text
stringlengths
4
267
በብርጭቆ ውስጥ ሲያንጸባርቅ፣እየጣፈጠም ሲወርድ በወይን ጠጅ ቅላት ዓይንህ አይማረክ፤
በመጨረሻ እንደ እባብ ይናደፋልና፤እንደ እፉኝትም መርዙን ይረጫል።
ዓይኖችህ እንግዳ ነገር ያያሉ፤ልብህም ጠማማ ነገር ይናገራል።
በባሕር መካከል እንደተኛ፣በመርከብ ምሰሶም ጫፍ ላይ እንደተጋደመ ሰው ትሆናለህ።
እንዲህ ትላለህ፦ “መቱኝ፤ ሆኖም አልተሰማኝም። ደበደቡኝ፤ ሆኖም አልታወቀኝም። ተጨማሪ መጠጥ እጠጣ ዘንድ የምነቃው መቼ ነው?”
ልጄ ሆይ፣ ለባልንጀራህ ዋስ ብትሆን፣የማታውቀውን ሰው እጅ ብትመታ፣
በገባኸው ቃል ብትጠመድ፣ከአፍህ በወጣው ቃል ብትያዝ፣
ልጄ ሆይ፣ በባልንጀራህ እጅ ወድቀሃልና፣ይህን በማድረግ ራስህን ነፃ አውጣ፦ ሂድና ባልንጀራህን በትሕትና አጥብቀህ ለምነው።
ይህን ሳታደርግ አትተኛ፤በዓይንህም እንቅልፍ አይዙር።
እንደ ሜዳ ፍየል ከአዳኝ እጅ፣እንደ ወፍም ከወፍ አዳኝ እጅ ራስህን አድን።
አንተ ሰነፍ፣ ወደ ጉንዳን ሂድ፤መንገዷንም በጥሞና ተመልክተህ ጥበበኛ ሁን።
አዛዥ፣ አለቃ ወይም ገዢ ባይኖራትም እንኳ፣
ምግቧን በበጋ ታዘጋጃለች፤ቀለቧንም በመከር ወቅት ትሰበስባለች።
አንተ ሰነፍ፣ የምትጋደመው እስከ መቼ ነው? ከእንቅልፍህ የምትነሳውስ መቼ ነው?
ቆይ ትንሽ ልተኛ፣ ቆይ ትንሽ ላንቀላፋ፣እጄንም አጣጥፌ እስቲ ትንሽ ጋደም ልበል ካልክ፣
ድህነት እንደ ወንበዴ፣እጦትም መሣሪያ እንደታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።
የማይረባና ክፉ ሰው ንግግሩ ጠማማ ነው፤
በዓይኑ ይጣቀሳል፤ በእግሩ ምልክት ይሰጣል፤ በጣቶቹም ይጠቁማል።
ጠማማ በሆነው ልቡ፣ነጋ ጠባ ሴራ ይጠነስሳል፤ ጠብም ይዘራል።
በመሆኑም ጥፋት በድንገት ይመጣበታል፤እንደማይጠገን ሆኖ በቅጽበት ይሰበራል።
ይሖዋ የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፤እንዲያውም እሱ የሚጸየፋቸው ነገሮች ሰባት ናቸው፦
ትዕቢተኛ ዓይን፣ ውሸታም ምላስ፣ ንጹሕ ደም የሚያፈሱ እጆች፣
ክፉ ሐሳብ የሚያውጠነጥን ልብና ወደ ክፋት በፍጥነት የሚሮጡ እግሮች፣
ባወራ ቁጥር ውሸት የሚናገር ሐሰተኛ ምሥክርናበወንድማማቾች መካከል ጠብ የሚዘራ ሰው።
ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፤የእናትህንም መመሪያ ቸል አትበል።
ምንጊዜም በልብህ አኑራቸው፤በአንገትህም ዙሪያ እሰራቸው።
በምትሄድበት ሁሉ ይመራሃል፤ስትተኛም ይጠብቅሃል፤ስትነቃም ያነጋግርሃል።
ትእዛዙ መብራት ነውና፤ሕጉም ብርሃን ነው፤የተግሣጽ ወቀሳም ወደ ሕይወት ይመራል።
ከክፉ ሴት፣ ከባለጌ ሴትምየሚያባብል አንደበት ይጠብቁሃል።
ውበቷን በልብህ አትመኝ፤የሚያማምሩ ዓይኖቿም አይማርኩህ፤
አንድ ሰው በዝሙት አዳሪ የተነሳ ለድህነት ይዳረጋልና፤አመንዝራ ሴት ደግሞ የሰውን ውድ ሕይወት ታጠምዳለች።
በጉያው እሳት ታቅፎ ልብሱ የማይቃጠልበት ሰው አለ?
