text stringlengths 4 267 |
|---|
ፀሐይን ባያይና ምንም ነገር ባያውቅም እንኳ ከዚያኛው ይልቅ ይሄኛው ይሻላል። |
ሰው ደስታ ካላገኘ ሁለት ጊዜ ሺህ ዓመት ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? ሁሉም የሚሄደው ወደ አንድ ቦታ አይደለም? |
የሰው ልጅ በትጋት የሚሠራው ሆዱን ለመሙላት ነው፤ የምግብ ፍላጎቱ ግን ፈጽሞ አይረካም። |
ታዲያ ጥበበኛው ከሞኙ ሰው የሚሻለው በምንድን ነው? ድሃስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዴት መኖር እንደሚችል ማወቁ የሚያስገኝለት ጥቅም ምንድን ነው? |
በምኞት ከመቅበዝበዝ ይልቅ ዓይን በሚያየው መደሰት ይሻላል። ይህም ቢሆን ከንቱና ነፋስን እንደማሳደድ ነው። |
አሁን ያለው ነገር ሁሉ አስቀድሞ ስያሜ የተሰጠው ነው፤ ደግሞም የሰው ምንነት የታወቀ ነው፤ ከእሱ ከሚበረታም ጋር ሊከራከር አይችልም። |
ቃል ሲበዛ ከንቱነት ይበዛል፤ ታዲያ ይህ ለሰው ምን ጥቅም ያስገኛል? |
ሰው በሕይወት ሳለ ይኸውም ከንቱ በሆነውና እንደ ጥላ በሚያልፈው አጭር የሕይወት ዘመኑ ሊያደርገው የሚችለው የተሻለ ነገር ምን እንደሆነ የሚያውቅ ማን ነው? እሱ ካለፈስ በኋላ ከፀሐይ በታች የሚሆነውን ነገር ማን ሊነግረው ይችላል? |
እንደ ጥበበኛው ሰው ያለ ማን ነው? የአንድን ችግር መፍትሔ የሚያውቅ ማን ነው? የሰው ጥበብ ፊቱ እንዲበራ እንዲሁም ኮስታራ ፊቱ እንዲፈታ ታደርጋለች። |
እኔም እንዲህ እላለሁ፦ “በአምላክ ፊት በገባኸው መሐላ የተነሳ የንጉሥን ትእዛዝ አክብር። |
ከንጉሡ ፊት ለመውጣት አትቸኩል። መጥፎ የሆነውን ነገር ሁሉ አትደግፍ፤ እሱ ደስ ያሰኘውን ሁሉ ማድረግ ይችላልና፤ |
ምክንያቱም የንጉሥ ቃል የማይሻር ነው፤ ‘ምን ማድረግህ ነው?’ ሊለው የሚችል ማን ነው?” |
ትእዛዛትን የሚጠብቅ ሰው ጉዳት አይደርስበትም፤ ጥበበኛ ልብም ትክክለኛውን ጊዜና አሠራር ያውቃል። |
የሰው ልጆች ብዙ መከራ ቢኖርባቸውም ማንኛውም ጉዳይ ትክክለኛ ጊዜና አሠራር አለው። |
ወደፊት የሚሆነውን ነገር የሚያውቅ ሰው ስለሌለ ይህ እንዴት እንደሚሆን ሊነግረው የሚችል ማን ነው? |
በመንፈስ ላይ ሥልጣን ያለው ወይም መንፈስን መግታት የሚችል ሰው እንደሌለ ሁሉ በሞት ቀን ላይም ሥልጣን ያለው የለም። በጦርነት ጊዜ ከግዳጅ የሚሰናበት እንደሌለ ሁሉ ክፋትም ክፋት የመሥራት ልማድ ያላቸውን ሰዎች እንዲያመልጡ ዕድል አይሰጣቸውም። |
ይህን ሁሉ የተገነዘብኩት ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ በልቤ ከመረመርኩ በኋላ ነው። በዚህ ሁሉ ወቅት ሰው ሰውን የገዛው ለጉዳቱ ነው። |
