text stringlengths 4 267 |
|---|
ሻላና ጃርት ይወርሷታል፤ባለ ረጅም ጆሮ ጉጉቶችና ቁራዎችም በእሷ ውስጥ ይኖራሉ። አምላክ፣ ምድሪቱ ባዶ እንደምትሆንና እንደምትጠፋ ለማሳየትበመለኪያ ገመድና በቱንቢ ይለካታል። |
ከታላላቅ ሰዎቿ መካከል ለንግሥና የሚበቃ አንድም ሰው አይኖርም፤መኳንንቷም ሁሉ ይጠፋሉ። |
በማይደፈሩ ማማዎቿ ላይ እሾህ፣በምሽጎቿም ላይ ሳማና ኩርንችት ይበቅላል። የቀበሮዎች ማደሪያ፣የሰጎኖችም መኖሪያ ትሆናለች። |
የበረሃ ፍጥረታት ከሚያላዝኑ እንስሶች ጋር ይገናኛሉ፤የዱር ፍየልም ባልንጀራውን ይጠራል። የሌሊት ወፍ በዚያ ታርፋለች፤ ማረፊያ ስፍራም ታገኛለች። |
ተወንጫፊ እባብ በዚያ ጎጆዋን ትሠራለች፤ እንቁላልም ትጥላለች፤ከዚያም ትቀፈቅፋለች፤ በጥላዋም ሥር ትሰበስባቸዋለች። ጭላቶችም ጥንድ ጥንድ ሆነው በዚያ ይሰበሰባሉ። |
በይሖዋ መጽሐፍ ውስጥ ፈልጉ፤ ድምፃችሁንም ከፍ አድርጋችሁ አንብቡ፤ ከእነሱ መካከል አንዳቸውም አይጎድሉም፤ሁሉም ተጓዳኝ አያጡም፤ይህ ትእዛዝ የወጣው ከይሖዋ አፍ ነውና፤አንድ ላይ የሰበሰባቸውም የእሱ መንፈስ ነው። |
ዕጣ የጣለላቸው እሱ ነው፤የተመደበላቸውን ቦታ የለካው የገዛ እጁ ነው። እነሱም ለዘለቄታው ይወርሱታል፤ከትውልድ እስከ ትውልድም በዚያ ይኖራሉ። |
ንጉሥ ዖዝያ በሞተበት ዓመት ይሖዋን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፤ የልብሱም ዘርፍ ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር። |
ሱራፌልም ከእሱ በላይ ቆመው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ስድስት ክንፎች ነበሯቸው። እያንዳንዱ በሁለቱ ክንፍ ፊቱን ይሸፍን፣ በሁለቱ ክንፍ እግሩን ይሸፍን፣ በሁለቱ ክንፍ ደግሞ ይበር ነበር። |
አንዳቸውም ሌላውን እንዲህ ይሉ ነበር፦ “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው። መላዋ ምድር በክብሩ ተሞልታለች።” |
ከድምፁ ጩኸት የተነሳ የበሩ መቃኖች ተናወጡ፤ ቤቱም በጭስ ተሞላ። |
በዚህ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “ወዮልኝ! ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ስለሆንኩናየምኖረውም ከንፈራቸው በረከሰ ሕዝብ መካከል ስለሆነበቃ መሞቴ ነው፤ዓይኖቼ ንጉሡን፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ራሱን አይተዋልና!” |
በዚህ ጊዜ ከሱራፌል አንዱ ወደ እኔ እየበረረ መጣ፤ እሱም ከመሠዊያው ላይ በጉጠት ያነሳውን ፍም በእጁ ይዞ ነበር። |
አፌንም ነክቶ እንዲህ አለኝ፦ “እነሆ፣ ይህ ከንፈሮችህን ነክቷል። በደልህ ተወግዶልሃል፤ኃጢአትህም ተሰርዮልሃል።” |
