text stringlengths 4 267 |
|---|
ለምሳሌ፣ ሙሴ በአንድ ወቅት ለይሖዋ ክብር ሳይሰጥ ቀርቷል። |
ኢያሱ የአምላክን መመሪያ ሳይጠይቅ ከገባኦናውያን ጋር ቃል ኪዳን ገብቷል። |
ሕዝቅያስም ቢሆን በአንድ ወቅት ልቡ ታብዮ ነበር። |
እነዚህ ሰዎች ፍጽምና የጎደላቸው ቢሆኑም እንኳ እስራኤላውያን የእነሱን አመራር መከተል ይጠበቅባቸው ነበር። |
ይሖዋ፣ በመላእክቱ ተጠቅሞ እነዚህን ሰዎች ደግፏቸዋል። |
በእርግጥም ሕዝቡን የሚመራው ይሖዋ ነበር። |
ብዙ ሰዎች ልብህ የሚልህን አድርግ ሲሉ ይሰማሉ። |
እንዲህ ማድረግ ግን አደገኛ ሊሆን ይችላል። |
ደግሞም ቅዱስ ጽሑፋዊ ድጋፍ የለውም። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ ፍጹም ያልሆነውን ልባችንን ተከትለን ወይም በስሜት ተገፋፍተን ውሳኔ እንዳናደርግ ያሳስበናል። |
ልባችን የሚለንን መከተል የሚያመጣውን አስከፊ መዘዝ የሚያሳዩ ዘገባዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰፍረው እናገኛለን። |
ፍጽምና የጎደለን በመሆናችን ልባችንን ማመን አንችልም፤ ምክንያቱም ልብ ከምንም ነገር በላይ ከዳተኛ ነው፤ ማንኛውንም ነገር ከማድረግ አይመለስም። |
ውሳኔ ስናደርግ ልባችን የሚለንን በመከተል ስሜታችን በአስተሳሰባችንና በድርጊታችን ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድር ብንፈቅድ ውጤቱ ምን ይሆናል? |
ለምሳሌ ያህል፣ በተበሳጨንበት ወቅት ውሳኔ ብናደርግ ምን ሊፈጠር ይችላል? |
ከዚህ ቀደም በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሆነን ውሳኔ አድርገን ከነበረ መልሱ አይጠፋንም። |
ተስፋ በቆረጥንበት ጊዜም ቢሆን ጥሩ ውሳኔ ማድረግ እንደማንችል የታወቀ ነው። |
በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው፣ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎችን ስናደርግ ስሜታችን እንዲቆጣጠረን ከፈቀድን በቀላሉ ልንሳሳት እንችላለን። |
በኢየሩሳሌም ከተሰበሰቡት ሰዎች መካከል ወደ ይሁዲነት የተለወጡ አንዳንድ ግሪካውያን ኢየሱስ ባደረገው ነገር በጣም ተደንቀው እንደነበር መገመት እንችላለን፤ ምክንያቱም ከኢየሱስ ጋር እንዲያገናኛቸው ሐዋርያው ፊልጶስን ጠይቀውት ነበር። |
ኢየሱስ ግን ከፊቱ ከሚጠብቀው ይበልጥ አስፈላጊ የሆነ ጉዳይ ትኩረቱ እንዲሰረቅ አልፈለገም። |
በአምላክ ጠላቶች እጅ መሥዋዕታዊ ሞት ላለመሞት ሲል በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅነት ለማትረፍ አልሞከረም። |
በመሆኑም በቅርቡ እንደሚገደል ከገለጸ በኋላ እንድርያስንና ፊልጶስን እንዲህ አላቸው፦ ሕይወቱን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ በዚህ ዓለም ሕይወቱን የሚጠላ ሁሉ ግን ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል። |