ደግሞም ወደ ቅዱሱ ስፍራ ይገቡና ይወጡ የነበሩት ክፉዎች ሲቀበሩ አይቻለሁ፤ ይሁንና ይህን ባደረጉበት ከተማ ወዲያው ተረሱ። ይህም ቢሆን ከንቱ ነው። |
በክፉ ሥራ ላይ በአፋጣኝ ፍርድ ስለማይሰጥ የሰው ልጆች ልብ ክፉ ነገር ለማድረግ ተደፋፈረ። |
ኃጢአተኛ መቶ ጊዜ መጥፎ ነገር እየሠራ ረጅም ዘመን ቢኖር እንኳ እውነተኛውን አምላክ የሚፈሩ ሰዎች አምላክን በመፍራታቸው የኋላ ኋላ መልካም እንደሚሆንላቸው ተረድቻለሁ። |
ክፉ ሰው ግን አምላክን ስለማይፈራ የኋላ ኋላ መልካም አይሆንለትም፤ እንደ ጥላ የሆነውን የሕይወት ዘመኑንም ማራዘም አይችልም። |
በምድር ላይ የሚፈጸም አንድ ከንቱ ነገር አለ፦ ክፉ እንደሠሩ ተደርገው የሚታዩ ጻድቃን አሉ፤ ጽድቅ እንደሠሩ ተደርገው የሚታዩ ክፉ ሰዎችም አሉ። ይህም ቢሆን ከንቱ ነው እላለሁ። |
በመሆኑም ደስታ መልካም ነው አልኩ፤ ምክንያቱም ለሰው ከፀሐይ በታች ከመብላትና ከመጠጣት እንዲሁም ከመደሰት የተሻለ ነገር የለም፤ ከፀሐይ በታች እውነተኛው አምላክ በሚሰጠው የሕይወት ዘመን በትጋት ሲሠራ ይህ ደስታ ሊርቀው አይገባም። |
ቀንም ሆነ ሌሊት እንቅልፍ በዓይኔ ሳይዞር ጥበብን ለማግኘትና በምድር ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ለማየት ከፍተኛ ጥረት አደረግኩ። |
ከዚያም የእውነተኛውን አምላክ ሥራ ሁሉ አጤንኩ፤ የሰው ልጆች ከፀሐይ በታች የሚሆነውን ነገር ሁሉ መረዳት እንደማይችሉም ተገነዘብኩ። ሰዎች የቱንም ያህል ጥረት ቢያደርጉ ሊረዱት አይችሉም። ይህን ለማወቅ የሚያስችል ጥበብ አለን ቢሉም እንኳ ሊረዱት አይችሉም። |
ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጠው የሰለሞን መዝሙር፦ |
“በከንፈሩ መሳም ይሳመኝ፤የፍቅር መግለጫዎችህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ ያሰኛሉና። |
የዘይትህ መዓዛ ደስ ይላል። ስምህ ጥሩ መዓዛ እንዳለው የሚፈስ ዘይት ነው። ቆነጃጅት የሚወዱህ ለዚህ ነው። |
ይዘኸኝ ሂድ፤ አብረን እንሩጥ። ንጉሡ ወደ እልፍኞቹ አስገብቶኛል! በአንተ ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ። ከወይን ጠጅ ይልቅ የፍቅር መግለጫዎችህን እናወድስ። አንተን መውደዳቸው ተገቢ ነው። |
የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ እኔ ጥቁር ብሆንም ውብ ነኝ፤እንደ ቄዳር ድንኳኖች፣ እንደ ሰለሞን ድንኳኖችም ነኝ። |
ጥቁር ስለሆንኩ ትኩር ብላችሁ አትዩኝ፤ፀሐይ ፊቴን አክስሎታልና። ወንድሞቼ በጣም ተቆጡኝ፤የወይን እርሻዎች ጠባቂ አደረጉኝ፤የገዛ ራሴን የወይን እርሻ ግን መጠበቅ አልቻልኩም። |
