text
stringlengths
4
267
በተጨማሪም ስጦታውን በአግባቡ በመጠቀም እንደ ተራ ነገር እንደማትቆጥረው ታሳያለህ።
ይሖዋ ለመኖር የሚያስፈልጉንንና ለደስታችን አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ነገሮችን ምንም ሳያጓድል ይሰጠናል።
ይህ ታዲያ እኛም በአጸፋው እንድንወደው አያነሳሳንም?
ይሖዋ እስራኤላውያንን ለበርካታ መቶ ዓመታት በፍቅር የተንከባከባቸው ሲሆን የተትረፈረፈ ቁሳዊም ሆነ መንፈሳዊ በረከት አፍስሶላቸዋል።
ይሁንና እነዚህን በረከቶች በቀጣይነት ማግኘታቸው የተመካው ምድሪቱ ያፈራችውን መጀመሪያ የደረሰውን ምርጥ ፍሬ ዘወትር ለይሖዋ መስጠትን የሚያዘውን ሕግ ጨምሮ መላውን የአምላክ ሕግ በመታዘዛቸው ላይ ነበር።
እስራኤላውያን እንዲህ በማድረግ የይሖዋን ፍቅርና በረከት አቅልለው እንደማይመለከቱ ማሳየት ይችላሉ።
ይሖዋ፣ የሰው ልጆችን የፈጠረው አስደናቂ ችሎታዎች እንዲኖሯቸው አድርጎ ነው።
ስለ ወደፊቱ ጊዜ ማቀድና ለችግሮቻችን መፍትሔ ማበጀት እንድንችል የማመዛዘን ችሎታ ሰጥቶናል።
ደግሞም ያቀድነውን ነገር ለመፈጸም የሚያስችል ኃይል ስለሰጠን ግባችን ላይ መድረስ እንችላለን።
በተጨማሪም ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር መለየት የምንችልበት ሕሊና ሰጥቶናል፤ ይህ በተፈጥሮ ያገኘነው ችሎታ ከመጥፎ ድርጊቶች እንድንርቅ እንዲሁም የሠራናቸውን ስህተቶች እንድናርም ይረዳናል።
ይሖዋ፣ ችሎታዎቻችንን መልካም ነገር ለማድረግ ልንጠቀምባቸው እንደሚገባ በቃሉ አማካኝነት በተደጋጋሚ አሳስቦናል።
ለምሳሌ ያህል፣ በዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ የሚከተሉት ሐሳቦች ይገኛሉ፦ የትጉ ሰው ዕቅድ ለስኬት ያበቃዋል እንዲሁም እጅህ የሚያገኘውን ሥራ ሁሉ በሙሉ ኃይልህ አከናውን።
በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ደግሞ አጋጣሚ እስካገኘን ድረስ ለሁሉም መልካም እናድርግ እንዲሁም እያንዳንዳችሁ በተቀበላችሁት ስጦታ መሠረት የተሰጣችሁን ስጦታ አንዳችሁ ሌላውን ለማገልገል ተጠቀሙበት የሚሉ ምክሮች ይገኛሉ።
ከዚህ በግልጽ ማየት እንደሚቻለው፣ ይሖዋ ራሳችንንም ሆነ ሌሎችን የሚጠቅም ነገር እንድናደርግ ይፈልጋል።
የይሖዋ ሕዝቦች ስለ አምላክ ከማወቃቸው፣ ለእሱ ፍቅር ከማዳበራቸውና እሱን ማገልገል ከመጀመራቸው በፊት ያፈሯቸው የነበሩትን ፍሬዎች አስወግደዋል።
ቀድሞ ከሚያደርጓቸው ነገሮች መካከል አንዳንዶቹን አሁን ያፍሩባቸዋል’፤ ደግሞም የእነዚህ ነገሮች መጨረሻ ሞት ነው።
