text stringlengths 4 267 |
|---|
በአንድ ወቅት በመቆፈሪያ ተመንጥረውና ከአረም ጸድተው የነበሩ ተራሮች ሁሉ ቁጥቋጦና አረም ስለሚወርሳቸው ወደዚያ መሄድ ትፈራለህ፤ እነዚህ ቦታዎች በሬዎች የሚሰማሩባቸውና በጎች የሚፈነጩባቸው ይሆናሉ።” |
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አምላኬ ነህ። ድንቅ ነገሮችን ስላደረግክናከጥንት ዘመን ጀምሮ ያሰብካቸውን ነገሮችበታማኝነትና እምነት በሚጣልበት መንገድ ስለፈጸምክከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አወድሳለሁ። |
ከተማዋን የድንጋይ ቁልል፣የተመሸገችውንም ከተማ የፍርስራሽ ክምር አድርገሃልና። የባዕዳኑ ማማ፣ ከተማ መሆኑ አብቅቶለታል፤ከተማዋ በምንም ዓይነት ዳግመኛ አትገነባም። |
ከዚህም የተነሳ ኃያል የሆነ ሕዝብ ያከብርሃል፤የጨቋኝ ብሔራት ከተማም ትፈራሃለች። |
ለችግረኛው ምሽግ ሆነሃልና፤ለድሃውም ከደረሰበት ጭንቀት መሸሸጊያ፣ከውሽንፍርም መጠለያ፣ከፀሐይ ንዳድም ጥላ ሆነሃል። የጨቋኞች ቁጣ ከግንብ ጋር እንደሚላተም ውሽንፍር በሚሆንበት ጊዜ ጥበቃ ታደርጋለህ፤ |
ውኃ በተጠማ ምድር እንዳለ ሙቀትየባዕዳንን ሁከት ጸጥ ታደርጋለህ። ሙቀት በደመና ጥላ እንደሚበርድ ሁሉየጨቋኞችም ዝማሬ ጸጥ ረጭ ይላል። |
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ በዚህ ተራራ ላይ ለሕዝቦች ሁሉምርጥ ምግቦች የሚገኙበት ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ፣መቅኒ የሞላባቸው ምርጥ ምግቦችእንዲሁም የተጣራና ጥሩ የወይን ጠጅ የሚቀርቡበት ታላቅ ግብዣ ያደርጋል። |
በዚህ ተራራ ላይ ሕዝቦችን ሁሉ የሸፈነውን ከፈንእንዲሁም ብሔራትን ሁሉ ተብትቦ የያዘውን መሸፈኛ ያስወግዳል። |
ሞትን ለዘላለም ይውጣል፤ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል። በሕዝቡ ላይ የደረሰውን ነቀፋ ከመላው ምድር ያስወግዳል፤ይሖዋ ራሱ ይህን ተናግሯልና። |
በዚያም ቀን እንዲህ ይላሉ፦ “እነሆ፣ አምላካችን ይህ ነው! እሱን ተስፋ አድርገናል፤እሱም ያድነናል። ይሖዋ ይህ ነው! እሱን ተስፋ አድርገናል። በእሱ ማዳን ደስ ይበለን፤ ሐሴትም እናድርግ።” |
የይሖዋ እጅ በዚህ ተራራ ላይ ያርፋልና፤ጭድ በፍግ ክምር ላይ እንደሚረገጥሞዓብም በስፍራው እንዲሁ ይረገጣል። |
አንድ ዋናተኛ በሚዋኝበት ጊዜ በእጆቹ ውኃውን እንደሚመታእሱም እጁን ዘርግቶ ሞዓብን ይመታዋል፤በእጆቹ በጥበብ በመምታትትዕቢቱን ያበርድለታል። |
