text
stringlengths
4
267
በየዕለቱ በማለዳ በራፌ ላይ መጥቶ፣በበሬ መቃን አጠገብ ቆሞ በመጠባበቅየሚያዳምጠኝ ሰው ደስተኛ ነው፤
እኔን የሚያገኝ ሕይወትን ያገኛልና፤በይሖዋም ዘንድ ሞገስ ያገኛል።
እኔን ችላ የሚል ግን ራሱን ይጎዳል፤የሚጠሉኝ ሁሉ ሞትን ይወዳሉ።”
ቂጣህን በውኃ ላይ ጣል፤ ከብዙ ቀናት በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህና።
ካለህ ነገር ላይ ለሰባት፣ እንዲያውም ለስምንት አካፍለህ ስጥ፤ በምድር ላይ የሚመጣውን አደጋ አታውቅምና።
ደመናት ውኃ ካዘሉ በምድር ላይ ዶፍ ያወርዳሉ፤ እንዲሁም ዛፍ በስተ ደቡብ ወይም በስተ ሰሜን ከወደቀ በዚያው በወደቀበት ይቀራል።
ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፤ ደመናትንም የሚመለከት አያጭድም።
መንፈስ፣ በእርጉዝ ሴት ውስጥ በሚገኝ ሕፃን አጥንቶች ላይ እንዴት እንደሚሠራ እንደማታውቅ ሁሉ፣ ሁሉንም ነገር የሚያከናውነውን የእውነተኛውን አምላክ ሥራም አታውቅም።
በማለዳ ዘርህን ዝራ፤ እስከ ምሽትም ድረስ እጅህ ሥራ አይፍታ፤ ይህ ወይም ያ የትኛው እንደሚያድግ ወይም ደግሞ ሁለቱም ይጸድቁ እንደሆነ አታውቅምና።
ብርሃን ደስ ያሰኛል፤ ፀሐይንም ማየት ለዓይን መልካም ነው።
ሰው የቱንም ያህል ብዙ ዓመት ቢኖር በእያንዳንዱ ቀን ደስ ይበለው። ሆኖም በጨለማ የተዋጡት ቀናት ብዙ ሊሆኑ እንደሚችሉ መዘንጋት አይኖርበትም፤ የሚመጣው ሁሉ ከንቱ ነው።
አንተ ወጣት፣ በወጣትነትህ ጊዜ ደስ ይበልህ፤ በወጣትነትህም ዘመን ልብህ ደስ ይበለው። የልብህን መንገድ ተከተል፤ ዓይንህ በሚመራህም መንገድ ሂድ፤ ሆኖም ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እውነተኛው አምላክ ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ እወቅ።
ስለዚህ የሚያስጨንቁ ነገሮችን ከልብህ አስወግድ፤ ጎጂ ነገሮችንም ከሰውነትህ አርቅ፤ ወጣትነትና የለጋነት ዕድሜ ከንቱ ናቸውና።
በኢየሩሳሌም የነገሠው የሰብሳቢው የዳዊት ልጅ ቃል።
ሰብሳቢው “የከንቱ ከንቱ ነው!የከንቱ ከንቱ ነው! ሁሉም ነገር ከንቱ ነው!” አለ።
ሰው ከፀሐይ በታች በትጋት ከሚያከናውነውና ከሚለፋበት ሥራ ሁሉየሚያገኘው ጥቅም ምንድን ነው?
