text stringlengths 4 267 |
|---|
እያንዳንዱም ባልንጀራውን ይረዳል፤ወንድሙንም “አይዞህ፣ በርታ” ይለዋል። |
የእጅ ጥበብ ባለሙያውም አንጥረኛውን ያበረታታል፤በመዶሻ ብረቱን የሚያሳሳውበመስፍ ላይ የሚቀጠቅጠውን ያበረታታዋል። ብየዳውን በተመለከተ “ጥሩ ነው” ይላል። ከዚያም ጣዖቱ እንዳይወድቅ አንድ ሰው በምስማር ይቸነክረዋል። |
“እስራኤል ሆይ፣ አንተ ግን አገልጋዬ ነህ፤ያዕቆብ ሆይ፣ አንተን መርጬሃለሁ፤የወዳጄ የአብርሃም ዘር ነህ፤ |
አንተን ከምድር ዳርቻዎች ወሰድኩህ፤እጅግ ርቀው ከሚገኙ ቦታዎችም ጠራሁህ። እንዲህ ብዬሃለሁ፦ ‘አንተ አገልጋዬ ነህ፤እኔ መርጬሃለሁ፤ ገሸሽ አላደረግኩህም። |
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ። እኔ አምላክህ ነኝና አትጨነቅ። አበረታሃለሁ፤ አዎ እረዳሃለሁ፤በጽድቅ ቀኝ እጄ አጥብቄ እይዝሃለሁ።’ |
እነሆ፣ በአንተ ላይ የተቆጡ ሁሉ ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም። ከአንተ ጋር የሚጣሉ ሁሉ እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ይጠፋሉም። |
ከአንተ ጋር የሚፋለሙትን ሰዎች ትፈልጋቸዋለህ፤ ሆኖም አታገኛቸውም፤ከአንተ ጋር የሚዋጉ ሰዎች እንደሌሉና ፈጽሞ እንዳልነበሩ ያህል ይሆናሉ። |
‘አትፍራ። እረዳሃለሁ’ የምልህእኔ፣ አምላክህ ይሖዋ ቀኝ እጅህን ይዣለሁና። |
ትል የሆንከው አንተ ያዕቆብ አትፍራ፤እናንተ የእስራኤል ሰዎች፣ እረዳችኋለሁ” ይላል የሚቤዥህ የእስራኤል ቅዱስ ይሖዋ። |
“እነሆ፣ ማሄጃ፣ በሁለቱም በኩል የተሳሉ ጥርሶች ያሉትአዲስ የመውቂያ መሣሪያ አድርጌሃለሁ። አንተም ተራሮቹን ረግጠህ ታደቃቸዋለህ፤ኮረብቶቹንም እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ። |
ወደ ላይ ትበትናቸዋለህ፤ነፋስም ይወስዳቸዋል፤አውሎ ነፋስ ይበትናቸዋል። በይሖዋ ደስ ይልሃል፤በእስራኤልም ቅዱስ ትኮራለህ።” |
“ችግረኞችና ድሆች ውኃ ይፈልጋሉ፤ ሆኖም አያገኙም። ከመጠማታቸው የተነሳ ምላሳቸው ደርቋል። እኔ ይሖዋ እመልስላቸዋለሁ። እኔ የእስራኤል አምላክ አልተዋቸውም። |
በተራቆቱ ኮረብቶች ላይ ወንዞች እንዲፈስሱ አደርጋለሁ፤በሸለቋማ ሜዳዎች መካከል ምንጮችን አፈልቃለሁ። ምድረ በዳውን ቄጠማ የሞላበት ኩሬ፣ውኃ የሌለበትንም ምድር የውኃ ምንጭ አደርጋለሁ። |
በበረሃ አርዘ ሊባኖስ፣ግራር፣ አደስና ዘይት የሚሰጥ ዛፍ እተክላለሁ። በበረሃማ ሜዳ የጥድ ዛፍ፣የአሽ ዛፍና የፈረንጅ ጥድ በአንድነት እተክላለሁ፤ |
ይህም የሚሆነው የይሖዋ እጅ ይህን እንዳደረገናየእስራኤል ቅዱስ ይህን እንደፈጠረሰዎች ሁሉ እንዲያዩና እንዲያውቁ፣ልብ እንዲሉና በጥልቅ እንዲያስተውሉ ነው።” |