ወይስ በፍም ላይ ተራምዶ እግሮቹ የማይቃጠሉበት ሰው ይኖራል?
ከባልንጀራው ሚስት ጋር የሚተኛ ሰውም እንደዚሁ ነው፤የሚነካት ሁሉ መቀጣቱ አይቀርም።
ሌባ በተራበ ጊዜ ራሱን ሊያጠግብ ቢሰርቅ፣ሰዎች በንቀት አያዩትም።
በተያዘ ጊዜ ግን ሰባት እጥፍ ይከፍላል፤በቤቱ ያለውን ውድ ነገር ሁሉ ያስረክባል።
ከሴት ጋር ምንዝር የሚፈጽም ሁሉ ማስተዋል ይጎድለዋል፤እንዲህ የሚያደርግ ሰው በራሱ ላይ ጥፋት ያመጣል።
የሚያተርፈው ነገር ቢኖር ቁስልና ውርደት ነው፤ኀፍረቱም መቼም አይወገድም።
ቅናት ባልን እጅግ ያስቆጣዋልና፤ለበቀል በሚነሳበት ጊዜም ፈጽሞ ርኅራኄ አያሳይም።
ማንኛውንም ዓይነት ካሳ አይቀበልም፤ምንም ያህል ስጦታ ብታቀርብለት ቁጣው አይበርድም።
ብዙ ጊዜ ተወቅሶ አንገቱን ያደነደነ ሰው፣ሊፈወስ በማይችል ሁኔታ በድንገት ይሰበራል።
ጻድቃን ሲበዙ ሕዝብ ሐሴት ያደርጋል፤ክፉ ሰው ሲገዛ ግን ሕዝብ ይቃትታል።
ጥበብን የሚወድ ሰው አባቱን ደስ ያሰኛል፤ከዝሙት አዳሪዎች ጋር የሚወዳጅ ግን ሀብቱን ያባክናል።
ንጉሥ ፍትሕ በማስፈን አገርን ያረጋጋል፤ጉቦ የሚፈልግ ሰው ግን ያወድማታል።
ባልንጀራውን የሚሸነግል ሰው፣ለእግሩ ወጥመድ ይዘረጋበታል።
መጥፎ ሰው በደሉ ወጥመድ ይሆንበታል፤ጻድቅ ግን እልል ይላል፤ ሐሴትም ያደርጋል።
ጻድቅ ለድሆች መብት ይቆረቆራል፤ክፉ ሰው ግን ለእንዲህ ዓይነት ጉዳይ ደንታ የለውም።
ጉራ የሚነዙ ሰዎች ከተማን ያቃጥላሉ፤ጥበበኞች ግን ቁጣን ያበርዳሉ።
ጥበበኛ ሰው ከሞኝ ጋር ቢሟገት፣ሁከትና ፌዝ ይነግሣል፤ ደስታ ግን አይኖርም።
ደም የተጠሙ ሰዎች ንጹሕ የሆነን ሰው ሁሉ ይጠላሉ፤ቅን የሆነውን ሰው ሕይወት ለማጥፋት ይሻሉ።
ሞኝ ስሜቱን ሁሉ እንዳሻው ይገልጻል፤ጥበበኛ ግን ስሜቱን ይቆጣጠራል።
ገዢ የሐሰት ወሬ የሚሰማ ከሆነ፣አገልጋዮቹ ሁሉ ክፉዎች ይሆናሉ።
ድሃንና ጨቋኝን የሚያመሳስላቸው ነገር አለ፦ ይሖዋ ለሁለቱም የዓይን ብርሃን ይሰጣል።
ንጉሥ ለድሆች በትክክል ሲፈርድ፣ዙፋኑ ምንጊዜም ጸንቶ ይኖራል።
በትርና ወቀሳ ጥበብ ያስገኛሉ፤መረን የተለቀቀ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።
ክፉዎች ሲበዙ ክፋት ይበዛል፤ጻድቃን ግን የእነሱን ውድቀት ያያሉ።