የተመሸገውን ከተማከረጃጅም የመከላከያ ግንቦችህ ጋር ያፈርሳል፤ምድር ላይ ጥሎ ከአፈር ይደባልቀዋል። |
የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ በራእይ ያየው በባቢሎን ላይ የተላለፈ ፍርድ፦ |
“በተራቆተ ዓለታማ ተራራ ላይ ምልክት አቁሙ። ታላላቅ ሰዎች ወደሚገቡባቸው በሮች እንዲመጡድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጥሯቸው፤ እጃችሁንም አውለብልቡ። |
እኔ ለሾምኳቸው ትእዛዝ ሰጥቻለሁ። ቁጣዬን ለመግለጥበኩራት ሐሴት የሚያደርጉትን ተዋጊዎቼን ጠርቻለሁ። |
ስሙ! በተራሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ ያለየብዙ ሰዎች ድምፅ ይሰማል! አዳምጡ! አንድ ላይ የተሰበሰቡ መንግሥታትናብሔራት ሁካታ ይሰማል! የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሠራዊቱን ለጦርነት አሰልፏል። |
ይሖዋና የቁጣው መሣሪያዎችመላ ምድሪቱን ለመደምሰስከሩቅ አገር፣ከሰማያትም ዳርቻ እየመጡ ነው። |
የይሖዋ ቀን ቀርቧልና ዋይ ዋይ በሉ! በዚያ ቀን ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ ዘንድ ጥፋት ይመጣል። |
ከዚህም የተነሳ እጆች ሁሉ ይዝላሉ፤የሰዎችም ልብ ሁሉ በፍርሃት ይቀልጣል። |
ሰዎቹ እጅግ ተሸብረዋል። ምጥ እንደያዛት ሴትብርክና ሥቃይ ይዟቸዋል። እርስ በርሳቸው በታላቅ ድንጋጤ ይተያያሉ፤ፊታቸው በጭንቀት ቀልቷል። |
እነሆ፣ የይሖዋ ቀን ምድሪቱን አስፈሪ ቦታ ለማድረግናበምድሪቱ ላይ ያሉትን ኃጢአተኞች ለማጥፋትበንዴትና በታላቅ ቁጣጨካኝ ሆኖ እየመጣ ነው። |
የሰማያት ከዋክብትና የኅብረ ከዋክብት ስብስቦቻቸውብርሃን አይሰጡም፤ፀሐይ ስትወጣ ትጨልማለች፤ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም። |
ምድሪቱን ስለ ክፋቷ፣ክፉዎችንም ስለ በደላቸው እቀጣለሁ። የእብሪተኞችን ኩራት አጠፋለሁ፤የጨቋኞችንም ትዕቢት አዋርዳለሁ። |
ሟች የሆነውን ሰው ከጠራ ወርቅ፣ሰዎችንም ከኦፊር ወርቅ ይበልጥ ብርቅ አደርጋለሁ። |
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ቁጣ በሚነድበት ቀን፣በታላቅ ቁጣ ሰማይን አናውጣለሁ፤ምድርንም ከቦታዋ አናጋለሁ። |
እንደሚታደን የሜዳ ፍየል፣ እረኛም እንደሌለው መንጋእያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል፤እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል። |
የተገኘ ሁሉ ይወጋል፤የተያዘም ሁሉ በሰይፍ ይወድቃል። |