“ሙግታችሁን አቅርቡ” ይላል ይሖዋ። “የመከራከሪያ ሐሳባችሁን አሰሙ” ይላል የያዕቆብ ንጉሥ። |
“ማስረጃ አቅርቡ፤ እንዲሁም ወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ንገሩን። በጥሞና እንድናስብባቸውና ፍጻሜያቸውን እንድናውቅስለቀድሞዎቹ ነገሮች ንገሩን። ወይም የሚመጡትን ነገሮች አሳውቁን። |
አማልክት መሆናችሁን እንድናውቅወደፊት የሚሆነውን ነገር ንገሩን። አዎ፣ አይተን በአድናቆት እንድንዋጥመልካምም ሆነ ክፉ፣ የሆነ ነገር አድርጉ። |
እነሆ፣ እናንተ ጨርሶ ሕልውና የሌላችሁ ናችሁ፤ምንም የምታከናውኑት ነገር የለም። እናንተን የሚመርጥ ሁሉ አስጸያፊ ነው። |
አንዱን ከሰሜን አስነስቻለሁ፤ እሱም ይመጣል፤የሚመጣው ከፀሐይ መውጫ ሲሆን ስሜንም ይጠራል። ጭቃውን እንደሚረግጥ ሸክላ ሠሪገዢዎችን እንደ ሸክላ አፈር ይረግጣቸዋል። |
እኛ እናውቅ ዘንድ ስለዚህ ነገር ከመጀመሪያው የተናገረወይም ‘እሱ ትክክል ነው’ እንድንል ከጥንት ጀምሮ የተናገረ ማን ነው? በእርግጥ የተናገረ የለም! ያሳወቀም የለም! ከእናንተ አንዳች ነገር የሰማ የለም!” |
ከማንም በፊት ጽዮንን “ወደፊት የሚሆነውን ነገር ተመልከቺ!” ያልኩት እኔ ነኝ፤ ለኢየሩሳሌምም ምሥራች ነጋሪ እልካለሁ። |
ሆኖም እኔ መመልከቴን ቀጠልኩ፤ አንድም ሰው አልነበረም፤ከእነሱ መካከል ምክር የሚሰጥ አልነበረም። እኔም መልስ እንዲሰጡ መጠየቄን ቀጠልኩ። |
እነሆ፣ ሁሉም ቅዠት ናቸው። ሥራቸው ከንቱ ነው። ከብረት የተሠሩት ምስሎቻቸው ነፋስና መና ናቸው። |
በደማስቆ ላይ የተላለፈ ፍርድ፦ “እነሆ፣ ደማስቆ ከተማ መሆኗ ይቀራል፤የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች። |
የአሮዔር ከተሞች ወና ይሆናሉ፤የመንጎች ማረፊያ ይሆናሉ፤የሚያስፈራቸውም አይኖርም። |
የተመሸጉ ከተሞች ከኤፍሬም፣መንግሥትም ከደማስቆ ይወገዳል፤የተረፉት የሶርያ ሰዎች ክብርምልክ እንደ እስራኤላውያን ክብር ይጠፋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። |
“በዚያን ቀን የያዕቆብ ክብር ይከስማል፤ጤናማ የሆነው ሰውነቱም ይከሳል። |
አጫጁ በማሳ ውስጥ ያለውን እህል በሚሰበስብበትናበእጁ ዛላውን በሚቆርጥበት ጊዜ እንደሚሆነው፣ደግሞም ሰው በረፋይም ሸለቆ እህል በሚቃርምበት ጊዜ እንደሚሆነው እንዲሁ ይሆናል። |
የወይራ ዛፍ ሲመታከፍ ባለው ቅርንጫፍ ላይ ሁለት ወይም ሦስት የወይራ ፍሬዎች ብቻ፣ ፍሬ በሚይዙት ቅርንጫፎችም ላይ አራት ወይም አምስት ፍሬዎች ብቻ እንደሚቀሩ፣በእሱም ላይ ቃርሚያ ብቻ ይቀራል” ይላል የእስራኤል አምላክ ይሖዋ። |
በዚያም ቀን ሰው ወደ ሠሪው ይመለከታል፤ ዓይኖቹም የእስራኤልን ቅዱስ ትኩር ብለው ያያሉ። |
