text stringlengths 4 267 |
|---|
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ ወደ እኔ የሚቀርበው በአፉ ብቻ ነው፤በከንፈሩም ያከብረኛል፤ልቡ ግን ከእኔ እጅግ የራቀ ነው፤እኔንም የሚፈራው፣ ሰዎች ያስተማሩትን ትእዛዛት በማክበር ነው። |
ስለዚህ እኔ በእነዚህ ሰዎች ላይ ዳግመኛ የሚያስደንቁ ነገሮች አደርጋለሁ፤በድንቅ ላይ ድንቅ ነገር እፈጽማለሁ፤የጥበበኞቻቸውም ጥበብ ይጠፋል፤የአስተዋዮቻቸውም ማስተዋል ይሰወራል።” |
ዕቅዳቸውን ከይሖዋ ለመሰወር ከፍተኛ ጥረት ለሚያደርጉ ወዮላቸው! “ማን ያየናል?ማንስ ያውቅብናል?” በማለት ተግባራቸውን በጨለማ ቦታ ያከናውናሉ። |
እናንተ ሰዎች፣ ነገር ታጣምማላችሁ! ሸክላ ሠሪው እንደ ሸክላው ሊቆጠር ይገባል? የተሠራው ነገር ስለ ሠሪው “እሱ አልሠራኝም” ማለቱ ተገቢ ነው? ደግሞስ ዕቃው ሠሪውን “ማስተዋል የለውም” ይላል? |
በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊባኖስ ወደ ፍራፍሬ እርሻነት ይለወጣል፤የፍራፍሬ እርሻውም እንደ ጫካ ይቆጠራል። |
በዚያ ቀን፣ መስማት የተሳናቸው ሰዎች የመጽሐፉን ቃል ይሰማሉ፤የዓይነ ስውራኑም ዓይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ተላቀው ያያሉ። |
የዋሆች በይሖዋ እጅግ ሐሴት ያደርጋሉ፤በሰዎች መካከል ያሉ ድሆችም በእስራኤል ቅዱስ ደስ ይላቸዋል። |
ጨቋኙ ያከትምለታልና፤ጉረኛውም ያበቃለታል፤ሌሎችን ለመጉዳት አሰፍስፈው የሚጠባበቁ ሁሉ ይጠፋሉ፤ |
ሌሎችን በውሸት ቃል በደለኛ የሚያደርጉ፣በከተማዋ በር፣ በተሟጋቹ ላይ ወጥመድ የሚዘረጉናመሠረተ ቢስ በሆነ ክስ ጻድቁን ሰው ፍትሕ የሚነፍጉ ይጠፋሉ። |
ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠው ይሖዋ ለያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፦ “ያዕቆብ ከእንግዲህ አያፍርም፤ፊቱም ከእንግዲህ አይገረጣም። |
የእጆቼ ሥራ የሆኑትን ልጆቹንበመካከሉ በሚያይበት ጊዜ፣ስሜን ይቀድሳሉና፤አዎ፣ የያዕቆብን ቅዱስ ይቀድሳሉ፤የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ። |
በመንፈስ የባዘኑ ማስተዋል ያገኛሉ፤የሚያጉረመርሙም የሚሰጣቸውን ትምህርት ይቀበላሉ።” |
ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “አንድ ትልቅ ጽላት ወስደህ በብዕር ‘ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ’ ብለህ ጻፍ። |
ታማኝ ምሥክሮች የሆኑት ካህኑ ኦርዮና የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ደግሞ የጽሑፍ ማረጋገጫ ይስጡኝ።” |
እኔም ከነቢዪቱ ጋር ተገናኘሁ፤ እሷም ፀነሰች፤ በኋላም ወንድ ልጅ ወለደች። ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ስሙን ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ ብለህ ጥራው፤ |