ይሖዋን ሲያውቁ ግን አኗኗራቸውን ቀየሩ።
ጳውሎስ ደብዳቤውን ከጻፈላቸው የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ብዙዎቹ እንዲህ ዓይነት ሕይወት ነበራቸው።
አንዳንዶቹ ጣዖት አምላኪዎች፣ አመንዝሮች፣ ግብረ ሰዶማውያን፣ ሌቦች፣ ሰካራሞች እና እንደነዚህ ያሉትን ኃጢአቶች የሚፈጽሙ ሰዎች ነበሩ።
ይሁንና ታጥበው ነጽተዋል እንዲሁም ተቀድሰዋል።
የሮም ጉባኤ አባላት የሆኑ አንዳንድ ክርስቲያኖች ሁኔታም ተመሳሳይ ነበር።
ጳውሎስ በመንፈስ መሪነት እንዲህ ሲል ጽፎላቸዋል፦ ሰውነታችሁን የክፋት መሣሪያ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፤ ከዚህ ይልቅ ከሞት ወደ ሕይወት እንደተሻገሩ ሰዎች አድርጋችሁ ራሳችሁን ለአምላክ አቅርቡ፤ ሰውነታችሁንም የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለአምላክ አቅርቡ።
ጳውሎስ፣ እነዚህ ክርስቲያኖች ምንጊዜም መንፈሳዊ ንጽሕናቸውን ከጠበቁ ከአምላክ ጸጋ ጥቅም ማግኘታቸውን መቀጠል እንደሚችሉ እርግጠኛ ነበር።
ኢዮርብዓም ንጉሥ በነበረበት ዘመን ይሖዋ ለዚህ ከሃዲ ንጉሥ ከባድ የፍርድ መልእክት እንዲያስተላልፍ አንድ ነቢይ ከይሁዳ ላከ።
ትሑት የነበረው ይህ ነቢይ የይሖዋን መልእክት በታማኝነት ያደረሰ ሲሆን ይሖዋም አገልጋዩን ከንጉሡ አስፈሪ ቁጣ ጠብቆታል።
ነቢዩ ወደ ቤቱ ሲመለስ በቤቴል አቅራቢያ ከሚኖር አንድ አረጋዊ ሰው ጋር በድንገት ተገናኘ።
አረጋዊው ሰው የይሖዋ ነቢይ እንደሆነ ተናገረ።
ሰውዬው፣ ወጣቱን ነቢይ በማታለል በእስራኤል ምግብ እንዳይበላና ውኃ እንዳይጠጣ እንዲሁም በመጣበት መንገድ እንዳይመለስ ይሖዋ የሰጠውን ግልጽ መመሪያ እንዲጥስ አደረገው።
ይሖዋ በዚህ አልተደሰተም።
ይህ የይሖዋ ነቢይ ወደ ቤቱ ሲመለስ አንድ አንበሳ መንገድ ላይ አገኘውና ገደለው።
በአንድ ወቅት ልኩን ያውቅ የነበረው ይህ ነቢይ የዚያን አታላይ አረጋዊ ቃል በመስማት እንዲህ ያለ የእብሪት እርምጃ የወሰደው ለምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ የሚናገረው ነገር የለም።
ሆኖም ይህ ነቢይ ልኩን አውቆ ከአምላክ ጋር መሄድ እንዳለበት ጨርሶ የዘነጋ ይመስላል።
የአዳምና የሔዋን ዘሮች ታዛዥ ሳይሆኑ ከቀሩት ወላጆቻቸው አለፍጽምናንና ሞትን ወርሰዋል።
ሆኖም የመምረጥ ነፃነታቸውን አላጡም።
አምላክ የእስራኤልን ብሔር የያዘበት መንገድ ይህን ያሳያል።
ይሖዋ፣ እስራኤላውያን የእሱ ልዩ ንብረት ለመሆን ወይም ላለመሆን መምረጥ እንደሚችሉ በአገልጋዩ በሙሴ አማካኝነት ገልጾላቸው ነበር።
ታዲያ እስራኤላውያን ምን ምላሽ ሰጡ?
