text stringlengths 4 267 |
|---|
ጥርሶችሽ ገና ተሸልተውናታጥበው እንደወጡ፣ሁሉም መንታ መንታ እንደወለዱ የበግ መንጋ ናቸው፤ደግሞም ከመካከላቸው ግልገሉን ያጣ የለም። |
ከንፈሮችሽ እንደ ደማቅ ቀይ ፈትል ናቸው፤ንግግርሽም አስደሳች ነው። በመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጉንጮችሽየተከፈለ ሮማን ይመስላሉ። |
አንገትሽ አንድ ሺህ ጋሻዎች፣ይኸውም ኃያላን ሰዎች የሚይዟቸው ክብ ጋሻዎች ሁሉ የተንጠለጠሉበትንናበንብርብር ድንጋዮች የተገነባውንየዳዊት ማማ ይመስላል። |
ሁለቱ ጡቶችሽበአበቦች መካከል የተሰማሩ፣መንታ የሆኑ ሁለት የሜዳ ፍየል ግልገሎችን ይመስላሉ።” |
“የቀኑ ነፋስ መንፈስ ከመጀመሩና ጥላው ከመሸሹ በፊትወደ ከርቤው ተራራናወደ ነጭ ዕጣኑ ኮረብታ እሄዳለሁ።” |
“ፍቅሬ ሆይ፣ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤እንከንም የለብሽም። |
ሙሽራዬ ሆይ፣ ተያይዘን ከሊባኖስ እንሂድ፤አዎ፣ ከሊባኖስ አብረን እንሂድ። ከአማና አናት፣ከሰኒር ጫፍ፣ ከሄርሞን አናት፣ከአንበሳ ዋሻዎች፣ ከነብር ተራሮች ውረጂ። |
እህቴ፣ ሙሽራዬ ሆይ፣ ልቤን ማርከሽዋል፤በአንድ አፍታ እይታሽ፣ከሐብልሽ ዶቃዎች በአንዱ ልቤን ማርከሽዋል። |
እህቴ፣ ሙሽራዬ ሆይ፣ የፍቅር መግለጫዎችሽ እንዴት ደስ ያሰኛሉ! የፍቅር መግለጫሽ ከወይን ጠጅ፣የሽቶሽም መዓዛ ከየትኛውም ዓይነት ቅመም እጅግ ይበልጣል! |
ሙሽራዬ ሆይ፣ ከንፈሮችሽ የማር እንጀራ ወለላ ያንጠባጥባሉ። ከምላስሽ ሥር ማርና ወተት ይፈልቃል፤የልብሶችሽም ጠረን እንደ ሊባኖስ መዓዛ ነው። |
እህቴ፣ ሙሽራዬ፣ የተቆለፈ የአትክልት ቦታ፣አዎ የተቆለፈ የአትክልት ቦታ፣ የታሸገም ምንጭ ናት። |
ቡቃያሽ ሮማንና ምርጥ ፍራፍሬዎችደግሞም የሂና እና የናርዶስ ተክሎች የበቀሉበት ገነት ነው፤ |
በተጨማሪም ናርዶስ፣ ሳፍሮን፣ ጠጅ ሣር፣ ቀረፋ፣ነጭ ዕጣን የሚገኝባቸው የተለያዩ ዛፎች፣ ከርቤ፣ እሬትናሁሉም ዓይነት ምርጥ ሽቶዎች ያሉበት ገነት ነው። |
አንቺ በአትክልት ቦታ ያለ ምንጭ፣ ንጹሕ ውኃ የሚገኝበት ጉድጓድናከሊባኖስ የሚፈስሱ ጅረቶች ነሽ። |
የሰሜን ነፋስ ሆይ፣ ንቃ፤የደቡብ ነፋስ ሆይ፣ ና። በአትክልት ቦታዬ ላይ ንፈስ። መዓዛውም አካባቢውን ያውደው።” “ውዴ ወደ አትክልት ቦታው ይግባናምርጥ የሆኑትን ፍራፍሬዎች ይብላ።” |
“ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽ ሆይ፣ውድሽ የት ሄደ? ለመሆኑ ውድሽ የሄደው በየት በኩል ነው? አብረንሽ እንፈልገው።” |
“ውዴ መንጋውን በአትክልት ቦታዎቹ መካከል ለማሰማራትናአበቦችን ለመቅጠፍየቅመማ ቅመም ተክሎች መደብ ወዳለበትወደ አትክልት ቦታው ወርዷል። |
እኔ የውዴ ነኝ፤ውዴም የእኔ ነው። እሱ መንጋውን በአበቦች መካከል እየጠበቀ ነው።” |
