text
stringlengths
4
267
ያን ጊዜ ይሖዋ በመላው የጽዮን ተራራ ላይና በመሰብሰቢያ ቦታዋ ላይ በቀን ደመናና ጭስ፣ በሌሊት ደግሞ የሚንበለበል የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤ እንዲሁም ክብራማ በሆነው ቦታ ሁሉ ላይ መጠለያ ይኖራል።
ደግሞም በቀን ካለው ንዳድ ጥላ እንዲሁም ከውሽንፍርና ከዝናብ መጠጊያና መሸሸጊያ የሚሆን ዳስ ይኖራል።
እነሆ፣ የይሖዋ እጅ ማዳን ይሳናት ዘንድ አላጠረችም፤ጆሮውም መስማት ይሳናት ዘንድ አልደነዘዘችም።
ከዚህ ይልቅ ከአምላካችሁ ያለያያችሁ የገዛ በደላችሁ ነው። የፈጸማችሁት ኃጢአት ፊቱን እንዲሰውርባችሁ አድርጎታል፤እናንተን ለመስማትም ፈቃደኛ አይደለም።
እጆቻችሁ በደም፣ጣቶቻችሁም በበደል ተበክለዋልና። ከንፈሮቻችሁ ውሸት ይናገራሉ፤ አንደበታችሁም ክፋትን ያጉተመትማል።
ጽድቅን የሚጣራ ማንም የለም፤እውነትን ይዞ ፍርድ ቤት የሚቀርብ የለም። በማይጨበጥ ነገር ይታመናሉ፤ ፍሬ ቢስ ነገሮችን ይናገራሉ። ችግርን ይፀንሳሉ፤ የሚጎዳ ነገርም ይወልዳሉ።
የመርዘኛ እባብን እንቁላሎች ይቀፈቅፋሉ፤የሸረሪት ድርም ያደራሉ። እንቁላሎቻቸውንም የሚበላ ሁሉ ይሞታል፤እንቁላሉም ሲሰበር እፉኝት ይወጣል።
የሸረሪት ድራቸው ልብስ ሆኖ አያገለግልም፤በሚሠሩትም ነገር ራሳቸውን መሸፈን አይችሉም። ሥራቸው ጉዳት የሚያስከትል ነው፤በእጃቸውም የዓመፅ ሥራ አለ።
እግሮቻቸው ክፋት ለመፈጸም ይሮጣሉ፤ንጹሕ ደም ለማፍሰስም ይጣደፋሉ። የሚያስቡት ጎጂ ሐሳብ ነው፤በመንገዳቸው ላይ ጥፋትና መከራ አለ።
የሰላምን መንገድ አያውቁም፤በጎዳናቸውም ፍትሕ የለም። መንገዳቸውን ጠማማ ያደርጋሉ፤በዚያም የሚሄድ ሁሉ ሰላምን አያውቅም።
ከዚህ የተነሳ ፍትሕ ከእኛ ራቀ፤ጽድቅም ወደ እኛ አይደርስም። ብርሃን ይሆናል ብለን በተስፋ ተጠባበቅን፤ ሆኖም ጨለማ ሆነ፤ጸዳልን ተጠባበቅን፤ ሆኖም በጨለማ እንመላለሳለን።
ልክ እንደ ዓይነ ስውራን ቅጥሩን እየዳበስን እንሄዳለን፤ዓይን እንደሌላቸው ሰዎች እንደናበራለን። በምሽት ጨለማ እንደሚሆነው በቀትር ብርሃን እንሰናከላለን፤በብርቱ ሰዎች መካከል እንደ ሙታን ነን።
ሁላችንም እንደ ድቦች እናጉረመርማለን፤እንደ ርግቦችም በሐዘን እናልጎመጉማለን። ፍትሕን በተስፋ ተጠባበቅን፤ ነገር ግን አላገኘንም፤መዳንን ተጠባበቅን፤ ነገር ግን ከእኛ ርቋል።
ዓመፃችን በፊትህ በዝቷልና፤የሠራነው ኃጢአት ሁሉ ይመሠክርብናል። ዓመፃችን ከእኛ ጋር ነውና፤በደላችንን በሚገባ እናውቃለን።
ሕግ ተላልፈናል፤ ይሖዋንም ክደናል፤ለአምላካችን ጀርባችንን ሰጥተናል። ግፍንና ዓመፅን ተናግረናል፤በልባችን ውሸትን ፀንሰናል፤ እንዲሁም የሐሰት ቃላትን አጉተምትመናል።
