text stringlengths 4 267 |
|---|
ምላሳችንንም ከገራነው አምላክን በሚያስከብርና ሌሎችን በሚጠቅም መንገድ ልንጠቀምበት እንችላለን። |
ድምፅ አውጥተን በመናገርም ይሁን በእጃችን ምልክት በመስጠት ሐሳባችንንና ስሜታችንን የመግለጽ ችሎታ ከአምላክ ያገኘነው ድንቅ ስጦታ ነው። |
ይሁንና ይህን ስጦታ፣ ለማፍረስ ሳይሆን ለማነጽ ልንጠቀምበት ይገባል። |
ሉቃስ ለጳውሎስ ከጤና ጋር የተያያዘ ምክር ሰጥቶት ሊሆን እንደሚችል እንዲሁም ለጳውሎስም ሆነ በሚስዮናዊ አገልግሎቱ ወቅት አብረውት ለተጓዙት ሌሎች ሰዎች የሕክምና እርዳታ አድርጎላቸው እንደሚሆን ማሰቡ ምክንያታዊ ነው። |
ሉቃስ እንዲህ ማድረግ ያስፈለገው ለምንድን ነው? |
ምክንያቱም ጳውሎስም እንኳ በጉዞው ላይ እያለ ታሞ ነበር። |
ኢየሱስ ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም ብሎ ከተናገረው ሐሳብ ጋር በሚስማማ መልኩ ሉቃስም በዚህ ወቅት የሕክምና እርዳታ መስጠት ይችል ነበር። |
ሉቃስ የሕክምና ሥልጠና ያገኘው የት ወይም መቼ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ አይነግረንም። |
ጳውሎስ ለቆላስይስ ክርስቲያኖች ሲጽፍ ሉቃስ የሕክምና ባለሙያ መሆኑን የጠቀሰው ሉቃስን ስለሚያውቁት ሊሆን ይችላል ተብሎ ይታሰባል። |
በቆላስይስ አቅራቢያ ባለችው በሎዶቅያ የሕክምና ትምህርት ቤት ነበረ። |
ሁኔታው ምንም ይሁን ምን፣ ሉቃስ የሕክምና ባለሙያ እንጂ የሕክምና ችሎታ ሳይኖረው ጤና ነክ ምክር የሚሰጥ ሰው አልነበረም። |
ሉቃስ የወንጌል ዘገባውንና የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን ሲጽፍ የተጠቀመባቸው የሕክምና ቃላት እንዲሁም ኢየሱስ የፈወሳቸው ሰዎች ላለባቸው ሕመም ትኩረት መስጠቱ ይህን ይጠቁማሉ። |
ይሖዋ፣ አንድያ ልጁን ወደ ምድር በመላክ ከሁሉ የላቀውን ስጦታ በፍቅር ተነሳስቶ ሰጥቶናል! ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን የአምላክ ስጦታ በቃላት ሊገለጽ የማይችል ነፃ ስጦታ በማለት ገልጾታል። |
ጳውሎስ፣ አምላክ ቃል የገባቸው አስደናቂ ተስፋዎች በሙሉ እንደሚፈጸሙ ዋስትና የሚሆነው የክርስቶስ ፍጹም መሥዋዕት እንደሆነ ስለሚያውቅ ነው። |
በቃላት ሊገለጽ የማይችለው ይህ ነፃ ስጦታ ይሖዋ በኢየሱስ በኩል የሚያደርግልንን መልካም ነገሮች በሙሉ እንዲሁም የሚያሳየንን ታማኝ ፍቅር ያካትታል። |
በእርግጥም ስጦታው እጅግ አስደናቂ በመሆኑ የሰው ልጆች ሙሉ በሙሉ በሚረዱት መንገድ መግለጽ አስቸጋሪ ነው። |
እንዲህ ያለ ልዩ ስጦታ በመቀበላችን ምን ሊሰማን ይገባል? |
ደግሞስ ከይሖዋ ያገኘነው ስጦታ ምን እንድናደርግ ሊገፋፋን ይገባል? |
አኗኗርህን መለስ ብለህ እንድታጤንና ሕይወትህን የምትመራበትን መንገድ እንድትቀይር ያነሳሳህ ይሆን? |
ይበልጥ ለጋስና አፍቃሪ እንድትሆን እንዲሁም የበደሉህን ይቅር እንድትል ያነሳሳህ ይሆን? |
ይሖዋ በክርስቶስ አማካኝነት የሰጠን ስጦታ ከየትኛውም ስጦታ በእጅጉ የላቀ ነው። |