ልጆቻቸው ዓይናቸው እያየ ይጨፈጨፋሉ፤ቤታቸው ይዘረፋል፤ሚስቶቻቸውም ተገደው ይደፈራሉ። |
እነሆ፣ ለብር ደንታ የሌላቸውን፣በወርቅም ደስ የማይሰኙትንሜዶናውያንን አስነሳባቸዋለሁ። |
ቀስታቸው ወጣቶችን ይፈጃል፤ለማህፀን ፍሬ አያዝኑም፤ለልጆችም አይራሩም። |
ከመንግሥታትም ሁሉ እጅግ የከበረችው፣የከለዳውያን ውበትና ኩራት የሆነችው ባቢሎን፣አምላክ እንደገለበጣቸው እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ትሆናለች። |
ከዚያ በኋላ የሚቀመጥባት አይኖርም፤እንዲሁም ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ የመኖሪያ ቦታ አትሆንም። በዚያም ዓረብ ድንኳኑን አይተክልም፤እረኞችም መንጎቻቸውን በዚያ አያሳርፉም። |
የበረሃ ፍጥረታት በዚያ ይተኛሉ፤ቤቶቻቸው በጉጉቶች ይሞላሉ። ሰጎኖች በዚያ ይኖራሉ፤የዱር ፍየሎችም በዚያ ይፈነጫሉ። |
የሚያላዝኑ ፍጥረታት በማማዎቿ፣ቀበሮዎችም በሚያማምሩ ቤተ መንግሥቶቿ ውስጥ ሆነው ይጮኻሉ። ጊዜዋ ቀርቧል፤ ቀኖቿም አይራዘሙም።” |
“እናንተ ጽድቅን የምትከታተሉ፣ይሖዋንም የምትፈልጉ ስሙኝ። ተፈልፍላችሁ የወጣችሁበትን ዓለት፣ተቆፍራችሁ የወጣችሁበትንም ካባ ተመልከቱ። |
አባታችሁን አብርሃምን፣የወለደቻችሁንም ሣራን ተመልከቱ። እሱ በጠራሁት ጊዜ ብቻውን ነበርና፤እኔም ባረክሁት፤ ደግሞም አበዛሁት። |
ይሖዋ ጽዮንን ያጽናናታልና። ፍርስራሾቿን ሁሉ ያጽናናል፤ምድረ በዳዋንም እንደ ኤደን፣በረሃማ ሜዳዋንም እንደ ይሖዋ የአትክልት ስፍራ ያደርጋል። በእሷም ውስጥ ሐሴትና ታላቅ ደስታእንዲሁም ምስጋናና ደስ የሚያሰኝ መዝሙር ይገኛሉ። |
ሕዝቤ ሆይ፣ በጥሞና አዳምጡኝ፤አንተም የእኔ ብሔር፣ ጆሮህን ስጠኝ። ሕግ ከእኔ ይወጣልና፤የፍትሕ እርምጃዬም ለሕዝቦች እንደ ብርሃን ጸንቶ እንዲቆም አደርጋለሁ። |
ጽድቄ ቀርቧል። ማዳኔ ወደ እናንተ ይመጣል፤ክንዴም በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል። ደሴቶች በእኔ ተስፋ ያደርጋሉ፤ክንዴንም ይጠባበቃሉ። |
ዓይኖቻችሁን ወደ ሰማያት አንሱ፤ወደታችም ወደ ምድር ተመልከቱ። ሰማያት እንደ ጭስ በነው ይጠፋሉና፤ምድርም እንደ ልብስ ታረጃለች፤ነዋሪዎቿም እንደ ትንኝ ይረግፋሉ። ማዳኔ ግን ለዘላለም ይኖራል፤ጽድቄም ፈጽሞ አይከስምም። |
እናንተ ጽድቅን የምታውቁ፣ሕጌንም በልባችሁ ያኖራችሁ ሰዎች፣ ስሙኝ። ሟች የሆኑ ሰዎች የሚሰነዝሩትን ትችት አትፍሩ፤ስድባቸውም አያሸብራችሁ። |
ብል እንደ ልብስ ይበላቸዋልና፤የልብስ ብል እንደ ሱፍ ጨርቅ ይበላቸዋል። ሆኖም ጽድቄ ለዘላለም፣ማዳኔም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።” |