ልጅህን ገሥጸው፤ ሰላም ይሰጥሃል፤ደግሞም እጅግ ደስ ያሰኝሃል።
ራእይ ከሌለ ሕዝብ እንዳሻው ይሆናል፤ሕግን የሚጠብቁ ግን ደስተኞች ናቸው።
አገልጋይ በቃል ብቻ ለመታረም ፈቃደኛ አይሆንም፤የሚነገረውን ነገር ቢረዳውም እንኳ እሺ ብሎ አይታዘዝምና።
ለመናገር የሚቸኩል ሰው አይተህ ታውቃለህ? ከእሱ ይልቅ ሞኝ የተሻለ ተስፋ አለው።
አገልጋይ ከልጅነቱ ጀምሮ ከተሞላቀቀ፣የኋላ ኋላ ምስጋና ቢስ ይሆናል።
በቀላሉ የሚቆጣ ሰው ጠብ ያስነሳል፤ግልፍተኛ የሆነም ብዙ በደል ይፈጽማል።
ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፤ትሑት መንፈስ ያለው ግን ክብር ይጎናጸፋል።
የሌባ ግብረ አበር ራሱን ይጠላል። እንዲመሠክር የቀረበለትን ጥሪ ቢሰማም ምንም አይናገርም።
ሰውን መፍራት ወጥመድ ነው፤በይሖዋ የሚታመን ግን ጥበቃ ያገኛል።
ብዙዎች ከገዢ ጋር ተገናኝተው መነጋገር ይሻሉ፤ሰው ግን ፍትሕ የሚያገኘው ከይሖዋ ነው።
ጻድቅ ፍትሐዊ ያልሆነን ሰው ይጸየፋል፤ክፉ ሰው ግን በቀና መንገድ የሚሄደውን ይጸየፋል።
ጥበብ እየተጣራች አይደለም? ማስተዋልስ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ እያሰማች አይደለም?
በጎዳና አጠገብ በሚገኙ ከፍታ ቦታዎች፣መንገዶች በሚገናኙበት ቦታ ላይ ቆማለች።
ወደ ከተማዋ በሚያስገቡት በሮች አጠገብ፣በደጆቹ መግቢያዎች ላይድምፅዋን ከፍ አድርጋ ትጮኻለች፦
“ሰዎች ሆይ፣ የምጣራው እናንተን ነው፤ድምፄን ከፍ አድርጌ የማሰማው ለሁሉም ነው።
እናንተ ተሞክሮ የሌላችሁ፣ ብልሃትን ተማሩ፤እናንተ ሞኞች፣ አስተዋይ ልብ ይኑራችሁ።
የምናገረው ነገር በጣም አስፈላጊ ስለሆነ አዳምጡኝ፤ከንፈሮቼ ትክክል የሆነውን ይናገራሉ፤
አንደበቴ በለሰለሰ ድምፅ እውነትን ይናገራልና፤ከንፈሮቼም ክፋትን ይጸየፋሉ።
ከአፌ የሚወጡት ቃላት ሁሉ ጽድቅ ናቸው። የተጣመመ ወይም የተወላገደ ነገር አይገኝባቸውም።
ጥልቅ ግንዛቤ ላለው፣ ሁሉም ቀና ናቸው፤እውቀት ላላቸውም ትክክል ናቸው።
ከብር ይልቅ ተግሣጼን፣ጥራት ካለውም ወርቅ ይልቅ እውቀትን ተቀበሉ፤
ጥበብ ከዛጎል ትበልጣለችና፤ተፈላጊ የሆኑ ሌሎች ነገሮች ሁሉ ከእሷ ጋር ሊወዳደሩ አይችሉም።