በአንድ ድምፅ ይሖዋ የተናገረውን ሁሉ ለመፈጸም ፈቃደኞች ነን በማለት ለስሙ የተመረጠ ሕዝብ መሆን የሚያስከትለውን ኃላፊነት ለመቀበል መረጡ።
ከጊዜ በኋላ ግን፣ የመምረጥ ነፃነታቸውን ያለአግባብ በመጠቀም የገቡትን ቃል አፈረሱ።
ከዚህ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ጠቃሚ ትምህርት ማግኘት እንችላለን፤ ከይሖዋ ጋር ተጣብቀን በመኖርና የጽድቅ መሥፈርቶቹን በመታዘዝ የመምረጥ ነፃነታችንን ምንጊዜም በአድናቆት እንደምንመለከት እናሳይ።
ታማኙ ባሪያ የመንግሥቱን ምሥራች በቅንዓት በማስፋፋትና በማዳረስ ታላቅ እምነት እንዳለው አሳይቷል።
አንተስ በዚህ አስፈላጊ ሥራ በመካፈል ቅቡዓኑን እየደገፍክ ነው?
ከሆነ መሪያችን ኢየሱስ ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ ያደረጋችሁት ሁሉ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ይቆጠራል ብሎ በሚናገርበት ጊዜ እንደምትደሰት ጥርጥር የለውም።
ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲመለስ ተከታዮቹን አልረሳቸውም።
ምድር ላይ ሆኖ አመራር ይሰጥ በነበረበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ፣ መላእክትና የአምላክ ቃል ምን ያህል እንደረዱት ያውቃል።
በመሆኑም በዛሬው ጊዜ ታማኙን ባሪያ በእነዚህ ሦስት መንገዶች እየረዳው ነው።
የዚህ ባሪያ አባላት የሆኑት ቅቡዓን ክርስቲያኖች ምንጊዜም በጉ በሄደበት ሁሉ ይከተሉታል።
እኛም የእነሱን መመሪያ ከተከተልን መሪያችን የሆነውን ኢየሱስን እየተከተልን ነው።
በቅርቡ ደግሞ በእሱ አመራር ሥር የዘላለም ሕይወት እናገኛለን።
ሁላችንም ጳውሎስ ከተወው ጥሩ ምሳሌ ትምህርት ማግኘት እንችላለን፤ ጳውሎስ፣ ወንድሞቹ የራሳቸውን ውሳኔ የማድረግ መብት እንዳላቸው በመገንዘብ ይህን መብታቸውን አክብሮላቸዋል።
በዛሬው ጊዜ ያሉ ሽማግሌዎችም ከግል ምርጫ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በተመለከተ ምክር ሲሰጡ የእሱን ምሳሌ ሊከተሉ ይገባል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ መመሪያዎችን ለመንጋው አባላት ለማካፈል ፈቃደኞች ናቸው።
ያም ሆኖ ሽማግሌዎች፣ ውሳኔ የማድረጉን ኃላፊነት ለእያንዳንዱ ግለሰብ መተው ይኖርባቸዋል።
እንዲህ ማድረጋቸው ተገቢ ነው፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ ግለሰብ፣ ውሳኔው የሚያስከትለውን ውጤት የሚቀበለው ራሱ ነው።
በመሆኑም ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የምናገኘው አንድ ጠቃሚ ትምህርት አለ፦ ቅዱስ ጽሑፋዊ መመሪያዎችን ወይም ምክሮችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ሌሎችን ልንረዳቸው እንችላለን።
ያም ሆኖ ሌሎች የራሳቸውን ውሳኔ የማድረግ መብት እንዳላቸው እንዲሁም ይህ የእነሱ ኃላፊነት እንደሆነ መዘንጋት የለብንም።