ልጁ ‘አባዬ!’ እና ‘እማዬ!’ ብሎ መጥራት ከመቻሉ በፊት የደማስቆ ሀብትና የሰማርያ ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወሰዳል።” |
ይሖዋ በድጋሚ እንዲህ አለኝ፦ |
“ይህ ሕዝብ ቀስ ብለው የሚወርዱትን የሺሎአ ውኃዎች ንቆበረጺንና በረማልያህ ልጅ ሐሴት ስላደረገ |
እነሆ፣ ይሖዋ ብርቱ የሆኑትንና ከፍተኛ መጠን ያላቸውን የወንዙን ውኃዎች ይኸውምየአሦርን ንጉሥና ክብሩን ሁሉበእነሱ ላይ ያመጣባቸዋል። እሱም የውኃ መውረጃዎቹን ሁሉ ሞልቶ ይፈስሳል፤ዳርቻዎቹንም ሁሉ ያጥለቀልቃል፤ |
ይሁዳንም ጠራርጎ ይሄዳል። አካባቢውን እያጥለቀለቀ በማለፍ እስከ አንገት ይደርሳል፤አማኑኤል ሆይ፣ የተዘረጉት ክንፎቹምድርህን ከዳር እስከ ዳር ይሸፍናሉ!” |
እናንተ ሕዝቦች፣ ጉዳት አድርሱባቸው፤ ሆኖም ድምጥማጣችሁ ይጠፋል። ራቅ ባሉ የምድር ክፍሎች የምትኖሩ ሁሉ አዳምጡ! ለውጊያ ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ድምጥማጣችሁ ይጠፋል! ለውጊያ ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ድምጥማጣችሁ ይጠፋል! |
ዕቅድ አውጡ፤ ይሁንና ይጨናገፋል! የፈለጋችሁትን ተናገሩ፤ ሆኖም አይሳካም፤አምላክ ከእኛ ጋር ነውና! |
ይሖዋ ብርቱ እጁን በእኔ ላይ አድርጎ የዚህን ሕዝብ መንገድ እንዳልከተል ለማስጠንቀቅ እንዲህ አለኝ፦ |
“ይህ ሕዝብ ‘ሴራ እንጠንስስ!’ ሲል እናንተ ‘በሴራው ተባበሩ!’ አትበሉ፤ እነሱ የሚያስፈራቸውን ነገር አትፍሩ፤አትንቀጥቀጡለትም። |
ቅዱስ አድርጋችሁ ልትመለከቱ የሚገባው የሠራዊት ጌታ ይሖዋን ነው፤ልትፈሩ የሚገባው እሱን ነው፤እንዲሁም ልትንቀጠቀጡ የሚገባው ለእሱ ነው።” |
እሱ እንደ መቅደስ ይሆናል፤ለሁለቱ የእስራኤል ቤቶች ግንእንደሚያሰናክል ድንጋይናእንደሚያደናቅፍ ዓለት፣ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎችምእንደ ወጥመድና እንደ አሽክላ ይሆንባቸዋል። |
ከእነሱ መካከል ብዙዎቹ ይደናቀፋሉ፣ ይወድቃሉ፣ ይሰበራሉ፤ወጥመድ ውስጥ ገብተው ይያዛሉ። |
በጽሑፍ የሰፈረውን ማረጋገጫ ጠቅልለው፤ሕጉን በደቀ መዛሙርቴ መካከል አሽገው! |
እኔም ፊቱን ከያዕቆብ ቤት የሰወረውን ይሖዋን እጠባበቃለሁ፤ በእሱም ተስፋ አደርጋለሁ። |
እነሆ፣ እኔና ይሖዋ የሰጠኝ ልጆች በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከይሖዋ ለእስራኤል እንደተሰጡ ምልክቶችና ተአምራት ነን። |
እነሱም “የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሹኩትን መናፍስት ጠሪዎች ወይም ጠንቋዮች ጠይቁ” ቢሏችሁ፣ አንድ ሕዝብ መጠየቅ ያለበት የራሱን አምላክ አይደለም? ስለ ሕያዋንስ ሙታንን መጠየቁ ተገቢ ነው? |
ከዚህ ይልቅ ሕጉንና የማረጋገጫ ሰነዱን መመርመር ይገባቸዋል! ከዚህ ቃል ጋር የሚስማማ ነገር ሳይናገሩ ሲቀሩ ብርሃን አይበራላቸውም። |
እያንዳንዱም ተጎሳቁሎና ተርቦ በምድሪቱ ላይ ይንከራተታል፤ ከመራቡና ከመበሳጨቱ የተነሳ ወደ ላይ እያየ ንጉሡንና አምላኩን ይረግማል። |
