text stringlengths 4 267 |
|---|
እኔም በልቤ “እስቲ ደስታን ልፈትንና ምን መልካም ነገር እንደሚገኝ ልይ” አልኩ። ይሁንና ይህም ከንቱ ነበር። |
ሳቅ “እብደት ነው!” ደስታም “ምን ይጠቅማል?” አልኩ። |
በገዛ ጥበቤ እየተመራሁና ራሴን በወይን ጠጅ እያስደሰትኩ በጥልቀት መረመርኩ፤ ሰዎች አጭር በሆነው የሕይወት ዘመናቸው ከሰማይ በታች ሊያደርጉት የሚችሉት ከሁሉ የተሻለ ነገር ምን እንደሆነ ለማወቅ በሞኝነት እንኳ ሳይቀር ተመላለስኩ። |
ታላላቅ ሥራዎችን አከናወንኩ። ለራሴ ቤቶችን ሠራሁ፤ ወይንም ተከልኩ። |
ለራሴ የአትክልት ስፍራዎችንና መናፈሻዎችን አዘጋጀሁ፤ በእነዚህም ቦታዎች ሁሉንም ዓይነት የፍራፍሬ ዛፎች ተከልኩ። |
በእርሻው መሬት ላይ እያደጉ ያሉትን ዛፎች ለማጠጣት የውኃ ማጠራቀሚያዎችን ሠራሁ። |
ወንድና ሴት አገልጋዮች አስመጣሁ፤ በቤቴ የተወለዱ አገልጋዮችም ነበሩኝ። በተጨማሪም ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይበልጥ ብዛት ያላቸው እንስሶች፣ ከብቶችና መንጎች ነበሩኝ። |
ለራሴም ብርና ወርቅ፣ የነገሥታትንና የአውራጃዎችን ውድ ሀብት አከማቸሁ። ወንድና ሴት ዘፋኞችን እንዲሁም የሰው ልጆች እጅግ የሚደሰቱባቸውን ብዙ ሴቶች ሰበሰብኩ። |
በመሆኑም ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ሰው ሆንኩ። ደግሞም ጥበቤ ከእኔ አልተለየችም። |
የተመኘሁትን ነገር ሁሉ ራሴን አልነፈግኩም። ልቤንም ደስ የሚያሰኘውን ነገር ሁሉ አልከለከልኩትም፤ ልቤ በትጋት በማከናውነው ሥራ ሁሉ ደስ ይሰኝ ነበርና፤ ብዙ ለደከምኩበት ሥራ ሁሉ ያገኘሁት ወሮታ ይህ ነበር። |
ሆኖም እጆቼ የሠሩትን ሥራ ሁሉና ዳር ለማድረስ የደከምኩበትን ሥራ ሁሉ መለስ ብዬ ሳስብ፣ ሁሉ ነገር ከንቱ፣ ነፋስንም እንደማሳደድ መሆኑን አስተዋልኩ፤ ከፀሐይም በታች እውነተኛ ፋይዳ ያለው አንዳች ነገር አልነበረም። |
ከዚያም ትኩረቴን ወደ ጥበብ፣ እብደትና ሞኝነት አዞርኩ። (ከንጉሥ በኋላ የሚመጣው ሰው ምን ሊያደርግ ይችላል? ሊያደርግ የሚችለው ቀደም ሲል የተደረገውን ነገር ብቻ ነው።) |
እኔም ብርሃን ከጨለማ የተሻለ ጥቅም እንዳለው ሁሉ ጥበብም ከሞኝነት የተሻለ ጥቅም እንዳለው ተገነዘብኩ። |
የጥበበኛ ሰው ዓይኖች ያሉት በራሱ ላይ ነው፤ ሞኝ ሰው ግን በጨለማ ውስጥ ይሄዳል። ደግሞም የሁለቱም ፍጻሜ አንድ እንደሆነ ተገነዘብኩ። |
እኔም በልቤ “በሞኙ ላይ የሚደርሰው በእኔም ላይ ይደርሳል” አልኩ። ታዲያ እጅግ ጥበበኛ በመሆኔ ምን አተርፋለሁ? በልቤም “ይህም ከንቱ ነው” አልኩ። |
ጥበበኛውም ሆነ ሞኙ ለዘለቄታው አይታወሱምና። ሁሉም በሚመጡት ዘመናት ይረሳሉ። ለመሆኑ ጥበበኛው የሚሞተው እንዴት ነው? ልክ እንደ ሞኙ ሰው ይሞታል። |