ትውልድ ይሄዳል፤ ትውልድ ይመጣል፤ምድር ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።
ፀሐይ ትወጣለች፤ ደግሞም ትጠልቃለች፤ከዚያም ዳግመኛ ወደምትወጣበት ቦታ ለመመለስ ትጣደፋለች።
ነፋስ ወደ ደቡብ ይነፍሳል፤ ወደ ሰሜንም ዞሮ ይሄዳል፤ክብ እየሠራ ያለማቋረጥ ይሽከረከራል፤ ደግሞም ነፋሱ ዑደቱን ይቀጥላል።
ጅረቶች ሁሉ ወደ ባሕር ይፈስሳሉ፤ ሆኖም ባሕሩ አይሞላም። ጅረቶቹ እንደገና ይፈስሱ ዘንድ ወደሚነሱበት ወደዚያው ቦታ ተመልሰው ይሄዳሉ።
ሁሉ ነገር አሰልቺ ነው፤ሁሉንም ነገር ሊገልጽ የሚችል ሰው የለም። ዓይን አይቶ አይጠግብም፤ጆሮም ሰምቶ አይሞላም።
ከዚህ በፊት የነበረው ነገር ወደፊትም ይሆናል፤ከዚህ በፊት የተደረገውም ነገር እንደገና ይደረጋል፤ከፀሐይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም።
አንድ ሰው “ተመልከት፣ ይህ አዲስ ነገር ነው” ሊል የሚችለው ነገር ይኖራል? ከጥንት ጀምሮ የነበረ ነው፤ከእኛ ዘመን በፊት የነበረ ነው።
በቀድሞ ዘመን የነበሩትን ሰዎች ማንም አያስታውሳቸውም፤ከጊዜ በኋላ የሚመጡትንም የሚያስታውሳቸው አይኖርም፤ከእነሱ በኋላ የሚነሱት ሰዎችም እንኳ አያስታውሷቸውም።
እኔ ሰብሳቢው በኢየሩሳሌም፣ የእስራኤል ንጉሥ ነበርኩ።
ከሰማይ በታች የተሠራውን ነገር ሁሉ ይኸውም አምላክ የሰው ልጆች እንዲጠመዱበት የሰጣቸውን አሰልቺ ሥራ በጥበብ ለማጥናትና ለመመርመር ከልቤ ጥረት አደረግኩ።
ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ ተመለከትኩ፤እነሆ፣ ሁሉም ከንቱ ነፋስንም እንደማሳደድ ነው።
የተጣመመ ነገር ሊቃና አይችልም፤የሌለም ነገር በምንም መንገድ ሊቆጠር አይችልም።
እኔም በልቤ እንዲህ አልኩ፦ “እነሆ፣ ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ እጅግ የላቀ ጥበብ አገኘሁ፤ ልቤም ከፍተኛ ጥበብና እውቀት አገኘ።”
እኔም ጥበብንና እብደትን እንዲሁም ሞኝነትን ለመረዳት ከልቤ ጥረት አደረግኩ፤ ይህም ቢሆን ነፋስን እንደማሳደድ ነው።
ጥበብ ሲበዛ ብስጭትም ይበዛልና፤በመሆኑም እውቀትን የሚጨምር ሁሉ ሥቃይንም ይጨምራል።
ጥሩ ስም ከጥሩ ዘይት፣ የሞትም ቀን ከልደት ቀን ይሻላል።
ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ይልቅ ወደ ሐዘን ቤት መሄድ ይሻላል፤ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ሞት ነውና፤ በሕይወት ያለ ሰውም ይህን ልብ ማለት ይገባዋል።
ከሳቅ ትካዜ ይሻላል፤ የፊት ሐዘን ለልብ መልካም ነውና።
የጥበበኞች ልብ በሐዘን ቤት ነው፤ የሞኞች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው።
የሞኞችን መዝሙር ከመስማት ይልቅ የጥበበኛን ወቀሳ መስማት ይሻላል።
የሞኝ ሳቅ ከድስት ሥር እንደሚንጣጣ የእሾህ ማገዶ ነው፤ ይህም ቢሆን ከንቱ ነው።
ግፍ ጥበበኛውን ሊያሳብደው ይችላል፤ ጉቦም ልብን ያበላሻል።
የአንድ ነገር ፍጻሜ ከጅማሬው ይሻላል። ትዕቢተኛ ከመሆን ይልቅ ታጋሽ መሆን ይሻላል።
የሞኞች ቁጣ በጉያቸው ውስጥ ስለሆነ ለቁጣ አትቸኩል።
“የቀድሞው ዘመን ከአሁኑ ዘመን ለምን ተሻለ?” አትበል፤ እንዲህ ብሎ መጠየቅ ጥበብ አይደለምና።
ጥበብ ከውርስ ጋር መልካም ነገር ናት፤ የቀን ብርሃን ለሚያዩ ሰዎችም ጠቃሚ ነች።
ገንዘብ ጥበቃ እንደሚያስገኝ ሁሉ ጥበብም ጥበቃ ታስገኛለችና፤ የእውቀት ብልጫ ግን፣ ጥበብ የባለቤቷን ሕይወት ጠብቃ ማቆየት መቻሏ ነው።
እውነተኛው አምላክ ያከናወነውን ሥራ ልብ በል፤ እሱ ያጣመመውን ማን ሊያቃና ይችላል?