የእጁ ሥራ ወደሆኑት መሠዊያዎች አይመለከትም፤ ጣቶቹ የሠሯቸውን የማምለኪያ ግንዶችም ሆነ የዕጣን ማጨሻዎች አተኩሮ አያይም። |
በዚያም ቀን፣ የተመሸጉ ከተሞቹ በጫካ እንዳለ የተተወ ቦታ፣በእስራኤላውያን ዘንድ እንደተተወ ቅርንጫፍ ይሆናሉ፤ቦታው ጠፍ መሬት ይሆናል። |
አንቺ፣ አዳኝ አምላክሽን ረስተሻልና፤መሸሸጊያ ዓለትሽንም አላስታወስሽም። ያማሩ ተክሎችን ያለማሽውናበመካከሉም የባዕድ ቡቃያ የተከልሽው ለዚህ ነው። |
በቀን በተክሎችሽ ዙሪያ አጥር ትሠሪያለሽ፤በማለዳም ዘርሽ እንዲበቅል ታደርጊያለሽ፤ይሁን እንጂ በበሽታና በማይሽር ሕመም ቀን አዝመራው ይጠፋል። |
አዳምጡ! እንደሚናወጥ ባሕር ያለየብዙ ሕዝቦች ትርምስ ይሰማል! እንደ ኃይለኛ ውኃዎች ድምፅ ያለየሚያስገመግም የብሔራት ጫጫታ ይሰማል! |
ብሔራት እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ ያለ የሚያስገመግም ድምፅ ያሰማሉ። እሱ ይገሥጻቸዋል፤ እነሱም ወደ ሩቅ ቦታ ይሸሻሉ፤በተራራ ላይ እንዳለ በነፋስ እንደሚበን ገለባናአውሎ ነፋስ እያሽከረከረ እንደሚወስደው ኮሸሽላ ይሆናሉ። |
ሲመሽ ሽብር ይነግሣል። ከመንጋቱም በፊት በዚያ አንዳቸውም አይገኙም። የዘረፉን ሰዎች ድርሻ፣የበዘበዙንም ሰዎች ዕጣ ይህ ነው። |
እርዳታ ለማግኘት ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፣በፈረሶች ለሚመኩ፣ብዛት ባላቸው የጦር ሠረገሎችናብርቱ በሆኑ የጦር ፈረሶች ለሚታመኑ ወዮላቸው! ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ ተስፋ አያደርጉም፤ይሖዋንም አይሹም። |
ይሁንና እሱም ጥበበኛ ነው፤ ጥፋትም ያመጣል፤ቃሉንም አያጥፍም። በክፉ አድራጊዎች ቤት ላይ፣እንዲሁም መጥፎ ነገር የሚሠሩ ሰዎችን በሚረዱ ላይ ይነሳል። |
ግብፃውያን ግን ተራ ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ፈረሶቻቸው ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም። ይሖዋ እጁን ሲዘረጋ፣እርዳታ የሚሰጥ ሁሉ ይሰናከላል፤እርዳታ ተቀባዩም ሁሉ ይወድቃል፤ሁሉም አንድ ላይ ይጠፋሉ። |
ይሖዋ እንዲህ ብሎኛልና፦ “አንበሳ ይኸውም ደቦል አንበሳ ባደነው እንስሳ ላይ ቆሞ እንደሚያገሳ፣ብዙ እረኞች ተጠራርተው ሲመጡበትምጩኸታቸው እንደማያሸብረው፣የሚያሰሙትም ሁካታ እንደማያስፈራው ሁሉየሠራዊት ጌታ ይሖዋም ለጽዮን ተራራና ለኮረብታዋ ሲልለመዋጋት ይወርዳል። |
ተወርውረው እንደሚወርዱ ወፎች፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋም እንዲሁ ኢየሩሳሌምን ይከልላታል። ይከልላታል፤ ደግሞም ያድናታል። ከአደጋ ያስጥላታል፤ እንዲሁም ይታደጋታል።” |
“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ እጅግ ወዳመፃችሁበት አምላክ ተመለሱ። |