ከዚያም የይሖዋ ድምፅ “ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?” ሲል ሰማሁ። እኔም “እነሆኝ! እኔን ላከኝ!” አልኩ። |
እሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፦ “ሄደህ ይህን ሕዝብ እንዲህ በለው፦ ‘ደጋግማችሁ ትሰማላችሁ፣ነገር ግን አታስተውሉም፤ደጋግማችሁ ታያላችሁ፣ነገር ግን ምንም እውቀት አታገኙም።’ |
በዓይናቸው እንዳያዩ፣በጆሯቸውም እንዳይሰሙ፣ልባቸውም እንዳያስተውል፣ተመልሰውም እንዳይፈወሱየዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፤ጆሯቸውንም ድፈን፤ዓይናቸውንም ሸፍን።” |
በዚህ ጊዜ “ይሖዋ ሆይ፣ እስከ መቼ ነው?” አልኩ። እሱም እንዲህ አለኝ፦ “ከተሞች እስኪፈራርሱና የሚኖርባቸው እስኪያጡ፣ቤቶችም ሰው አልባ እስኪሆኑ፣ምድሪቱም እስክትጠፋና ባድማ እስክትሆን ድረስ ነው፤ |
ይሖዋም ሰዎችን ወደ ሩቅ ቦታ እስከሚሰድ፣የምድሪቱም በረሃነት በእጅጉ እስኪስፋፋ ድረስ ነው። |
“ይሁንና በእሷ ውስጥ አንድ አሥረኛ ይቀራል፤ እሱም በድጋሚ ይቃጠላል፤ ከተቆረጡ በኋላ ጉቷቸው እንደሚቀር እንደ ትልቅ ዛፍና እንደ ባሉጥ ዛፍ ይሆናል፤ በምድሪቱ ላይ የቀረው ጉቶ የተቀደሰ ዘር ይሆናል።” |
“እኔን ላልጠየቁ ሰዎች ተገለጥኩ፤ላልፈለጉኝ ሰዎች ተገኘሁ። ስሜን ላልጠራ ብሔር ‘እነሆኝ፤ እነሆኝ!’ አልኩ። |
የራሳቸውን ሐሳብ እየተከተሉ፣መልካም ባልሆነ መንገድ ወደሚሄዱግትር ሰዎች ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ፤ |
እነሱ ዘወትር በፊቴ እኔን የሚያስከፋ ነገር ይፈጽማሉ፤በአትክልት ቦታዎች ይሠዋሉ፤ በጡቦችም ላይ የሚጨስ መሥዋዕት ያቀርባሉ። |
በመቃብር መካከል ይቀመጣሉ፤በተሰወሩ ቦታዎችም ውስጥ ያድራሉ፤የአሳማ ሥጋ ይበላሉ፤ዕቃዎቻቸው ጸያፍ በሆኑ ነገሮች መረቅ የተሞሉ ናቸው። |
‘እዚያው ባለህበት ሁን፤ አትጠጋኝ፤እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝና’ ይላሉ። እነዚህ ሰዎች በአፍንጫዬ እንዳለ ጭስ፣ ቀኑን ሙሉ እንደሚነድ እሳት ናቸው። |
እነሆ፣ በፊቴ ተጽፏል፤እኔ ዝም አልልም፤ከዚህ ይልቅ እንደ ሥራቸው እከፍላቸዋለሁ፤ብድራቱን ሙሉ በሙሉ እመልስባቸዋለሁ፤ |
ይህን የማደርገው እነሱ በሠሩት በደልና አባቶቻቸው በሠሩት በደል የተነሳ ነው” ይላል ይሖዋ። “ምክንያቱም በተራሮች ላይ የሚጨስ መሥዋዕት አቅርበዋል፤በኮረብቶችም ላይ አዋርደውኛል፤እኔም በመጀመሪያ፣ ዋጋቸውን ሙሉ በሙሉ እከፍላቸዋለሁ።” |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አዲስ ወይን፣ በወይን ዘለላ ውስጥ ሲገኝአንድ ሰው ‘በውስጡ ጥሩ ነገር ስላለ አታጥፋው’ እንደሚል፣ እኔም ለአገልጋዮቼ ስል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ሁሉንም አላጠፋቸውም። |
