስትቀመጥ፣በፊትህ ያለውን በሚገባ አስተውል፤
ለመብላት ብትቋምጥ እንኳበጉሮሮህ ላይ ቢላ አስቀምጥ።
የእሱ ጣፋጭ ምግብ አያስጎምጅህ፤ምግቡ አታላይ ነውና።
ሀብት ለማግኘት አትልፋ። ይህን ትተህ በማስተዋል ተመላለስ።
ዓይንህን ስትጥልበት በዚያ አታገኘውም፤የንስር ዓይነት ክንፎች አውጥቶ ወደ ሰማይ ይበርራልና።
የስስታምን ምግብ አትብላ፤ጣፋጭ ምግቡ አያስጎምጅህ፤
እሱ ሒሳብ እንደሚይዝ ሰው ነውና። “ብላ፣ ጠጣ” ይልሃል፤ የሚናገረው ግን ከልቡ አይደለም።
የበላሃትን ቁራሽ ምግብ ታስመልሳለህ፤የተናገርካቸው የምስጋና ቃላትም ከንቱ ይሆናሉ።
የምትናገራቸውን ጥበብ ያዘሉ ቃላት ስለሚንቅለሞኝ ሰው ምንም አትናገር።
የጥንቱን የወሰን ምልክት ከቦታው አታንቀሳቅስ፤ደግሞም አባት የሌላቸውን ልጆች መሬት አትያዝ።
የሚከራከርላቸው ብርቱ ነውና፤እሱ ራሱ ከአንተ ጋር ይሟገትላቸዋል።
ልብህን ለተግሣጽ፣ጆሮህንም ለእውቀት ቃል ስጥ።
ልጅን ከመገሠጽ ወደኋላ አትበል። በበትር ብትመታው አይሞትም።
ከመቃብር ታድነው ዘንድበበትር ምታው።
ልጄ ሆይ፣ ልብህ ጥበበኛ ቢሆን፣የእኔ ልብ ሐሴት ያደርጋል።
ከንፈሮችህ ትክክል የሆነውን ሲናገሩውስጤ ደስ ይለዋል።
ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፤ከዚህ ይልቅ ቀኑን ሙሉ ይሖዋን በመፍራት ተመላለስ፤
እንዲህ ብታደርግ የወደፊት ሕይወትህ የተሳካ ይሆናል፤ተስፋህም ከንቱ አይሆንም።
ልጄ ሆይ፣ አዳምጥ፤ ጥበበኛም ሁን፤ልብህንም በትክክለኛው መንገድ ምራ።
ብዙ የወይን ጠጅ እንደሚጠጡ፣ሥጋም ያለልክ እንደሚሰለቅጡ ሰዎች አትሁን፤
ሰካራምና ሆዳም ይደኸያሉና፤ድብታ ሰውን የተቦጫጨቀ ልብስ ያስለብሰዋል።
የወለደህን አባትህን ስማ፤እናትህንም ስላረጀች አትናቃት።
እውነትንና ጥበብን፣ ተግሣጽንና ማስተዋልን ግዛ፤ፈጽሞም አትሽጣቸው።
የጻድቅ አባት ደስ ይለዋል፤ጥበበኛ ልጅ የወለደ ሁሉ በልጁ ሐሴት ያደርጋል።
አባትህና እናትህ ሐሴት ያደርጋሉ፤አንተን የወለደችም ደስ ይላታል።
ልጄ ሆይ፣ ልብህን ስጠኝ፤ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ።
ዝሙት አዳሪ ጥልቅ ጉድጓድ፣ባለጌ ሴትም ጠባብ ጉድጓድ ናትና።
እንደ ዘራፊ ታደባለች፤ታማኝ ያልሆኑ ወንዶችን ቁጥር ታበዛለች።
ዋይታ የማን ነው? ጭንቀት የማን ነው? ጠብ የማን ነው? እሮሮ የማን ነው? ያለምክንያት መቁሰል የማን ነው? የዓይን ቅላት የማን ነው?
ይህ ሁሉ የሚደርሰው የወይን ጠጅ በመጠጣት ረጅም ጊዜ በሚያሳልፉ፣የተደባለቀም ወይን ጠጅ ፍለጋ በሚዞሩ ሰዎች ላይ ነው።