እኔም ከፀሐይ በታች የሚሠራው ሥራ ሁሉ አስጨናቂ ሆኖ ስለታየኝ ሕይወትን ጠላሁ፤ ሁሉም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደማሳደድ ነውና። |
ከኋላዬ ለሚመጣው ሰው ትቼው ስለምሄድ ከፀሐይ በታች እጅግ የደከምኩበትን ሥራ ሁሉ ጠላሁ። |
ጥበበኛ ወይም ሞኝ እንደሚሆን የሚያውቅ ማን ነው? ሆኖም ከፀሐይ በታች በድካሜና በጥበቤ ያፈራሁትን ነገር ሁሉ ይወርሰዋል። ይህም ቢሆን ከንቱ ነው። |
በመሆኑም ከፀሐይ በታች በለፋሁበት አድካሚ ሥራ ሁሉ ልቤ ተስፋ መቁረጥ ጀመረ። |
ሰው በጥበብ፣ በእውቀትና በብልሃት እየተመራ ሥራውን በትጋት ሊያከናውን ይችላል፤ ይሁንና ድርሻውን ምንም ላልደከመበት ሰው ያስረክባል። ይህም ከንቱና እጅግ አሳዛኝ ነው። |
ሰው ከፀሐይ በታች ከደከመበት ሁሉና ተግቶ እንዲሠራ ከሚገፋፋው ብርቱ ፍላጎት የሚያገኘው ትርፍ ምንድን ነው? |
በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሥራው የሚያስገኝለት ነገር ቢኖር ሥቃይና ብስጭት ነው፤ በሌሊትም እንኳ ልቡ አያርፍም። ይህም ከንቱ ነው። |
ሰው ከመብላትና ከመጠጣት እንዲሁም ተግቶ በመሥራት እርካታ ከማግኘት የሚሻለው ነገር የለም። ይህም ቢሆን ከእውነተኛው አምላክ እጅ የተገኘ መሆኑን ተገንዝቤአለሁ፤ |
ደግሞስ ከእኔ የተሻለ የሚበላና የሚጠጣ ማን ነው? |
አምላክ እሱን ለሚያስደስት ሰው ጥበብ፣ እውቀትና ደስታ ይሰጣል፤ ኃጢአተኛ ለሆነው ግን እውነተኛውን አምላክ ለሚያስደስት ሰው ይሰጥ ዘንድ የመሰብሰብና የማከማቸት ሥራ ሰጥቶታል። ይህም ከንቱና ነፋስን እንደማሳደድ ነው። |
የሞቱ ዝንቦች በጥሩ ቀማሚ የተዘጋጀውን ሽቶ እንዲበላሽና እንዲገማ እንደሚያደርጉት ሁሉ ትንሽ ሞኝነትም ጥበብንና ክብርን ዋጋ ያሳጣል። |
የጥበበኛ ሰው ልብ በትክክለኛ መንገድ ይመራዋል፤ የሞኝ ልብ ግን በተሳሳተ መንገድ ይመራዋል። |
ሞኝ ሰው በየትኛውም መንገድ ቢመላለስ ማስተዋል ይጎድለዋል፤ ሞኝ መሆኑንም ሰው ሁሉ እንዲያውቅ ያደርጋል። |
የገዢ ቁጣ በአንተ ላይ ቢነድ ስፍራህን አትልቀቅ፤ የረጋ መንፈስ ታላቅ ኃጢአትን ጸጥ ያደርጋልና። |
ከፀሐይ በታች ያየሁት አንድ የሚያስጨንቅ ነገር አለ፤ ይህም በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች እንደሚሠሩት ያለ ስህተት ነው፦ |
ሞኞች በከፍተኛ የሥልጣን ቦታዎች ላይ ሲቀመጡ የናጠጡ ሀብታሞች ግን በዝቅተኛ ቦታዎች ላይ ይገኛሉ። |
አገልጋዮች በፈረስ ተቀምጠው ሲጓዙ፣ መኳንንት ግን እንደ አገልጋዮች በእግራቸው ሲሄዱ አይቻለሁ። |
ጉድጓድ የሚቆፍር ራሱ ሊገባበት ይችላል፤ ግንብን የሚያፈርስም በእባብ ሊነደፍ ይችላል። |