ከያዕቆብ ዘርን፣ከይሁዳም ተራሮቼን የሚወርሰውን አወጣለሁ፤የመረጥኳቸው ምድሪቱን ይወርሳሉ፤አገልጋዮቼም በዚያ ይኖራሉ። |
እኔን ለሚፈልገኝ ሕዝቤ፣ሳሮን የበጎች መሰማሪያ፣የአኮርም ሸለቆ የከብቶች ማረፊያ ይሆናል። |
እናንተ ግን ይሖዋን ከተዉት፣ቅዱስ ተራራዬን ከረሱት፣መልካም ዕድል ለተባለ አምላክ ማዕድ ካሰናዱት፣ዕጣ ለተባለም አምላክ የተደባለቀ ወይን ጠጅ በዋንጫ ከሞሉት ሰዎች መካከል ናችሁ። |
በመሆኑም ዕጣችሁ በሰይፍ መውደቅ ይሆናል፤ሁላችሁም ለመታረድ ታጎነብሳላችሁ፤ምክንያቱም ስጣራ አልመለሳችሁም፤ስናገር አልሰማችሁም፤በዓይኔ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ማድረጋችሁን ቀጠላችሁ፤እኔ የማልደሰትበትንም ነገር መረጣችሁ።” |
ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ አገልጋዮቼ ይበላሉ፤ እናንተ ግን ትራባላችሁ። እነሆ፣ አገልጋዮቼ ይጠጣሉ፤ እናንተ ግን ትጠማላችሁ። እነሆ፣ አገልጋዮቼ ሐሴት ያደርጋሉ፤ እናንተ ግን ኀፍረት ትከናነባላችሁ። |
እነሆ፣ አገልጋዮቼ ከልባቸው ደስታ የተነሳ እልል ይላሉ፤እናንተ ግን ከልባችሁ ሐዘን የተነሳ ትጮኻላችሁ፤መንፈሳችሁ ስለተሰበረም ዋይ ዋይ ትላላችሁ። |
የተመረጡት አገልጋዮቼ ለእርግማን የሚጠቀሙበት ስም ትታችሁ ታልፋላችሁ፤ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋም እያንዳንዳችሁን ይገድላችኋል፤የራሱን አገልጋዮች ግን በሌላ ስም ይጠራቸዋል፤ |
ስለዚህ በምድር ላይ በረከትን የሚሻ ሁሉበእውነት አምላክ ይባረካል፤በምድር ላይ መሐላ የሚምልም ሁሉበእውነት አምላክ ይምላል። ቀደም ሲል የነበሩት የሚያስጨንቁ ነገሮች ይረሳሉና፤ከዓይኔ ይሰወራሉ። |
እነሆ፣ አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር እየፈጠርኩ ነውና፤የቀድሞዎቹ ነገሮች አይታሰቡም፤ወደ ልብም አይገቡም። |
በመሆኑም በምፈጥረው ነገር ለዘላለም ደስ ይበላችሁ፤ ሐሴትም አድርጉ። እነሆ፣ ኢየሩሳሌምን ለደስታ፣ሕዝቧንም ለሐሴት እፈጥራለሁና። |
እኔም በኢየሩሳሌም ደስ እሰኛለሁ፤ በሕዝቤም ሐሴት አደርጋለሁ፤ከዚህ በኋላ በውስጧ የለቅሶ ድምፅም ሆነ የጭንቅ ጩኸት አይሰማም።” |
“ከእንግዲህ በዚያ፣ ለጥቂት ቀን ብቻ የሚኖር ሕፃንም ሆነዕድሜ የማይጠግብ አረጋዊ አይኖርም። መቶ ዓመት ሞልቶት የሚሞት ማንኛውም ሰው ገና በልጅነቱ እንደተቀጨ ይቆጠራል፤ኃጢአተኛው መቶ ዓመት ቢሞላውም እንኳ ይረገማል። |