ፍትሕ ወደ ኋላ ተመልሷል፤ጽድቅም በሩቅ ቆሟል፤እውነት በአደባባይ ተሰናክሏልና፤ቀና የሆነውም ነገር ወደዚያ መግባት አልቻለም።
እውነት ጠፍቷል፤ከክፋት የራቀ ሁሉ ለጥፋት ተዳርጓል። ይሖዋ ይህን አየ፤ ደስም አልተሰኘም፤ፍትሕ አልነበረምና።
እርዳታ የሚሰጥ ሰው እንደሌለ አየ፤ጣልቃ የሚገባ ባለመኖሩም ተገረመ፤በመሆኑም የገዛ ክንዱ መዳን አስገኘ፤የገዛ ጽድቁም ድጋፍ ሆነለት።
ከዚያም ጽድቅን እንደ ጥሩር ለበሰ፤በራሱም ላይ የመዳንን ቁር አደረገ። የበቀልንም ልብስ ለበሰ፤ቅንዓትንም እንደ ካባ ተጎናጸፈ።
ላደረጉት ነገር ብድራት ይከፍላቸዋል፦ ቁጣን ለባላጋራዎቹ፣ በቀልን ለጠላቶቹ ይከፍላል። ለደሴቶችም የሚገባቸውን ዋጋ ይከፍላቸዋል።
በፀሐይ መግቢያ ያሉ የይሖዋን ስም ይፈራሉ፤በፀሐይ መውጫም ያሉ ክብሩን ይፈራሉ፤እሱ የይሖዋ መንፈስ እንደሚነዳውኃይለኛ ወንዝ ሆኖ ይመጣልና።
“ጽዮንን፣ በደል መፈጸም ያቆሙትንምየያዕቆብ ቤት ሰዎች የሚቤዥ ይመጣል” ይላል ይሖዋ።
“በእኔ በኩል ከእነሱ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳን ይህ ነው” ይላል ይሖዋ። “በአንተ ላይ ያለው መንፈሴና በአፍህ ያኖርኩት ቃሌ፣ ከአንተ አፍ ወይም ከልጆችህ አፍ ወይም ከልጅ ልጆችህ አፍ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም አይወሰዱም” ይላል ይሖዋ።
የሉዓላዊው ጌታ የይሖዋ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ምክንያቱም ይሖዋ የዋህ ለሆኑ ሰዎች ምሥራች እንድናገር ቀብቶኛል። ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ለተማረኩት ነፃነትን እንዳውጅእንዲሁም ‘የእስረኞች ዓይን ይከፈታል’ ብዬ እንድናገር ልኮኛል፤
ይሖዋ በጎ ፈቃድ የሚያሳይበትን ዓመት፣አምላካችን የሚበቀልበትንም ቀን እንዳውጅ፣የሚያለቅሱትንም ሁሉ እንዳጽናና ልኮኛል፤
በጽዮን የተነሳ ላዘኑትበአመድ ፋንታ የራስ መሸፈኛ፣በሐዘን ፋንታ የደስታ ዘይት፣በተደቆሰም መንፈስ ፋንታ የውዳሴ ልብስ እንድሰጥ ልኮኛል። እነሱም ይሖዋ ራሱን ክብር ለማጎናጸፍየተከላቸው ትላልቅ የጽድቅ ዛፎች ተብለው ይጠራሉ።
የጥንቶቹን ፍርስራሾች መልሰው ይገነባሉ፤በቀድሞዎቹ ጊዜያት ባድማ የሆኑትን ቦታዎች ይሠራሉ፤የወደሙትን ከተሞች፣ከትውልድ እስከ ትውልድም ፈራርሰው የቆዩትን ቦታዎች መልሰው ይገነባሉ።
“እንግዳ ሰዎች መጥተው መንጎቻችሁን ይጠብቃሉ፤የባዕድ አገር ሰዎችም ገበሬዎቻችሁና የወይን አትክልት ሠራተኞቻችሁ ይሆናሉ።
እናንተም የይሖዋ ካህናት ተብላችሁ ትጠራላችሁ፤የአምላካችን አገልጋዮች ብለው ይጠሯችኋል። የብሔራትን ሀብት ትበላላችሁ፤በእነሱም ክብር ትኮራላችሁ።