ድንጋይ የሚፈነቅል ሰው በፈነቀለው ድንጋይ ሊጎዳ ይችላል፤ ግንድንም የሚፈልጥ አደጋ ሊያደርስበት ይችላል። |
ከብረት የተሠራ መሣሪያ ቢደንዝ፣ ሰውም ባይስለው ብዙ ጉልበት መጠቀም ያስፈልገዋል። ጥበብ ግን ስኬታማ ለመሆን ይረዳል። |
እባብ በድግምት ከመፍዘዙ በፊት ቢነድፍ፣ በድግምት የተካነው ሰው ምንም ጥቅም አያገኝም። |
ጥበበኛ ሰው ከአፉ የሚወጡት ቃላት ሞገስ ያስገኙለታል፤ የሞኝ ሰው ከንፈር ግን ለጥፋት ይዳርገዋል። |
ከአፉ የሚወጡት የመጀመሪያ ቃላት ሞኝነት ይንጸባረቅባቸዋል፤ የንግግሩ ማሳረጊያም የከፋ እብደት ነው። |
ይሁንና ሞኙ ማውራቱን ይቀጥላል። ሰው ወደፊት የሚሆነውን ነገር አያውቅም፤ ከእሱ በኋላ የሚመጣውን ነገር ማን ሊነግረው ይችላል? |
ሞኝ ሰው የሚሠራው አድካሚ ሥራ እንዲዝል ያደርገዋል፤ ወደ ከተማ የሚወስደውን መንገድ ማግኘት እንኳ አይችልምና። |
አንዲት አገር ንጉሥዋ ልጅ ቢሆን፣ መኳንንቷ ደግሞ በጠዋት ግብዣ ላይ የሚገኙ ቢሆኑ ምንኛ አሳዛኝ ነው! |
ከትልቅ ቤተሰብ የተወለደ ንጉሥ ያላት እንዲሁም ለስካር ሳይሆን ብርታት ለማግኘት በተገቢው ጊዜ የሚመገቡ መኳንንት ያሏት አገር ምንኛ ደስተኛ ናት! |
ስንፍና ሲበዛ ጣሪያ ይዘብጣል፤ እጆችም ካልሠሩ ቤት ያፈሳል። |
ምግብ ለሳቅ ይዘጋጃል፤ የወይን ጠጅም ሕይወትን አስደሳች ያደርጋል፤ ይሁን እንጂ ገንዘብ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ያሟላል። |
በሐሳብህ እንኳ ንጉሡን አትርገም፤ በመኝታ ቤትህም ሆነህ ባለጸጋውን አትርገም፤ ቃሉን ወፍ ልትወስደው አሊያም ክንፍ ያላት ፍጥረት የተወራውን ደግማ ልትናገር ትችላለችና። |
ወደ እውነተኛው አምላክ ቤት በምትሄድበት ጊዜ ሁሉ አካሄድህን ጠብቅ፤ ሞኞች እንደሚያደርጉት መሥዋዕት ለማቅረብ ከመሄድ ይልቅ ለመስማት መሄድ ይሻላል፤ እነሱ እየሠሩ ያሉት ነገር መጥፎ መሆኑን አያውቁምና። |
በአፍህ ለመናገር አትጣደፍ፤ ልብህም በእውነተኛው አምላክ ፊት ለመናገር አይቸኩል፤ እውነተኛው አምላክ በሰማያት፣ አንተ ግን በምድር ላይ ነህና። ስለዚህ የምትናገራቸው ቃላት ጥቂት ሊሆኑ ይገባል። |
ሐሳብ ሲበዛ ለቅዠት ይዳርጋል፤ የቃላት ብዛትም ሞኝን ሰው ለፍላፊ ያደርገዋል። |
ለአምላክ ስእለት በምትሳልበት ጊዜ ሁሉ ስእለትህን ለመፈጸም አትዘግይ፤ እሱ በሞኞች አይደሰትምና። ስእለትህን ፈጽም። |
ስእለት ተስለህ ሳትፈጽም ከምትቀር ባትሳል ይሻላል። |
አፍህ ወደ ኃጢአት እንዲመራህ አትፍቀድ፤ በመልአክም ፊት “ተሳስቼ ነው” አትበል። እውነተኛው አምላክ በተናገርከው ነገር ተቆጥቶ የእጅህን ሥራ ለምን ያጥፋ? |