ቤቶችን ይሠራሉ፤ በዚያም ይኖራሉ፤ወይንንም ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ። |
እነሱ በሠሩት ቤት ሌላ ሰው አይኖርም፤እነሱ የተከሉትንም ሌላ ሰው አይበላውም። የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፤የመረጥኳቸው አገልጋዮቼም በእጃቸው ሥራ የተሟላ እርካታ ያገኛሉ። |
በከንቱ አይለፉም፤ወይም ለመከራ የሚዳረጉ ልጆች አይወልዱም፤ምክንያቱም እነሱም ሆኑ ልጆቻቸውይሖዋ የባረከው ዘር ናቸው። |
ገና ሳይጣሩ እመልስላቸዋለሁ፤እየተናገሩ ሳሉ እሰማቸዋለሁ። |
ተኩላና የበግ ግልገል በአንድነት ይበላሉ፤አንበሳ እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤የእባብም መብል አፈር ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳትም ሆነ ጥፋት አያደርሱም” ይላል ይሖዋ። |
በአንተ የተነሳ ተራሮች ይናወጡ ዘንድምነው ሰማያትን ቀደህ በወረድክ! |
እሳት ጭራሮን አቀጣጥሎውኃን እንደሚያፈላ ሁሉ፣ያን ጊዜ ጠላቶችህ ስምህን ያውቃሉ፤ብሔራትም በፊትህ ይሸበራሉ! |
እኛ ፈጽሞ ያልጠበቅናቸውን እጅግ አስደናቂ ነገሮች ባደረግክ ጊዜ፣አንተ ወረድክ፤ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ። |
ከጥንት ዘመን ጀምሮ፣ እሱን በተስፋ ለሚጠባበቁት ሲል እርምጃ የወሰደከአንተ በቀር ሌላ አምላክ እንዳለ የሰማም ሆነ በጆሮው ያዳመጠወይም በዓይኑ ያየ ማንም የለም። |
ትክክል የሆነውን ነገር በደስታ ከሚያደርጉ፣አንተን ከሚያስቡና መንገዶችህን ከሚከተሉ ሰዎች ጋር ተገናኝተሃል። እነሆ፣ ኃጢአት መሥራታችንን በቀጠልን ጊዜ ተቆጣህ፤ይህን ያደረግነውም ለረጅም ጊዜ ነው። ታዲያ አሁን መዳን ይገባናል? |
ሁላችንም እንደረከሰ ሰው ሆነናል፤የጽድቅ ሥራችንም ሁሉ እንደ ወር አበባ ጨርቅ ነው። ሁላችንም እንደ ቅጠል እንጠወልጋለን፤በደላችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎ ይወስደናል። |
ስምህን የሚጠራ የለም፤አንተን የሙጥኝ ብሎ ለመያዝ የሚነሳሳ የለም፤ፊትህን ከእኛ ሰውረሃልና፤በበደላችን የተነሳ እንድንመነምን አድርገኸናል። |
አሁን ግን ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አባታችን ነህ። እኛ ሸክላ ነን፤ አንተም ሠሪያችን ነህ፤ሁላችንም የእጅህ ሥራ ነን። |
ይሖዋ ሆይ፣ እጅግ አትቆጣ፤በደላችንንም ለዘላለም አታስታውስ። እባክህ ተመልከተን፤ እኛ ሁላችን ሕዝብህ ነንና። |
የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆነዋል። ጽዮን ምድረ በዳ፣ኢየሩሳሌምም ጠፍ ምድር ሆናለች። |