የይሖዋ ክንድ ሆይ፣ተነስ! ተነስ! ብርታትንም ልበስ! ከረጅም ጊዜ በፊት፣ በጥንቶቹ ትውልዶች ዘመን እንደሆነው ተነስ። ረዓብን ያደቀከው፣ግዙፉንም የባሕር ፍጥረት የወጋኸው አንተ አይደለህም? |
ባሕሩን፣ የተንጣለለውን የጥልቁን ውኃ ያደረቅከው አንተ አይደለህም? የተቤዠሃቸው ሰዎች እንዲሻገሩ ጥልቁን ባሕር መንገድ ያደረግከው አንተ አይደለህም? |
ይሖዋ የዋጃቸው ይመለሳሉ። በእልልታ ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ማብቂያ የሌለውንም ደስታ እንደ አክሊል ይጎናጸፋሉ። ሐሴት ያደርጋሉ፤ ታላቅ ደስታም ያገኛሉ፤ሐዘንና ሲቃም ከእነሱ ይሸሻሉ። |
“የማጽናናችሁ እኔ ራሴ ነኝ። ሟች የሆነውን ሰው፣እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ የምትፈሪው ለምንድን ነው? |
ሰማያትን የዘረጋውንና የምድርን መሠረት የጣለውንሠሪህን ይሖዋን የምትረሳው ለምንድን ነው? ደግሞም ጨቋኙ ሊያጠፋህ የተዘጋጀ ይመስልከእሱ ቁጣ የተነሳ ቀኑን ሙሉ በፍርሃት ተውጠህ ነበር። ታዲያ አሁን የጨቋኙ ቁጣ የት አለ? |
በሰንሰለት ታስሮ ያጎነበሰው እስረኛ ቶሎ ይፈታል፤ሞትን አያይም፤ ወደ ጉድጓድም አይወርድም፤የሚበላውም ነገር አያጣም። |
ባሕሩን የማናውጥና ኃይለኛ ማዕበል የማስነሳ፣እኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ፤ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው። |
ሰማያትን እዘረጋና የምድርን መሠረት እጥል ዘንድ፣ጽዮንንም ‘አንቺ ሕዝቤ ነሽ’ እል ዘንድቃሌን በአፍህ አኖራለሁ፤በእጄም ጥላ እጋርድሃለሁ። |
ከይሖዋ እጅ የቁጣውን ጽዋ የጠጣሽኢየሩሳሌም ሆይ፣ ተነሺ! ተነሺ! ቁሚ። ዋንጫውን ጠጥተሻል፤የሚያንገዳግደውን ጽዋ ጨልጠሻል። |
ከወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ሁሉ መካከል አንድም የሚመራት የለም፤ካሳደገቻቸውም ወንዶች ልጆች ሁሉ መካከል እጇን ይዞ የወሰዳት ማንም የለም። |
እነዚህ ሁለት ነገሮች ደርሰውብሻል። ማን ያስተዛዝንሻል? ጥፋትና ውድመት እንዲሁም ረሃብና ሰይፍ መጥቶብሻል! ማንስ ያጽናናሻል? |
ወንዶች ልጆችሽ ራሳቸውን ስተዋል። በመረብ እንደተያዘ የዱር በግበየመንገዱ ማዕዘን ላይ ይተኛሉ። የይሖዋ ቁጣ፣ የአምላክሽም ተግሣጽ ሙሉ በሙሉ ወርዶባቸዋል።” |
ስለዚህ አንቺ የተጎሳቆልሽና ያለወይን ጠጅ የሰከርሽ ሴት ሆይ፣እባክሽ ይህን ስሚ። |
