text
stringlengths
4
267
ይሖዋ ሆይ፣ እጅህ ከፍ ብሏል፤ እነሱ ግን አላዩትም። ለሕዝብህ ያለህን ቅንዓት በምታሳይበት ጊዜ ያያሉ፤ ለኀፍረትም ይዳረጋሉ። አዎ፣ ለጠላቶችህ የተዘጋጀው እሳት ይበላቸዋል።
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ሰላም ትሰጠናለህ፤ምክንያቱም የሠራነውን ነገር ሁሉያከናወንክልን አንተ ነህ።
ይሖዋ አምላካችን ሆይ፣ ከአንተ ሌላ፣ ሌሎች ጌቶች ገዝተውናል፤እኛ ግን የአንተን ስም ብቻ እንጠራለን።
እነሱ ሞተዋል፤ በሕይወትም አይኖሩም። በሞት ተረተዋል፤ አይነሱም። ታጠፋቸውና ስማቸው ጨርሶ እንዳይነሳ ታደርግ ዘንድትኩረትህን ወደ እነሱ አዙረሃልና።
ሕዝቡን አበዛህ፤ ይሖዋ ሆይ፣ሕዝቡን አበዛህ፤ራስህን አስከበርክ። የምድሪቱን ወሰን ሁሉ እጅግ አሰፋህ።
ይሖዋ ሆይ፣ በተጨነቁ ጊዜ አንተን ፈለጉ፤በገሠጽካቸው ጊዜ በሹክሹክታ ድምፅ በመጸለይ ልባቸውን አፈሰሱ።
ይሖዋ ሆይ፣ ነፍሰ ጡር ሴት ልትወልድ ስትልምጥ እንደሚይዛትና በምጥ ጣር እንደምትጮኽ ሁሉእኛም በአንተ የተነሳ እንዲሁ ሆነናል።
እኛ አርግዘናል፤ ደግሞም አምጠናል፤ይሁንና ነፋስ የወለድን ያህል ሆነናል። ለምድሪቱ መዳን አላስገኘንምእንዲሁም በምድሪቱ ላይ እንዲኖር የተወለደ አንድም ልጅ የለም።
“ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ። የእኔ አስከሬኖች ይነሳሉ። እናንተ በአፈር ውስጥ የምትኖሩ፣ተነሱ፤ በደስታም እልል በሉ! ጠልህ እንደ ማለዳ ጠል ነውና፤ምድርም በሞት የተረቱት ዳግም ሕይወት እንዲያገኙ ታደርጋለች።
ሕዝቤ ሆይ፣ ሂድ ወደ ውስጠኛው ክፍልህ ግባ፤በርህንም ከኋላህ ዝጋ። ቁጣው እስኪያልፍ ድረስለጥቂት ጊዜ ተሸሸግ።
እነሆ፣ ይሖዋ የምድሪቱ ነዋሪ የፈጸመውን በደል ለመፋረድከመኖሪያ ቦታው ይመጣልና፤ምድሪቱም በላይዋ የፈሰሰውን ደም ትገልጣለች፤በላይዋም የተገደሉትን ከዚህ በኋላ አትደብቅም።”
የይሁዳ ነገሥታት በሆኑት በዖዝያ፣ በኢዮዓታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ፦
ሰማያት ሆይ፣ ስሙ፤ ምድር ሆይ፣ አድምጪ፤ይሖዋ እንዲህ ሲል ተናግሯልና፦ “ወንዶች ልጆችን ተንከባክቤ አሳደግኩ፤እነሱ ግን በእኔ ላይ ዓመፁ።
በሬ ጌታውን፣አህያም የባለቤቱን ጋጣ በሚገባ ያውቃል፤እስራኤል ግን እኔን አላወቀም፤የገዛ ሕዝቤም አላስተዋለም።”
ኃጢአተኛ የሆነው ብሔር፣ከባድ በደል የተጫነው ሕዝብ፣የክፉዎች ዘር፣ ብልሹ የሆኑ ልጆች ወዮላቸው! እነሱ ይሖዋን ትተዋል፤የእስራኤልን ቅዱስ አቃለዋል፤ጀርባቸውን ሰጥተውታል።
በዓመፅ ላይ ዓመፅ የምትጨምሩት፣ አሁን ደግሞ ምናችሁ ላይ መመታት ፈልጋችሁ ነው? መላው ራስ ታሟል፤መላው ልብም በበሽታ ተይዟል።
ከእግር ጥፍር አንስቶ እስከ ራስ ፀጉር ድረስ አንድም ጤነኛ የአካል ክፍል የለም። በቁስልና በሰምበር ተሞልቷል፤ እንዲሁም ተተልትሏል፤ቁስሉ አልታከመም ወይም አልታሰረም አሊያም በዘይት አለዘበም።