አባቶቻችን አንተን ያወደሱበትየቅድስናና የክብር ቤታችንበእሳት ተቃጥሏል፤ከፍ አድርገን እንመለከታቸው የነበሩት ነገሮች በሙሉ ፈራርሰዋል። |
ይሖዋ ሆይ፣ ይህ ሁሉ ሆኖ እያለ እርምጃ ከመውሰድ ትታቀባለህ? ዝም ብለህስ ታያለህ? ደግሞስ ከልክ በላይ እንድንጎሳቆል ትፈቅዳለህ? |
“አጽናኑ፣ ሕዝቤን አጽናኑ” ይላል አምላካችሁ። |
“ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፤የግዳጅ አገልግሎቷ እንዳበቃናየበደሏ ዋጋ እንደተከፈለ ንገሯት። ለሠራችው ኃጢአት ሁሉ ከይሖዋ እጅ ሙሉ ዋጋ ተቀብላለች።” |
አንድ ሰው በምድረ በዳ እንዲህ ብሎ ይጮኻል፦ “የይሖዋን መንገድ ጥረጉ! በበረሃ ለአምላካችን አውራ ጎዳናውን አቅኑ። |
ሸለቆው ሁሉ ይሞላ፤ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል። ወጣ ገባውም መሬት ይስተካከል፤ጎርበጥባጣውም ምድር ሸለቋማ ሜዳ ይሁን። |
የይሖዋ ክብር ይገለጣል፤ሥጋም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፤የይሖዋ አፍ ተናግሯልና።” |
አዳምጥ! አንድ ሰው “ጮክ ብለህ ተናገር!” አለ። ሌላውም “ምን ብዬ ልናገር?” አለ። “ሥጋ ሁሉ ለምለም ሣር ነው። ታማኝ ፍቅሩ ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው። |
ለምለሙ ሣር ይደርቃል፤አበባው ይጠወልጋል፤ምክንያቱም የይሖዋ እስትንፋስ ይነፍስበታል። ሕዝቡ በእርግጥ ለምለም ሣር ነው። |
ለምለሙ ሣር ይደርቃል፤አበባው ይጠወልጋል፤የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” |
አንቺ ለጽዮን ምሥራች የምትነግሪ ሴት ሆይ፣ከፍ ወዳለ ተራራ ውጪ። አንቺ ለኢየሩሳሌም ምሥራች የምትነግሪ ሴት ሆይ፣ድምፅሽን በኃይል ከፍ አድርጊ። ድምፅሽን ከፍ አድርጊ፤ አትፍሪ። ለይሁዳ ከተሞች “እነሆ፣ አምላካችሁ” በማለት አስታውቂ። |
እነሆ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በኃይል ይመጣል፤ክንዱም ስለ እሱ ይገዛል። እነሆ፣ የሚከፍለው ወሮታ ከእሱ ጋር ነው፤የሚመልሰውም ብድራት በፊቱ አለ። |
መንጋውን እንደ እረኛ ይንከባከባል። ግልገሎቹን በክንዱ ይሰበስባል፤በእቅፉም ይሸከማቸዋል። ግልገሎቻቸውን የሚያጠቡትን በቀስታ ይመራል። |
ውኃዎችን በእፍኙ የሰፈረ፣ሰማያትን በስንዝሩ የለካ፣ የምድርን አፈር ሰብስቦ በመስፈሪያ የያዘወይም ተራሮችን በመለኪያ፣ኮረብቶችንም በሚዛን የመዘነ ማን ነው? |
የይሖዋን መንፈስ የለካእንዲሁም አማካሪው ሆኖ ሊያስተምረው የሚችል ማን ነው? |
ማስተዋል ለማግኘት ከማን ጋር ተማከረ?የፍትሕን መንገድ ያስተማረውአሊያም እውቀትን ያካፈለው ማን ነው?ደግሞስ የእውነተኛ ማስተዋልን ጎዳና ያሳየው ማን ነው? |