በጥሩ ቀን አንተም ይህን ጥሩነት መልሰህ አንጸባርቅ፤ በአስቸጋሪ ቀን ግን ይሄኛውንም ሆነ ያኛውን ያደረገው አምላክ እንደሆነ አስተውል፤ ይህም የሆነው ሰዎች ወደፊት የሚደርስባቸውን ማንኛውንም ነገር በተመለከተ እርግጠኞች መሆን እንዳይችሉ ነው።
ከንቱ በሆነው የሕይወት ዘመኔ ሁሉንም ነገር አይቻለሁ፤ ጻድቁ ሰው በጽድቁ ሲጠፋ፣ ክፉው ሰው ደግሞ ክፉ ቢሆንም ረጅም ዘመን ሲኖር ተመልክቻለሁ።
ከልክ በላይ ጻድቅ አትሁን፤ እጅግም ጥበበኛ መስለህ ለመታየት አትሞክር። በራስህ ላይ ለምን ጥፋት ታመጣለህ?
እጅግ ክፉ አትሁን፤ ሞኝም አትሁን። ያለጊዜህ ለምን በሞት ትቀጫለህ?
አንደኛውን ማስጠንቀቂያ ሳትተው ሌላኛውንም አጥብቀህ መያዝህ የተሻለ ነው፤ አምላክን የሚፈራ ሰው ሁለቱንም ይሰማልና።
ጥበብ ጥበበኛውን ሰው፣ በአንድ ከተማ ካሉ አሥር ብርቱ ሰዎች ይበልጥ ኃያል ታደርገዋለች።
ሁልጊዜ ጥሩ ነገር የሚያደርግና ፈጽሞ ኃጢአት የማይሠራ ጻድቅ ሰው በምድር ላይ የለምና።
በተጨማሪም ሰዎች የሚናገሩትን ነገር ሁሉ ትኩረት ሰጥተህ አትከታተል፤ አለዚያ አገልጋይህ ስለ አንተ መጥፎ ነገር ሲናገር ልትሰማ ትችላለህ፤
አንተ ራስህ ስለ ሌሎች ብዙ ጊዜ መጥፎ ነገር እንደተናገርክ ልብህ በሚገባ ያውቃልና።
ይህን ሁሉ በጥበብ ፈተንኩ፤ እኔም “ጥበበኛ እሆናለሁ” አልኩ። ይህ ግን ከአቅሜ በላይ ነበር።
የተከናወነው ነገር ሁሉ ሊደረስበት የማይቻል ከመሆኑም ሌላ እጅግ ጥልቅ ነው። ማንስ ሊረዳው ይችላል?
እኔም ጥበብንና የነገሮችን መንስኤ ለመረዳት፣ ለመመርመርና ለማጥናት እንዲሁም የሞኝነትን ክፋትና የእብደትን ቂልነት ለመገንዘብ ልቤን አዘነበልኩ።
ከዚያም የሚከተለውን ነገር ተገነዘብኩ፦ እንደ አዳኝ ወጥመድ የሆነች ደግሞም እንደ መረብ ያለ ልብ፣ እንደ እስር ቤት ሰንሰለትም ያሉ እጆች ያሏት ሴት ከሞት እጅግ የመረረች ናት። እውነተኛውን አምላክ የሚያስደስት ሰው ከእሷ ያመልጣል፤ ኃጢአተኛ ግን በእሷ ይያዛል።
ሰብሳቢው እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ መርምሬ ያገኘሁት ነገር ይህ ነው። አንድ መደምደሚያ ላይ ለመድረስ እያንዳንዱን ነገር በሚገባ አጠናሁ፤
ሆኖም ስፈልገው የነበረውን ነገር ላገኘው አልቻልኩም። ከሺህ መካከል አንድ ወንድ አገኘሁ፤ ከእነዚህ ሁሉ መካከል ግን አንዲትም ሴት አላገኘሁም።
ይህን አንድ ነገር ብቻ አገኘሁ፦ እውነተኛው አምላክ የሰውን ልጆች ቅን አድርጎ ሠራቸው፤ እነሱ ግን ሌላ ብዙ ዕቅድ አወጡ።”
ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ከሰማይ በታች ለሚከናወን ነገር ሁሉ ጊዜ አለው፦
ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ለመትከል ጊዜ አለው፤ የተተከለውን ለመንቀልም ጊዜ አለው፤
ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለመፈወስም ጊዜ አለው፤ለማፍረስ ጊዜ አለው፤ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤
ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ለዋይታ ጊዜ አለው፤ ለጭፈራም ጊዜ አለው፤
ድንጋይ ለመጣል ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤ለማቀፍ ጊዜ አለው፤ ከማቀፍ ለመቆጠብም ጊዜ አለው፤
ለመፈለግ ጊዜ አለው፤ ጠፍቷል ብሎ ለመተውም ጊዜ አለው፤ለማስቀመጥ ጊዜ አለው፤ አውጥቶ ለመጣልም ጊዜ አለው፤
ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ዝም ለማለት ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፤
ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው።
ሠራተኛ ከልፋቱ ሁሉ የሚያገኘው ጥቅም ምንድን ነው?