ምድራችሁ ባድማ ሆኗል። ከተሞቻችሁ በእሳት ጋይተዋል። የባዕድ አገር ሰዎች ዓይናችሁ እያየ ምድራችሁን ይውጣሉ። ባዕዳን እንዳወደሙት ጠፍ መሬት ሆኗል።
የጽዮን ሴት ልጅ በወይን እርሻ ውስጥ እንዳለ መጠለያ፣በኪያር የእርሻ ቦታ እንዳለ ጎጆ፣እንደተከበበችም ከተማ ተትታለች።
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ጥቂት ሰዎች ከጥፋት እንዲተርፉልን ባያደርግ ኖሮእንደ ሰዶም በሆንን፣ገሞራንም በመሰልን ነበር።
እናንተ የሰዶም አምባገነኖች፣ የይሖዋን ቃል ስሙ። እናንተ የገሞራ ሰዎች፣ የአምላካችንን ሕግ አዳምጡ።
“የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምን ይጠቅመኛል?” ይላል ይሖዋ። “የሚቃጠሉ የአውራ በግ መባዎችና የደለቡ እንስሳት ስብ በቅቶኛል፤በወይፈኖች፣ በበግ ጠቦቶችና በፍየሎች ደምደስ አልሰኝም።
በፊቴ ለመቅረብ የምትመጡት፣ይህን እንድታደርጉ፣የቤተ መቅደሴን ግቢ እንድትረግጡ ማን ጠይቋችሁ ነው?
ከንቱ የሆኑትን የእህል መባዎች ከዚህ በኋላ አታምጡ። ዕጣናችሁ በፊቴ አስጸያፊ ነው። የአዲስ ጨረቃ በዓልንና ሰንበትን ታከብራላችሁ፤ ስብሰባም ትጠራላችሁ። በአንድ በኩል የተቀደሱ ጉባኤዎችን እያከበራችሁ በሌላ በኩል የምትፈጽሙትን አስማታዊ ድርጊት መታገሥ አልችልም።
የአዲስ ጨረቃ በዓሎቻችሁንና ሌሎች በዓሎቻችሁን ጠልቻለሁ። ለእኔ ሸክም ሆነውብኛል፤እነሱንም ከመሸከሜ የተነሳ ዝያለሁ።
እጆቻችሁን ስትዘረጉዓይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ። ጸሎት ብታበዙም እንኳአልሰማችሁም፤እጆቻችሁ በደም ተሞልተዋል።
ታጠቡ፤ ራሳችሁንም አንጹ፤ክፉ ሥራችሁን ከፊቴ አስወግዱ፤መጥፎ ድርጊት መፈጸማችሁን አቁሙ።
መልካም ማድረግን ተማሩ፤ ፍትሕን ፈልጉ፤ጨቋኙ እንዲታረም አድርጉ፤አባት የሌለውን ልጅ መብት አስከብሩ፤ለመበለቲቱም ተሟገቱ።”
“ኑና በመካከላችን የተፈጠረውን ችግር ተወያይተን እንፍታ” ይላል ይሖዋ። “ኃጢአታችሁ እንደ ደም ቢቀላእንደ በረዶ ይነጣል፤እንደ ደማቅ ቀይ ጨርቅ ቢቀላምእንደ ነጭ የሱፍ ጨርቅ ይሆናል።
እሺ ብትሉና ብትታዘዙየምድሪቱን መልካም ፍሬ ትበላላችሁ።
እንቢ ብትሉና ብታምፁ ግንሰይፍ ይበላችኋል፤የይሖዋ አፍ ይህን ተናግሯልና።”
ታማኝ የነበረችው ከተማ እንዴት ዝሙት አዳሪ ሆነች! ፍትሕ የሞላባትናጽድቅ የሰፈነባት ነበረች፤አሁን ግን የነፍሰ ገዳዮች ጎሬ ሆናለች።
ብርሽ እንደ ዝቃጭ ሆኗል፤መጠጥሽ በውኃ ተበርዟል።
አለቆችሽ ግትሮችና የሌባ ግብረ አበሮች ናቸው። ሁሉም ጉቦ የሚወዱና እጅ መንሻ የሚያሳድዱ ናቸው። አባት የሌለው ልጅ ፍትሕ እንዲያገኝ አያደርጉም፤የመበለቲቱም አቤቱታ ወደ እነሱ አይደርስም።