እነሆ፣ ብሔራት በገንቦ ውስጥ እንዳለች ጠብታ ናቸው፤በሚዛንም ላይ እንዳለ አቧራ ይቆጠራሉ። እነሆ፣ ደሴቶችን እንደ ደቃቅ አፈር ያነሳቸዋል። |
እሳት መንደዱን እንዲቀጥል ለማድረግ የሊባኖስ ዛፎች እንኳ አይበቁም፤በውስጡም ያሉት የዱር እንስሳት የሚቃጠል መባ ለማቅረብ በቂ አይደሉም። |
ብሔራት ሁሉ በፊቱ የሌሉ ያህል ናቸው፤በእሱም ዘንድ ከምንም የማይቆጠሩና ዋጋ ቢስ ናቸው። |
አምላክን ከማን ጋር ታወዳድሩታላችሁ? ከየትኛውስ ምስል ጋር ታነጻጽሩታላችሁ? |
የእጅ ጥበብ ባለሙያ ብረት አቅልጦ ጣዖት ይሠራል፤አንጥረኛውም በወርቅ ይለብጠዋል፤የብር ሰንሰለትም ይሠራለታል። |
አንድ ሰው መዋጮ አድርጎ ለመስጠትየማይበሰብስ ዛፍ ይመርጣል። የማይወድቅ ምስል ቀርጾ እንዲያዘጋጅለትበእጅ ጥበብ ሥራ የተካነ ባለሙያ ይፈልጋል። |
ይህን አታውቁም? ደግሞስ አልሰማችሁም? ከመጀመሪያ አንስቶስ አልተነገራችሁም? የምድር መሠረት ከተጣለበት ጊዜ ጀምሮ የነበረውን ማስረጃስ አላስተዋላችሁም? |
እሱ ክብ ከሆነችው ምድር በላይ ይኖራል፤በእሷም ላይ የሚኖሩት እንደ ፌንጣ ናቸው። እሱ ሰማያትን እንደ ስስ ጨርቅ ይዘረጋል፤እንደ መኖሪያ ድንኳንም ይወጥራቸዋል። |
ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ያስወግዳል፤የምድር ፈራጆችንም እንዳልነበሩ ያደርጋል። |
ገና እንደተተከለ፣ገና እንደተዘራ፣ግንዱም በአፈር ውስጥ ሥር እንዳልሰደደ ተክል ናቸው፤ሲነፍስባቸውም ይደርቃሉ፤ነፋስም እንደ ገለባ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል። |
“እኩያው እሆን ዘንድ ከማን ጋር ታመሳስሉኛላችሁ?” ይላል ቅዱሱ። |
“ዓይናችሁን ወደ ሰማይ አንስታችሁ ተመልከቱ። እነዚህን ነገሮች የፈጠረ ማን ነው? እንደ ሠራዊት በቁጥር የሚመራቸው እሱ ነው፤ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል። ገደብ ከሌለው ብርቱ ጉልበቱና አስፈሪ ከሆነው ኃይሉ የተነሳአንዳቸውም አይጎድሉም። |
ያዕቆብ ሆይ፣ እስራኤልም ሆይ፣‘መንገዴ ከይሖዋ ተሰውሯል፤ከአምላክ ፍትሕ አላገኝም’ ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? |
ይህን አታውቅም? ደግሞስ አልሰማህም? የምድር ዳርቻዎች ፈጣሪ የሆነው ይሖዋ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነው። እሱ ፈጽሞ አይደክምም ወይም አይዝልም። ማስተዋሉ አይመረመርም። |
ለደከመው ኃይል፣ጉልበት ለሌላቸውም የተሟላ ብርታት ይሰጣል። |
ወንዶች ልጆች ይደክማሉ፤ ደግሞም ይዝላሉ፤ወጣቶችም ተደናቅፈው ይወድቃሉ፤ |