በዚያ ቀን እያንዳንዱ ሰው በገዛ እጆቻችሁ በኃጢአት የሠራችኋቸውን የማይረቡ የብር አማልክቱንና ከንቱ የሆኑ የወርቅ አማልክቱን ያስወግዳልና። |
አሦራዊውም የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፤የሰው ያልሆነም ሰይፍ ይበላዋል። እሱም ሰይፉን ፈርቶ ይሸሻል፤ወጣቶቹም የግዳጅ ሥራ ይሠራሉ። |
ቋጥኙ እጅግ ከመፍራቱ የተነሳ ደብዛው ይጠፋል፤መኳንንቱም ምልክት ሆኖ የሚያገለግለውን ምሰሶ ሲያዩ ይሸበራሉ” ይላልብርሃኑ በጽዮን፣ እቶኑም በኢየሩሳሌም የሆነው ይሖዋ። |
ይሖዋ ለቀባው ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦ብሔራትን በፊቱ ለማስገዛት፣ነገሥታትን ትጥቅ ለማስፈታትእንዲሁም የከተማው በሮች እንዳይዘጉመዝጊያዎቹን በፊቱ ለመክፈት ስልቀኝ እጁን ለያዝኩት ለቂሮስ፦ |
“እኔ በፊትህ እሄዳለሁ፤ኮረብቶቹንም ደልዳላ አደርጋለሁ። የመዳብ በሮቹን እሰባብራለሁ፤የብረት መቀርቀሪያዎቹንም እቆርጣለሁ። |
በስምህ የምጠራህእኔ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ መሆኔን እንድታውቅ፣በጨለማ ያለውን ውድ ሀብትናስውር በሆኑ ቦታዎች የተደበቀውን ውድ ሀብት እሰጥሃለሁ። |
ለአገልጋዬ ለያዕቆብ፣ ለመረጥኩትም ለእስራኤል ስልበስምህ እጠራሃለሁ። አንተ ባታውቀኝም እንኳ የክብር ስም እሰጥሃለሁ። |
እኔ ይሖዋ ነኝ፤ ከእኔም ሌላ ማንም የለም። ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም። አንተ ባታውቀኝም እንኳ አበረታሃለሁ፤ |
ይኸውም ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ያሉ ሕዝቦችከእኔ በቀር ሌላ እንደሌለ እንዲያውቁ ነው።እኔ ይሖዋ ነኝ፤ ከእኔም ሌላ ማንም የለም። |
ብርሃንን እሠራለሁ፤ ጨለማንም እፈጥራለሁ፤ሰላምን አሰፍናለሁ፤ ጥፋትንም እፈጥራለሁ፤እኔ ይሖዋ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አደርጋለሁ። |
እናንተ ሰማያት፣ ከላይ አዝንቡ፤ደመናት ጽድቅን እንደ ዶፍ ያውርዱ። ምድር ትከፈት፤ መዳንንም ታፍራ፤ጽድቅንም በአንድነት ታብቅል። እኔ ይሖዋ ፈጥሬዋለሁ።” |
ከሠሪው ጋር ሙግት ለሚገጥም ወዮለት!እሱ መሬት ላይ በተጣሉሌሎች ገሎች መካከል ያለ ተራ ገል ነውና። ሸክላ፣ ሠሪውን “የምትሠራው ምንድን ነው?” ይለዋል? የሠራኸውስ ነገር “እሱ እጅ የለውም” ይላል? |
አንድን አባት “ምን ልትወልድ ነው?” ብሎ ለሚጠይቅ፣ ሴትንም “ምን ልትወልጂ ነው?” ለሚል ወዮለት! |
የእስራኤል ቅዱስ፣ ሠሪው የሆነው ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ወደፊት ስለሚሆኑት ነገሮች ልትጠይቁኝ፣ደግሞስ ልጆቼንና የእጆቼን ሥራ በተመለከተ ልታዙኝ ትፈልጋላችሁ? |