“እጅግ የምወድህ ፍቅረኛዬ፣መንጋህን የት እንደምታሰማራ፣እኩለ ቀንም ላይ የት እንደምታሳርፍ ንገረኝ። በጓደኞችህ መንጎች መካከልበመሸፈኛ ፊቷን ተሸፋፍና እንደምትቅበዘበዝ ሴት ለምን ልሁን?” |
“አንቺ ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣ የማታውቂ ከሆነየመንጋውን ዱካ ተከትለሽ ሂጂ፤የፍየል ግልገሎችሽንም በእረኞቹ ድንኳኖች አጠገብ አሰማሪ።” |
“ፍቅሬ ሆይ፣ የፈርዖንን ሠረገሎች በሚጎትቱ ፈረሶች መካከል እንዳለች ባዝራ ውብ ነሽ። |
ጉንጮችሽ በማስዋቢያ ተውበዋል፤አንገትሽም በጨሌ ሐብል አጊጧል። |
በብር ፈርጥ የተንቆጠቆጡየወርቅ ጌጦች እንሠራልሻለን።” |
“ንጉሡ ክብ ጠረጴዛው ጋ ተቀምጦ ሳለየሽቶዬ መዓዛ አካባቢውን አወደው። |
ውዴ ለእኔ ጥሩ መዓዛ እንዳለው በከረጢት ያለ ከርቤ ነው፤በጡቶቼ መካከል ያድራል። |
ውዴ በኤንገዲ የወይን እርሻዎች መካከልእጅብ ብሎ እንደበቀለ የሂና ተክል ነው።” |
“ፍቅሬ ሆይ፣ እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። ዓይኖችሽ እንደ ርግብ ዓይኖች ናቸው።” |
“ውዴ ሆይ፣ እነሆ፣ አንተ ውብ ነህ፤ ደግሞም ደስ ትላለህ። አልጋችን በለምለም ቅጠል መካከል ነው። |
የቤታችን ተሸካሚዎች አርዘ ሊባኖሶች፣ጣሪያችንም የጥድ ዛፎች ናቸው። |
“አንቺ የተከበርሽ ልጃገረድ ሆይ፣እግሮችሽ በነጠላ ጫማሽ ውስጥ ሲታዩ እንዴት ያምራሉ! የዳሌዎችሽ ቅርጽየእጅ ባለሙያ የተጠበበባቸው ጌጦች ይመስላሉ። |
እምብርትሽ እንደ ክብ ሳህን ነው። የተደባለቀ ወይን ጠጅ ከእሱ አይታጣ። ሆድሽ ዙሪያውን በአበቦች እንደታጠረየስንዴ ክምር ነው። |
ሁለቱ ጡቶችሽ ሁለት ግልገሎችን፣የሜዳ ፍየል መንታዎችን ይመስላሉ። |
አንገትሽ በዝሆን ጥርስ የተሠራ ማማ ይመስላል። ዓይኖችሽ በባትራቢም በር አጠገብ እንዳሉትየሃሽቦን ኩሬዎች ናቸው። አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ እንደሚመለከትየሊባኖስ ማማ ነው። |
ራስሽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ አክሊል ሆኖልሻል፤ፀጉርሽ ሐምራዊ ሱፍ ይመስላል። ንጉሡ በዘንፋላው ፀጉርሽ ተማርኳል። |
አንቺ የተወደድሽ ልጃገረድ ሆይ፣ ምንኛ ውብ ነሽ! እንዴትስ ደስ ታሰኛለሽ!በጣም ከሚያስደስቱ ነገሮች ሁሉ በላይ ትማርኪያለሽ! |
ቁመናሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፤ጡቶችሽ ደግሞ የቴምር ዘለላ ይመስላሉ። |