ለሕዝቡ የሚሟገተው ጌታሽና አምላክሽ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ የሚያንገዳግደውን ጽዋ፣ ይኸውም ዋንጫውን፣የቁጣዬን ጽዋ ከእጅሽ እወስዳለሁ፤ከእንግዲህ ዳግመኛ አትጠጪም። |
ጽዋውን ‘በላይሽ ላይ እንድንሻገር አጎንብሺልን!’ ባሉሽ፣አንቺን በሚያሠቃዩት እጅ ላይ አደርገዋለሁ፤ አንቺም ጀርባሽን እንደ መሬት፣እንደሚሄዱበትም መንገድ አደረግሽላቸው።” |
“አንቺ ያልወለድሽ መሃን ሴት፣ እልል በይ! አንቺ አምጠሽ የማታውቂ ሴት፣ ደስ ይበልሽ፤ በደስታም ጩኺ፤የተተወችው ሴት ወንዶች ልጆች፣ባል ካላት ሴት ወንዶች ልጆች ይልቅ በዝተዋልና” ይላል ይሖዋ። |
“የድንኳንሽን ቦታ አስፊ። ታላቅ የሆነውን የማደሪያ ድንኳንሽን ሸራዎች ዘርጊ። ፈጽሞ አትቆጥቢ፤ የድንኳንሽን ገመዶች አስረዝሚ፤ካስማዎችሽንም አጠንክሪ። |
በቀኝም ሆነ በግራ ትስፋፊያለሽና። ዘሮችሽ ብሔራትን ይወርሳሉ፤ባድማ በሆኑትም ከተሞች ውስጥ ይኖራሉ። |
ኀፍረት ስለማይደርስብሽ አትፍሪ፤ለሐዘን ስለማትዳረጊም አትሸማቀቂ። በልጅነትሽ ዘመን የደረሰብሽን ኀፍረት ትረሺዋለሽና፤መበለትነትሽ ያስከተለብሽን ውርደትም ከእንግዲህ አታስታውሽም።” |
“ታላቁ ሠሪሽ ባልሽ ነውና፤ስሙም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው፤የሚቤዥሽም የእስራኤል ቅዱስ ነው። እሱም የምድር ሁሉ አምላክ ተብሎ ይጠራል። |
ይሖዋ የተተወችና በሐዘን የተደቆሰች ሚስት፣ደግሞም በልጅነቷ አግብታ፣ ከጊዜ በኋላ የተጠላች ሚስት እንደሆንሽ ቆጥሮ ጠርቶሻልና” ይላል አምላክሽ። |
“ለአጭር ጊዜ ተውኩሽ፤ሆኖም በታላቅ ምሕረት መልሼ እሰበስብሻለሁ። |
በቁጣ ጎርፍ ለጥቂት ጊዜ ፊቴን ከአንቺ ሰውሬ ነበር፤ሆኖም በዘላለማዊ ታማኝ ፍቅር ምሕረት አሳይሻለሁ” ይላል የሚቤዥሽ ይሖዋ። |
“ይህ ለእኔ እንደ ኖኅ ዘመን ነው። የኖኅ ውኃ ምድርን ዳግመኛ አያጥለቀልቅም ብዬ እንደማልኩ ሁሉአንቺንም ከእንግዲህ ላለመቆጣትም ሆነ ላለመገሠጽ እምላለሁ። |
ተራሮች ከቦታቸው ሊወገዱ፣ኮረብቶችም ሊናወጡ ይችላሉ፤ይሁንና ታማኝ ፍቅሬ ከአንቺ አይለይም፤የሰላም ቃል ኪዳኔም አይናጋም” ይላል ምሕረት የሚያሳይሽ ይሖዋ። |
“አንቺ የተጎሳቆልሽ፣ በአውሎ ነፋስ የተናወጥሽና ማጽናኛ ያላገኘሽ ሴት ሆይ፣እነሆ ድንጋዮችሽን በኃይለኛ ማጣበቂያ እገነባለሁ፤መሠረትሽንም በሰንፔር እሠራለሁ። |
መጠበቂያ ማማዎችሽን በሩቢ ድንጋዮች፣የከተማሽንም በሮች በሚያብረቀርቁ ድንጋዮች፣ወሰኖችሽንም ሁሉ በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ። |
ልጆችሽም ሁሉ ከይሖዋ የተማሩ ይሆናሉ፤የልጆችሽም ሰላም ብዙ ይሆናል። |