እኔ ምድርን ሠርቻለሁ፤ በላይዋም ላይ ሰውን ፈጥሬአለሁ። በገዛ እጆቼ ሰማያትን ዘርግቻለሁ፤ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዛለሁ።” |
“እኔ አንድን ሰው በጽድቅ አስነስቻለሁ፤መንገዱንም ሁሉ ቀና አደርጋለሁ። እሱ ከተማዬን ይገነባል፤በግዞት ያለውንም ሕዝቤን ያለዋጋ ወይም ያለጉቦ ነፃ ያወጣል” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የግብፅ ትርፍ፣ የኢትዮጵያ ሸቀጦችና ቁመተ ረጃጅሞቹ የሳባ ሰዎችወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የአንቺም ይሆናሉ። በሰንሰለት ታስረው ከኋላሽ ይሄዳሉ። መጥተው ይሰግዱልሻል። ደግሞም በጸሎት ‘አምላክ በእርግጥ ከአንቺ ጋር ነው፤ከእሱም በቀር ሌላ የለም፤ ሌላም አምላክ የለም’ ይሉሻል።” |
አዳኝ የሆንከው የእስራኤል አምላክ ሆይ፣በእርግጥ አንተ ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ። |
ሁሉም ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም፤ጣዖቶችን የሚሠሩ ሁሉ ውርደት ተከናንበው ይሄዳሉ። |
እስራኤል ግን በይሖዋ ዘላለማዊ መዳን ያገኛል። እናንተም ለዘላለም አታፍሩም ወይም አትዋረዱም። |
ሰማያትን የፈጠረው፣ እውነተኛው አምላክ፣ምድርን የሠራትና ያበጃት፣ አጽንቶም የመሠረታት፣መኖሪያ እንድትሆን እንጂ ለከንቱ ያልፈጠራትይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እኔ ይሖዋ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም። |
ስውር በሆነ ቦታ፣ ጨለማ በዋጠው ምድር አልተናገርኩም፤ለያዕቆብ ዘር‘በከንቱ ፈልጉኝ’ አላልኩም። እኔ ይሖዋ ጽድቅ የሆነውን እናገራለሁ፤ ቅን የሆነውንም አወራለሁ። |
ተሰብስባችሁ ኑ። እናንተ ከብሔራት ያመለጣችሁ፣ በአንድነት ቅረቡ። የተቀረጹ ምስሎቻቸውን ተሸክመው የሚዞሩም ሆኑሊያድናቸው ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ ምንም እውቀት የላቸውም። |
ጉዳያችሁን ተናገሩ፤ እንዲሁም ሙግታችሁን አቅርቡ። ተሰብስበው በአንድነት ይማከሩ። ከረጅም ጊዜ በፊት ይህን አስቀድሞ የተናገረ ማን ነው?ከጥንትስ ጀምሮ ይህን ያወጀ ማን ነው? ይህን ያደረግኩት እኔ ይሖዋ አይደለሁም? ከእኔ ሌላ አምላክ የለም፤ከእኔ በቀር ጻድቅ አምላክና አዳኝ የሆነ ማንም የለም። |
የምድር ዳርቻዎች ሁሉ፣ ወደ እኔ ተመለሱ፤ ትድናላችሁ፤እኔ አምላክ ነኝና፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም። |