እኔም እንዲህ አልኩ፦ ‘የቴምር ዘለላዎቹን መያዝ እንድችልዛፉ ላይ እወጣለሁ።’ ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ ይሁኑ፤የትንፋሽሽ መዓዛ እንደ ፖም ሽታ ይሁን፤ |
አፍሽም እንደ ምርጥ ወይን ጠጅ ይሁን።” “ይህ የወይን ጠጅ ለውዴ እየተንቆረቆረ ይውረድ፤በተኙ ሰዎች ከንፈር በቀስታ ይፍሰስ። |
እኔ የውዴ ነኝ፤እሱም የሚመኘው እኔን ነው። |
ውዴ ሆይ፣ ና፤ወደ መስክ እንሂድ፤በሂና ተክሎች መካከል እንቀመጥ። |
ወይኑ ለምልሞ፣አበባው ፈክቶ፣የሮማን ዛፎቹም አብበው እንደሆነ ለማየትበማለዳ ተነስተን ወደ ወይን እርሻዎቹ እንሂድ። እኔም በዚያ ለአንተ ያለኝን ፍቅር እገልጽልሃለሁ። |
የዱዳይም ፍሬዎቹ መዓዛቸውን ሰጥተዋል፤በደጆቻችንም ሁሉም ዓይነት ምርጥ ፍሬዎች አሉ። ውዴ ሆይ፣ አዲሶቹንም ሆነ በፊት የተቀጠፉትን ፍሬዎችለአንተ አስቀምጬልሃለሁ። |
“ሌሊት በአልጋዬ ላይ ሆኜየምወደውን ሰው ለማግኘት ተመኘሁ። ፈለግኩት፤ ግን አላገኘሁትም። |
ተነስቼ በከተማዋ ውስጥ እዘዋወራለሁ፤የምወደውን ሰውእስቲ በጎዳናዎቹና በአደባባዮቹ ልፈልገው። ፈለግኩት፤ ግን አላገኘሁትም። |
በከተማዋ ውስጥ የሚዘዋወሩት ጠባቂዎች አገኙኝ። እኔም ‘የምወደውን ሰው አይታችሁታል?’ ብዬ ጠየቅኳቸው። |
ከእነሱ ገና እልፍ እንዳልኩየምወደውን ሰው አገኘሁት። አጥብቄም ያዝኩት፤ወደ እናቴ ቤት፣ ወደ ፀነሰችኝም ሴት እልፍኝእስካስገባው ድረስ አለቀኩትም። |
የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ በራሱ እስኪነሳሳ ድረስፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ በሜዳ ፍየሎችና በመስክ ላይ ባሉ አጋዘኖች አምላችኋለሁ።” |
“በከርቤና በነጭ ዕጣን፣ጥሩ መዓዛ ባላቸውም የነጋዴ ቅመማ ቅመሞች ታውዶ፣እንደ ጭስ ዓምድ ከምድረ በዳ እየመጣ ያለው ይህ ነገር ምንድን ነው?” |
“እነሆ፣ ይህ የሰለሞን ድንክ አልጋ ነው። ከእስራኤል ኃያላን የተውጣጡስልሳ ኃያላን አጅበውታል፤ |
ሁሉም ሰይፍ የታጠቁናበውጊያ የሠለጠኑ ናቸው፤እያንዳንዳቸውም በሌሊት የሚያጋጥሙ አስፈሪ ነገሮችን ለመከላከልሰይፋቸውን ወገባቸው ላይ ታጥቀዋል።” |
“ይህ፣ ንጉሥ ሰለሞን ከሊባኖስ እንጨትለራሱ ያሠራው የንጉሥ ድንክ አልጋ ነው። |
ዓምዶቹን የሠራው ከብር፣መደገፊያዎቹን ደግሞ ከወርቅ ነው። መቀመጫው በሐምራዊ ሱፍ የተሠራ ነው፤ውስጡንም የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆችበፍቅር ተነሳስተው ለብጠውታል።” |
“እናንተ የጽዮን ሴቶች ልጆች ሆይ፣ወጥታችሁ ንጉሥ ሰለሞንን ተመልከቱ፤በሠርጉ ዕለት፣ልቡ ሐሴት ባደረገበት በዚያ ቀን፣እናቱ የሠራችለትን የሠርግ አክሊል ደፍቷል።” |
