text stringlengths 4 267 |
|---|
ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትም፣ ዛሬም፣ ለዘላለምም ያው ነው። |
በልዩ ልዩና እንግዳ በሆኑ ትምህርቶች አትወሰዱ፤ ልባችን በምግብ ሳይሆን በአምላክ ጸጋ ቢጠናከር መልካም ነውና፤ በዚህ የተጠመዱ ምንም አልተጠቀሙም። |
እኛ መሠዊያ ያለን ሲሆን በድንኳኑ ውስጥ ቅዱስ አገልግሎት የሚያቀርቡት ከመሠዊያው ላይ ወስደው መብላት አይፈቀድላቸውም። |
ምክንያቱም ሊቀ ካህናቱ የእንስሳቱን ደም የኃጢአት መባ አድርጎ ወደ ቅዱሱ ስፍራ የሚወስደው ሲሆን ሥጋው ግን ከሰፈሩ ውጭ ይቃጠላል። |
ስለዚህ ኢየሱስም ሕዝቡን በገዛ ራሱ ደም ለመቀደስ ከከተማው በር ውጭ መከራ ተቀበለ። |
እንግዲህ እኛም እሱ የተሸከመውን ነቀፋ ተሸክመን ከሰፈር ውጭ እሱ ወዳለበት እንሂድ፤ |
በዚህ ቋሚ ከተማ የለንምና፤ ከዚህ ይልቅ ወደፊት የምትመጣዋን ከተማ በጉጉት እንጠባበቃለን። |
ስለዚህ በኢየሱስ አማካኝነት የውዳሴ መሥዋዕት ዘወትር ለአምላክ እናቅርብ፤ ይህም ስሙን በይፋ የምናውጅበት የከንፈራችን ፍሬ ነው። |
በተጨማሪም መልካም ማድረግንና ያላችሁን ነገር ለሌሎች ማካፈልን አትርሱ፤ አምላክ እንዲህ ባሉት መሥዋዕቶች እጅግ ይደሰታልና። |
ተግተው ስለሚጠብቋችሁና ይህን በተመለከተ ስሌት ስለሚያቀርቡ በመካከላችሁ ሆነው አመራር ለሚሰጧችሁ ታዘዙ እንዲሁም ተገዙ፤ ይህን የምታደርጉት ሥራቸውን በደስታ እንጂ በሐዘን እንዳያከናውኑ ነው፤ አለዚያ ሥራቸውን የሚያከናውኑት በሐዘን ይሆናል፤ ይህ ደግሞ እናንተን ይጎዳችኋል። |
ለእኛ መጸለያችሁን ቀጥሉ፤ ምክንያቱም ሐቀኛ ሕሊና እንዳለን እናምናለን፤ ደግሞም በሁሉም ነገር በሐቀኝነት ለመኖር እንፈልጋለን። |
በተለይ ደግሞ ወደ እናንተ በፍጥነት ተመልሼ እንድመጣ ትጸልዩልኝ ዘንድ አሳስባችኋለሁ። |
እንግዲያው ታላቅ የበጎች እረኛ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ የዘላለማዊውን ቃል ኪዳን ደም ይዞ ከሞት እንዲነሳ ያደረገው የሰላም አምላክ |
ፈቃዱን እንድታደርጉ በመልካም ነገር ሁሉ ያስታጥቃችሁ፤ እሱ በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን ነገር እንድናደርግ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ያነሳሳናል። ለእሱ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን። |
እንግዲህ ወንድሞች፣ የጻፍኩላችሁ ደብዳቤ አጭር ስለሆነ ይህን የማበረታቻ ቃል በትዕግሥት እንድታዳምጡ አሳስባችኋለሁ። |
ወንድማችን ጢሞቴዎስ መፈታቱን እንድታውቁ እፈልጋለሁ። ቶሎ ከመጣ አብረን መጥተን እናያችኋለን። |
በመካከላችሁ ሆነው አመራር ለሚሰጧችሁ ሁሉና ለቀሩት ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጣሊያን ያሉት ሰላምታ ልከውላችኋል። |