“ፍቅሬ ሆይ፣ አንቺ እንደ ቲርጻ ቆንጆ ነሽ፤እንደ ኢየሩሳሌምም ውብ ነሽ፤በዓርማዎቻቸው ዙሪያ እንደተሰለፉ ወታደሮች እጅግ ታምሪያለሽ። |
ስሜቴን አውከውታልና፣ዓይኖችሽን ከእኔ ላይ አንሺ። ፀጉርሽ ከጊልያድ እየተግተለተለ እንደሚወርድየፍየል መንጋ ነው። |
ጥርሶችሽ ታጥበው እንደወጡ፣ሁሉም መንታ መንታ እንደወለዱየበግ መንጋ ናቸው፤ከመካከላቸውም ግልገሉን ያጣ የለም። |
በመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጉንጮችሽየተከፈለ ሮማን ይመስላሉ። |
እርግጥ 60 ንግሥቶች፣80 ቁባቶችናቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ቆነጃጅት ሊኖሩ ይችላሉ። |
እንከን የሌለባት ርግቤ ግን አንድ ብቻ ናት። እሷ ለእናቷ ብርቅዬ ልጅ ናት። በወለደቻት ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ናት። ሴቶች ልጆች አይተዋት ‘የታደልሽ ነሽ’ ይሏታል፤ንግሥቶችና ቁባቶችም ያወድሷታል። |
‘እንደ ማለዳ ወጋገን የምታበራ፣እንደ ሙሉ ጨረቃ ውብ የሆነች፣እንደ ፀሐይ ብርሃን የጠራች፣በዓርማዎቻቸው ዙሪያ እንደተሰለፉ ወታደሮች እጅግ የምታምረው ይህች ሴት ማን ናት?’” |
“በሸለቆው ውስጥ ያቆጠቆጡትን ተክሎች ለማየት፣ደግሞም ወይኑ ለምልሞ፣የሮማን ዛፎቹም አብበው እንደሆነ ለመመልከትየገውዝ ዛፎች ወዳሉበት ወደ አትክልት ቦታው ወረድኩ። |
ምንም ሳይታወቀኝምኞቴ የተከበሩ ወገኖቼየያዟቸው ሠረገሎች ወዳሉበት ወሰደኝ።” |
“አንቺ ሱላማዊት፣ ተመለሺ፤ ተመለሺ! እናይሽ ዘንድተመለሺ፤ ተመለሺ!” “በሱላማዊቷ ላይ የምታፈጡት ለምንድን ነው?” “እሷ የመሃናይምን ጭፈራ ትመስላለች!” |
“ምነው አንተ፣ የእናቴን ጡት እንደጠባ፣እንደ ወንድሜ በሆንክ! እንዲህ ቢሆን ኖሮ ውጭ ሳገኝህ በሳምኩህ ነበር፤ማንም ባልናቀኝ ነበር። |
እኔም ወዳስተማረችኝወደ እናቴ ቤት በወሰድኩህናወደዚያ ባስገባሁህ ነበር። ትጠጣው ዘንድ ቅመም የተጨመረበት ወይን ጠጅናየሮማን ጭማቂ በሰጠሁህ ነበር። |
ግራ እጁን በተንተራስኩ፣ቀኝ እጁም ባቀፈኝ ነበር። |
የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፣ በራሱ እስኪነሳሳ ድረስ ፍቅርን በውስጤ እንዳትቀሰቅሱ ወይም እንዳታነሳሱ አምላችኋለሁ።” |
“ውዷን ደገፍ ብላከምድረ በዳ የምትመጣው ይህች ማን ናት?” “ከፖም ዛፍ ሥር ቀሰቀስኩህ። በዚያ እናትህ አንተን ለመውለድ አማጠች። በዚያም ወላጅ እናትህ ምጥ ይዟት ነበር። |
እንደ ማኅተም በልብህ፣እንደ ማኅተም በክንድህ አስቀምጠኝ፤ፍቅር እንደ ሞት የበረታ ነውና፤ታማኝነትም እንደ መቃብር ጽኑ ነው፤ የፍቅር ወላፈን የእሳት ወላፈን ነው፤ የያህም ነበልባል ነው። |
ጎርፍ ፍቅርን ሊያጠፋው አይችልም፤ወንዞችም ጠራርገው ሊወስዱት አይችሉም። አንድ ሰው ለፍቅር ሲል የቤቱን ሀብት ሁሉ ለመስጠት ቢያቀርብሰዎች በጣም ይንቁበታል።” |