በኀፍረት ፋንታ እጥፍ ድርሻ ይኖራችኋል፤በውርደትም ፋንታ በሚያገኙት ድርሻ በደስታ እልል ይላሉ። አዎ፣ በምድራቸው እጥፍ ድርሻ ይወርሳሉ። የዘላለም ሐሴት የእነሱ ይሆናል።
እኔ ይሖዋ ፍትሕን እወዳለሁና፤ዝርፊያንና ክፋትን እጠላለሁ። ደሞዛቸውን በታማኝነት እሰጣቸዋለሁ፤ከእነሱም ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።
ዘሮቻቸው በብሔራት፣ልጆቻቸውም በሕዝቦች መካከል የታወቁ ይሆናሉ። የሚያዩአቸው ሁሉይሖዋ የባረካቸው ዘሮች እንደሆኑ ይገነዘባሉ።”
እኔ በይሖዋ እጅግ ደስ ይለኛል። ሁለንተናዬ በአምላኬ ሐሴት ያደርጋል። የመዳንን መጎናጸፊያ አልብሶኛልና፤የካህን ዓይነት ጥምጥም እንደሚያደርግ ሙሽራ፣በጌጣጌጧም ራሷን እንዳስዋበች ሙሽሪትየጽድቅ ቀሚስ አልብሶኛል።
ምድር ቡቃያዋን እንደምታበቅል፣የአትክልት ቦታም በላዩ ላይ የተዘሩትን ዘሮች እንደሚያበቅልሉዓላዊው ጌታ ይሖዋምበብሔራት ሁሉ ፊት ጽድቅንና ውዳሴን ያበቅላል።
በዚያን ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ፣ የባላዳን ልጅ ሜሮዳክባላዳን ሕዝቅያስ ታሞ እንደነበረና ከሕመሙ እንዳገገመ በመስማቱ ደብዳቤና ስጦታ ላከለት።
ሕዝቅያስም መልእክተኞቹን በደስታ ተቀበላቸው፤ ከዚያም ግምጃ ቤቱን ይኸውም ብሩን፣ ወርቁን፣ የበለሳን ዘይቱን፣ ሌላውን ምርጥ ዘይት፣ የጦር መሣሪያውን ሁሉና በግምጃ ቤቶቹ ውስጥ ያለውን ንብረት በሙሉ አሳያቸው። ሕዝቅያስ በቤቱም ሆነ በግዛቱ ሁሉ ያላሳያቸው ምንም ነገር አልነበረም።
ከዚያ በኋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ መጥቶ “እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? የመጡትስ ከየት ነው?” ሲል ጠየቀው። ሕዝቅያስም “የመጡት ከሩቅ አገር፣ ከባቢሎን ነው” አለው።
ቀጥሎም “በቤትህ ያዩት ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ሕዝቅያስም “በቤቴ ያለውን ነገር ሁሉ አይተዋል። በግምጃ ቤቶቼ ውስጥ ካለው ንብረት ሁሉ ያላሳየኋቸው ምንም ነገር የለም” ሲል መለሰለት።
በዚህ ጊዜ ኢሳይያስ ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፦ “የሠራዊት ጌታ የይሖዋን ቃል ስማ፤
‘እነሆ፣ በቤትህ ያለው ሁሉና አባቶችህ እስካሁን ድረስ ያከማቹት ነገር ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚጋዝበት ቀን ይመጣል። አንድም የሚቀር ነገር አይኖርም’ ይላል ይሖዋ።
‘ከአንተ ከሚወለዱት ከገዛ ልጆችህ መካከልም አንዳንዶቹ ይወሰዳሉ፤ በባቢሎን ንጉሥ ቤተ መንግሥትም ባለሥልጣናት ይሆናሉ።’”