ኢየሱስ የእነዚህን ግሪካውያን ስሜት ከማስተናገድ ይልቅ እሱ ያሳየውን የራስን ጥቅም መሥዋዕት የማድረግ መንፈስ ማንጸባረቅ የተሻለ እንደሆነ ከገለጸ በኋላ በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ ያለውን ሐሳብ ተናገረ። |
ፊልጶስ ይህን አበረታች መልእክት ሄዶ ለግሪካውያኑ እንደነገራቸው ምንም ጥርጥር የለውም። |
ምንም እንኳ ኢየሱስ ትኩረቱን ሙሉ በሙሉ በስብከቱ ሥራ ላይ ያደረገ ቢሆንም ሁልጊዜ ስለ ሥራ ብቻ ያስብ ነበር ማለት አይደለም። |
ስደት ቢደርስብንም እንኳ የይሖዋን የጽድቅ መሥፈርቶችና ሕጎች ለመጠበቅ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን። |
የይሖዋን መመሪያዎች በሕይወታችን ውስጥ በሥራ ላይ በማዋል ብርሃናችን በሰው ፊት እንዲበራ እናደርጋለን፤ ይህ ደግሞ ለይሖዋ ስም ክብር ያመጣል። |
የአምላክ ቅዱስ ሕዝቦች እንደመሆናችን መጠን፣ የይሖዋ ሕጎች ትክክለኛ መሆናቸውንና የሰይጣን ክስ ሐሰት መሆኑን በአኗኗራችን እናሳያለን። |
እርግጥ ነው፣ እንደ ማንኛውም ሰው ስህተት መሥራታችን አይቀርም፤ በዚህ ጊዜ ከልባችን ንስሐ በመግባት ይሖዋን ከሚያስነቅፉ ድርጊቶች እንርቃለን። |
ይሖዋ በክርስቶስ መሥዋዕት ላይ እምነት ካለን ኃጢአታችንን ይቅር ይለናል። |
ራሳቸውን ለእሱ የወሰኑ ሰዎችን አገልጋዮቹ አድርጎ ይቀበላቸዋል። |
ይሖዋ፣ ቅቡዓን ክርስቲያኖችን ልጆቹ አድርጎ በመቀበል ጻድቃን ብሎ ጠርቷቸዋል፤ ሌሎች በጎችን ደግሞ ወዳጆቹ አድርጎ በመቀበል እንደ ጻድቃን ይቆጥራቸዋል። |
በመሆኑም በአሁኑ ጊዜም እንኳ ቤዛው፣ በሰማዩ አባታችን ዘንድ የጽድቅ አቋም እንዲኖረንና ስሙን በማስቀደስ ረገድ የበኩላችንን ድርሻ እንድናበረክት አስችሎናል። |
እኛም ይሖዋ እንደሚሰማንና በደስታ ለመጽናት የሚያስችል ብርታት እንደሚሰጠን ስለምናውቅ የሚያስጨንቀንን ነገር ሁሉ አውጥተን ለእሱ መናገር እንችላለን። |
አምላክ ለጸሎታችን መልስ ሲሰጠን ደግሞ እምነታችን እየጠነከረ ይሄዳል። |
እምነት ከመንፈስ ፍሬ ገጽታዎች አንዱ በመሆኑ መንፈስ ቅዱስን ለማግኘት ኢየሱስ እንደመከረን ደጋግመን መለመን ይኖርብናል። |
ይሁን እንጂ የምንጸልየው አምላክ እንዲረዳን ለመጠየቅ ብቻ መሆን የለበትም። |
ይሖዋን በየዕለቱ እንድናመሰግነውና እንድናወድሰው የሚያነሳሱንን ድንቅ ሥራዎቹን ዘርዝረን መጨረስ አንችልም! በተጨማሪም ጸሎታችን፣ በእስር ላይ ያሉትን ከእነሱ ጋር ታስረን እንዳለን አድርገን በማሰብ ሁልጊዜ እንደምናስታውሳቸው የሚያሳይ መሆን አለበት። |
ከዚህም ሌላ ለመላው የወንድማማች ማኅበር በተለይም በመካከላችን ሆነው አመራር ለሚሰጡት ልንጸልይ ይገባል። |
ይሖዋ፣ ሁላችንም ለምናቀርበው ጸሎት መልስ እንደሚሰጥ ስንመለከት ልባችን በደስታ ይሞላል! |
ቦዔዝ የሩት ሁኔታ እንዲሁም የባዕድ አገር ሰው በመሆኗ ሊያጋጥማት የሚችለው ችግር አሳስቦት ነበር። |
ይህን ከሚጠቁሙት ነገሮች አንዱ፣ ማሳ ውስጥ የሚሠሩት ወንዶች እንዳያስቸግሯት ከወጣት ሴት ሠራተኞቹ ሳትርቅ እንድትሠራ የነገራት መሆኑ ነው። |
ሌላው ቀርቶ እንደ ቅጥር ሠራተኞቹ ሁሉ እሷም በቂ ምግብና ውኃ ማግኘት እንድትችል አድርጎ ነበር። |
በተጨማሪም ቦዔዝ ሩትን ያነጋገረበት መንገድ ይህችን ድሃ የባዕድ አገር ሴት ዝቅ አድርጎ እንደማይመለከታት የሚያሳይ ነው፤ እንዲያውም አበረታቷታል። |