ስለዚህ እውነተኛው ጌታ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣የእስራኤል ኃያል አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እንግዲያው ስሙ! ባላጋራዎቼን አጠፋለሁ፤ጠላቶቼንም እበቀላለሁ።
እጄን በአንቺ ላይ አነሳለሁ፤በመርዝ የማጥራት ያህል ቆሻሻሽን አቅልጬ አወጣለሁ፤ዝቃጭሽንም ሁሉ አስወግዳለሁ።
መጀመሪያ ላይ እንደነበረው ፈራጆችሽን፣እንደቀድሞውም አማካሪዎችሽን መልሼ አመጣለሁ። ከዚያ በኋላ የጽድቅ መዲና፣ የታመነች ከተማ ተብለሽ ትጠሪያለሽ።
ጽዮን በፍትሕ፣የሚመለሱት ነዋሪዎቿም በጽድቅ ይቤዣሉ።
ዓመፀኞችና ኃጢአተኞች በአንድ ላይ ይደቅቃሉ፤ይሖዋን የሚተዉም ያከትምላቸዋል።
እናንተ በተመኛችኋቸው ግዙፍ ዛፎች ያፍራሉና፤በመረጣችኋቸው የአትክልት ቦታዎች የተነሳም ትዋረዳላችሁ።
ቅጠሉ እንደጠወለገ ትልቅ ዛፍ፣ውኃም እንደሌለው የአትክልት ቦታ ትሆናላችሁና።
ብርቱውም ሰው እንደ ተልባ እግር ይሆናል፤የሥራውም ውጤት እንደ እሳት ብልጭታ ይሆናል፤ሁለቱም አብረው ይቃጠላሉ፤እሳቱንም ማጥፋት የሚችል ማንም የለም።”
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ፍትሕን ጠብቁ፤ ጽድቅ የሆነውንም አድርጉ፤ማዳኔ በቅርቡ ይመጣልና፤ጽድቄም ይገለጣል።
ይህን የሚያደርግ ሰው፣ደግሞም ይህን አጥብቆ የሚይዝ፣ሰንበትን የሚጠብቅና የማያረክስ፣እንዲሁም ከማንኛውም ዓይነት ክፋት እጁን የሚመልስ የሰው ልጅ ደስተኛ ነው።
ከይሖዋ ጋር የሚቆራኝ የባዕድ አገር ሰው‘ይሖዋ ከሕዝቡ እንደሚለየኝ ጥርጥር የለውም’ አይበል። ጃንደረባም ‘እነሆ፣ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ’ አይበል።”
ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “ሰንበቶቼን ለሚጠብቁ፣ ደስ የሚያሰኘኝን ነገር ለሚመርጡና ቃል ኪዳኔን አጥብቀው ለሚይዙ ጃንደረቦች፣
በቤቴና በቅጥሮቼ ውስጥከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የሚሻል ነገር፣ ይኸውም የመታሰቢያ ሐውልትና ስም እሰጣቸዋለሁ።ለዘላለም የማይጠፋ ስም እሰጣቸዋለሁ።
እሱን ለማገልገል፣ የይሖዋን ስም ለመውደድናየእሱ አገልጋዮች ለመሆንከይሖዋ ጋር የሚቆራኙትን የባዕድ አገር ሰዎች፣ሰንበትን የሚጠብቁትንና የማያረክሱትን፣ቃል ኪዳኔንም አጥብቀው የሚይዙትን ሁሉ፣
ቅዱስ ወደሆነው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤በጸሎት ቤቴም ውስጥ እጅግ እንዲደሰቱ አደርጋቸዋለሁ። የሚያቀርቧቸውም ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያገኛሉ። ቤቴም ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”
የተበተኑትን የእስራኤል ሰዎች የሚሰበስበው ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አስቀድሞ ከተሰበሰቡት በተጨማሪ ሌሎችን ወደ እሱ እሰበስባለሁ።”