የአምላክ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን። |
ስለሆነም የሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች፣ በእሱ እንደምናምን በይፋ የምንናገርለትን፣ ሐዋርያና ሊቀ ካህናት የሆነውን ኢየሱስን አስቡ። |
ሙሴ በመላው የአምላክ ቤት ላይ ታማኝ እንደነበረ ሁሉ እሱም ለሾመው ታማኝ ነበር። |
ቤቱን የሠራው፣ ከቤቱ የበለጠ ክብር ስላለው እሱ ከሙሴ የበለጠ ክብር ይገባዋል። |
እያንዳንዱ ቤት ሠሪ እንዳለው የታወቀ ነው፤ ሁሉን ነገር የሠራው ግን አምላክ ነው። |
ሙሴም በመላው የአምላክ ቤት ላይ ታማኝ አገልጋይ ነበር። አገልግሎቱም ከጊዜ በኋላ ለሚነገሩ ነገሮች ምሥክር ነው። |
ክርስቶስ ግን በአምላክ ቤት ላይ የተሾመ ታማኝ ልጅ ነበር። እኛም አፋችንን ሞልተን የመናገር ነፃነታችንንና የምንደሰትበትን ተስፋችንን እስከ መጨረሻው አጥብቀን ከያዝን የአምላክ ቤት ነን። |
ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ዛሬ ድምፁን የምትሰሙ ከሆነ |
በምድረ በዳ እጅግ የሚያስቆጣ ድርጊት በተፈጸመበት በፈተና ቀን እንደሆነው ልባችሁን አታደንድኑ፤ |
በዚያ፣ አባቶቻችሁ ያደረግኩትን ሁሉ ለ40 ዓመት ቢያዩም እኔን በመፈተን ተገዳደሩኝ። |
በዚህም ምክንያት በዚያ ትውልድ በጣም ተንገሸገሽኩ፤ እንዲህም አልኩ፦ ‘ሁልጊዜ ልባቸው ይስታል፤ መንገዴንም ሊያውቁ አልቻሉም።’ |
በመሆኑም ‘ወደ እረፍቴ አይገቡም’ ብዬ በቁጣዬ ማልኩ።” |
ወንድሞች፣ ሕያው ከሆነው አምላክ በመራቅ እምነት የለሽ የሆነ ክፉ ልብ ከእናንተ መካከል በማናችሁም ውስጥ እንዳያቆጠቁጥ ተጠንቀቁ፤ |
ከዚህ ይልቅ ከእናንተ መካከል አንዳችሁም ኃጢአት ባለው የማታለል ኃይል እንዳትደነድኑ “ዛሬ” ተብሎ የሚጠራ ጊዜ እስካለ ድረስ በየዕለቱ እርስ በርሳችሁ ተበረታቱ። |
የክርስቶስ ተካፋዮች የምንሆነው በመጀመሪያ የነበረንን ትምክህት እስከ መጨረሻው አጽንተን ከያዝን ብቻ ነውና። |
ይህም “ዛሬ ድምፁን የምትሰሙ ከሆነ እጅግ የሚያስቆጣ ድርጊት በተፈጸመበት ጊዜ እንደሆነው ልባችሁን አታደንድኑ” እንደተባለው ነው። |
ድምፁን ቢሰሙም እንኳ እጅግ ያስቆጡት እነማን ነበሩ? ይህን ያደረጉት ሙሴ እየመራቸው ከግብፅ የወጡት ሁሉ አይደሉም? |
ከዚህም ሌላ ለ40 ዓመት አምላክ በእነሱ እንዲንገሸገሽ ያደረጉት እነማን ናቸው? እነዚያ ኃጢአት የሠሩትና ሬሳቸው በምድረ በዳ ወድቆ የቀረው አይደሉም? |
ደግሞስ ወደ እረፍቴ አይገቡም ብሎ የማለው ስለ እነማን ነው? እነዚያን ያልታዘዙትን በተመለከተ አይደለም? |
ስለዚህ ሊገቡ ያልቻሉት እምነት በማጣታቸው የተነሳ እንደሆነ እንረዳለን። |
የቀድሞው ቃል ኪዳን በበኩሉ ቅዱስ አገልግሎት የሚከናወንባቸው ደንቦችና በምድር ላይ የራሱ ቅዱስ ስፍራ ነበረው። |
መቅረዙ፣ ጠረጴዛውና በአምላክ ፊት የቀረበው ኅብስት የሚገኙበት የድንኳኑ የመጀመሪያው ክፍል ተሠርቶ ነበር፤ ይህም ቅድስት ይባላል። |