ቦዔዝ፣ ሩትን እንዲያደንቃት ያደረገው ለአማቷ ለናኦሚ የነበራት ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍቅር ብቻ ሳይሆን የይሖዋ አምላኪ ለመሆን መወሰኗም ጭምር ነው። |
ቦዔዝ፣ በክንፎቹ ሥር ለመጠለል ብላ ወደ እስራኤል አምላክ ለመጣችው ለሩት ደግነት ማሳየቱ እንደ ይሖዋ ዓይነት ታማኝ ፍቅር እንደነበረው ይጠቁማል። |
እኛም በተመሳሳይ ደግነት ማሳየታችን ሁሉም ዓይነት ሰዎች እውነትን እንዲያውቁ እንዲሁም ይሖዋ ምን ያህል እንደሚወዳቸው እንዲገነዘቡ ሊረዳቸው ይችላል። |
የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች የነበራቸውን ድፍረትና ሐቀኝነት እንመልከት። |
ብዙዎቹ የጥንት ጸሐፊዎች ያሰፈሯቸው ዘገባዎች መሪዎቻቸውን የሚክቡና አገራቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ናቸው። |
የይሖዋ ነቢያት ግን ምንጊዜም እውነተኛውን ዘገባ ያሰፍሩ ነበር። |
የሕዝባቸውን ሌላው ቀርቶ የንጉሦቻቸውንም ጭምር ድክመት አስፍረዋል። |
ከዚህም ሌላ ጸሐፊዎቹ ራሳቸውም ሆኑ ሌሎች የአምላክ አገልጋዮች የፈጸሟቸውን ስህተቶች ሳይሸሽጉ ዘግበዋል። |
መጽሐፍ ቅዱስ ለሕይወት ጠቃሚ የሆኑ መመሪያዎችን የያዘ በመሆኑ፣ ብዙዎች ይህ መጽሐፍ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፈ መሆኑን እንዲያምኑ አድርጓቸዋል። |
የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎች ተግባራዊ ማድረጋችን በሐሰት አምልኮ እንዳንካፈል የጠበቀን ከመሆኑም ሌላ ብዙዎችን ባሪያ ካደረጉት አጉል እምነቶች ነፃ አውጥቶናል። |
እንደ ዝግመተ ለውጥ ያሉ ትምህርቶች ለይሖዋ ብቻ የሚገባውን የአምላክነት ቦታ ለፍጥረት እንዲሰጥ አድርገዋል። |
አምላክ የለም የሚሉ ሰዎች የወደፊት ሕልውናችን ሙሉ በሙሉ በሰው ልጆች እጅ እንደሆነ ይሰማቸዋል። |
ይሁንና የተሻለ የወደፊት ሕይወት እንደሚኖረን እርግጠኛ የሆነ ተስፋ ሊሰጡን አይችሉም። |
አምላክ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ሕግ አንድ ግለሰብ ወንድ ይሁን ሴት ለመለየት የሚያስቸግር አለባበስን ይሖዋ አጥብቆ እንደሚጠላ በግልጽ ያሳያል፤ በዛሬው ጊዜ ይህ ዓይነቱ አለባበስ ፋሽን እየሆነ መጥቷል። |
አምላክ አለባበስን በተመለከተ ከሰጠው መመሪያ በግልጽ መመልከት እንደሚቻለው ወንዶች ሴት እንዲመስሉ፣ ሴቶች ደግሞ ወንድ እንዲመስሉ አሊያም በሁለቱ ፆታዎች መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ አዳጋች እንዲሆን የሚያደርጉ አለባበሶችን አምላክ ይጠላል። |
የአምላክ ቃል፣ ክርስቲያኖች ከአለባበስ ጋር በተያያዘ ጥሩ ውሳኔ እንዲያደርጉ የሚረዷቸው መሠረታዊ ሥርዓቶችን ይዟል። |
ክርስቲያኖች የሚኖሩበት ቦታ፣ ባሕላቸው ወይም የአየሩ ሁኔታ ምንም ይሁን ምን እነዚህን መሠረታዊ ሥርዓቶች ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። |