ከዚያም ወደ ምድር ይመለከታል፤ የሚያየውም ነገር ጭንቀትና ጨለማ፣ ግራ የሚያጋባ ሁኔታ፣ አስቸጋሪ ወቅትና ብርሃን የሌለበት ፅልማሞት ብቻ ይሆናል። |
ኤርምያስ አምላካቸው ይሖዋ ለእነሱ እንዲነግራቸው የላከውን የአምላካቸውን የይሖዋን ቃል ሁሉ፣ አንድም ሳያስቀር ለሕዝቡ በሙሉ ተናግሮ ሲጨርስ |
የሆሻያህ ልጅ አዛርያስ፣ የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን እና እብሪተኛ የሆኑት ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፦ “የምትናገረው ነገር ውሸት ነው! አምላካችን ይሖዋ ‘በግብፅ ለመኖር ወደዚያ አትሂዱ’ ብሎ አላከህም። |
ከዚህ ይልቅ ከለዳውያን እንዲገድሉን ወይም ወደ ባቢሎን በግዞት እንዲወስዱን በእጃቸው አሳልፈህ ትሰጠን ዘንድ በእኛ ላይ ያነሳሳህ የነሪያህ ልጅ ባሮክ ነው።” |
በመሆኑም የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን፣ የሠራዊቱ አለቆች ሁሉና ሕዝቡ በሙሉ በይሁዳ ምድር እንዲቀመጡ ያዘዛቸውን የይሖዋን ቃል አልሰሙም። |
እንዲያውም የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን እና የሠራዊቱ አለቆች በሙሉ፣ በይሁዳ ምድር ለመኖር ከተበተኑባቸው ብሔራት ሁሉ የተመለሱትን የይሁዳ ቀሪዎች በሙሉ ይዘው ሄዱ። |
ወንዶቹን፣ ሴቶቹን፣ ልጆቹን፣ የንጉሡን ሴቶች ልጆችና የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን ከሳፋን ልጅ፣ ከአኪቃም ልጅ ከጎዶልያስ ጋር የተዋቸውን ሁሉ እንዲሁም ነቢዩን ኤርምያስንና የነሪያህን ልጅ ባሮክን ይዘው ሄዱ። |
የይሖዋን ቃል ባለመታዘዝ ወደ ግብፅ ምድር ገቡ፤ እስከ ጣፍነስ ድረስም ሄዱ። |
ከዚያም የይሖዋ ቃል በጣፍነስ እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ |
“ትላልቅ ድንጋዮችን ውሰድና አይሁዳውያኑ እያዩ በጣፍነስ በሚገኘው በፈርዖን ቤት መግቢያ፣ ከጡብ ከተሠራው መደብ ሥር ሸሽገህ በቅጥራን ለስናቸው። |
ከዚያም እንዲህ በላቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ አገልጋዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን እጠራዋለሁ፤ ዙፋኑንም እኔ ከሸሸግኳቸው ከእነዚህ ድንጋዮች በላይ አስቀምጣለሁ፤ ንጉሣዊ ድንኳኑንም በእነሱ ላይ ይዘረጋል። |
እሱም መጥቶ የግብፅን ምድር ይመታል። ገዳይ መቅሰፍት የሚገባው ሁሉ ለገዳይ መቅሰፍት፣ በምርኮ መወሰድ የሚገባው ሁሉ ለምርኮ እንዲሁም ሰይፍ የሚገባው ሁሉ ለሰይፍ ይሰጣል። |
የግብፅን አማልክት ቤቶችም በእሳት አያይዛለሁ፤ እሱም ያቃጥላቸዋል፤ ማርኮም ይወስዳቸዋል። እረኛ ልብሱን እንደሚጎናጸፍ የግብፅን ምድር ይጎናጸፋል፤ ከዚያም ቦታ በሰላም ይሄዳል። |
በግብፅም ምድር የሚገኙትን የቤትሼሜሽን ዓምዶች ይሰባብራል፤ የግብፅን አማልክት ቤቶችም በእሳት ያቃጥላል።”’” |