እናንተ በሜዳ ያላችሁ አራዊት ሁሉ፣እናንተ በጫካ የምትኖሩ አራዊት ሁሉ፣ ኑና ብሉ።
ጠባቂዎቹ ዕውሮች ናቸው፤ አንዳቸውም አላስተዋሉም። ሁሉም መናገር የማይችሉ ውሾች ናቸው፤ መጮኽ አይችሉም። ተጋድመው ያለከልካሉ፤ እንቅልፍም ይወዳሉ።
በቀላሉ የማይጠግቡ ውሾች ናቸው፤ጠገብኩ ማለትን አያውቁም። ማስተዋል የሌላቸው እረኞች ናቸው። ሁሉም በገዛ ራሳቸው መንገድ ሄደዋል፤እያንዳንዳቸው አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሻሉ፤ እንዲህም ይላሉ፦
“ኑ! የወይን ጠጅ ላምጣናእስኪወጣልን ድረስ እንጠጣ። ነገም እንደ ዛሬ ይሆናል፤ እንዲያውም በጣም የተሻለ ይሆናል።”
ንጉሥ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ዘምቶ ያዛቸው።
ከዚያም የአሦር ንጉሥ፣ ራብሻቁን ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ፣ በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ላከው። እነሱም ወደ ልብስ አጣቢው እርሻ በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ በሚገኘው በላይኛው ኩሬ የውኃ መውረጃ ቦይ አጠገብ ቆሙ።
ከዚያም የቤቱ ኃላፊ የሆነው የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣ ጸሐፊው ሸብና እንዲሁም ታሪክ ጸሐፊው የአሳፍ ልጅ ዮአህ ወደ እሱ መጡ።
ራብሻቁም እንዲህ አላቸው፦ “እስቲ ሕዝቅያስን እንዲህ በሉት፦ ‘ታላቁ ንጉሥ፣ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ “ለመሆኑ እንዲህ እንድትተማመን ያደረገህ ምንድን ነው?
‘የጦር ስልትና ለመዋጋት የሚያስችል ኃይል አለኝ’ ትላለህ፤ ይሁንና ይህ ከንቱ ወሬ ነው። ለመሆኑ በእኔ ላይ ለማመፅ የደፈርከው በማን ተማምነህ ነው?
እነሆ፣ ሰው ቢመረኮዘው እጁ ላይ ሊሰነቀርና ሊወጋው ከሚችለው ከዚህ ከተቀጠቀጠ ሸምበቆ፣ ከግብፅ ድጋፍ አገኛለሁ ብለህ ተማምነሃል። የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ለሚታመኑበት ሁሉ እንዲሁ ነው።
‘እኛ የምንታመነው በአምላካችን በይሖዋ ነው’ የምትለኝ ከሆነ ደግሞ፣ ሕዝቅያስ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ‘መስገድ ያለባችሁ በዚህ መሠዊያ ፊት ነው’ ብሎ የእሱን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎችና መሠዊያዎች አስወግዶ የለም?”’
በል እስቲ፣ አሁን ከጌታዬ ከአሦር ንጉሥ ጋር ተወራረድ፦ ጋላቢዎች ማግኘት የምትችል ከሆነ 2,000 ፈረሶች እሰጥሃለሁ።
አንተ የምትታመነው በግብፅ ሠረገሎችና ፈረሰኞች ነው፤ ታዲያ ከጌታዬ አገልጋዮች መካከል ዝቅተኛ ደረጃ ያለውን አንዱን አለቃ እንኳ እንዴት መመከት ትችላለህ?
