text stringlengths 4 267 |
|---|
ከዚህ ይልቅ ጉዳዩን በጥሞና እንዲያመዛዝን በትዕግሥት እርዱት። |
እንደ እውነቱ ከሆነ ልጃችሁ በቅንነት የሚያነሳቸው ጥያቄዎች፣ ለጉዳዩ ትኩረት እንደሰጠውና የማወቅ ፍላጎት እንዳለው ይጠቁማሉ። |
ኢየሱስ ገና በ12 ዓመቱ ቁም ነገር ያዘሉ ጥያቄዎችን ጠይቋል። |
ልጆቻችሁን በሚገባ እወቋቸው፤ ይኸውም አስተሳሰባቸውን፣ ስሜታቸውንና የሚያሳስቧቸውን ነገሮች ለመረዳት ጥረት አድርጉ። |
አብረዋችሁ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ስለሚገኙና በአገልግሎት ስለሚካፈሉ ብቻ በይሖዋ ላይ እምነት እንዳላቸው አድርጋችሁ አታስቡ። |
ከልጆቻችሁ ጋር አብራችሁ በምታሳልፉት በማንኛውም ጊዜ በውይይታችሁ ውስጥ መንፈሳዊ ነገሮችን ለማካተት ጥረት አድርጉ። |
ከልጆቻችሁ ጋር ሆናችሁ ጸልዩ፤ እንዲሁም እነሱን በተመለከተ ጸልዩ። |
ከእምነታቸው ጋር በተያያዘ የሚያጋጥማቸውን ማንኛውንም ፈተና ለማስተዋል ጥረት አድርጉ፤ ፈተናውን እንዲወጡትም እርዷቸው። |
ኢየሱስ ዋነኛ ሥራው የመንግሥቱን ምሥራች ማወጅ ነበር። |
ይሁንና እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሌሎችን ለማሠልጠን ጊዜ መድቧል። |
ፊልጶስ በወንጌላዊነቱ ሥራ ተጠምዶ የነበረ ቢሆንም አራት ሴቶች ልጆቹን፣ ቅዱስ ጽሑፋዊ እውነቶችን ለሌሎች በማካፈሉ ሥራ ውጤታማ እንዲሆኑ እንደረዳቸው አያጠራጥርም። |
በዛሬው ጊዜስ እንዲህ ዓይነቱን ሥልጠና መስጠት ምን ያህል አስፈላጊ ነው? |
በዓለም ዙሪያ ለምሥራቹ አዎንታዊ ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። |
አዲሶች ገና ከመጠመቃቸውም በፊት መጽሐፍ ቅዱስን በግላቸው የማጥናትን አስፈላጊነት እንዲገነዘቡ ማድረግ ያስፈልጋል። |
ለሌሎች ምሥራቹን መስበክና እውነትን ማስተማር የሚችሉት እንዴት እንደሆነ መማርም ይኖርባቸዋል። |
በጉባኤዎቻችን ውስጥ ያሉ ወንድሞች፣ የጉባኤ አገልጋዮችና ሽማግሌዎች ለመሆን የሚያስፈልጓቸውን ብቃቶች ለማሟላት እንዲጣጣሩ መበረታታት ያስፈልጋቸዋል። |
የጎለመሱ ክርስቲያኖች ለአዲሶች ጥሩ መመሪያ በመስጠት መንፈሳዊ እድገት እንዲያደርጉ ሊረዷቸው ይችላሉ። |
ጠንካራ ትዳር፣ አንዳቸው የሌላውን ስህተት በትዕግሥት የሚያልፉ ባልና ሚስት ጥምረት ነው። |
እንዲህ ያሉ ባልና ሚስት እርስ በርስ ይቻቻላሉ፤ እንዲሁም በነፃ ይቅር ይባባላሉ። |
እርግጥ ነው፣ ሁለቱም ስህተት መሥራታቸው አይቀርም። |
እንዲህ ዓይነት ሁኔታ በሚፈጠርበት ጊዜ ባልና ሚስት ከስህተታቸው መማር፣ የትዳር ጓደኛቸውን ይቅር ማለት እንዲሁም ፍጹም የሆነ የአንድነት ማሰሪያ የሆነውን ፍቅር ማሳየት ይችላሉ። |
በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው። |
ፍቅር የበደል መዝገብ የለውም ይላል። |
አለመግባባቶች በተቻለ ፍጥነት መፈታት አለባቸው። |
በመሆኑም አንድ ክርስቲያን ባልና ሚስት በመካከላቸው ለተፈጠረው ለማንኛውም ቅራኔ፣ ጀምበር ሳትጠልቅ እልባት ማበጀት ይኖርባቸዋል። |
ስላስከፋሁህ ይቅርታ አድርግልኝ ብሎ ከልብ ይቅርታ መጠየቅ ትሕትና እና ድፍረት ይጠይቃል፤ ይሁንና የትዳር ጓደኛሞች እንዲህ ማድረጋቸው ችግሮችን በመፍታት ብሎም በመካከላቸው ያለውን ጥምረት በማጠናከር ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል። |
ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ የሚለውን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ፣ ፍላጎት ብቻ በቂ አይደለም። |
በጌትሴማኒ የአትክልት ቦታ ደቀ መዛሙርቱ ካጋጠማቸው ሁኔታ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ኢየሱስ ለይሖዋ ምልጃ እንዲያቀርቡ ነግሯቸው ነበር። |
እኛም በመንፈሳዊ እንዳናንቀላፋ ከፈለግን በጸሎት ረገድ ምንጊዜም ንቁዎች መሆን አለብን። |
ኢየሱስ መጨረሻው የሚመጣው ባላሰብነው ሰዓት እንደሆነ ስለተናገረ አሁን በመንፈሳዊ የምናሸልብበት እንዲሁም ሰይጣንም ሆነ እሱ የሚቆጣጠረው ዓለም የሚያቀርባቸውን የማይጨበጡና ሥጋችንን የሚያማልሉ ነገሮች የምናሳድድበት ጊዜ አይደለም። |
ይሖዋና ኢየሱስ፣ ስላዘጋጁልንና በቅርቡ ስለምናገኛቸው በረከቶች እንዲሁም ምንጊዜም ነቅተን መጠበቅ ስለምንችልበት መንገድ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ነግረውናል። |
ለመንፈሳዊነታችንና ከይሖዋ ጋር ላለን ዝምድና ትኩረት መስጠት እንዲሁም የአምላክን መንግሥት ማስቀደም አለብን። |
በቅርቡ የሚፈጸመውን ክንውን ዝግጁ ሆነን መጠበቅ እንድንችል፣ ያለንበትን ጊዜ እንዲሁም በዙሪያችን የሚከናወኑትን ነገሮች ማስተዋል ይኖርብናል። |
እንደተናቅን ወይም ተገቢ ያልሆነ ነገር እንደተደረገብን በሚሰማን ጊዜ ስሜታችንን መቆጣጠር ከባድ ሊሆንብን ይችላል። |
በዘራችን፣ በቆዳችን ቀለም አሊያም በውጫዊ ገጽታችን ምክንያት ብንነቀፍ ስሜታችን በጣም እንደሚጎዳ የታወቀ ነው። |
ይህን ያደረገው የእምነት ባልንጀራችን ሲሆን ደግሞ ሁኔታው ምንኛ የከፋ ይሆናል! በዚህ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ስሜታችንን እንድንቆጣጠር እንዲሁም ቶሎ እንዳንቆጣ የሚሰጠንን ምክር ተግባራዊ ማድረጋችን ምንኛ ጠቃሚ ነው! ማንኛችንም ብንሆን ቶሎ ቅር ላለመሰኘትና ይበልጥ ይቅር ባይ ለመሆን ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልገን ጥርጥር የለውም። |