የትኛው አለባበስ ተቀባይነት እንዳለውና የትኛው ደግሞ ተገቢ እንዳልሆነ የሚገልጽ ዝርዝር መመሪያ አያስፈልገንም። |
በቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረታዊ ሥርዓቶች የምንመራ ሲሆን እነዚህ መሠረታዊ ሥርዓቶች ምንም ዓይነት የግል ምርጫ እንዳይኖረን የሚከለክሉ አይደሉም። |
ይሖዋ በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት እኛን ለማበርታት ችሎታውም ሆነ ፍላጎቱ አለው። |
በመሆኑም ሰይጣንና ይህ ክፉ ሥርዓት የሚያመጡብንን ማንኛውንም ፈተና መቋቋም እንድንችል ይሖዋ መንፈሱን እንዲሰጠን መጠየቃችን ወሳኝ ነገር ነው። |
በተጨማሪም በአምላክ ቅዱስ መንፈስ መሪነት የተጻፈው ቃሉ ስላለን እጅግ አመስጋኞች ነን። |
እስቲ በየወሩ ስለምናገኘው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ መንፈሳዊ ምግብም አስቡ። |
ላይ የሚገኘው ትንቢት የተነገረው በኢየሩሳሌም የነበረው ቤተ መቅደስ በድጋሚ በሚገነባበት ወቅት ነው፤ በዚህ ጥቅስ ላይ የሚገኘው ማበረታቻ ለእኛም በጣም ጠቃሚ ነው። |
ከዚህም ሌላ በጉባኤ ስብሰባዎችና በትላልቅ ስብሰባዎች እንዲሁም በቲኦክራሲያዊ ትምህርት ቤቶች አማካኝነት ከሚሰጠን ትምህርት ብርታት እናገኛለን። |
የምናገኘው ሥልጠና መንፈሳዊ ግቦች እንድናወጣ እንዲሁም ያሉብንን በርካታ ክርስቲያናዊ ኃላፊነቶች እንድንፈጽም ያነሳሳናል። |
ወጣቶች በይሖዋ አገልግሎት ብዙ ነገር ለማከናወን የሚያስችል ጉልበት አላቸው። |
በቤቴል የሚያገለግሉ አንዳንድ ወጣቶች፣ መጽሐፍ ቅዱሶችንና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን በማተሙና በመጠረዙ ሥራ ይካፈላሉ። |
ጥቂት የማይባሉ ወጣት ወንድሞችና እህቶች የመንግሥት አዳራሾችን በመገንባትና በማደስ ሥራ ይሳተፋሉ። |
የተፈጥሮ አደጋዎች ሲከሰቱ ወጣቶች፣ ተሞክሮ ካላቸው ወንድሞች ጋር በመሆን በአደጋው ለተጎዱ ሰዎች እርዳታ ይሰጣሉ። |
እንዲሁም በርካታ ወጣት አቅኚዎች ምሥራቹን ለመስበክ ሲሉ ሌላ ቋንቋ ይማራሉ፤ ወይም ወደ ሌላ አካባቢ ተዛውረው ያገለግላሉ። |
መዝሙራዊው ይሖዋን የሚሹ መልካም ነገር አይጎድልባቸውም ሲል ዘምሯል። |
በእርግጥም ይሖዋ በቅንዓት የሚያገለግሉትን ፈጽሞ አያሳፍራቸውም። |
በይሖዋ አገልግሎት የቻልነውን ሁሉ ስናደርግ በግለሰብ ደረጃ፣ ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ቀምሰን ማየት እንችላለን። |
አምላክን በሙሉ ነፍሳችን ማገልገላችን ተወዳዳሪ የሌለው ደስታ ያስገኝልናል። |
አንድ ሰው በፆታ ብልግና ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሕጋዊ ፍቺ ቢፈጽምም እንኳ ሌላ ሰው ለማግባት ነፃ አይሆንም። |
እርግጥ ነው፣ ሆሴዕ የፆታ ብልግና የፈጸመችውን ሚስቱን ጎሜርን ይቅር እንዳላት ሁሉ ክህደት የተፈጸመበት አንድ ባለትዳርም ንስሐ የገባውን የትዳር ጓደኛውን ይቅር ለማለት ሊመርጥ ይችላል። |
በመንፈሳዊ ሁኔታ ምንዝር የፈጸሙት እስራኤላውያን ንስሐ ሲገቡ ይሖዋ ምሕረት አድርጎላቸዋል። |
በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ባለትዳር፣ የትዳር ጓደኛው ምንዝር እንደፈጸመ ካወቀ በኋላም ከእሱ ጋር የፆታ ግንኙነት መፈጸሙን ቢቀጥል እንዲህ ማድረጉ ለበዳዩ ይቅርታ እንዳደረገለት ስለሚቆጠር ከዚያ በኋላ ፍቺ ለመፈጸም የሚያስችል ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረት አይኖረውም። |
ኢየሱስ በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ ያለውን ሐሳብ ከተናገረ በኋላ ነጠላ ሆነው ለመኖር ስጦታው ያላቸው ሰዎች እንዳሉ ገልጿል። |
አክሎም ይህን ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው በማለት ተናግሯል። |
ብዙዎች፣ ሐሳባቸው ሳይከፋፈል ይሖዋን ለማገልገል ሲሉ ነጠላ ሆነው ለመኖር መርጠዋል። |
እንዲህ በማድረጋቸውም አድናቆት ሊቸራቸው ይገባል። |
የይሖዋ ጸጋ ብዙ በረከቶች የሚያስገኝልን ቢሆንም ይሖዋ የፈለግነውን ብናደርግ በቸልታ እንደሚያልፈን አድርገን ማሰብ አይኖርብንም። |
ከጥንቶቹ ክርስቲያኖች መካከል አንዳንዶቹ በአምላክ ጸጋ እያሳበቡ ዓይን ያወጣ ምግባር ይፈጽሙ ነበር። |
እነዚህ ታማኝ ያልሆኑ ክርስቲያኖች፣ ኃጢአት ቢፈጽሙም ይሖዋ ሁልጊዜ ይቅር እንደሚላቸው ያስቡ የነበረ ይመስላል። |
ይባስ ብለው ደግሞ ወንድሞቻቸውም የእነሱን አስጸያፊ አካሄድ እንዲከተሉ ይገፋፉ ነበር። |
ዛሬም ቢሆን እንዲህ የሚያደርግ ማንኛውም ሰው የጸጋን መንፈስ በንቀት እያጥላላ ነው። |
በዛሬው ጊዜ ሰይጣን፣ አንዳንድ ክርስቲያኖችን ኃጢአት ቢፈጽሙም አምላክ ምሕረት እንደሚያደርግላቸውና ምንም ቅጣት እንደማይደርስባቸው አድርገው እንዲያስቡ በማድረግ እያታለላቸው ነው። |
ይሖዋ ንስሐ የሚገቡ ኃጢአተኞችን ይቅር የሚል ቢሆንም እንኳ የኃጢአት ዝንባሌያችንን ለማሸነፍ አጥብቀን እንድንታገል ይጠብቅብናል። |
‘ለአምላክ ያደሩ መሆንን የሚያሳዩ ተግባሮች በጉባኤ ውስጥ የምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሲሆኑ አዘውትሮ በስብሰባ ላይ መገኘትንና በአገልግሎት መካፈልን ያካትታሉ። |
በግልህ እንደምታቀርበው ጸሎትና የግል ጥናት የመሳሰሉ ሰዎች የማያዩአቸው መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችም በዚህ ውስጥ ይጠቃለላሉ። |
ራሱን ለይሖዋ የወሰነ ግለሰብ እነዚህን ነገሮች እንደ አድካሚ ሥራ አይመለከታቸውም። |
ከዚህ ይልቅ ንጉሥ ዳዊት የገለጸው የሚከተለው አመለካከት ይኖረዋል፦ አምላኬ ሆይ፣ ፈቃድህን ማድረግ ያስደስተኛል፤ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው። |
ራስህን የወሰንክና የተጠመቅክ ክርስቲያን ስትሆን በይሖዋ ፊት የምትቆመው ራስህን ችለህ እንደሆነ አስታውስ። |
ለእሱ የምታቀርበው አገልግሎት በማንም ላይ ሌላው ቀርቶ በወላጆችህ ላይ የተመካ መሆን የለበትም። |
ቅዱስ ሥነ ምግባር መያዝህ እንዲሁም ለአምላክ ያደርክ መሆንህን የሚያሳይ ተግባር መፈጸምህ እውነትን የራስህ እንዳደረግክና ለመጠመቅ ብቃቱን እያሟላህ እንደሆነ ያሳያል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.