በጽድቅ ጽኑ ሆነሽ ትመሠረቺያለሽ። ጭቆና ከአንቺ ይርቃል፤ምንም ነገር አትፈሪም፤ የሚያሸብርሽም ነገር አይኖርም፤ወደ አንቺ አይቀርብምና። |
ማንም ጥቃት ቢሰነዝርብሽእኔ አዝዤው አይደለም። ጥቃት የሚሰነዝርብሽ ሁሉ ከአንቺ የተነሳ ይወድቃል።” |
“እነሆ፣ የከሰል እሳቱን በወናፍ የሚያናፋውንየእጅ ጥበብ ባለሙያ የፈጠርኩት እኔ ነኝ፤የሚያከናውነውም ሥራ የጦር መሣሪያ ያስገኛል። ደግሞም ጥፋት እንዲያደርስ አጥፊውን ሰው የፈጠርኩት እኔ ራሴ ነኝ። |
አንቺን ለማጥቃት የተሠራ ማንኛውም መሣሪያ ይከሽፋል፤አንቺን ለመክሰስ የሚነሳን ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የይሖዋ አገልጋዮች ውርሻ ይህ ነው፤ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው” ይላል ይሖዋ። |
ይህ ከኤዶም የሚመጣው፣ደማቅ ቀለም ያለው ልብስ ለብሶ ከቦስራ የሚገሰግሰው ማን ነው?ይህ እጅግ ያማረ ልብስ ለብሶናበታላቅ ኃይል ተሞልቶ የሚራመደው ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር፣ለማዳን የሚያስችል ታላቅ ኃይል ያለኝ እኔ ነኝ።” |
መጎናጸፊያህ የቀላውናልብሶችህ በመጭመቂያ ውስጥ ወይን እንደሚረግጥ ሰው ልብስ የሆኑት ለምንድን ነው? |
“በወይን መጭመቂያው ውስጥ ወይኑን ብቻዬን ረገጥኩ። ከሕዝቦች መካከል ከእኔ ጋር ማንም አልነበረም። በቁጣዬም ረጋገጥኳቸው፤በታላቅ ቁጣዬም ጨፈላለቅኳቸው። ደማቸውም ልብሶቼ ላይ ተረጨ፤ልብሴንም ሁሉ በከልኩ። |
የምበቀልበት ቀን በልቤ ውስጥ ነውና፤የምቤዥበትም ዓመት ደርሷል። |
ተመለከትኩ፤ ሆኖም እርዳታ የሚሰጥ አልነበረም፤ማንም ድጋፍ ባለመስጠቱ ደነገጥኩ። ስለዚህ ክንዴ መዳን አስገኘልኝ፤የገዛ ቁጣዬም ድጋፍ ሆነልኝ። |
ሕዝቦችን በቁጣዬ ረጋገጥኩ፤በታላቅ ቁጣዬም አሰከርኳቸው፤ደማቸውንም በምድር ላይ አፈሰስኩ።” |
ይሖዋ በምሕረቱና ታላቅ በሆነው ታማኝ ፍቅሩለእኛ ባደረገልን ነገሮች ሁሉይኸውም ለእስራኤል ቤት ባደረጋቸው በርካታ መልካም ነገሮች የተነሳየይሖዋን የታማኝ ፍቅር መግለጫዎች፣ደግሞም ሊወደሱ የሚገባቸውን የይሖዋን ሥራዎች እናገራለሁ። |
እሱ እንዲህ ብሏልና፦ “እነሱ በእርግጥ ሕዝቤ፣ የማይከዱ ወንዶች ልጆች ናቸው።” ስለዚህ አዳኝ ሆነላቸው። |
በጭንቃቸው ሁሉ እሱ ተጨነቀ። የግል መልእክተኛውም አዳናቸው። እሱ በፍቅሩና በርኅራኄው ተቤዣቸው፤በቀድሞውም ዘመን ሁሉ አነሳቸው እንዲሁም ተሸከማቸው። |
እነሱ ግን ዓመፁ፤ ቅዱስ መንፈሱንም አሳዘኑ። በዚህ ጊዜ ጠላት ሆነባቸው፤ደግሞም ተዋጋቸው። |
እነሱም የጥንቱን ዘመን፣አገልጋዩ ሙሴ የኖረበትን ጊዜ አስታወሱ፦ “ከመንጋው እረኞች ጋር ከባሕሩ ያወጣቸው የት አለ? በእሱ ውስጥ ቅዱስ መንፈሱን ያኖረው፣ |