“እኔ ግን በባሕር ዳርቻ ላይ የሚበቅል የሳሮን አበባ ነኝ፤የሸለቆም አበባ ነኝ።” |
“ፍቅሬ በሴቶች መካከል ስትታይበእሾህ መካከል እንዳለ አበባ ናት።” |
“ውዴ በወንዶች መካከል ሲታይበዱር ዛፎች መካከል እንዳለ የፖም ዛፍ ነው። በጥላው ሥር ለመቀመጥ እጅግ እጓጓለሁ፤ፍሬውም ለአፌ ጣፋጭ ነው። |
ወደ ግብዣ ቤት ወሰደኝ፤የፍቅር ዓርማውንም በእኔ ላይ አውለበለበ። |
በዘቢብ ቂጣ ኃይሌን አድሱልኝ፤በፖም አበረታቱኝ፤በፍቅሩ ተይዤ ታምሜአለሁና። |
ግራ እጁን ተንተርሻለሁ፤ቀኝ እጁም አቅፎኛል። |
የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ በራሱ እስኪነሳሳ ድረስፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ፣ በሜዳ ፍየሎችና በመስክ ላይ ባሉ አጋዘኖች አምላችኋለሁ። |
እነሆ፣ ውዴ ተራሮቹን እየወጣና በኮረብቶቹ ላይ እየዘለለ ሲመጣድምፁ ይሰማኛል! |
ውዴ፣ የሜዳ ፍየል ወይም የአጋዘን ግልገል ይመስላል። በመስኮት በኩል ትኩር ብሎ እየተመለከተ፣በፍርግርጉ በኩል አጮልቆ እያየከግድግዳችን ጀርባ ቆሟል። |
ውዴ እንዲህ አለኝ፦ ‘ፍቅሬ ሆይ፣ ተነሽ፤የእኔ ቆንጆ፣ ነይ አብረን እንሂድ። |
እነሆ፣ ክረምቱ አልፏል። ዝናቡ ቆሟል፤ ደግሞም ጠፍቷል። |
በምድሩ ላይ አበቦች አብበዋል፤ተክሎች የሚገረዙበት ጊዜ ደርሷል፤በምድራችንም ላይ የዋኖስ ዝማሬ ተሰምቷል። |
የበለስ ዛፏ መጀመሪያ ላይ ያፈራቻቸው ፍሬዎች በስለዋል፤የወይን ተክሎቹም አብበው መዓዛቸውን ሰጥተዋል። ፍቅሬ ሆይ፣ ተነሽና ነይ፤የእኔ ቆንጆ፣ ነይ አብረን እንሂድ። |
በዓለቶች መሃል በሚገኝ መሸሸጊያ፣በገደላማ ስፍራ ባለ ሰዋራ ቦታ ያለሽ ርግቤ ሆይ፣እስቲ ልይሽ፤ ድምፅሽንም ልስማው፤ድምፅሽ ማራኪ፣ ቁመናሽም ያማረ ነውና።’” |
“ቀበሮዎቹን ይኸውም የወይን እርሻዎቹን የሚያበላሹትንትናንሽ ቀበሮዎች ያዙልን፤የወይን እርሻችን አብቧልና።” |
“ውዴ የእኔ ነው፤ እኔም የእሱ ነኝ። መንጋውን በአበቦች መካከል እየጠበቀ ነው። |
የቀኑ ነፋስ መንፈስ ከመጀመሩና ጥላው ከመሸሹ በፊትውዴ ሆይ፣ እንደ ሜዳ ፍየልወይም በመካከላችን ባሉት ተራሮች ላይ እንደሚገኝ የአጋዘን ግልገል በፍጥነት ተመለስ። |
“እህቴ፣ ሙሽራዬ ሆይ፣ወደ አትክልት ቦታዬ ገብቻለሁ። ከርቤዬንና ቅመሜን ወስጃለሁ። የማር እንጀራዬንና ወለላውን በልቻለሁ፤የወይን ጠጄንና ወተቴን ጠጥቻለሁ።” “ውድ ጓደኞቼ፣ ብሉ! ጠጥታችሁም በፍቅር መግለጫዎች ስከሩ!” |
“እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቷል። ውዴ በሩን ሲያንኳኳ ይሰማኛል!” “እህቴ ሆይ፣ የእኔ ፍቅር፣እንከን የለሽ ርግቤ ሆይ፣ ክፈቺልኝ! ራሴ በጤዛ፣ፀጉሬም በሌሊቱ እርጥበት ርሷል።” |