በዚህ ጊዜ ሕዝቅያስ ኢሳይያስን “የተናገርከው የይሖዋ ቃል መልካም ነው” አለው። አክሎም እንዲህ አለ፦ “ምክንያቱም በእኔ የሕይወት ዘመን ሰላምና መረጋጋት ይኖራል።”
የአሦር ንጉሥ ሳርጎን የላከው ታርታን ወደ አሽዶድ በመጣበት ዓመት አሽዶድን ወግቶ ያዛት።
በዚያን ጊዜ ይሖዋ የአሞጽ ልጅ በሆነው በኢሳይያስ በኩል እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “ሂድ፣ ማቁን ከወገብህ ላይ አስወግድ፤ ጫማህንም ከእግርህ ላይ አውልቅ።” እሱም እንደተባለው አደረገ፤ ራቁቱንና ባዶ እግሩንም ተመላለሰ።
ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለ፦ “አገልጋዬ ኢሳይያስ በግብፅና በኢትዮጵያ ላይ ለሚደርሰው ነገር ምልክትና ማስጠንቀቂያ እንዲሆን ለሦስት ዓመት ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደተመላለሰ ሁሉ፣
የአሦር ንጉሥም የግብፅን ምርኮኞችና የኢትዮጵያን ግዞተኞች፣ ልጆችንና ሽማግሌዎችን ሳይቀር መቀመጫቸውን ገልቦ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን እየነዳ ይወስዳቸዋል፤ የግብፅንም እርቃን ያጋልጣል።
ተስፋቸውን በጣሉባት በኢትዮጵያና በሚኮሩባት በግብፅ የተነሳ በፍርሃት ይርዳሉ፤ ብሎም ያፍራሉ።
በዚያም ቀን በዚህ የባሕር ዳርቻ የሚኖረው ሕዝብ ‘ተስፋ የጣልንበትን ይኸውም እርዳታ ለማግኘትና ከአሦር ንጉሥ ለመዳን የሸሸንበትን አገር ተመልከቱ! በዚህ ዓይነት እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’ ማለቱ አይቀርም።”
በዚያ ቀን በእርግጥ እንዲህ ትላለህ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ ተቆጥተኸኝ የነበረ ቢሆንምቁጣህ ቀስ በቀስ ስለበረደደግሞም ስላጽናናኸኝ አመሰግንሃለሁ።
እነሆ፣ አምላክ አዳኜ ነው! በእሱ እታመናለሁ፤ ምንም የሚያስፈራኝ ነገር የለም፤ያህ ይሖዋ ብርታቴና ኃይሌ ነው፤ለእኔም አዳኝ ሆኖልኛል።”
ከመዳን ምንጮችበደስታ ውኃ ትቀዳላችሁ።
በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦ “ይሖዋን አመስግኑ! ስሙን ጥሩ፤ሥራውን በሕዝቦች መካከል አስታውቁ! ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱን አውጁ።
አስደናቂ ነገሮችን ስላከናወነ ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ። ይህም በመላው ምድር ይታወጅ።
እናንተ የጽዮን ነዋሪዎች ሆይ፣ ጩኹ፤ በደስታም እልል በሉ፤የእስራኤል ቅዱስ በመካከላችሁ ታላቅ ነውና።”
ከእኛ የሰማውን ነገር ያመነ ማን ነው? የይሖዋስ ክንድ ለማን ተገለጠ?