ይሖዋና ኢየሱስ ይቅር ባይ መሆንን ትልቅ ቦታ ይሰጡታል። |
አንተስ ይቅር ባይ ከመሆን ወይም ቁጣህን ከመቆጣጠር ጋር በተያያዘ ይበልጥ መሥራት ያስፈልግህ ይሆን? |
ቁጣቸውን የመቆጣጠር ችግር ያለባቸው ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ምሬት ያድርባቸዋል። |
በመሆኑም ሌሎች ይርቋቸዋል። |
በምሬት የተሞላ ሰው በጉባኤ ውስጥ መጥፎ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። |
በአሁኑ ጊዜ የምንኖረው ይሖዋ እኛን ለመቅረጽ ሲል ባዘጋጀው መንፈሳዊ ገነት ውስጥ ነው። |
በዙሪያችን ያለው ዓለም በክፋት የተሞላ ቢሆንም ያለ ስጋት ተረጋግተን እንኖራለን። |
ይሖዋን ማወቅና የእሱን አባታዊ ፍቅር ማጣጣም ችለናል። |
በአዲሱ ዓለም ውስጥ ስንኖር ደግሞ መንፈሳዊው ገነት ከሚያስገኛቸው በረከቶች የተሟላ ጥቅም ማግኘት እንችላለን። |
ከዚህም በተጨማሪ በዚያ ወቅት በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር ምድር ወደ ገነትነት ትለወጣለች። |
ዓለም አቀፍ ተሃድሶ በሚኖርበት በዚያ ጊዜ፣ ይሖዋ የምድርን ነዋሪዎች መቅረጹን የሚቀጥል ሲሆን ከእሱ የሚያገኙት ትምህርት ከምንገምተው በላይ ይሆናል። |
በተጨማሪም እሱ የሚሰጠንን ትምህርት መቀበልና ፈቃዱን ሙሉ በሙሉ መፈጸም እንድንችል ይሖዋ አእምሯችንንና አካላችንን ፍጹም ያደርግልናል። |
እንግዲያው ለይሖዋ መገዛታችንን ለመቀጠል ቁርጥ ውሳኔ እናድርግ፤ ይህን ስናደርግ ይሖዋ የሚቀርጸን ስለሚወደን መሆኑን እንደተገነዘብን እናሳያለን። |
ከክርስቶስ ልደት በኋላ በነበሩት የመጀመሪያዎቹ ጥቂት መቶ ዓመታት ውስጥ በርካታ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በግሪክኛ ወይም በላቲን ማንበብ ይችሉ ነበር። |
በመሆኑም በአምላክ ቃል ውስጥ ያለውን ትምህርት ከቤተ ክርስቲያኗ ትምህርት ጋር የማወዳደር አጋጣሚ ነበራቸው። |
አንዳንዶች መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ካነበቡት ነገር በመነሳት የቤተ ክርስቲያኗ ትምህርቶች ቅዱስ ጽሑፋዊ ድጋፍ የላቸውም የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሱ፤ እርግጥ ይህን አመለካከታቸውን በግልጽ መናገር አደገኛ አልፎ ተርፎም ለሞት የሚዳርግ ነበር። |
ውሎ አድሮ ግን አብዛኛው ሕዝብ መጽሐፍ ቅዱስ በሚገኝባቸው ቋንቋዎች መጠቀም እየተወ ሄደ፤ ቤተ ክርስቲያኗ ደግሞ የአምላክን ቃል ሕዝቡ ወደሚጠቀምበት ቋንቋ ለመተርጎም የተደረጉትን ጥረቶች ተቃወመች። |