ኃጢአትና ሞት ወደ ዓለም እንዲገባ ምክንያት የሆነው አንድ ሰው ሲሆን እሱም አዳም ነው። |
መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ሰው በደል የተነሳ ሞት እንደነገሠ የሚናገረው ለዚህ ነው። |
ጳውሎስ የአምላክን የተትረፈረፈ ጸጋ ማግኘት የሚቻለው በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት እንደሆነ ተናግሯል። |
ይህ ጸጋ የሰውን ዘር በሙሉ ጠቅሟል። |
ጳውሎስ በአንዱ ሰው በኢየሱስ መታዘዝም ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ ብሏል። |
በመሆኑም የአምላክ ጸጋ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የዘላለም ሕይወት ያስገኛል። |
ይሖዋ፣ ልጁ ወደ ምድር መጥቶ ቤዛውን እንዲከፍል የማድረግ ግዴታ አልነበረበትም። |
ይሖዋና ኢየሱስ፣ ኃጢአተኛ የሆኑት የሰው ልጆች በቤዛው አማካኝነት ይቅርታ ማግኘት የሚችሉበትን ዝግጅት ያደረጉት የሰው ልጆች ይህን ለማግኘት የሚበቁ ወይም የሚገባቸው ስለሆኑ አይደለም። |
በመሆኑም የኃጢአት ይቅርታ እና የዘላለም ሕይወት ተስፋ ማግኘታችን ይገባናል የማንለው ደግነት ወይም ጸጋ ነው። |
እንግዲያው የአምላክን የደግነት ስጦታ ይኸውም ጸጋውን ከፍ አድርገን ልንመለከተውና ይህንንም በአኗኗራችን ልናሳይ ይገባል። |
ራሳችንን መመርመራችን አስፈላጊ ነው። |
ለምን? |
ጳውሎስ በሥጋዊ ነገሮች ላይ ማተኮር ሞት ያስከትላል ሲል ጽፏል። |
ይህ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፤ በሥጋዊ ነገሮች ላይ ማተኮር በአሁኑ ጊዜ መንፈሳዊ ሞት የሚያስከትል ሲሆን ወደፊት ደግሞ ቃል በቃል ሕይወታችንን ያሳጣናል። |
ሆኖም ጳውሎስ፣ አንድ ሰው በሥጋዊ ነገሮች ላይ ማተኮር ስለጀመረ ብቻ መጨረሻው ሞት እንደሚሆን መናገሩ አልነበረም። |
ለውጥ ማድረግ ይቻላል። |
በቆሮንቶስ ይኖር የነበረውን የሥነ ምግባር ብልግና የፈጸመ ሰው እንደ ምሳሌ እንውሰድ፦ ይህ ሰው በሥጋዊ ነገሮች ላይ በማተኮሩ ከጉባኤ ተወግዷል። |
ያም ቢሆን ለውጥ ማድረግ ይችል ነበር፤ ደግሞም ለውጥ አድርጓል። |
ግለሰቡ ሥጋዊ ነገሮችን መከተሉን ትቶ ወደ ትክክለኛው ጎዳና ተመልሷል። |
ይህ ሰው ለውጥ ማድረግ ከቻለ በዛሬው ጊዜ የሚገኝ ክርስቲያንም ለውጥ ማድረግ ይችላል፤ በተለይ ደግሞ በቆሮንቶስ የነበረውን ሰው ያህል ሥጋዊ ነገሮችን በመከተል ረገድ የከፋ ጎዳና ያልተከተለ ሰው መቀየር ላይከብደው ይችላል። |
ይሖዋ እንደሚደግፈን ተማምነን ሸክማችንን በእሱ ላይ መጣል መቻላችን ምንኛ የሚያጽናና ነው! አምላክ ከምንጠይቀው ወይም ከምናስበው ሁሉ በላይ እጅግ አብልጦ እንደሚያደርግልን ሙሉ በሙሉ መተማመን እንችላለን። |
እስቲ አስበው፤ ይሖዋ የሚያደርግልን አብልጦ ወይም እጅግ አብልጦ ብቻ ሳይሆን ከምናስበው ሁሉ በላይ እጅግ አብልጦ ነው! ሽልማታችንን ማግኘት ከፈለግን በይሖዋ ላይ ሙሉ እምነት ማሳደር እንዲሁም መመሪያዎቹን መታዘዝ ይኖርብናል። |