“ገና ጡት ያላወጣችትንሽ እህት አለችን። እሷን በሚጠይቁን ቀንለእህታችን ምን ብናደርግ ይሻላል?” |
“እሷ ቅጥር ብትሆንበላይዋ ላይ የብር ጉልላት እንሠራለን፤በር ብትሆን ግንከአርዘ ሊባኖስ በተሠራ ሳንቃ እናሽጋታለን።” |
“እኔ ቅጥር ነኝ፤ጡቶቼም እንደ ማማ ናቸው። በእሱም ፊትሰላም እንዳገኘች ሴት ሆንኩ። |
ሰለሞን በበዓልሃሞን የወይን እርሻ ነበረው። እሱም የወይን እርሻውን ለጠባቂዎች በአደራ ሰጠ። እያንዳንዳቸውም ለሚያገኙት ፍሬ አንድ ሺህ የብር ሰቅል ያመጡ ነበር። |
የራሴ የሆነ የወይን እርሻ አለኝ። ሰለሞን ሆይ፣ አንድ ሺው የብር ሰቅል የአንተ ነው፤ሁለት መቶው ደግሞ ፍሬውን ለሚጠብቁት ነው።” |
“አንቺ በአትክልት ቦታዎቹ የምትኖሪ ሆይ፣ጓደኞቼ ድምፅሽን ያዳምጣሉ። እስቲ እኔም ልስማው።” |
“ውዴ ሆይ፣ ቶሎ ና፤እንደ ሜዳ ፍየልወይም የቅመም ተክሎች በሚበቅሉባቸው ተራሮች ላይ እንዳለየአጋዘን ግልገል ፍጠን።” |
አሁን ግን፣ ያዕቆብ ሆይ ፈጣሪህ፣እስራኤልም ሆይ የሠራህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እኔ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ። በስምህ ጠርቼሃለሁ። አንተ የእኔ ነህ። |
በውኃዎች መካከል ስታልፍ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤በወንዞችም መካከል ስትሻገር አያሰምጡህም። በእሳት መካከል ስትሄድ አትቃጠልም፤ነበልባሉም አይፈጅህም። |
እኔ ይሖዋ አምላክህ፣የእስራኤል ቅዱስ፣ አዳኝህ ነኝና። ግብፅን ለአንተ ቤዛ አድርጌ ሰጥቻለሁ፤ኢትዮጵያንና ሴባን በአንተ ምትክ ሰጥቻለሁ። |
አንተ በዓይኔ ፊት ውድ ሆነሃልና፤የተከበርክም ነህ፤ እኔም ወድጄሃለሁ። ስለዚህ በአንተ ምትክ ሰዎችን፣በሕይወትህም ምትክ ብሔራትን እሰጣለሁ። |
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ። ዘርህን ከምሥራቅ አመጣለሁ፤ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ። |
ሰሜንን ‘ልቀቃቸው!’ እለዋለሁ፤ ደቡብንም እንዲህ እለዋለሁ፦ ‘አታግታቸው። ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ፣ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ አምጣ፤ |
በስሜ የተጠራውን፣ለክብሬም የፈጠርኩትን፣የሠራሁትንና ያበጀሁትን ሁሉ አምጣ።’ |
ዓይን ቢኖራቸውም ዕውር የሆኑትን፣ጆሮ ቢኖራቸውም ደንቆሮ የሆኑትን ሰዎች አውጣ። |
ብሔራት ሁሉ አንድ ቦታ ይሰብሰቡ፤ሕዝቦችም በአንድነት ይሰብሰቡ። ከመካከላቸው ይህን ሊናገር የሚችል ማን አለ? ወይስ የመጀመሪያዎቹን ነገሮች ሊነግሩን ይችላሉ? ትክክል መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ምሥክሮቻቸውን ያቅርቡ፤ወይም ሰምተው ‘ይህ እውነት ነው!’ ይበሉ።” |
“እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ” ይላል ይሖዋ፤“አዎ፣ የመረጥኩት አገልጋዬ ናችሁ፤ይህም ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድደግሞም እኔ ምንጊዜም ያው እንደሆንኩ ታስተውሉ ዘንድ ነው። ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም፤ከእኔም በኋላ የለም። |
እኔ፣ አዎ እኔ ይሖዋ ነኝ፤ ከእኔ በቀር አዳኝ የለም።” |
“በመካከላችሁ ባዕድ አምላክ ባልነበረበት ጊዜየተናገርኩት፣ ያዳንኩትና ያሳወቅኩት እኔ ነኝ። ስለዚህ እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ” ይላል ይሖዋ፤ “እኔም አምላክ ነኝ። |
ደግሞም እኔ ምንጊዜም ያው ነኝ፤ከእጄም አንዳች ነገር ሊነጥቅ የሚችል የለም። እርምጃ በምወስድበት ጊዜ ሊያግድ የሚችል ማን ነው?” |
እናንተን የሚቤዠው የእስራኤል ቅዱስ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለእናንተ ስል ወደ ባቢሎን እሰዳለሁ፤ የበሮቹንም መቀርቀርያዎች ሁሉ እጥላለሁ፤በመርከቦቻቸው ላይ ያሉት ከለዳውያንም በጭንቀት ይጮኻሉ። |
እኔ ይሖዋ የእናንተ ቅዱስ፣ የእስራኤል ፈጣሪ፣ ንጉሣችሁ ነኝ።” |
ይሖዋ ይኸውምበባሕር መካከል መንገድ የሚያበጀው፣በሚናወጡ ውኃዎችም መካከል ጎዳና የሚዘረጋው፣ |
የጦር ሠረገላውንና ፈረሱን፣ሠራዊቱንና ኃያላን ተዋጊዎቹን በአንድነት የሚያወጣው አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ይተኛሉ፤ አይነሱምም። እንደሚነድ የጧፍ ክር ተዳፍነው ይጠፋሉ።” |
“የቀድሞዎቹን ነገሮች አታስታውሱ፤ያለፈውንም ነገር አታውጠንጥኑ። |
እነሆ፣ አዲስ ነገር አደርጋለሁ፤አሁንም እንኳ መከናወን ጀምሯል። ይህን አታስተውሉም? በምድረ በዳ መንገድ አዘጋጃለሁ፤በበረሃም ወንዞችን አፈልቃለሁ። |
የዱር አውሬ፣ ቀበሮዎችናሰጎኖች ያከብሩኛል፤በምድረ በዳ ውኃ፣በበረሃም ወንዞችን እሰጣለሁና፤ይህን የማደርገው የመረጥኩት ሕዝቤ እንዲጠጣ፣ |
ለራሴ የሠራሁትም ሕዝብ እንዲጎነጭ ነው፤ሕዝቤ ውዳሴዬን እንዲያውጅ ይህን አደርጋለሁ። |
እስራኤል ሆይ፣ አንተ ግን የእኔ ነገር ስለታከተህ፣ያዕቆብ ሆይ፣ አልጠራኸኝም። |
ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ ለማቅረብ በግ አላመጣህልኝም፤ወይም መሥዋዕቶች በማቅረብ አላከበርከኝም። ስጦታ እንድታመጣልኝ አላስገደድኩህም፤ነጭ ዕጣን አቅርብልኝ ብዬም አላሰለቸሁህም። |
በገንዘብህ ጠጅ ሣር አልገዛህልኝም፤በመሥዋዕቶችህም ስብ አላጠገብከኝም። ከዚህ ይልቅ ኃጢአትህን አሸክመኸኛል፤በምትፈጽማቸውም በደሎች አሰልችተኸኛል። |