እሱ በፊቱ እንደ ቅርንጫፍ፣ በደረቅ ምድር እንዳለ ሥር ይበቅላል። የሚያምር ቁመናም ሆነ ግርማ ሞገስ የለውም፤ባየነውም ጊዜ መልኩ አልሳበንም።
ሰዎች የናቁትና ያገለሉት፣ሥቃይን ያየ፣ ሕመምንም የሚያውቅ ሰው ነበር። ፊቱ የተሰወረብን ያህል ነበር። ሰዎች ናቁት፤ እኛም ከቁብ አልቆጠርነውም።
በእርግጥም እሱ ራሱ ሕመማችንን ተሸከመ፤ሥቃያችንንም ተቀበለ። እኛ ግን እንደተቀሰፈ፣ በአምላክ እንደተመታና እንደተጎሳቆለ አድርገን ቆጠርነው።
እሱ ግን ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ስለ በደላችን ደቀቀ። በእሱ ላይ የደረሰው ቅጣት ለእኛ ሰላም አስገኘልን፤በእሱም ቁስል የተነሳ እኛ ተፈወስን።
ሁላችንም እንደ በጎች ተቅበዘበዝን፤እያንዳንዳችን በየራሳችን መንገድ ሄድን፤ይሖዋም የሁላችንንም በደል እሱ እንዲሸከም አደረገ።
ግፍ ተፈጸመበት፤ መከራም ለመቀበል ፈቃደኛ ሆነ፤ነገር ግን አፉን አልከፈተም። እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ፤በሸላቾቿ ፊት ዝም እንደምትል በግ፣እሱም አፉን አልከፈተም።
ፍትሕ ተነፈገ፤ በአግባቡም ሳይዳኝ ተወሰደ፤ትኩረት ሰጥቶ ትውልዱን በዝርዝር ለማወቅ የሚሞክር ማን ነው? ከሕያዋን ምድር ተወግዷልና፤በሕዝቤ መተላለፍ የተነሳ ተመታ።
ምንም ዓይነት በደል አልፈጸመም፤እንዲሁም ከአንደበቱ የማታለያ ቃል አልወጣም፤ሆኖም በሚሞትበት ጊዜ የመቃብር ቦታውከክፉዎችና ከሀብታሞች ጋር ይሆናል።
ይሁንና እሱን ማድቀቅ የይሖዋ ፈቃድ ነበር፤ ለሕመም እንዲዳረግም ፈቅዷል። ሕይወቱን የበደል መባ አድርገህ የምታቀርበው ከሆነዘሩን ያያል፤ ዘመኑን ያስረዝማል፤እንዲሁም በእሱ አማካኝነት ይሖዋ ደስ የሚሰኝበት ነገር ይከናወናል።
በእሱ ላይ ከደረሰው ሥቃይ የተነሳ፣ በሚያየው መልካም ነገር ይደሰታል። ጻድቅ አገልጋዬ በእውቀቱ አማካኝነትብዙ ሰዎች ጻድቅ ሆነው እንዲቆጠሩ ይረዳል፤በደላቸውንም ይሸከማል።
ስለዚህ ከብዙዎች ጋር ድርሻውን እሰጠዋለሁ፤ምርኮውን ከኃያላን ጋር ይካፈላል፤ሕይወቱን እስከ ሞት ድረስ አፍስሷልና፤ከሕግ ተላላፊዎችም ጋር ተቆጥሯል፤የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸክሟል፤ስለ ሕግ ተላላፊዎችም ማልዷል።
እናንተ ራሳችሁን በእስራኤል ስም የምትጠሩ፣ከይሁዳ ምንጭ የፈለቃችሁ፣በእውነትና በጽድቅ ባይሆንምበይሖዋ ስም የምትምሉናየእስራኤልን አምላክ የምትጠሩየያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ይህን ስሙ።
እነሱ የቅድስቲቱ ከተማ ነዋሪ እንደሆኑ ይናገራሉና፤ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ የሆነውንየእስራኤልን አምላክ ድጋፍ ለማግኘት ይጥራሉ።
“ከብዙ ዘመን በፊት የቀድሞዎቹን ነገሮች ነግሬአችኋለሁ። ከአፌም ወጥተዋል፤እንዲታወቁም አድርጌአለሁ። በድንገት እርምጃ ወሰድኩ፤ እነሱም ተፈጸሙ።
ምን ያህል ልበ ደንዳና እንደሆንክ፣ይኸውም የአንገትህ ጅማት ብረት፣ ግንባርህም መዳብ መሆኑን ስለማውቅ፣