ከዚያም የሠራዊቱ አለቆች ሁሉ፣ የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን፣ የሆሻያህ ልጅ የዛንያህ እና ሕዝቡ ሁሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ ቀርበው |
ነቢዩ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፦ “ሞገስ ለማግኘት የምናቀርበውን ልመና እባክህ ስማ፤ ስለ እኛና ስለ እነዚህ ቀሪዎች ሁሉ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ጸልይ፤ ይኸው እንደምታየው ከብዙዎች መካከል የቀረነው ጥቂቶች ብቻ ነን። |
አምላክህ ይሖዋ በየት መሄድ እንደሚገባንና ምን ማድረግ እንዳለብን ይንገረን።” |
ነቢዩ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እሺ፣ ሰምቻችኋለሁ፤ በጠየቃችሁኝ መሠረት ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋ እጸልያለሁ፤ ይሖዋ የሚመልስላችሁንም ቃል ሁሉ እነግራችኋለሁ። አንድም ቃል አላስቀርባችሁም።” |
እነሱም ለኤርምያስ እንዲህ ብለው መለሱለት፦ “አምላክህ ይሖዋ በአንተ በኩል እንዳዘዘን ባናደርግ፣ ይሖዋ በእኛ ላይ እውነተኛና ታማኝ ምሥክር ይሁን። |
የአምላካችንን የይሖዋን ቃል በመታዘዝ መልካም እንዲሆንልን፣ ነገሩ ቢስማማንም ባይስማማንም፣ ወደ እሱ የምንልክህ አምላካችን ይሖዋ የሚለውን ሁሉ እንፈጽማለን።” |
ከአሥር ቀን በኋላ የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ። |
ስለዚህ የቃሬሃን ልጅ ዮሃናንን፣ ከእሱ ጋር የነበሩትን የሠራዊቱን አለቆች ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡን ሁሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ ድረስ ጠራ። |
እንዲህም አላቸው፦ “ሞገስ ለማግኘት ያሰማችሁትን ልመና በፊቱ እንዳቀርብ ወደ እሱ የላካችሁኝ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ |
‘በእርግጥ በዚህች ምድር ላይ የምትኖሩ ከሆነ፣ እገነባችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፤ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም፤ በእናንተ ላይ ባመጣሁት ጥፋት እጸጸታለሁና። |
ከምትፈሩት ከባቢሎን ንጉሥ የተነሳ አትሸበሩ።’ “‘ከእሱ የተነሳ አትፍሩ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘አድናችሁና ከእጁ እታደጋችሁ ዘንድ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና። |
ምሕረት አደርግላችኋለሁ፤ እሱም ምሕረት ያደርግላችኋል፤ ወደ ገዛ ምድራችሁም ይመልሳችኋል። |
“‘እናንተ ግን “አይሆንም፤ በዚህች ምድር ላይ አንኖርም!” ብትሉና የአምላካችሁን የይሖዋን ቃል ባትታዘዙ፣ |
ደግሞም “አይሆንም፤ ጦርነት ወደማናይበት፣ የቀንደ መለከት ድምፅ ወደማንሰማበት ወይም ምግብ አጥተን ወደማንራብበት ወደ ግብፅ ምድር እንሄዳለን፤ በዚያም እንኖራለን” ብትሉ፣ |