“‘ልብሴን አውልቄአለሁ። መልሼ መልበስ ሊኖርብኝ ነው? እግሬን ታጥቤአለሁ። እንደገና ላቆሽሸው ነው?’ |
ውዴ እጁን ከበሩ ቀዳዳ መለሰ፤ለእሱ ያለኝ ስሜትም ተነሳሳ። |
እኔም ለውዴ በሩን ለመክፈት ተነሳሁ፤የመዝጊያው እጀታ ላይእጆቼ ከርቤ፣ጣቶቼም የከርቤ ፈሳሽ አንጠባጠቡ። |
ለውዴ በሩን ከፈትኩለት፤ውዴ ግን በዚያ አልነበረም፤ ሄዶ ነበር። በመሄዱም ተስፋ ቆረጥኩ። ፈለግኩት፤ ግን አላገኘሁትም። ጠራሁት፤ እሱ ግን አልመለሰልኝም። |
ከተማዋን እየተዘዋወሩ የሚጠብቁት ሰዎች አገኙኝ። መቱኝ፤ አቆሰሉኝ። የቅጥሩ ጠባቂዎች ነጠላዬን ገፈፉኝ። |
የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ ውዴን ካገኛችሁት በፍቅሩ ተይዤ መታመሜንእንድትነግሩት አምላችኋለሁ።” |
“አንቺ ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣ውድሽ ሌሎች ከሚያፈቅሯቸው ወንዶች ሁሉ እንዴት ቢበልጥ ነው? እንዲህ ያለ መሐላ ያስገባሽን፣ለመሆኑ ውድሽ ሌሎች ከሚያፈቅሯቸው ወንዶች ሁሉ እንዴት ቢበልጥ ነው?” |
“ውዴ በጣም ቆንጆና ቀይ ነው፤በአሥር ሺህ ሰዎች መካከል እንኳ ጎልቶ ይታያል። |
ራሱ እንደ ወርቅ፣ አዎ እንደጠራ ወርቅ ነው። ፀጉሩ እንደሚወዛወዝ የዘንባባ ዝንጣፊ ነው፤እንደ ቁራም ጥቁር ነው። |
ዓይኖቹ በውኃ ጅረት አጠገብ እንዳሉ፣ጢም ብሎ በሞላ ኩሬ ዳርቻ ሆነውበወተት እንደሚታጠቡ ርግቦች ናቸው። |
ጉንጮቹ የቅመማ ቅመም መደብ፣ጥሩ መዓዛ ያላቸው ዕፀዋት ክምር ይመስላሉ። ከንፈሮቹ ፈሳሽ ከርቤ የሚያንጠባጥቡ አበቦች ናቸው። |
የእጆቹ ጣቶች ወርቅ፣ የጣቶቹም ጫፎች ክርስቲሎቤ ናቸው። ሆዱ በሰንፔር የተሸፈነ የተወለወለ የዝሆን ጥርስ ነው። |
እግሮቹ ከምርጥ ወርቅ በተሠሩ መሰኪያዎች ላይ የቆሙ የእብነ በረድ ዓምዶች ናቸው። መልኩ እንደ ሊባኖስ ያማረ ነው፤ እንደ አርዘ ሊባኖስም አቻ የለውም። |
አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፤ሁለመናውም ደስ ያሰኛል። የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ ውዴ ይህ ነው፤ ፍቅሬ እንዲህ ያለ ነው።” |
“ፍቅሬ ሆይ፣ እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። እነሆ፣ አንቺ ውብ ነሽ። ዓይኖችሽ በፊትሽ መሸፈኛ ውስጥ ሲታዩ እንደ ርግብ ዓይኖች ናቸው። ፀጉርሽ ከጊልያድ ተራሮችእየተግተለተለ እንደሚወርድ የፍየል መንጋ ነው። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.