እኔ ጥበብ፣ ከብልሃት ጋር አብሬ እኖራለሁ፤እውቀትና የማመዛዘን ችሎታ አግኝቻለሁ።
ይሖዋን መፍራት ማለት ክፉ ነገርን መጥላት ነው። ትዕቢትን፣ ኩራትን፣ ክፉ መንገድንና ጠማማ ንግግርን እጠላለሁ።
ጥሩ ምክር መስጠት እችላለሁ፤ ማስተዋል የታከለበት ጥበብም አለኝ፤ማስተዋልና ኃይል የእኔ ናቸው።
ነገሥታት የሚገዙት በእኔ ነው፤ከፍተኛ ባለሥልጣናትም የጽድቅ ድንጋጌ የሚያወጡት በእኔ ነው።
መኳንንት የሚገዙት በእኔ ነው፤ታላላቅ ሰዎችም በጽድቅ የሚፈርዱት በእኔ ነው።
የሚወዱኝን እወዳቸዋለሁ፤የሚፈልጉኝም ያገኙኛል።
ሀብትና ክብር፣ዘላቂ ብልጽግናና ጽድቅ በእኔ ዘንድ አሉ።
ፍሬዬ ከወርቅ፣ አልፎ ተርፎም ከጠራ ወርቅ ይሻላል፤ከእኔ የምታገኙት ስጦታም ጥራት ካለው ብር ይበልጣል።
በጽድቅ መንገድ፣በፍትሕ ጎዳና መካከል እጓዛለሁ፤
ለሚወዱኝ ውድ የሆኑ ነገሮችን አወርሳለሁ፤ግምጃ ቤቶቻቸውንም እሞላለሁ።
ይሖዋ የመንገዱ መጀመሪያ አድርጎ ፈጠረኝ፤ከብዙ ዘመን በፊት ካከናወናቸው ሥራዎች ቀዳሚው አደረገኝ።
ከጥንት፣ ከመጀመሪያው አንስቶ፣ምድርም ከመፈጠሯ አስቀድሞ ከፍ ያለ ቦታ ተሰጠኝ።
ጥልቅ ውኃዎች ባልነበሩበት ጊዜ፣ምንጮች ከመፍለቃቸው በፊት ተወለድኩ።
ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፣ከኮረብቶች በፊት ተወለድኩ፤
ምድርንም ሆነ ሜዳዎቹን እንዲሁምየመጀመሪያዎቹን የአፈር ጓሎች ከመሥራቱ በፊት ተወለድኩ።
ሰማያትን ባዘጋጀ ጊዜ በዚያ ነበርኩ፤በውኃዎች ላይ የአድማስን ምልክት ባደረገ ጊዜ፣
ደመናትን በላይ ባዘጋጀ ጊዜ፣የጥልቅ ውኃ ምንጮችን በመሠረተ ጊዜ፣
የባሕሩ ውኃከትእዛዙ አልፎ እንዳይሄድ በደነገገ ጊዜ፣የምድርን መሠረቶች ባቆመ ጊዜ፣
በዚያን ወቅት የተዋጣለት ሠራተኛ ሆኜ ከጎኑ ነበርኩ። በየዕለቱ በእኔ የተነሳ ልዩ ደስታ ይሰማው ነበር፤እኔም በፊቱ ሁልጊዜ ሐሴት አደርግ ነበር፤
እሱ በፈጠረው፣ ሰው በሚኖርበት ምድር ሐሴት አደረግኩ፤በተለይ ደግሞ በሰው ልጆች እጅግ እደሰት ነበር።
እንግዲህ ልጆቼ ሆይ፣ አዳምጡኝ፤አዎ፣ መንገዴን የሚጠብቁ ደስተኞች ናቸው።
ተግሣጽን ስሙ፤ ጥበበኞችም ሁኑ፤ፈጽሞም ቸል አትበሉት።