ከረጅም ጊዜ በፊት ነግሬሃለሁ። ‘ይህን ያደረገው የራሴ ጣዖት ነው፤ይህን ያዘዘው የተቀረጸው ምስሌና ከብረት የተሠራው ምስሌ ነው’ እንዳትልገና ከመፈጸሙ በፊት አሳውቄሃለሁ።
አንተም ሰምተሃል፤ ደግሞም ይህን ሁሉ አይተሃል። ይህን አታሳውቅም? ከአሁን ጀምሮ አዳዲስ ነገሮችን፣የማታውቃቸውን ጥብቅ ሚስጥሮች እነግርሃለሁ።
እነዚህ ነገሮች የተፈጠሩት ጥንት ሳይሆን ገና አሁን ነው፤‘እነዚህንማ ከዚህ በፊት አውቃቸዋለሁ!’ እንዳትል፣ከዛሬ በፊት ሰምተሃቸው አታውቅም።
አዎ፣ አንተ አልሰማህም፤ አላወቅክምም፤ከዚህ በፊት ጆሮህ ክፍት አልነበረም። በጣም አታላይ እንደሆንክናከተወለድክበት ጊዜ ጀምሮ ዓመፀኛ ተብለህ እንደተጠራህ አውቃለሁና።
ይሁንና ስለ ስሜ ስል ቁጣዬን እቆጣጠራለሁ፤ስለ ውዳሴዬም ስል ራሴን እገታለሁ፤ደግሞም አላጠፋህም።
እነሆ፣ እንደ ብር ባይሆንም አንጥሬሃለሁ። እንደ ማቅለጫ ምድጃ ባለ መከራ ፈትኜሃለሁ።
ለራሴ ስል፣ አዎ ለራሴ ስል እርምጃ እወስዳለሁ፤ስሜ እንዲረክስ እንዴት እፈቅዳለሁ? ክብሬን ለማንም አልሰጥም።
ያዕቆብ ሆይ፣ የጠራሁህም እስራኤል ሆይ፣ ስማኝ። እኔ ምንጊዜም ያው ነኝ። የመጀመሪያው እኔ ነኝ፤ የመጨረሻውም እኔ ነኝ።
የገዛ እጄ የምድርን መሠረት ጣለ፤ቀኝ እጄም ሰማያትን ዘረጋ። እነሱን ስጠራቸው በአንድነት ይቆማሉ።
ሁላችሁም አንድ ላይ ተሰብስባችሁ ስሙ። ከመካከላቸው እነዚህን ነገሮች ያሳወቀ ማን ነው? ይሖዋ ወዶታል። እሱ ደስ የሚያሰኘውን በባቢሎን ላይ ይፈጽማል፤ክንዱም በከለዳውያን ላይ ያርፋል።
እኔ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ እሱንም ጠርቼዋለሁ። አምጥቼዋለሁ፤ መንገዱም የተቃና ይሆናል።
ወደ እኔ ቅረቡ፤ ደግሞም ይህን ስሙ። ከመጀመሪያው አንስቶ በሚስጥር አልተናገርኩም። ከተፈጸመበት ጊዜ አንስቶ እኔ በዚያ ነበርኩ።” አሁንም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ መንፈሱም ልኮኛል።
የሚቤዥህ፣ የእስራኤል ቅዱስ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የሚጠቅምህን ነገር የማስተምርህ፣ልትሄድበትም በሚገባህ መንገድ የምመራህእኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ።
ትእዛዛቴን ብትሰማ ምንኛ መልካም ነው! እንዲህ ብታደርግ ሰላምህ እንደ ወንዝ፣ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ ይሆናል።
ዘርህ እንደ አሸዋ፣የአብራክህም ክፋዮች እንደ አሸዋ ቅንጣቶች ብዙ ይሆናሉ። ስማቸው ከፊቴ አይጠፋም ወይም አይደመሰስም።”
ከባቢሎን ውጡ! ከከለዳውያን ሽሹ! ይህን በእልልታ አስታውቁ! አውጁትም! እስከ ምድር ዳርቻ እንዲሰማ አድርጉ። እንዲህም በሉ፦ “ይሖዋ አገልጋዩን ያዕቆብን ተቤዥቶታል።
ባድማ በሆኑ ቦታዎች በመራቸው ጊዜ አልተጠሙም። ከዓለት ውስጥ ውኃ አፈለቀላቸው፤ዓለቱን ሰንጥቆ ውኃ አንዶለዶለላቸው።”
“ክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል ይሖዋ።
በክንፋቸው ጥዝ የሚል ድምፅ የሚያሰሙ ጥቃቅን ነፍሳት ላሉባትበኢትዮጵያ ወንዞች አካባቢ ለምትገኝ ምድር ወዮላት!