የከበረ ክንዱ ከሙሴ ቀኝ እጅ ጋር እንዲሄድ ያደረገው፣ለራሱ ዘላለማዊ ስም ለማትረፍውኃዎቹን በፊታቸው የከፈለው፣ |
አውላላ ሜዳ ላይ እንዳለ ፈረስ፣በሚናወጡ ውኃዎች መካከልሳይደናቀፉ እንዲሄዱ ያደረገው የት አለ? |
የከብት መንጋ ወደ ሸለቋማ ሜዳ ሲወርድ እንደሚሆነው፣የይሖዋ መንፈስ አሳረፋቸው።” ለራስህ የከበረ ስም ለማትረፍ ስትልሕዝብህን የመራኸው በዚህ መንገድ ነው። |
ከሰማይ ተመልከት፤ከፍ ካለው የቅድስናና የክብር መኖሪያህም ሆነህ እይ። ቅንዓትህና ታላቅ ኃይልህ፣የሚንሰፈሰፈው አንጀትህና ምሕረትህ የት አለ? እነዚህን ነገሮች ነፍገኸኛል። |
አንተ አባታችን ነህና፤አብርሃም ባያውቀን፣እስራኤልም ባያስታውሰን እንኳይሖዋ ሆይ፣ አንተ አባታችን ነህ። ስምህም ከጥንት ዘመን ጀምሮ “እኛን የተቤዠ” የሚል ነው። |
ይሖዋ ሆይ፣ ከመንገዶችህ ወጥተን እንድንቅበዘበዝ የፈቀድከው ለምንድን ነው? አንተን እንዳንፈራ ልባችን እንዲደነድን የፈቀድከው ለምንድን ነው? ስለ አገልጋዮችህ፣ርስትህ ስለሆኑትም ነገዶች ስትል ተመለስ። |
ቅዱስ ሕዝብህ ለጥቂት ጊዜ ወርሶት ነበር። ጠላቶቻችን መቅደስህን ረግጠዋል። |
እኛ ለረጅም ጊዜ፣ ፈጽሞ እንዳልገዛኻቸው፣ጨርሶ በስምህ እንዳልተጠሩ ሰዎች ሆነናል። |
እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ ኑ፤ ወደ ውኃው ኑ! እናንተ ገንዘብ የሌላችሁ ኑና ገዝታችሁ ብሉ! አዎ፣ ኑና ያለገንዘብ፣ ያለዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ። |
ምግብ ላልሆነ ነገር ለምን ገንዘባችሁን ታወጣላችሁ?እርካታ ለማያስገኝ ነገርስ ለምን ገቢያችሁን ታባክናላችሁ? እኔን በጥሞና አዳምጡ፤ መልካም የሆነውንም ብሉ፤ምርጥ ምግብ በመብላትም ሐሴት ታደርጋላችሁ። |
ጆሯችሁን አዘንብሉ፤ ወደ እኔም ኑ። አዳምጡ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ለዳዊት ካሳየሁት የማይከስም ታማኝ ፍቅር ጋር በሚስማማ ሁኔታከእናንተ ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ። |
እነሆ፣ ለብሔራት ምሥክር፣መሪና አዛዥ አድርጌዋለሁ። |
እነሆ፣ የማታውቀውን ብሔር ትጠራለህ፤የማያውቅህ ብሔርም ለአምላክህ ለይሖዋና ለእስራኤል ቅዱስ ሲልወደ አንተ ሮጦ ይመጣል፤ምክንያቱም እሱ ክብር ያጎናጽፍሃል። |
ይሖዋን በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት። በቅርብም ሳለ ጥሩት። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.