ስለ ራሴ ስል በደልህን እኔ ራሴ እደመስሰዋለሁ፤ኃጢአትህንም አላስታውስም። |
እስቲ አስታውሰኝ፤ ጉዳያችንን አቅርበን እንሟገት፤ትክክለኛ መሆንህን ለማረጋገጥ በበኩልህ ጉዳይህን ተናገር። |
የመጀመሪያው አባትህ ኃጢአት ሠርቷል፤የገዛ ቃል አቀባዮችህም በእኔ ላይ ዓምፀዋል። |
ስለዚህ በቅዱሱ ስፍራ የሚገኙትን መኳንንት አረክሳለሁ፤ያዕቆብንም ለጥፋት አሳልፌ እሰጠዋለሁ፤እስራኤልንም ለስድብ እዳርገዋለሁ። |
እነሆ፣ ደግፌ የያዝኩት፣ ደስ የምሰኝበትና የመረጥኩት አገልጋዬ! መንፈሴን በእሱ ላይ አድርጌአለሁ፤እሱ ለብሔራት ፍትሕን ያመጣል። |
አይጮኽም ወይም ድምፁን ከፍ አያደርግም፤ድምፁንም በጎዳና ላይ አያሰማም። |
የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፤የሚጨስንም የጧፍ ክር አያጠፋም። ፍትሕን በታማኝነት ያመጣል። |
እሱ ፍትሕን በምድር ላይ እስኪያሰፍን ድረስ አይሰበርም ወይም ብርሃኑ አይደክምም፤ደሴቶችም ሕጉን በተስፋ ይጠባበቃሉ። |
ሰማያትን የፈጠረውና የዘረጋው፣ምድርንና በውስጧ ያሉትን ነገሮች ሁሉ የሠራው፣በላይዋም ለሚኖሩ ሰዎች እስትንፋስን፣በእሷም ላይ ለሚመላለሱ መንፈስን የሰጠውእውነተኛው አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ |
“እኔ ይሖዋ በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፤እጅህን ይዣለሁ። እጠብቅሃለሁ፤ እንዲሁም ለሰዎች ቃል ኪዳን፣ለብሔራትም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ፤ |
አንተም የዓይነ ስውራንን ዓይን ታበራለህ፤እስረኛውን ከወህኒ ቤት፣በጨለማ ውስጥ የተቀመጡትንም ከእስር ቤት ታወጣለህ። |
እኔ ይሖዋ ነኝ። ስሜ ይህ ነው፤ክብሬን ለሌላ፣ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም። |
እነሆ፣ የቀደሙት ነገሮች ተፈጽመዋል፤አሁን ደግሞ አዳዲስ ነገሮችን እናገራለሁ። ገና ከመከሰታቸው በፊት ስለ እነሱ እነግራችኋለሁ።” |
እናንተ በባሕር ላይና በውስጡ ባሉት ፍጥረታት መካከል የምትጓዙ፣እናንተ ደሴቶችና በእነሱ ላይ የምትኖሩ ሁሉ፣ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፤ከምድር ዳርቻም ውዳሴውን አሰሙ። |
ምድረ በዳውና በዚያ ያሉ ከተሞች፣ቄዳር ያለችባቸውም ሰፈሮች ድምፃቸውን ከፍ ያድርጉ። ዓለታማ በሆኑ ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎች በደስታ እልል ይበሉ፤በተራሮችም አናት ላይ ሆነው ይጩኹ። |
ለይሖዋ ክብር ይስጡ፤በደሴቶችም ላይ ውዳሴውን ያውጁ። |
ይሖዋ እንደ ኃያል ሰው ይወጣል። እንደ ተዋጊ ቅንዓቱን ይቀሰቅሳል። ይጮኻል፤ አዎ፣ ቀረርቶ ያሰማል፤ከጠላቶቹ ይበልጥ ኃያል መሆኑን ያሳያል። |