ለመሆኑ ይህን ምድር ለማጥፋት የመጣሁት ይሖዋ ሳይፈቅድልኝ ይመስልሃል? ይሖዋ ራሱ ‘በዚህ ምድር ላይ ዘምተህ አጥፋው’ ብሎኛል።”
በዚህ ጊዜ ኤልያቄም፣ ሸብና እና ዮአህ ራብሻቁን እንዲህ አሉት፦ “እባክህ፣ እኛ አገልጋዮችህ ቋንቋውን ስለምናውቅ በአረማይክ ቋንቋ አናግረን፤ በቅጥሩ ላይ ያለው ሕዝብ በሚሰማው በአይሁዳውያን ቋንቋ አታነጋግረን።”
ራብሻቁ ግን እንዲህ አለ፦ “ጌታዬ ይህን ቃል እንድናገር የላከኝ ለጌታህና ለአንተ ብቻ ነው? ከእናንተ ጋር የገዛ ራሳቸውን እዳሪ ለሚበሉትና የገዛ ራሳቸውን ሽንት ለሚጠጡት በቅጥሩ ላይ ለተቀመጡት ሰዎች ጭምር አይደለም?”
ከዚያም ራብሻቁ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ በአይሁዳውያን ቋንቋ እንዲህ አለ፦ “የታላቁን ንጉሥ፣ የአሦርን ንጉሥ ቃል ስሙ።
ንጉሡ እንዲህ ይላል፦ ‘ሕዝቅያስ አያታላችሁ፤ እሱ ሊታደጋችሁ አይችልምና።
ደግሞም ሕዝቅያስ “ይሖዋ በእርግጥ ይታደገናል፤ ይህችም ከተማ በአሦር ንጉሥ እጅ አትወድቅም” እያለ በይሖዋ እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።
ሕዝቅያስን አትስሙት፤ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላልና፦ “ከእኔ ጋር ሰላም ፍጠሩ፤ እጃችሁንም ስጡ፤ እያንዳንዳችሁም ከራሳችሁ ወይንና ከራሳችሁ በለስ ትበላላችሁ፤ ከራሳችሁም የውኃ ጉድጓድ ትጠጣላችሁ፤
ይህም የሚሆነው መጥቼ የእናንተን ምድር ወደምትመስለው፣ እህልና አዲስ ወይን፣ ዳቦና የወይን እርሻ ወደሚገኝባት ምድር እስክወስዳችሁ ድረስ ነው።
ሕዝቅያስ ‘ይሖዋ ይታደገናል’ በማለት አያታላችሁ። ከብሔራት አማልክት መካከል ምድሩን ከአሦር ንጉሥ እጅ ያስጣለ አለ?
የሃማትና የአርጳድ አማልክት የት አሉ? የሰፋርዊም አማልክትስ የት አሉ? ሰማርያን ከእጄ ማስጣል ችለዋል?
ከእነዚህ አገሮች አማልክት ሁሉ ምድሩን ከእጄ ማስጣል የቻለ የትኛው ነው? ታዲያ ይሖዋ ኢየሩሳሌምን ከእጄ ሊያስጥላት ይችላል?”’”
እነሱ ግን ንጉሡ “ምንም መልስ አትስጡት” ብሎ አዝዞ ስለነበር ዝም አሉ፤ አንድም ቃል አልመለሱለትም።
ይሁንና የቤቱ አስተዳዳሪ የሆነው የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣ ጸሐፊው ሸብና እንዲሁም ታሪክ ጸሐፊው የአሳፍ ልጅ ዮአህ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፤ ራብሻቁ ያለውንም ነገሩት።
በዖዝያ ልጅ፣ በኢዮዓታም ልጅ በይሁዳ ንጉሥ በአካዝ ዘመን፣ የሶርያው ንጉሥ ረጺንና የእስራኤል ንጉሥ የሆነው የረማልያህ ልጅ ፋቁሄ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፤ እሱ ግን ድል ሊያደርጋት አልቻለም።
የዳዊት ቤት፣ “ሶርያ ከኤፍሬም ጋር ግንባር ፈጥራለች” የሚል ወሬ ደረሰው። በዚህ ጊዜ የአካዝም ሆነ የሕዝቡ ልብ በነፋስ እንደሚናወጥ የዱር ዛፍ መናወጥ ጀመረ።
ከዚያም ይሖዋ ኢሳይያስን እንዲህ አለው፦ “እባክህ፣ አንተና ልጅህ ሸአርያሹብ ከአካዝ ጋር ለመገናኘት ወደ አጣቢው እርሻ በሚወስደው መንገድ አጠገብ ወዳለው ወደ ላይኛው ኩሬ የውኃ መውረጃ ቦይ ጫፍ ውጡ።