ሙሴ የእስራኤልን ብሔር እንዲህ ብሏቸዋል፦ አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርገህ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ላይ ይሖዋ ይባርክሃል፤ ይህ የሚሆነው ግን የአምላክህን የይሖዋን ቃል በትኩረት የምትሰማና እኔ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዛት በሙሉ በጥንቃቄ የምትፈጽም ከሆነ ነው። |
አምላክህ ይሖዋ በገባልህ ቃል መሠረት ይባርክሃል። |
ይሖዋ፣ በታማኝነት እስካገለገልከው ድረስ እንደሚባርክህ ሙሉ በሙሉ ትተማመናለህ? |
ይህን ለማድረግ በቂ ምክንያት አለህ። |
ይሖዋ፣ ሰዎች በሕይወት እንዲኖሩ እንጂ እንዲሞቱ አይፈልግም። |
የሕይወት ምንጭ እንደመሆኑ መጠን ከሞት ለተነሱ ሁሉ አባት ይሆንላቸዋል። |
ከዚህ አንጻር ኢየሱስ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ ብለን እንድንጸልይ ማስተማሩ ተገቢ ነው። |
ይሖዋ ሙታንን ከማስነሳት ጋር በተያያዘ ኢየሱስ ትልቅ ሚና እንዲኖረው አድርጓል። |
ኢየሱስ ትንሣኤና ሕይወት እንደሆነ የተናገረው ቃል በገነት ውስጥ ፍጻሜውን ያገኛል። |
ይሖዋ የቤተሰቡ አባላት እንዲሆኑ የጋበዘው የተመረጡ ጥቂት ሰዎችን ብቻ አይደለም፤ ኢየሱስ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ ለእኔ ወንድሜ፣ እህቴና እናቴ ነው በማለት መናገሩ ይህን ያሳያል። |
የአምላክ ፈቃድ ከሁሉም ብሔራት፣ ነገዶች፣ ሕዝቦችና ቋንቋዎች የተውጣጡና ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ እጅግ ብዙ ሕዝብ አገልጋዮቹ እንዲሆኑ ነው። |
በክርስቶስ ቤዛ ላይ እምነት እንዳላቸው የሚያሳዩና የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉ ሁሉ መዳን ያገኘነው በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከአምላካችን እንዲሁም ከበጉ ነው በማለት በታላቅ ድምፅ ከሚጮኹት ሰዎች መካከል የመሆን አጋጣሚ አላቸው። |
የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በተለያዩ ቋንቋዎች ለማሰራጨት ሲባል ዛየንስ ዎች ታወር ትራክት ሶሳይቲ የተባለው ማኅበር በ1884 ተቋቋመ፤ የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ቻርልስ ቴዝ ራስል ነበር። |
ወንድም ራስል መጽሐፍ ቅዱስን በትጋት ያጠና የነበረ ሲሆን አምላክ ሥላሴ እንደሆነና ነፍስ እንደማትሞት የሚገልጹት ትምህርቶች ሐሰት መሆናቸውን በድፍረት አጋልጧል። |
ክርስቶስ የሚመለሰው በማይታይ ሁኔታ እንደሆነ እንዲሁም የተወሰኑት የአሕዛብ ዘመናት በ1914 እንደሚያበቁ ተገንዝቦ ነበር። |
ወንድም ራስል ጊዜውን፣ ጉልበቱንና ገንዘቡን ምንም ሳይቆጥብ እነዚህን እውነቶች ለሌሎች አካፍሏል። |
በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ይሖዋና የጉባኤው ራስ የሆነው ኢየሱስ በዚያ ወሳኝ ወቅት ወንድም ራስልን ተጠቅመውበታል። |
ወንድም ራስል ከሰዎች ክብር ለማግኘት አልሞከረም። |
በ1896 እንዲህ ሲል ጽፏል፦ ለእኛም ሆነ ለምናዘጋጃቸው ጽሑፎች ሙገሳና ውዳሴ መቀበል አንፈልግም፤ አባ ወይም ረቢ ተብለን መጠራት አንፈልግም። |
ማንም ሰው በእኛ ስም እንዲጠራም አንፈልግም። |
አክሎም ይህ የአምላክ እንጂ የሰው ሥራ አይደለም ብሏል። |
ሁላችንም በሕይወታችን ውስጥ የተለያዩ ምርጫዎችንና ውሳኔዎችን ማድረግ ይኖርብናል። |
ሁሉም ውሳኔዎቻችን የሕይወትና የሞት ጉዳይ ናቸው ማለት ላይሆን ይችላል። |
ይሁንና የምናደርጋቸው ብዙዎቹ ምርጫዎች ወይም ውሳኔዎች በሕይወታችን ላይ ትልቅ ለውጥ ሊያስከትሉ ይችላሉ። |
ጥሩ ውሳኔዎችን ካደረግን በአንጻራዊ ሁኔታ የተረጋጋና ሰላማዊ ሕይወት መኖር እንችላለን፤ በሌላ በኩል ደግሞ የተሳሳቱ ውሳኔዎች ካደረግን ሕይወታችን በችግርና በብስጭት የተሞላ ሊሆን ይችላል። |
ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ ለማድረግ ምን ሊረዳን ይችላል? |
በአምላክ ላይ እምነት ሊኖረን ይኸውም ጥበበኞች እንድንሆን እኛን ለመርዳት ፍላጎቱም ሆነ ችሎታው እንዳለው ልንተማመን ይገባል። |
በተጨማሪም በይሖዋ ቃልና ነገሮችን በሚያከናውንበት መንገድ ላይ እምነት ማዳበር አለብን፤ በሌላ አባባል በመንፈሱ መሪነት ባስጻፈው ቃሉ ውስጥ በሚገኘው ምክር መተማመን ይኖርብናል። |
ወደ እሱ እየቀረብንና ለቃሉ ያለን ፍቅር እየጨመረ ሲሄድ እሱ በሚሰጠን ምክር ይበልጥ እንተማመናለን። |
በመሆኑም ውሳኔዎችን ከማድረጋችን በፊት የአምላክን ቃል የመመርመር ልማድ እናዳብራለን። |
አፍቃሪው አምላካችን ምንጊዜም ለታማኝ አገልጋዮቹ ከሁሉ የተሻለውን ነገር ያደርጋል። |
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም። |
የይሖዋን ፍቅር ከልባቸው የሚያደንቁና እንደ ገዢያቸው አድርገው የሚታዘዙት ሁሉ ከፊታቸው እጅግ ግሩም ተስፋ ተዘርግቶላቸዋል! የይሖዋ ቃል እንዲህ ይላል፦ ነቀፋ የሌለበትን ሰው ልብ በል፤ ቀና የሆነውንም ሰው በትኩረት ተመልከት፤ የዚህ ሰው የወደፊት ሕይወት ሰላማዊ ይሆናልና። |
ኃጢአተኞች ሁሉ ግን ይጠፋሉ። |
ነቀፋ የሌለበት ሰው ይሖዋንና ልጁን ያውቃል፤ እንዲሁም ታዛዥ በመሆን የአምላክን ፈቃድ ይፈጽማል። |
እንዲህ ያለው ሰው ላይ የሚገኘውን ዓለምም ሆነ ምኞቱ ያልፋሉ፤ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል የሚለውን ሐሳብ በቁም ነገር ይመለከተዋል። |
ይህ ዓለም የሚጠፋበት ጊዜ እየተቃረበ በመሆኑ ይሖዋን ተስፋ አድርግ፤ መንገዱንም ተከተል የሚለውን ምክር ተግባራዊ ማድረጋችን አጣዳፊ ነው። |
ማርታ፣ ለኢየሱስ ለየት ያለ ምግብ በማዘጋጀት ተጠምዳለች፤ እንዲሁም የማርያም ሁኔታ አበሳጫት። |
ኢየሱስ፣ ማርታ ብዙ ነገር ለማከናወን እየጣረች እንደሆነ ስላስተዋለ በደግነት ማርታ፣ ማርታ፣ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ደግሞም ትጠበቢያለሽ አላት። |