ቤተ ክርስቲያኗ የምታስተምረውን ነገር የሚቃወም ማንኛውም ሰው ከፍተኛ ቅጣት ይበየንበት ነበር። |
በመሆኑም ታማኝ የሆኑ የአምላክ ቅቡዕ አገልጋዮች በትናንሽ ቡድኖች ሆነው ለመሰብሰብ ተገደዱ፤ ያውም መሰብሰብ ከቻሉ ነው። |
ንጉሣዊ ካህናት የሆኑት ቅቡዓን በተደራጀ መልኩ ሥራቸውን ማከናወን አልቻሉም። |
የሚረብሽ፣ የሚያስፈራ ወይም የሚያስጨንቅ ሁኔታ ሲያጋጥምህ በሰማይ ላለው አፍቃሪ አባትህ የልብህን አውጥተህ ንገረው። |
አንድን ችግር ለመፍታት የቻልከውን ያህል ጥረት ካደረግህ በኋላ፣ የተሻለ የሚሆነው ስለ ጉዳዩ መጨነቅ ሳይሆን ወደ ይሖዋ ከልብ የመነጨ ጸሎት ማቅረብ ነው። |
ላይ እንደተገለጸው ይሖዋ ደጋግመን ለምናቀርበው ከልብ የመነጨ ምልጃ ምላሽ ይሰጣል። |
እንዴት? |
አእምሯችንንና ልባችንን፣ ከሚረብሹ ስሜቶች የሚያሳርፍ ውስጣዊ ሰላም በመስጠት ነው። |
በርካታ ሰዎች ይህን በሕይወታቸው ተመልክተዋል። |
አምላክ ጭንቀታቸውና ስጋታቸው ተወግዶ፣ ከመረዳት ችሎታ በላይ የሆነ ውስጣዊ ሰላምና መረጋጋት እንዲያገኙ አድርጓቸዋል። |
አንተም እንዲህ ዓይነት ሰላምና መረጋጋት ልታገኝ ትችላለህ። |
የአምላክ ሰላም የሚያጋጥምህን ማንኛውንም ተፈታታኝ ሁኔታ መቋቋም እንድትችል ይረዳሃል። |
ይሖዋ እኔ አምላክህ ነኝና አትጨነቅ። |
አበረታሃለሁ፤ አዎ እረዳሃለሁ በማለት በገባልን ርኅራኄ የተንጸባረቀበት ቃል ላይ ሙሉ በሙሉ መተማመን ትችላለህ። |
ይሖዋ እሱ የሰጠንን ችሎታዎች በጥሩ ሁኔታ እንድንጠቀምባቸው ይፈልጋል። |
ለምን? |
ምክንያቱም እኛን ይወደናል፤ እንዲሁም ያሉንን ችሎታዎች በዚህ መንገድ መጠቀማችን ደስታና እርካታ እንደሚያስገኝልን ያውቃል። |
ይሁንና ይሖዋ፣ የሰው ልጆች የአቅም ገደብ እንዳለባቸው ያውቃል። |
በራሳችን ጥረት አለፍጽምናን፣ ኃጢአትንና ሞትን ማስወገድ አንችልም፤ በተጨማሪም እያንዳንዱ ሰው የመምረጥ ነፃነት ስላለው ሌሎች የሚያደርጉትን ነገር መቆጣጠር አንችልም። |
ከዚህም ሌላ የቱንም ያህል እውቀትና ተሞክሮ ያካበትን ብንሆን ከይሖዋ አንጻር ስንታይ ምንጊዜም ሕፃናት ነን። |
ይሖዋ እንደሚደግፈንና እኛ ማድረግ የማንችለውን ነገር ለእኛ ሲል እንደሚያደርግልን በመተማመን ምንጊዜም የእሱን መመሪያዎች መፈለግ ይኖርብናል። |
በሌላ በኩል ደግሞ እጃችንን አጣጥፈን ከመቀመጥ ይልቅ የሚያጋጥሙንን ችግሮች ለመፍታትና ሌሎችን ለመርዳት አቅማችን የሚፈቅደውን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል። |
በሌላ አባባል በይሖዋ መታመን እና መልካም የሆነውን ማድረግ ያስፈልገናል። |
ቤርዜሊ የቀረበለትን ግብዣ አልተቀበለም። |
ለምን? |
ምክንያቱም ዕድሜው ገፍቶ ስለነበር ለንጉሡ ሸክም መሆን አልፈለገም። |
ስለዚህ ቤርዜሊ በእሱ ምትክ ኪምሃም ልጁ ሳይሆን አይቀርም እንዲሄድ ሐሳብ አቀረበ። |