ሐሳብ ሲበዛ ቅዠት እንደሚያስከትል፣ የቃላት ብዛት ደግሞ ከንቱነትን ያስከትላልና። አንተ ግን እውነተኛውን አምላክ ፍራ። |
በምትኖርበት ግዛት ውስጥ በድሃ ላይ ግፍ ሲፈጸም፣ ፍትሕ ሲጓደልና ጽድቅ ወደ ጎን ገሸሽ ሲደረግ ብታይ በዚህ ጉዳይ አትገረም። ይህን ባለሥልጣን፣ ከእሱ ከፍ ያለ ቦታ ያለው ይመለከተዋልና፤ ከእነሱም በላይ የሆኑ ሌሎች አሉ። |
ከምድሩ የሚገኘውን ትርፍ ሁሉም ይከፋፈሉታል፤ ንጉሡ እንኳ የሚያስፈልገውን ነገር የሚያገኘው ከእርሻው ነው። |
ብርን የሚወድ ብርን አይጠግብም፤ ሀብትንም የሚወድ በሚያገኘው ገቢ አይረካም። ይህም ቢሆን ከንቱ ነው። |
መልካም ነገሮች ሲበዙ፣ በላተኛውም ይበዛል። ታዲያ በዓይኑ ብቻ ከማየት በቀር ይህ ለባለቤቱ ምን ይጠቅመዋል? |
የሚበላው ጥቂትም ሆነ ብዙ፣ የሠራተኛ እንቅልፍ ጣፋጭ ነው፤ ባለጸጋ ሰው ያለው ብዙ ሀብት ግን እንቅልፍ ይነሳዋል። |
ከፀሐይ በታች ያየሁት እጅግ አሳዛኝ የሆነ ነገር አለ፦ ይህም ባለቤቱ በገዛ ራሱ ላይ ጉዳት ለማምጣት ያከማቸው ሀብት ነው። |
ይህ ሰው አደገኛ ነገር ውስጥ በመግባቱ ሀብቱን አጥቷል፤ ልጅ በሚወልድበት ጊዜም ለልጁ የሚያወርሰው ምንም ነገር አይኖረውም። |
ሰው ከእናቱ ማህፀን ራቁቱን እንደወጣ ሁሉ፣ ልክ እንደዚያው ተመልሶ ይሄዳል። ደግሞም ከደከመበት ነገር ሁሉ ሊወስደው የሚችል አንዳች ነገር የለም። |
ይህም ደግሞ እጅግ የሚያሳዝን ነገር ነው፦ ሰው በዚያው በመጣበት መንገድ ተመልሶ ይሄዳል፤ ለነፋስ የሚደክም ሰው የሚያገኘው ትርፍ ምንድን ነው? |
ደግሞም በየቀኑ ጨለማ ውስጥ በከፍተኛ ብስጭት፣ በሕመምና በንዴት ይበላል። |
እኔ ያየሁት መልካምና ተገቢ የሆነ ነገር፣ ሰው እውነተኛው አምላክ በሰጠው አጭር የሕይወት ዘመን ሁሉ መብላቱና መጠጣቱ እንዲሁም ከፀሐይ በታች በደከመበትና በትጋት ባከናወነው ሥራ ሁሉ ደስታ ማግኘቱ ነው፤ ይህ ብድራቱ ነውና። |
ደግሞም እውነተኛው አምላክ ለሰው ሀብትና ቁሳዊ ንብረት ብሎም በእነዚህ ነገሮች የመደሰት ችሎታ ሲሰጠው ብድራቱን ተቀብሎ በትጋት በሚያከናውነው ሥራ መደሰት ይገባዋል። ይህ የአምላክ ስጦታ ነው። |
እውነተኛው አምላክ ልቡን ደስ በሚያሰኙ ነገሮች እንዲጠመድ ስለሚያደርገው የሚያልፈውን የሕይወት ዘመኑን ፈጽሞ ልብ አይለውም። |
ከፀሐይ በታች የሚፈጸመውን ግፍ ሁሉ በድጋሚ ተመለከትኩ። ግፍ የተፈጸመባቸውን ሰዎች እንባ ተመለከትኩ፤ የሚያጽናናቸውም ሰው አልነበረም። ግፍ የሚፈጽሙባቸውም ሰዎች ኃይል ነበራቸው፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም። |
እኔም ‘ዛሬ በሕይወት ካሉት ሕያዋን ይልቅ በቀድሞ ዘመን የሞቱ ሙታን ይሻላሉ’ አልኩ። |
ደግሞም ከሁለቱ ይልቅ ገና ያልተወለደው፣ ከፀሐይ በታች የሚፈጸሙትንም አስጨናቂ ድርጊቶች ያላየው ይሻላል። |