እናንተ የይሁዳ ቀሪዎች ሆይ፣ እንግዲህ የይሖዋን ቃል ስሙ። የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ወደ ግብፅ ለመግባት ቆርጣችሁ ከተነሳችሁና በዚያ ለመኖር ከሄዳችሁ፣ |
የፈራችሁት ሰይፍ ራሱ በግብፅ ምድር ያገኛችኋል፤ የፈራችሁትም ረሃብ ወደ ግብፅ ተከትሏችሁ ይሄዳል፤ በዚያም ትሞታላችሁ። |
በዚያ ለመኖር ሲሉ ወደ ግብፅ ለመሄድ ቆርጠው የተነሱ ሰዎች ሁሉ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር ይሞታሉ። በእነሱ ላይ ከማመጣው ጥፋት ከመካከላቸው የሚተርፍ ወይም የሚያመልጥ አይኖርም።”’ |
“የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ወደ ግብፅ ከሄዳችሁ፣ ቁጣዬና ንዴቴ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ እንደወረደ ሁሉ በእናንተም ላይ ቁጣዬ ይወርዳል፤ እናንተም ለእርግማን፣ ለውርደትና ለነቀፋ ትዳረጋላችሁ፤ መቀጣጫም ትሆናላችሁ፤ ይህን ቦታም ዳግመኛ አታዩትም።’ |
“የይሁዳ ቀሪዎች ሆይ፣ ይሖዋ በእናንተ ላይ ተናግሯል። ወደ ግብፅ አትሂዱ። ዛሬ እንዳስጠነቀቅኳችሁ በእርግጥ እወቁ፤ |
በደላችሁም ሕይወታችሁን እንደሚያሳጣችሁ እወቁ። እንዲህ ስትሉ ወደ ይሖዋ አምላካችሁ ልካችሁኝ ነበርና፦ ‘ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ስለ እኛ ጸልይ፤ አምላካችን ይሖዋም የሚለውን ነገር ሁሉ ንገረን፤ እኛም የተባልነውን እናደርጋለን።’ |
እኔም ዛሬ ነግሬአችኋለሁ፤ እናንተ ግን የአምላካችሁን የይሖዋን ቃልም ሆነ ወደ እናንተ ልኮኝ የነገርኳችሁን ሁሉ አትታዘዙም። |
ስለዚህ ሄዳችሁ ልትኖሩበት በፈለጋችሁት ቦታ በሰይፍ፣ በረሃብና በቸነፈር እንደምትሞቱ በእርግጥ እወቁ።” |
በሰባተኛው ወር፣ ከንጉሣውያን ቤተሰብ የሆነውና ከንጉሡ ባለሥልጣናት አንዱ የነበረው የኤሊሻማ ልጅ፣ የነታንያህ ልጅ እስማኤል ከሌሎች አሥር ሰዎች ጋር ሆኖ በምጽጳ ወዳለው ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ። በምጽጳ አንድ ላይ ምግብ እየበሉ ሳለ |
የነታንያህ ልጅ እስማኤልና ከእሱ ጋር የነበሩት አሥሩ ሰዎች ተነስተው የሳፋንን ልጅ፣ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መተው ገደሉት። በዚህ መንገድ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በምድሪቱ ላይ የሾመውን ሰው ገደለው። |
በተጨማሪም እስማኤል በምጽጳ ከጎዶልያስ ጋር የነበሩትን አይሁዳውያን በሙሉ እንዲሁም በዚያ የነበሩትን ከለዳውያን ወታደሮች ገደላቸው። |
ጎዶልያስ በተገደለ በሁለተኛው ቀን ስለ ሁኔታው ማንም ሰው ከማወቁ በፊት፣ |
ከሴኬም፣ ከሴሎና ከሰማርያ 80 ሰዎች መጡ። ጢማቸውን ላጭተው፣ ልብሳቸውን ቀደውና ሰውነታቸውን ተልትለው የነበረ ሲሆን በይሖዋ ቤት የሚያቀርቧቸውን የእህል መባዎችና ነጭ ዕጣን ይዘው ነበር። |