አምላክ የሰው ልጆች እንዲጠመዱበት የሰጣቸውን ሥራ ተመለከትኩ።
አምላክ ሁሉንም ነገር በወቅቱ ውብ አድርጎ ሠርቶታል። ደግሞም ዘላለማዊነትን በልባቸው ውስጥ አኑሯል፤ ይሁንና የሰው ልጆች እውነተኛው አምላክ ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ መጨረሻው ድረስ ያከናወነውን ሥራ በምንም ዓይነት መርምረው ሊደርሱበት አይችሉም።
ለሰው በሕይወት ዘመኑ ከመደሰትና መልካም ከማድረግ የተሻለ ነገር የለም ብዬ ደመደምኩ፤
ደግሞም ለሰው ከመብላትና ከመጠጣት እንዲሁም ተግቶ በሚሠራው ሥራ ሁሉ ደስታ ከማግኘት የተሻለ ነገር የለም። ይህ የአምላክ ስጦታ ነው።
እውነተኛው አምላክ የሚሠራው ነገር ሁሉ ለዘላለም ጸንቶ እንደሚኖር ተረድቻለሁ። በእሱ ላይ የሚጨመር ምንም ነገር የለም፤ ከእሱም ላይ የሚቀነስ ምንም ነገር የለም። እውነተኛው አምላክ በዚህ መንገድ የሠራው ሰዎች ይፈሩት ዘንድ ነው።
አሁን የሚሆነው ነገር ሁሉ ከዚህ በፊት የሆነ ነው፤ ወደፊት የሚመጣው ነገር ከዚህ በፊት የነበረ ነው፤ ሆኖም እውነተኛው አምላክ፣ ሲያሳድዱት የነበረውን አጥብቆ ይሻዋል።
ደግሞም ከፀሐይ በታች ይህን አየሁ፦ በፍትሕ ቦታ ክፋት፣ በጽድቅም ቦታ ክፋት ነበር።
እኔም በልቤ እንዲህ አልኩ፦ “እውነተኛው አምላክ በጻድቁም ሆነ በኃጢአተኛው ላይ ይፈርዳል፤ ማንኛውም ድርጊትና ማንኛውም ተግባር ጊዜ አለውና።”
እኔም በልቤ፣ እውነተኛው አምላክ የሰው ልጆችን ይፈትናቸዋል፤ እንደ እንስሳት መሆናቸውንም ያሳያቸዋል አልኩ፤
የሰው ልጆች ፍጻሜና የእንስሳት ፍጻሜ ተመሳሳይ ነውና፤ የሁሉም ፍጻሜ አንድ ነው። አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፤ የሁሉም መንፈስ አንድ ዓይነት ነው። በመሆኑም ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም፤ ሁሉም ከንቱ ነውና።
ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሄዳሉ። ሁሉም የተገኙት ከአፈር ነው፤ ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳሉ።
የሰው ልጆች መንፈስ ወደ ላይ ይወጣ እንደሆነ፣ የእንስሳት መንፈስ ደግሞ ወደ ታች ወደ ምድር ይወርድ እንደሆነ በእርግጠኝነት የሚያውቅ ማን ነው?
ሰው በሥራው ደስ ከመሰኘት የተሻለ ነገር እንደሌለው አስተዋልኩ፤ ምክንያቱም ይህ ወሮታው ነው፤ እሱ ካለፈ በኋላ የሚከናወነውን ነገር ተመልሶ እንዲያይ ሊያደርገው የሚችል ማን ነው?
ስለዚህ ይህን ሁሉ በጥሞና ተመልክቼ ጻድቃንም ሆኑ ጥበበኞች እንዲሁም የሚያከናውኗቸው ሥራዎች በእውነተኛው አምላክ እጅ ናቸው ብዬ ደመደምኩ። ሰዎች ከእነሱ በፊት በነበረው ዘመን የታየውን ፍቅርና ጥላቻ አያውቁም።
ጻድቁና ክፉው ሰው፣ ጥሩው ሰውም ሆነ ንጹሕ የሆነውና ንጹሕ ያልሆነው ሰው፣ መሥዋዕት የሚያቀርቡትም ሆኑ የማያቀርቡት ፍጻሜያቸው ተመሳሳይ ነው። ጥሩው ሰው ከኃጢአተኛው ጋር አንድ ነው፤ የሚምለውም ሰው፣ ላለመማል ከሚጠነቀቀው ሰው ጋር አንድ ነው።
ከፀሐይ በታች የሚፈጸመው አስጨናቂ ነገር ይህ ነው፦ የሁሉም ፍጻሜ አንድ ስለሆነ የሰዎችም ልብ በክፋት የተሞላ ነው፤ በሕይወታቸው ዘመን በልባቸው ውስጥ እብደት አለ፤ ከዚያም ይሞታሉ!