ከሁለተኛው መጋረጃ በስተ ኋላ ግን ቅድስተ ቅዱሳን የሚባለው የድንኳኑ ክፍል ይገኝ ነበር። |
በዚህ ክፍል ውስጥ የወርቅ ጥና እና ሙሉ በሙሉ በወርቅ የተለበጠው የቃል ኪዳኑ ታቦት ይገኙ ነበር፤ በታቦቱ ውስጥም መና የያዘው የወርቅ ማሰሮ፣ ያቆጠቆጠችው የአሮን በትርና የቃል ኪዳኑ ጽላቶች ነበሩ፤ |
በላዩ ላይ ደግሞ የስርየት መክደኛውን የሚጋርዱ ክብራማ ኪሩቦች ነበሩ። ይሁንና ስለ እነዚህ ነገሮች በዝርዝር ለመናገር አሁን ጊዜው አይደለም። |
እነዚህ ነገሮች በዚህ መንገድ ከተሠሩ በኋላ ካህናቱ ቅዱስ አገልግሎቶችን ለማከናወን ወደ ድንኳኑ የመጀመሪያ ክፍል ሁልጊዜ ይገባሉ፤ |
ወደ ሁለተኛው ክፍል የሚገባው ግን ሊቀ ካህናቱ ብቻ ነበር፤ የሚገባውም በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው፤ ደግሞም ለራሱና ሕዝቡ ባለማወቅ ለፈጸመው ኃጢአት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም። |
በዚህ መንገድ፣ የመጀመሪያው ድንኳን ተተክሎ ሳለ ወደ ቅዱሱ ስፍራ የሚወስደው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ግልጽ አድርጓል። |
ይህ ድንኳን ለአሁኑ ዘመን ምሳሌ ሲሆን ከዚህ ዝግጅት ጋር በሚስማማ ሁኔታ ስጦታዎችና መሥዋዕቶች ይቀርባሉ። ይሁን እንጂ እነዚህ ነገሮች ቅዱስ አገልግሎት የሚያቀርበው ሰው ፍጹም በሆነ መንገድ ንጹሕ ሕሊና እንዲኖረው ሊያደርጉ አይችሉም። |
እነዚህ ነገሮች ከምግብ፣ ከመጠጥና ከተለያዩ የመንጻት ሥርዓቶች ጋር ብቻ የተያያዙ ናቸው። ደግሞም አካልን የሚመለከቱ ደንቦች ሲሆኑ በሥራ ላይ የዋሉትም፣ ሁኔታዎች የሚስተካከሉበት የተወሰነው ጊዜ እስኪመጣ ድረስ ነበር። |
ይሁን እንጂ ክርስቶስ አሁን ላሉት መልካም ነገሮች ሊቀ ካህናት ሆኖ በመጣ ጊዜ በሰው እጅ ወዳልተሠራው ይኸውም ከዚህ ፍጥረት ወዳልሆነው ይበልጥ ታላቅና ፍጹም ወደሆነው ድንኳን ገብቷል። |
ወደ ቅዱሱ ስፍራ የገባው የፍየሎችንና የወይፈኖችን ደም ይዞ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ የገዛ ራሱን ደም ይዞ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገባ፤ ደግሞም ለእኛ ዘላለማዊ መዳን አስገኘልን። |
የፍየሎችና የኮርማዎች ደም እንዲሁም በረከሱ ሰዎች ላይ የሚረጭ የጊደር አመድ ሥጋን በማንጻት የሚቀድስ ከሆነ |
በዘላለማዊ መንፈስ አማካኝነት ራሱን ያላንዳች እንከን ለአምላክ ያቀረበው የክርስቶስ ደም ሕያው ለሆነው አምላክ ቅዱስ አገልግሎት እንድናቀርብ ሕሊናችንን ከሞቱ ሥራዎች እንዴት አብልጦ አያነጻም? |
የአዲስ ቃል ኪዳን መካከለኛ የሆነው በዚህ ምክንያት ነው። መካከለኛ የሆነውም የተጠሩት የዘላለማዊውን ውርሻ ተስፋ ይቀበሉ ዘንድ ነው። ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው በሞቱ የተነሳ ሲሆን በእሱ ሞት አማካኝነት በቀድሞው ቃል ኪዳን ሥር ሆነው ሕግ በመተላለፍ ከፈጸሟቸው ድርጊቶች በቤዛ ነፃ ወጥተዋል። |