በራሴ ምያለሁ፤ቃል ከአፌ በጽድቅ ወጥቷል፤ደግሞም አይመለስም፦ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ምላስም ሁሉ ታማኝ ለመሆን ይምላል፤ |
እንዲህም ይላል፦ ‘በእርግጥም በይሖዋ ዘንድ እውነተኛ ጽድቅና ብርታት አለ። በእሱ ላይ የተቆጡ ሁሉ ኀፍረት ተከናንበው ወደ እሱ ይመጣሉ። |
የእስራኤል ዘር ሁሉ በይሖዋ ትክክለኛ ሆኖ ይገኛል፤በእሱም ይኮራል።’” |
በግብፅ ላይ የተላለፈ ፍርድ፦ እነሆ፣ ይሖዋ በፈጣን ደመና እየጋለበ ወደ ግብፅ እየመጣ ነው። የግብፅ ከንቱ አማልክት በእሱ ፊት ይንቀጠቀጣሉ፤የግብፅም ልብ በውስጧ ይቀልጣል። |
“ግብፃውያንን በግብፃውያን ላይ አስነሳለሁ፤እርስ በርሳቸውም ይጨራረሳሉ፤እያንዳንዱ ወንድሙን፣ እያንዳንዱም ባልንጀራውን፣ከተማም ከተማን፣ መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል። |
የግብፅም መንፈስ በውስጧ ይረበሻል፤ዕቅዷንም አፋልሳለሁ። እነሱም እርዳታ ለማግኘት ከንቱ ወደሆኑት አማልክት፣ወደ ድግምተኞች፣ ወደ መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቋዮች ይዞራሉ። |
ግብፅ በኃይለኛ ገዢ እጅ እንድትወድቅ አደርጋለሁ፤ጨካኝ ንጉሥም ይገዛቸዋል” ይላል እውነተኛው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። |
የባሕሩ ውኃ ይደርቃል፤ወንዙም ይተናል፤ ጨርሶም ይደርቃል። |
ወንዞቹም ይገማሉ፤በግብፅ የሚገኙት የአባይ የመስኖ ቦዮች ይጎድላሉ፤ ይደርቃሉም። ቄጠማውና እንግጫው ይበሰብሳል። |
በአባይ ወንዝ መዳረሻ አካባቢ፣ በአባይ ዳር ያለው ተክልእንዲሁም በአባይ ወንዝ አጠገብ ዘር የተዘራበት መሬት ሁሉ ይደርቃል። በነፋስ ተጠርጎ ይወሰዳል፤ ደብዛውም ይጠፋል። |
ዓሣ አጥማጆቹም ያዝናሉ፤ወደ አባይ ወንዝ የዓሣ መንጠቆ የሚወረውሩም ሁሉ ያለቅሳሉ፤በውኃው ላይ የዓሣ ማጥመጃ መረቦችን የሚጥሉም ይመናመናሉ። |
በተነደፈ የተልባ እግር የሚሠሩም ሆኑነጭ ሸማ የሚሠሩ ሸማኔዎች ለኀፍረት ይዳረጋሉ። |
የሽመና ባለሙያዎቿ ይደቆሳሉ፤ቅጥር ሠራተኞቹ ሁሉ ያዝናሉ። |
የጾዓን መኳንንት ሞኞች ናቸው። ጥበበኞች የሆኑ የፈርዖን አማካሪዎች የሚሰጡት ምክር ማስተዋል የጎደለው ነው። ፈርዖንን “እኔ የጥበበኞች ልጅ፣ የጥንት ነገሥታትም ዘር ነኝ”እንዴት ትሉታላችሁ? |
ጥበበኞችህ ታዲያ የት አሉ? የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ስለ ግብፅ የወሰነውን የሚያውቁ ከሆነ ይንገሩህ። |
የጾዓን መኳንንት የሞኝ ሥራ ሠርተዋል፤የኖፍ መኳንንት ተታለዋል፤የነገዶቿ አለቆች ግብፅ እንድትባዝን አድርገዋል። |
ይሖዋ በእሷ ላይ ግራ የመጋባት መንፈስ አፍስሷል፤የሰከረ ሰው በትፋቱ ላይ እንደሚንገዳገድ ሁሉእነሱም ግብፅ በሥራዋ ሁሉ እንድትባዝን አድርገዋል። |