የነታንያህ ልጅ እስማኤልም ከእነሱ ጋር ለመገናኘት ከምጽጳ ወጥቶ እያለቀሰ ሄደ። ባገኛቸው ጊዜ “ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ኑ” አላቸው። |
ሆኖም ወደ ከተማዋ ሲገቡ የነታንያህ ልጅ እስማኤልና ከእሱ ጋር የነበሩት ሰዎች አረዷቸው፤ ወደ ውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድም ጣሏቸው። |
ይሁንና በመካከላቸው የነበሩ አሥር ሰዎች እስማኤልን “በእርሻ ውስጥ የደበቅነው የተከማቸ እህል ይኸውም ስንዴ፣ ገብስ፣ ዘይትና ማር ስላለን አትግደለን” አሉት። ስለዚህ ከወንድሞቻቸው ጋር አልገደላቸውም። |
እስማኤል የገደላቸውን ሰዎች አስከሬን በሙሉ በአንድ ትልቅ የውኃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ውስጥ ጣለ፤ ይህ ጉድጓድ ንጉሥ አሳ የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ባስፈራራው ጊዜ የሠራው ነበር። የነታንያህ ልጅ እስማኤል ይህን ጉድጓድ ባረዳቸው ሰዎች አስከሬን ሞላው። |
እስማኤል በምጽጳ የቀረውን ሕዝብ በሙሉ ይኸውም የዘቦች አለቃ የሆነው ናቡዛራዳን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው ገዢ አድርጎ የሾመባቸውን፣ የንጉሡን ሴቶች ልጆችና በምጽጳ የቀሩትን ሰዎች ሁሉ ማረከ። የነታንያህ ልጅ እስማኤል እነሱን ማርኮ ወደ አሞናውያን ለመሻገር ጉዞ ጀመረ። |
የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን እና ከእሱ ጋር የነበሩት የሠራዊቱ አለቆች የነታንያህ ልጅ እስማኤል ስላደረገው ክፉ ነገር ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ |
ከእነሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች በሙሉ ይዘው ከነታንያህ ልጅ ከእስማኤል ጋር ለመዋጋት ሄዱ፤ እሱንም በገባኦን ባለው በታላቁ ውኃ አጠገብ አገኙት። |
ከእስማኤል ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ የቃሬሃን ልጅ ዮሃናንን እና ከእሱ ጋር የነበሩትን የሠራዊቱን አለቆች ሁሉ ባዩ ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው። |
ከዚያም እስማኤል ከምጽጳ ማርኮ የወሰዳቸው ሰዎች ሁሉ ዞረው ከቃሬሃ ልጅ ከዮሃናን ጋር ተመለሱ። |
የነታንያህ ልጅ እስማኤልና ከእሱ ጋር የነበሩት ስምንት ሰዎች ግን ከዮሃናን ፊት ሸሽተው ወደ አሞናውያን ሄዱ። |
የቃሬሃ ልጅ ዮሃናን እና ከእሱ ጋር የነበሩት የሠራዊቱ አለቆች ሁሉ ከምጽጳ የተወሰዱትን የቀሩትን ሰዎች ይዘዋቸው ሄዱ፤ እነዚህ ሰዎች የነታንያህ ልጅ እስማኤል፣ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ከገደለው በኋላ ዮሃናን እና የሠራዊቱ አለቆች ከእሱ የታደጓቸው ናቸው። ወንዶቹን፣ ወታደሮቹን፣ ሴቶቹንና ልጆቹን እንዲሁም የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱን ከገባኦን መልሰው አመጧቸው። |