አንድ ዓይነት ምግብ ብቻ በቂ እንደሆነ ሐሳብ ሰጣት። |
ከዚያም ኢየሱስ ትኩረቱን ወደ ማርያም ዞር በማድረግ ማርያም በበኩሏ ጥሩ የሆነውን ድርሻ መርጣለች፤ ይህም ከእሷ አይወሰድም በማለት ድርጊቷ እንደ ቸልተኝነት ሊታይ እንደማይገባ ተናገረ። |
ማርያም በዚህ ልዩ ወቅት የተመገበችውን ምግብ ብዙም ሳይቆይ ትረሳው ይሆናል፤ ይሁንና ትኩረቷ ሳይከፋፈል ኢየሱስን በማዳመጧ የተቸራትን ምስጋናም ሆነ ያገኘችውን ግሩም መንፈሳዊ ምግብ መቼም አትረሳውም። |
ሐዋርያው ዮሐንስ ከ60 ከሚበልጡ ዓመታት በኋላ ኢየሱስ ማርታንና እህቷን ይወዳቸው እንደነበር ጽፏል። |
በመንፈስ መሪነት የተጻፈው ይህ ሐሳብ ማርታ፣ ኢየሱስ የሰጣትን ፍቅራዊ እርማት እንደተቀበለችና በቀሪው ሕይወቷ ይሖዋን በታማኝነት ለማገልገል ጥረት እንዳደረገች በግልጽ ያሳያል። |
የይሖዋ ምሥክሮች ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ከባድ ስደት ቢደርስባቸውም ምንጊዜም በተስፋቸው ይደሰታሉ። |
ለምሳሌ በሲንጋፖር፣ በኤርትራ እና በደቡብ ኮሪያ በርካታ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ታስረዋል፤ አብዛኞቹ የታሰሩት ኢየሱስ ሰይፍ እንዳንመዝ የሰጠውን ትእዛዝ በማክበራቸው ነው። |
በሌላ በኩል ደግሞ አብዛኞቹ የይሖዋ ሕዝቦች ከባድ ስደት አላጋጠማቸውም። |
እነሱ የደረሰባቸው የእምነት ፈተና ሌላ ነው። |
ድህነትን ተቋቁመው የሚኖሩ አሊያም በጦርነት ወይም በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት መከራ የደረሰባቸው በርካታ ወንድሞች አሉ። |
ሌሎች ደግሞ እንደ ሙሴና የጥንት የእምነት አባቶች፣ በዚህ ዓለም ላይ የተደላደለ ሕይወት ወይም ዝና የማግኘት አጋጣሚያቸውን መሥዋዕት አድርገዋል። |
ቁሳዊ ነገሮችን በማሳደድና የራሳቸውን ፍላጎት በማሟላት ላይ ያተኮረ ሕይወት እንዲመሩ በሚቀርብላቸው ፈተና ላለመሸነፍ ከፍተኛ ትግል ያደርጋሉ። |
እነዚህ ወንድሞች እንዲጸኑ የረዳቸው ምንድን ነው? |
ለይሖዋ ያላቸው ፍቅር እንዲሁም ይሖዋ ማንኛውንም የፍትሕ መጓደል እንደሚያስተካክልና ታማኝ አገልጋዮቹን ጽድቅ በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የዘላለም ሕይወት በመስጠት እንደሚባርካቸው ያላቸው ጠንካራ እምነት ነው። |
ኢየሱስ ተከታዮቹ ምን ብለው እንደሚያምኑ ከመጠየቅ ወደኋላ አላለም። |
እናንተም የእሱን ምሳሌ ተከተሉ። |
ከልጆቻችሁ ጋር ስትጨዋወቱ ስሜታቸውን እንዲገልጹ አበረታቷቸው። |
ልጃችሁ አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተመለከተ ጥርጣሬ ካደረበት፣ ከመቆጣት ወይም እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ማንሳቱ ተገቢ እንዳልሆነ እንዲሰማው ከማድረግ ተቆጠቡ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.