ቃል ኪዳን ሲኖር ቃል ኪዳኑን የፈጸመው ሰው መሞቱ መረጋገጥ አለበት፤ |
ምክንያቱም ቃል ኪዳኑን የፈጸመው ሰው በሕይወት እስካለ ድረስ ቃል ኪዳኑ መቼም ተፈጻሚ ሊሆን ስለማይችል ቃል ኪዳን የሚጸናው ሞትን መሠረት በማድረግ ነው። |
ከዚህም የተነሳ የቀድሞው ቃል ኪዳንም ያለደም ሥራ ላይ መዋል አልጀመረም። |
ሙሴ በሕጉ ላይ የሰፈረውን እያንዳንዱን ትእዛዝ ለሕዝቡ ሁሉ ከተናገረ በኋላ የወይፈኖችንና የፍየሎችን ደም ከውኃ፣ ከቀይ ሱፍና ከሂሶጵ ጋር ወስዶ መጽሐፉንና ሕዝቡን ሁሉ ረጭቷል፤ |
የረጨውም “አምላክ እንድትጠብቁት ያዘዛችሁ የቃል ኪዳኑ ደም ይህ ነው” ብሎ ነው። |
በተመሳሳይም በድንኳኑና ቅዱስ አገልግሎት በሚቀርብባቸው ዕቃዎች ሁሉ ላይ ደም ረጭቷል። |
አዎ፣ በሕጉ መሠረት ሁሉም ነገር ማለት ይቻላል በደም ይነጻል፤ ደም ካልፈሰሰ በስተቀር ይቅርታ ማግኘት አይቻልም። |
ስለዚህ በሰማያት ላሉት ነገሮች ዓይነተኛ አምሳያ የሆኑት ሁሉ በዚህ መንገድ መንጻታቸው የግድ አስፈላጊ ነበር፤ በሰማያት ያሉት ነገሮች ግን የተሻሉ መሥዋዕቶች ያስፈልጓቸዋል። |
ክርስቶስ የገባው በሰው እጅ ወደተሠራውና የእውነተኛው ቅዱስ ስፍራ አምሳያ ወደሆነው ስፍራ አይደለምና፤ ከዚህ ይልቅ አሁን ስለ እኛ በአምላክ ፊት ይታይ ዘንድ ወደ ሰማይ ገብቷል። |
የገባው ግን ሊቀ ካህናቱ የራሱን ሳይሆን የእንስሳ ደም ይዞ በየዓመቱ ወደ ቅዱሱ ስፍራ ይገባ እንደነበረው ራሱን ብዙ ጊዜ መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ አይደለም። |
አለዚያማ ዓለም ከተመሠረተ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ መቀበል ባስፈለገው ነበር። አሁን ግን ራሱን መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ኃጢአትን ለማስወገድ በሥርዓቶቹ መደምደሚያ ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ራሱን ገልጧል። |
ሰው ሁሉ አንድ ጊዜ መሞቱ አይቀርም፤ ከዚያ በኋላ ግን ፍርድ ይቀበላል፤ |
በተመሳሳይም ክርስቶስ የብዙዎችን ኃጢአት ለመሸከም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕት ሆኖ ቀርቧል፤ ለሁለተኛ ጊዜ የሚገለጠውም ኃጢአትን ለማስወገድ አይደለም፤ መዳን ለማግኘት እሱን በጉጉት የሚጠባበቁትም ያዩታል። |
ቀስ በቀስ እንዳንወሰድ ለሰማናቸው ነገሮች ከወትሮው የበለጠ ትኩረት መስጠታችን አስፈላጊ የሆነው ለዚህ ነው። |
በመላእክት አማካኝነት የተነገረው ቃል የጸና መሆኑ ከተረጋገጠ እንዲሁም ማንኛውም አለመታዘዝና መተላለፍ ከፍትሕ ጋር የሚስማማ ቅጣት የሚያስከትል ከሆነ |
እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንል እንዴት ከቅጣት ልናመልጥ እንችላለን? ይህ መዳን መጀመሪያ ጌታችን የተናገረው ሲሆን እሱን የሰሙት ሰዎችም ለእኛ አረጋግጠውልናል፤ |