እነዚህ ሰዎች ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ ሲያደርጉ እንደሚጠቀሙ ጥርጥር የለውም።
በግልጽ ለመረዳት እንደምንችለው፣ ለሌሎች ወንድሞችና እህቶች ውሳኔ የማድረግ ሥልጣን እንዳለን አድርገን ፈጽሞ ልናስብ አይገባም።
ብዙ ሰዎች እነሱ በሚያደርጉትና አምላክ በሚያደርገው ነገር መካከል ምንም ግንኙነት ያለ አይመስላቸውም።
እንዲያውም አንዳንዶች አምላክ በሰዎች ላይ የሚደርሰው ነገር ግድ እንደማይሰጠው ይሰማቸዋል።
ኅዳር 2013፣ ሃያን የተባለው ዝናብ የቀላቀለ ከባድ አውሎ ነፋስ መካከለኛውን ፊሊፒንስ ባወደመበት ወቅት የአንድ ትልቅ ከተማ ከንቲባ አምላክ የሆነ ቦታ ሄዶ መሆን አለበት ብለዋል።
ሌሎች ሰዎች ደግሞ የሚያደርጉትን ነገር አምላክ ማየት የሚችል አይመስላቸውም።
እነዚህ ሰዎች ሐዋርያው ጳውሎስ ለአምላክ እውቅና መስጠት ተገቢ መስሎ አልታያቸውም ብሎ የገለጻቸው ዓይነት ሰዎች ናቸው።
እንዲህ ያሉ ሰዎች በዓመፅ፣ በኃጢአተኝነት፣ በስግብግብነት፣ በክፋት የተሞሉ ናቸው።
ስለ እኛስ ምን ማለት ይቻላል?
ቀደም ሲል ከተጠቀሱት ሰዎች በተለየ ይሖዋ የምናደርገውን ነገር ሁሉ እንደሚመለከት እንገነዘባለን።
መጽሐፍ ቅዱስን ማግኘት የማትችልበት ሁኔታ ሊፈጠር ቢችልም ቀደም ሲል በአእምሮህ ባከማቸኸው እውቀት ላይ ማለትም በምትወዳቸው ጥቅሶች ወይም የመዝሙር ስንኞች ላይ እንዳታሰላስል ሊያግድህ የሚችል ሰው የለም።
ደግሞም የአምላክ መንፈስ ከዚህ በፊት የተማርካቸውን መልካም ነገሮች እንድታስታውስ ሊረዳህ ይችላል።
በመሆኑም ዛሬውኑ የሳምንቱን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ለማንበብና ለማሰላሰል ጊዜ መድብ።
ኢየሱስ በተናገረውና ባደረገው ነገር ላይ ለማሰላሰልም ጊዜ መመደብ አለብህ።
ስለ ኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት የሚገልጹት የወንጌል ዘገባዎች በሰፊው ከሚታወቁት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መካከል እንደሚገኙ ግልጽ ነው።
እንዲያውም የአምላክ ሕዝቦች፣ ኢየሱስ በምድር ላይ ያሳለፈውን ሕይወት በጊዜ ቅደም ተከተል የሚያቀርብ ጽሑፍ አግኝተዋል።
በእያንዳንዱ የመጽሐፉ ምዕራፍ ላይ የቀረቡትን ተዛማጅ የወንጌል ዘገባዎች በጥሞና ማንበባችንና በዚያ ላይ ማሰላሰላችን በጣም ይጠቅመናል።
ፍቅር የይሖዋ አምላክ ዋነኛ ባሕርይ ነው።
የመጀመሪያ የፍጥረት ሥራው ኢየሱስ ነው፤ እሱም ከአባቱ ጋር ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ዘመናት በሰማይ ሲኖር ፍቅር ስለሚንጸባረቅባቸው የአምላክ መንገዶች ተምሯል።
ኢየሱስ በምድር ላይ ያሳለፈውን ጊዜ ጨምሮ መላ ሕይወቱ፣ ይሖዋ የፍቅር አምላክ መሆኑን እንደተገነዘበና በዚህ ረገድ እሱን እንደሚመስል ያሳያል።
በመሆኑም የይሖዋና የኢየሱስ አገዛዝ ምንጊዜም ፍቅር የሚንጸባረቅበት እንደሚሆን እርግጠኞች መሆን እንችላለን።
ኢየሱስ ከሕጉ ውስጥ ከሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ የትኛው እንደሆነ ሲጠየቅ እንዲህ ብሏል፦ አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ።