በሕያዋን መካከል ያለ ማንኛውም ሰው ተስፋ አለው፤ ምክንያቱም በሕይወት ያለ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላል።
ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን ምንም አያውቁም፤ ከእንግዲህም የሚያገኙት ብድራት የለም፤ ምክንያቱም የሚታወሱበት ነገር ሁሉ ተረስቷል።
በተጨማሪም ፍቅራቸው፣ ጥላቻቸውና ቅናታቸው ጠፍቷል፤ ከዚህም በኋላ ከፀሐይ በታች በሚሆነው ነገር ሁሉ ፈጽሞ ድርሻ አይኖራቸውም።
ሂድ፣ ምግብህን በደስታ ብላ፤ ልብህም ደስ ብሎት ወይንህን ጠጣ፤ እውነተኛው አምላክ በሥራህ ደስ ተሰኝቷልና።
ልብስህ ምንጊዜም ነጭ ይሁን፤ ራስህንም ዘይት መቀባት አትዘንጋ።
አምላክ ከፀሐይ በታች በሰጠህ ከንቱ በሆነው የሕይወት ዘመንህ ሁሉ፣ ከንቱ በሆነውም ዕድሜህ ሁሉ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር ተደስተህ ኑር፤ በሕይወትህ እንዲሁም ከፀሐይ በታች በምትደክምበትና በትጋት በምታከናውነው ሥራ ዕጣ ፋንታህ ይህ ነውና።
እጅህ የሚያገኘውን ሥራ ሁሉ በሙሉ ኃይልህ አከናውን፤ አንተ በምትሄድበት በመቃብር ሥራም ሆነ ዕቅድ፣ እውቀትም ሆነ ጥበብ የለምና።
እኔም ከፀሐይ በታች ሌላ ነገር ተመለከትኩ፤ ፈጣኖች በውድድር ሁልጊዜ አያሸንፉም፤ ኃያላን በውጊያ ሁልጊዜ ድል አይቀናቸውም፤ ጥበበኞች ሁልጊዜ ምግብ አያገኙም፤ አስተዋዮች ሁልጊዜ ሀብት አያገኙም፤ እውቀት ያላቸው ሰዎችም ሁልጊዜ ስኬታማ አይሆኑም፤ ምክንያቱም ሁሉም መጥፎ ጊዜና ያልተጠበቁ ክስተቶች ያጋጥሟቸዋል።
ሰው የራሱን ጊዜ አያውቅምና። ዓሣዎች በአደገኛ መረብ እንደሚጠመዱና ወፎች በወጥመድ እንደሚያዙ፣ የሰው ልጆችም ድንገት በሚያጋጥማቸው ክፉ ጊዜ ይጠመዳሉ።
ደግሞም ከፀሐይ በታች ስላለች ጥበብ ይህን አስተዋልኩ፤ በእሷም እጅግ ተገረምኩ፦
ጥቂት ሰዎች የሚኖሩባት አንዲት ትንሽ ከተማ ነበረች፤ አንድ ኃያል ንጉሥም መጥቶ ከበባት፤ በዙሪያዋም ትልቅ ቅጥር ገነባ።
በከተማዋ ውስጥ ጥበበኛ የሆነ አንድ ድሃ ሰው ነበር፤ እሱም በጥበቡ ከተማዋን አዳናት። ሆኖም ይህን ድሃ ማንም ሰው አላስታወሰውም።
እኔም ለራሴ እንዲህ አልኩ፦ ‘ጥበብ ከኃይል ትበልጣለች፤ ይሁንና የድሃው ጥበብ ተናቀ፤ የተናገረውም ነገር ሰሚ አላገኘም።’
ሞኞችን የሚገዛ ሰው ከሚያሰማው ጩኸት ይልቅ ጥበበኞች በዝግታ የሚናገሩትን ቃል መስማት ይሻላል።
ከጦር መሣሪያ ይልቅ ጥበብ ትሻላለች፤ አንድ ኃጢአተኛ ግን ብዙ መልካም ነገርን ሊያጠፋ ይችላል።