ከዚያም ተነስተው ሄዱ፤ ወደ ግብፅ ለመሄድ ስላሰቡም በቤተልሔም አጠገብ በሚገኘው በኪምሃም ማረፊያ ቦታ ቆዩ፤ |
ይህን ያደረጉት ከከለዳውያን የተነሳ ነው። የነታንያህ ልጅ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በምድሪቱ ላይ ሾሞት የነበረውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ስለገደለው ከለዳውያንን ፈርተዋቸው ነበር። |
“የይሁዳ ኃጢአት በብረት ብዕር ተጽፏል። በሾለ የአልማዝ ጫፍ በልባቸው ጽላትናበመሠዊያዎቻቸው ቀንዶች ላይ ተቀርጿል፤ |
ያን ጊዜ ወንዶች ልጆቻቸው ከፍ ባሉ ኮረብቶች ላይ ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ አጠገብ ያሉትንመሠዊያዎቻቸውንና የማምለኪያ ግንዶቻቸውን ያስታውሳሉ፤ |
በአውላላ ሜዳ ላይ ባሉት ተራሮች ላይ ያሉትንም ያስባሉ። ንብረትህን ይኸውም ውድ ሀብትህን ሁሉ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣለሁ፤አዎ፣ በመላው ክልልህ ካለው ኃጢአት የተነሳ ከፍ ያሉ ቦታዎችህ እንዲበዘበዙ አደርጋለሁ። |
የሰጠሁህን ርስት በገዛ ፈቃድህ አሳልፈህ ትሰጣለህ። በማታውቀውም ምድር ጠላቶችህን እንድታገለግል አደርግሃለሁ፤ቁጣዬን እንደ እሳት አቀጣጥለሃልና። እሳቱም ለዘላለም ይነዳል።” |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሰዎች የሚታመን፣በሰብዓዊ ኃይል የሚመካናልቡ ከይሖዋ የራቀ ሰው የተረገመ ነው። |
በበረሃ ብቻውን እንዳለ ዛፍ ይሆናል። መልካም ነገር ሲመጣ አያይም፤ይልቁንም በምድረ በዳ ደረቅ በሆኑ ስፍራዎች፣ማንም መኖር በማይችልበት የጨው ምድር ይኖራል። |
በይሖዋ የሚታመን፣መመኪያውም ይሖዋ የሆነ ሰው የተባረከ ነው። |
በውኃዎች አጠገብ እንደተተከለ፣ሥሮቹን ወደ ጅረት እንደሚሰድ ዛፍ ይሆናል። ሙቀት ሲመጣ አያስተውልም፤ከዚህ ይልቅ ቅጠሉ ሁልጊዜ ይለመልማል። ድርቅ በሚከሰትበት ዓመትም ምንም አይጨነቅም፤ፍሬ ማፍራቱንም አያቋርጥም። |
ልብ ከምንም ነገር በላይ ከዳተኛ ነው፤ ማንኛውንም ነገር ከማድረግ አይመለስም። ማንስ ሊያውቀው ይችላል? |
እኔ ይሖዋ፣ ለእያንዳንዱ እንደ መንገዱ፣እንደ ሥራውም ፍሬ ለመስጠትልብን እመረምራለሁ፤የውስጥ ሐሳብንም እፈትናለሁ። |
በማጭበርበር ሀብት የሚያከማች ሰው፣ያልጣለችውን እንቁላል እንደምትሰበስብ ቆቅ ነው። በዕድሜው አጋማሽ ላይ ሀብቱ ትቶት ይሄዳል፤በመጨረሻም የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ሰው መሆኑ ይረጋገጣል።” |
ከመጀመሪያ አንስቶ ክብራማ የሆነ ዙፋን ከፍ ከፍ ብሏል፤እሱም መቅደሳችን ነው። |
የእስራኤል ተስፋ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣አንተን የሚተዉ ሁሉ ያፍራሉ። አንተን የሚክዱ ስማቸው በአፈር ላይ ይጻፋል፤ምክንያቱም የሕያው ውኃ ምንጭ የሆነውን ይሖዋን ትተዋል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.