ቤርዜሊ ጥሩ ውሳኔ እንዲያደርግ የረዳው ልኩን ማወቁ ነው። |
የዳዊትን ግብዣ ያልተቀበለው ተጨማሪ ኃላፊነት ለመሸከም ብቁ እንዳልሆነ ስለተሰማው አሊያም የጡረታ ዘመኑን ዘና ብሎ ማሳለፍ ስለፈለገ አልነበረም። |
ይህን ያደረገው ያለበት ሁኔታ እንደተቀየረና የአቅም ገደብ እንዳለበት አምኖ ስለተቀበለ ነው። |
ከአቅሙ በላይ የሆነ የኃላፊነት ሸክም መሸከም አልፈለገም። |
ሥልጣን፣ ኃላፊነት ወይም እውቅና በማግኘት ላይ ትኩረት ካደረግን በውስጣችን የራስ ወዳድነትና የፉክክር መንፈስ ሊያቆጠቁጥ ይችላል፤ ይህም የኋላ ኋላ ለሐዘን ይዳርገናል። |
ከዚህ በተቃራኒ ግን ልካችንን ማወቃችን ከወንድሞቻችን ጋር ተባብረን በመሥራት፣ ችሎታችንንና አቅማችንን ለአምላክ ክብር ለማምጣትና ሌሎችን ለመርዳት እንድንጠቀምበት ያነሳሳናል። |
ይሖዋ በጣም አስደናቂ የሆነ ፈጣሪ ነው። |
የፍጥረት ሥራዎቹ በሙሉ ተወዳዳሪ አይገኝላቸውም። |
ይሖዋ በፍቅር ተነሳስቶ ለሁሉም የፍጥረት ሥራዎቹ ገደብ አበጅቷል። |
ሁሉም ነገር እርስ በርስ ተቀናጅቶ መሥራት እንዲችል የተፈጥሮ ሕጎችንና የሥነ ምግባር ደንቦችን አውጥቷል። |
በመሆኑም በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ያሉት ነገሮች በሙሉ በአምላክ ዓላማ ውስጥ የየራሳቸው ቦታና ድርሻ አላቸው። |
ለምሳሌ ያህል፣ የስበት ሕግ ከባቢ አየር ምንጊዜም በምድር ዙሪያ እንዲኖር ያደርጋል፤ እንዲሁም የባሕር ሞገድንና ውቅያኖሶችን ይቆጣጠራል። |
የስበት ኃይል ባይኖር ኖሮ በምድር ላይ ሕይወት አይኖርም ነበር። |
ይሖዋ ለፍጥረት ሥራዎቹ ያወጣቸው ገደቦች በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ፍጹም የሆነ ሥርዓት እንዲሰፍን አስተዋጽኦ አድርገዋል። |
እንዲህ ያለ ሥርዓት መኖሩ አምላክ ምድርንም ሆነ የሰውን ዘር ሲፈጥር ዓላማ እንዳለው በግልጽ ያሳያል። |
በአገልግሎታችን ላይ የምናገኛቸውን ሰዎች፣ ይህን አስደናቂ አጽናፈ ዓለም የፈጠረውን አምላክ እንዲያውቁ ልንረዳቸው እንችላለን። |
ሙሴን ተክቶ የእስራኤል መሪ የሆነው ኢያሱ፣ የአምላክን ሕዝቦች እየመራ ከከነዓናውያን ጋር በተዋጋበት ወቅት የይሖዋ ሠራዊት አለቃ ረድቶታል። |
ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ደግሞ ንጉሥ ሕዝቅያስ፣ ኢየሩሳሌምን ሊወር ከመጣው አስፈሪ የአሦራውያን ሠራዊት ጋር ተፋጥጦ ነበር። |
በዚህ ጊዜ የይሖዋ መልአክ ወጥቶ በአሦራውያን ሰፈር የነበሩትን 185,000 ሰዎች በአንድ ሌሊት ገደለ። |
እርግጥ ነው፣ መላእክቱ ፍጹማን ቢሆኑም የእነሱን እርዳታ ያገኙት ሰዎች ፍጹማን አልነበሩም። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.