ግብፅ ለራስም ሆነ ለጅራት፣ ለቀንበጥም ሆነ ለእንግጫልታደርገው የምትችለው ምንም ነገር የለም። |
በዚያ ቀን ግብፃውያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በእነሱ ላይ እጁን በዛቻ ስለሚያወዛውዝ ይንቀጠቀጣሉ፤ ይሸበራሉም። |
የይሁዳም ምድር ግብፅን ታሸብራለች። ስለ ምድሪቱ ሲወራ የሚሰሙ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በግብፃውያን ላይ ከወሰነው ውሳኔ የተነሳ በፍርሃት ይርዳሉ። |
በዚያ ቀን በግብፅ ምድር የከነአንን ቋንቋ የሚናገሩና ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ታማኝ እንደሚሆኑ በመሐላ የሚያረጋግጡ አምስት ከተሞች ይኖራሉ። ከእነዚህም መካከል አንዷ ‘የማፍረስ ከተማ’ ተብላ ትጠራለች። |
በዚያ ቀን በግብፅ ምድር መካከል ለይሖዋ መሠዊያ ይሠራል፤ በድንበሯም ላይ ለይሖዋ ዓምድ ይቆማል። |
ይህም በግብፅ ምድር ለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ምልክትና ምሥክር ይሆናል፤ እነሱ ከጨቋኞቻቸው የተነሳ ወደ ይሖዋ ይጮኻሉና፤ እሱም የሚታደጋቸው አዳኝ፣ አዎ ታላቅ አዳኝ ይልክላቸዋል። |
ይሖዋም በግብፃውያን ዘንድ የታወቀ ይሆናል፤ በዚያም ቀን ግብፃውያን ይሖዋን ያውቁታል፤ መሥዋዕትና ስጦታ ያቀርባሉ፤ ለይሖዋም ይሳላሉ፤ የተሳሉትንም ይፈጽማሉ። |
ይሖዋ ግብፅን ይመታታል፤ መትቶ ይፈውሳታል፤ እነሱም ወደ ይሖዋ ይመለሳሉ፤ እሱም ልመናቸውን ሰምቶ ይፈውሳቸዋል። |
በዚያ ቀን ከግብፅ ወደ አሦር የሚወስድ አውራ ጎዳና ይኖራል። ከዚያም አሦር ወደ ግብፅ፣ ግብፅም ወደ አሦር ይመጣል፤ ግብፅና አሦርም በአንድነት አምላክን ያገለግላሉ። |
በዚያ ቀን እስራኤል ሦስተኛ ወገን ሆና ከግብፅና ከአሦር ጋር ትተባበራለች፤ በምድርም መካከል በረከት ትሆናለች፤ |
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ “ሕዝቤ ግብፅ፣ የእጄም ሥራ አሦር፣ ርስቴም እስራኤል የተባረኩ ይሁኑ” ብሎ ይባርካቸዋልና። |
አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፣ክህደት ሳይፈጸምብህ ክህደት የምትፈጽም ወዮልህ! ማጥፋትህን እንዳጠናቀክ አንተም ትጠፋለህ። ክህደት መፈጸምህን እንዳበቃህ ትካዳለህ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየን። በአንተ ተስፋ አድርገናል። በየማለዳው በክንድህ ደግፈን፤አዎ፣ በጭንቅ ጊዜ አዳኛችን ሁን። |
የድምፅህን ነጎድጓድ ሲሰሙ ሕዝቦች ይሸሻሉ። በምትነሳበት ጊዜ ብሔራት ይበታተናሉ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.