እንዲህም በለው፦ ‘አይዞህ፣ ተረጋጋ። በእነዚህ ከእሳት ተርፈው በሚጤሱ ሁለት የግንድ ጉማጆች ማለትም በሶርያ ንጉሥ በረጺንና በረማልያህ ልጅ ኃይለኛ ቁጣ የተነሳ አትፍራ፤ ልብህም አይደንግጥ።
ሶርያ ከኤፍሬምና ከረማልያህ ልጅ ጋር እንዲህ ብላ አሲራብሃለች፦
“በይሁዳ ላይ እንዝመትና እንበታትነው፤ በቁጥጥራችንም ሥር እናውለው፤ የታብኤልንም ልጅ እናንግሥበት።”
“‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሴራ አይሳካም፤ደግሞም አይፈጸምም።
የሶርያ ራስ ደማስቆ፣የደማስቆ ራስ ደግሞ ረጺን ነውና። ኤፍሬም በ65 ዓመት ውስጥብትንትኑ ወጥቶ ሕዝብ መሆኑ ይቀራል።
የኤፍሬም ራስ ሰማርያ ነው፤የሰማርያም ራስ የረማልያህ ልጅ ነው። ጠንካራ እምነት ከሌላችሁጸንታችሁ መቆም አትችሉም።”’”
ከዚያም ይሖዋ አካዝን እንዲህ አለው፦
“አምላክህ ይሖዋ ምልክት እንዲያሳይህ ጠይቅ፤ ምልክቱም እንደ መቃብር ጥልቅ የሆነ ወይም እንደ ሰማይ ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል።”
አካዝ ግን “አልጠይቅም፤ ይሖዋንም አልፈትንም” አለ።
ከዚያም ኢሳይያስ እንዲህ አለ፦ “የዳዊት ቤት ሆይ፣ እባካችሁ ስሙ። የሰውን ትዕግሥት መፈታተናችሁ አንሶ የአምላክንም ትዕግሥት ልትፈታተኑ ትፈልጋላችሁ?
በመሆኑም ይሖዋ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፦ እነሆ፣ ወጣቷ ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ አማኑኤል ብላም ትጠራዋለች።
ክፉውን መጥላትና መልካሙን መምረጥ በሚችልበት ጊዜ ቅቤና ማር ይበላል።
ልጁ ክፉውን መጥላትና መልካሙን መምረጥ ከመቻሉ በፊት በጣም የምትፈራቸው የሁለቱ ነገሥታት ምድር ጨርሶ የተተወ ይሆናል።
ይሖዋ፣ ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ጊዜ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ ዘመን በአንተ፣ በሕዝብህና በአባትህ ቤት ላይ ያመጣል፤ የአሦርን ንጉሥ ያመጣልና።
“በዚያ ቀን ይሖዋ በግብፅ፣ ርቀው በሚገኙት የአባይ ጅረቶች ያሉትን ዝንቦች፣ በአሦርም ምድር ያሉትን ንቦች በፉጨት ይጠራል፤
ሁሉም መጥተው ጥልቅ በሆኑ ሸለቆዎች፣ በየዓለቱ ንቃቃት፣ በቁጥቋጦዎች ሁሉና ውኃ ባሉባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ ይሰፍራሉ።
“በዚያም ቀን ይሖዋ በወንዙ አካባቢ ከሚገኘው ቦታ በተከራየው ምላጭ ይኸውም በአሦር ንጉሥ አማካኝነት ራሱንና የእግሩን ፀጉር ይላጨዋል፤ ጢሙንም ሙልጭ አድርጎ ያስወግደዋል።
“በዚያም ቀን አንድ ሰው ከመንጋው መካከል አንዲት ጊደርና ሁለት በጎች በሕይወት ያተርፋል።
በብዛት ከሚገኘው ወተት የተነሳም ቅቤ ይበላል፤ በምድሪቱ መካከል የቀረው ሰው ሁሉ ቅቤና ማር ይበላል።
“በዚያ ቀን 1,000 የብር ሰቅል የሚያወጣ 1,000 የወይን ተክል ይገኝበት የነበረው ቦታ ሁሉ ቁጥቋጦና አረም ይወርሰዋል።
ምድሪቱ በቁጥቋጦና በአረም ስለምትሸፈን ሰዎች ወደዚያ የሚሄዱት ቀስትና ደጋን ይዘው ነው።