እኔም በሰዎች መካከል ያለው ፉክክር፣ ከፍተኛ ጥረት እንዲያደርጉና የተዋጣለት ሥራ እንዲያከናውኑ እንደሚያነሳሳቸው ተመለከትኩ፤ ይህም ከንቱና ነፋስን እንደማሳደድ ነው። |
ሞኝ ሰው ሥጋው እየመነመነ ሲሄድ፣ እጁን አጣጥፎ ይቀመጣል። |
ብዙ በመልፋትና ነፋስን በማሳደድ ከሚገኝ ሁለት እፍኝ ይልቅ ጥቂት እረፍት በማድረግ የሚገኝ አንድ እፍኝ ይሻላል። |
እኔም ከፀሐይ በታች ያለውን ሌላ ከንቱ ነገር እንደገና ተመለከትኩ፦ |
ብቸኛ የሆነና ጓደኛ የሌለው ሰው አለ፤ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ይሁንና የሚሠራው ሥራ ማብቂያ የለውም። ዓይኖቹ ሀብትን አይጠግቡም። ሆኖም ‘እንዲህ በትጋት የምሠራውና ራሴን መልካም ነገር የምነፍገው ለማን ብዬ ነው?’ ብሎ ራሱን ይጠይቃል? ይህም ቢሆን ከንቱና አሰልቺ ሥራ ነው። |
አንድ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል፤ ምክንያቱም ሁለት ሆነው የሚያከናውኑት ሥራ ጥሩ ውጤት ያስገኝላቸዋል። |
አንዱ ቢወድቅ ሁለተኛው ባልንጀራውን ደግፎ ሊያነሳው ይችላልና። ይሁንና ደግፎ የሚያነሳው ሰው በሌለበት አንዱ ቢወድቅ እንዴት ይሆናል? |
በተጨማሪም ሁለት ሰዎች አብረው ቢተኙ ይሞቃቸዋል፤ ሆኖም አንድ ሰው ብቻውን ሆኖ እንዴት ሊሞቀው ይችላል? |
ደግሞም አንድ ሰው ብቻውን ያለን ሰው ሊያሸንፈው ይችል ይሆናል፤ ሁለት ከሆኑ ግን ሊቋቋሙት ይችላሉ። በሦስት የተገመደ ገመድም ቶሎ አይበጠስም። |
የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ እንዳያደርግ ማስተዋል ከጎደለው በዕድሜ የገፋ ሞኝ ንጉሥ ይልቅ ድሃ የሆነ ጥበበኛ ልጅ ይሻላል። |
በእሱ ግዛት ውስጥ ድሃ ሆኖ የተወለደ ቢሆንም ከእስር ቤት ወጥቶ ንጉሥ ይሆናል። |
እኔም ከፀሐይ በታች የሚመላለሱት ሕያዋን ሁሉ እንዲሁም በንጉሡ ቦታ የሚተካው ልጅ ምን እንደሚገጥማቸው አጤንኩ። |
ስፍር ቁጥር የሌላቸው ደጋፊዎች ቢኖሩትም በኋላ የሚመጡት ሰዎች በእሱ አይደሰቱም። ይህም ቢሆን ከንቱና ነፋስን እንደማሳደድ ነው። |
እንግዲያው አስጨናቂ የሆኑት ዘመናት ከመምጣታቸው እንዲሁም “ደስ አያሰኙኝም” የምትላቸው ዓመታት ከመድረሳቸው በፊት በወጣትነትህ ጊዜ ታላቁን ፈጣሪህን አስብ፤ |
ፀሐይ፣ ብርሃን፣ ጨረቃና ከዋክብት ከመጨለማቸው በፊት እንዲሁም ዶፍ ከጣለ በኋላ ደመናት ተመልሰው ከመምጣታቸው በፊት ፈጣሪህን አስብ፤ |
በዚያን ጊዜ ቤት ጠባቂዎች ይንቀጠቀጣሉ፤ ጠንካራ የነበሩ ሰዎች ይጎብጣሉ፤ የሚፈጩ ሴቶች ጥቂት በመሆናቸው ሥራቸውን ያቆማሉ፤ በመስኮት የሚያዩ ወይዛዝርትም ይጨልምባቸዋል፤ |