“ለረጅም ጊዜ ዝም አልኩ። ጸጥ ብዬ ቆየሁ፤ ራሴንም ገታሁ። ምጥ እንደያዛት ሴትእቃትታለሁ፣ አለከልካለሁ እንዲሁም ቁና ቁና እተነፍሳለሁ። |
ተራሮችንና ኮረብቶችን አወድማለሁ፤ደግሞም በላያቸው ላይ ያለውን ተክል ሁሉ አደርቃለሁ። ወንዞችን ደሴቶች አደርጋለሁ፤ቄጠማ የሞላባቸውንም ኩሬዎች አደርቃለሁ። |
ዓይነ ስውራንን በማያውቁት መንገድ እመራቸዋለሁ፤ባልለመዱት ጎዳናም እንዲሄዱ አደርጋቸዋለሁ። ጨለማውን በፊታቸው ብርሃን፣ወጣ ገባ የሆነውንም ምድር ደልዳላ ሜዳ አደርጋለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፤ ደግሞም አልተዋቸውም።” |
በተቀረጸ ምስል የሚታመኑ፣ከብረት የተሠሩትን ሐውልቶች “እናንተ አምላኮቻችን ናችሁ” የሚሉወደ ኋላ ይመለሳሉ፤ እጅግም ያፍራሉ። |
እናንተ ደንቆሮዎች፣ ስሙ፤እናንተ ዕውሮች እዩ፤ ተመልከቱም። |
ከአገልጋዬ በቀር የታወረ፣እንደምልከው መልእክተኛዬም ደንቆሮ የሆነ ማን አለ? ብድራት እንደተከፈለው ሰው ዕውር የሆነወይም እንደ ይሖዋ አገልጋይ የታወረ ማን ነው? |
ብዙ ነገሮች ብታዩም ልብ የምትሉት ነገር የለም። ጆሮዎቻችሁን ብትከፍቱም ምንም አትሰሙም። |
ይሖዋ ለጽድቁ ሲልሕጉን ታላቅና ክብራማ በማድረግ ደስ ተሰኝቷል። |
ይህ ሕዝብ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ ነው፤ሁሉም ጉድጓድ ውስጥ ተይዘዋል፤ በእስር ቤትም ተሰውረዋል። የሚታደጋቸው በሌለበት ተበዝብዘዋል፤“መልሷቸው!” የሚል በሌለበትም ተዘርፈዋል። |
ከእናንተ መካከል ይህን የሚሰማ ማን ነው? በትኩረት የሚያዳምጥና ለወደፊቱ ጊዜ ትምህርት የሚወስድ ማን ነው? |
ያዕቆብን ለዘረፋ፣እስራኤልንም ለበዝባዦች አሳልፎ የሰጠ ማን ነው? በእሱ ላይ ኃጢአት በመፈጸም የበደልነው ይሖዋ አይደለም? እነሱ በመንገዱ ለመሄድ አልፈለጉም፤ሕጉንም አይታዘዙም። |
ስለዚህ ንዴቱን፣ ቁጣውንና የጦርነቱን መዓትበእስራኤል ላይ አፈሰሰ። የጦርነቱም እሳት በዙሪያው ያለውን ሁሉ በላው፤ እሱ ግን አላስተዋለም። አቃጠለው፤ እሱ ግን ጨርሶ ልብ አላለም። |
“እናንተ ደሴቶች፣ ዝም ብላችሁ አዳምጡኝ፤ብሔራትም ኃይላቸውን ያድሱ። በመጀመሪያ ይቅረቡ፤ ከዚያም ይናገሩ። ለፍርድ አንድ ላይ እንሰብሰብ። |
ብሔራትን አሳልፎ ይሰጠውናነገሥታትን ድል ይነሳ ዘንድከፀሐይ መውጫ አንዱን ያስነሳው፣በጽድቅ ወደ እግሩ የጠራው ማን ነው? በሰይፉ ፊት አቧራ የሚያደርጋቸው፣በቀስቱ ፊት በነፋስ እንደተወሰደ ገለባ የሚያደርጋቸው ማን ነው? |
እግሩ ባልረገጠው መንገድ በመጓዝምንም ነገር ሳያግደው እነሱን ያሳድዳል። |
ይህን የሠራና ያደረገ፣ትውልዶቹንም ከመጀመሪያ አንስቶ የጠራ ማን ነው? እኔ ይሖዋ የመጀመሪያው ነኝ፤ከመጨረሻዎቹም ጋር እኔ ያው ነኝ።” |
ደሴቶች አይተው ፈሩ። የምድር ዳርቻዎች ተንቀጠቀጡ። ቀረቡ፤ ወደ ፊትም መጡ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.