ይህች ምድር በባሕር ላይ፣በደንገል ጀልባ ውኃዎችን አቋርጠው የሚሄዱ መልእክተኞችን እንዲህ በማለት ትልካለች፦ “እናንተ ፈጣን መልእክተኞች፣ረጃጅም የሆኑና ለስላሳ ቆዳ ያላቸው ሰዎች ወደሚገኙበት ብሔር፣ከቅርብም ሆነ ከሩቅ ወደሚፈራ ሕዝብ፣ጥንካሬ ወዳለውና ድል አድራጊ ወደሆነውእንዲሁም መሬቱ በወንዞች ተጠርጎ ወደተወሰደበት ብሔር ሂዱ።”
እናንተ በአገሪቱ የምትኖሩ ሁሉና እናንተ የምድር ነዋሪዎች ሁሉ፣በተራሮች ላይ እንደሚቆም ምልክት ያለ ነገር ትመለከታላችሁ፤እንዲሁም ቀንደ መለከት ሲነፋ የሚሰማው ዓይነት ድምፅ ትሰማላችሁ።
ይሖዋ እንዲህ ብሎኛልና፦ “በቀን ብርሃን እንዳለ የሚያጥበረብር ሐሩር፣በመከርም ሙቀት እንዳለ የደመና ጠል፣ጸጥ ብዬ ተቀምጬ ጽኑ ሆኖ የተመሠረተውን ስፍራዬን እመለከታለሁ።
ከመከር በፊት፣አበባው በሚረግፍበትና የወይን ፍሬው በሚበስልበት ጊዜቀንበጦቹ በማጭድ ይቆረጣሉና፤ሐረጎቹም ተቆርጠው ይወገዳሉ።
ሁሉም በተራሮች ላይ ላሉ አዳኝ አሞሮችናለምድር አራዊት ይተዋሉ። አዳኝ አሞሮቹም እነሱን በመመገብ በጋውን ያሳልፋሉ፤በምድር ላይ ያሉ አራዊትም ሁሉ እነሱን በመመገብ የመከሩን ወቅት ያሳልፋሉ።
በዚያን ጊዜ ረጃጅም የሆኑና ለስላሳ ቆዳ ያላቸው ሰዎች የሚገኙበት ብሔር፣ከቅርብም ሆነ ከሩቅ የሚፈራው ሕዝብ፣ጥንካሬ ያለው፣ ድል አድራጊ የሆነውናመሬቱ በወንዞች ተጠርጎ የተወሰደበት ብሔርለሠራዊት ጌታ ለይሖዋ ስጦታ ያመጣል፤ስጦታውንም የሚያመጣው የሠራዊት ጌታ የይሖዋ ስም ወዳለበት ወደ ጽዮን ተራራ ነው።”
ጻድቁ ሞቷል፤ይህን ግን ማንም ልብ አይልም። ታማኝ ሰዎች ተወስደዋል፤ሆኖም ጻድቁ የተወሰደውከመከራ የተነሳ እንደሆነ የሚያስተውል የለም።
እሱ ሰላም ያገኛል። በቅንነት የሚሄዱ ሁሉ አልጋቸው ላይ ያርፋሉ።
“ይሁንና እናንተ የአስማተኛዋ ወንዶች ልጆች፣የአመንዝራና የዝሙት አዳሪ ልጆች፣ኑ ወደዚህ ቅረቡ፦
የምታሾፉት በማን ላይ ነው? አፋችሁን የምትከፍቱትና ምላሳችሁን የምታወጡትስ በማን ላይ ነው? እናንተ የዓመፅ ልጆች፣የሐሰትም ልጆች አይደላችሁም?
በትላልቅ ዛፎች መካከል፣ቅጠሉ በተንዠረገገም ዛፍ ሥር ሁሉ በስሜት የተቃጠላችሁ፣በሸለቆዎች ውስጥ፣ በቋጥኞች መካከልልጆችን የምታርዱ አይደላችሁም?