ወደ መንገድ የሚያወጡ በሮች ይዘጋሉ፤ የወፍጮ ድምፅ ይቀንሳል፤ ሰውም የወፍ ድምፅ ይቀሰቅሰዋል፤ ሴቶች ልጆችም ሁሉ ዝግ ባለ ድምፅ ይዘምራሉ። |
በተጨማሪም ሰው ከፍታ ያስፈራዋል፤ በመንገድ ሲሄድም ይሸበራል። የአልሞንድ ዛፍ ያብባል፤ ፌንጣም እየተጎተተ ይሄዳል፤ የምግብ ፍላጎት ይጠፋል፤ ምክንያቱም ሰው ለረጅም ጊዜ ወደሚኖርበት ቤት ይሄዳል፤ አልቃሾችም በጎዳና ይዞራሉ፤ |
የብር ገመድ ሳይበጠስ፣ የወርቅ ሳህን ሳይሰበር፣ እንስራ በምንጭ አጠገብ ሳይከሰከስ፣ ከጉድጓድ ውኃ ለማውጣት የሚያገለግለው መንኮራኩር ሳይሰበር ፈጣሪህን አስብ። |
አፈር ቀድሞ ወደነበረበት መሬት ይመለሳል፤ መንፈስም ወደ ሰጪው፣ ወደ እውነተኛው አምላክ ይመለሳል። |
ሰብሳቢው “የከንቱ ከንቱ ነው! ሁሉም ነገር ከንቱ ነው!” ይላል። |
ሰብሳቢው ጥበበኛ ከመሆኑም በተጨማሪ ለሕዝቡ የሚያውቀውን ነገር ሁልጊዜ ያስተምር ነበር፤ ብዙ ምሳሌዎችንም ማጠናቀር ይችል ዘንድ አሰላሰለ እንዲሁም ሰፊ ምርምር አደረገ። |
ሰብሳቢው ደስ የሚያሰኙ ቃላትን ለማግኘትና የእውነትን ቃል በትክክል ለመመዝገብ ጥረት አደረገ። |
የጥበበኞች ቃላት እንደ በሬ መውጊያ ናቸው፤ የሰበሰቧቸው አባባሎችም በሚገባ እንደተቸነከሩ ምስማሮች ናቸው፤ እነዚህ ቃላት ከአንድ እረኛ የተሰጡ ናቸው። |
ልጄ ሆይ፣ ከዚህም ሌላ ይህን ማስጠንቀቂያ ልብ በል፦ ብዙ መጻሕፍት መጻፍ ማብቂያ የለውም፤ በእነሱ ዙሪያ ምርምር ማብዛትም ሰውነትን ያደክማል። |
ሁሉ ነገር ከተሰማ በኋላ መደምደሚያው ይህ ነው፦ እውነተኛውን አምላክ ፍራ፤ ትእዛዛቱንም ጠብቅ፤ ይህ የሰው አጠቃላይ ግዴታ ነውና። |
እውነተኛው አምላክ እያንዳንዱን የተሰወረ ነገር ጨምሮ ማንኛውንም ሥራ፣ ጥሩም ይሁን መጥፎ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና። |
ከፀሐይ በታች ያየሁት ሌላ አሳዛኝ ነገር አለ፤ ይህም በሰው ልጆች ላይ በተደጋጋሚ ሲከሰት ይታያል፦ |
እውነተኛው አምላክ፣ ሰው የሚፈልገውን ነገር ሁሉ እንዳያጣ ሀብትን፣ ቁሳዊ ንብረትንና ክብርን ይሰጠዋል፤ ሆኖም እውነተኛው አምላክ በእነዚህ ነገሮች እንዲደሰት አያስችለውም፤ ከዚህ ይልቅ እንግዳ ሰው ይደሰትባቸዋል። ይህም ከንቱና እጅግ አስከፊ ነገር ነው። |
አንድ ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፣ ብዙ ዓመት ቢኖርና ለእርጅና ቢበቃ፣ ወደ መቃብር ከመውረዱ በፊት ባሉት መልካም ነገሮች መደሰት ካልቻለ ከእሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል እላለሁ። |
ከማህፀን የወጣው በከንቱ ነውና፤ በጨለማም ሄዷል፤ ስሙም በጨለማ ተሸፍኗል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.