አምላክም በምልክቶች፣ በድንቅ ነገሮች፣ በተለያዩ ተአምራትና ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን በማደል መሥክሯል። |
ይህን የምንናገርለትን መጪውን ዓለምያስገዛው ለመላእክት አይደለምና። |
ነገር ግን አንድ ምሥክር፣ አንድ ቦታ ላይ እንዲህ ብሏል፦ “ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ወይስ ትንከባከበው ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው? |
ከመላእክት ጥቂት አሳነስከው፤ የክብርና የሞገስ ዘውድ ደፋህለት፤ እንዲሁም በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምከው። |
ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች አስገዛህለት።” አምላክ ሁሉንም ነገር ለእሱ ስላስገዛ፣ ያላስገዛለት ምንም ነገር የለም። ይሁንና በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ነገር ተገዝቶለት አናይም። |
ነገር ግን ከመላእክት በጥቂቱ እንዲያንስ ተደርጎ የነበረው ኢየሱስ እስከ ሞት ድረስ መከራ በመቀበሉ አሁን የክብርና የሞገስ ዘውድ ደፍቶ እናየዋለን፤ እሱ በአምላክ ጸጋ ለሰው ሁሉ ሲል ሞትን ቀምሷል። |
ሁሉ ነገር የሚኖረው ለአምላክ ነው፤ የሚኖረውም በእሱ አማካኝነት ነው። ስለዚህ አምላክ ብዙ ልጆችን ክብር ለማጎናጸፍ ሲል ለመዳን የሚያበቃቸውን “ዋና ወኪል” በመከራ አማካኝነት ፍጹም ማድረጉ የተገባ ነበር። |
የሚቀድሰውም ሆነ የሚቀደሱት ሰዎች፣ ሁሉም ከአንድ አባት የመጡ ናቸውና፤ ከዚህም የተነሳ እነሱን ወንድሞች ብሎ ለመጥራት አያፍርም፤ |
ምክንያቱም “ስምህን ለወንድሞቼ አሳውቃለሁ፤ በጉባኤ መካከልም በመዝሙር አወድስሃለሁ” ይላል። |
ደግሞም “እኔ እምነቴን በእሱ ላይ እጥላለሁ” ይላል። እንደገናም “እነሆ! እኔና ይሖዋ የሰጠኝ ልጆች” ይላል። |
ስለዚህ እነዚህ “ልጆች” ሥጋና ደም ስለሆኑ እሱም ሥጋና ደም ሆነ፤ ይህም የሆነው ለሞት የመዳረግ አቅም ያለውን ዲያብሎስን በሞቱ አማካኝነት እንዳልነበረ ያደርገው ዘንድ ነው፤ |
እንዲሁም ሞትን በመፍራታቸው በሕይወት ዘመናቸው በሙሉ በባርነት ቀንበር የተያዙትን ሁሉ ነፃ እንዲያወጣ ነው። |
እሱ እየረዳ ያለው መላእክትን እንዳልሆነ የታወቀ ነውና፤ ከዚህ ይልቅ እየረዳ ያለው የአብርሃምን ዘር ነው። |
ስለሆነም ለሕዝቡ ኃጢአት የማስተሰረያ መሥዋዕት ለማቅረብ በአምላክ አገልግሎት መሐሪና ታማኝ ሊቀ ካህናት ይሆን ዘንድ በሁሉ ረገድ እንደ “ወንድሞቹ” መሆን አስፈለገው። |
በተፈተነ ጊዜ እሱ ራሱ መከራ ስለደረሰበት በፈተና ላይ ላሉት ሊደርስላቸው ይችላል። |
ሕጉ ወደፊት ለሚመጡት መልካም ነገሮች ጥላ ነው እንጂ የእነዚህ ነገሮች እውነተኛ አካል አይደለም፤ ስለዚህ ሕጉ ከዓመት ዓመት እነዚያኑ መሥዋዕቶች በማቅረብ አምላክን የሚያመልኩትን ሰዎች ፍጹም ሊያደርጋቸው አይችልም። |