ይሖዋን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ኃይላቸው ይታደሳል። እንደ ንስር በክንፍ ወደ ላይ ይወጣሉ። ይሮጣሉ፤ አይዝሉም፤ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።” |
“ለአርዔል፣ ዳዊት ለሰፈረባት ከተማ ለአርዔል ወዮላት! በዓመት ላይ ዓመት ጨምሩ፤ዓመታዊ በዓሎቻችሁን ማክበራችሁን ቀጥሉ። |
እኔ ግን በአርዔል ላይ የሚያስጨንቅ ነገር አመጣለሁ፤ለቅሶና ዋይታም ይሆናል፤እሷም ለእኔ፣ እንደ አምላክ የመሠዊያ ምድጃ ትሆናለች። |
አንቺን ለማጥቃት በዙሪያሽ እሰፍራለሁ፤በሹል እንጨት አጥርሻለሁ፤በአንቺም ዙሪያ ቅጥር እገነባለሁ። |
ትወድቂያለሽ፤ ትዋረጃለሽም፤መሬት ላይ ሆነሽ ትናገሪያለሽ፤የምትናገሪው ነገር በአፈር ይታፈናል። ድምፅሽ እንደ መናፍስት ጠሪ ድምፅከመሬት ይመጣል፤ቃልሽም ከአፈር ይጮኻል። |
የጠላቶችሽ ሠራዊት እንደላመ ዱቄት ይሆናል፤የጨቋኞች መንጋ ተጠርጎ እንደሚሄድ ገለባ ይሆናል። ይህም ሳይታሰብ፣ በቅጽበት ይፈጸማል። |
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ትኩረቱን ወደ አንቺ በማዞርበነጎድጓድ፣ በምድር መናወጥ፣ በታላቅ ድምፅ፣በውሽንፍር፣ በአውሎ ነፋስና በሚባላ የእሳት ነበልባል ያድንሻል።” |
በዚያን ጊዜ አርዔልን የሚወጉ የብሔራት ሠራዊት ሁሉ፣ይኸውም ጦርነት የሚከፍቱባት ሁሉ፣በእሷ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ማማዎችን የሚሠሩናጭንቀት ላይ የሚጥሏት ሁሉእንደ ሕልም፣ በሌሊትም እንደሚታይ ራእይ ይሆናሉ። |
አዎ፣ የተራበ ሰው በሕልሙ ሲበላ ቆይቶሲነቃ ግን ረሃቡ እንደማይለቀው ሁሉ፣ደግሞም የተጠማ ሰው በሕልሙ ሲጠጣ ቆይቶሲነቃ ግን ዝሎና ተጠምቶ እንደሚነሳ ሁሉ እንዲሁ ይሆናል። በጽዮን ተራራ ላይ ጦርነት የሚከፍቱ የብሔራት ሠራዊትም ሁሉተመሳሳይ ነገር ይደርስባቸዋል። |
ክው በሉ፤ ተደነቁም፤ዓይናችሁን ጨፍኑ፤ ዕውሮችም ሁኑ። በወይን ጠጅ አይሁን እንጂ ሰክረዋል፤በሚያሰክር መጠጥ አይሁን እንጂ ተንገዳግደዋል። |
ይሖዋ ኃይለኛ የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋልና፤ዓይኖቻችሁን ይኸውም ነቢያትን ጨፍኖባችኋል፤ራሶቻችሁን ይኸውም ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል። |
የሁሉ ነገር ራእይ እንደታሸገ መጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል። መጽሐፉን ማንበብ ለሚችል ሰው “እባክህ፣ ጮክ ብለህ አንብበው” ብለው ሲሰጡት “ታሽጓልና አልችልም” ይላል። |
መጽሐፉንም ማንበብ ለማይችል ሰው “እባክህ፣ ይህን አንብበው” ብለው ሲሰጡት “ፈጽሞ ማንበብ አልችልም” ይላል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.