ይህ ከሁሉ የሚበልጠውና የመጀመሪያው ትእዛዝ ነው።
ሁለተኛውም ይህንኑ የሚመስል ሲሆን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ ይላል።
ኢየሱስ ይሖዋን ከመውደድ ቀጥሎ ሁለተኛውን ቦታ የሚይዘው ለባልንጀራችን ያለን ፍቅር መሆኑን እንደገለጸ ልብ በል።
ይህም ከሁሉም ሰው ጋር ባለን ግንኙነት ረገድ ፍቅር ማሳየት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የሚያጎላ ነው።
አምላክ ሐሳቡን ለሰው ልጆች ለመግለጽ ከዕብራይስጥ በተጨማሪ በሌሎች ቋንቋዎች ተጠቅሟል።
የአምላክ ሕዝቦች ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሱ በኋላ የአንዳንዶቹ የዕለት ተዕለት ቋንቋ አረማይክ ሆነ።
ይሖዋ አስቀድሞ ይህን ስለተገነዘበ ሳይሆን አይቀርም፣ ነቢዩ ዳንኤልና ነቢዩ ኤርምያስ እንዲሁም ካህኑ ዕዝራ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙት ዘገባዎቻቸው ውስጥ የተወሰኑትን ክፍሎች በአረማይክ እንዲጽፉ በመንፈሱ መርቷቸዋል።
ከጊዜ በኋላ ታላቁ እስክንድር ከጥንቱ ዓለም አብዛኛውን በቁጥጥሩ ሥር ሲያደርግ ኮይኔ ወይም የጋራ መግባቢያ የነበረው ግሪክኛ ዓለም አቀፍ ቋንቋ ሆነ።
በርካታ አይሁዳውያን ይህን ቋንቋ መናገር ጀመሩ፤ በዚህ የተነሳ የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ወደ ግሪክኛ ተተረጎሙ።
በ72 ተርጓሚዎች እንደተዘጋጀ የሚታሰበው ይህ ትርጉም ሰብዓ ሊቃናት ሴፕቱጀንት በመባል ይታወቃል።
ሰብዓ ሊቃናት የመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሲሆን ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው ትርጉሞች አንዱ ነው።
በሥራው የተካፈሉት ተርጓሚዎች ብዙ በመሆናቸው የተጠቀሙበት የአተረጓጎም ስልትም የተለያየ ነው፤ አንዳንዶቹ ቃል በቃል ሲተረጉሙ ሌሎቹ ግን እንዲህ አላደረጉም።
ያም ቢሆን ግሪክኛ ተናጋሪ አይሁዳውያን፣ በኋላ ላይ ደግሞ ክርስቲያኖች ሰብዓ ሊቃናትን እንደ አምላክ ቃል አድርገው ተቀብለውታል።
ያዕቆብ በዚህ ምሳሌ ላይ ሊያጎላው የፈለገውን ነጥብ ቁጥር 6 ላይ ግልጽ አድርጎታል።
ጥቅሱ ምላስም እሳት ናት ይላል።
ምላስ የሚለው ቃል የመናገር ችሎታችንን ያመለክታል።
እንደ እሳት ሁሉ ንግግራችንም ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።
እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ አንደበት የሞትና የሕይወት ኃይል አላት ይላል።
እርግጥ ነው፣ እሳት የሚያስከትለውን ጉዳት በመፍራት በእሳት መጠቀማችንን እንደማናቆም ሁሉ፣ ጎጂ ነገር እንዳንናገር በመስጋት መናገራችንን እስከ ጭራሹ አናቆምም።
ቁልፉ አንደበታችንን መቆጣጠር መቻላችን ላይ ነው።
እሳትን በተገቢው መንገድ የምንጠቀምበት ከሆነ ምግባችንን ለማብሰልና ሰውነታችንን ለማሞቅ ሊያገለግለን እንዲሁም ብርሃን ሊሰጠን ይችላል።