ቢችልማ ኖሮ መሥዋዕት ማቅረቡን ይተዉት አልነበረም? ምክንያቱም ቅዱስ አገልግሎት የሚያቀርቡት ሰዎች አንዴ ከነጹ በኋላ ሕሊናቸው በጥፋተኝነት ስሜት አይወቅሳቸውም ነበር። |
ይሁንና እነዚህ መሥዋዕቶች ከዓመት ዓመት ኃጢአት እንዲታወስ ያደርጋሉ፤ |
የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን ማስወገድ አይችልምና። |
ስለዚህ ወደ ዓለም በመጣ ጊዜ እንዲህ አለ፦ “‘መሥዋዕትንና መባን አልፈለግክም፤ ከዚህ ይልቅ አካል አዘጋጀህልኝ። |
ሙሉ በሙሉ በሚቃጠል መባና ለኃጢአት በሚቀርብ መባ ደስ አልተሰኘህም።’ |
በዚህ ጊዜ ‘እነሆ፣ አምላክ ሆይ፣ (ስለ እኔ በመጽሐፍ ጥቅልል እንደተጻፈ) ፈቃድህን ለማድረግ መጥቻለሁ’ አልኩ።” |
በመጀመሪያ እንዲህ አለ፦ “መሥዋዕትን፣ መባን፣ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባንና ለኃጢአት የሚቀርብ መባን አልፈለግክም፤ እንዲሁም ደስ አልተሰኘህበትም።” እነዚህ መሥዋዕቶች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት የሚቀርቡ ናቸው። |
ከዚያም “እነሆ፣ ፈቃድህን ለማድረግ መጥቻለሁ” አለ። ሁለተኛውን ለማቋቋም የመጀመሪያውን ያስወግዳል። |
በዚህ “ፈቃድ” መሠረት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕት ሆኖ በቀረበው የኢየሱስ ክርስቶስ አካል አማካኝነት ተቀድሰናል። |
በተጨማሪም እያንዳንዱ ካህን ቅዱስ አገልግሎት ለማቅረብና ኃጢአትን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ የማይችሉትን እነዚያኑ መሥዋዕቶች በየጊዜው ለማቅረብ ዕለት ዕለት በቦታው ይገኛል። |
ይህ ሰው ግን ስለ ኃጢአት ለሁልጊዜ የሚሆን አንድ መሥዋዕት አቅርቦ በአምላክ ቀኝ ተቀምጧል፤ |
ከዚያን ጊዜ አንስቶ ጠላቶቹ የእግሩ መርገጫ እስኪደረጉ ድረስ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። |
እነዚያን የሚቀደሱትን ለሁልጊዜ ፍጹማን ያደረጋቸው አንድ መሥዋዕት በማቅረብ ነውና። |
ከዚህ በተጨማሪ መንፈስ ቅዱስም ስለ እኛ ይመሠክራል፤ በመጀመሪያ እንዲህ ይላልና፦ |
“‘ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእነሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው’ ይላል ይሖዋ። ‘ሕግጋቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ፤ በአእምሯቸውም ላይ እጽፋቸዋለሁ።’” |
በመቀጠልም “ኃጢአታቸውንና የዓመፅ ድርጊታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስታውስም” ይላል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.